የዩኤስ አሜሪካ መርሃግብር እና ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአፍሪቃ እድገት እና ብልፅግና ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ያሏቸውን ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት የተውጣጡ 500 ወጣት አፍሪቃውያንን ዘንድሮ ወደ ሀገራቸው ጋብዘው ነበር።
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአፍሪቃ እድገት እና ብልፅግና ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ያሏቸውን ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት የተውጣጡ 500 ወጣት አፍሪቃውያንን ዘንድሮ ወደ ሀገራቸው ጋብዘው ነበር።
በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገሮች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን አመታዊውን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በማክበር ላይ ናቸው።
ምዕራብ አፍሪቃ ዉስጥ የኤቦላ ተሕዋሲ የገደላቸዉ ሰዎች ቁጥር ከሰባት መቶ ልቋል። በተጠቀሰዉ አካባቢ በተሕዋሲዉ ክፉኛ የተጎዱት ሃገራት የኤቦላ ወረርሽኝን ለመቋቋም ጠንካራና አዲስ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።
የደቡብ ሱዳን መንግስትና አማፂያን አቋርጠዉት የነበረዉን የሰላም ንግግር የፊታችን ሳምንት እንደሚጀምሩ አደራዳሪዎች አስታዉቀዋል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ማለትም IGAD አደራዳሪዎች ዛሬ እንደገለጹት በያዝነዉ ሳምንት ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ የሁለቱ ወገኖች የሰላም ንግግር የፊታችን ሰኞ ይጀመራል።
ጉዳዩ፥ ከአንድነት ፓርቲ ሶስቱ ፕሬዘዳንታዊ እጩዎች የተሰጠ የጋራ መግለጫ ውድ ወገኖች፣ የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ በዴሞክራሲ ሂደትና ባህል አጥብቆ ያምናል። በአጭር እድሜው ፓርቲው አባላቶቹ በነጻነት የአሳብ ፍጭት አድርገው አሳባቸውን እንዲገልጹ በማድረግ ሶስት ፕረዚዳንቶችን ግልጽና ተጠያቂነት በተሞላበት ሁኔታ መርጧል። ፓርቲያችን መሪዎቹን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ ባህሉን ይጠብቃል። የፓርቲያችን አባላቶችና ደጋፊዎች የዚህ ባህል ደጋፊ ብቻ ሳይሆኑ ሐዋሪያትም እንዲሆኑ […]
የአንድነት ቦስተን ድጋፍ ድርጅት፣ ለአመታት አገር ቤት የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል የሚደግፍ ድርጅት እንደ መሆኑ፣ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ የሚደረገዉን የዉህደት እንቅስቃሴ በደስታና በጉጉት እየተከታተለው ነው። የአመራር አባላትን ለመምረጥ የሚደረገዉ አስደሳች ዴሞክራሲያዊ ዉይይትና ቅስቀሳ ፣ አንድነት ምን ያህል የዲሞክራሲ ባህል እያዳበረ እንዳለ አመላካች ከመሆኑም በተጨማሪም ያኮራን ነገር ነው። የእጩ ፕሬዘዳንት ምርጫ ላይ ድምጽ የሚሰጡትና የሚወስኑት፣ አገር ቤት […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነ ስራ ሲሰራ ነበር፡፡ እሱም ውህደት ነው፡፡ የአንድነት/መኢአድ ውህደት ወሳኝና መሰረታዊ ድርድሮችን አልፎ የቅድመ ውህደት ፊርማው ከተቀመጠም ከወር በላይ ሆነው፡፡ ከፊርማው በኋላ ውህደት አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሮ በአጭር ጊዜ ነገሮችን መልክ ለማስያስ የቻለ ሲሆን ውህደቱም የሁለቱ መስራች የጉባዔ አባላት በተገኙበት ነሐሴ 3 እና 4 ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ታዲያ […]
በቀላሉ ሊሰሩ ከሚችሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ዋሽንት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በገጠሩ አካባቢ ሰዎች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ነበር ከቀርቀሀ የተሰራች ዋሽንታቸውን ይዘው ሙዚቃ ሲጫወቱ የሚስተዋሉት።
የሐገሪቱን የሥልክና የኢንተርኔት አግልግሎት በብቸኝነት የሚቆጣጠረዉ ኢትዮ-ቴሌኮም በየጊዜዉ ለሚነሱት ወቀሳዎችና ለሚፈጠሩት ችግሮች ምክንያት የሚላቸዉን ቴክኒካዊ ሠበቦች መደርደሩ አልቀረም።ችግሩ ግን የመቃለል እዝማሚያ አልታየበትም።
የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ለሰባተኛ የስልጣን ዘመን ዳግም ከተመረጡ ዛሬ አንድ ዓመት ደፈኑ ።አምና በአብላጫ ድምጽ ተመርጠው በፕሬዝዳንትነት የቀጠሉት ሙጋቤ አሁንም በዚምባብዌ ነጮች የመሬት ባለቤት እንዳይሆኑ በያዙት አቋም እንደፀኑ ነው።
የእስራኤል የጋዛ ድብደባ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል ። እስራኤል ተጨማሪ ተጠባባቂ ጦር ወደ ጋዛ አዝምታለች ። የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎችም ወደ ደቡባዊ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሳቸውን ቀጥለዋል ። ስደተኞች በተጠለሉበት በጋዛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትምሕርት ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና አሜሪካን አውግዘዋል ።
በቅርቡ የኣሜሪካ ፌደራል ኣቪየሽን ኣስተዳደር(FAA) በዓለም ላይ ለበረራ ኣደገኛ የሆኑትን መስመሮች በካርታው ላይ ከቦ ኣስጠንቅቆ የነበረ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ እንደሚታየው እነዚህን ኣደገኛ ቦታዎች በሁለት ከፍሏቸዋል። ኣንደኛው መስመር ኣደገኛነት ያለው ክልል (potentially hostile region) ሲሆን ሁለተኛው ክልል ግን በረራን ጨርሶ የከለከለ(Flight prohibited) ክልል ነው። ኣደገኛነት ኣላቸው ተብለው ኣብራሪዎች ከግምት እንዲያስገቡ የተመከሩባቸው ክልሎች ኬንያ፣ኣፍጋኒስታን፣ኢራን፣ሶሪያ፣ ማሊ፣የመን፣ ኮንጎና ግብጽ […]
«ኤዲያ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ቤት የተነሳውን እሳት እንደምንም ብለን ስናደፋፍነው አሁን ደግሞ አንድነት ፓርቲ ቤት ሌላ እሳት ተነሳ ….እርስ በርስ እየተጠዛጠዙ ፌስቡክን አጨናነቁት እኮ፡፡ ምናለ ዙከምበርግ ልክ የውስጥ ስልክ መስመር ወይም የውስጥ ሚሞ እንዳለ ሁሉ ለውስጥ ጉዳይ ብቻ የሚሆን ሌላ የፌስቡክ አይነት ቢፈጥርላቸው» ይሄን የጻፉት ከበደ ካሳ የሚባሉ የአገዛዙ ካድሬ ናቸው። የመኢአድ እና የአንድነት ዉህድ ፓርቲ […]
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።
አቶ ግርማ ሰይፉ
የመንግሰትን ቀጣይ እርምጃ የሚያሳዩ ተከታታይነት ያላቸው በግል ሚዲያዎች ላይ የሚደረጉ ዘመቻው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መልክቶች እየታዩ ነው። በቀጣይ ለሚቀርበው ዶክመንተሪ ተጋባዥ አንግዳ ሆኜ ለቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ቃለ ምልልስ እንደሰጣቸው ጥያቄዎቹ ደረስውኝ ተመልክቸዋለሁ። የጥያቄዎቹን ዝርዝር እንተወው እና ዓላማው ግን ባለፈው ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም የተለየ ነገር የለውም። በነገራችን ላይ ባለፈው የቀረበውም ዘጋቢ ፊልም ላይ እንድሳተፍ ተጠይቄ እንደማይሆን ገልጨላቸው ነበር። ውሳኔዬ ትክክል መሆኑን ዘጋቢ ፊልሙን ካየሁ በኋላ ገብቶኛል።
Sheraton Addis layoffs, 07-30-14
በቅርቡ ከአንድነት ጋር ዉህደት ይመሰርታል ተብሎ የሚጠበቀዉ መኢአድ ፣ የዉህዱን ፓርቲ ለመምራት እጩ መሆን የሚፈልጉ የድርጅቱ አባላት፣ ስማቸዉን እንዲያቀርቡ፣ የመኢአድ የዉህደቱ አመቻች ጉባኤ አሳወቀ። ከቀረቡ እጩዎች መካከል መኢአድ በድርጅቱ ልማዳዊ በሆነው አሰራር መሰረት፣ የመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ፣ መኢአድን ወክሎ ለዉህዱ ፓርቲ ተወዳዳሪ የሚሆነውን አንድ እጩ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ ሁኔታ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥም እጩዎች መቅረባቸው ይታወቃል። […]
ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ፣ ጊዜያቸዉን ወስደው ፣ በአንድነት ዉስጥ እየታየ ያለዉን በሌሎች ድርጅቶች ያልተለመደ፣ ዲሞክራሲያዊ ፉክክርን በመቀላቀል፣ የድርሻቸዉን ለማበርከት በርካታ ጽሁፎችን አስነብበዉናል። ለዚህም ያለኝን ምስጋና እና አድናቆት መግለጽ እወዳለሁ። ከርሳቸው ጋር በግል የተለዋወጥናቸው ሐሳቦች እንደተጠበቁ ፣ በአደባባይ ፣ በፌስ ቡክ ላቀረቡልኝ አንዳንድ ጥያቄዎች ግን ፣ እኔም በአደባባይ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ። «ምርጫ በአንድነት ዉስጥ ፤ ለአቶ በላይ […]
Michelle Obama spoke on YALI summit, Washington, 07-30-14
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት ረዘም ያለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የበለጠ የተጠናከረው እና የዛሬ መልኩን የያዘው ግን ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነው።
የግል የኅትመት ዉጤቶች በማተሚያ ቤቶች ችግር ምክንያት ወቅታቸዉን ጠብቀዉ እንደማይወጡ አሳታሚዎች ገለጹ።
የዓለም ዜና
ባለፈዉ ዓመት ከሩሲያ ጋር የ326 ቢሊዮን ዩሮ የንግድ ልዉዉጥ ያደረጉት የአዉሮጳ ሐገራት በማዕቀቡ የወለፊንድ ዉጤት ባንድ ወይም በሌላ መንገድ መነካታቸዉ አይቀርም።ከዩናይትድ ስቴትስና ከቻይና ቀጥሎ ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ የንግድ ልዉዉጥ ያላት ጀርመን ደግሞ ከሕብረቱ አባል ሐገራት ሁሉ ቀዳሚዋ ናት።
ለአፍሪቃ ሕብረት፤ ለአፍሪቃ ምጣኔ ሐብት ኮሚሽን ወዘተ እየተባለ በርካታ አፍሪቃዉን የሚመላለሱ፤ የሚስተናገዱባት ኢትዮጵያ እስካሁን የወሰደችዉ የጥንቃቄ እርማጃ ሥለመኖር-አለመኖሩ በይፋ የሰመነዉ የለም። ኬንያ ግን ወደ ሐገሯ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ጀምራለች።
ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባት የምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰት እድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁን ግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸው ክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡
ክሱ በአጭሩ1. ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
እንዲሁም ፓሊስ 18 የሰው ማስረጃ ለማሰማት የስም ዝርዝር ማስገባቱን እና የስም ዝርዝሩም እጃችን ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከፍርድ ቤት ለሚመጣው የፍርድ ውጤት ሳይሆን በአጠቃላይ የፍትህ ስርአትን ማክበር ሃላፊነት ስላለብን ብቻ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ ላለማካተት ወስነናል፡፡
እንደማጠቃለያየታሰራችሁ ጦማርያንን እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ለከፈላችሁት መስዋእትነት ውለታችሁ አለብን፡፡ እንኮራባችኋለን!!
#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsmamaw #FreeAllPoliticalPrisoners
ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ እንዲሁም የኮንግረስ አባላት ጋር አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ስላላት ግንኙነት፣ የወጣቶች ሚና፣ አልፎም በአፍሪካ የወደፊት ዕድገትና ፈተናዎች ዙሪያ ትናንት ሲወያዩ የዋሉት 500 የአፍሪካ ወጣቶች ዛሬ ደግሞ ለውጥ እንዴት ሊያመጡ እንደሚችሉ ሲነጋገሩ ውለዋል፡፡
ወጣቶቹ የለውጥ መሪዎች እንደሆኑ፤ ለዚህም የተጠናከረ ድጋፍ እንዳላቸው ፕሬዝደንት ኦባማ ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ስልታዊ ውይይቶችን እርስ-በርስ ሲያካሂዱ ነው የዋሉት።
በሌላ በኩል ደግሞ ከኢትዮጵያዊያኑ ተሣታፊዎች አንዱና በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የተጀመረውና በዚህ ዓመት በታላቁ ደቡብ አፍሪካዊ መሪ ኔልሰን…
Young African Leaders Washington DC summit – Day Two
South Sudan peace deals to resume in Addis on Wed. 07-29-14
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ « ለቀጣይ ጥቃት ዝግጁ መሆን ይኖርብናል» ሲሉ ትናትና ምሽት በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጥሪ አሰምተዋል።
በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ የአየር ማረፊያ አቅራቢያ የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ በኧዤን ከተማ በኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ለስድስት ቀናት በተካሄደው እና ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማኅበር ፌዴሬሽን የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የሦስተኛነትን ደረጃ አግኝታ ተጠናቋል።
በአሁኑ ጊዜ ምዕራባውያንን፣ በተለይም ፣ አውሮጳን እያሳሰበ ያለው ፈተናም ውስጥ የጣለው የዩክሬይን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ ከሩስያ ጋ የገቡበት እሰጣ ገባ እና የፖለቲካ ፍጥጫ ነው።
በጎርጎሪዮሳዊዉ 1990 እና 1992ዓ,ም በቢሊዮን ይገመት የነበረዉ ለምግብ እጥረት የተጋለጠዉ ሕዝብ አሁን ወደ 842 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ አንድ ነገር ነዉ ቢባልም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉን ወገኖች አሁን የሚያሳስበዉ የተደበቀ ወይም ስዉር ረሃብ መኖሩ መሆኑን ያመለክታሉ።
#Ethiopia #FreeZone9Bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw
የኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ለዞን9 ጦማርያን ሽልማት አበረከተ
በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ኢትዮጲያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ በእስር ለሚገኙት የዞን 9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ያልተዘመረላቸው ጀግኖች በሚል በአራተኛው አመታዊ ክብረ በአል ላይ ሽልማትን አበርክቶላቸዋል፡፡
በየአመቱ በሚደረገው በዚህ ክብረ በአል መዝጊያ ስነስርአት ላይ የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አበበ የዞን9 ጦማርያን ከፍተኛ መስዋእትነትን የሚከፈልበትን ሃሳብን አገር ውስጥ ሆኖ እውነትን የመናገርን ሃላፌነት ወስደው እየከፈሉት ላሉት መስዋእትነት እውቅና መስጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል።
ይህ ያልተነገረላቸው ጀግኖች በሚለው ምድብ የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ከዚያ በተጨማሪ ሁለት ተሸላሚዎች ከአገረ አሜሪካን ሽልማት ወስደዋል፡፡
የዞን9 ጦማርያን በታሰሩ ጦማሪ ጓደኞቻችን እና ጋዜጠኞችን ስም ለተሰጠው እውቅና ሽልማት ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
የመን ውስጥ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት የተሰጡትን የግንቦት ሰባት የፍትህ ነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ዓለም አቀፋዊና ሕጋዊ መብት መነሻ ያደረገ ዝግጅት ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ “የትጥቅ ትግል ያወጀ ነው፤” ሲል ድርጅታቸውን ግንቦት ሰባትንና አቶ አንዳርጋቸውን በአሸባነት ይወነጅላል።
“ለጥያቄዎ መልስ” በሳምንታዊ ቅንብሩ፥ ተንታኝ ባለ ሞያው መልስ የሚሰጡባቸውን የበርካታ አድማጮችን ጥያቄዎች አስተናግዷል።
ለመሆኑ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ሕግ የሁለቱን ጉዳይና የየመንን አሳልፎ መስጠት እንዴት ይመለከቱታል? ዝርዝሩን ከዝግጅቱ ይከታተሉ።
የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን እቅድ በመቃወም ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ በመንግሥት ኃይሎች ተፈጽሟል፤ ያሉትን ግድያ፥ ድብደባና እሥራት በመቃወም፥ እዚህ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት፥ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ለሦሥት ቀናት የዘለቀ የረሃብ አድማ አድርገዋል።
“መንግሥት በዜጐቹ ላይ እያደረሰ ያለው ችግር ተባብሶ ቀጥሏል፤” የሚሉት በWhite House ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት ለሦስት ቀናት በረሃብ አድማው የተሳተፉ ሰላሳ የሚጠጉ ሰዎች፥ ዓላማቸው ሁኔታውን ለአሜሪካና ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ መሆኑን ይናገራሉ። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያድምጡ።