የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ትምህርት ቤት
ትምሕርት ቤቱን የምታሠራው ለሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ያቆመችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት። አቡነ ጴጥሮስ በአደባባይ በፋሺሽት ኢጣልያ የተረሸኑት ሐምሌ 22: 1928 ዓም ነበር።
ትምሕርት ቤቱን የምታሠራው ለሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ያቆመችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት። አቡነ ጴጥሮስ በአደባባይ በፋሺሽት ኢጣልያ የተረሸኑት ሐምሌ 22: 1928 ዓም ነበር።
በተለያዩ አራት የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የታየዉ የኤቦላ ተሕዋሲ እስካሁን ለ826 ሰዎች ህልፈተ ሕይወት ምክንያት ሆኗል። ባለፈዉ ሳምንት ሴራሊዮን ዉስጥ ተሕዋሲዉ በሽተኞችን ይረዱ የነበሩ አንድ ዶክተርን ህይወት መቅጠፉ አጀብ ተብሎለት ሳያበቃ፤ አሁንም ሌላ ዶክተር በኤቦላ መያዛቸዉን ናይጀሪያ አረጋግጣለች።
የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ከመሆኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሰው ነበር ። ላለፉት 28 ቀናት በተካሄደው ድብደባ ቤታቸው ታስረው የቆዩት ፍልስጤማውያንም ዛሬ መንገዶችንና ገበያዎችን ሞልተው ታይተዋል ።
የኢትዮጵያ መንግስት ለመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ይፋ አድርጓል። የደሞዝ ጭማሪዉ ከ 2003ዓ,ም በኋላ ሲደረግ የመጀመሪያ መሆኑ ነዉ። የመንግስት ሠራተኛውን ከሃገሪቱ እድገት ተጠቃሚ ለማድረግ የታሰበ ነው የተባለው ይህ ጭማሪ ከኤኮኖሚ አኳያ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል?
ከመፅሄቶቹ ዋና አዘጋጆች አንዳንዶቹ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ሥራቸውን በህጉ መሠረት እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል ። ክሱን በተመለከተም ከህዝብ ጋር በቴሌቪዥን ከመስማታቸው ውጭ እስከ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድረስ ምንም ዓይነት መጥሪያ ሆነ ክስ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል ።
በቅርቡ በኢትዮ ሚዲያ የታዋቂው ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ አሳዛኝ ህልፈት/አሟሟት በተመለከተ “በዓሉ ግርማን የበሉት ጅቦች አልጮህ አሉ” በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ ቀርቦ ነበር። ይሄ ጽሁፍ የቀረበው በማን፣ በየትኛው የስነፅሁፍ ወይም የጋዜጠኝነት መስፈርት ተመዝኖ እንደሆነ ባይታወቅም “ድንቅ ጽሁፍ” የሚል ክብር ተሰጥቶታል። ይህን ጽሁፍ የፃፈው አበራ ለማ ይባላል። ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ በተገደለበት ዘመን በአንድ መስሪያ ቤት […]
ናትናኤል በርሔ ( ኖርዌይ ቲንግቮል)
ለአንድ አገር አስተዳደር መንግስት ለዜጎቹ መሰረታዊ ፍላጎቶች ከሆኑ ነገሮች አንዱ የሆነው ሰው ስራውን ሰርቶ በቂ የላፋቱን ዋጋ ማግኘት መብት ነው በተለይ በአሁኑ ሰዖት መንግስት እከተለዋለሁ ከሚለው መርህ የተገላቢጦሽ እየሆነ ዜጎች በገዛ አገራቸው በተፈጥሮዋዊ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋ የኢኮኖሚ ግሽበት ከድጡ ወደ ማጡ እየተሸጋገሩ ይገኛል።የቀድም ጠቅላይ ሚኒስተር የሽግግር መንግስቱ ሲመሩበት በነበር ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ october 1995 በተጠየቁት ጥያቄ ” የዛሬ 10 ዖመት ወይም 20 ዖመት በሗል ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ባየው ደስ ይለኛል ብለው የሚያስቡት” ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ እሳቸው ሲመልሱ የዛሬ 10 ዖመት ይሆናል ብየ ተስፋ የማደርገው እና የምመኘው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀን 3 ጊዜ ምግብ ያገኛል የሚል ነው።ከዛም ቀጥሎ ምናልባት በጣም የተሳካልን እንደሆን በአመት 2 ቅያሪ ወይም 3 ቅያሪ ልብስ ያገኛል እንዲሁም ከዛ በጣም የተሳካልን እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህዝብ ግፋ ቢል ከመንገድ 2 ሰዖት ርቀት በላይ ይኖራል።በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህዝብ ምግብ አማርጦ ይበላል።ነገር ግን ከ19 ዖመት በፊት የተናገሩት ቃል የተስፋ ቃል ከመሆን ያለፈ እና የዘለል አልሆነም።የኑሮ ውድነቱ ይልቁንስ የታችኛው ክፍል <!–more–>ህብረተሰብ ፈተና ውስጥ እና አደጋ ውስጥ ከቶታል።በተለይ የደመወዝ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ጭማሪው ይመለከተናል የተባለው የመንግስት ሰራተኞች አብዛኞቹ ይጨመርላቸዋል የተባለው ጭማሪ የኑሮውን ሁኔታ ከመቅረፍ ይልቅስ ኑሮው የባሰ የሚያደገረሽ እና ገንዘብ የመግዛት አቅም ያሳጣዋል።መንግስት ከወራት በፊት የደምዝ ጭማሪ አደርጋለሁ በማለቱ ምክንያት በአንዳንድ ምርቱን አምራች ፋብሪካዎች የምርት አቅርቦታቸው ላይ ጭማሪ አሳይተዋል።
በዚህም በተያያዘ ዜጎች፣ገበሬዎች፣ተማሪዎች፣ክሊኒኮች፣ሆስፒታሎች፣ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች የጥራት መጋደል እና በበቂ ሁኔታ ያለመቅረብ ችግሮች ያመጣል።ነጋዴ እና ቸርቻሪ ነን ባዮች ሕዝቡን ጨርቁን አስጥሎ ለመስደድ ቆርጠው የተነሱ ይመስል ከመንግስት ጋር እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ መንግስት ዋጋ ተምንኩ ሲል፣ እነሱ ከላይ ከላይ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ሸማቹ ግን የእነሱን ጭማሪ ያክል እድገት በየወሩ እንደማያስመዘግብ የታወቀ ነውና ግራ መጋባትን ሲጋፈጥ ይስተዋላል ይህ መተረማመስ ወራትን ተሻግሮ እንደ ከዚህ በፊቱ ድስት ጥዶ የዘይቱን ማለቅ ያየ ሮጥ ብሎ ከሱቅ ማግኘት አልቻለም፡፡ ብዙዎችም ቡና በጨው ሳይወዱ ለመጠጣት ተገደዱ፡፡ ልብሳቸውን በአመድና በእንዶድ ማጠብ እስኪከጅሉ ድረስ የሳሙና ዋጋ የማይቀመስ ሆነ፡፡ አሁን ደግሞ መንግስት የቸርቻሪነትና የአከፋፋይነት መብቱን መንግስት ነክ ለሆኑ ተቋማት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ እውነት ይሄ ግና እስከምን ድረስ ያስኬዳል ?
ለመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ከመደረጉ በፊት ደሞዝ ሲጨምር አብረው ዋጋ የሚጨምሩትን ነጋዴዎች ለመቆጣጠር ተብሎ የዋጋ ተመን መደረጉ በብዙ ሚዲያዎች ተወራ፡ ፡ ደስ ብሎን ሳናበቃ የደሞዝ ጭማሪው ምን ያክል እንደሆነ ሳናውቅ የዋጋ ጭማሪን መንግስት ራሱ አንድ ብሎ ጀመረው፡፡ ማባሪያና ማቆሚያ ያጣው የየወሩ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ያልነካካው ማን አለ?
በመጀመሪያው ወር የትራንስፖርት ወጭው አንድ መቶ ብር የነበረ ግለሰብ፣ በሁለተኛው ወር ወደ አንድ መቶ አስራ አምስት ብር፤ በሶስተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ሃያ አምስት ብር፤ በአራተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ስልሳ ብር እያደገ ይገኛል፡ ፡ ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ ነው በየወሩ ይህንን ያክል ጭማሪ መሸከም የሚችለው; በደሞዙ ወይም በገቢው ይህን ያክል ጭማሪ መቋቋም የሚያስችል እድገት እያገኘ ያለው የትኛው ሰው ነው? ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች እጅግ እጅግ አስጨናቂ በሆኑበት በዚህ ዘመን በእግር መሄድን ምርጫ ማድረግ የብዙዎች
ግዴታ እየሆነ ነው፡፡
መንግስት ነዳጅ ወር እየጠበቀ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ የዚህን ምክንያት በተመለከተ በየጊዜው ምክንያቶች ይደረደራሉ፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የአረብ ሀገራት በአብዮታቸው ምክንያት ያቀርቡት የነበረው የነዳጅ መጠን ስለቀነሰ ወዘተ ይባላል፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ቆዳ ከመወጠር ሌላ አማራጭ የለውም ? ለመንግስት ሰዎች ስብሰባ የቅንጦት ውሃና ኩኪስ መግዣ በየጊዜው እንደ ርችት ለሚረጩት የጽህፈት መሳሪያዎች ወይም ለሌላ አልባሌ መዝናኛ የሚወጡ ወጭዎችን ቆጥቦ ነዳጅ ላይ ድጎማ ማደረግ አይቻልም እንዴ ?
የደሞዝ ጭማሪው የተደረገው ለመንግስት ሰራተኞች እንጅ ለሁሉም የሀገሪቱ ሰራተኞች አይደለም፡፡ እንደውም ይህንን ልብ ብለን ከተመለከትነው ከምሬት ብዛት ሊያስቀን የሚደርስ እውነታ እናያለን፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ሁለት መምህራንን ብናነጻጽር፣ ይህንን እውነታ ማየት እንችላለን፡፡ ለነገሩ የግል መስሪያ ቤቶች ጉዳይ አሁንም ስግብግብ ነጋዴዎችን የሚመለከት ቢሆንም፣ ተቀጥረው የሚሰሩት ግን እንደዜጋም፣ እንደነጋዴም፣ እንደሰራተኛም ሊታሰብላቸው ይገባል፡፡
መንግስትም ቢሆን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቅ ከነበረው የደሞዝ ጭማሪ በታች እንደ ጨመረ ብዙዎች ይስማማሉ፡ ፡ በሰላሳና አርባ ፐርሰንት ብቻ የሚወሰን ጭማሪ ያደርጋል ብሎ ላለመገመት ታላቁ መነሻ መንግስት ቀድሞ ይሰጣቸው የነበሩ የሚያጓጉ መግለጫዎች ነበሩ፡፡የሆነው ሆኖ፣ ሀገራችን ይህን በመሰለ የወል እውነታ ውስጥ እንዳለች እየታወቀ፣ የኑሮ ውድነት ከእለት እለት ሲባባስ፣ አሁንም መፍሄ እየተባሉ የሚወሰዱ እርምጃዎች ችግር ሲያባብሱ እንጅ ሲያሻሽሉ እያየን አይደለም፡፡
ሰሞኑ የተጨመረው የደምዝ ጭማሪ ውጤታማ እና አመርቂ አለመሆኑን በሰራ ላይ እናየዋለን ለምሳሌ ያክል ስኳር አቅርቦትን መንግስት አገር ውስጥ የሚያደርሳቸውን ምርት ለህብረተሰቡ በበቂ ከማዳረስ ያለፍ ገበያውን በማን አለብኝነት ተቆጣጥሮ ድሃውን ህዝብ የዕለት ጉርሱን በመንጠቅ ለረሃብ እና እርዛት ዳርጎታል።ታሪክ
እንደሚያወሳው ከሆነ በንጉሱ ዘመን የመጨረሻ ስርዓት መውደቅ ለፊውዳሉ የቀረቡና የንጉሱን ቤተሰቦች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ስልጣን ላይ መቀመጥ መሞከር ትልቁ ምክንያት በትራንስፖርት ላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በአገሪቱ ላይ በመደረጉ ነበር።የኢህአዴግ መንግስት ስልጣን በተረከበ ዘመን ኢኮኖሚውን በምኒተሪ እና በፊሲካሊ ፖሊሲ በነፃ የንግድ ስም ህዝቡን እያታለሉ በማደናገር የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚደረግ ስልታዊ መንገድ ነው።
በአገራችን የምትገኝበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ምስቅልቅል፣የፖለቲካው ነፀብራቅ ነው።የዚህ ምስቅልቅል በመሆኑም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አንዱ ማሳያ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ስደት ነው።ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚው እና ፖለቲካው ዙሪያው ባጠኑት ጥናት ተቋማት የኢትዮጵያ ዜጎቿ ለኑሮ የማይመርጧት ሀገር እንደሆነች ተዘግቧል። 46% የሚቆጠሩ ዜጎች ከሀገራቸው ውጭ በስደት የመከራን ሕይወት ለመግፋት ተገደዋል።ዜጎች ባገራቸው ሰርቶ የመኖር ዕድሉን ማግኘት ካልቻሉበት ሀገር፣ስደት መምረጣቸው ፣የትምህርት፣የስራ ፣የቁጠባ ዕድል ለሁሉም እንዲደርስ ማድረግ ግድ የሚል በተለይ ወደ ዓረብ አገራት የሚሄዱ እህቶቻችን የሚደርስባቸው ግፍና ውርደት ፣ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ነው።ሁሉም አንገት የሚያስደፋ ሆኖዋል።በነዚህ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰሩበትን የደመወዝ ይከለከላሉ፣ ዜጎች በቂ ጥሪት እንዲያፈሩ ከማገዝ ጎን ለጎን ይደበደባሉ፤ ይደፈራሉ፤ በግፍ ይታሰራሉ፤ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ይገደላሉ፡፡ ይህ ዓይነት የዜጎች መብት በድርጅት፣በማህበረሰብን ጥቅም መብት ማስከበር አልቻለም።በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ሕዝቡ በመንግስት ላይ ግፊት ማድረግ አለበት።በምርጫ ሰምን የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ ማስተካከያ ህዝብን መደለል አይቻልም።ቸር እንሰንብት፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
በቅርቡ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስለኢየሩሳሌም ማኅበር ስናወራ መሥራቹ አቶ መኮንን ዘውዴ ትዝ አሉኝና ስለሳቸው ውለታ ሳወራ ነበር፤ ከሳቸው ጋር ተያይዞም ከዚህ በፊት አይ አበሻ! በሚል አጠቃላይ ርእስ አበሻና ልመና ወዘተ. እያልሁ መጻፍ ጀምሬ የነበረው ትዝ አለኝ፤ አንዳንድ ስላልገባቸው ነገር ሁሉ መጻፍ የሚወዱ ሰዎች አቅጣጫውን ሊለውጡት ሙከራ ሲጀምሩ ትቼው ነበር፤ አሁን የመክሸፍን ጉዳይ ደግሜ ለመጻፍ ስጀምር አንዳንድ በጣም መሠረታዊ የሆኑ የመክሸፍ መገለጫዎችን ስጽፍ በመጽሐፍ መልክ እስኪወጣ አላስችል አለኝና አንዱን ሀሳብ አደባባይ ለማውጣት ወሰንሁ፤ በዚያውም አቶ መኮንን ዘውዴን ማስታወሻ ይሆነኛል።
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
«በአፍሪቃ አሕጉራዊ ልማት፥ ጸጥታ፥ ልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ፤ እንዲሁም ንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ለማጠናከር የታለመ ሳምንት፤» ዋሽንግተን
“ጉባኤው ለአፍሪቃ ልማት መወጠኑ ይገባናል፤ የሕዝቡ ጉዳይ ግን የታል?” ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን የጉባኤው ተቃዋሚዎች።
በቅርቡ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን በዕጩነት ቀዳሚ ሆነው ማለፋቸው የፓርቲው ልሳን የሆነው ፍኖተ ነጻነት አስታውቋል፡ ፡በዚህ ጉዳያ ያልተናደደና ያልተበሳጨ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብሎ መገመት ይከብዳል፡፡ በተለይ ያእቆብ ሀ/ማሪያም በግንቦት 25/2005 በሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ በኩባ አደባባይ ለሰልፈኛው አቅርበውት በነበረው ንግግቸው ላይ “እኛ አባቶች ከእንግዲህ ሀላፊነት ለወጣቶች በመስጠት በምክርና የተለያየ […]
መንግሥታት ክፍት የሆነና ሲቪል ማኅበረሰቡን ያሣተፈ አሠራር በመከተላቸው ምክንያት የሚያተርፉት ተዓማኒነትን፤ ውጤቴማነትንና ሙስናን መዋጋትን እንደሆነ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተየመረው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ላይ ተነግሯል፡፡
የክፍት መንግሥታዊ አሠራር አጋርነት መድረክ ሲቪል ማኅበረሰቡን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማጠናከር የሚቻልባቸውንም መንገዶች አንስቷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የፀጥታና የግልፅነት፣ ጉዳዮች ሲቪል ማኅበረሰቦችና የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማትና የለጋሾቻቸው ፍላጎቶችን የሚመለከቱ አስተያየቶች ተንፀባርቀዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Africa-US leaders summit started
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከአንጎላ አቻው ጋር ትናንት ሉዋንዳ ውስጥ ተጋጥሞ 1 ለባዶ ተሸንፏል። ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ለዓለም የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ሚያሚ ውስጥ ለዋንጫ ይገናኛሉ። በሜዳ ቴኒስ ጥቁር አሜሪካዊቷ ሴሬና ዊሊያምስን በድል ጎዳና የሚያቆማት አልተገኘም። ጀርመናዊቷ ተፎካካሪዋን ከኋላ ተነስታ ድል ነስታለች።
ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደዉ የአፍሪቃ አሜሪካ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች የምትገኘዉ የአፍሪቃ አህጉር ላይ ያላትን ፍላጎት እንደሚያሳይ ነዉ የተነገረዉ። የጉባኤዉ አዘጋጆች ዓላማዉ የተጠናከረዉ የቻይና አፍሪቃ የንግድ ግንኙነት ያስከተለዉ ነዉ የሚለዉን ጥርጣሬ ወደጎን ነዉ ያደረጉት።
ከበርካታ አፍሪቃ ሃገራት ተጓዦችን በአየር መንገዷ የምታስተናግደው ምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ኢትዮጵያ እንዲሁም ወረርሽኙ ጉዳት ካደረሰባቸዉ ካሃገራት ብዙም ሳትርቅ የምትገኘው ጊኒ ቢሳው የኤቦላ ወረርሽኝ ወደየሀገራቸው እንዳይገባ ምን እያደረጉ ይሆን?
ያለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለአፍሪቃ ጠቃሚ ድርሻ ሊያበረክቱ ይችላሉ ካሏቸው 500 ወጣት አፍሪቃውያን ጋር ተነጋግረዋል። ዛሬ ደግሞ 50 ከሚሆኑ አፍሪቃውያን መሪዎች ጋር ለሶስት ቀናት ሊወያዩ ሌላ ጉባኤ ከፍተዋል።
ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር በሚመሩት የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና በአንፃሩ በሚዋጋው የሪየክ ማቸር ያማፅያን ቡድን መካከል የሰላሙ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ እንደገና ጀመሩ ተሰምቷል። በዚሁ እአአ እስከ 12.08.2014 ዓም ድረስ በሚዘልቀው
የዕለቱ ዜና
በዳዊት ሰለሞን
ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣን ዛሬ አነበብኳት ፡፡የጋዜጣዋ ባልደረባ የሆነው በላይ ማናዬ በቅርቡ ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው የሺዋስ አሰፋ ቤት ተገኝተው የየሺዋስን ሁለት ህጻናት ልጆች ማግኘታቸውንና ህጻናቱም ስለ አባታቸው የሚያስቡትን እንደነገሩት ይተርካል፡፡
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
መኢአድ እና አንድነት የሚፈጥሩት የዉህዱ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን፣ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ከቀረቡት መካከል አቶ በላይ ፍቃዱ በረዳ ይገኙበታል። አገር ቤት የሚገኙ የአንድነት አባላትና መሪዎች ዘንድ አድናቆትና ከበሬታ እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ በላይ፣ ለነባሩ የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው እንደተገኙ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት ሥራ አስፈጻሚ አባል፣ የቀድሞ የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት አሁን […]
መኢአድ እና አንድነት የሚፈጥሩት የዉህዱ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን፣ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ከቀረቡት መካከል አቶ በላይ ፍቃዱ በረዳ ይገኙበታል። አገር ቤት የሚገኙ የአንድነት አባላትና መሪዎች ዘንድ አድናቆትና ከበሬታ እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ በላይ፣ ለነባሩ የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው እንደተገኙ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት ሥራ አስፈጻሚ አባል፣ የቀድሞ የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት አሁን […]
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል የኤኮኖሚ ዕድገት አስገኙ ከሚባሉ ሀገራት አንዷ መሆኗ ይነገራል።
የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋውክ እና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ፍራንስዋ ኦሎንድ ከ100 ዓመት በፊት የዓለም ጦርነት ያስነሳውን ቀን በአንድነት አስበው ዋሉ።
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣን ዛሬ አነበብኳት ፡፡የጋዜጣዋ ባልደረባ የሆነው በላይ ማናዬ በቅርቡ ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው የሺዋስ አሰፋ ቤት ተገኝተው የየሺዋስን ሁለት ህጻናት ልጆች ማግኘታቸውንና ህጻናቱም ስለ አባታቸው የሚያስቡትን እንደነገሩት ይተርካል፡፡ ህሊና የየሺዋስ ሁለተኛ ልጅ ስትሆን የ5 ዓመት ህጻን ናት፡፡‹‹አባቴ ደሴ ሄዷል››እንዳለችው በላይ ይገልጻል፡፡ጋዜጠኛው አባቷ ደሴ እንዳልሄደና ሰው እንዳይጠይቀው ተደርጎ […]
ሳምሶን አስፋው – አውስትራሊያ
የአቶ አንዳርጋቸው ቃልና የወያኔ ፕሮፓጋንዳ
ሰሞኑን በወያኔ መንግስት የፖሊስ ፕሮግራም የቀረበው “አቶ አንዳርጋቸው ለመንግስት ጠቃሚ መረጃ ሰጡ” የሚለው ዜና ኢትዮጵያዊውን ሁሉ እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው። የዜናው አነጋጋሪነት የሚነሳው ለዜናው አብይ ግብአት እንዲሆን፤ በወጉም ሳይታሰብበት ተለጣጥፎ የቀረበው የቪዲዮ ክሊፕ የዜናውን ጩኸት አለማስተጋባቱ ነው። በመጀመሪያ የምናነሳው ጥያቄ የወያኔ ባለስልጣናት ይህንን በተራ ግለሰብ እንኳ ቢቀርብ የሚያሳፍር ደካማ የማስመሰል ስራ በመንግስት ደረጃ ለማቅረብ ያስገደዳቸው ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ይመስለኛል። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ መላምቶችን መሰንዘር እንችላለን።
African Leaders Summit in Washington DC
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው ሲሉ ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን ገለፁ፡፡
ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት በስተቀር ያልተጋበዙት መሪዎች አለመጋበዝ ትክክለኛ ውሣኔ ነው ብለው እንደማያስቡም ተናግረዋል – አምባሳደር ሺን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የመጭው ሣምንት የአፍሪካ መሪዎች የዋሺንግተን ጉባዔ ይህንን ጉባዔ የረጥነው ከአፍሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሳደግ መወሰናችንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የሥልታዊ ግንኙቶች የብሄራዊ ፀጥታ ምክትል አማካሪ…
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በሞዛምቢክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተዋጊዎች ያሉት ትልቁ የተቃውሞ ቡድን፣ በፈሬሊሞ ፓርቲ በሚመራው መንግሥት አንፃር ሬናሞ እአአ ከጥቅምት 2013 ዓም ወዲህ ውጊያ በማካሄድ ላይ ነው።
አንድ እስራኤላዊ ወታደር ጋዛ ሠርጥ ውስጥ ሳይታገት አልቀረም መባሉን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ከባድ የተሰኘ የአፀፋ ጥቃት መሰንዘሩ ተነገረ።
ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለ አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ መንግስት በመተቸታቸው በግልጽ በመጻፋቸውና በአደባባይ በመናገራቸው ከዚህም አልፎ በጥርጣሬ በተለይም በብሄረሰብ ማንነታቸው እያሳደደ የሚያፍን የሚያሰቃይና የሚገል የሽብር ተቋም ካለ ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የተቃውሞ ሃይል በተግባርም ሆነ በአስተሳሰብ ከወያኔ ውጪ አንዳች ሃይል የለም።
አፋኙ የወያኔ ስርአት በተለየም የህዝቡን ሀብትና ንብረት እየዘረፉ የሚቀማጠሉት የህወሃት መሪዎችና ሎሌዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ በሰሙ ቁጥር እንደሚሸበሩና እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ይታወቃል። አፍነውና ዘርፈው ገለው የሚገዙት ህዝብ ግፍ በዛብኝ ብሎ በተናገረ ቁጥር የሚሸበሩት እነሱ ብቻ እንጂ ህዝቡ አይደለም።
በኢትዮጵያ ምድር ያለው አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ሺ ምሳሌዎችን ጠቅሶ ማስረዳት ይቻላል። ሶስት አመት ሙሉ የሰላም እጃቸውን እየዘረጉ ከልመና ባልተለየ ሁኔታ መብታቸውን የጠየቁና ድምጻችን ይሰማ ያሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማንንም ዜጋ አላሸበሩም። የተገላቢጦሽ እነሱ አሸባሪ ተብለው የግፍ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል።
ጋዜጠኞችና ጦማሪዎቹ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁ በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። እነሱ ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም። ከመንገድ ላይ ጎትተው እንደ እባብ ቀጥቅጠውና ፈነካክተው በማግስቱ ፍርድ ቤት ያቀረቧት ወየንሸት ሞላ የተባለች ባለ ተስፋ ወጣት የወያኔ አረመኔዎች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ጭፍጨፋ እግር ጥሏት ከማየትና ከመታዘብ ውጪ ያሸበረችው ሰው፣ ሀገር የለም። በየወህኒ ቤቱ እና አፈና ጣቢያው ታስረው የሚቀጠቀጡት የኦሮሞ ልጆች ለጥያቄያቸው መልስ ሲጠብቁ ከመጨፍጨፍ ያለፈ የፈጸሙት እብሪት የለም። በየክልሉ ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ ጥያቄ ጠየቅክ፣ ባለስልጣን ደፈርክ፣ ተሰብስበህ አየንህ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ገበሬ የሰራው ወንጀል የለም። አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሊያፈነዱ ሲሉ ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ ብሎ በአደባባይ የሚሳለቀው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ አይደለም።
የኛ መሪ አንዳርጋቸው ከልጅነት እድሜው ጀምሮ ራሱን ለህዝብ ነጻነት የሰጠ አርበኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም። በተመሳሳይ ውንብድና ከጎረቤት ሀገር ድረስ በአለም አቀፍ የወረበሎች ውንብድና መንገድ ወያኔ እያፈነ የገደላቸው አሮሞዎችና፣ ሱማሌዎች፣ አኙዋኮች፣ አማሮችና ሌሎችም ነጻነት ከመፈለግ ውጪ ያሸበሩት ህዝብና ሀገር የለም።
በኢትዮጵያ ምድር የነጻነት ድምጽና ኮሽታ በሰማ ቁጥር የሚሸበረው ህወሃትና በለሟሎች ብቻ ናቸው። ይህ የነጻነት ድምጽ ደግሞ እየጎላ መሄዱ የማይቀር ነውና ወያኔ ሰፈር ሽብር ይሆናል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወጣት፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ገበሬ እና በየቦታው ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ! አሸባሪህ ወያኔና ወያኔ ብቻ መሆኑን አውቀህ በገዛ ሀገርህ ላይ ነጻነት በተመኘህና በጠየቅህ ጊዜ ሁሉ ለሽብር ጥቃቱ ኢላማ ያደረጉህን ወያኔ ተባብረን ከላያችን ለማውረድ ተነስ! በያለህበት እምቢ በል! ለወያኔ የሚጠቅም የመሰለህን ነገር ሁሉ አታድርግ! አትተባበር! ሸቀጣቸውን አትግዛ! ወያኔዎችን ከማህበራዊ ሂወትህ አግል! የቻልክ ሁሉ ደግሞ የነጻነት አርበኞችን ዛሬ ነገ ሳትል አሁን ተቀላቀል!!! ነጻነታችን ያለው በእጃችን ላይ መሆኑን አትዘንጋ። ግንቦት 7 ሁልጊዜም ከመቼውም ጠንክሮ ከጎንህ ነው።
የወያኔን ሽብር በተባበረ ሃይል እናቁመው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ግንቦት7
የትግራይ ስብስቡ በጂጁ ሆቴል እቅዳቸው የህወሓትና የደህንነት ሰዎች ባሉበት ኣውጥተዋል ::
ሕወሓት በትግራይ ከዚህ ቀደም በሚደረጉ ምርጫዎች ካለምንም ተወዳዳሪ በብቸኝነት ተወዳዳሪ ሲመጣ ደሞ ስም በማጥፋት እና በጉልበት በመደቆስ በብቸኝነት ምርጫዎችን እያሸነፈ ላለፉት 23 አመታት ዘልቋል። ካለፉት 6 አመታት በኋላ አረና ትግርያ ብሎ የሚጠራ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ ተመስርቶ በትግራይ ውስጥ እንቅስቃሴውን እያስፋፋ ባለበት ሰአት በመጭው ምርጫ እሸነፋለሁ ሕዝቡ በድምጹ ይጥለኛል የሚል ከባድ ስጋት ስላለበት ከአረና ፓርቲ ጋር ይመሳሰላልኛል ያለውን ተለጣፊ ፓርቲ ለመመስረን እንቅስቃሴ መጀመሩን ታውቋል።
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የማለዳ ወግ … ጥሩ ምግባር ሁሌም ያስመሰግናል ! * አይታክቴውን የመረጃ ምንጩን ፣ ጋዜጠኛውንና ድምጻዊዋንም ላመስግን ! ለእኔ ለፈጣሪ በታች በጎ ለሚሰሩ የሰው ዘሮች በሙሉ የሚሰጥ ምስጋና ቃል ይስበኛል። ብዙ ጊዜ የመልካምና የበጎ ምግባር ፋና ወጊዎች ስራ ተመልክቸና መስጦኝ ለቀሪው አርአያ ፣ ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ምንጭ ነው ብየ ካሰብኩና ካመንኩበት የምስክርነት ቃሌን የምሰጠው ምስጋና በማቅረብ […]
የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሚስተር ጆን ኬሪ በቅርቡ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡ በዚህ ጉብኝታቸዉ ወቅትም በኢትዮጵያ እየደረሰ ባለዉ የሰባዊ መብት ጥሰት ላይ ብዙም ሳይሉና የተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን በሁኔታዉ ላይ ሳያነጋግሩ በመሔዳቸዉ ብዙዎችን ሳያሳዝን አልቀረም፡፡ በእርግጥ የእርሳቸዉ አመጣጥ በእርስ በእረስ ጦርነት በመታወክ ላይ ያለችዉን የደቡብ ሱዳን ችግር በመፍታት ላይ ያተኮረ ቢሆንም ቅሉ የኢትዮጵያዉያንን ችግርም ሳይቃጠል […]
Ethiopia, bloggers, rights advocates, open letter
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች