Tag: Ethiopia
የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ በአዲስ አበባ
በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ እየታየ ያለዉን የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ መንግሥት ሊቆጣጠረዉ እንደሚገባ ተገለጸ።
ቱርክና የኤርዶጋን ቀጣይ የአመራር ዘይቤ፣
እ ጎ አ፣ ከ 2003 ዓ ም አንስቶ ፣ ላለፉት 11 ዓመታት ገደማ ፣ ቱርክን በ ጠ/ሚንስትርነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት ሪቸፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ በዚያች ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዚዳንት በህዝብ እንዲመረጥ በተደረገበት ደንብ፤
ኖየር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች መባሉ
የጀርመን ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድንና የባየር ሙኒክ ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኖየር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ። ኖየርን የመረጠዉ ታዋቂዉ የጀርመን የስፖርት መጽሔት ኪከር የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮአኺም ለቭንም የዓመቱ ምርጭ አሰልጣኝ በማለት መርጧል።
በደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ የተያዙት 24 ኢትዮጵያውያን
ባለፈው ሳምንት 24 ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ 16 ሰዎችን በምትጭን አንዲት ታክሲ ውስጥ ተሳፍረው ሲጓዙ የትራፊክ ፖሊስ እንዳስቆማቸው እና በብሪክስተን የፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተሰምቷል።
ሰሜን ኢራቅና የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት
በሃይማኖት ተጨቁነው እና በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ወደሚገኝ ተራራ ተሰደው የሚገኙ 20 000 የሚደርሱ የያዚዲ እምነት ተከታዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነ ነው የሚሰማው። ይህም አንዳንድ ጠበብት እንደሚሉት አሜሪካ ጣልቃ ከገባች በኋላ የተገኘ ለውጥ ነው።
”አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ”
በፍቃዱ ኃይሉ (የዞን 9 ብሎገር ከቂሊንጦ እስር ቤት)
”ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!”፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ። በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ”አባሪዎቼ” ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል።
”አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ” በፍቃዱ ኃይሉ ከቂሊንጦ እስር ቤት
በፍቃዱ ኃይሉ (የዞን 9 ብሎገር ከቂሊንጦ እስር ቤት)
”ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!”፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ። በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ”አባሪዎቼ” ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል።
A Note From Prison
![]() |
| The picture shows the six bloggers and three journalists |
”ለሰብአዊ መብትና ለዴሞክራሲ ጥብቅና መቆም ሽብርተኝነት ነው” ፡- የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ
”ለሰብአዊ መብትና ለዴሞክራሲ ጥብቅና መቆም ሽብርተኝነት ነው”፡- የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ
የሂዩማን ራይትስ ዎች የዓለም አቀፍ ዘገባ ስለ ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያ የፖሊስ ሃይል፤ በጦር አባላትና በሌሎችም ተመሳሳይ አባላት፤ በደህንነት አባላት በቅጣት መልክ በተቃዋሚ ደጋፊዎችና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ላይ የሚፈጸመው ስቃይና የእስረኞች የአያያዝ ሁኔታ አሳሳቢነትና መከራ የከፋ ከመሆኑም ባሻገር በሚስጣራዊ ማጎሪያዎች፤ በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ በእስር የሚገኙት ንጹሃን ዜጎች ሁኔታ አሳሳቢነቱ በየጊዜው እየከፋ የሚሄድ መሆኑን በተደጋጋሚ በግልጽ አስቀምጧል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መለቀቅ አለባቸው፡፡ ሁኔታቸው በአ……..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ//
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኦገስት 10, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በሐሰት መንግስታዊ ማጭበርበሮች ሳንታለል በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎችን እናረጋግጥ !!! ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ በትክክለኛው መንገድ የማያስቀምጡ የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ዘገባዎችን በመስራት እና እውነትን ለመሸፋፈን በመትጋት የሕዝቦችን የማወቅ መብት ያለርሕራሄ እየተጋፉ ይገኛል። ይህ በወያኔ የፕሮፓጋንዳ አካላት የሚፈጸም ማጭበርበር እና ማደናገር የገዢውን ፓርቲ ውስጣዊ ዝርክርክነት በይፋ ያሳብቃል።ያለለውን እንዳለ ድሮ ተግንብቶ የታደሰውን እንደ አዲስ እንደተገነባ ፤ ያልተሰራውን እንደተሰራ ሕዝቡ የማያገኘውን አገልግሎት እንደሚያገኝ ወዘተ በማድረግ በሁለት እና […]
መፍትሔ ያላገኘው የደቡብ ሱዳን ውዝግብ
በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት የሚያበቃበትን መንገድ የሚያፈላልገው ተቋርጦ የነበረው የሰላም ድርድር ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ ቢጀምርም፣ በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አንፃር የሚፋለሙት
የገንዘብ ዋጋ መቀነስ
የአንድ ሀገር መገበያያ ገንዘብ በተለያዩ ምክንያቶች ዋጋዉ ወይም የመግዛት አቅሙ የሚቀንስበት አጋጣሚ በርካታ ነዉ። በተለይ ደግሞ ጠንካራ ከሚባሉት ዓለም አቀፍ መገበያያ ገንዘቦች ጋ ሲወዳደር እያደር አቅሙ ዝቅ የሚልበት አጋጣሚ ነው ያለው ።
ባግዳድ፤ በመቶዎች የሚገመቱ ያዚዲዎች ተገደሉ
የኢራቅ የሰብዓዊ መብቶች ሚኒስትር በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል 500 የሚሆኑ ያዚዲዎች በእስላማዊ መንግሥት ሚሊሺያዎች መገደላቸዉን አስታወቁ።
‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ
![]() |
|
| Befekadu Hailu |
ተከብሮ ያላስከበረ፣ ሰርቶ ያላሰራ የኛ ‘ሕገ-መንግስት’
ተከብሮ ያላስከበረ፣ ሰርቶ ያላሰራ ‘ሕገ-መንግስት’
ሕዝባዊ መንግስት ማለት ሕዝቡ በቀጥታ የራሱ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት ማለታችን ነው:: ህዝቡ መሪዎቹን በነጻ የመምረጥ እና የማዉረድ መብቱ የተረጋገጠበት ማለት ነው:: ሕዝባዊ መንግስት ስንል የመግስት ስልጣን መነሻ እና መድረሻው ህዝቡ ነው ማለታችን ነው::
ህገ መንግስት ደግሞ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ‘ህገ መንግስት’ እንደሚለው ከሆነ ‘ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን አሰራር ከህገ መንግስቱ የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም።’
ሙሉውን ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ http://t.co/tM139HuDYt
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኦገስት 09, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
መፍትሔ ያላገኘው የደቡብ ሱዳን እና ውዝግብ
በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት የሚያበቃበትን መንገድ የሚያፈላልገው ተቋርጦ የነበረው የሰላም ድርድር ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ ቢጀምርም፣ በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አንፃር የሚፋለሙት
UTC 16:00 የዓለም ዜና 090814
የዕለቱ ዜና
ጋዛ ፤ የጋዛ ድብደባ ቀጥሏል
እስራኤል ዛሬ በጋዛ 30 ጊዜ ባካሄደችው የአየር ድብደባ 5 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተዘገበ ። በዚሁ በዛሬው እለት የሃማስ ደፈጣ ተዋጊዎችም 6 ጓዳ ሰራሽ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሰዋል።
የመለስ “ትሩፋቶች” – መጽሃፍ ቅኝት (በክንፉ አሰፋ)
ደራሲ፣ ኤርምያስ ለገሰ ብዛት፣ 406 ገጾች አሳታሚ፣ ነጻነት አሳታሚ ድርጅት እንደ መንደርደርያ በስፋት ሲወራለት የነበረውን ይህን መጽሃፍ ሙኒክ-ጀርመን ላይ ገዝቼ ለማንበብ እያፈላለግኩ ሳለሁ፤ አንድ ወዳጄ ይዞት አየሁ። የደበዘዘ የመለስ ፎቶ ያለበትን ይህንን መጽሃፍ የኦስሎው አበበ እጅ ላይ ነበር። ገና ሰላምታ ሳንለዋወጥ ነበር መጽሃፉን ከእጁ ላይ የነጠቅኩት። ታማኝ በየነም እዚያው አብሮን ስለነበር አስተያየቱን ጣል አደረገ። “መነበብ […]
በፈራረሰችው ጋዛ የጨለመው ተስፋ ! * በደም ምድሯ የሚንሰራፋው ጥላቻ! ነቢዩ ሲራክ
ወር በተጠጋው የእስራኤል ጋዛን የማጥቃት ዘመቻ በአሳር በመከራ የተደረሰው የ 72 ሰዓቱ የጦርነት ማቆም ሊያልቅ የቀሩት ጥቂት ሰአታት ብቻ ናቸው። በእስራኤል የአየር የየብስና የባህር ድብደባ ከ1800 በላይ አብዛኛው የጋዛ ንጹሃን ፍልስጥኤማውያንን ተገድለዋል። ከ 9000 የማያንሱትን ቆሰለዋል። በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ በሃገራቸው ተሰደው ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ጋዛ እንዳልነበረች ሆናለች ይህ ሁሉ ሆኖ ጦርነቱ እንዲያቆም በተደረሰው የ 72 ሰአታቱ […]
እነ ወይንሸት በይግባኝ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው
ሐምሌ 29 ጠዋት ሜክሲኮ ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው በ5000 ብር ዋስ እንዲወጡ የታዘዘላቸው ወይንሸት፣ አዚዛ እና ኡስታዝ በድብቅ በተካሄደ ይግባኝ ዋሱ ተነስቶ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ ተፈቅዶለታል፡፡ በእለቱም ከሰዓት በኋላ በድብቅ ፍርድ ቤት ተወስደው የዋስ መብታቸው በይግባኝ ተገፏል፡፡ አሁን በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡
እንዲሁም በተያያዘ ዜና ሐምሌ 30 ቀን ኢብራሂም አብዱልሰላም 5000 ብር ደመወዝተኛ ዋስ እንዲለቀቅ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ከ3 ሰዓታት በኋላ ፖሊስ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ አድርጎ ዋስትናው እንዲታገድ በማድረግ በእስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡
የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ
ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል …
በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሪታንያ መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ትኩረት ሰጥታ እንደትከታተለው የሚያሳስቡ የተቃውሞ ሰልፎች ካለፈው ወር ጀምሮ በእየሳምንቱ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ዛሬ አርብም ለአምስተኛ ጊዜ ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ ስሜታቸውን በከፍተኛ ቁጣ በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው ያነጋገርነው ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹ ገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ግብረሃይል በውጭ …
የኢህአዴግ ተወካዮች ምሬታቸውን ገለጹ
ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ የምክር ቤት አባላት ፣” የህዝብ ወኪሎች ብንሆንም ስራ አስፈጻሚው አካል የምናቀርበውን ሪፖርት አይቀበልም” ብለዋል። አንድ ኢንቨስተር ከአንድ የህዝብ ተመራጭ የተሻለ ተሰሚነት አለው ያሉት ተማራጮች መፍትሄ ለማምጣት ካልቻልን የእኛ ተመራጭነት ምንድነው ሲሉ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል የህዝብ ተወካዮቹ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በፍድር ቤቶች …
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ሁለት ኢትዮጵያውያን ዩጋንዳ ውስጥ ተያዙ
ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኒው ቪዥን እንደዘገበው አበበ መኮንንና አስፋው ወንዶሰን ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊሶች ተይዘው ተወስደዋል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹንለመያዝ ለሁለት ቀናት አሰሳ ሲያካሂድ እንደነበር ተዘግባል። ኢትዮጵያውያኑ ለኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ተላልፈው ይሰጡ ወይም ጉዳያቸው በዩጋንዳ ፍርድ ቤት ይታይ በዘገባው አልተጠቀሰም። ፖሊስ እስረኞቹ የታሰሩበትን ቦታም ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።
በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ያለው ግጭት አገረሸ
ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ሶስት ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው የእስራኤልና የፍልስጤማውያን ግጭት እንደገና ማገርሸቱን እስራኤል አስታውቃለች። በግብጽ አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር ሃማስ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፉን ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባ ጀምራለች። ሃማስ የሰላም ድርድሩ እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረገቸውን ከበባ ማስቆም አለበት የሚል አቋም ይዟል፡፤ እስረኤል በግብጽ በመካሄድ ላይ ያለውን የሰላም ድርድር …
ልጆችም ወላጆችም የሚተባበሩበት የፍልሰታ ለማርያም መታሰቢያ ጾምና በዓል
(አለቃ አያሌው ታምሩ) በኢትዮጵያ እመቤታችንን መውደድ በልማድ እንደ ተረት በማይታይ ዓይነት ኹኔታ ተስፋፍቶ የኖረ አይደለም፡፡ ወንድም ሴትም ቢኾኑ እንዳላቸው የእምነት መጠን በእመቤታችን ስም ጸሎት ጸልየው፣ ስእለት ተስለው፣ ምጽዋት አድርገው፣ ዝክርዋን ዘክረው፣ ስምዋን ጠርተው፣ በአማላጅነትዋ ተማፅነው ዐሳባቸው እየተፈጸመላቸው፣ የጎደለው እየሞላላቸው፣ የጠመመው እየተቃናላቸው፣ ድውያን ፈውስ በማግኘት፣ ሠራተኞች ለሥራቸው የተቃና መንገድ በማግኘት፣ መምህራን በሚያስተምሩበት፣ ቅዱሳን ገድላቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜና …![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ኦገስት 08, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ኢትዮ ቴሌኮምና የ4G ቴክኖሎጂ
በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም አራተኛው ትውልድ እየተባለ የሚጠራውን ቴክኖሎጂ በአንድ ወር ውስጥ የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።
የዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ
የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በዴሞክራሲ ግንባታ‘ በሚል ርዕስበተካሄደ ውይይት ላይ የተካፈሉ ተሳታፊዎች ሴቶች መብታቸውን ለማስከበርም ሆነ በአገራቸው ተጠቃሚ ለመሆን በየመስኩ ተሳትፎአቸውን ማጎልበት እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።
የተቋረጠው የደቡብ ሱዳን የሰላም ንግግር
በዚህ ሳምንት ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ የተጀመረው የሰላም ንግግር የተቋረጠው ተቃዋሚው SPLM A አንዳንድ ተወካዮች በንግግሩ ላይ መሳተፋቸውን በመቃወሙ መሆኑን የድርድሩ ተካፋይ የሆኑት የሴቶች ተወካይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።
የመለስ “ትሩፋቶች” – መጽሃፍ ቅኝት
በክንፉ አሰፋ
ደራሲ – ኤርምያስ ለገሰ
ብዛት – 406 ገጾች
አሳታሚ – ነጻነት አሳታሚ ድርጅት
እንደ መንደርደርያ
በስፋት ሲወራለት የነበረውን ይህን መጽሃፍ ሙኒክ-ጀርመን ላይ ገዝቼ ለማንበብ እያፈላለግኩ ሳለሁ፤ አንድ ወዳጄ ይዞት አየሁ። የደበዘዘ የመለስ ፎቶ ያለበትን ይህንን መጽሃፍ የኦስሎው አበበ እጅ ላይ ነበር። ገና ሰላምታ ሳንለዋወጥ ነበር መጽሃፉን ከእጁ ላይ የነጠቅኩት። ታማኝ በየነም እዚያው አብሮን ስለነበር አስተያየቱን ጣል አደረገ። “መነበብ ያለበት መጽሃፍ” እንደሆነ አበክሮ ነገረኝ። ታማኝ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መጻህፍት በሙሉ እንደማያመልጡት አውቃለሁ። በዚህ አዲስ መጽሃፍ ላይ አንዳች አዲስ ነገር እንደሚኖር ከንግግሩ ለመረዳት አያዳግትም።
ብሄራዊ መግባባት ወይስ አገራዊ ውህደት
ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም
አንዳንድ እንደዘረኝነት፣ ጐሰኝነትና የሃይማኖት ጥላቻ ስለመሳሰሉ አጸያፊ ክስተቶችና ሕዝባዊ ግንኙነቶች ማንሳትና ስለእነርሱም መጻፍ የሚቀፍ ከመሆኑም በላይ፤ ያልሆነ ስም ሊያሰጥና በዘረኝነት ተጠቃሚ የሆኑ አካላትንም ሊያስከፋ ይችላል። ሆኖም ሳይመሽ አገርን ከውድቀት ለመታደግ እና ሕዝብን ከጥፋት አፋፍ ለመመለስ ሲባል፤ ከአገርና ከሕዝብ የሚበልጥ የለምና ይሉኝታን ዋጥ አድርጐ በፍርሃት ሳይገደቡ፣ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳይሽሞነሞኑ እነዚህን አገር በታኝ ክስተቶችን በአደባባይ አፍርጦ ለማውጣት ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ሰው መሆንም በቂ ነው።
“ባሕል ግን ምንድ ነው?” ሥነ ግጥም በትእግስት አለምነህ – ኦገስት 08, 2014
ባሕል ግን ምንድ ነው?
የሁለት ከተሞች የሥነ ግጥም ጉባኤ ወጎችና ግጥሞች፤ – ኦገስት 08, 2014
ባሕል ግን ምንድ ነው?
ባሕል ግን…የቅምሻ ድምጽ (2) – ኦገስት 08, 2014
ባሕል ግን ምንድ ነው?
ባህል ግን…የቅምሻ ድምጾች (1) – ኦገስት 08, 2014
ባሕል ግን ምንድ ነው?
የሁለት ከተሞች የሥነ ግጥም ጉባኤ
ለሥነ ግጥምና ቅኔ ቀልባቸውን የሰጡ ወጣትና ታዋቂ ገጣምያንን ጨምሮ የሥነ ጽሁፍና ጥበብ አድናቂዎች የተሰባሰቡቸው ሁለት መድረኮች ናቸው። በአዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲ።
ዘመን የጠገበ ጥበባዊ ባሕል፥ ሥነ ግጥምና ወጎች፤ ጥቂቱን በቅምሻ እናጣጥም።
ሙሉው ቀጥሎ ያድምጡ።
የአማራ ክልል አመራሮች ከግንቦት7 የኦህዴድ ደግሞ ከኦነግ ጋር እያበሩ ነው ሲል አቶ አዲሱ ለገሰ ያዘጋጁትና ለጠ/ሚ አማካሪዎች የተላከው ሰነድ አመለከተ
ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰነዱ ላይ ኢህአዴግ የአመራር ችግር እንዳጋጠመው፣ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ አለመሳካቱ እንዲሁም በጋምቤላ ተማኝ መሪ መጥፋቱ ተዝርዝሯል። በሃምሌ ወር መጨረሻ የተዘጋጀው ሰነድ ግልባጭ ለጠ/ሚኒስትሩ አማካሪዎች ለአቶ በረከት ስምኦን፣ ለአቶ ደስታውና ለአቶ ኩማ ደመቅሳ ተደርጓል። የቀድሞው ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ የፖሊሲ ስልጠና ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ” የኢህአዴግን ተቃዋሚ ሃይላት …
ወጣቱ ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እስር ቤት ውስጥ እንደተደበደበ ለፍርድ ቤት ተናገረ
ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመቀሌ በሚጽፋው ጽሁፎችና በሚሰጣቸው አስተያየቶች የበርካታ ወጣቶችን ቀልብ የሳበው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር አብርሃ ደስታ፣ በአሸባሪነት ተከሶ መእከላዊ እስር ቤት ከገባ በሁዋላ ፖሊስ ፍድር ቤት ያቀረበው ሲሆን፣ አብርሃ በፖሊሶች መደብደቡን፣ እርሱ ያልጻፋቸውን ጽሁፎች የራሱ ጽሁፎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲፈርም መገደዱን፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ብቻውን እንዲቀመጥ መደረጉን እንዲሁም ፖሊሶች ያልሆኑ ሰዎች ምርምራ …
መኢአድና አንድነት ህዝቡ ለትግል እንዲነሳ ጥሪ አቀረቡ
ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመላውኢትዮጵያአንድነትድርጅት (መኢአድ) እናከአንድነትለዲሞክራሲናለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በጋራ ባወጡት መግለጫ “በህውሓት/ኢህአዴግአባላትየሚመራውየኢትዮጵያምርጫቦርድበሰላማዊትግሉላይከፍተኛ መሰናክሎችንበመፍጠርከዚህቀደምየተደረጉምርጫዎች እንዲቀሙ፣እንዲዘረፉናኮሮጆእየተገለበጠለገዢውፓርቲእንዲሰጥከፍተኛሚናሲጫወትመቆየቱ”አንሶ ፣ “ዛሬበግልጽፓርቲዎችንለመዝጋትመሞከሩ በኢትዮጵያሕዝብላይእየፈፀመውያለውከድፍረቶችሁሉድፍረትነው ” ብሎአል፡፡ ” የኢትዮጵያብሔራዊምርጫቦርድከዚህአድራጐቱተቆጥቦትክክለኛየሆነየምርጫሜዳየማያዘጋጅከሆነበሰላማዊሰልፍናማንኛውንምየሰላማዊትግልስልቶችን ሁሉበመጠቀምየምንታገልመሆኑንእናሳውቃለን፡፡” የሚለው መግለጫው፣ ይህንስናደርግሊያስሩን፣ሊያሳድዱንናሊገድሉንእንደሚሞክሩብናውቅም፣በሕዝባችን ላይእየደረሰካለውመከራናየሰቆቃኑሮስለማይብስየሚደርስብንንሁሉለ መሸከምዝግጁዎችስንሆንሕዝባችንምከጐናችንእንደሚቆምበመተማመንነው፡፡ ” ብለዋል። ወጣቱናአዛውንቱበሚደረገውማንኛውምየሰላማዊትግልእንቅስቃሴሁሉ፣በተግባርከጐናቸው እንዲቆም፣በእድሜየገፉአባቶችናእናቶችደግሞበፀሎታቸው እንዲያግዙ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል። ምርጫ ቦርድ ውህደትለመፈፀምያጠናቀቁትንመኢአድናአንደነትንየተለያዩመሰናክሎችንእንዳይዋሃዱ ለማድረግ እየሞከረ መሆኑንም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብሁኔታውንበጥሞናናበእርጋታበመከታተልየዜጎችንመብትለማስከበርበሚደረገውጥረትሁሉከታጋዩችጐንእንዲቆም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል። ለደህንነት፣የፖሊስ እናየመከላከያሠራዊቱአባላት ባቀረቡት ጥሪ ደግሞ …

