ይህን የአንዱአለም አራጌን በራሱ አገላለጽ ከጠባቧ የቃሊቲ እስር ቤት የተጻፈ ግሩም መጽሐፍ ሳነብ የተሰማኝን ስሜት ባጭሩ ለመግለጽ እንጂ ሥነ ጽሑፋዊ ደንብ የተከተለ ሂስ ወይም የመጽሐፍ ግምገማ ለመስጠት አለመነሳቴን መግለጽ እፈልጋለሁ – መሆኑን እንዴት ከረማችሁ? ከሁሉ በፊት ግን ከሰሞነኛ ጉዳዮች መካከል ቂላቂሉ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሠራውን አስቂኝ ድራማ ስመለከት እያዘንኩ የታዘብኩትን በዓለም ወደር የማይገኝለት […]

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት  ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባቁጠባቤቶችኢንተርፕራይዝእስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን  በሰንጋተራእና ቃሊቲ ክራውን ሆቴልበመሳሰሉአካባቢዎችላይእየገነባመሆኑየታወቀሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶችእስከሚቀጥለውዓመትአጋማሽድረስለዕድለኞችለማስተላለፍታቅዷል። የአስተዳደሩምንጮችእንደገለጹትቤቶቹከቀጣይዓመትምርጫበፊትሙሉበሙሉ ተጠናቀውእንዲተላለፉከአስተዳደሩመመሪያተሰጥቷል። ሆኖም ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራምየተመዘገበውጠቅላላሕዝብቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን  በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን የመገንባትአቅምባለመፍጠሩየተመዘገቡትንብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታትበላይጊዜንእንደሚፈልግየአስተዳደሩምንጮችአስታውቀዋል፡፡ …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በአንዋር መስጊድ የተፈጠረውን ተቃውሞ መርተዋል በሚል ከታሰሩት መካከል 6 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የዋስትና መብታቸውን ተነጥቀው ለሰኞ ችሎት እንዲቀርቡ ታዘዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ወ/ት ወይንሸት ሞላ ፣ የፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ ሙሃመድ እና ኢብራሂም አብዱልሰላም በ5 ሺ ብር  ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት በድጋሜ አዟል። …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳግማዊ ሚኒልክና በሌሎችም አካባቢዎች የሚሰለጥኑ ፖሊሶች በቀን የሚታሰብላቸው ገንዘብ በቂ ባለመሆኑ ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊሶቹ ለቁርስና ምሳ እንዲሁም ለሻሂና ቡና 24 ብር በቀን የሚታሰብላቸው ቢሆንም፣ ገንዘቡ አይበቃንም በሚል ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊሶቹ  ስልጣናውን ሳያቋርጡ ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለማግባባት እየሞከሩ ነው። በዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ውስጥ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ከ500 …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆኑ በአዲስ አበባ ለአመታት ታጥረው የተቀመጡ የግንባታ ቦታዎች፣ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት እንዲነጠቁ ውሳኔ አስተላልፈው ውሳኔውም ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጅ ሪፖርተር እንደዘገበው ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤ የግባኝ በማለታቸው የተወሰደባቸው ቦታ እንደሚለስላቸው መደረጉንና የመስተዳድሩ ውሳኔ መቀልበሱን ገልጿል። ተወስደው የነበሩት ቦታዎች ልደታ ክ/ከተማ ዋቢ ሸበሌ ጎንና በየካ …

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊኒ ፣ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ የታየው የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት እንዳይዛመት ከፍተኛ ስጋት በደቀነበት በዚህ ወቅት፣ ከምስራቅ አፍሪካ ኬንያ በበሽታው ከሚጠቁ ቀዳሚ አገራት ተርታ ተሰልፋለች።ኬንያ የብዙ የምእራብ አፍሪካ አገራት የትራንስፖርት ማእከል በመሆኗ በበሽታው የመጠቃት እድላን ከፍ እንዳደረገው የተባበሩት መንግስታት የጤና ድርጅት አስታውቋል። ጀርመን ዜጓቿ ከላይበሪያ፣ ጊኒና ሴራሊዮን እንዲወጡ …

 

 

 

ኢትዮጵያና ሱዳን የጋራ የመከላከያ ኃይል ለመፍጠር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሁለቱም ሃገሮች የመከላከያ ሚኒስትሮች አስታውቀዋል፡፡

ኃይሉ ሥራ የሚጀምረው የፊታችን መስከረም ላይ እንደሚሆን የኢትዮጵያው የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

 

 

 

በምሥራቅ ሐረርጌ በሚዻጋ ቶላ ወረዳ ቆንቆ ዲሞ በሚባል ሥፍራ በሶማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ።

የአከባቢውም ሆነ የክልሉ ባለሥልጣናት ስለግጭቱ ማብራሪያ አልሰጡም።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መረጃው እንደደረሰው ይናገራል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

 

 

 

ኢትዮጵያ ተወልዳ በሦስት ዓመት ዕድሜዋ ከቤተሰቧ ጋር ወደ አሜሪካ የተጓዘችው ሜሮን በጤናና በሕብረተሰብ ሣይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን አግኝታለች፡፡

ሜሪላንድ ግዛት ሞንትጎመሪ አውራጃ ውስጥ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ሜሮን የተቀዳጀችው ሁለት ሽልማት ነው፡፡ አንደኛው ሚስ አፍሪካ-ዩኤስኤ እና በሕዝብ ድምፅ ብልጫም አሸናፊነት ነው፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በስፋት ከተዋወቁት የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች መካከል « ኤሜርጄንሲ ኮንትራሴፕቲቭ» ወይም ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ

ባለፈው ቅዳሜ በአንባብያን ይጠበቁ የነበሩ ሦስት መፅሄቶችና አንድ ጋዜጣ ሳይታተሙ ቀርተዋል ። ያልታተሙት መፅሄቶችና ጋዜጣ የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ክስ እንደመሠረተባቸው ካስታወቀው አምሥት መፅሄቶችና ጋዜጣ መካከል ናቸው ።

የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑሪ አልማሊኪ የኢራን መንግሥት ድጋፍ እንዳላቸዉ ይነገራል። የቴህራን መንግሥት አል ማሊኪ ገና በጎርጎሪዮሳዊዉ 2006ዓ,ም ባግዳድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር ለመጀመሪያ ከያዙበት ጊዜ አንስቶ አዎንታዊ አመለካከቱን ሲቸራቸዉ ታይቷል።

በሃይማኖት ተጨቁነው እና በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ወደሚገኝ ተራራ ተሰደው የሚገኙ 20 000 የሚደርሱ የያዚዲ እምነት ተከታዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነ ነው የሚሰማው። ይህም አንዳንድ ጠበብት እንደሚሉት አሜሪካ ጣልቃ ከገባች በኋላ የተገኘ ለውጥ ነው።

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናት በመያዝ ከአብድራፊ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በአስተዳደር እና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት መማረሩን ተወካዮቹ ተናግረዋል። አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ ህዝቡ በመብራት፣ ውሃ እና በመንገድ ችግር እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላ ተናጋሪ ደግሞ ህዝቡ በድብቅ ጠመንጃ እየተዳደረ መሆኑንና  ወረዳው ህዝቡን ማስተዳዳር …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢ/ር ይልቃል ከ20 የአውሮፓ ህብረት አገራት ልኡካን ጋር በህብረቱ ጽ/ቤት ተገኝተው በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት ፣ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር ወደ ባሰ ችግር ሳትገባ ህብረቱ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል። ኢ/ር ይልቃል ገዢው ፓርቲ ስለሚያደርገው አፈና፣ በሚዲያው ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ፣ በእስር ላይ ስለሚገኙት ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና ጸሃፊዎች የተናገሩ ሲሆን፣ ኢህአዴግ በርእዮታለም መደናበርና በአመራር …

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራልአቃቢያነህጎችእናዳኞች፣የፈደራልማረሚያቤቶችባለስልጣናት፣የፌደራልናየአዲስአበባፖሊስ አመራሮችናየደህንነትሃላፊዎችበአቶአባዱላገመዳአሰልጣኝነት  የኢትዮጵያህዝቦችትግልናሃገራዊሕዳሴያችንበሚልርእስስልጠናጀምረዋል። ስልጠናው ምናልባትም በቅርቡበቀድሞውም/ል ጠ/ሚ  አዲሱለገሰ  በቀረበዉና የኢህአዴግን የአመራር ችግር በሚዘረዝረውን  ጥናት ላይ ለመወያየት ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች ጠቁመዋል። በዚህጥናትኢህኣዴግበከፍተኛየአመራርእጥረትእየተቸገረመሆኑን፣ኦሮሞየሆኑየኦህዴድኣባላትሙሉበሙሉወደኦነግእንዳደሉእንዲሁምደግሞ፣የአማራውክፍልየሆነውብሄረ አማራዲሞክራሲያዊንቅናቄ ከግንቦት7 ጋር ሽርክና መፍጠሩን መግለጻቸው ይታወሳል። አቶ አዲሱ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ ሊሳካ ያልቻለው በአመራር ችግር ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል። ስብሰባው ነሃሴ5የተጀመረሲሆንለ3 ሳምንት ያክል ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢቦላን ለመከላከል የሰለጠኑ ባለሙያዎች ከዛሬ ማክሰኞ፤ ነኀሴ 6/2006 ዓ.ም ጀምሮ ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ተመድበው ፍተሻ እያካሄዱ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በአለባበስ እና በአመጋገብ በክርስቲያንና በሙስሊም ተማሪዎች መካከል አድልዎ ይፈጸማል በተማሪዎች ዲኑ ማንአለብኝነት ተማሪዎች የፍልሰታ ለማርያምን ጾም ለመጾም ተቸግረዋል የጅማ የማኅበረ ቅዱሳን ማዕከል ምእመኑን በማስተባበር ለተማሪዎቹ ድጋፍ እያደረገ ነው ቅ/ሲኖዶስ ሃይማኖታዊ መብታቸውን የሚያስከብር አቋም እንዲወስድ ተማሪዎቹ ጠይቀዋል ‹‹ኦርቶዶክሳዊ ሥርዐተ እምነትን በማንአለብኝነት ለይቶ የመጋፋት አካሔዱ፣ አኹን በደረሰበት ደረጃ አሳሳቢ የሃይማኖታዊል ነፃነት መረገጥ እንጂ የመብል ጉዳይና የአንድ ዩኒቨርስቲ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በምሥራቃዊው ሱዳን ገዳርፍ አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በሰበብ-አስባቡ የአንዳንድ አክራሪ ቡድኖች የጥላቻ ሰለባዎች ሆንን» ሲሉ ብሶታቸውን ገለጡ። በ« ኤስ ኤም ኤስ » የሚደርሱን አጫጭር መልእክቶች እንደሚሉት ከሆነ ብዙዎች

በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ያለቀበት አንደኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት መቶኛ ዓመት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ታስቧል ።በቅርቡ የጦርነቱ መቶኛ ዓመት ከታሰበባቸው ሃገራት አንዷ የጦርነቱ የመጀመሪያዋ ሰለባ ቤልጂግ ናት ።

ዩክሬይን በሀገርዋ ምሥራቃዊ ከፊል በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያን መካከል በቀጠለው ውጊያ ሰበብ የመሠረታዊ አቅርቦት ችግር ላጋጠመው ያካባቢው ነዋሪ ሩስያ በ280 የጭነት ተሽከርካሪዎች አጀብ ሰብዓዊ ርዳታ ልካለች፣

ኢንጂነሩ ካቤኔ ውስጥ መቀጠላቸው ትርጉመ ቢስ መሆኑን መረዳታቸውን በመግለጽ ለግዛቸው ደብዳቤ ያስገቡት የአንድነት አመራሮች ተክሌ በቀለ –ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት በላይ ፈቃዱ —ምክትል ፕሬዘዳንት ሰለሞን ስዮም —የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ዳንኤል ተፈራ — የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳዊት አስራደ —የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሀላፊ ኢንጂነር ግዛቸው በአንድነት እና በመኢአድ መካከል የሚደረገውን ውህደት በማኮላሸት ስራ ላይ ከመሰማራታቸውም ሌላ ሰርጎገቦችን እየሰበሰቡ ፓርቲው […]

አብዛኞቻችን የአንድነት እና መኢአድ ዉህደት ተጠናቆ፣ በአዲስ መንፈስ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄን እንቀጥላለን የሚል ተስፋና ጉጉት ነበረን። የኢትዮጵያዉያንን መተባበር የማይፈልገው ሕወሃት/ኢሕአዴግ፣ በሚቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ አማካኝነት፣ ዉህደቱን ለማጉዋተት እንደተለመደው መስራት ጀመረ። «መኢአድ ያላሙዋላቸው ወረቀቶች አሉ» በማለት ዉህድቱን ማድረግ እንደማይችል አሳወቀ። (የተለመደው የማሰናከል እጁት ተግባር) መኢአድ ሕዝብ ያውቀው ዘንድ፣ ያለውን ሁኔታ ለማሳወቅ መግለጫ አወጣ። በጉዳዩ ላይም ከምርጫ ቦርድ […]

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባወጣው መግለጫ በቡርጅ ብሄረሰብና በቦረና ህዝብ መካከል ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው መልካም ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጸረ-ሰላም ሃይሎች እየደፈረሰ እንደሚገኝ ገልጿል። ከ2 ሺ በላይ የሆኑ የቡርጅ ብሄረሰብ አባላት ከታህሳስ ወር 2006 ኣም ጀምሮ  ከአካባቢው ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእረፍት ላይ የሚገኙ ነባር የዩኒቨርስቲ  ተማሪዎችን፣ የኮሌጅና የቴክኒክ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን እንዲሁም የዘንድሮውን የሁለተኛ ደረጃ ፈተና አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎችን ስለመጪው ምርጫ እና ስለአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ለማወያየት በየክልሎች ስብሰባ መጠራቱ ታውቋል። ከነሃሴ 10 እስከ ነሃሴ 25 በሚቆየው ሰሚናር ላይ ተማሪዎች ምርጫውን ተከትሎ ስለሚፈጠሩ  ረብሻዎች፣ ስለአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳትና …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ሳምንታዊ መጽሔት ባለቤት  እና የመጽሔቱ ሶስት አዘጋጆች ሀገር ለቀው ተሰደዋል። የመጽሔቱ ባለቤት አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ ለኢሳት እንደገለጸው፤ እርሱና ጋዜጠኞቹ  በስርአቱ ሲደርስባቸው የነበረውን ወከባና አፈና ተቋቁመው የአዲስ ጉዳይ መጽሔትን  ህልውና ለማስቀጠል ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ፤ መጽሔቱዋ  በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነት ከማግኘቷም ባሻገር በገንዘብ አቅምም …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የስኳር፣ የቡናና ዱቄት እጥረት ተፈጥሯል። በዱቄት እጥረት የተነሳ በተለይ በአማራ ክልል ሰዎች ዳቦ ለማግኘት ራጃጅም ሰልፎችን ተሰልፈው ወረፋ ለመተበቅ ተገደዋል። ቡና የመጨረሻ ደረጃ የሚባለው በኪሎ እስከ 100 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ ሁለተኛና አንደኛ ደረጃ የሚባሉትን የቡና አይነቶች ፈልጎ …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፈቃዱ ሃይሌን ጠቅሶ እንደዘገበው ከባቡር ፕሮጀክቱ ጋር የተያያዙትን መንገዶች ከመምራት ጋር የተያያዘ ችግር አለ። ዋና ስራ አስኪያጁ ያለምንም ዝግጅትና እውቀት የአስፋልት መንገድ ይቆራጣሉ፣ በቅንጅትም ለመስራት ፈቃደኞች አልሆኑም በማለት ተናግረው፣ “የባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆኜ እንዲህ የተቸገርኩኝ እዚያ ውስጥ ያልገባ ሰው …

ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግብጽ ከስልጣን በተወገዱት ሙሀመድ ሙርሲ ዳጋፊዎች ላይ የጸጥታ ሃይሎች  የወሰዱትን እርምጃ የሚዘረዝረውንሪፖርት ይፋ ለማድረግ ካይሮ የተገኙት የሂውማር ራይትስ ወች ዋና ስራ አስኪያጅ ኬኒስ ሮዝና ሌላዋ ከፍተኛ ባለስልጣን ሳራ ሊህ ወደ መጡበት አገር እንዲመለሱ ተደርጓል። ከ1500 በላይ የተገደሉበትን በአንዳንዶች ዘንድ እንደመፈንቅለ መንግስት የሚታየውን ድርጊት ሂውማን ራይትስ ወች በተደጋጋሚ ሲያወግዝ መቆየቱ …

– ኢንጂነግር ግዛቸው በሕዝብ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀዉን፣ ለአገዛዙ ራስ ምታት የሆነው፣ የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት አመቻች ኮሚቴን አፈረሱ። በአባላትና ደጋፊዎች ዘንድም ትልቅ ድንጋጤ ተፈጥሩዋል። በአገዛዙም ዘንድ ደስታው ጨምሩዋል። – በዉጭ አገር ያሉ የአንድነት ደጋፊዎች በኢንጂነር ገዛቸው ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ እያሰሙ ናቸው። የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ፣ አቶ ተስፋሁን አለምነህ፣ ለሕብር ራዲዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ጸሓፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ

——–

የሀገራችን ቋንቋዎች ከውጪ ቋንቋዎች በርካታ ቃላትን ወርሰዋል፡፡ ይህም ከብሉይ ዘመን ጀምሮ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡ የመወራረሱ አድማስ ስፋቱን የጨመረው ግን በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቀጣዮቹ አንድ መቶ ሀያ ዓመታት ውስጥ የታዩት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ክስተቶች የሀገራችን ቋንቋዎችን ለውጪ ቋንቋዎች ተጽእኖ የበለጠ ክፍት እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል፡፡  

  ታዲያ ከሶስት ሺህ ከሚልቁት የውጪ ቋንቋዎች መካከል ለሀገራችን ቋንቋዎች ብዙ ቃላትን ለማውረስ የበቁት አራቱ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም ዐረብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣሊያንኛና እንግሊዝኛ ናቸው፡፡ የቱርክ እና የጀርመን ቋንቋዎችም ጥቂት ቃላትን ለሀገራችን ቋንቋዎች አበርክተዋል፡፡

*****

   ዐረብኛ በሀገራችን ቋንቋዎች ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር የቻለው በዋናነት የእስልምና ሀይማኖት የአምልኮና የትምህርት ቋንቋ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም ከእስልምና እምነት ጋር በተያያዘ ለአምልኮና ለትምህርት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቃላት በአብዛኛው ከዐረብኛ የተገኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ መስጊድ/መስጂድ፣ ኢማም፣ ቃዲ፣ አዛን፣ መጅሊስ፣ መድረሳ ወዘተ… የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በሂደት ደግሞ የዐረብኛ ቃላት በአምልኮ ውስጥ ካላቸው አስፈላጊነት አልፈው በተራው ሰው ንግግር ውስጥም ገብተዋል፡፡ ይህ ክስተት በስፋት የሚስተዋለው ግን አብላጫው ነዋሪ ህዝብ ሙስሊም በሆነባቸው እንደ ወሎ፣ ሀረርጌ፣ ባሌ፣ ጅማ፣ ሶማሊ (ኦጋዴን)፣ ቤኒሻንጉልና አፋር አካባቢዎች ነው፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ከሚነገሩት ቋንቋዎች “መርሐባ”፣ “አሕለን”፣ “ፉጡር”፣ “ሀድራ”፣ “ሙሐባ”፣ “መናም”፣ “ጂስም”፣ “አዛ”፣ “ኩርሲ”፣ “ማዕና”፣ “ዒልም”፣ “አስል” እና ሌሎች በርከት ያሉ የዐረብኛ ቃላትን በቀላሉ ለይቶ ማውጣት ይቻላል፡፡

ታዲያ የዐረብኛ ቃላትን የመውረሱ ተግባር በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩል ደረጃ የሚጠቀምባቸው በርከት ያሉ የዐረብኛ ቃላትንም ወርሰናል፡፡ ይህም ክስተት የተፈጠረው ከንግድ መስፋፋት ጋር ነው፡፡ በተለይ እስከ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ የሀገራችንን ንግድ በበላይነት ተቆጣጥረው የነበሩት ሲራራ ነጋዴዎች ዐረብኛን በንግድ ቋንቋነት በስፋት ይጠቀሙበት የነበረ ከመሆኑ የተነሳ በሀገራችን ቋንቋዎች ውስጥ መሰረት ያልነበራቸው በርካታ ቃላት እንዲወረሱ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ለምሳሌ ዛሬ የአማርኛ ቃላት አድርገን የምንጠቀምባቸው እንደ  ሀዋላ፣ ጉምሩክ፣ ሰንዱቅ፣ ሱቅ፣ መጋዘን፣ ሽርክና፣ ወኪል፣ ሰነድ፣ ደላላ፣ መሃለቅ ወዘተ የመሳሰሉት የአማርኛ ቃላት ምንጫቸው ዐረብኛ ነው፡፡ እንደ ሐዲድ፣ ባቡር እና መኪና የመሳሰሉ ቃላትም ከዐረብኛ ነው የተወረሱት፡፡ ይሁንና ዐረብኛና አማርኛ ሴማዊ ቋንቋዎች በመሆናቸው የሚጋሯቸውን ቃላት እንደ ውርስ ቃላት ማየት ስህተት ነው፡፡ ለምሳሌ ሰላም፣ ደም፣ ቤት፣ ፎቅ፣ ክፍል፣ ዐይን፣ ፈረስ፣ ዘመን፣ ሐሩር፣ ሚዛን የመሳሰሉ ቃላት በሁለቱም ቋንቋዎች ውስጥ አሉ፡፡ ሁለቱም ቋንቋዎች ሴማዊ በመሆናቸው ነው እነዚህን ቃላት የተጋሩት፡፡ የነዚህ ቃላት መነሻ የሁሉም ሴማዊ ቋንቋዎች አባት እንደሆነ የሚታመንበት ግንደ-ሴማዊ ቋንቋ (Proto-Semetic Language) ነው፡፡

*****

     አዲስ አበባን ከጅቡቲ ጋር የሚያገናኘው የኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር መስመር ሲሰራ ደግሞ ፈረንሳይኛ ወደ ሀገራችን ቋንቋዎች እየሰረገ መግባት ጀምሮ ነበር፡፡ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትም በ1910ዎቹ ውስጥ ሲከፈት የፈረንሳይኛ ተጽእኖ በጣም ተጠናክሯል፡፡ የዘመኑ የትምህርት ካሪኩለምም ከፈረንሳይ የተቀዳ በመሆኑ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና ምሩቃኑ ፈረንሳይኛን ይናገሩ ነበር፡፡ በነዚያ ምሩቃን በተሞላው ሲቪል ሰርቪስም ሆነ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ፈረንሳይኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ለመንግሥታዊ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ሰነዶችና የስራ መመሪያዎችም ከፈረንሳይኛ ሲተረጎሙ ነው የኖሩት (የመጀመሪያው ህገ-መንግሥትም ከፈረንሳይ የተቀዳ ነው)፡፡  በዚህም ሂደት በርካታ የፈረንሳይኛ ቃላት በአማርኛ ተወርሰዋል፡፡ ከፈረንሳይኛ ከወረስናቸው ቃላት መካከል “ኦፊሴል”፣ “ሞኖፖል”፣ “ሌጋሲዮን”፣ “ኮሚስዮን”፣ “ፔኒስዮን”፣ “ዲክላራሲዮን”፣ “ኦፕራሲዮን”፣ “ካሚዮን”፣ “ፍሪሲዮን”፣ “ሬኮማንዴ”፣ “ለገሀር (ላጋር)፣ “ቡፌ”፣ “ሌሲ ፓሴ”፣ “ዴኤታ”፣ “ ካፌ”፣ “ራንዴቩ”፣ የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

   የኢጣሊያ ወረራ ከተወልን ማስታወሻዎች መካከል ትልቁ በሀገራችን ቋንቋዎች ውስጥ የሚታየው የጣሊያንኛ ተጽእኖ ነው፡፡ በአማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጣሊያንኛ ቃላትን መቁጠር ይቻላል፡፡ በተለይም በቀድሞ ዘመናት ከተሽከርካሪ እና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ጋር በተያያዘ ከሚሰራባቸው ቃላት መካከል ብዙዎቹ የጣሊያንኛ መሰረት ያላቸው ናቸው፡፡ ዛሬም ድረስ የነዚያ ቃላት ቅሪቶች በሀገርኛ ቋንቋዎች ውስጥ ይስተዋላሉ፡፡ ከጣሊያንኛ ከወረስናቸው ቃላት መካከል “ፓስታ”፣ “ማካሮኒ”፣ “ላዛኛ”፣ “ስፓጌቲ”፣ “ስልስ” (ሳልሳ)፣ “አሮስቶ”፣ “ፋብሪካ”፣ “ጋዜጣ”፣ “ሊቼንሳ”፣ “ፉርኖ”፣ “ቪያጆ” (በመኪና የሚደረግ ጉዞ)፣ “ላቫጆ”፣ “ካሮሴሪያ”፣ “ካምቢዮ”፣ “ሞቶሪኖ”፣ “ፍሬን”፣ “ፊልትሮ”፣ “ሳልቫታዮ”፣ “ፖርቶ መጋላ”፣ “ፒንሳ”፣ “ቺንጊያ” ፣ “ፈረፋንጎ”፣ “ኩሽኔታ” “ኪያቤ”፣ “ካቻቢቴ” “ባሌስትራ”፣ “ቸርኬ” “ፒስታ” “ኮማርዳሬ” “ጎሚኒ” “ሮንዴላ” “ዲፍረንሻሌ” “ስፒናታ” “ሳልዳሬ” “ቡኮ”፣ “ፖምፓ” (ቧንቧ)፣ “አውታንቲ”፣ “ማኖ”፣ “ኢሊ ጎሬ”፣ “ቴስታ”፣ “ፑንቶ”፣ “ቦጦሎኒ”፣ “ካምቦ” ወዘተ…. የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

*****

ጣሊያኖች ከተባረሩ በኋላ እንግሊዝኛ በሀገርኛ ቋንቋዎች ውስጥ ሰርጾ መግባት ጀመረ፡፡ በተለይ እንግሊዞች በኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩባቸው አስር ዓመታት የእንግሊዝኛ ቃላት በሀገራችን ቋንቋዎች በብዛት ተወረሱ፡፡ በዚያን ጊዜ ከተወረሱት ቃላት ውስጥ እስከ አሁን ድረስ በአገልግሎት ላይ ያሉትን እንደ “ፖሊስ”፣ “ባንክ”፣ “ሚኒስቴር”፣ “ካፒታል”፣ “ኤሌክትሪክ”፣ “ኮሌጅ”፣ “አካዴሚ”፣ “ኤክስፐርት”፣ “ዲሬክተር” የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም እንደ ፕሮፌሰር፣ ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ጄኔራል፣ አድሚራል፣ ኮሞዶር፣ ኮሎኔል እና ካፒቴን የመሳሰሉ የማዕረግ ስሞችም የተወረሱት ከእንግሊዝኛ ነው፡፡

    በእንግሊዝኛ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የተነሳ ፈረንሳይኛና ጣሊያንኛ በሀገራችን ቋንቋዎች ላይ የነበራቸው ተጽእኖ በፊት ከነበረበት ደረጃ ሊያድግ አልቻለም፡፡ ነገር ግን በሀገራችን ቋንቋዎች የተወረሱት የጣሊያንኛና የፈረንሳይኛ ቃላት በዘመኑ አገልግሎት መስጠታቸውን አላቆሙም፡፡ ለምሳሌ በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዘመን “ኮሚሲዮን” እንጂ “ኮሚሽን” የሚባል የአማርኛ ቃል አይታወቅም፡፡ ከፈረንሳይኛና ከጣሊያንኛ የተወረሰ የሀገርና የከተማ አጠራርም ቢሆን በአማርኛ ቋንቋ አንዳች ለውጥ ሳይደረግበት ያገለግል ነበር፡፡ እንደ ምሳሌም “ቤልጅግ”፣ “ስዊስ”፣ “ሎንዶን”፣ “መስኮብ”፣ “ብሩክሴል” የመሳሰሉትን የሀገርና የከተማ ስሞች መጥቀስ ይቻላል፡፡

    ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ውድቀት በኋላ ግን ከፈረንሳይኛና ከጣሊያንኛ የተገኙ የሀገርና የከተማ ስያሜዎች ከእንግሊዞች በተወረሱ ስሞች ተተክተዋል፡፡ በዚህም መሰረት “ቤልጅግ” ወደ “ቤልጅየም”፤ “ስዊስ” ወደ “ስዊትዘርላንድ.፣ “ብሩክሴል” ወደ “ብራሰልስ”፣ “መስኮብ”ም ወደ “ሞስኮ” ተለውጠዋል፡፡ በመሆኑም ከልዩ ልዩ  ቋንቋዎች በተገኙ የቦታ ስያሜዎችና ቃላት ተውቦ ይታይ የነበረው አማርኛ የመኮማተር ባህሪን ለማዳበር ተገዷል፡፡

   ይህ ቀደምት ውርስ ስሞችን በእንግሊዝኛ አጠራሮች የመተካቱ ሂደት ሳያቋርጥ በመቀጠሉ ከሁለቱ ቋንቋዎች (ከፈረንሳይኛና ጣሊያንኛ) የተወረሱ የሀገር ስሞችን ከማራገፍ አልፎ በጥንታዊው አማርኛ ውስጥ መሰረት የነበራቸውን የሀገር ስሞችንም በእንግሊዝኛ ስያሜዎች መለወጥ ተጀምሯል፡፡ ለምሳሌ የዓለም ትልቋ ሀገር ከጥንት ጀምሮ በአማርኛ ስትጠራ “ሩሲያ” ነው የምትባለው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን “ራሽያ” የሚለው አጠራር እያየለ መጥቷል፡፡ “ስጳኝ” የሚለው ትክክለኛ የአማርኛ አጠራር “ስፔን” በሚለው የእንግሊዝኛ ቅጂ ተቀይሯል፡፡ “አርመን” የሚለው አጠራርም በ“አርሜኒያ” ተተክቷል፡፡ “ቤልጅግም” ወደ “ቤልጅየም” ተቀይሯል፡፡ “ቆጵሮስ” የሚለውን ጥንታዊ የአማርኛና የግዕዝ አጠራር “ሳይፕረስ” በሚለው አዲስ ደራሽ የቅጂ ስም የሚለውጡ ሰዎችም እየበረከቱ ነው፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በኦፊሴል ያገለግሉ የነበሩት እንደ “ነምሳ” (አውስትሪያ) እና “ናርበጅ” (ኖርዌይ) የመሳሰሉ የሀገራት መጠሪያዎች በዚህ ዘመን በአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት መስጠታቸውን አቁመዋል፡፡

   ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ የፈረንሳይኛና የጣሊያንኛ ውርስ ቃላትም ቢሆኑ የመጥፋት እጣ ደርሶአቸዋል፡፡ ለምሳሌ በዛሬው ዘመን ከፈረንሳይኛ በተወረሰው “ኮሚሲዮን” የሚገለገል ሰው የለም፡፡ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች በስፋት ሲያገለግል የነበረው “ኦፕራሲዮን”ም በዚህ ዘመን “ቀዶ ጥገና” እና “ኦፕሬሽን” በሚሉት ስሞች ተተክቷል፡፡ “ፔኒሲዮን” የሚለው ቃልም ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱን አቁሟል፡፡

*****

 “እነዚህ ቃላት ድሮውንም የውጪ ቃላት በመሆናቸው ከአማርኛ መጥፋታቸው የሚያስነሳው አቧራ የለም” ይባል ይሆናል፡፡ ነገሩን በታሪክና በአንትሮፖሎጂ መነጽር ካየነው ግን ትልቅ ጉዳት አለው፡፡ ምክንያቱም የነዚህ ቃላት በቋንቋዎቻችን ውስጥ መኖር የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታሪካችን የተጓዘበትን መንገድና የእኛነታችንን ህብርነት የሚያሳይ በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው የፈረንሳይኛ ቃላት በአማርኛ ውስጥ በመኖራቸው ተገርሞ “ይህ እንዴት ተከሰተ?…” የሚል ጥያቄ ቢያቀርብ የጅቡቲው ምድር ባቡርና የተፈሪ መኮንን ትምህርት ታሪክ ይተረክለታል፡፡ በጣሊያንኛ ቃላት ላይ ጥያቄ ለሚያቀርብ ሰውም የአምስቱ ዓመቱ የኢጣሊያ ወረራና የአርበኞቻችን የተጋድሎ ታሪክ ይነገረዋል፡፡

በሌላ በኩል በአንድ ቋንቋ ውስጥ ያሉ ውርስ ቃላትና ሀረጋት የታሪካዊ ምርምር መሰረቶች የሚሆኑበት አጋጣሚም ሞልቷል፤ ቃላቱና ሐረጋቱ እንደ ታሪክ ማስረጃ የሚያገለግሉበት ሁኔታም አለ፡፡ ብዙ የታሪክ እንቆቅልሾች በቃላትና በሀረጋት መነሻነት ሊፈቱ ችለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዛሬ በግዴለሽነት ከኦሮምኛና ከአማርኛ ቋንቋ ውስጥ እየተወገዱ ያሉት የፈረንሳይኛና የጣሊያንኛ ውርስ ቃላቶቻችን ጠሊቅ የሆኑ ኪነታዊ ስራዎች የሚወጠኑበት መሰረቶች ሆነው ሲያገለግሉ ታይተዋል፡፡ እንደምሳሌም የቴዲ አፍሮን “ሼ-መንደፈር” እና “ላምባ ዲና”ን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ቴዲ እየረሳናቸው ያሉትን አንድ የፈረንሳይኛና አንድ የጣሊያንኛ ቃላትን ወስዶ የሁለት ውብ ዜማዎች መሰረት አድርጎአቸዋል፡፡ በመሆኑም ውርስ ቃላቱን በነበሩበት ሁኔታ ማስቀጠሉ ተገቢ ነው፡፡  

   በዚህ ረገድ የሀገራችን ሚዲያዎችና ፕሬሶች ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ እያካሄዱት ያለውን አጥፊ ሚና መግታት አለባቸው፡፡ ፈረንሳይም ሆነ እንግሊዝ፣ ጣሊያንም ሆነ ጀርመን ሁሉም ባዕድ ነው፡፡ ፊት የመጣውንና በህዝቡ ውስጥ የቆየውን ቃል አስወግዶ በሌላ የባዕድ ቃል መተካት በምንም መልኩ የስኬት መለኪያ አይሆንም፡፡ በተለይ ግን በረጅም ዘመናት የታሪክ ጉዞአችን ያዳበርናቸውንና እኛ ብቻ የምንጠቀምባቸውን ጥንታዊ የሀገርና የከተማ አጠራሮች (ሩሲያ፣ ቆጵሮስ፣ አርመን፣ ደማስቆ፣ ስዊስ፣ ኡክራኒያ፣ ቱርክ፣ ኢጣሊያ፣ ሮማ፣ አቴና፣ ሶሪያ፣ ፍልስጥኤም፣ ሊባኖስ፣ ግብጽ ወዘተ.. የመሳሰሉትን) ከእንግሊዝኛ በተኮረጁ ስሞች (ራሽያ፣ ሳይፕረስ፣ ደማስከስ፣ ፓለስታይን፣ ኢጂፕት ወዘተ..) መተካት ይቅርታ የማይሰጠው ጥፋት ነው፡፡ ቴክኖሎጂንና የተቀላጠፈ አሰራርን መኮረጅ እንጂ ነባር ቃላትን ማጥፋት የእድገት መሰረት ሊሆን አይችልም፡፡ ዐረቦችም ሆኑ ፈረንጆች፣ ቱርኮችም ሆኑ ህንዶች እንዲህ ዓይነት ጥፋት ሲያጠፉ አይታዩም፡፡ እኛም ይህንኑ ፈለግ መከተል አለብን፡፡ ስለዚህ የሚመለከተው ሁሉ ለጉዳዩ አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል፡፡

——–

አፈንዲ ሙተቂ

ግንቦት 13/2006

ሸገር-አዲስ አበባ