”አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ” በፍቃዱ ኃይሉ ከቂሊንጦ እስር ቤት
በፍቃዱ ኃይሉ (የዞን 9 ብሎገር ከቂሊንጦ እስር ቤት)
”ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!”፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ። በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ”አባሪዎቼ” ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል።