ሀገራችን የጀግና ደሀ አይደለችም ጀግኖች የሞሉባት ሀገር ናት። በየተሰለፍንበት መሰኩ አለምን ያስደመመ ጀግኖች ያፈራች አገር ነች።በትምህርቱ ዘርፍ እስከ ሳይንቲስት የደረሱ የትምህርት ጀግኖች አሉ። በሰዕሉ እስከ የአለም ሎሬት የደረሱ የስእል ባለሞያ…

The post በአገር ሙሉ ጀግና ሞልቶ ወያኔን ጀግና አሉት። appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የቅዳሜ ምሽት የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በዘንድሮው Grammy Award በስድስት የተለያዩ ከፍሎች ብእጩነት ቀርቦ በአራቱ አሸንፎ 4 ዋንጫዎችን ይዞ እቤቱ የገባውን የ Sam Smithን ሙዚቃዎቸ ያካትታል

• ‹‹የራዲዮ ጣቢያውን አድሎአዊነት ያረጋገጠ ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ • ‹‹ፓርቲዎች ኢህአዴግ በቀደደው ቦይ እንዲፈስሱ የሚያስገድድ ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ (ኤፍ ኤም 96.3)…

The post ኤፍ.ኤም 96.3 የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም መለሰ – ነገረ ኢትዮጵያ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የካቲት ፳፬(ሃያአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጊቱ የተፈጸመው  ማክሰኞ የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም ሲሆን አንድ የሱዳን ታርጋ ያለው ፣ በሱዳናዊ ሹፌር የሚሽከረከር ማዳበሪያ ያጫነ ከባድ መኪና  ከሱዳን ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ ነው። መኪናው እንፍራዝ እየተበላ በሚጠራ አነስተኛ ከተማ ላይ ሲደርስ አንዲት መኪና በመጠበቅ ላይ የነበረች ኢትዮጵያዊት ወጣት ሹፌሩን ትብብር ጠይቃው  ትሳፈራለች።  ምክንያቱ በውል …

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ፣ ኤፍ ኤም 96.3፣ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ ያቀረባቸውን መልእክቶች እንዲለውጥ፣ ካልለወጠ ግን እንደማያስተላልፍ ገለጸ። ጣቢያው እንዲወጡ ከጠየቃቸው መልእክቶች መካከል ‹‹ሀገራችን ዛሬ በቀሪው ዓለም የምትታወቀው በእርስ በርስ ጦርነት ነው›› የሚለው የሚገኝበት ሲሆን፣ መልእክቱ ለአመጽና ለሁከት የሚያጋልጥ ነው የሚል ምክንያት …

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞ የደርግ ወታደሮችን በማሰባሰብ  በህወሓት በጎ ፈቃድ የተመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተመሠረተበትን 25 ዓመት በድምቀት ለማክበር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳባ ደበሌ  በሰጡት መግለጫ ኦህዴድ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ከመጋቢት 1 እሰከ መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሃግብሮች …

የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅዱስ ጊዮርጊስ እና  የአልጀሪያው -ኤል ኡልማ  ቡድኖችን  ጨዋታ ለማየት በባህርዳር ስታዲየም በእንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከጨዋታው በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ሰአት ጨዋታውን ለመመልከት በስቴዲየሙ የተገኘው ሕዝብ በታላቅ ቁጣ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማቱ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የክልሉ ወኪላችን ገልጻለች፡፡ አብዛኛው ህዝብ ከተቃውሞ ድምጹ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት በእጁ …

የዩክሬን መንግሥትና አማፅያን ከሁለት ሳምንት በፊት ሚንስክ ቤላሩስ ውስጥ የተስማሙበት የተኩስ አቁም አሁንም መጣሱ ቀጥሏል ። ከስምምነቱ በኋላ በሩስያ ይደገፋሉ የሚባሉት አማፅያን በአንዳንድ የምሥራቅ ዩክሬን ከተሞች ይዞታቸውን እያጠናከሩ ነው ። ለመሆኑ በምሥራቅ ዩክሬን ከተሞች ህይወት ምን ይመስላል ?

የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙ 6 የኦሮሞ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በድሎናል ሲሉ አማረሩ ። የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ግን ያልተፈታ ችግር እንደሌለና በተለይ በአባላት ላይ ይደርሳል ስለተባለው እንግልት ቦርዱ እንዳልሰማ ተናግረዋል ።

የሞ ኢብራሂም ድርጅት የመልካም አስተዳደር ሽልማቱን ትናንት እንደገና ለአንድ አፍሪቃዊ መሪ ሰጠ። የድርጅቱ ሽልማት ሰጪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው፣ ዘንድሮ ለዚሁ ሽልማት የበቁት ተሰናባቹ የናሚቢያ ፕሬዚደንት ሂፊኬፑንዬ ፖሀምባ ናቸው።

ወርሃ የካቲት በሃገራችን በርከት ያሉ ወሳኝ ታሪካዊ ሁነቶች የተካሄዱባት ወር ነች፡፡ከሃገራችን አልፎ አፍሪካን፣ ከዛም ገፍቶ የላቲን አሜሪካን ጥቁሮችን ያኮራው፣ በአጠቃላይ በነጭ ቅኝ አገዛዝ ስር ለነበሩ ሁሉ የነፃነት ተስፋ ለመሆን የበቃው…

The post አድዋ እና ደደቢት የተቀመጡበት ሰባራ ሚዛን -(ፍቱን መፅሄት ላይ የተስተናገደ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱን የገዳሙ መነኰሳት እየተናገሩ ነው፡፡ ከጠዋቱ 2፡00 ገደማ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው፡፡ ይህ አቅጣጫ፣ የገዳሙ ሞፈር ቤት የሚገኝበት መውጫ መንገድ ሲኾን በአኹኑ ሰዓት በበርካታ ቦታዎች ጭስ እንደሚታይ በመነኰሳቱ ተገልጧል፡፡ የቃጠሎው መንሥኤ በውል …

ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ

የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ

በአበበ ገላው@ አዲስ ቮይስ
Image
ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር። ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።

በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።

ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።

ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።

 

የመሠረተ ልማት ሕጎች በሀገሮች መካከል የሚፈጠሩ ግንኙነቶችን ከሌሎች ሀገሮች በተሻለ መንገድ እንደሚያስተሳስሩ አንድ ጥናት አመለከተ።

የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮችን የሚያስተሳስሩ በርካታ የመሠረተ-ልማት ፕሮጄክቶች ቢቀረፁም ለማስፈፀም እንቅፋት የሚሆን ብርቱ የገንዘብ እጥረት እንዳለም ተጠቁሟል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የካቲት ፳፫(ሃያሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን የጣሊያንን ወራሪ ሃይል ድል የመቱበትና ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁሮች በነጮች ላይ የአሸናፊነት ታሪክ የጻፉበት የአድዋ ድል 119 አመት በአል በአዲስ አበባ ተከብሮአል። በርካታ አርበኞችና ወጣቶች ፣ የአድዋን ድል በመሩት በአጼ ሚኒሊክ ሃውልት ዙሪያ በመሰባሰብ ቀኑን አክበረው የዋሉ ሲሆን ወጣቶች  የጀግንነት መገለጫ የሆነውን ባህላዊ ሽለላ ሲያሰሙ፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፖሊስ …

የካቲት ፳፫(ሃያሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብረታብረት ኢንዱስትሪዎች  ከኃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ ከአቅርቦት ማነስ እንዲሁም ከውጪ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ በሙሉ አቅማቸው ማምረት አለመቻላቸውና ለኪሳራም እየተዳረጉ መሆናቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሰሞኑን በግዮን ሆቴል የ2007 ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ባሳወቀበት ወቅት እንደተጠቀሰው በብረታበረት ዘርፍ ወደ 60 የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን …

የካቲት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ዘንዘልማ ግቢ ውስጥ በተካሄደው ስልጠና ለመሳተፍ ከአማራ ክልል ከሚገኙ ከተሞች ለመጡ 450 የከተማ ልማት ዘርፍ  ባለሙያዎችና ሃላፊዎች በተሰጠው ግምገማ አስር ባለሙያዎች ብቻ የተሰጣቸውን የብቃት መመዘኛ ማለፋቸው የክልሉንና የፌዴራል ሃላፊዎችን ክፉኛ ማስደንገጡን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ባለሙያዎቹና ሃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሙያ ሁኔታ የተሰማሩ የከተማ ፕላን …

በኢትዮጵያ ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ለዲሞክራሲ ፣ ለፍትህ እና ለነጻነት ለሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርጫፍ ጽ/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ክፍል…

The post የ119ኛው የአድዋ ድል በዓል በኖርዌይ በርገን ከተማ ቅዳሜ መጋቢት 19.2007 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተከበረ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

እጎአ በ2022 በረሃማዋ ቓታር ውስጥ ሊከናወን ዕቅድ የተያዘለት የዓለም ዋንጫ ውድድር ከወዲሁ ውዝግብ አስነስቷል። የአውሮጳ ቀዳሚ ሊጎች ያከናወኑዋቸውን ጨዋታዎች ከእንግሊዝ ተነስተን ጀርመን፣ ብሎም ስፔን እና ጣሊያን ደርሰን እንቃኛለን።

የሁቲ አማፂዎች ርዕሰ-ከተማ ሰነዓ የዶለዉ ግን ከኢራን ርዳታ ይልቅ በዩናይትድ ስቴትስና በአረብ ተባባሪዎችዋ የሚረዱት የየመን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ግራ አጋቢ ግን ተመሳሳይ የጅል ስልት ነዉ።የፕሬዝዳንት አብድ ረቦ መንሱር ሐዲ፤ የዓሊአብደላ ሳላሕና የጄኔራል አሊማ ሑሴይን ተቃራኒ ግን ተመሳሰይ ሴራ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ በአፄ ዳግማዊ ምንይልክ መሪነት ፣ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ ም ፤ ቅኝ ግዛት ለማስፋፋት ዘምቶ በነበረው የኢጣልያ ጦር ላይ ድል የተቀዳጀበት 119ኛው የአድዋ ድል በዓል፤ ዛሬ በሀገሪቱ በመላ ተክብሮአል ።

በቅድሚ የኢሳት አድማጭ እንደሆንኩ ይታወቅልኝ። ኢሳት ከኢቲቪ ( 400 እጥፍ ይሻላል) “አሉ አሁንም ፖለቲከኞች አሉ የሚያወሩ። ስንሰባሰብ ሁሉ ጄነራል እንትና ይሄን አድርገው፤ እና ኮሎኔል እንትና …እኔ ስሙን ልከየት እንደሚያመጡት አላወቅም። እንትን ሬዲይ ይጎረጉራሉ። አገር ቤት ጠዋት ተነስትው አንድ ወንድም ትልቅ የ እግዚባሄር ሰው ነው ፣ እኮ ተነስቶ ዜና ልሰማ ነው አለ። የምን የአገር ቤት … […]

ክርስትና ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ የሚል አጅግ በሳል የስው ልጆችን ከግፍ የሚያወጣ ግፍና ግፈኞችን የሚፋለም አንጂ በህዝቦች ላይ ግፍ አየተፈጸመ ዝም በሉ ወይንም  ግፈኞችን ሺ አመት ያንግስ የሚል  የግፍ ተባባሪ…

The post ዜና አትሰሙ ስብከት ክርስቶሳዊ አይደለም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ፖሊሶች “ያልተፈቀደ ስብሰባ” ነው በለው በተኗቸው:: ‪
ይህ የምታዩት ቪዲዮ (መክስተ ምስል) ዛሬ የአድዋን በዓልን አያከበርን ባለበት ወቅት እድሜአቸው ከ10-16 የሚሆኑ ህፃናት እንደ አባቶቻችን ሽለላና ቀረርቶ እያሰሙ እያለ ፖሊሶች “ያልተፈቀደ ስብሰባ” ነው በለው በተኗቸው …ሰዉ ቢቃወምም በሃይል በተኑን…..ግን ለምን?? በአሉ የነሱስ አይደለም እንዴ????? እረ ምን ጉድ ነው::

Please wait, video is loading…

የታዛቢነት ግብዣም ከመንግስት አልቀረበልኝም ብሏል የግንቦቱን ምርጫ ለመታዘብ ከመንግስት ግብዣ እንዳልቀረበለት የገለፀው የአውሮፓ ህብረት፣ ባለፉት ሁለት ምርጫዎች በታዛቢዎቼ የቀረቡ ሪፖርቶች በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት ማጣታቸውም ከታዛቢነት እንድርቅ ገፋፍቶኛል አለ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት…

The post የአውሮፓ ህብረት “ሪፖርቶቹን መንግስት ስለማይቀበል ነው ምርጫውን የማልታዘበው” አለ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

Image
እንኳን ለአንድ መቶ አስራ ዘጠነኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
ዋ!….ያቺ ዓድዋ
ዋ!….
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ….
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመሰዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና….
ዋ !
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስርዋ
የኢትዩጵያነት ምሰክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው -እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው !
ዋ !…ዓድዋ…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ ፥ በለው -በለው !
ዋ !….ዓድዋ….
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እንደገና ።
….ዋ!….ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የእለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…..
የካቲት – (፲ ፱ ፻ ፷ ፬- ዓድዋ )
እሳት-ወይ-አበባ
ከጸጋዬ-ገብረ-መድኅን

“አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!” አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር -ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። “ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን” ሲሉ አሳቁን። ቀጠል አድርገውም “ምጽዋና አሰብን ወያኔ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፈልገው” እንደነበር ተናግረው አሳቁን። “…የሰራነው ጥፋት ስለሌለ የሚጸጥተን […]

“አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!” አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር – ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር…

 ኤሊያስ ገብሩ -ጋዜጠኛ

‹‹የ‹አዲስ ነገር› ጋዜጣን ሳስብ ኩራት ይሰማኛል››
‹‹በዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋዜጠኝነትን ለመስራት ምን ያህል ተጠቀምንባቸው?!›› 
                                                          ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ 

‹‹በ ‹አዲስ ጉዳይ›› መጽሔታችን ብዙ እንሰራለን ብለን በአጭሩ ተቀጭተናል››

‹‹በሙያችን ለሀገራችን አበርክቶት መስጠት ይጠበቅብናል፡፡››
                                                          ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ

‹‹በሀገራችን የነጻነት ጥያቄ ፊት ለፊት ፍጥጥ ብሎ መጥቷል››
‹‹…ብዙዎቻችን የምንሻው ነጻነት የሚመጣው ጥቂቶች በሚከፍሉት ዋጋ ብቻ አይደለም››
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

ባሳለፍነው ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍቃዱ ማህተመወርቅ እና ሳሙኤል አበበ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አብርተን ነበር፡፡ ፍቃዱም ወደዞን አንድ፣ ሳሙኤል ወደዞን እኔ ደግሞ ወደዞን ሶስት ለጥየቃ ገባን፡፡ ከታሰሩ አንድ ዓመት ሊሞላቸው ያሉትን ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ እንዲሁም የዞን 9 ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀን አስጠራኋቸው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

አቡ ዳውድ ኡስማን በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ የህገ ወጡ መጅሊስ ሰብሳበቢ የሆነው አቶ አብዱ እና የክፍለከተማው የመስጂድ እና አውቃፍ ዘርፍ ሃላፊ የነበረው አቶ ሰኢድ በተለያዩ ክሶች ወደ እስር ቤት መግባታቸውን…

The post አስገራሚ ዜና! – በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ የህገ ወጡ መጅሊስ አመራር የሆኑት አቶ አብዱ እና አቶ ሰኢድ በተለያዩ ክሶች ወደ እስር ቤት መግባታቸውን ታወቀ! appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በግሩም ተ/ሀይማኖት ኢትዮጵያዊኖች በአረብ ሀገራት ስደታቸው ጥሩም መጥፎም ይገጥማቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ራሳቸውን አጠፉ በሚል ሰበብም አሰሪዎቻቸው ይገሏቸዋል፡፡ እንዴት ሞቱ የሚል ማጣሪያ ወይም ምርመራ አይደረግም፡፡ ከተቻለ ሬሳቸው ይላካል ካልሆነም ፍሪጅ ውስጥ…

በጨረታ የተሰጠ የ61 ሚ. ሕንፃ በዲዛይን ክለሳ ስም ያለጨረታ ብር 175 ሚ. ተደርጓል ሢሦ ለማይሞላ ሥራ የተፈጸመው ከብር 25 ሚ. በላይ ክፍያ እንዲመረመር ተጠይቋል ሊቀ ጳጳሱ ያልፈቀዱት የብር 40 ሚልዮን የኪራይ ውል ከንግድ ባንክ ጋራ ተፈጽሟል ከባንኩ የተለቀቀው ብር 14 ሚ. ያህል ገንዘብ በሕገ ወጥ ክፍያ እንዳይባክን ተሰግቷል ያለውድድር በተሠራ ፕላን ከብር 12 ሚ. በላይ …

ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰት ያጣችው ገንዘብ መጠን 10 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል ። ኢትዮጵያም አጣች የተባለው ገንዘብ በሃገሪቱ ድህነትን ለመቀነስ የተወሰዱትን እርምጃዎች ሊያፋጥን ይችል እንደነበርም ነው የተገለፀው ።

በከፊል የተቀዳውን የፓስተሩን ንግግር የሰማሁት “ሰልማ” የተሰኘውን ፊልም አይቼ እንደተመለስኩ ነበር። በዚህ አመት ለአራት የኦስካር ሽልማት የበቃው “ሰልማ” ፊልም ኦፕራ ዊንፍሬን ጨምሮ ምርጥ አክተሮች ይተውኑታል። ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ1965 በዩናይትድ ስቴትስ የጥቁሮች የመምረጥ መብት ገፈፋን ተከትሎ፣ ዶክተር ማርቲን ሉተር ይህ መብት እንዲከበር የሚያደርገውን ትንቅንቅ ያሳየናል። ፓስተር ሉተር ለዜጎች የመምረጥ መብት እንዲከበር ያለማቋረት በመስበኩ ሲደበደብ፣ ሲንገላታና ሲታሰር […]

መግቢያ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ከተመሠረተ ጀምሮ የተለያዩ ስሞችን፣ መርኆዎችን፣ ተግባራትን፣ ባጠቃላይም ማንነትን ተከናንቧል። ይህ ማለት፤ በሂደቱ እየተቀያየረ የሄደ ድርጅት ነው። ሲነሳ፤ አሁን የያዘው እምነት፣ ግብና አሠራር አልነበረውም። እግረ መንገዱን ለዕለቱ የሚረዳውን የፖለቲካ አቋም እየውለበለበ ተጓዘ እንጂ፤ ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ አቋም አልነበረውም። ይህ የሚነግረን፤ ይህ ድርጅት፤ አጋጣሚዎችን ተጠቃሚነትን፣ ሥልጣንን፣ ቂምና በቀልን፣ የሕልውናው መሠረቶች አድርጎ የተጓዘ […]