ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ሳምንታት በውዴታና በግዴታ ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ  ወጣቶች አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸውን አምለጠው የመጡ ወጣቶች ለኢሳት ተናግረዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ወጣት “በመጀመሪያ የወረዳው ባለስልጣናት ለስብሰባ ጠርተውን መንጃ ፈቃድና ልዩ ልዩ ስልጠና ስለምንሰጥ ከነገ ጀምሮ ተነሱ አሉን። እኔና 50 የምንሆን ጓደኞቼ በማግስቱ …

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በተወሰኑ የፊደራል ፖሊስ አባላትና እና በማረሚያ ቤቶች ጠባቂዎች ላይ በተካሄደ ድንገተኛ ማጣራት፣ በ18 የፀጥታ አባላት ስልኮች ላይ በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም  ፎቶዎች መገኝታቸውን የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል። የደህንነት ሃይሉ ከባለቤቱ ፈቃድ ውጭ ስልክ የመጥለፍ ፤ የኢንተርኔት አካውንት በመስበር …

ሚያዝያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ ሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ መብራት እየተቆራረጠ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በህዝቡ ጥያቄ የተወጠሩት የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት  ሃላፊ ሠራተኞቻቸውን ተጠያቂ አድርገዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት  የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገብረእግዚአብሔር ታፈረ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ለመብራት መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ ምግባረ ብልሹ ሠራተኞቻቸው መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን …

የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ አዳዲስ ዜና ዘገባዎችን እና ካለፈው የቀጠለ የሰሃራ በረሃ ተጓዦች ትዝታን የሚያስቃኝ ትረካ ቀጣዩን ክፍል 3 እና 4 ይዘን ልናስደምጣቹ ተዘጋጅተናል::የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባዬ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጸጋዬ አላምረው ከስደት ካሉበት ያሳለፉትን የፖለቲካ ሕይወት እና የአንድነት ፓርቲን በተመለከተ ያደረጉት ቃለመጥይቅ በዚህ ፕሮግራም ይቀርባል:: ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ

በዚህም መሰረት ዛሬ ወይም ነገ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ይዛወራሉ ገዢው ፓርቲ እነወይንሸትን ለምን በእስር እንዲቆዩ እንደፈለገ ሀቅ ነው እነወይንሸት ከታሰሩ ምርጫውን ሲያጭበረብር ለምን የሚል ትውልድ በከተማው ሊኖር አይገባም የወይንሸትን ጥንካሬ ደግሞ ገዢዎቻችን ጭምር ያውቁታል ወይንሸት ብቻዋን ከማንም በላይ የምርጫን ውጤት መወሰን የምትችል የዘመናችን ጅግና ነች ወይንሸትን ከዚህ በፊት የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት የምትፈልጊውን ሀገር ቪዛ […]

ዶክተር መስፍን አርአያ ይባላሉ። የታወቁ የፖለቲካ ሳይንቲስት እንደነበሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። በኒው ዮርክ ሃንተር ኮሌጅ ለብዙ አመታት አስተምረዋል ። አሜሪካዊት አይሁድ አግብተው የሁለት ልጆች አባትም ነበሩ። ። ከኤርትራ ወላጆች የሚወለዱት ዶክተር መስፍን የኢህአፓ አባል በመሆን አብዛኛውን ዕድሜያቸውን በትግል እንዳሳለፉ ይነገራል። አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ እንግሊዘኛ እና የደች ቋንቋ ይናገሩ እንደነበርም ታሪካቸው ያሳያል። ከዚህ ሁሉ አመት አገልግሎትና […]

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላ እና በደቡብ ክልል አዋሳኝ ከተሞች የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ እየተበላሸ መሄዱን ተከትሎ  ዜጎች እየተፈናቀሉና እየተገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከሁለት ቀን በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በጎደሬ ወረዳ በየሪ ቀበሌ በፈጸሙት ጥቃት 6 ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሰው ደግሞ በጽኑ ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷል። ሌሎች ወገኖች ደግሞ የማቾች ቁጥር 7 …

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅማ ዩኒቨርስቲ ሰሞኑ በተደረገ አውደጥናት ላይ ፣ በየዓመቱ በየጊዜው የሚቀያየረው የትምህርት ፖሊሲ  ርእይ ያለው ወጣት እንዳይፈጠር ማድረጉ ተገልጿል ፡፡ ሀገሪቱ  ወጥ የሆነ የትምህርት ፖሊሲ ይዛ ባለመማራቷ ችግሩ መፈጠሩንም ምሁራን ተናግረዋል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ማምጣት የቻሉ ብዙ ተማሪዎች በምደባ  ከፍላጐታቸው የራቀ ትምህርት እንዲያጠኑ …

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ ላይ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል  ስድስትወርእንደተፈረደበት ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጋዜጣው እንደሚለው ግንቦት 3/2007 ዓ.ምቄራየመጀመሪያ ፍርድቤት የቀረበው አቶ ስንታየሁ ፖሊስ በሰልፉ ወቅት ድንጋይ ወርወሯል በሚል በቀረበበትክስ  የስድስት ወር እስር ተፈርዶበታል፡፡ አቶስንታየሁመቃወሚያና …

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በሲሚንቶ እጥረት ግንባታዎች እንዲቋረጡ መደረጉን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችና በግንባታ ላይ የሚገኙ የህብረተሰቡ ክፍሎች ለዘጋቢያችን አስታውቀዋል፡፡ ችግሩ የህወሃቱ ንብረት በሆነው መሰቦ ስሚንቶና የሼክ አላሙዲን ንብረት በሆነው ደርባን ስሚንቶ መካከል ባለው ውዝግብ የተፈጠረ ነው ይላሉ ነጋዴዎች።  በዚህም የተነሳ ህብረተሰቡ ለአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ከ80 እስከ 100 …

በጋምቤላ ክልል፣ መጃንግ ዞን፣ ጎደሬ ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች በመንግስት በተቀነባበረ ሴራ ጭፍጨፋ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለይ ከግንቦት 2006 ዓ.ም ጀምሮ 400 ያህል ነዋሪዎች እንደተገደሉ የገለጹት ነዋሪዎች መንግስት የእርስ በእርስ ግጭት ለማስመሰል ቢሞክርም ችግሩ በመንግስት የተቀነባበረ እንደሆነ እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የአብዛኛዎቹ ነዋሪዎች እርሻ ለገዥው ፓርቲው ካድሬዎች በመስጠት እኛ ከቦታችን እንድንፈናቀል ጥረዋል፡፡ አንወጣም ስንል ግን በግድ […]

(በዳንኤል አማረ)

ሁላችንም አጥቢ እንሰሳ እንደመሆናችን መጠን በሰውነት ፀጉር የታደልን ነን በተጨማሪም ሶስት የመሀል ጆሮ አጥንት አለን። የወለድናቸውን ልጆች ሴቶች ተፈጥሮ በቸረቻቸው የማማሪ ግላንድ አማካኝነት ጡት በማጥባት እንመግባቸዋለን።

ሁላችንም (ወንድና ሴት) ገና በጽንስ ውስጥ እያለን በተመሳሳይ የዕድገት መንገድ…

(በዳንኤል አማረ)

ትርፍ አንጀት ከትልቁ አንጀታችን ስር ተያይዞ የሚገኝ ተቀጥላ የሰውነት ክፍል ነው። የትርፍ አንጀት ግድግዳ ነጭ የደም ህዋስ የሚሸከመውን ፈሳሽ አካል(Lymph) ይይዛል። ይህ ባክቴሪያ ተከላካይ(አንቲቦዲ) ለመስራት የሚያያገለግል የሰውነታችን በሽታ የመከላከያ ዘዴ አንድ ክፍል ነው።

የትርፍ…

ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን የሽብር ድርጊት ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳትና በመሳተፍ›› ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሚያዝያ 30/2007 ዓ.ም ጠዋት በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው የ6000 ብር የሰው ዋስትና ተፈቅዶላቸው የነበር ቢሆንም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ በእስር ላይ እንዳቆያቸው ይታወቃል፡፡ የፍርድ ቤቱን […]

ሚያዚያ 11/2007ዓ.ም ዳና ድራማ ከኢቢሲ ጋር የነበረው ኮንትራት ተጠናቋል፡፡ በቀጣይም ኢቢሲ የውል ስምምነቱን አላደሰም፡፡ ባለፈው ሳምንት በቀጥታ ስርጭት ምክንያት ድራማው አልተላለፈም፡፡ ነገር ግን የቀጥታ ስርጭቱ ባይኖርም ኢስት አፍሪካ ፊልም ፕሮዳክሽን ድራማውን ለኢቢሲ አላመጣም ነበር፡፡ ሙሉ መረጃውን ይከታተሉ አሰግድ ታመነ Filed under: Uncategorized

ግለሰቡ የ 7 ወር ነብሰ ጡር የሆነችውን ወጣት ሚስጥሬን አወጣሽ በሚል አስገድዶ ከደፈረ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏታል፡፡ ሙሉ የፖሊስን ዘገባ ይከታተሉ posted by Aseged TameneFiled under: NEWS

  ሻለቃ ፅጌ ትባላለች፤ (አሁን ኰሎኔል) ..የጄ/ል ሰዓረ መኮንን ባለቤት ናት። ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 1997ዓ.ም ምሽት ኢህአዴግ ምርጫውን አስመልክቶ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ጠርቶ ነበር። ሻለቃ ፅጌ ከጠባቂዋ ደህንነት ጋር በስፍራው ተገኝታ ሻማዋን እያበራች በጦር ሃይሎች ሆ/ል በር በኩል ታልፋለች። በሆስፒታሉ በር ከቆመው ጠባቂ ዘብ ጋር አብራ የምታወራ የሆ/ ሉ ሜንስ ቤት ሰራተኛ እያፌዘች «ስሚ […]

ሪፖርተር እንዳስነበበን የሰማያዊዎቹ በጀት ኢህአዴግን ጭንቀት ላይ ጥሎታል። ዋ….አይ ከየታባታቸው አመጡት፤ ብለው ግራ ግብት ያላቸው አቶ ሬድዋን ”ኮንሰርት አላዘጋጁ፣ ቱጃሮች አይደሉ፣ ልማታዊ ባለሃብቶች አልደገፏቸው” ሲሉ ጭንቀታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል። አቶ ሬድዋን ተጨንቀውም አላባሩ ይሄንን ጉዳይ የሚመለከተው አካል እንዲመርምር አዘናል አይነትም ብለዋል። (እኛ ግን እነርሱ ሃያ ሶስት ሚሊዮን ሲያወጡ የአባይን መዋጮ ለቅስቀሳ አዞሩት እንዴ ብለን አልመረመርንም!) የሰማያዊ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ሀገሪቱ በቅርብ ጊዜያት በተነሳ የውጪ ዜጎችን ኢላማ ባደረገ ተቃውሞና ጥቃት ስትታመስ ቆይታለች “አፍሮ ፎቢያ” ተብሎ እስኪሰደብ ድረስ በዛ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ስደተኞች በዚሁ ዜኖ ፎብያ በተባለ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውም የሚዘነጋ አይደለም አሁን ደግሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በህገ ወጥ መንገድ ወደሀገሪቱ ገብተዋል ያሏቸውን የውጪ ዜጎች ማደንና ማሰር እንደጀመሩ ነው የተነገረው ደቡብ […]

(ያሬድ ሹመቴ)

አያልቅበት ስንታየሁ ሱዳን ውስጥ ለ3 ዓመት ያህል የኖረ የብርሀኑ ጌታነህ ወዳጅ ነው። የሚናፍቃቸውን እና ያላባት ብቻቸውን ያሳደጉትን፤ ለስደቱ ምክንያት የሆኑትን እናቱን ለማየት የዛሬ ዓመት ገደማ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።

ሱዳን በነበረበት ወቅት ከራሱ ተርፎ እናቱን ለመርዳት የሚልካት ጥቂት ገንዘብ በስተርጅናቸው ሰው ቤት ተቀጥረው የጉልበት ስራ ከመስራት አላዳናቸውም።

ወይዘሮ አለሚቱ በላይነህ ልጃቸው ሱዳን ሳለ የሚልክላቸው ገንዘብ ከቤት ክራይ ክፍያ ውጪ የማይሸፍንላቸው ቢሆንም፤ ችግራቸውን ለልጃቸው ነግረው ከማሳቀቅ፤ በስተርጅናቸው የጉልበት ስራ ውስጥ ገብተው ኑሮዋቸውን በመከራ ተያይዘው ቆዪ።


የእናቱ ነገር የማይሆንለት አያልቅበት፤ በናፍቆቱ ምክንያት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ግን ሱዳን እያለ ይልክ የነበረው ገንዘብ ምን ያህል የእናቱን ህይወት ፈቅ ማድረግ እንደተሳነው ተረዳ።
የዚያን ጊዜ ታድያ ከሱዳን አድማስ ማዶ፤ እናቱን ለመጦር ይችልበት ዘንድ ተስፋ የጣለበትን የባህር ላይ ጉዞ ህልም ሰነቀ።

ለልጆቹ ህይወት በእጅጉ ከሚጨነቀው የረዥም ጊዜ ወዳጁ ብርሀኑ ጌታሁን ጋርም ሀሳባቸው ገጠመ። ወደ ሊቢያም በጋራ ሊሻገሩ ተቃጠሩ። ልጆችን ለማሳደግና እናትን ለመጦር።
አያልቅበት በሀምሌ 5፣ 2007 ዓ.ም ወደ ሱዳን ለመመለስ በሚሸኝበት ጊዜ፤ ከዚህ ቀደም በሰላም ደርሶ የተመለሰው ልጃቸው ተመልሶ የሚመጣው መርዶው መሆኑን ፈፅሞውኑ ባይገቱም ካይናቸው ልጃቸው ከሚርቅ በርሀብ ቀድመውት ቢሞቱ መርጠው ነበር።

የብርሀኑ እና አያልቅበት ቀጠሮ ቀን ሲደርስ፤ ብርሀኑ ሚስቱን “ድሬዳዋ ለስራ መሄዴ ነው፤ ስልኬ ግን አይሰራም” ብሎ ሀገሩን ለቆ ወደ ሱዳን አመራ።

በተቀጣጠሩ በስድስት ወራቸው ሱዳን ላይ የተገናኙት እኒህ የልብ ወዳጆች፤ አንዳቸው ስለ ልጅ አንዳቸው ስለ እናት ፍቅር ምስክር ሆነው። ልጆቹን ለናታቸው አደራ ሰጥቶ የተሰደደው፤ ለእናት የሚሰጥ ፍቅር ሀያልነት በአያልቅበት ሲማር፤ ለልጆቹ ሲል የተሰደደው ብርሀኑ ደግሞ በተራው የአባት ፍቅር ምሳሌው ነበር።

ወይዘሮ አለሚቱ፤ አያልቅበት ከሄደ በጝላም ቢሆን የዘወትር ፀሎታቸው የሚወዱት ልጃቸው መንከራተት በቅቶት ከእቅፋቸው ዳግም እንዲገባ ነበር።

የሀገራችን ሰማይ ጠቁሮ፤ ኢትዮጵያም አምርራ በልጆችዎ የግፍ ሞት ስታለቅስ፤ እንደ ብርሀኑ ባለቤት ብርቱካን እና መላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአያልቅበት እናትም እንባቸውን ይዘረግፉት ነበር። ሊቢያ የማን ሀገር ጎረቤት እንደሆነች እንክዋን የማያውቁት እናት እንዲሁ በደፈናው ልጆቼ ለሚልዋቸው የኢትዮጵያ ሰማዕታት ሁሉ ያነቡ ነበር።

ከሚወደው ወዳጁ ብርሀኑ ጎን በሊቢያ በርሀ አንገቱን ለሰይፍ የሰጠው አያልቅበት ሰማዕትነቱ የተሰማው ዘግይቶ የሁሉም ቤት ሀዘን በመብረድ ላይ ሳለ ነበር።

የእኒህን እናት አይን ለማየት በውነቱ ማን ይደፍር ይሆን? የሀዘናቸውንስ ጥልቀት ምን ይገልፀው ይሆን? በምንስ አይነት መንገድ….?

ዛሬም ቢሆን ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቶአል። ገርጂ ከጊዮርጊስ ቤ.ክርስቲያን ጀርባ በምትገኘው ሰማዕቱ ልጃቸው በተከራየላቸው ጠባብ ቤት ውስጥ፤ በብቸኝነት ተኮራምተው፤ አንድያ ልጃቸው ተመልሶ እንደማያዪት ከተረዱ ሳምንት ሳይሞላቸው ያለ አስተዛዛኝ ብቻቸውን የተቀመጡት እናት፤ የሚያነጋግራቸው ዘመድ፣ ሲቦርቁ እያዪ የሚፅናኑባቸው ህፃናት የሌሉበት ጠባብ ቤት ያለመጠን ሰፍቶ ፍርሀት ሲያነግስባቸው፤ ቤታቸው የተሰቀለው ልጃቸውን ከነገዳዩ የሚያሳይ ምስል እያባነነ እንቅልፍ ሲከለክላቸው፤ ይህንን ሁሉ እየሰማን እና ይህን ሁሉ እያየን ዝም የምንል መሆናችን ያሳፍራል። (በእርግጥ ለህዝቡ ማን ነገረው? የመንግስት ሚድያዎች በሌሎች ጉዳዮች ተጠምደዋል።

ሀላፊነታቸውን በብርቱ ይወጡ የነበሩ ጋዜጦች እና መጵሄቶች ዛሬ በስራ ላይ የሉም) ዛሬስ እኔም እፍረት በዝቶብኝ አንቆ ሊደፋኝ ደርሶዋል።

አያልቅበት እኮ “የሞተው ሁላችንንም ተክቶ ነው። እሱ እኮ አንገቱን የደፋው የናቱን አንገት ቀና ሊያደርግ ነው።”

በኢትዮጵያ አምላክ እለምናለው አዛውንት እናትና ህፃናት ልጆች አንድ ናቸው። ስደቱም የመጣው ለማሳደግና ለመጦር ነው። እኚህን እናት አጠገባቸው ሄደን እናጽናናቸው። ቀሪ ህይወታቸውንም ወድቀው እንዳይቀሩ እንደግፋቸው።

የሰማዕቱ አያልቅበት ድምጽ ግን ይሰማል። ብቸኛዋን “እናቴን አደራ”።

ለሰማዕቱ አያልቅበት ነፍስ ይማርልን!! እንፀድቅባቸው ዘንድ እናቱንም ትቶልን ከሱ ሰማዕትነት
በረከት እንድንሳተፍ እነሆ “እናቴን አደራ” ይለናል።

ከቻሉ በአካል ተገኝተው እናታችንን ያፅናኑ፤ ካልቻሉ ይህን መልዕክት share በማድረግ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች መሆናችንን (እንግለጥ።)

አሁንም በድጋሚ እናገራለው። ከብዙ ቃል መግባት ጥቂት ቃልን መፈፀም ዋጋው የላቀ ነው። እግዚአብሔር ይርዳን!!

ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመሻር ዋስትና የከለከላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እየወሰደ እየመረመረ ነው፡፡ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ትናንት ሚያዝያ 30/2007 ዓ.ም ጠዋት በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው የ6000 ብር የሰው ዋስትና እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመሻር በእስር […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ኦህዴድ/ኢህአዴግ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ መጠመዱ ተነገረ የወያኔ /ህወሃት ካድሬዎች እርስ በራሳቸው እንደማይተማመኑ ተገለፀ በሁመራ አከባቢ ህወሀት እስከአሁን ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል የአሜሪካ ም/የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዌንዲ ሸርማን አዲስ አበባ የተናገሩትን አስተባበሉ ወያኔ ከአቶ አንዳርጋቸው የረባ መረጃ ለማግኘት ባለመቻሉ የስነ ልቦና ጫና በማሳረፍና ህክምና በመከልከል ለመጉዳት ማሳቡን ምንጮች ገለፁ    የኖርዌይ አንባሳደር በኢትዮጵያ ዜጎቻቸውን አስጠነቀቁ የኖርዌይ ኢንባሲ በኢትዮጵያ […]

የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊብያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን። እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በእንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት። መቼም ሼም የሚባል ነገር ከነሱ ዘንድ ጠፍቷል። በስራቸው ማፈር ሲገባቸው አይናቸውን […]

  በታይላንድ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ የሆኑት ዶ / ር ዮናስ ተገኝ የቤት ሰራተኛ የነበረችው አኔት የተባለች የቤት ሰራተኛ በደል ደርሶብኛል ብላለች ባንግኮክ የተሰኘው የዜና ምንጭ እንዳስነበበው ሰራተኛዋ በዶ / ር ዮናስ ቤት ውስጥ ልክ እንደባሪያ ሲያስተዳድሯት እንደነበር ትናገራለች ለአመታት ያህል ወርሀዊ ደመወዟ ሳይከፈላት እንደቆየም ተነግሯል ገንዘብ የማድረስ ስራ የፖሊስ እንዳልሆነ ተገልፆ 89 ሺ የታይላንድ […]

ኢሳት ዜና ፦ ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ «ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ተስተናጋጅ ባለጉዳይ ሽጉጥን ጨምሮ የትኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው እንዳይገቡ፣ የመስሪያ ቤት […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ ” ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ተስተናጋጅ ባለጉዳይ” ሽጉጥን ጨምሮ የትኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው እንዳይገቡ፣ የመስሪያ ቤት ጠባቂዎች ጥብቅ ፍተሻና …

በሃገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ የዶላር እጥረት አስመጪና ላኪዎችን ማማረሩን ዘጋቢያችን ምንጮቹች ዋቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ የላከው ዜና ያመለክታል። የቡና ኤክስፖርት ከቆመ ወራት ተቆጥረዋል፣ በሃገሪቱ ያሉ ባንኮች ዶላር ሽያጭ አቁመዋል የሚለው ዘጋቢያችን፣ ከዲያስፖራው የሚገኘውን የውጭ ዶላር ገቢ ለማሳደግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አዘጋጅቷል ብለአል። በአስመጪና ላኪ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ዶላር ማገኘት ያልቻሉበት መንገድ አልተገለጸላቸውም። ይሁን እንጅ የቡና …

በተራዘመ የፍርድ ሄደት የሚሰቃዩት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ፣ የመጨረሻ ብይን ሚያዚያ 30 እንደሚሰጥ አስቀድሞ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ የብይኑ ቀን እንደገና ተራዝሟል። የመራዘሙ ዜና አስቀድሞ በኢሳትና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተዘገበ በመሆኑ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስገራሚ አላደረገውም። አገሪቱን የሚመራት የደህንነት መስሪያ ቤት ከምርጫው በፊት ምንም አይነት ውሳኔ እንዳይሰጥ ትእዛዝ አስተላልፎአል። በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ …

በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የኢህአዴግ ካድሬዎች እያደረጉት ያለውን የምርጫ ቅስቀሳና የካርድ እደላ የታዘበው ዘጋቢያችን የምርጫው ሂደት አስቂኝ ሆኗል ብሎአል። በከምሴ፣ ደብረብርሃን፣ ደብደረማርቆስና ሌሎችም ቦታዎች ካርድ ያለወጡ ሰዎች ኢህአዴግን እንደሚመርጡ ካርድ እየተሰጣቸው ነው። በአንድ ለአምስት፣ በአንድ ለአስር እንዲሁም በቡና ጠጡ መስተንግዶ ዜጎች በቡድን እንዲመርጡ እየተደራጁ ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በዩኒቨርስቲዎች የቅስቀሳና የማደራጀት ስራ እየሰሩ ነው። ወሎ፣ ድብረብርሃን፣ ጅማና …

በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ፣ አምና በሚያዚያ ወር ከ79 በላይ የኦሮሞ ወጣቶች በአምቦና አካባቢዋ ከተገደሉ በሁዋላ፣ ባለፉት 10 ቀናት ደግሞ 50 የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መያዛቸውን ገልጿል፤፡ ከ20 በላይ ወጣቶች በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸው በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ። ድርጅቱ ባሰባሰበው መረጃ በእስር ላይ የሚገኙ 20 ተማሪዎችን ስም ይፋ አድርጓል። ወጣቶቹ …

ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ በጣለው ድንገተኛ ዝናብ፣ እስካሁን ባለው መረጃ 9 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል። ሟቾቹ ለገሃሪ እንደገበሬ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። የ9 ሰዎች አስከሬን ተፈልጎ መገኘቱን ምንጮች ገልጸዋል። ድሬዳዋ ከዚህ ቀደም በደረሰ ጎርፍ በርካታ ነዋሪዎቿን ማጣቷ ይታወቃል።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሳውድ አረቢያዊ የሆኑት ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን በሸራተን አዲስ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ በስፍራው የተገኙትን የመንግስት ጋዜጠኞችና አንዳንድ የግል ሚዲያ ሃላፊዎችን ወቅሰዋል። ሼክ አላሙዲን በአሜሪካና በአውሮፓ የደሀ መሬት እየወሰዱ ነው እያሉ ስማችንን የሚያጠፉ ስራፈት ሚዲያዎች አሉ ያሉ ሲሆን፣ እናንተም የተባለው ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብላችሁ፣ መርምራችሁ ለህዝቡ ማቅረብ ነበረባችሁ በማለት ለዘገባ የተላኩ …

በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በማካሄድ ላይ ባለው 56ኛው አፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና ህዝቦች መብቶች መደበኛ ጉባኤ ላይ ፣ አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት የተባለው ተቋም ባቀረበው ጽሁፍ ፣ ነጻነትን በማፈን የአለም ሻምፒዮን ከሆኑ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዳ መሆኗን ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚባለውና የሚደረገው የተለያየ ነው የሚለው ድርጅቱ ፣ የአገሪቱ ህዝብ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃንን እንዳያገኝ መታፈኑን ገልጿል። በአገሪቱ አስገድዶ …

ይህ የምርጫ ማኒፌስቶም ሀገሪቱ አሁን ካለችበት የኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚደረግ ሽግግር ወቅት በሀገራችን ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድሮ ማሸነፍ ቢችል የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር የሚተነትን ነው፡፡ ይህ የምርጫ ማኒፌስቶ በዋናነት በሦስት ምዕራፍ የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው የፖለቲካ ሥርዓቱ አደረጃጀት ምን መምሰል እንዳለበት የሚገልፅ ክፍል ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ሰማየዊ ፓርቲ ባለፉት 24 ዓመታት የህወሀት/ኢህአዴግ መራሹ ሥርዓት በሀገራችን ላይ የፈፀማቸውን የተሣሣቱ የፖለቲካ ሂደቶች በዝርዝር የሚያስቃኝ ሲሆን፤ በአንፃሩም ፓርቲው በሥልጣን ላይ ቢቀመጥ በዋነኛነት በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን የፌደራል ሥርዓት በመቀየር መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈርንና፣ ልማትና ሌሎች ማህበራዊ ትስስሮችን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡ በመንግሥት አወቃቀሩ፣ በነፃ-ፕሬስ፣ በመከላከያ ፖሊስና ደህንነቱ አወቃቀር እንዲሁም የውጭ ግንኙነት አማራጭ ፓሊሲውም በዝርዝር በማኒፌስቶው ላይ የተቀመጡ አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡

በሁለተኛዉ ምዕራፍ የማህበራዊ ሥርዓቱን በተመለከተ የተዘረዘሩ ነጥቦችን የያዘ ሲሆን ህወሃት /ኢህአዴግ በሀገራችን ሕዝብ ላይ በማህበራዊ ዕድገቱ ላይ ያስከተለውን ሁለንተናዊ ቀውሰ በማስቃኘት፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሠረታዊ የማህበራዊ ጉዳይ ፍልስፍና የሆነውን ጤነኛና በእውቀት ላይ የተመሠረተ በራሱ የሚተማመን ዜጋን ለመፍጠር ዋነኛ ምሰሶ የሆነውን ትምህርትና ጤና ላይ ያለውን ፖሊሲ በማስቃኘት ጀምሮ በማኅበረሰቡ ውስጥ በዕድሜያቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የዕድሜ አንጋፋዎችና በተፈጥሮና በአደጋ አካላቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰቡ ክፍሎች የሚሰጠውን ድጋፍ ይተነትናል፡፡ በተጨማሪም ሰማያዊ ፓርቲ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ፣ ስፖርት እና መሰል ማኅበራዊ ጉዳዮች የሚመለከትባቸውን እይታዎች ያስቃኛል፡፡

በመጨረሻም በዚህ ማኒፌስቶ በጥልቀት የተገለፀው የፓርቲውን የኢኮኖሚ አማራጭ የሚያሣየው ምዕራፍ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የህወሃት/ኢህአዴግ ሥርዓት እከተለዋለሁ የሚለውን ገጠርን ማዕከል ያደረገ ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በማስቀድም ልማት የሀገሪቱ መሠረታዊ ጥያቄ ስለሆነ በሚል ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ቅንጦት እንደሆነ በመቁጠር ሁሉ ነገራችንን ለልማት በሚል ሰበብ በሀገራችን ኢኮኖሚ ለውጥና ዕድገት ላይ የፈጠረውን ደንቃራ በጥልቀት ይመረምራል፣ ትችቱንም ያቀርባል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ በሕዝብ ተመርጦ የመንግሥትነት ሥልጣኑን ቢይዝ፤ በሀገሪቱ ውስጥ የሚያሰፍነውን የኢኮኖሚ መርህ ያሳያል፡፡ በዚህም መሠረት ሰማያዊ በሀገራችን ተግባራዊ ለማድረግ ያቀዳቸዉን የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማራጮች በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን በዋነኝነትም የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በተመለከተ አርሶ አደሩን የመሬቱ ባለቤት የሚሆንበትን መብት ማረጋገጥ፤ እንዲሁም ሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች የትኩረት አቅጣጫ ገበያ መር ሆኖ ዜጎች በፈለጉት ሙያ እና የሥራ መስክ ተሰማርተው፣ ሀብት የማፍራት፣ በሕጋዊ መንገድ የንብረት ባለቤት የሚሆኑበት በተጨማሪም በሀገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች ተሰማርተው የሚሠሩበትን መብት የሚያረጋግጥ እንዲሆን የሚረዳ የፖሊሲ አማራጩን አስቀምጧል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ሚያዝያ 29/2007 ዓ.ም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ ምርጫ ቦርድ በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣ ጠይቋል፡፡ የተሻሻለውን የምርጫ ህግ 532/1999 ዓ.ም አንቀፅ 58 ቁጥር 1 ላይ ‹‹አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ መታወቂያ ካገኘበት ቀን አንስቶ ምርጫው ሁለት ቀን እስኪቀረው ድረስ ከአስተዳደሩ ሆነ ከማዘጋጃ ቤት ፈቃድ ሳይጠይቅ በፅሁፍ በማሳወቅ ብቻ የድጋፍ ስብሰባዎች አሊያም ሰላማዊ ሰልፎችን የመጥራት […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዐት ጀምሮ ለአራት ቀናት ያካሔደውን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ኹለተኛ ዓመታዊ ቀኖናዊ ጉባኤ ሲያጠናቀቅ ባወጣው ባለዐሥራ አንድ ነጥቦች መግለጫው÷ በሊቢያ ራሱን እስላማዊ መንግሥት(ዳኢሽ) እያለ የሚጠራው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን ስለ ክርስቲያንነታቸው በግፍ እና በአሠቃቂ አኳኋን የገደላቸውን ኢትዮጵያውያን እና ግብጻውያን ኦርቶዶክሳውያን የሰማዕትነት ሥያሜ …

  ባለፈው ቅዳሜ ከወልቂጤ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው አነስተኛዋ የዳርጌ ከተማ በፖሊሶች እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የተነሳው ግጭት ይህንን ዜና እስከፃፍኩበት ድረስ የቀጠለ ሲሆን በርካቶች ከተማዋን በመልቀቅ ወደወልቂጤ እና ወሊሶ ከተሞች በመሠደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአካባቢው ከሚኖር ግለሠብ ለማጣራት እንደሞከርኩት ግጭቱ የተቀሰቀሰው ቅዳሜ በ24/08/2007 ዓ.ም አንድ በአካባቢው በስራ ላይ የተሠማራ ፖሊስ በግብርና የሚተዳደር ግለሠብን በአጋጣሚ በተነሳ […]

የዙሉ አክራሪዎች በኢትዮጵያዉያን እና ሌሎች የአፍሪካ ዜጎችን ላይ ኢሰብዓዊ ጥቃት በሚፈጽሙበት ጊዜ፣ እንደ ናይጄሪያ ያሉ አገሮች በዙማ መንግስት ላይ ጠንካራ አቋም ወሰዱ። ዙማ ተጽኖ ሲበረታባቸው፣ አስቸኳይ እርምጃዎች ለመዉሰድና ነገሮችን ለማረጋጋት ተገደዱ። ከነናይጄሪያ በደረሰው ግፊትና ጫና በደቡብ አፍሪካ ያለው ሁኔታ ለጊዜውም ቢሆን መረጋጋት ታየበት። በዚሁ ሁሉ ግን ሕወሃት/ኢሕአዴጎች የተከሰተዉን ቀውስ አሳንሰው በማቅረብ፣ ለኢትዮጵያዉያን ጥብቅና የቆሙ ሳይሆን፣ […]

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ከአሁኑ እንደጀመረው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎች መራጮችን በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ እያደራጁ ‹‹ኦህዴድ/ኢህአዴግን መርጫለሁ›› በሚል እያስፈረሙና ፎርም እያስሞሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ ተደራጅተው ‹‹ኦህዴድን መርጠናል›› ብለው እንዲፈርሙ የተደረጉ ዜጎች ፎርሙን ከሞሉበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ መሪዎቻቸው እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ […]

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች ህዝብ አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ የማደናገርያ ቃል እየገቡለት መሆናቸውን ተገለፀ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው- የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘውን ህዝብ በማዳበሪያ እዳ ተማርሮ እንደሚገኝ አስቀድመው ስለተረዱ ሱሪያችሁን በጭንቅላታችሁ አውጡ አይነት አስገዳች መመሪያ በመስጠት እያስጨነቁት እንዳልቆዩ አሁን ላይ ደርሰው ከህብረተሰቡ በርካታ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው የወሰዳችሁትን […]