ገዥው ፓርቲ ኦሮሚያ ውስጥ ምርጫውን ጀምሮታል ተባለ
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ከአሁኑ እንደጀመረው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎች መራጮችን በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ እያደራጁ ‹‹ኦህዴድ/ኢህአዴግን መርጫለሁ›› በሚል እያስፈረሙና ፎርም እያስሞሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ ተደራጅተው ‹‹ኦህዴድን መርጠናል›› ብለው እንዲፈርሙ የተደረጉ ዜጎች ፎርሙን ከሞሉበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ መሪዎቻቸው እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ […]![]()