የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከፓርቲ ፖለቲካ መራቅ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በእንግሊዝኛው ምህጻሩ UDJ ሊቀመንበርነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ።
ሊቀመንበርነታቸውን ብቻም ሳይሆን ከUDJ አባልነትም የተሰናበቱት ዶ/ር ነጋሶ ከዚህ በኃላ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አልሳተፍም ብለዋል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በእንግሊዝኛው ምህጻሩ UDJ ሊቀመንበርነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ።
ሊቀመንበርነታቸውን ብቻም ሳይሆን ከUDJ አባልነትም የተሰናበቱት ዶ/ር ነጋሶ ከዚህ በኃላ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አልሳተፍም ብለዋል።
ግብፆች ሕይወት፥ ደም አካላቸዉን መስዋዕት ያደረጉበት አብዮት የምክር ቤት እንደራሴዎቻቸዉን፥ ለመጀመሪያ ጊዜ በነፃ እንዲመርጡ አስችሏቸዋል።ፕሬዝዳታቸዉንም እንደዚሑ።ሕገ-መንግሥትም አፅድደቀዋል።ዳር ግን አልዘለቀም።ከ1952 ጀምሮ የግብፅን የሚቆጣጠረዉ ጦር ሐይል የግብፅ ሠላማዊ ሕዝብ ፍላጎትና ምኞት እንዲሳካ ሥልጣኑን መልቀቅ አልፈቀደም።
የዓለም ዜና
ጃኑዋሩ 22 ቀን 33ኛ አመቷን ታከብራለች። በሃይ ስኩል የእንግሊዘኛ አስተማሪ ነበረች። በሕገ መንግስቱ ላይ የተደነገገዉን መብት በመጠቀም፣ በተለያዩ አገር ውስጥ በሚታተሙ ሜዲያዎች ትጽፋለች። «እነርሱ እንዲጻፍ ከሚፈልጉት ዉጭ እንዲጻፍ የማይፈልጉት ባለስልጣናት፣ የሃሰት ክስ መሰርተዉ፣ ዳኛ ለተብዬዎች መመሪያ ሰጠዉ፣ መሰረተ ልማቶችን ለማፍረስ አሴራለች፣ ሽብርተኛ ናት» ብለዉ ፈረዱባት። ይች ሴት ርዮት አለሙ ትባላለች። ጡቷ አካባቢ ችግር ስላለበት ክትትል […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በሱዳን፣ ግብጽና ኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረዉ የሶስትዮች ንግግር መበተኑን አስመልክቶ ፣ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት እንዲሁም የፓርላማ አባል፣ የግብጽን አቋም «የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቅ» እንደሆነ በመግልጽ፣ መንግስት የወሰደዉን አቋም ደገፉ። በአባይ ግድብ ዙሪያ እንኳን የተቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓርላማ አባል የሆኑት እርሳቸዉም በቂ መረጃ እንደሌላቸዉ የገለጹት አቶ ግርማ፣ «የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከዚህ አንፃር በጭፍን የአባይን ግድብ እንዲደግፉ እንጂ […]
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም። የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። […]
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
ምንሊክ ሳልሳዊ አገር በኔ ብቻ ተመርታ አገር አትሆንም ብሎ፤ ኃይለኛውና አሸናፊው ከወጣበት መሠላል ዝቅ ብሎ፤ ግማሽ መንገድ ወርዶ እንነጋገር፣ እንወያይ የማለት ባህል፤ ተሸናፊውም ከቁጭቱ፣ ከቂሙ፣ ለመጣል እንጂ አብሮ ለመቀመጥ አልፈልግም የሚልበትን ግትር አቋም ትቶ፤ እኔም የሀገር ጉዳይ ያገባኛል፣ “እንድትሰፉ እንጂ እንደትጠፉ አልፈልግም” ብሎ፤ መንገድ መሻት ያሻዋል፡፡
ቤት ንብረት በሀራጅ ከሚያስሸጥ ድህነት ይሰውረን፡፡ በሎተሪ ከሚያሳምን የገጠመኝ ዘመን ያውጣን፡ ከሁሉም በላይ ግን ለመለመን እንኳ ጥቂት የራስ መንቀሳቀስ እንደሚያሻን መገንዘቢያ የሚሆነን ልብ ይስጠን!!በሀገራችን ከድህነት እኩል የሚፈታተነን ችግር፤ ቢያንስ ግማሽ መንገድ እንኳ ሄዶ ለመደራደር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን አሊያም ቀና ልቡናውን ማጣታችን ነው፡፡ ግማሽ መንገድና የመቻቻል፣ ልዩነትን የማስተናገድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመልመድ ትልቅ ፀጋ ነው፡፡
የኋላ ታሪክ የሌለው የሚያውቀው ዛሬን ብቻ ነው፡፡የአንድ ቀን ታሪክ የሌለው የሚያውቀው ዛሬን ብቻ ነው፡፡ አንድ ቀን ባዶነት መሰማቱ አይቀርም፡፡ ከሌላ አካል ተከፍሎ መፈጠር ዕድሜ ልክ ሙሉነት ሳይሰማን እንድንኖር ማድረጉ አሌ አይባልም፡፡ ራስን ችሎ፤ በራስ ተማምኖ ለመኖር ራስን ሆኖ መፈጠርን ይጠይቃል፡፡በሀገራችን በፖለቲካ መከፋፈል እንጂ ተስማምቶ መጓዝ አይሆንልንም፡፡ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ እንደባህል የተያዘ ፈሊጥ ነው፡፡
አይጥና ድመት የታረቁ ለታ ባለግሮሰሪው/ባለንብረቱ ወዮለት! አይጥና ድመት እንኳ ታርቀው ጠላታቸውን የሚያጠቁበት ቀን ይመጣል ነው የሚሉን፡፡ “የማይለወጥ ነገር የለም – ከለውጥ ህግ በስተቀር” ታሪካችንን ወደኋላ ብንመረምር ምን ያህል እንደተለወጥን ወይም እንደተለዋወጥን መገንዘብ ቀላል ነው፡፡
ስለተሰሩ መንገዶች፣ ስለፈረሱ ቤቶችና ስለተሠሩ ህንፃዎች፣ ስለታሰሩ ሰዎችና ስለተፈቱ ሰዎች፤ ስለተፃፉ ደንቦችና ስለተጣሱ ህጐች፤ ስለማይሸጡ መሬቶችና በሊዝ ስለተወሰዱ መሬቶች፤ ስለማይነኩ ሰዎችና ኋላ ስለተወረወሩ ሰዎች፡፡ ለውጥ አይቀሬ ነው፡፡ ህገመንግስቱን እንኳን “የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም ሰው ነው የፈጠረው ሰው ይለውጠዋል፡፡” ብለው ነበር የቀድሞው መሪ፡፡ የብሔር ብሔረሰብ አካሄዳችንም ወደ ኢንዱስትሪ ልማት የሚሸጋገርበት ቀን ሊመጣ ይችላል፡፡
“ዘለዓለም ውሻ ሆኖ ከመኖር አንድ ቀን አንበሳ ሆኖ መሞት” የሚለውን መዘንጋትም ተገቢ አይሆንም፡፡ ሁሉም ወቅት ወቅት አለውና! ሁኔታዎችን እንደየአመጣጣቸው መመዘን፣ እንደየልኬታቸው ዓይነተኛ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ በደስታ ሰዓት ደስታችንን መግለጽ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የሚያዘናጉንን ሁኔታዎች፤ ይሆነኝ ብሎ ማሰብ ወሳኝ ነው! ይሄ በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም፣ በባህልም፣ በሥነ አዕምሮአዊ ሂደትም፤ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ መንግሥትም፣ ፓርቲም፣ ግለሰብም ተሁኖ ቢታሰብ፤ ዋናው ነገር ይሄው ነው፡፡
የአባይ ጉዳይ ላይ ያጠላበት የፖለቲካ ድባብ አሁን ሊገፈፍ ይገባል!! ግርማ ሠይፉ ማሩ
የውሃ፣ ኢነርጂና መስኖ ሚኒስትር በአባይ ተፋሰሰ ሀገሮች መካከል በተለይም በግብፅ፣ በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረውን ውይይት እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ያለበትን ደረጃ አሰመልክቶ ለምክር ቤት አባላት በባለሞያ የታገዘ ገለፀ ለማድግ ህዳር 22/2006 በምክር ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡ ይህ ገለፃ እና ማብራሪያ ከዚህ ቀደም ለዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ቀርቦ የነበረ መሆኑ በሚዲያ ተከታትለናል፡፡ በእኔ እምነት ቀድሞ መቅረብ የነበረበት ለምክር ቤቱ ሆኖ ከዚያ ቀጥሎ በየደረጃው ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ቢቀርብጥሩ የፕሮቶኮል አካሄድ ነው ለማለት እችል ነበር፡፡ ለማነኛውም ፕሮቶኮሉን እነተው እና በዚህ ደረጃ ለህዝብ ለማቅረብ ተነሳሸነቱ መፈጠሩ የዘገየም ቢሆን ተገቢ ነው ብዬ መውሰድ አልቸገርም፡፡ “ዘገዬ” የሚለውን ቃል ኢህአዴግና ሹሞቹ በጓዳ ግምገማ ካልሆነ በአደባባይ ውይየት ጊዜ ደስ አይላቸውም፡፡
በነገራችን ላይ ይህ ማብራሪያ አሁን መቅረቡ ጥሩ መሆኑን፤ ነገር ግን ዘግይቷል በሚል ለውሃ፣ መሰኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ለሰጠሁት አስተያየት ሚኒስትሩ “አልዘገየም ድርድሩ እዚህ ጋ የደረሰው በጥቅምት ወር ነው፡፡” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በእኔ እምነት ኢትዮጵያዊያን ማወቅ ያለባቸው የሶስትዮሽ ድርድሩን ሳይሆን አጠቃላይ መንግሰት ግድቡን ለመገንባት የሄደበትን መንገድ ነው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያዊ ምሁራን እና ጋዜጠኞች ከግብፅ እና የግብፅ ወዳጆች በተለያየ መልክ በሚያስረጩት መረጃ ሳይሆን በቀጥታ ከሀገራቸው ታማኝ መረጃ አግኝተው ጠንካራ አቋም እንዲይዙ ማድረግ የግድ የሚል ነው፡፡ የምሁራኑ እና የጋዜጠኞች መረጃ ማግኘት ያለጥርጥር ህዝቡ ሀገር በቀል መረጃ እንዲያገኝ ዋናኛ መንገዶች ናቸው፡፡ የዘገየ ማብራሪያ የምለውም ስለግድቡ አጠቃላይ ሁኔታ ነው እንጂ ስለ ሶስትዮሽ ውይይት ሂደትና ውጤት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በአባይ ተፋሰስ ላይ ቀደም ሲል በአሜሪካ ድጋፍ ቀጥሎም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2005/6 በተፋሰስ አገሮች ትብብር ሱዳን እና ግብፅ ጨምሮ በተደረገው ጥናት ሶሰት የግድብ ቦታዎች ተመርጠው የአሁኑ “ቦርደር ሳይት” በመባል የሚታወቀው የግንባታ ቦታ በሁሉም ተመራጭ እንደነበር ብዙ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ በአቶ አለማየሁ ተገኑ አገላለፅ “ፕሮጀክቱ ግማሽ
ድረስ በትብብር የተሰራ ነው”፡፡ ይህን የትብብር ስሜት ያፈረስው ምን አልባትም የግብፅ ከልክ ያለፈ አልጠግብ ባይነት እና በኢትዮጵያ ምድር ላይ የሚገኝ ቢሆንም አባይን የሚመለከት ፕሮጀክት በባለቤትነትን የመያዝ እና የማስተዳደር ፍላጎት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመጣው ከንቀት ጭምር ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከግብፅ ጋር በሽግግር መንግስት ወቅት የገቡት ቃል ወይም ስምምነት ለመናቃችን አንዱ የቅርብ ምሳሌ ነው፡፡ ኦቶ መለስ ይህን ቃላቸውን አጥፈው፣ ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያዊያን ቁጥጥር እና ባለቤትነት እንዲካሄድ የወሰዱት አቋም ተገቢም ትክክል ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ተመሳሳይ አቋሞች በብዙ ሁኔታዎች የታዘብን ቢሆንም
በዋነኛነት “ባንዲራ ጨርቅ ነው” በባንዲራ ቀን አከባበር፤ “የአክሱም ሀውልት ለወላይታ ምኑ ነው” በብሔር ብሔረሰቦች በዓል አከባበር ቀጥሎም በብሔር መለያየትን “ልዩነታችን ውበታችን” በሚል መፈክር መታጀቡ እና በሌሎች ሁኔታዎችን የተገነዘብን ሰዎች የሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ መታጠፍ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡ ለማንኛውም ኢትዮጵያን እና ህዘቦቿን ወደሚጠቅም አቋም በፈለጉት ዲግሪ መታጠፍ ቢዘገይም በአዎንታ መቀበል ይኖርብናል፡፡
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ጥሩ አካሄድ ሊባል የሚችለው የውጭ ዜጎችን በመጠቀም ዙሪያ በመንግሰት የተያዘው አቋም ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከወንድሞቻችን ኤርትራዊያኖች ጋር በመሪዎች ፍላጎት በገቡት “የድንበር” ተብዬ ግጭት፣ ችግሩን ለመፍታት በተለይም የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ የሀገር ውስጥ ባለሞያዎችን እና ታሪክ አዋቂዎቸን ባለመጠቀም የደረሰባትን ኪሳራ በደንብ የተረዱት ይመስላሉ፡፡ በአባይ ጉዳይ ዋናዎቹ ተዋናዮች ኢትዮጵያዊያኖች እንደ ነበሩ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም በቀጣይ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በሚደረግ ውይይት ከውጭ የሚባል አይኖርም፤ የሚያስፈልግ ባለሞያ ቢኖር ቀጥረን አገልግሎት ከመስጠት በዘለለ ገብቶ መፍተፈት አይፈቀድም፡፡ የሚል አቋም ኢትዮጵያ ይዛለች የሚለው መስመር እሰይ የሚያስብል ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አቋም የሚመራው በኢህአዴግም ቢሆን መደግፍ የግድ ይለናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ እሰከ ዛሬ በነበረው ውይይት ከውጭ ሀገር ማለትም ከጀርመን፣ ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ እና ከደቡብ አፍሪካ ተወክለው ምክረ ሃሳብ ያቀረቡት ባለሞያዎች ጥንቅር “ለምን ከወዳጆቻችን ከነቻይና አልመጣም?” የሚል ፈገግ የሚያሰኝ በዚያውም የህውሃት አባላት አሁንም መንግሰት ሶሻሊሲት እንደሆነ የሚያሳብቅ ጥያቄ አንድ የምክር ቤት አባል ሰንዝረዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጭ ካፒታሊዝም ነው የምንከተለው ይበሉ እንጂ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በዚህ የሚስማሙ እንዳልሆነ በተለያየ መግለጫ ታዝበናል፡፡ እኛም ብንሆንን የምንስማማው አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በሚገልፁት መስመር ነው፡፡ የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከካፒታሊዝም ሳይሆን ወደ ሶሻሊዝም የሚጠጋ ርዕዮት እንደሆነ ነው የሚገባን፡፡ መድበለ ፓርቲ ስርዓት፣ ነፃ ገበያ፣ የግል ሀብት፣ ወዘተ ለእርዳታ ሰጪዎች ሲባል የሚቀርቡ ሹፈቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሹፈቶች ግን ይዋል ይደር አንጂ ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡
በግሌ የኢህአዴግ በደል ከፍቶ ፅዋው ሞልቶ ቢፈስ እንኳን የሀገሬን ጥቅም አሳልፌ የምሰጥበት ምንዳም ሆነ የግፍ መጠን እንደሌለ በተደጋጋሚ ይፋ አድርጊያለሁ፣ ከዚህ የግል እምነቴ ጋር የሚፃረር ፓርቲም ሆነ ሌላ ስብስብ ጋር እንደማልሰራ አውቃለሁ፡፡ እንደዚያም ሆኖ የመንግሰት ሹማምንት የአባይ ግድብን ያህል ትልቅ ፕሮጀክት ይዘው ተቃዋሚና ገዢ ፓርቲ የሚል ክፍተት መፍጠር እንደሌለባቸው ሲነገራቸው፣ በተግባር የሚሰሩትን ሀቅ ወደ ጎን ትተው ጉዳዩን በሙሉ ፕሮፓጋንዳ ያደርጉታል፡፡ ኢህአዴግ ለፕሮፓጋንዳ የሚከፍለው መሰዋዕትነት የፈለገ ውድ ቢሆን ለመክፈል ዝግጁ ነው፡፡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስለግድቡ በቂ መረጃ በሌላቸው እና ይልቁንም ግርማ ሠይፉ ማሩ በመንግሰት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ፍፁም ደስተኛ ባልሆኑበት ሁኔታ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መንግሰትን ደግፈው ገንዘባቸውንያለምንም ጥያቄ እንዲቸሩ ይጠይቃል፡፡ በሀገር ውስጥም ቢሆን ሁሉን ተዉት ገንዘብ አምጡ ዘመቻ የሚያስገርም ነው፡፡ በውጭ የሚኖሩኢትዮጵያዊያን ይህን ግድብ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሊገነቡት የሚችሉበት አቅም እንዳለ ተገንዝቦ ግብፅን አንገት የሚያስደፋ መንገድ ከመቀየስ ይልቅ አሁንም በውጭ የሚገኙትን ዜጎች መከፋፈል ተገቢ አይደለም የሚል እምነት አለኝ፡፡ መንግሰት ከዚህ አንፃር
የሚጠበቅበት ለውጥ፤ ግብፅን አና ወዳጆቿን እሞኑኝ ብሎ ለልምምጥ ከሚያጠፋው ጉልበትና ሀብት የሚበልጥ አይደለም፡፡ መንግሰት ከዚህ አንፃር የሚከተለውን የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂ እንደገና መገምገም እና ሁሉንም በሚያሳትፍ መልኩ መቀረፅ እንዳለበት ማስገንዘብ ቢዘገየም የረፈደ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ግን የሚሰማ አይመስልም፡፡ ማን ነው ኢህአዴግ ሀፍ እንጂ ጆሮ የለውም ያለው?
በአባይ ዙሪያ በኢየትዮጵያ ለሚታሰብ ማንኛውም እንቅስቃሴ በቂ ተቃውሞ በግብፅ ስለ አለ በሀገር ውስጥ ሌላ ጠላት ለምን ትፈልጋላችሁ? ለሚል ጥያቄ ኢህአዴግ ሆደ ሰፊ መሆን አይችልም፡፡ ኢህአዴግ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ማግኘት የሚፈልገው፣ ለአብታዊ ዲሞክራሲ እግረ መንገዳቸውን ገብረው እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ እኔ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ አባል ለስልጣን ነው ትግል የማደርገው፡፡ ስልጣን ብንይዝ ይህች ሀገር ኢነርጂ እንደሚያስፈለጋት ለማወቅ ስልጣን መያዝ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ የአባይን ግድብ ለመገንባት መንግሰት የሚያወጣውን ዕቅድ በተመለከተ የተሟላ መረጃ እንዲኖረኝ የግድ ይላል፡፡
የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከዚህ አንፃር በጭፍን የአባይን ግድብ እንዲደግፉ እንጂ መረጃን መሰረት አድርገው ትንተና እንዲሰሩ እና የራሳቸውን ምክረ ሃሳብ እንዲሰጡ እድል የላቸውም፡፡ ለዚህ ጉዳይ የሚፈለጉት ልማታዊ የሚባሉት ጋዜጠኞች ብቻ ናቸው እነርሱም መንግሰት የሚለውን እንደ በቀቀን መድገም ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ በግብፅ ግን የግልም ሆነ የመንግሰት ሚዲያዎች ለሀገራቸው ይጠቅማል ያሉትን እንዲዘግቡ መረጃ ይስጣቸዋል፡፡ ማግለል ይቅር ስንል የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን
ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን ሚዲያውንም ጭምር ነው፡፡ አሁንም የአባይ ጉዳይ እና መረጃ ሁሉም ሚዲያዎች በሚያሳትፍ መልኩ ለሚዲያዎች መሰጠት ይኖርበታል፣ ሚዲያዎችም ይህን ኃላፊነት እንደሚወጡ ጥርጥር የለኝም፡፡ ለዚህም ማሳያ የ “ፋክት” አምደኞች ቤተሰብ የነበረችው መፅሄት አዲስ ታይምስ ከዓመት በፊት የአባይን ጉዳይ በልዩ ዕትም ቅፅ 1 ቁጥር 9 ህዳር 2005 ማውጣቷ እና በዚህ ዕትም ያስተላለፈችው መልዕክት ድጋሜ መነበብ የሚገባው ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ በኤክሰፐርቶች ፓናል ውስጥ ተሳታፊ ለሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ሁሉ ከመቀመጫዬ ብድግ ብዬ አድናቆቴን መግለፅ እፈልጋለሁ፡፡
ግብፆች የአባይ ጉዳይ ሲነሳ የፖለቲካ ልዩነታቸውን ትተው እንደ ግብፅ ሲያስቡ እኛን መለያየት ለምን ያስፈልጋል? የአባይ ግድብ ፕሮጀክት በተግባር የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮጅክት አንዲሆን የፖለቲካ ድባቡ ላይ ያጠላው የፕሮፓጋንዳ አዚም ሊገፈፍ ይገባል፡፡ አንድነት ፓርቲ ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን መጠቀም ተፍጥሯዊ መብቷ ነው ይላል፡፡ ይህ የማይገሰስ መብት ላይ ምን ፕሮፓጋንዳ ያስፈልጋል፡፡ የዛሬው መልዕክቴ ዋና ማጠንጠኛ በሀገር ጉዳይ እንዳንግባባ አዚም ያደረገብን ማን ነው? የዚህ አዚም መፍቻ ቁልፍ መተማመን እና ሀገራዊ ዕርቅ ይመስለኛል፡፡
መልካም በዓል ቸር ይግጠመን !!!!!!
‹‹የሕዝብ መብት ከሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ጋር መሥራት አስቸጋሪ ነው›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
‹‹የአንድነትን አቋም ሳያውቁ የፓርቲው አባል ሆነዋል ለማለት ያስቸግራል›› m አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ
ላለፉት ሁለት ዓመታት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር የነበሩትና ለ45 ዓመታት በፖለቲካ ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ከጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም.
ጀምሮ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት የወሰኑት አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ስላልተመቻቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ምላሽ ባለማግኘታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ነጋሶ እንደገለጹት፣ መድረክ ግንባር ከመሆኑ አስቀድሞ ባነሳቸው ሐሳቦች ላይ ሁሉም ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባዔ በማድረግ ከተወያዩባቸው በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ መስማማታቸውንም ለመድረክ በመግለጽ መድረክ ወደ ግንባር መሸጋገሩን አስታውሰዋል፡፡
በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. በአንድነት ፓርቲና በእሳቸው የአመለካከት፣ የአቋምና የአቅጣጫ ልዩነት መፈጠሩን የገለጹት ዶ/ር ነጋሶ፣ አንድነት ፓርቲ መድረክ ወደ ግንባር የተቀየረው በጠቅላላ ጉባዔውና በብሔራዊ ምክር ቤቱ እምነትና ውሳኔ ሳይሆን በአመራሮች መሆኑን በመጥቀስ፣ እንደማይስማማ በዚያን ወቅት ባደረገው ግምግማ ላይ በመግለጹ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
መድረክ ወደ ግንባር ከመቀየሩ አስቀድሞ ይፋ ባደረገው ፕሮግራም ላይ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተወያይተውና ተመካክረው በሕገ መንግሥት ጉዳይ፣ በቤት ጥያቄና በሌሎችም በተነሱ ነጥቦች ላይ መስማማታቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ነጋሶ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ላይ ብቻ ልዩነት እንዳለው አንድነት ገልጾ የሽግግር ሒደቱ በሰላም መፈጸሙን አስታውሰዋል፡፡
ሽግግሩ ወራትን ካስቆጠረ በኋላ በሕገወጥ መንገድ እንደተደረገ በማስመሰል ወደኋላ መመለስ አሳፋሪ ድርጊት ከመሆኑም በተጨማሪ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትና የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት፣ ፓርቲው የማይስማማበትን ነጥብ ይዞ ወደ መድረክ በመሄድ መወያየት ሲገባቸው፣ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠታቸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የነበሩትን የተሳሳቱ ሒደቶች በመጥቀስ እርማት እንዲደረግ ዶ/ር ነጋሶ ለአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ቢሆንም፣ ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላው ዶ/ር ነጋሶ የሚያነሱት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ላይ የተጠቀሰውን ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት የራስን ዕድል በራስ ከመወሰን እስከ መገንጠል›› የሚለውን የሕዝቦች የመብት ጥያቄ አንድነት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አለመሆኑን ሲሆን፣ ‹‹የሕዝብን መብት ከሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ጋር መሥራት አስቸጋሪ ነው፤›› ብለዋል፡፡
አንድነት የመድረክን ወደ ግንባር መቀየር የማይቀበለው ‹‹የውህደት›› ኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ መመሥረት እንዳለበት ስለሚፈልግ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ነጋሶ፣ በሕጋዊና በትክክለኛ መንገድ ስምምነት የተፈጸመበትን ‹‹ግንባር›› ‹‹ውህደት›› ካልሆነ ማለት የማይሆንና የማያስኬድ መንገድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ያልተስማሙባቸውን ነጥቦችና ስምምነት ከተደረገ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አግባብ አለመሆኑን በመጠቆም ላቀረቧቸው ጥያቄዎች የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ምላሽ በመንፈጉ ምክንያት፣ ዶ/ር ነጋሶ ከፖለቲካው ዓለም መሰናበታቸውን ይፋ ቢያደርጉም፣ ቀደም ብሎም ከፖለቲካ ሥራና ተሳትፎ ለመልቀቅ በማኮብኮብ ላይ እንደነበሩ አልሸሸጉም፡፡
ምክንያታቸውንም ሲገልጹ ነሐሴ 3 ቀን 2005 ዓ.ም 70 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡ ከዕድሜያቸው ከግማሽ በላይ ለ45 ዓመታት በፖለቲካ ውስጥ ቆይተዋል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብን የፖለቲካ ባህል ሲያስታውሱ፣ በኦሮሞ ገዳ ዲሞክራሲ አንድ መሪ ዕድሜው 48 ሲሆነው የአመራር ሥልጣኑን ለወጣቱ መልቀቅ እንዳለበት የሚገልጸውን ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ መሆኑንም ማሰባቸውን አብራርተዋል፡፡
ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ዓለም ራሳቸውን ማግለላቸውን ከዚህ በኋላ በማንኛውም መንገድ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በአባልነትም ሆነ በመአራርነት እንደማይሳተፉ ያረጋገጡት ዶ/ር ነጋሶ፣ ‹‹ጆሮዬ ለፖለቲካ ክፍት ይሆናል፤ የማስበውን በጽሑፍና በአፌ እናገራለሁ፤ አንድነትንም ሆነ ሌሎችንም በመዋቅራዊ መልክ ሳይሆን እደግፋለሁ፤ ሲያስፈልግ እተቻለሁ፤ ሲያስፈልግ እቃወማለሁ፤›› ብለዋል፡፡
አንድነት ፓርቲ ለዶ/ር ነጋሶ ከፖለቲካ መገለል ምክንያት ስለመሆኑ ለተነሳለት ጥያቄ በሕዝብ ግንኙነት አማካይነት ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ፓርቲው በቅርቡ አዲስ አመራር መምረጡንና ቀደም ሲል በሊቀመንበርነት ሲመሩ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ፣ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሥልጣን ሽግግሩን ፈጽመው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አቅርበው ሽግግሩን ማፅደቃቸውን የገለጹት የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ናቸው፡፡
ለብሔራዊ ምክር ቤቱ የአዲሱን አመራር ቀጣይ የሥራ የሽግግር ጊዜ ሲያቀርቡ፣ ከዕድሜያቸው ጋር በተገናኘ ለቤተሰቦቻቸው ራሳቸውን ከፖለቲካ እንደሚያገሉ ቃል መግባታቸውን የተናገሩት አቶ ሀብታሙ፣ በመድረክ ላይ ያላቸውን አቋምም ግልጽ ማድረጋቸውን አክለዋል፡፡
ዶ/ር ነጋሶ አንድነት መድረክን መገምገሙና ማጥናቱ ትክክልና ተገቢም ነው፡፡ የግንባሩ አባል የሆነ ድርጅት ፖለቲካውን አግባብ ባለው መንገድ እየመራ ነው? አይደለም? የሚለውን ጥናት ማድረግ ተገቢ ነው ካሉ በኋላ፣ መድረክ አሁን ባለው ሁኔታ የሚታየውን ነገር ሁሉ ማሻሻያ በማድረግ ሊቀጥል ይገባል የሚል አቋም እንዳላቸው መናገራቸውን አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል፡፡
አንድነት ፓርቲ መድረክ ወደ ውህደት በማደግ አንድ ግዙፍ ብሔራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር ያቀረበውን ሐሳብ በቀላሉ ሊሳካ የሚችል ባለመሆኑ፣ ሐሳቡን እንደማይደግፉም ዶ/ር ነጋሶ ማሳወቃቸውን አቶ ሀብታሙ ጠቁመዋል፡፡
ዶ/ር ነጋሶ ያነሱትን የልዩነትና የድጋፍ ሐሳብ አንድነት ፓርቲ እንደሚያከብር የገለጹት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው፣ ፓርቲው ግን ግልጽ የሆኑ የፖለቲካ አማራጮች እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግልን ወደፊት ለመግፋት ብሔራዊ ምክር ቤቱና ጠቅላላ ጉባዔው አስቀድሞ ባዘጋጁዋቸውና በሚያሻሽሉዋቸው ነጥቦች ትግሉን እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡
አንቀጽ 39ን በሚመለከት አንድነት የብሔር ብሔረሰቦችን መብት በተመለከተ ሕገ መንግሥቱ የሚያነሳቸውን ነጥቦች ፍፁም በሆነ ሁኔታ እንደሚያከብር የተናገሩት አቶ ሀብታሙ፣ ዶ/ር ነጋሶ የአንድነት ፓርቲን አቋም በግልጽ ሳያውቁ የፓርቲው አባል ሆነዋል ለማለት እንደሚያስቸግር አክለዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ ከአንቀጽ 39 የማይቀበለው በመጨረሻው ንዑስ አንቀጽ ላይ የተቀመጠውን ‹‹እስከ መገንጠል›› የሚለውን ሐረግ መሆኑን ይህንንም በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት ላይ የተቃጣ አደጋ በመሆኑ፣ መቼም ቢሆን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማንም ለድርድር እንደማያቀርብ በግልጽ ሊታወቅ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
ዶ/ር ነጋሶ ላለፉት 45 ዓመታት በቆዩበት የፖለቲካ ሕይወታቸው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል፣ እንዲሁም የኢሕአዴግ አባል የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) አመራር እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ከኢሕአዴግ ጋር ከመለያየታቸው በፊት ለስድስት ዓመታት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ከቀድሞ የአገር መከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ ጋር በመሆን የአንድነት ፓርቲ አባል ከመሆናቸውም በላይ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የፓርቲው አመራር አባልና ሊቀመንበር መሆን ችለው ነበር፡፡
ዓለም አቀፍ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ብድርና ዕርዳታ እንዲያቆሙ ግብፅ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን መንግሥት መረጃ እንዳለው አስታወቀ፡፡
በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው የሦስትዮሽ ድርድር ሦስተኛ ስብሰባ በቅርቡ ያለውጤት ከተበተነ በኋላ፣ በግብፅ በኩል አፍራሽ የሆኑ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓርብ ረፋድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና፣ በግብፅ በኩል የቀረበውና በኢትዮጵያና በሱዳን ውድቅ የሆነው ሐሳብ፣ እስካሁን ግድቡን አስመልክቶ የተጀመሩ ውይይቶችን ወደኋላ የሚመልስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የውጭ ባለሙያዎች ያሉበትና ከሦስቱም አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የኤክስፐርቶች ፓነል ለአንድ ዓመት በግድቡ ዙሪያ ጥናት አካሂዶ ባወጡት ሪፖርት፣ ከተወሰኑ ቴክኒካዊ ማስተካከያዎች ውጪ ግድቡ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላ መሆኑን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
የፓነሉ ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሦስቱ አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች ያሉበት ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑን፣ ግብፆች አዲስ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የኮሚቴውን ሥራ በበላይነት እንዲከታተል የሚል ሐሳብ ነው ያቀረቡት፡፡
እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ፓነል መቋቋም ላይ ሳይሆን፣ ሚናውን በተመለከተ ነው፡፡ በዚህ ልዩነት የተነሳ ያለውጤት ስብሰባው ከተበተነ በኋላ፣ ግብፆች በሚዲያዎቻቸው ‹‹ኢትዮጵያ ለመተባበር እምቢተኛ ሆነች›› እያሉ እያቀረቡ መሆኑንና ከዓለም ባንክ፣ ከአይኤምኤፍና በሌሎች ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በምንም ምክንያት ኢትዮጵያ በገንዘብ እንዳትደገፍ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን መንግሥት መረጃ እንደደረሰው አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል፡፡
የግድቡ ግንባታ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ይቋረጣል የሚል እምነት ያላቸው ግብፃውያን፣ የገንዘብ ተቋማቱ ኢትዮጵያ የዚህን ግድብ ግንባታ ካላቆመች በማንኛውም መንገድ የሚያደርጉትን ዕርዳታ እንዲያቆሙ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡ ግብፃውያን ከዚህ አፍራሽ ድርጊታቸው ተቆጥበው በኤክስፐርቶች ፓነል ሪፖርት መሠረት መተባበራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ ከተለመደው አፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማስታወቅ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሑመራና በመተማ አካባቢ ኢትዮጵያ ለሱዳን መሬት ስለመስጠቷ እየተነገረ ስላለው ጉዳይ መንግሥት አስተባብሏል፡፡ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሱዳን በግድቡ ላይ ባሳየችው አዎንታዊ አቋም ምክንያት፣ ሲያወዛግብ የቆየውን ሰፊ የድንበር መሬት መስጠቷ የተዘገበ ቢሆንም፣ አምባሳደር ዲና ግን፣ ‹‹እንኳን መሬት ሊሰጥ ይቅርና በጉዳዩ ላይ የሚደረገው ውይይትም አልተቋጨም፤ እስካሁንም ስምምነት ላይ የተደረሰ ነገር የለም፤›› ብለዋል፡፡
ላለፉት አሥር ዓመታት ድንበሩን በተመለከተ ሲሠራ የቆየው የጋራ ኮሚሽን፣ በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር እንዲካለልና የግጭት መንስዔ የሆነውን ጉዳይ ለመፍታት እየሞከረ መሆኑን፣ በቅርቡ ‹‹ለሱዳን መሬት ተሰጠ›› ተብሎ የተነገረው ግን መሠረት የሌለው ወሬ መሆኑን አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል፡፡
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
News, Radio Magazine or Mestawot
የዓለም ዜና
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የገጠሙትን አስከፊ ጦርነት ለማስቆም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የጀመረዉ የማደራደር ጥረት እስካሁን ተጨባጭ ዉጤት አላመጣም።
አዲስ አድማስ አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ ገቡ ብሊ በዘገበዉ «አንጻር የአዲስ አድማሱ ዘገባ፣ በቀጥታ አቶ ሌንጮ ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ ከሰጡት ጋር የሚቃረን ሲሆን፣ ጉዳዩን በትክክል ለማጣራት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።የአቶ ሌንጮ የጀርመኑ ቃለ ምልልስ ወይንም የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ ትክክል መሆኑ የሚያመላከት መረጃ እንዳገኘን ለአንባቢያ ግልጽ እናደርጋለን”” ብለን ነበር። አቶ ሌንጮ ለታ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የኦዴፍ […]
Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. Jan 18, 2014)፦ በሳኡዲ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያኖች ያሉበት አሳሳቢ ሁኔታ ያስጨነቃቸው በቫንኩቨር ካናዳ ነዋሪዎች ምሽቱን ባደረጉት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ወደ 10ሺህ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰባቸው ተገለጸ።
«የቀድሞ የኦነግ አመራር ሌንጮ ለታ፣ አዲስ ፓርቲ ይዘው አዲስ አበባ ገቡ» ሲል አዲስ አድማስ በቅዳሜ ጥር 10 እትሙ ላይ ዘገበ። አቶ ሌንጮን ለማነጋገር ያደረግነዉ ሙከራ እንዳልተሳካለት የዘገበው አዲስ አድማስ ፣ መረጃዎን ያገኘነው ከምንጮቹ እንደሆነም ገልጿል። አቶ ሌንጮ በጀርመን ድምጽ ራዲዮ በቅርቡ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ኢትዮያጵያ ዉስጥ ገብቶ በሰላም ለመታገል ፍልጎቱ እንዳላቸው ገልጸው፣ ከኢሕአዴግ ጋር ምንም […]
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana
ተመስገን ደሳለኝ
አምስተኛው ዙር አገር አቀፍ ‹‹ምርጫ›› እንደወትሮው ሁሉ በቀጣዩ ዓመት ሊደረግ በዕቅድ ተይዟል፤ ወሬውም ከወዲሁ ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው፤ ኢህአዴግም በበኩሉ ‹አውራ ፓርቲ›ነቱን ከቀደመው በበለጠ አጠናክሮ የሚቀጥልበትን ሴራ ፈትሎ በመግመድ ውሎ ማደሩን ገና በማለዳ እያቀላጠፈው መሆኑን እየታዘብን ነው፡፡
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የደቡብ ሱዳን መንግሥት፤ ከአማጽያኑ ጋር በቅርቡ የተኩስ አቁም ሥምምነት ለመድረስ ተስፋ እንዳለዉ መግለጹን አሁን ማምሻዉን የደቡብ ሱዳን መንግሥትን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። በሌላ በኩል በኢጋድ የቀረበዉ መደራደርያ ነጥብ በአማፅያኑ ተቀባይነት ማግኘቱን ተልጸዋል።
ከብዙ አዳጋች ሁኔታ በኋላ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት የተቃረበችው ቱኒዝያ ” ባለፈው ማክሰኞ ቤን አሊ የተወገዱበትን 3ኛ ዓመት አስባ ዋለች። የቱኒዝያ ሕዝብ ዓመፅ እና ቤን አሊ የሸሹበት ድርጊት ግብፅ፣ ሊብያ ፣የመን እና ሶርያን ለዓብዮት ማበረታታቱ አይዘነጋም።
የዕለቱ ዜና
ሐበሾቹ ነገ ጠዋት የጌታን ጥምቀት በዩጋንዳ በልዩ መንፈሣዊ ስርዓት ያከብሩታል!!!
መንበረ ፓትርያኩን በሰሜን አሜሪካ ባደርገው በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው የካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የደብሩ ማሕበረ ካህናትና ማህበረ ምዕመናን በዩጋንዳ ነገ ጠዋት ጥር ዐሥራ ዐንድ ቀን የጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓልን በከፍተኛ መንፈሣዊ ሥነ ሥርዓት እንደሚያከብሩ ተገለፀ።
ከሠንበት ቅዳሤ በኋላ የመድሃኒያለምና የቅዱስ ሚካዔል ታቦታት በምዕመናን ታጅበው በመሪጌታ ይህይስ ዓለሙ መሪነት ያሬዳዊ ዝማሬ የዕለቱ ምልጣን<ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ወልደነ ዳግመ እማየ ወእመንፈሠ ቅዱስ እሙነኮነ ለፀሐየ ፅድቅ አስተርዕዮቱ አማን መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ > የሚቀርብ ሲሆን የደብሩ ማሕበረ ካህናት ከማህበረ ምዕመናን ጋር ፈጣሪ አምላካቸውን በያሬዳዊ ዜማ ያመሠግናሉ። ጥምቀተ ባሕሩም ይባርካል።
አስተማማኝ የፖሊስ ጥበቃ ስለሚደረግ ምዕመናን መኪናቸውን ደብሩ ባዘጋጀው የማቆሚያ ስፍራ በማድረግ ያለስጋት በዓሉን እንዲያከብሩ የቤተክርስትያኒቱ አስተዳደር ጽ /ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
ሐበሾቹ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በዩጋንዳ በጋራ በመሆን ፈጣሪያቸውን በተለይ ዘወትር ዕሁድ እንደሚያመሠግኑ ይታወቃል።አባ ኃይለማርያም በአሉን በማስመልከት የወንጌል ማዕድ የሚያቀርቡ ሲሆን የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ፀሐይ ደስታ በበበዓሉ ፍፃሜ ላይ ቃለ ምዕዳን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
የካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ማህበረ ካህናትና የደብሩ አስተዳደር ጽ /ቤት ለመላ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ጥምቀቱ አደረሣችሁ እያሉ መልካም ምኞታቸውን እንዳስተላለፉ የዚህ ዜና ዘጋቢ ጨምሮ ገልጿል።
አክሊለ ሠማዕት
penEthiopian
የከተራው በአል ከተራ ምንድን ነው? ከሚለው ትርጓሜ እንነሳ … በየዓመቱ የጥምቀት በዓል በድመቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ገለጻ ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን […]
በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡
በአደባባይ የሚጽፉ ሰዎች ሁለት ነገሮችን ለይተው መገንዘብና ለሌሎችም ሲየያስተላልፉ ለይተው ማስተላለፍ አለባቸው፤ አንዱ የሆነና የተረጋገጠ ሁነት ነው፤ይህንን ሳይበርዙና ሳይከልሱ እንዳለና እንደተገኘ ማስተላለፍ ግዴታ ነው፤ ሁለተኛው የራስ አስተያየት ነው፤ የጠራውንና የነጣውን አውነት ከጎደፈ የግል አስተያየት ጋር አጋብቶ ማቅረብ ወይ አለማወቅ ነው፤ አውቀው ከሆነም ለማታለል ከመሞከር የሚቆጠር ነው፤ በአለንበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ የምናየው ፊደሎቹን ማወቅ እንደሙሉ እውቀት ይቆጠራል፤ ወይም በሌላ አነጋገር ፊደልን ማወቅ የመጻፍ ችሎታን ይሆናል፤ ይህ ትልቅ ስሕተት ነው፤ ፊደሎችን ማወቅ ትልቅና መሠረታዊ የእውቀት ጎዳና ላይ መግባት ነው፤ ጎዳናው ግን በጣም ረጅም ነው፤ በእውቀት ጎዳና ላይ መግባት የእውቀት ባለቤት ከመሆን ጋር እንዳይደባለቅ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአገራችን ፊደልን ማወቅ ሌላም አደጋ አለው፤ ፊደልን ማወቅ ከሥልጣን ጋር ሲጋባ የሚያስከትለውን ውድቀት ከአንዴም ሁለቴ አይተናል፤ እያየንም ነው፤ ስለዚህም ፊደል ኃላፊነትን ያመጣል፤ አለዚያ በአለፉት ሠላሳ ዓመታት ያየነው ውድቀት እየተከበረ ይቀጥላል፡፡
መጻፍ እንደመናገር ሊቆጠር ይቻላል፤ሆኖም በመጻፍና በመናገር መሀከል ትልቅ ልዩነት አለ፤ በንግግር ላይ ከሰዎች በሚቀርበው ጥያቄም ሆነ ተቃውሞ እንዲህ ማለቴ ነው ብሎ የተናገሩትን እዚያው ለማረምና ለማስተካከል ይቻላል፤ በተጻፈ ነገር ላይ እንዲህ ዓይነቱ ወዲያው የመታረም ዕድል የለም፤ ስለዚህም ለመጻፍ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው፤ ከላይ እንደተገለጸው ፊደልና ሥልጣን ሲጋቡ ሰንደቅ ዓላማው ጨርቅ ነው ከማለትም ሊያልፍ ይችላል፤ ለምሳሌ የደርግን የትርፍ ቤቶች አዋጅ ብንመለከተው ‹‹ትርፍ ቤት›› ሲል ትርፍን እንተወውና ‹‹ቤት›› ለሚለው ትክክለኛ ትርጉም አልሰጠም፤ ስለዚህም በጭራሮ የተያያዘ ምንም ‹‹ቤት›› የሚያሰኘው (መኝታ ቤት፣ ወጥ ቤት፣ መታጠቢያ ቤት፣ … የሌለው) በሃምሳ ሳንቲም የሚከራይ ነገር ‹‹ቤት›› ተብሎ በሺህ ብር ከሚከራይ ቤት ጋር ተወረሰ! ያፈረ የለም እንጂ አሳፋሪ ነው!
እንዲህ ዓይነቱ ችግር ከየት የሚመጣ ነው? አንድ አጠቃላይ የአስተሳሰብ ችግር አለ፤ ለየት ያለውን ከጅምላው፣ ግዙፉን ከረቂቁ፣ አንዱን ከብዙው ያለጥንቃቄ ማደባለቅ በአማርኛ በጣም የተለመደ እየሆነ ነው፤ የአስተሳሰብ ችግር ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ (አበሻና ሆድ የሚለው ጽሑፍ ባሕር ተሻግሮ የአበሻን ነገር-ዓለም ትቶ የተጠበሰ ውሻ (ሆት ዶግ) የሚበላውንም አስቀየመውና ሌሎች ስለአበሻ የጻፍኋቸውን ተውኩት እንጂ አበሻና መናገር የሚለው በተለይ ለባሕር ማዶው ዘሎ-ጥልቅ ተስማሚው ነበር፤) በማናቸውም ነገር ላይ ለመቀባጠር በጣም ኃይለኛ ምኞት አለው፤ አንዱ ያስተሳሰብ ችግር ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፤ ሳያስቡና ሳይጨነቁ አፍ እንዳመጣ ከመናገር ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፤ አሁን ደግሞ የጎሠኛነት ሥርዓት ካመጣብን ጣጣ ዋኖቹ የአስተሳሰብ ችግሮች እነዚህ ናቸው፤ የቡድን መብትን መሠረታዊ አድርጎ የግለሰብን መብት ጨፍልቆ የተነሣው የወያኔ የጎሣ ሥርዓት ከሃያ ዓመታት በኋላ በስንት ጥረት የደረሰበት አሁንም የተዛባ ድምዳሜ የቡድን መብትንና የግለሰብ መብትን ጎን ለጎን አቁሞ እኩል ናቸው ማለትን ነው፤ ለውጡ የተጣራ ባይሆንም ሃያ ዓመታት መፍጀቱ የወያኔን የመማር ፍጥነት የሚያመለክት ነው፤ የሥልጣን ጉልበትና የሥልጣን ምኞት ተጽእኖ እንደአንድነት ያለውንም የፖሊቲካ ፓርቲ ፐሮግራሙን እንዲለውጥና የግለሰቦችንና የቡድን መብቶች በአንድ ደረጃ ላይ እንዲያስቀምጥ ተደርጎአል፤ ከቡድን ውስጥ ግለሰቦች ሁሉ ሙልጭ ብለው ሲወጡ ስለቡድን መብት የሚያወራ ምን እንደሚባል እንጃ! ከቀኝ ወደግራ የዞረ? ወይስ ከግራ ወደቀኝ? ወይስ … ቀኝ ፖሊቲካ ባዶ ከረጢት ይዞ ይቀራል።
በተደጋጋሚ እንዳየሁት ለግለሰብ መብቶች የቆመ ቀኝ-ዘመም፣ ለቡድን መብቶች የቆመ ግራ-ዘመም የሚባል ይመስላል ይህ ስሕተት ነው።
ቀደም ሲል የታወቀው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እኔን ቀኝ-ዘመም እያለ ጽፎ ሳይ ይህ ሰው በአውነት አንድ መዝገበ ቃላት ማየት አቅቶት ነው? ወይስ እኔን በተለየ ዓይን ለማየት ከመፈለግ የተነሣ ነው? ወይስ የሲአይኤውን መልክተኛ ፖል ሄንዜን ሰምቶ ነው? የሱ ጎሣ አባል መሆንንና አለመሆንን እኔ የምመርጠውና የምወስነው አይደለም፤ ታምራት በኢትዮጵያዊነት ወይም በዜግነት ዓይን ሊመለከተኝ አለመቻሉም የእኔ ጥፋት አይደለም፤ ሁሉም ቢቀር በሰውነት ደረጃ ሊያየኝ ይችል ነበር፤ ይህንንም አልቻለም፤ እንግዲህ ወይ እኔ ሰው አልሆንኩለትም፤ ወይ እሱ ወደሰውነት ደረጃ አልደረሰም፤ በታምራት ነገራ ቀኝ-ግራ መጋባት እንደኔው ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ የነበረው ክፍሉ ሁሴን ወደጥናት ተመልሶ የታምራትን ስሕተት አረጋገጠ፤ እኔም እንዲሁ አደረግሁና የታምራት ነገራን ግራ መጋባት አረጋገጥሁ፤ ታምራት ነገራ የጎሣ ቀኝ ገብቶት ግራ ፖሊቲካ ቀኝ ሆኖበታል! ቀኝ-ግራ ፖሊቲካ በጎሣ አባልነት የሚገኝ ወይም የሚታጣ ይመስለዋል፤ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ሀብትና ሌላ ማናቸውንም ነገር ከቁም-ነገር ሳይቆጥሩ ለማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ ማግኘት የሚገባውን መብት እንዲያገኝ ቆሞ መከራከር ለታምራት እንግዳ ነገር ይመስለኛል፤ ገና እሱ ሳይወለድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር በተደረገ ስብሰባ ላይ ለምን የኢትዮጵያ ራድዮ በኦሮምኛ አይናገርም? በማለት ጌታቸው ኃይሌ ጋር ሆነን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሰዎችን ሞግተን ነበር፤ ይህ ለታምራት የቀኝ ፖሊቲካ ነው፤ የሱ ጎሣ-ዘመም ፖሊቲካ ግራ መሆኑ ነው! ጎሠኛነት ምን ጊዜም የትም ቦታ እንደግራ ፖሊቲካ ተፈርጆ አያውቅም።
አሁን ደግሞ ሰሎሞን አብርሃም ይህንኑ የታምራት ነገራን ስሕተት ለመድገም የዳዳው ስለመሰለኝ በዝምታ ለማለፍ አልፈለግሁም፤ ሰሎሞን (liberalism) የሚለውን የአንግሊዝኛ ቃል በባሕርዩ የሌለበትን ትርጉም ሊሰጠው ይዳዳዋል፤ ሰሎሞን አብርሃም ሊጽፍበት የተነሣው ጉዳይ በእኔ ግምት በጣም ወቅታዊና አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን የግል ስሜትን ከሁነት ጋር፣ ያልተጣራ የተውሶ ሀሳብን (‹‹ፊዩዳሊዝም፣ ሊበራሊዝም››…) ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር በማያያዝ አስተሳሰቡን ያጎደፈው ይመስለኛል፤ ያነሣው ጉዳይ በተለይም እንደሱ ላለ ፖሊቲከኛ ከስሜተኛነትና ከወገንተኛነት የጸዳ ቢያደርገው (‹‹ወግ አጥባቂ፣ቀኝ አክራሪ›› ..)፣ወይም ደግሞ ያልተጣራ (‹‹የሊበራል ዴሞክራሲን ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ይመስላሉ፤›› እያለ በጎን ከሚጎሽም የጸዳውን እውነት ፊት ለፊት እያቀረበ ድካማቸውን ቢተነትን የሚጠቅም ይሆን ነበር።
ግራና ቀኝ ፖሊቲካ የሚባለውን ከጎሣ ፖሊቲካ ጋር ለማገናኘት የሚፈልጉ ሰዎች ወጣቶችን ወደአስከፊ ስሕተት እንዳይመሩ መጠንቀቅ ያለባቸው ይመስለኛል፤ የጎሣ ሥርዓትን የሚቃወሙትን ወገኖች በሌላ መንገድ ለመቋቋም ቢሞክሩ የተሻለ ነው፤ በጎሣ ክፍፍል ማመን ሌላው ቀርቶ በሰውነት ደረጃ ለመሰለፍም ያስቸግራል፤ ለማናቸውም የጎሣ ፖሊቲካን ከግራ ፖሊቲካ ማዛመዱ እሳትና ውሀ ነው።
የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባፈለግ፣ ቁሸት ሕኖይቶ) ህዝብ የከፈተው ዓመፅ ዛሬ (ዓርብ 09/05/06 ዓም ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ከአስር ደቂቃ (12:10) ላይ ቆሟል። ህዝብ ወደየቤቱ ተመልሷል። የፀጥታ ሃይሎች ግን ከአከባቢው አልራቁም።
አስተዳዳሪዎች ህዝቡን በፌደራል ፖሊስ አስከብበው ሲያስፈራሩት የዋሉ ሲሆን የህዝቡን ጥያቄ (ካሳ የመክፈሉ ጉዳይ) ለመመለስ ተስማምተዋል። ስለዚህ ህዝቡ በጠየቀው መሰረት መንግስት ተገቢውን ካሳ ይከፍላል። የታሰሩት የአከባቢው ኗሪዎች ግን አይፈቱም። ህዝቡ “የታሰሩትን ይፈቱልን” ብሎ ሲጠይቅ “እርምጃ እንወስድባችኋለን፣ ማንም መጥቶ አያድናችሁም” የሚል ማስፈራርያ ደርሷቸዋል። ስለዚህ መንግስት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የታሰሩትን ዜጎች ለመልቀቅ ዝግጁ አይደለም።
የመንግስት አካላት ህዝቡን ካሳ ለመክፈል ሲስማሙ የህዝቡን ጥያቄ ትክክለኛነት ተቀብለውና አምነው እንደሆነ አቅርበዋል። ጥያቄው ያነሱት ዜጎች ከእስር ለመፍታት ግን ፍቃደኛ አይደሉም። በትግራይ ዜጎች መብታቸው ሲጠይቁ ለእስር ይዳረጋሉ። የአፅቢ ወንበርታ ጠያቂዎች ምሳሌ ናቸው። ታሳሪዎች የዛሬን ጨምሮ ስምንት ናቸው።
ጥያቄ የጠየቀ ዜጋ ለምን ይታሰራል? ጥያቄ የመጠየቅ መብት የለውም? መንግስት የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ለምን ወደ ሃይል እርምጃ ይሄዳል? አምባገነኖች በራስ የመተማመን ባህሪ ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።
አብርሃ ደስታ
በቤተ ክርስቲያናችን ሸፍጥና ጉቦ ተንሰራፍቷል›› /ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/ ሰንበት ት/ቤቶቹ የአማሳኝ አስተዳዳሪዎችን ዶሴ ለፓትርያርኩ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፩፤ ቅዳሜ ጥር ፲ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በተንሰራፋውና ለዕድገቷ መሰናክል ኾኖ በተደነቀረው ሙስናና ሸፍጥ ላይ …![]()
ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ የሚሰማው የካህናቱና ምእመናኑ ጩኸት በርክቷል (ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፳፱ ጥር ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ መዋቅሯ ትክክለኛውን መሥመር ይዛ ወደ ቀደመ የቅድስናና ንጽሕና ክብሯ እንድትመለስ በአደረጃጀትዋና አሠራሯ ላይ እየተካሔደ የሚገኘው የተቋማዊ ለውጥ ጥናት፣ ‹‹ከጅምሩም የእኔ ጩኸት ነው፤ የእኔ አጀንዳ ነው፤ ዛሬ ከደረሰበትም ወደ ኋላ አይመለስም፤›› ሲሉ ፓትርያርክ …![]()
የወያኔን የሚዲያ አፈና ማመከን የጊዜው አጣዳፊ ተግባር ነው::
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የአገራችንን በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝባችን ስለራሱና ሰለአገሩ ምንም አይነት መረጃ ከአማራጭ የመገናኛ ብዙሃን ምንጮች እንዳያገኝ ያሉትን ዕድሎች በሙሉ ድርግም አድርጎ ዘግቶ ኖሮአል።
የወያኔ መሪዎችና ተሿሚዎች በየግላቸው ምንም ቁብ በማይሰጡትና ተቃዋሚዎች እንዲያከብሩት ነጋ ጠባ በሚወተውቱት የአገሪቱ ህገመንግሥት አንቀጽ 29 ዕውቅና ካገኙ የዜግች መብቶች አንዱ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ተፈጥሮአዊ መብት ሆኖ ሳለ እየተካሄደ ያለውን የሥልጣን ብልግናና አገሪቱን እያራቆተ ያለውን ዘረፋ በመተቸታቸው ብቻ በአንድ ወቅት እንደ አሸን ፈልተው የነበሩ የነጻ ጋዜጣ አዘጋጆችና አሳታሚዎች በሽብርተኝነት ተወንጅለው ከፊሉ ከአገር እንዲሸሽ ሌላው አፉን ዘግቶ እንዲቀመጥ አለያም የፈጠራ ክስ እየተመሰረተባቸው እስር ቤት እንዲማቅቁ ተደርገዋል። አሁንም በመደረግ ላይ ናቸው። በወያኔ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት አፈና የአሜሪካና የጀርመን መንግሥታት በየግላቸው የሚያስተዳድሩዋቸው የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮኖች እንኳ ከጥቃቱ ማምለጥ ስላልቻሉ እነሆ እስከዛሬ ያልተቋረጠ የማጥላላት ዘመቻ ይካሄድባቸዋል።
ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ከቻሉና ከየትኛውም መዲያ መረጃ የማግኘት መብታቸው ከተረጋገጠ ሥልጣን ላይ ውሎ እንደማያድር ጠንቅቆ የተረዳው የወያኔ አገዛዝ በዚህ የሚዲያ አፈና ተግባሩ በመቀጠል ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮን እንዲሁም ህዝብ አልፎ አልፎ ሃሳቡን ለመግለጽ በሚገለገልባቸው ጥቂት የአገር ውስጥ ህትመቶች ላይ የተለመደውን የጥቃት ጅራፉን ለማሳረፍ ታጥቆ ተነስቶአል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በመረጃና ደህንነት መሥሪያ ቤቱ ተዘጋጅቶ የህወሃት ቀድሞ ታጋዳላዮች በሚቆጣጠሩትና እንደግል ንብረታቸው በሚፈነጩባቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የተሰራጨው ዘገባ እንደሚያመለክተው ከአሁን ቦኋላ ማንኛዉም የመንግስት ባለስልጣን፤ የገዢዉ ፓርቲ አባላትና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ምንም አይነት ቃለመጠይቅ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ እንዳይሰጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአል። ማስጠንቀቂያውን ተላልፎ በተገኘ ማንም ሰው ወይም ድርጅት ላይ የአሸባሪነት ወንጀል ክስ እንደሚመሰረትበትም ዛቻና ማስፈራሪያ በተለመደው የቃላት ጋጋታ ተገልጾአል።
ይህ ከሰሞኑ የወያኔ ብሄራዊ መረጃ ደህንነትና ኮሚኒኬሽን መስሪያቤት ያወጣዉ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎች የሚናገሩትን ፤ የሚጽፉትን፤ የሚያነቡትንና የሚሰሙትን ብቻ ሳይሆን የሚያስቡትንና ሊደግፉት ወይም ሊቃወሙት ይችላል ተብሎ የሚጠረጠረውን ሁሉ አስቀድሞ ለመቆጣጠር ፍላጎቱ ያለው መሆኑን ነው።
ከሰሞኑ መግለጫ የተለየ ነገር ቢኖር ህዝባችንን በፍርሃት አንገት ለማስደፋት ሲባል የወያኔ ፓርላማ በሽብርተኝነት የፈረጀውን ንቅናቄያችንን ግንቦት 7ንና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንን በአንድነት የመፈረጅ ስልት ይፋ መደረግ መቻሉ ብቻ ነው።
የወያኔን ቁንጮዎች ጨምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይገነዘበዋል ብለን እንደምናምነው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት የተቋቋመው የአገራቸው ጉዳይ የሚያንገበግባቸው ቅን ዜጎች ባዋጡት የገንዘብ መዋጮና በሚሰጡት ያልተቋረጠ የእውቀትና የፋይናንስ ድጋፍ ነው። ተቋሙ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 22 አመታት በወያኔ የሚዲያ ሞኖፖሊ ተይዞ የኖረውን የአገራችንን አየር ክልል ሰንጥቆ በመግባት ህዝባችን ስለ አገሩና ስለራሱ ጉዳይ በቂ መረጃ እንዲያገኝ በመጣር ላይ ያለ ብቸኛ መገናኛ ብዙሃን ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኝ ነው።
ሃቁ ይሄ ሆኖ ሳለ ለምንድነዉ ታዲያ ላለፉት ሁለት አመታት ስብሀት ነጋን ጨምሮ የተለያዩ የገዢዉ ፓርቲ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ሳይቀሩ በተደጋጋሚ ቀርበዉ በስነ ስርኣት የተስተናገዱበትን ይህንን ሚዲያ የወያኔ ፓርላማ ቀደም ሲል በአሸባሪነት ከፈረጀው ንቅናቄያችን ግንቦት 7 ጋር መወንጀሉ ለምን ይሆን ? መልሱ ቀላል ነው። ከአገዛዙ ያልወገኑ ማናቸውም ሚዲያዎች እንደሚያደርጉት ኢሳት ስርጭቱን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነጋ ጠባ በኢትዮጵያ ቴለቪዥንና ሬዲዮ የሚደሰኮረው ልማትና ዕድገት ተጠቃሚው ሥልጣንን የሙጥኝ ያሉ የቀድሞ ታጋዳላዮችና የቅርብ ዘመዶቻቸው እንጂ ህብረተሰቡ አለመሆኑን በግልጽ ከማጋለጥ ባለመቆጠቡ ጥርስ ውስጥ ገብቶአል። ከዚህም በተጨማር ለምዕራባዊያን ፍጆታና ድጋፍ ማግኛ በየአምስት አመቱ የሚደረገው የምርጫ ተውኔት ወቅት ስለተቃረበ ተቃዋሚዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው በዚህ ሚዲያ ያብጠለጥሉኛል፤ የስልጣን ብልግናውንና የሙስናውን ጉዳይ ይዘከዝኩታል የሚል ፍርሃትና ስጋትም አለው። በእርግጥ ዝክዘካው በይስሙላ ምርጫው ላይ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ እኛ የጉዳዩ ባለቤቶች ቀርተን ምዕራባዊያን ለጋሾችም አያጡትም። ሆኖም ግን ወያኔ ፈርቶአል ተረብሾአል። ስለዚህም ኢሳትና አሁን በአክራሪ ድርጅቶች ልሳንነት የተፈረጁት የአገር ውስጥ ህትመቶች ከምርጫው በፊት መጥፋት ይኖርባቸዋል። ያ ካልሆነ በመላው አገሪቱ የሰፈነው የሥልጣን ብልግናና የሃብት ዘረፋ የፈጠረው የኑሮ ውድነት ያስመረራቸው ሚሊዮኖች የመጪውን ምርጫ ውጤት አስታከው ሆ ብለው አደባባይ ሊወጡና የአገዛዙን የሥልጣን እድሜ ለማሳጠር ተቃዋሚዎች ለሚያካሄዱት ትግል መሳሪያ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ተፈርቶአል። ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከብዙ የወያኔ ጥቃትና አፈና ተርፈው አገር ውስጥ በመታተም ላይ በሚገኙ 8 መጽሄቶች እና ለኢትዮጵያዊያን ብቸኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ በማገልገል ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ ላይ የተጀመረውን አዲሱን ዘመቻ በቸልታ አይመለከተውም።
መረጃ ሃይል ነውና አገራችን ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ሥር እየሰደደ የመጣው ድህነት እንዲቀረፍና ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የሚሻ ዜጋ ሁሉ ወያኔ በሚዲያ ላይ የጀመረውን ጥቃት ለማስቆም ከጎናችን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል።
ወያኔ በመረጃና ደህንነት መሥሪያቤቱ አማካይነት ያስተላለፈው የሰሞኑ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ በተለይም በሰላማዊና ህጋዊ ትግል ወያኔን መቀየር ይቻላል በማለት አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች መተንፈሻ ለማሳጣት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ህዝባችን እንዲረዳና በህዝባዊ እምቢተኝነት ሴራውን ለማክሸፍ መነሳት ጊዜው ግድ የሚል የወቅቱ አንገብጋቢ የትግል ጥሪ መሆኑን ግንቦት 7 የፍትህና የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያስገነዝባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የአማራ ክልል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ይኖራቸል ብለው የሚጠረጥሩትን ሁሉ እንዲይዙ ታዘዙ::
ባለፈው ወር በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር የተካሄደውን የብአዴን እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዞን እና የወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ኢህአዴግ አሸባሪ እያለ ከሚጠራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ በሚጠረጠሩት ወጣቶች ላይ የቁጥጥር ዘመቻ እንዲካሄዱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል።
ጥር 8፣ 2006 ዓም በሁሉም የአማራ ክልል ወረዳዎች በተደረገው የብአዴን ስብሰባ ላይ ወጣቶች መረጃ በማስተላለፍ እና ለአሸባሪዎች መሳሪያ የሚሆኑ ሰዎችን በመመልመል ላይ በመሆናቸው የግንኙነት ሰንሰለቱን ለመበጠስ አባላቱና አመራሩ ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው ተገልጾላቸዋል። እያንዳንዱ አባል በአሸባሪዎች ፕሮፓጋንዳ ሳይዘነጋ ጠንክሮ እንዲሰራም ትእዛዝ ተላልፎለታል።
“ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ወጣቶች ባላይ የአማራ ክልል ወጣቶች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ አለኝ” ያለው ኢህአዴግ በክልሉ እነዚህን ወጣቶች የመቆጣጠርና የመከታተል ዘመቻ በዘርፈ ብዙ ስልቶች ታጅቦ መካሄድ እንዳለበት አሳስቧል።
“በመሰረተ ቢስ አሉባልታዎች ከኢህአዴግ የኮበለሉና ወስጣቸው የሸፈተ የብአዴን አባላትም ሀቁን ተገንዝበው ከኢህአዴግ ጋር እንዲቀጥሉና ሀገሪቱን ወደ ላቀ እድገት እንዲያሸጋግሩ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊዎች በስብሰባው ላይ ተናግረዋል፡፡
የመወያያ አጀንዳዎች ትምህርትና የመኖሪያ ቤት ሊዝ ጉዳይ ቢሆኑም የስብሰባው ውሎ ግን ከአጀንዳዎች ውጭ አሸባሪዎች በሚሏቸው አካላት ላይ ነበር ያሉት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የድርጅት አባላት፣ መንግስት በመኖሪያ ቤት ሊዝ ያቀረበው ጉዳይ ግን ከፍተኛ ተቀዋውሞ አስነስቷል ብለዋል፡፡ ህጉ የማንንም ኢትዮጵያዊ ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ያላገናዘበ፣በአሰራር ውጣ ውረድ የተበተበና በዘፈቀደ እንዲወጣ የተደረገ ይመስላል ያሉት አባላቱ በተለይ የመንግስት ሠራተኞችን ከጨዋታ ውጭ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከብአዴን እየኮበለለ የሚጠፋውንና ለአሸባሪዎች መጠቀሚያ እየዋለ ነው ያሉትን ሃይል እንቅስቃሴ ለመግታት እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአማራ ክልል የሚገኙ ወጣቶችና የብአዴን አባላት ” ብአዴን የህወሀት በቅሎ መሆኑ ያብቃ” በማለት ጥያቄዎችን እያነሱ ነው።
በክልሉ ውስጥ የተንሰራፋው ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና አፈና መባባስ አባላቱን ለተስፋ መቁረጥ መዳረጉንም ወጣቶች ይናገራሉ።
አቡጊዳ – ርዮት አለሙ ጡቷ ላይ ቱመር አለ፣ ግን ክትትል አላገኝችም ! ሴፍ ዎርልድ ፎር ዎማን ( safe world for women) የተሰኘው ለሴቶች መብት የሚሟገተዉ ድርጅት፣ ርዮት አለሙ እንድትፈታ የሚጠይቅ ፔትሽኖች እያስፈረመ ነዉ። ድርጅቱ, የርዮት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጎቤዶን በመጥቀስ እንዳስቀመጠዉ፣ ርዮት አለሙ፣ በአንድ ጡቷ ላይ ቱመር ያለ ሲሆን ፣ ከጡቷም ደም እንደሚፈስ ይገልጻል። […]
ሁለተኛ መልስ ለኢሳቱ አቶ ፋሲል – ግርማ ካሳ ============================= ጤና ይስጥልኝ፣ ዉድ ወንድሜ አቶ ፋሲል። «የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና» በሚል ርእስ በጻፉት ላይ ለሰጠኹት አስተያየት፣ ለአንባቢያን ያቀረቡትን የመልስ መልስ አነበብኩ። ግሩም አቀራረብና ለዉይይት የሚረዱ ነጥቦች በማንሳትዎ ተደስቻለሁ። ዜጎች የተለያዩ ሃሳቦች ሊኗራቸው ይችላል። ብዙ ጊዜ፣ በተለይም በዳያስፖራ ፖለቲካ የተለመደው ፣ የሃሳብ ልዩነቶች በተፈጠሩ ጊዜ ያኛው […]
በሰንበት ት/ቤቶቹ የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ÷ የፓትርያርኩ ፀረ ሙስና መግለጫዎች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናት ተግባራዊነትና የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ የሚያሻው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ * * * የድጋፍ መግለጫ ስብሰባውን ለማሰናከል የሞከሩት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ፣ ሰንበት ት/ቤቶቹ ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጡ ድጋፋቸውን ለመግለጽና ስለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ …![]()
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጽቢ ወንበርታ ወረዳ በሩሃ ቀበሌ ከመስኖ ግድብ ጋር በተያያዘ ሃሙስ እለት የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ እስከ አርብ ምሽት የቆየ ሲሆን፣ የወረዳው የአስተዳደር ሰራተኞች እና የደህንነት ሀይሎች አመጹን የቀሰቀሱት እነማን ናቸው አውጡ በማለት ከህዝቡ ጋር እየተወዛገቡ ነው። ህዝቡ በበኩሉ ጥያቄው የህዝብ እንጅ የተወሰኑ ግለሰቦች ባለመሆኑ በግፍ የታሰሩት ሰዎች ይፈቱና …
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ወር በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር የተካሄደውን የብአዴን እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዞን እና የወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ኢህአዴግ አሸባሪ እያለ ከሚጠራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ በሚጠረጠሩት ወጣቶች ላይ የቁጥጥር ዘመቻ እንዲካሄዱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል። ጥር …
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቃቢ ህጎቹ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ መባረራቸው ተግልጿል። የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች እንደገለጹት ከ100 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ የተለያዩ የዲሲፒሊን እርምጃዎችን ወስደዋል። ከ40 በላይ በሚሆኑ የእስር ቤቶች ሃላፊዎች ላይም እንዲሁ የዲሲፒሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን 10 ከስራ ተባረዋል። ጉቦ መቀበል፣ ወገናዊነት፣ ፍትህ ማዛባት እንዲሁም እስረኞችን እየፈቱ መልቀቅ ከዋና ዋና …
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት እና በአማጽያን መካከል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ድርድር እንደቀጠለ ቢሆንም፣ ሁለቱም ሀይሎች በሚያቀርቡዋቸው ቅድመ ሁኔታዎች እስካሁን ውጤት አለመገኘቱ ታወቀ። አማጽያኑ የታሰሩት ባልደረቦቻቸው እንዲፈቱ፣ የዩጋንዳ ጦር አገሪቱን ለቆ እንዲወጣና የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያበቃ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡ ሲሆን፣ በመንግስት በኩል ደግሞ በአማጽያኑ የቀረቡትን በተለይም እስረኞችን መፍታት የሚለውን …
በኢትዮጵያ ዉስጥ በምርጫ ቢርድ ተመዝግቦ እየተንቀሳቀስ ያለው የሰማያዊ ፓርቲ ፣ በጎንደር ከተማ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እየተዘጋጀ እንደሆነ ፓርቲዉ በፌስ ቡኩ ገጽ ባወጣው መግለጫ ገለጸ። «ሕወሓት ኢህአዴግ በህገ ወጥ መንገድ ሉዓላዊ መሬታችንን ለሱዳን መንግስት አሳልፎ አሳልፎ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ህገወጥና ሀገር ቆርሶ የመስጠት ወንጀል በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ ጥር 25 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ታላቅ […]
News, Community Heroes or Call-in, Crossfire and African Topics
የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦመር ሓሰን አልበሺር፣ ለሶሳት ቀናት ጉብኝት ትላንት አስመራ መግባታቸው ተዘግቧል።
በሶሪያ እየተካሄደ ያለውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም በሚቀጥለው ሳምንት በጄኔቫ ሲውዘርላንድ በተጠራው የሰላም ውይይት የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች መሳተፍ አለመሳተፋቸውን ዛሬ ቱርክ ኢስታምቡል ላይ የተሰበሰበው የተቃዋሚዎች ህብረት ይገልፃል ተብሎ ይጠበቃል።
በደቡብ አፍሪቃ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪቃ ዋንጫ ሻምፒዎና እንደቀጠለ ነው።
ሰሞኑን በሕንድ አንዲት ጀርመናዊት ወጣት እና ዴንማርካዊት እዛው ህንድ ውስጥ ተደፍረው ጉዳያቸው እያነጋገረ ይገኛል። በሕንድ ስለደረሱት የአስገድዶ መድፈር እና በኢትዮጵያ የሚደርሱ የወሲብ ጥቃቶች እንዲሁም ያለውን የፍትህ አሰራር በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንቃኛለን።