አቡጊዳ – ሌንጮ ለታ ኖርዌይ እንጂ አዲስ አበባ አይደሉም አሉ – አቶ ሌንጮ ባቲ
አዲስ አድማስ አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ ገቡ ብሊ በዘገበዉ «አንጻር የአዲስ አድማሱ ዘገባ፣ በቀጥታ አቶ ሌንጮ ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ ከሰጡት ጋር የሚቃረን ሲሆን፣ ጉዳዩን በትክክል ለማጣራት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።የአቶ ሌንጮ የጀርመኑ ቃለ ምልልስ ወይንም የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ ትክክል መሆኑ የሚያመላከት መረጃ እንዳገኘን ለአንባቢያ ግልጽ እናደርጋለን”” ብለን ነበር።
አቶ ሌንጮ ለታ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የኦዴፍ ሌላዉ የአመራር አባል፣ አቶ ሌንጮ ባቲ፣ ከሚኒሶታ ለዘበሃሻ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ አቶ ሌንጮ ለታ ደዉለው እንዳነጋጋሯቸውና፣ አዲስ አበባ ናቸው የተባለው ወሬ ፍጹም ዉሸት መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ሌንጮ ለታ በጀርመን ድምጽ ራዲዮ እንደተናገሩት፣ ከጅምሩ ድርጅቱን ስቋቁም በሰላም አገር ዉስጥ ገብቶ ለመታገል ፍላጎት እንደነበራቸው ይሄን ያኔም ይፋ እንዳደርጉ የገለጹት፣ አቶ ሌንጮ ባቲ፣ «አገር ቤት ስንገባ በግልጽ እንጂ በድብቅ አይደለም» ሲሉ ነበር ለዘሃበሻ የገለጹት።