ሽንፈትን መቀበል ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ ሽንፈትን ለመቀበል ዝግጁ የሆነ ሲያሸንፍ ጉራ አይነዛም፡፡ንቅዘት ብቻ ነው ጉዞው፡፡ የዓለም ታላቅ ኃይለም ያሸንፍ አገራዊ ኃይል፤ በምን ሁኔታ አሸነፈን እንጂ፤ አልሸነፍም ማለትን መመርመር አለብን፡፡ የማረከውን ሰው በሰብዓዊ መንገድ ለመያዝ የሚችል ተዋጊ ጀግንነትን ከጭካኔ በመለስ ማየት አይሳነውም፡፡ ምህረት ለማድረግም ፍርሃትና ሥጋት አይኖርበትም፡፡ “የተጠማ ከፈሳሽ፣ የተበደለ ከነጋሽ” የሚለው ምሣሌያዊ አነጋገር በቀላሉ ይገባዋል፡፡ ምርጫ፣ በተለይም በአገራችን፣ በሚካሄድበት ጊዜ የሚያጋጥመን የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽ፤ 1ኛ/ የተሸናፊው ሽንፈትን አለመቀበል እና 2ኛ/ የአሸናፊው ዘራፍ ባይነት ነው፡፡ ይህ ማለት ከምርጫው በኋላ አሸናፊና ተሸናፊ አይጥና ድመት ናቸው ማለት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ዐይን መተያየት ቀርቶ እንደ ዜጋ መተሳሰብም ይቀራል፡፡ “የማትወልደውን ሶሻሊዝም ሲያማምጡዋት፤ ከነ ካፒታሊዝሟም አስወረዳት!” እንደተባለው ነው፡፡ አዲስ ሥርዓት መፍጠር ቀርቶ አሮጌውንም ማጣት አለ፡፡ ቁልቁል ማደግ የሚባለው ዓይነት!

ዲሞክራሲ በምርጫ ሳጥን ብቻ ሳይሆን፤ በኑሮአችን ድርና ማግ ውስጥ ሁሉ የሚኖር መሆን አለበት፡፡ ሁሉን ጐራሽ የሆነ አሠራር ከተከተልን ፖለቲካውም ሆነ ባህሉ ልሙጥ ይሆናል፡፡ ይህም ህዝብን ሽባ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ይሰውረን፡፡ ሥልጣንን ማጋራት፣ ሥራን ማከፋፈል ይቻለን ዘንድ ትምህርታችንን ይግለጽልን! የችግር ጊዜ ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ፡፡ የላዩ ታች የታቹ ላይ ቦታ ሊቀይር ይችላል፡፡ በደስታው በተድላው ጊዜ የሚደረገው ሁሉ ይቀራል፡፡ ድህነት ጥላውን ሲጥል ማጀት ጓዳው መራቆቱ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብም ይራቆታል፡፡ ዕምነት ይመነምናል፡፡ ጀግንነት ይኮሰምናል፡፡ ቆራጥነት ይከሳል፡፡ የሌለው ላለው ያድራል፡፡ ተገዢ ገዢውን ከልኩ በላይ እጅ ይነሳል፡፡ አድር ባይነት የዕለት የሠርክ ጉዳይ ይሆናል፡፡

ሁሌ በተለመደው የፖለቲካ መንገድ መሄድ ለህዝብ ዕድል አይሰጥም፡፡ ሌላው ይቅርና ለፖለቲከኛው ለራሱም ዕድል አይሰጥም ፡፡ እስከንቅዘት ብቻ ነው ጉዞው፡፡ ወደ አዲስ አይን መክፈት አያመራም፡፡ የትኛውም ዘመን በየትኛውም ፓርቲ አንድና አንድ መንገድ ብቻ ልከተል ባለ ሰዓት የሚከሰት ችግር ነው፡፡ የታየ፣ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው!! “እወርካ ሥር የገደለ፣ ዘወትር እወርካ ሥር ያደፍጣል” የሚባለው እንዲህ ሲሆን ነው! ጦርነት ሰልችቶናል፡፡ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ጦርነታችን ብዙ ሰው አልቆብናል፡፡ ብዙ ንብረት ወድሞብናል፡፡ ኢኮኖሚያችን ደቅቋል፡፡ ስለዚህ ሌላ ጦርነት ይጎዳናል እንጂ ምንም አይፈይደንም!

እንቢኝ ለመብቴ እንታገላለን ያሉት የደሴ ሙስሊሞች ደሴን በበራሪ ወረቀት አሸብርቀዋት አደሩ::

መንግስት የደሴን ሙስሊም በሀይል ቀጥቅጨ ተቆጣጥሬዋለሁ ብልም ፉከራውን መና የሚያሰቀር ሁኟን:: በተያያዘ ዜናም በዚሁ ድርጊት የተደናገጡት የመንግስት ደህንነቶች እና አቀንቃኝ ካድሬወች በሌሊቱ ተነስተው በስራ ተጠምደው እንዳደሩም ለማወቅ ተችሏል::

በበራሪ ወረቀቱ ላይ ጎልተው ከሚታዩት መፈክሮች መካከል 1.ኮሚቴወቻችን ወንጀለኝ አይደሉም ንፁህ ናቸው ይፈቱልን 2.መንግስት በሙስሊም እና ክሪስቲያን መካከል ግጭት ለመፍጠር ድራማ እየሰራ በ Etv የሚያቀርበው ፕሮፓጋንዳ ይቁም 3.አሸባሪ አይደለንም 4.ትግሉ ይቀጥላል 5.ድምዻችን ይሰማ እና ኮሚቴው በፍጥንነ ትይፈታ አለያ አንደራደርም የሚሉት ይገኙበታል::

የደሴ ሙስሊም በኮሚቴወቹ ላይ መንግስት የጥፋት እጁን ከሰነዘረ እንደማይደራደሩ ዛሬ ተበትኖ ባደረው 50000 ሺ በራሪ ወረቀት አስረግጦ አሳስቧል:: ሲቀጥልም ዱላ እስር እና ግድያ የማይበግረው የደሴ ሙስሊም ትግሉ እስከ ድላችን ድረስነው በቀይ ይሰመርበት ሲሉ አሳስበዋL:: ድል ፍትህ ለተጠማው ሙስሊም አላህ አክበር!

አንደኛው መስከረም ጠብቶ ሌላኛው መስከረም እስኪጠባ ድረስ ባሉት የ365.25 ቀናት ውስጥ ስንት ጉድ መስማት እንዳለብን የሚጠቁም አሃዛዊ መረጃ ሊኖር እንደማይችል መቼም ግልጥ ነው፤ ነገር ግን የዘመናችን ኢትዮጵያ የታሪክ ጎርፍ ያመጣብን ከወያኔና መሰሎቹ በስተቀር ሌሎቻችን ያልጠበቅነው ዱብዕዳ ክስተት ምሥጋና ይንሳውና በዬቀኑ የማንሰማውና የማናየው ዕንቆቅልሽ እንዳይኖረን ሆነናል፡፡ በዚህ መልክ በተለይ ባለፉት 22.8 ዓመታት ውስጥ የታዘብነው የታሪክ ምፀትና […]

የሰማያዊ ፓርቲ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ መሰረት፣ ቅዳሜ ጥር 17 ቀን በፓርቲዉ ጽ/ቤት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ የዉይይት መድረክ አዘጋጅቷል። « ድንበራችንን ጉዳይ በተመለከተ በተጨባጭ መረጃ በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ይፈጠር ዘንድ ትምህርታዊ ውይይት መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይም በዘርፉ ለረጅም አመታት በመስራት የሚታወቁት የረጅም ጊዜ የጆግራፊ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ድንበሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ […]

የአንድነት ፓርቲ በሱዳን ድንበር ጉዳይ፣ ተደረጉ እየተባለ ያሉ ስምምነቶች ዙሪያ ለአማራዉ ክልል አስተዳዳሪ እንዲሁም ለጠቅላ ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ማብራሪይ መጠይቁ ይታወሳል። እንኳን አንድ በአገሪቱ ያለ አብይ የፖለቲክ መሪ ቀርቶ፣ማንም ዜጋ በአገር ጉዳይ ላይ ጠያቄ ጠይቆ፣ ለጠያቄው ማብራሪይ የመቀብል መብት እንዳለዉ ቢታወቅም፣ የክልሉም ሆነ የፌደራል አስተዳዳሪዎች የሕዝብንም ሆነ የአንድነት ፓርቲን ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብልዉታል። የሱዳን […]

«አባቶቻችን በደምና በጥንታቸው ገትረው ያቆዩልንን መሬት ስንዝር አናሳልፍም» በሚል መርህ የሰማያዊ ፓርቲ በጎንደ ከተማ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ ጠርቷል። ሰልፉ የሚደረገዉ እሁድ ጥር 25 ቀን ሲሆን፣ ቦታውም በጎንደር መስቀል አደባባይ እንደሚሆን የሰማያዊ መግለጫ ይጠቁማል። ሰማያዊ ሌሎች የሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ድርጅቶ እንዲተባበሩ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ የአደባባይ ጥሪ ከማስተልለፍ ባሻገር፣ ምን ያህል ግን ሰልፉን በጋራ ለማቀናጀት ከሌሎች […]

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ባለፉት 15 ዓመታት ከኤጀንሲው ፈቃድ የወሰዱ 6ሺህ 500 ፕሮጀክቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ ወደሥራ ባለመግባታቸው የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸውን ለመሰረዝ መወሰኑ ታወቀ፡፡ በዚሁ መሠረት 2 ሺህ 500 ፕሮጀክቶች ፈቃዳቸው እንደሚሰረዝ ታውቋል፡፡ ከኤጀንሲው የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የቱርክ፣የሕንድና የቻይና ባለሃብቶች በአገሪቱ በግብርና በማኒፋክቸሪንግ እና …

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አባይ ወንዘን ተንተርሶ በሱዳናዊው ባለሀብት የተቋቋመው የስጋ ፣ የዶሮ፣ የዘይት፣ የአትክልትና ፍራፍሮ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ላለፋት አምስት ዓመታት የተወራለትን ያህል ማምረት እና ማሰራጨት ባለመቻሉ   የክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቤሮ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ ወስኗል። የከተማ አሰተዳደረም ቦታውን  ለሌላ አልሚ እንዲሰጥ ታዟል፡፡ የክልሉ መንግስት ለሱዲናዊው ባለሃብት ሚ/ር አሽራፍ፣  …

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከለጋሽ አገሮች ባገኘው ድጋፍ ተመስርቶ የውጭ ባለሀብቶችን በማሳተፍ ባስደረገው ጥናት የመንግስት ግዢዎችና ኮንትራቶች ግልጽነት የጎደላቸው መሆናቸውን አረጋግጧል። የውጭ ባለሀብቶች አራት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ሙሰኞች ብለው እንደፈረጁዋቸው ሪፖርተር ዘግቧል። 71 በመቶ የሚሆኑ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ቢዝነስ ለማቀላጠፍ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። ባለሀብቶቹ በዋናነት ያነሱትም ሙስና …

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ ባለስልጣናት የአባይን ግድብ በተመለከተ ከኢትዮጵያና ሱዳን  ጋር ሲያደርጉት የነበረውን ድርድር ካቋረጡ በሁዋላ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች ለጋሽ አጋራት ለመውሰድ መወሰናቸውን የግብጽ ባለስልጣኖች መናገራቸውን ተከትሎ ግብጽ በየትኛውም መድረክ ብትሄድ ምንም የምታመጣው ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እየተናገሩ ነው። አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን የመንግስትን ባለስልጣናት በመጥቀስ  …

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶሪያ መንግስት እና የተቃዋሚዎች ተደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ የተሰበሰቡ ሲሆን ፣ሁለቱም ተደራዳሪዎች ከማለዳው ሃይለ ቃሎችን ተለዋውጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለቱም ተደራዳሪዎች ወደ ገንቢ ውይይት እንዲመጡ ቢጠይቁም እስካሁን ተስፋ የሚሰጥ ነገር አልተገኘም። አንዱ እና ዋናው አጀንዳ ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ ስልጣን ላይ ስለመቆየታው ሲሆን፣ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ …

ከኣንድ ወር በላይ ለዘለቀውና ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞቱበት የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ውጊያ መፍትሄ ለመሻት ነገ ሐሙስ እዚያው ደቡብ ሱዳን ር/ከተማ ጁባ ውስጥ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የምስራቅ ኣፍሪካ የልማት ቤይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ አባል ሓገራት መሪዎች ጉባዔ ቢሰረዝም የሰላም ጥረቱ ግን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት አሁን ጦሩ በአሚሶም ዕዝ ሥር የተጠቃለለዉ በጋራ መንቀሳቀሱ የጦሩን ተዕልኮ ከግብ ለማድረስ ጠቃሚ በመሆኑ ነዉ።የወጪ ጉዳይም ከግምት የሚገባ ነዉ።አሚሶምን የተቀየጠዉ የኢትዮጵያ ጦር አራት ሺሕ ወታደሮች አሉት።

የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን ኣልበሺር በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ኣጎራባች ኣገሮች ግንኙነት ከማጎልበት ጎንለጎን በአካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ።

ኣልበሺር ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት የሶስት ቀናት ቆይታ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ

ከኣንድ ወር በላይ ለዘለቀውና ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞቱበት የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ውጊያ መፍትሄ ለመሻት ነገ ሐሙስ እዚያው ደቡብ ሱዳን ር/ከተማ ጁባ ውስጥ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የምስራቅ ኣፍሪካ የልማት ቤይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ አባል ሓገራት መሪዎች ጉባዔ ቢሰረዝም የሰላም ጥረቱ ግን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ግንባታ ማንኛውንም ዓይነት ሕግ የጣሰ አይደለም በማለት መንግሥት የግብፅን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡

አል ሞኒተር የተባለ የግብፅ ሚዲያ የተለያዩ የአገሪቱ ባለሥልጣናትን በመጥቀስ፣ ግብፅ በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ተቃውሞ ዓለም አቀፍ ማድረግ እንደምትፈልግ ዘግቧል፡፡

‹‹የህዳሴው ግድብ አሁን ባለው የግንባታ ደረጃ ተገንብቶ ዕውን የሚሆን ከሆነ በግብፅ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከባድ ነው፡፡ በመሆኑም ጉዳዩን ወደሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መውሰድ እንደሚገባ፣ ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው፤›› ያሉት የአገሪቱ የመስኖና ውኃ ሀብት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ካህሊድ ዋሲፍ ናቸው፡፡

‹‹ግብፅ የህዳሴው ግድብ ግንባታን ፈፅሞ አትፈቅድም፡፡ ይህንን ለማሳካትም ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የውጭ ዕርዳታ ለግድቡ እንዳታገኝ ግፊት እናደርጋለን፤›› ሲሉ በይፋ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ የኢትዮጵያን ግድብ በማውገዝ ከግብፅ ጐን እንዲቆም አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ በዓለም አቀፍ ሕግ የተከበረና የተረጋገጠ መብት አላት፡፡ ነገር ግን ይህ የግብፅ መብት በኢትዮጵያ እየተጣሰ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ሕጋዊ መብት አላት የሚሉት ቃል አቀባዩ፣ ማናቸውም የተፋሰሱ አገሮች ተፋሰሱን በመጠቀም ወደ ልማት መግባት ሲፈልጉ በቅድሚያ ግብፅን የማማከርና ይሁንታ የማግኘት ግዴታ አለባቸው ሲሉ የአገራቸውን አቋም አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን ግዴታ በመጣስ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ መጀመሯ በራሱ ሕግን የጣሰ መሆኑን፣ ነገር ግን የግብፅ መንግሥት ጉዳዩን በወዳጅነት በመያዝ ሲወያይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ምንም ዓይነት ጉዳት በግብፅ ላይ እንደማያደርስ ኢትዮጵያ ለማረጋገጥ እንቢተኛ በመሆኗ ግብፅ ከውይይቱ ራሷን እንዳገለለች አስረድተዋል፡፡

የግብፅ የቀድሞ የመስኖና የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሙሐሙድ ናስር አል ዲን አላም በበኩላቸው፣ ግብፅ ከዚህ በኋላ በህዳሴው ግድብ ላይ ሌላ አማራጭ የላትም ብለዋል፡፡ የቀረውና በፍጥነት ተግባራዊ መሆን የሚገባው አማራጭ ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው ማድረግ፣ በዋናነትም ይፋዊ ቅሬታና ተቃውሞ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማቅረብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

‹‹ማንኛውም የዓባይ ተፋሰስ ተጋሪ አጋር በወንዙ ላይ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የግብፅን ይሁንታ ማግኘት አለባት የሚለው ስምምነት ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለው ነው፤›› በማለት የሚከራከሩት የቀድሞው ሚኒስትር ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት በመጣስ ለጀመረችው ግንባታ በተባበሩት መንግሥትት ድርጀት ልትጠየቅ ይገባታል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል አሁን ያለውን አለመግባባት በተመለከተም ዓለም አቀፍ እውነት አፈላላጊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ማጥናት ይኖርበታል በማለት ተከራክረዋል፡፡

የግብፅ ባለሥልጣናት እያንፀባረቁት ስላለው አዲስ አቋም የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ፣ ‹‹ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ውል አይመለከታትም፣ ምክንያቱም አልፈረመችም፤›› ሲሉ የግብፅ ባለሥልጣናት መግለጫን አጣጥለዋል፡፡ የቅኝ ግዛት ውሉ የተፈረመው በግብፅና በእንግሊዝ መካከል መሆኑን ያስታወሱት አቶ ፈቅ፣ እንግሊዝ ቅኝ የገዛቻቸውን ኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ በመወከል ስምምነቱን ፈርማለች፡፡ ይህ ግን ኢትዮጵያን ፈፅሞ አይመለከትም ብለዋል፡፡

የግብፅ የቀድሞው የመስኖና የውኃ ሀብት ሚኒስትር በተደጋጋሚ ይህንን መሳይ ነገር ያነሳሉ በማለት ያስታወሱት አቶ ፈቅ፣ ‹‹ሰውዬው ከሳይንስ ውጭ ነው የሚናገሩት፣ ከእሳቸው የሚጠበቅ አይደለም፤›› ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ የጀመረችው የህዳሴው ግድብ ግንባታ የትኛውንም ዓለም አቀፍ ሕግ የጣሰ አይደለም፡፡ ወደፈለጉበት ቢሄዱ የሚመጣ ነገር የለም፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡ ጉዳዩን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ መምራት ሊያተርፍ የሚችለው በሁለቱ አገሮች ያለውን የትብብር መንፈስ ማጥፋት ነው ሲሉ የግብፅ ባለሥልጣናትን የሰሞኑን ዘመቻ አውግዘዋል፡፡ Reporter

ከኡጋንዳ ኢንቴቤ ተነስቶ ወደ ሰንዓ የመን በመብረር ላይ የነበረ ንብረትነቱ የዩክሬን የሆነ አንቶኖቭ 28 የመንገደኞች አውሮፕላን ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ አቅራቢያ ለገዳዲ አካባቢ ተከሰከሰ፡፡

ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ የአውሮፕላኑ አብራሪዎች ሰኞ ማለዳ ከባለሥልጣኑ ጋር ባደረጉት የሬዲዮ ግንኙነት ከኢንቴቤ ተነስተው በኢትዮጵያ በኩል ወደ የመን ለመብረር ፈቃድ ጠይቀው ነበር፡፡ ባለሥልጣኑም የበረራ ፈቃድ ሰጥቷቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ኤር ናቪጌሽን ክፍል ለአብራሪዎቹ የሚበሩበትን ከፍታ ሰጥቷቸዋል፡፡ አውሮፕላኑ የኢትዮጵያን አየር ክልል አቋርጦ በማለፍ ላይ ሳለ አዲስ አበባ አካባቢ ሲደርስ የሞተር ብልሽት ያጋጥመዋል፡፡ ይህንኑ ለአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ መቆጣጠሪያ ማማ አሳውቆ ‹‹ኢመርጀንሲ ላንዲንግ›› እንደሚያደርግ (በድንገተኝነት እንደሚያርፍ) ሪፖርት አድርጐ፣ ከጠዋቱ 3፡35 ሰዓት ላይ ለማረፍ ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በማምራት ላይ ሳለ ለገዳዲ አካባቢ ተከስክሷል፡፡

አደጋው እንደደረሰ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፈልጐ ማዳን ቡድን ወደ ሥፍራው ተንቀሳቅሶ የአውሮፕላኑ አብራሪዎችን ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ሕክምና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፋሪዎች እንዳልነበሩ ታውቋል፡፡ በአደጋው አብራሪዎቹ የተጐዱ ቢሆንም፣ ሕይወቱ ያለፈ ሰው እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአውሮፕላን አደጋ መከላከልና ምርመራ ክፍል ባለሙያዎች የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ምርመራ ጀምረዋል፡፡ ባለሙያዎቹ አውሮፕላኑ ወደ ወደቀበት ሥፍራ በማምራት መረጃ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሩሲያ ሰራሽ የሆኑ አንቶኖቭ አውሮፕላኖች ከተመረቱ ረዥም ጊዜ ያስቆጠሩ በመሆኑ በየጊዜው እክል እየገጠማቸው በተለያዩ አገሮች በመከስከስ ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ ዕድሜ ጠገብ አውሮፕላኖች ዋጋቸው ርካሽ በመሆኑ በአፍሪካ አገሮች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ያረጁ በመሆኑና ተገቢ የሆነ ጥገና ስለማይደረግላቸው በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በተደጋጋሚ አደጋ እንደሚያደርሱ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ Reporter

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሁለተኛው ‹‹የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት›› ዘንድሮ በመጋቢት ወር መጨረሻ ይከናወናል፡፡ ለሀገሪቱ በጎ ሠርተዋል የሚሏቸውን ሰዎች ይጠቁሙ፡፡ ለጥቆማ የሚረዷችሁ ነጥቦች

  1. ለሀገር ሰላም፣ ለሕዝቦች መቀራረብና መደጋገፍ፣ ለውጥ አምጭ አስተዋጽዖ ያደረጉ፣

  2. በበጎ አድራጎትና ሰብአዊ ተግባራት ተሠማርተው የሰው ልጅን ሕይወት የለወጡ፣

  3. በሥነ ጽሑፍ፣ በኪነ ሕንጻ፣ በሥነ ጥበብና በመሳሰሉት መስኮች ለኢትዮጵያውያን የሚጠቅሙ፣ የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉ፣ የሀገሪቱን ሥነ ጥበብ ወደ አንድ የላቀ ደረጃ የሚያደርሱ ሥራዎች የሠሩ፣

  4. በግብርና፣ በቢዝነስ፣ በኢንዱስትሪና በመሳሰሉት መስኮች አዲስ፣ የራሱ ወጥነት ያለውና ያልተደፈረ የሚመስለውን ሥራ ያከናወኑ፣ ለሀገሪቱ ዕድገትና ሥልጣኔም ለውጥ አምጭ አስተዋጽዖ ያደረጉ፣

  5. በጋዜጠኛነት መስክ ተሠማርተው ሙያውን የጠበቀ፣ ለሌሎች አርአያ የሚሆን፣ የሕዝቡን ኑሮ የሚለውጥ ሥራ ያከናወኑ፣

  6. በዲፕሎማሲው መስክ የሀገሪቱን ክብርና ደረጃ ያስጠበቁ፣ የሀገሪቱንም መብት ያስከበሩ፣

  7. በመንግሥትና በሥራ ተቋሞቻቸው የተሰጧቸውን የተለያዩ ሀገራዊ ግዳጆችን በብቃት የተወጡ፣ መሥዋዕትነት የሚጠይቁ ተልዕኮዎችን ያከናወኑ፣ ለትውልድ አርአያ የሚሆኑ ብቁ አመራሮችን የሰጡ፣ በአመራሮቻቸውም ድርጅታቸውንና መሥሪያ ቤቶቻቸውን የለወጡ፣

  8. ሀገራዊ ዕውቀቶችን በማስተማር፣ ቅርሶችንና ባህልን በማስጠበቅና በመከባከብ ለውጥ አምጭ ተግባር ያከናወኑ፣

  9. በጥናትና ምርምር መስክ ተሠማርተው ችግር ፈች የሆኑ ውጤቶችን ያስመዘገቡ፣

  10. በማስታረቅ፣ ግጭቶችን በመፍታት፣ ሀገራዊ የሽምግልና ሥራ የሠሩ፣

  11. በሌሎችም መስኮች የሚጠቀስ፣ ለሀገር የሚጠቅም፣ ለትውልድ አርአያነት ያለው፣ የሀገርን ክብር የሚጨምር፣ ታሪክና ማንነትን የሚያጎላ ተግባር ያከናወኑ ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜጎችን ይጠቁሙ፤

 ማስተዋሻ
    • የሚጠቁሟቸው ኢትዮጵያውያን በተቻለ መጠን ከዚህ በፊት ያልታወቁና ይህን መሰል ዕድል ያላገኙ ቢሆኑ ይመረጣል፣

    • በተቻለ መጠን ከአዲስ አበባ ወጣ ባሉ ቦታዎች ሰው ሳውቃቸው ለሀገራቸው አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ዜጎችን በመጠቆም ይተባበሩ፣

    • ሲጠቁሙ የጠቆሙትን ሰው ስም፣ ያለበትን ቦታ፣ የሠሩትን በጎ ሥራ ዘርዘር አድርገው ይግለጹ፣ ከቻሉም ስልካቸውን ወይም ኢሜይላቸውን ይላኩልን፣

    • ጥቆማውን እስከ የካቲት 15 ቀን 2006 ዓም ያድርጉልን

    • ከሀገር ውጭ ሆነው ሀገራዊ ሥራዎችን የሚሠሩና ሀገራቸውንንና ሕዝባቸውን የሚጠቅሙትን በጎ ዜጎች እንጠቁም

    • ከጥቆማው በኋላ የተቋቋመው ኮሚቴ ሃያ አምስት ዕጩዎችን ይጠቁማል፤ በእነዚህ ዕጩዎችም ላይ ከተለያየ ሙያ፣ መስክ፣ ዕድሜ፣ እምነት፣ አካባቢ፣ የዕውቀት መስክ የተወጣጡ ነገር ግን እርስ በርሳቸው የማይተዋወቁ 100 ሰዎች ድምጽ ይሰጧቸዋል፡፡ በእነዚህ ሰዎች ድምጽም የመጨረሻዎቹ አምስት ሰዎች ይመረጣሉ፣

    ለመጠቆም ይህንን የኢሜይል አድራሻ ይጠቀሙ  [email protected]

    ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው የሠሩትን ዜጎቻችንን እናበረታታ፣ እንሸልም፣ ዕውቅና እንስጥ

    በምስራቅ ሃረርጌ ከ59 ሰዎች በላይ መገደላቸውን መንግስት ግጭቱን ሆን ብሎ መቀስቀሱን የኦሮሞ ጥናት ማህበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ገለጡ:: የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ኢሌሞ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ጥቂት ወራት በአንያ፣ ማቶ እና ሙለቄ ቆላማ ወረዳዎች ላይ በፌደራል መንግስቱ እውቅና የተቋቋመውና ስልጠና የሚሰጠው ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ሃይሎች በኦሮሞዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት 59 ገድለው፣ 42 አቁስለዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከልም ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል።

    “በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ሰላም ካገኙ ለተቃዋሚዎች ምቹ ቦታ ሊፈጥሩ ይችላል በሚል እሳቤ የሁለቱን ክልል ህዝቦች እያጋጨና እርስበርስ ተጠባብቀው እንዲኖሩ ለማድረግ ” መንግስት ግጭቱን ሆን ብሎ መቀስቀሱን የገለጡት ዶ/ር ኢብራሂም ፣ በግጭቱም እድሜውን ለማራዘም እንደሚያስብ ተናግረዋል። ማህበሩ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ለሌሎችም አገራት ደብዳቤ ማስገባታቸውን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል ። ኢሳት ዜና

    ምንሊክ ሳልሳዊ
    እኛ ሃገራችንን የምንወድ ኢትዮጵያን ስለ ፖለቲካ ድርጅቶች አያገባንም::እንዲያድጉ እንዲለሙ እንዲመነደጉ እናበረታታለን እንጂ በነዙ ስትራቴጂ አልባ ድፍን ደረቅ ፖለቲካ ውስጥ ገብተን አብረን በጭቃቸው መቡካት አንፈልግም::የወደደ ይውደድ የጠላ ይጥላ እትዮጵያ ውስጥ ወያኔን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ጎራ ጥያቄው የስልጣን እና የአገዛዝ ሩጫ ነው::የእኛ የዜጎች ጥያቄ ግን ፍትህ መልካም አስተዳደር የአገልግሎት አቅርቦት እና ሰላም ነው::

    ወያኔ የሚያደፈርሳቸው ተቃዋሚ ነን የሚሉትም በአቅማቸው የሚያደፈርሷቸው ሰላሞቻችን ይመለሱልን::ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የሚበጅ አስተዳደር ለማምጣት መጀመሪያ የህዝቦች ጥያቄ መመለስ የለውጥ እርምጃ መምጣት አለበት::
    ለዘላቂ ልማት እንሰራለን በሚል ስርኣት ውስጥ የመሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች በጊዜያዊነት መኖር እና እንደመነገጃ መጠቀም ህዝብን አገለግላለሁ ሳይሆን አጭበረብራለሁ እንደማለት ይቆጠራል:: የወያኔ ስርኣት ባለስልጣናት በፍርሃት ተውጠው በሚኖሩባት በዚች ኢትዮጵያችን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አሁንም እጅግ መልስ የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው::ዜጎች በሃገራቸው እንዳይኮሩ በመኖር ደህንነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ እየተደረገ ስለሆነ ይህ ደሞ ወያኔ በዘላቂነት የያዘውን ስልጣን ላለመነጠቅ የሚሰራው ፖለቲካዊ ደባ ውጤት መሆኑ እሙን ነው::

    ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን ወደ እውነት ያመጡ ህጎች በኢትዮጵያ አሉ የሚለው ወያኔ ህዝቦች ግን በተግባር ተጠቃሚ ሲሆኑ አላየንም::ህጎቹ በተግባር ይዋሉ ይህንን ህጎች በመመሪያ በደብዳቤ እና በስልክ የሚቀይሩ የሚደፈጥጡ በጥቅም የሚሸጡ የሚረጋግጡ የሚለውጡ ከየወንበራቸው ተሽቀንጥረው ይጣሉ:: የቀን ተቀን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ሂደት ውስጥ እጃቸውን እያጠለቁ ፍትህን የሚያዛቡ አስተዳደራዊ በደሎችን የሚፈጽሙ ባለስልጣናት የህዝብን ማህበራዊ ህይወቶች ከማፋለሳቸውም በላይ ፖለቲካው እንዲጭበረበር ኢኮኖሚው እንዲደቅ ሃገር በብድር እንድትዘፈቅ ህዝብ እንዲደኽይ ከባዱን ሚና እየተጫወቱ ነው::

    ህዝቦች ህግ እየጸደ ህግ እየተሽሞነሞነ እና እየተብለጨለጨ ቢቀመጥ ምንም የሚጠቅማቸው ነገር እንደሌለ መታወቅ ያለበት ሲሆ አንድ ህዝብ ባላረቀቀ ባልተወያየበት እና ባላጸደቀው ህግ እየተገዛ ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እንዴት ማስፈን ይቻላል??? መተማመን እና የዜግነት ኩራቱን በሚሰብሩ ባለስልጣናት እየተሰበረበት ያለ ህዝብ ፍትህን እና አስተዳደራዊ እንዲሁም አገልግሎቶችን በተግባል ለማየት እና ለመጨበጥ አልቻለም:: ለተበደለና ፍትሕ ላጣ ዜጋ፣ መልካም አስተዳደር አጥቶ ለሚንገላታ ዜጋ ፍትሕና መልካም አስተዳደር እንዲኖር በአንቀጽ ተደንግጓል እያልን ብናወራ ዋጋ የለውም::

    ህዝብ ባለው ስርኣት ላይ እምነት የለውም:; ይህ ደግሞ ራሱ ስርኣቱ ያረጋገጠው ነገር ነው ኢትዮጵያውያን የስርኣቱ ታጣቂ ሃይሎች በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚያደርሱትን የሰብኣዊ መብት ጥሰት እያዩ በሃገሪቱ ህግ የለም እኔም ነገ እደበደባለሁ እታሰራለሁ ንብረቴን እነጠቃለሁ መብቴን እነፍርጋለሁ እጠቃልሁ እገደዳለሁ እሰደዳለሁ እገደላለሁ በሚል በስርኣቱ ላይ ያላቸው እምነት የተሟጠጠ ከመሆኑም በላይ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከሃገር የመውጣት ንብረትን እና ሃብትን የማሸሽ ተግባር ላይ በመሰማራት በዜግነት አለመተማመን እንዲፈጠር በሩን በርግዶ ከፍቷል ይህ ደሞ ህጎች በተግባር ህዝብን አለማገልገላቸው እና በባለስልጣናት የመደፍጠጣቸው ውጤት ነው::

    በተግባር ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት የተነሳ ማንም የለም::ስርኣቱም በጥቅመኞች የሚመራ ህዝቡም ላላወጣው ህግ በዝምታ ደንታቢስነቱን እየገለጸ ነው; ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን የሚጥስና የሚያደናቅፍ የስርኣቱ ባለሥልጣን፣ ዜጋም ሆነ ግለሰብ፣ በማስረጃ ሲታይና ሲረጋገጥ ዕርምጃ ለመውሰድ ሕግ ፊት ለማቅረብ ምንም አይነት የተሰራ ስራ ካለመኖሩም በላይ በባሰ መልኩ በይፋ ህጎች ሲደፈጠጡ እያየን ነው:: ባለሥልጣንም ሆነ ባለ ሀብት፣ ታዋቂም ይሁን ተራ ዜጋ፣ ከፈለገው ብሔር ብሔረሰብ ይምጣ፣ የፈለገውን ሃይማኖት የሚከተል ይሁን፣ የጾታና የዕድሜ ልዩነት ሳይኖር ተቃዋሚም ይሁን ደጋፊ ሁሉም ሕግ ፊት፣ ፍትሕ ፊት፣ መልካም አስተዳደር ፊት እኩል መሆኑን አምነን በተግባር ለማዋል ቁርጠኝነት በፍጹም የለም:: ፍትህ እና መልካም አስተዳደር እንዴት ሊረጋገጡ ይችላሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየተጓዝን ነው ጥያቄያችን ;ስለዚህ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል::

    ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌና በሱዳኑ አቻቸው ጃፋር ኤሊ ሜሪ መካከል የተጀመረ እና እስካሁኑም የዘለቀ መሆኑን ባለስልጣኑ አውስተዋል። …

    ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ኢሌሞ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ጥቂት ወራት በአንያ፣ ማቶ እና ሙለቄ ቆላማ ወረዳዎች ላይ በፌደራል መንግስቱ እውቅና የተቋቋመውና ስልጠና የሚሰጠው ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ሃይሎች በኦሮሞዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት 59 ገድለው፣ 42 አቁስለዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከልም ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል። “በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች …

    ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አቶ ዘርዓይ አስገዶምየኢትዮጵኢያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው መንግስት ከምርጫ 2007 በፊት በፕሬሱ ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠንካራ አስፈጻሚ በማስፈለጉ ሊሆን እንደሚችል ኢቲቪን የለቀቁ አንዳንድ ጋዜጠኞች ተናገሩ። የአቶ ዘርዓይ ከቴሌቪዥን ዳይሬክተርነት መነሳት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ …

    ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ላይ ወቀሳቸውን የሰነዘሩት ድርጅቱ ራሱን እንደ ሁለተኛ መንግስት በመቁጥር የጦር መሳሪያዎችንና አማጽያንን አስጠልሏል በማለት ነው። ፕ/ር ሳልቫኪር የተመድ ዋና ጸሀፊ አገሪቱን ማስተዳደር የሚፈልጉ ከሆነ በግልጽ ይንገሩን ያሉ ሲሆን፣ ተመድ ወደ አገራቸው ሲገባ ተጓዳኝ መንግስት ሆኖ መግባቱን አላውቅም ነበር ብለዋል። ተመድ …

    የኢዜአ ማደናገሪያ ዜና – አንድ ተጨባጭ ምሳሌ January 20, 2014 ታደሰ ብሩ በቅድሚያ የሚከተለውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን (ኢዜአ) ዜና አጣጥሙልኝ። … ጎባ ጥር 10/2006 በባሌ ዞን ከእርሻ ስራ በተጓዳኝ በንብ ማነብ ፓኬጅ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከ53 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘታቸውን የዞኑ የእንስሳት ሀብት ልማትና ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በጽህፈት ቤቱ የእቅድና ግምገማ በለሙያ […]

    ክንፉ አሰፋ

    የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።

    ሙሉውን አስነብበኝ …

    አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ በሲዳማ ጭሬ የአንድነት ፓርቲ አባል ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ወደ ክልሉ ሲመለሱ አርሲ ሚጣ ነሴቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም እንደተያዙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከታሰሩበት ወረዳ ያንተ ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ስለሆነ እዚህ አይታይም በማለት ጥር 9 ቀን ወደ ሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ተወስደው ታሰሩ፡፡ ዝርዝር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

    የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የሚካሄደውን ግጭት ለማስቆም የሚያግዙ ወታደሮችን ለመላክ ተስማምተዋል ። የአውሮፓ ህብረት የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ዘመቻና የጀርመን የአፍሪቃ ወታደራዊ ተልዕኮ የዛሬው አውሮፓ ና ጀርመን ዝግጅታች ትኩረት ነው ።

    ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ […]

    ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ  ”የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን  ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት …

    ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ብድር የሚሰጡ 2  ባንኮችን ጨምሮ 17 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት ስራዎችን ለተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ብቻ እየሰጡ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተከትሎ ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር መልስ መስጠቱን ሪፖርተር ዘግቧል። ጋዜጣው እንዳለው መንግስት ቅሬታዎችን ለማስተካከል ቃል ገብቷል። መንግስት የግዢ ስርአት እንደሚዘረጋና የመሰረተ ልማት ተቋማት …

    ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በአዲስ አበባ ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ለማስማማት ውይይት ቢጀመርም፣ በመሬት ላይ እየተደረገ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አልተቻለም። በዩጋንዳ መንግስት የሚደገፈው የመንግስት ጦር ቦር እየተባለ የሚጠራውን ስትራቴጂክ ከተማ ከተቆጣጠረ በሁዋላ በቅርቡ የተነጠቀውን ማላካልን መልሶ ለመያዝ ከፍተኛ ትግል እያደረገ ነው። መንግስት ከተማዋን መልሶ መያዙን ቢያስታውቅም፣ አማጽያኑ …

    ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ያንኮቪች መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን በተመለከተ ያወጣው አዲስ ህግ ያስቆጣቸው ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት ከፖሊሶች ጋር እየተጋጩ ነው። መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን ለመገደብ ያወጣው አዲሱ ህግ በሌሎች የአውሮፓ አገራት ሳይቀር ተወግዟል። ተቃዋሚዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ከመወርወራቸውም በተጨማሪ፣ መኪኖችን ሲያቃጥሉ ታይቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ያንኮቪች ድርጊቱ የዩክሬንን ደህንነት አደጋ …

    የኦሮሚያ ክልል የቱሪዝምና ባህል ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሞሃመድ ጂሊ፣ የአኖሌ ሃዉልት እንደተሰራና በመሰራቱም ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው፣ ገዛ ተጋሩ በተባለ የፕላቶክ ክፍል ቀርበው ገለጹ። የአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች በአርሲ የሴቶችን ጡት ቆርጠዋል የሚባለዉ ወሬ፣ የቀድሞ የሕወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ተስፋዬ ገብረ አብ በጻፉት መጽሃፍ ከመጻፉና በአንዳድን አክራሪ የኦሮሞ ድህረ ገጾች ላይ ከመዉጣቱ መቀር፣ በታሪክ ባለሞያዎች […]

    የአዉሮጳ ህብረት መንግስት አልባ እየሆነች በመጣችዉ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ወታደሮችን ለመላክ ዛሪ ብራስልስ ላይ ተስማማ። የህብረቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ካለፈዉ አጋማሽ ጀምሮ ቀዉስ በተጠናወታት በዚችዉ ሀገር ወታደሮቻቸዉን የሚልኩት እየተጠናከረ የመጣዉን ዉጥረት ለመግታት ነዉ።