የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከፓርቲ ፖለቲካ መራቅ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በእንግሊዝኛው ምህጻሩ UDJ ሊቀመንበርነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ።

ሊቀመንበርነታቸውን ብቻም ሳይሆን ከUDJ አባልነትም የተሰናበቱት ዶ/ር ነጋሶ ከዚህ በኃላ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አልሳተፍም ብለዋል።