ዶክመንተሪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አካል እንደኾነ ተጠቁሟል ‹‹ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› ለሚለው የማኅበሩ ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም (ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች …

የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባዉ መሃሪ በደብተራው ፓልቶክ ክፍል ቀርበዉ ባደረጉት ሰፊ ዉይይት፣ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ስላለዉ የዉህደት እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል። «አንድነቶች እኮ ልጆቻችን ናቸው። መኢአድ የነበሩ ናቸው» ያሉት አቶ አበባዉ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶች እንደሌሉ ተናገረዋል። «ታዲያ የሁለቱም ፓርቲዎች ምክር ቤቶች ከወሰኑ በኋላ ምንድን ነው ምክንያቱ መኢአድ ለመፈረም ያልቻለው ? » […]

የተባበሩት መንግሥታት  የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ድርጅት – ዩኔስኮ ሎሬአል ከሚባል ዓለምአቀፍ የውበትና የሠውነት ጥራት መጠበቂያ አቅርቦቶች አምራች ቡድን ጋር በየዓመቱ የሚያካሂደው ሴቶች በሣይንስ ሽልማት ኢትዮጵያዊቱ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ አሸናፊ ሆኑ፡፡

ሣይንቲስቷ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ ተቀማጭነቱ ናይሮቢ – ኬንያ የሆነው የነፍሣት አካላት እና አካባቢ ጥናት ዓለምአቀፍ ማዕከል /ኢሲፔ/ (International Center for Insect Physiology and Ecology – ICIPE) ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡

ዶ/ር ሰገነት ከትናንት በስተያ (ረቡዕ) ፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ ላይ በተካሄደው የዓለምአቀፍ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለዘንድሮው16ኛው የዩኔስኮ እና ሎሬአል ሽልማት በአሸናፊነት ከቀረቡት መካከል አንዷ…

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በስምምነቱ ሰነድ ላይ እንደተገለፀው የበርሊን አስተዳደር ስደተኞቹ ያቀረቡለትን ጥያቄዎች ለመመለስ ቃል ገብቷል ።እርዳታ ሰጭዎች አስፈላጊውን እንክብካቤ እንዲያደርጉላቸውም ፈቃደኝነቱን ገልጿል ።

ህወሓቶች በዓረና እንቅስቃሴና በትግራይ ህዝብ የተቃውሞ መንፈስ በጣም ደንግጠዋል። የዓረና ተከታታይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ተከትሎ ህወሓትም ተከታታይ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ለማድረግ ወስኗል፤ ጀምሯልም። የህዝብ ተወካዮች ተብለው የተመረጡ የየአከባቢያቸው ህዝብ እንዲሰበስቡ መመርያ ተሰጥቷል። ይቅርታ የህዝብ ተወካዮች ሳይሆኑ የፓርቲ ተወካዮች መባል አለባቸው፤ ምክንያቱም የተመረጡት በህዝብ ሳይሆን በህወሓት ነው። የሚያገለግሉትም ለህዝብ ሳይሆን ለህወሓት ነው። ምክንያቱም በህዝብ ተመርጠው ተብለው የህዝብ ችግር ከመናገር ይልቅ የህወሓት አጀንዳ ደግፈው የሚያጨበጭቡ ናቸው። እስካሁን የመረጠውን ህዝብ ችግር የተናገረ የህዝብ ተወካይ የህወሓት አባል አላገኘሁም። በህወሓት የፖለቲካ ፍልስፍና የተማእከለ ዴሞክራሲ መሰረት አንድ አባል ከፓርቲው አስተሳሰብ ወጥቶ የፓርቲው ብልሹ አሰራሮች ባደባብይ ወይ በፓርላማ ማጋለጥ አይችልም። ካጋለጠ ከፓርቲው ይባረራል። ለዚህም ነው የህዝብ ተወካዮች ተብለው ፓርላማ ይገቡና የፓርቲው ተወካዮች ሁነው የሚቀሩ።

የህዝብ ወይም የህወሓት ተወካዮች ህዝብ ሲሰበስቡ ፈተና እያጋጠማቸው ነው። የሽረ ተወካይ ህዝቡ ሰድቦ አባሯታል። ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ በዓድዋ ህዝብ ተሰድባለች። የዓድዋ ህዝብ ለቅዱሳን “እናንተ ቤተሰቦቻቹ ለመርዳት እንጂ መቼ ለህዝብ ደህንነት ሰርታቹ ታውቃላቹ?” የሚል አስተያየት ሰጥቷል። በመቐለም አዲሳለም ባሌማ ህዝብ (ይቅርታ በመቐለ ህዝብ ተብለው የተሰበሰቡ ካድሬዎች ነበሩ) ሰብስቦ እርዱን ማለቱ ታውቋል። የመቐለ ዉሃ በ2007 ዓም ፕሮጀክት ቀርፀን እንፈተዋለን፤ ብቻ እኛን ምረጡ ብሎ ተማፅኗል። የመቐለ ነጋዴዎች ሰብስቦ ችግሮቻቹ ለመፍታት ተዘጋጅተናል ብሎዋል።

አጠቃላይ የህወሓት ስትራተጂ ህዝብን ለመሸወድ ያለመ ሲሆን የሚያጠነጥነውም “ህወሓት ካልተመረጠ የትግራይ ማንነት ይጠፋል” የሚል ነው። “ጠላቶቻችን እየመጡ ናቸው፤ ከህወሓት ጎን ተሰለፉ! ጦርነት ሊከፈትና ልጆቻችሁ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ” እያሉ ይገኛሉ።

ግን የትግራይ ማንነት በህወሓት ህልውና የተንጠለጠለ አይደለም። እንኳን የህዝብ ማንነት የአንድ ግለሰብ ማንነትም ሊጠፋ አይችልም። ምክንያቱም የህዝብ ማንነት ቀርቶ የአንድ ሰው ማንነት ከጠፋ የሰውየው መብትና ነፃነት ተጥሷል ማለት ነው። መብቱ ወይ ነፃነቱ ከተጣሰ ደግሞ አዲስ የመጣ ስርዓት ልክ እንደ ህወሓት አምባገነናዊ ስርዓት ነው ማለት ነው። የህውሓትን ያህል አምባገነን ስርዓት ከመሰረትን ደግሞ ህወሓት አልተቀየረም ማለት ነው። ህወሓት ካልተቀየረ የፖለቲካ ለውጥ አልመጣም ማለት ነው። የፖለቲካ ለውጥ ካልመጣ ደግሞ ትግላችን ይቀጥላል (ለውጥ እስኪመጣ ድረስ)። ስለዚህ እኛ የምንታገለው ከህወሓት የተሻለ ስርዓት ለመመስረት እንጂ ህወሓትን በሌላ አምባገነን ስርዓት ለመተካት አይደለም። ስለዚህ ላረጋግጥላቹ የምፈልገው ነገር ቢኖር የማንም ህዝብ ወይ ግለሰብ ማንነት ይከበራል እንጂ አይጠፋም።

“ጠላቶቻችን እየመጡ ነው” የሚለው ዉንጀላ ግዜው ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ ነው። የህዝብ ጠላት ጨቋኝ ስርዓት ነው። ህዝብ ከጨቋኝ ስርዓት ዉጭ ሌላ ጠላት የለውም። ጨቋኝ ስርዓት የህዝብ ጠላት እስከሆነ ድረስ እንታገለዋለን። ጨቋኝ ስርዓት ምን ግዜም አንቀበልም። ጨቋኝ ስርዓት ስለማንቀበል ነው አሁን ህወሓትን የምንቃወመው። ስለዚህ ዓላማችን የስርዓት ለውጥ ማምጣት እስከሆነ ድረስ ለጨቋኞች ቦታ የለንም፤ ህወሓትም ሌሎችም። እኛ የምንቀበለው ዴሞክራሲያዊ የህዝብ መንግስት ብቻ ነው።

ህወሓቶች በዓረና አጀንዳዎች በመስጋታቸው ምክንያት የዓረና ሐሳቦችን ለመቀበል እየተገደዱ ነው። በቅርቡ በህዝብ ፊት እየቀረቡ የመሬት ይዞታ ጉዳይ በዓረና እየቀረበ ያለውን ሐሳብ እንደሚደግፉ እየገለፁ ነው። (የዓረና ሐሳብ እንደግፋለን እያሉ ሳይሆን የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት እንሞክራለን በሚል ነው። የህዝቡ ፍላጎት ደግሞ የዓረና የመሬት ፖሊሲ ነው)። የዓሰብ ወደብም በሰለማዊ መንገድ ለማስመለስ እንሞክራለን በማለት እየተመፃደቁ ነው። ለነጋዴዎችም ግብር እንቀንሳለን በሚል ምክንያት ለመጀንጀን እየሞከሩ ነው።

አሁን ግራ ሲገባቸው ስራ የሌላቸው ወጣቶች ለውትድርና ለመመልመል እየሞከሩ ሲሆን ማንም ወጣት ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም። በወጣቶቹ ዉሳኔ የተደናገጡ ህወሓቶች የጎዳና ተዳዳሪ የነበሩ ህፃናት ልጆች አታለው (ስራ እንሰጣቸዋለን በሚል ምክንያት) ለዉትድርና መመልመላቸው ታውቋል። ለምሳሌ በመቐለ ከተማ የነበሩ ብዙ የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት ተወስደዋል (ማረጋገጥ ይቻላል፤ አሁን በመቐለ ከነበሩ ህፃናት አንድ የቀረ የለም)። ግን አብዛኞቹ ህፃናት ከ16 ዓመት በታች ናቸው። ከ16 ዓመት በታች ህፃናት ለውትድርና የሚመለምል የቸኛ ሕገወጥ መንግስት ኢህአዴግ መሆኑ አይቀርም። ምክንያቱም በማንኛውም ሕግ ከ16 ዓመት በታች ህፃናት ለውትድርና መመልመል ሕጋዊ ሊሆን አይችልም። ጉዳዩ የሚከታተለው ካገኘ በዓለም አቀፍ ሕግ ወንጀል ሊሆን ይችላል።

በዓዲግራት የፈፀሙብንን ድብደባ በጣም አክስሮባቸዋል። የትግራይ ህዝብ ሙሉበሙሉ እንዲጠላቸው ሁነዋል። እናም በጣም ሰግተዋል። በቅርቡ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሊጀምሩ ይችላሉ። በወታድሩም ቢሆን ህወሓቶች ድጋፍ የላቸውም።

It is so!!!
አብረሃ ደስታ

Image

መለስ በመጀመሪያው የኤርትራውያን ነፃነት ቀን ዝግጅት ላይ ለኤርትራውያን እንዲ ብሎ ነበር። «ቁስል እንዳለባችሁ አውቃለው። ለምን? ብትሉ ጀርባችሁ ላይ ያለው ቁስል በእኔ ጀርባ ላይም አለ። ይህንን ያለፈ ምህራፍ እርሱት አልላችሁም። ነገር ግን ቁስላችንን ማከክ የለብንም አሁን ሁሉ ነገር አልቋል (ተውዲኡ ኣሎ)ክፉ፣ ክፉውን ቀብረነዋል!!» ነበር ያለው።

ይህንን የመለስ ዜናዊ አነጋገር አንድምታ ስናይ «ይኸው ደረስንላችሁ! ጠላት ተቀበረ! መቀበር ብቻ አይደለም አስተሳሰቡንም አዛብተነዋል! ያለበት ነበር። እንግዲህ ማነው ጠላት? ኢትዮጵያ? የማን አስተሳሰብ ነው? የኢትዮጵያ! ምን አይነት አስተሳሰብ? እንግዲህ እንደምናውቀው በተለየ ጊዜ የኢትዮጵያን ሳይኮሎጂ የሚያዛቡ ነገሮችን ሲናገሩ ነበር። ለምሳሌ፦ «ባንዲራ እኮ ጨርቅ ነው!» ይሄ አባባልን ለሚያይ ሌላ ሰው በቀላሉ የአፍ ወለምታ ሊመስለው ይችላል።ነገር ግን ሆን ተብሎ የኢትዮጵያውያንን አስተሳሰብ ለማዛባትና ለማሽመድመድ የሚደረግ ሴራ ነው።

በባንዲራችን እንደምንኮራ ያውቃሉ! የሶስት ሺህ አመት ታሪክ አለን ብለን እንደምንኮራ ያውቃሉ! ነገር ግን ይህንንም ታሪካችንን ወደ መቶ አመት ዝቅ ለማድረግ ይጥራሉ፤ ባለፉት መሪዎቻችን በአጼ ምንሊክ ፣ በነ አጼ ቴዎድሮስ፣ በነ አጼ ዩሐንስ፣ በነ አሉላ እንደምንኮራና እንደምንወዳቸው ከእነሱ ጋርም ያለንን ትስስር ያውቃሉ! ወያኔዎቹ ባንዳዎች ግን በየጊዜው ቴሌቭዥን ላይ እየወጡ «የኢትዮጵያ አጼዎች እኮ ጊዜያቸውን ያሳለፉት በጦርነት ነበር።» ይላሉ። ይሄን መናገር በተለይ አቶ መለስ እንደሆቢ ነበር የወሰዱት የሚመስለው። እንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎቹ «ለካ እንዲህ ነበሩ» ብሎ እንዲያፍር! የዛሬውም ቅጥ ያጣ ድህነት «እነሱ ያመጡት ጣጣ ነው!» ብለውም ለመናገር ይሞክራሉ።

እንደዚህ አይነት ቀጣይ ነገሮችን አምጥተን አገጣጥመን «ባንዲራ ጨርቅ ነው!» ካሉበት ጊዜ ጀምሮ ያሉትን ሰብስበን ብናያቸው መለስ የተያያዘው ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ፣ በኢትዮጵያዊነቱ አፍሮ፣ ድህነትን እንዲቀበል፣ ከኋላ ቀርነት ጋር ተቆራኝቶ እንዲኖርና የበታችነት ስሜት እንዲኖረው አድርገዋል እየተደረገም ነው»

Image

በቅርቡ ባህርዳር ላይ በተካሄደው የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ሼኽ አልሙዲ በክብር እንግድነት ተጋብዘው ነበር። የበአሉን መክፈቻ በቲቪ ስከታተል አንድ ጥያቄ ወደ በአእምሮዬ መጣ። አልሙዲንን የክብር እንግዳ አድርጐ መጋበዙ ለምን አስፈለገ?..ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። “የገዢው ፓርቲና የባለስልጣናቱ ታማኝ ወዳጅ ስለሆኑ፣ በባህርዳሩ ስታዲየም ግንባታ ድርጅታቸው ስለተሳተፈ ወይም ሼኹ ለስፖርት ያላቸውን ፍቅር በማየት..” የሚሉ ነገሮችን መደርደር ይቻላል።

በእኔ ግምት አልሙዲ በባህርዳሩ በአል በእንግድነት የተጋበዙት በሰሜን አሜሪካ ስፖርት በአል ላይ ስለተዋረዱ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት የፈጠርዋት ማፅናኛ ትመስለኛለች። ባለፈው አመት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ሳምንት ሁለት የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ተከበሮዋል። አንድኛው በሼኽ አልሙዲና የዳይስፖራውን ማንነትና ፍላጐት ባልተገነዘቡ ወዳጆቻቸው የተዘጋጀ ነበር። በነዚህ ወገኖች ግምት “ዳያስፖራው በተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ካድሬዎች የሚሽከረከር የዋህ ህዝብ” አድርገው ይወስዱታል።

አሜሪካ ሀገር ከኅይለስላሴ ጀምሮ በደርግ ጊዜ ከዛም በኋላ የመጣው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ (በምንም መንገድ አሜሪካ ይምጣ) ለዘሩ፣ ለጐሳው ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ጥልቅ የሆነ ፍቅርና ክብር አለው። በዚህ ምክንያት የኢህአዴግን የዘር ፖለቲካ አይደግፍም። ከደጋፊዎቹም ጋር የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ የገባው በዚህ አገር ወዳድ አቋሙ ነው። ይህ እውነት ያለገባቸው አልሙዲና ተከታዮቻቸው በስፖርቱ አስታከው ዳያስፖራውን እንቆጣጠራለን በማለት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ቢከሰክሱም አልተሳካላቸውም። ባዶ ስታዲየም ታቅፈው ነው የቀሩት። ሁለተኛው ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን የሚባለው ኢትዮጵያዊ ፌዴሬሽን የነሱን ያክል ገንዘብ ሳይኖረው በርካታ ህዝብ ከጎኖ ማሰለፍ ችሎዋል። እንዲያውም ስታዲየሙ ሞልቶ ሰው እስኪመለስ ድረስ። በዚህ በአል ከፍተኛ የሆነ የአንድነትና የአገር ፍቅር ስሜት የታየበት፣ የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ በብዛት የተውለበለበበትና ያሸበረቀበት፣ ሰዎች ከብሄራቸው ይልቅ ኢትዮጵያዊነታቸውን ያገነኑበት ትልቅ በአል ነበር።

ባዶ ስታድየም የታቀፉትና አፍረው በውርደት ለተመለሱት አልሙዲ የባህርዳሩ እድል በማፅናኛነት ተሰጣቸው። ኢትዮጵያዊያን በነፃነት በሚኖሩበት አሜሪካ ግን አልሙዲ በገንዘባቸው የህዝብን ድጋፍ መግዛት አይችሉም። በገንዘብ ምንም ማድረግ እንደማይችሉም ሊያውቁት ይገባል።

  በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። በዘመነ ኢሕአዲግ ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ የኑሮ ውድነቱ እየተባባሰ መምጣት ሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን ጥላቻ እንዲከር እያደረገው ነው የኢህአዲግ ወያኔ መንግስት   የስልጣን ወንበር በትሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአኖኖር ሁኔታ …

በዘመነ ኢሕአዲግ ኑሮ ከድጡ ወደማጡ Read more »

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ዛሬ በጽ/ቤቱ መግለጫ ሰጠ ፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!

ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!

Image
ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡

ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡
የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው
መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የሕዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
Image
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የሕዝብ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን ተቃዋሚዎች ‹‹ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ›› ጥያቄ ለመመለስ በስትራቴጂና አምስት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የውህደት ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሰሞን ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂክ ግብ ነው፡፡ የዚሁ አካል የሆነ እንቅስቃሴ በመኢአድና አንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባላት በእጅጉ እያሳዘነ ነው፡፡
Image
በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓም የተፃፈልንን ደብዳቤ መሠረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀውን ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ ተቀብለነዋል፡፡ በዚሁ መሠረት መጋቢት 4 ቀን 2ዐዐ6 ዓም በሰጠነው የደብዳቤ መልስ ላይ እንደገለጽነው በአንድነት ፓርቲ እይታ አመራሩ የፊት ለፊት ውይይት የምንፈልገውና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተጠራውና የሁለቱ ፓርቲዎች የብ/ም/ቤት አባላትና የላዕላይ ም/ቤት አባላት በተገኙበት ለታሪክ በተቀረፀ ወሳኝ ስብሰባ ሠፊ የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደው የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉትን አስገዳጅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡
በዚሁም መሠረት፡-
የሁለቱም ፓርቲዎች አባላት አላስፈላጊ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት ውህደቱን አታጓቱ ውህደት የማትፈፅሙ ከሆነ እኛ አባላት በራሳችን ውህደት እንፈፅማለን የሚል ጥብቅ ተማፅኖና ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዚደንቶችና አደራዳሪ ሽማግሌዎች በገቡት ቃል መሠረት ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቅድመ ውህደት የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረም ከስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡
የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የውህደት አስፈፃሚውን ጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑትን የስም ዝርዝር፣ የፊርማው ስነ ሥርዓት በሚከናወንበት እለት እንዲያመጡ ተስማምተን ነበር፡፡
በከፍተኛ አመራሮችና በሁለቱ ሥራ አስፈፃሚዎች ውሳኔ መሠረት የሁለቱ ፓርቲ ፕሬዝደንቶች ተስማምተው፣ የቅድመ ውህደት መግባቢያ ሰነድ በሁለቱ ፓርቲዎች የድርድር ኮሚቴ አባላት መካከል ተፈራርመን፤ ሆቴል ተከራይተንና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል የዕውቅና ሠነድ አግኝተን የመጨረሻ የስነ-ስርዓቱን መርሃ-ግብር በመጠባበቅ ላይ እያለን በድንገት በመኢአድ ፕሬዝደንት በኩል በቁጥር መ/ኢ/አ/ድ 278/06 መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም በእለቱ የቅድመ ውህደት ፊርማውን መፈረም እንዳማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓርቲያችን መድረሱ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ ከደብዳቤው እንደተረዳነው መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ከበርካታ የሃሳብ ልውውጥ በኋላ የደረሱበትን ውሳኔ የሚቀለብስ፣ የሁለቱ ፓርቲዎች ተደራዳሪዎች እየተስማሙ በቃለ ጉባኤ ያፀደቁትንና ከሁሉም በላይ የሁለቱ ፓርቲ ተደራዳሪዎች ለቅድመ ውህደት ባዘጋጁትና ባፀደቁት የመግባቢያ ሰነዶች ላይ የሰፈሩ ነጥቦችን እንደ አዲስ በማንሳትና በጥቃቅን ጉዳዮች በመጠመድ የቅድመ ውህደቱ እንዳይፈረም ተደርጓል፡፡ ለዚህ ታሪካዊና የሕዝብ ጥያቄ መደናቀፍ ምክንያቱ የመኢአድ ፕሬዚንት ሲሆኑ ይህን ሁኔታ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ለሁለቱ ፓርቲዎች አባላት፣ ደጋፊዎች፣ በግል ተነሳሽነትና በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ሁለቱን ፓርቲዎች ለማደራደር ሲደክሙ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ለሕዝቡ ጥሩ ዜና ባይሆንም ላለመፈረሙ ኃላፊነቱን የሚወስዱት የመኢአድ አመራሮች በተለይም ፕሬዝደቱ መሆናቸውን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለውህደቱ መሳካት የመኢአድ አባላትና ከፊል አመራሩ እያሳዩ ለሚገኘው ፍላጎትና ጥረት ፓርቲያችን መልካም አክብሮቱን መግለፅ ይወዳል፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም

ኢትዮጵያ፣ 152 ሃገራትን ያቀፈው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO)አባል ለመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በ 4ኛውና በመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ እንደምትገኝ ተገለጠ። ስለዚህ ድርድር ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

አፍሪቃ ውስጥ ከውዝግብ ካልተላቀቁት አካባቢዎች አንዲዱ የሱዳን ምዕራባዊ ክፍለ ሀገር ፣ ዳርፉር መሆኑ አይታበልም። የዳርፉር ኑዋሪዎች፤ እ ጎ አ ከ 2003 ዓ ም አንስቶ ፤ ከሽብር ሁከት ግድያና ስደትገና አልተገላገሉም፤ በመኻሉ በቆዩ ችግሮች ላይ አዳዲስ ታክለዋል።

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ! ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!! ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ዛሬ በጽ/ቤቱ መግለጫ ሰጠ ፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ! ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!! ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ […]

የአውሮፓ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፤ በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የሚመራውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር በሚያደናቅፉት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ። የሕብረቱና የአሜሪካ ተወካዮች፤ አምባሳደር ዶናልድ

በዓለም ላይ ያሉ በርካታ ሃገራት ቱሪዝምን ዋና የኤኮኖሚ ምንጭ በማድረግ በየዓመቱ በሚሊያርድ የሚቆጠር ገንዘብ በማግኘት፤ ቱሪዝምን ጠቃሚ የኤኮኖሚ ዘርፍ ማድረጋቸዉ ይታወቃል። ቱሪዝም ከገቢ ማስገኛነቱ ባሻገር ባህልና ሃገርን በማስተዋወቁ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ ይታወቃል።

ጽሕፈት ቤቱ ኦስሎ ኖርዌይ የሚገኘዉ የሃገራት የተፈጥሮ ሃብት አስተዳደር ይዞታ ግልፅነት ሊኖረዉ ይገባል የሚለዉ በእንግሊዝኛ ምህፃሩ EITI የተሰኘዉ ስብስብ ኢትዮጵያ ለአባልነት ያቀረበችዉን ማመልከቻ ተቀበለ። በአንፃሩ መንግስት የሲቪል ማኅበራትን እንቅስቃሴ ማረጋገጥ እንደሚኖርበት የEITI ቦርድ በአፅናኦት አሳስቧል።

ይሁንና የማማከሩ ምግባር መሳካቱን የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ይጠራጠራሉ።ምክንያታቸዉ የሶማሊያ ጦር ግልፅ አደረጃጃት የለዉም የሚል ነዉ።ማቲያስ ቬበር እንደሚሉት የሶማሊያ ጦር አደረጃጃትን ቅጥ ካሳጡት ዋናዉ በጎሳ ልይ የተመሠረተ መሆኑ ነዉ።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የሕዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የሕዝብ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን ተቃዋሚዎች ‹‹ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ›› ጥያቄ ለመመለስ በስትራቴጂና አምስት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ […]

በፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም፦  በነጻነትለሀገሬ

“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!”

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !

እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

በቦስተን እና አካባቢዋ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የሕሊና እስረኛ አንዱአለም አራጌ የውደሳ እና የምስጋና ቀን በቦስተን እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2006 / Sunday, March 30, 2014 ከቀኑ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ/From 2:00 PM to 6:00 PM በካምብሪጅ፤ ዋልደን የኮሚኒቲ አዳራሽ፣ 21 ዋልደን ስኩዬር ሮድ፤ ካምብሪጅ፤ ማሳቹሴትስ 02140፣ (Walden Square Community Rm, 21 Walden Sq. Rd., […]

በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረቱ ዘማች ኃይል – አሚሶም በቅርቡ ከአልሻባብ አስለቅቆ የያዛት ዑዱር ከተማ በአማፂያኑ ተዋጊዎች የተከበበች መሆኑን የባኩል ክልል አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገለፁ፡፡

የግዙፉን የአባይ ግድብ ግንባታ የሥራ ጥራትና ደህንነት በተመለከተ ምንም ዓይነት ጉድለት አይኖርም፤ ሲሉ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አመለከቱ። ለታችኛው የተፋሰሱ አገሮችም የአባይ ውሃ ፍሰት መቼም እንደማይቋረጥ ሥራ አስኪያጁ አረጋግጠዋል።

እስካሁን በችግርነት ሊነሳ የሚችል ሁኔታ አላጋጠመንም ብለዋል። የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያዳምጡ፤

የደቡብ ሱዳን መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል በሚል ያሰራቸዉንና አራት የቀድሞ ባላሰልጣናት እንዲፈታና እርቁን እንዲቀላቀሉ የአሜሪካና የአዉሮፓ ባለስልጣናት አሳሰቡ

የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን በተመለከተ የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች ውሃ በፈረቃ የሚያገኙበት ያልታወጀ አሰራር እየተስተዋለ ነው። ብዙ አካባቢዎች ከ24 ሰዓታት በላይ የመጠጥ ውሃ በተደጋጋሚ በመጥፋቱ ነዋሪዎች መደበኛ ሥራዎቻቸውን ጭምር በመተው ጄሪካን ይዘው ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ የሚንከራተቱበት ትይዕንት አዲስነቱ እየቀረ የመጣ ይመስላል። አቶ ድሪባ ኩማ ግን በያዝነው በጀት […]

በአዲስአበባ በተለይም በስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓታት የሚታየው የትራንስፖርት ችግር ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ መምጣቱ ብቻም ሳይሆን ሠራተኞች በሰዓት ወደስራ ገበታቸው እንዳይገቡ በማድረግ በምርታማነት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ እንዲሁም አብዛኛውን ሠራተኞች ላልተፈለገ ወጪ በመዳረግ የኑሮ ውድነትን በማባባስ ረገድ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ከታክሲ የዞን ስምሪት አንስቶ ተጨማሪ አውቶብሶችን ወደመስመር በማስገባት በመንግስት በኩል የተደረጉ ጥረቶች ቢኖሩም […]

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) ETHIOPIAN JOURNALISTS FORUM (EJF) በጋዜጠኞች ላይ ያለ ማስረጃ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን! ማህበራችን ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዶ የምዝገባ ሰርተፊኬት ለማግኘት የጀመረው እንቅስቀሴ በቅርቡ ከመንግስት አወንታዊ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ በማድረግ የተቋቋመለትን አላማ ለማሳካት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅና የመናገር ነፃነትን ከማበረታታት ባለፈም ከአህጉራችን አፍሪቃ ጋዜጠኞች ጋር በመተባበር […]

አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ አደረጃጀቱን ሊዘረጋ መሆኑንና ይህንኑ በተመለከተም ከፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት፣ከወረዳ ሰብሳቢዎችና ከወረዳ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች ጋር ምክክር እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ያሬድ አማረ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቀ፡፡ ግንኙነት ኃላፊው ወጣት ያሬድ እንዳስታወቁት ቅዳሜ መጋቢት13 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ […]

በመኢአድ ጽ/ቤት እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በእነ ዶክተር ያእቆም ኃይለማሪያም፣ በዶክተር ዳኛቸው አሰፋ አደራዳሪነት የተጀመረው የቅድመ የፓርቲዎች ውህደት ድርድር ውጪ የሚገኙ ተቃዋሚ ኃይሎች የቀመሩት አይደለም ሲሉ ከአደራዳሪዎቹ አንዱ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ። ስማቸው አይጠቀስ ያሉ ዶክተር አሁን የያዙትን ኃላፊነት በምን መልኩ እንዳገኙት ለሰንደቅ እንደገለፁት፤ “እኛ ይህን […]

በ2002ቱ ጠቅላላ ምርጫ መቃረቢያ ላይ ከ60 ያላነሱ ሀገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፓርቲዎችም እንገዛበታለን ብለው ከፈረሙበት በኋላም ሕግ ሆኖ የወጣው የስነ-ምግባር ደንብ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደማይፈርም አስታወቀ። የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለሰንደቅ እንደተናገሩት፤ የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ በሀገሪቱ ፓርላማ ሕግ ሆኖ እስከወጣ ድረስ ፓርቲው እንደገና የሚፈርምበት ምክንያት የለም ብለዋል። ኢህአዴግን ጨምሮ ዘጠኝ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች በሚሳተፉበት […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በጀርመን የሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት፤ የቀድሞው የውጭ ፖለቲካ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሩፕሬሽት ፖሌንዝ ፣ ሩሲያ፣ የክሪሚያን ልሳነ-ምድር በኃይል መያዟ ፤ በኃላፊነት፤ የአውሮፓውን ሕብረት አይመለከትም አሉ። እንደርሳቸው ትዝብት፤ ትናንት፤

ለሰወስት ወር በሚቆየዉ ጉባኤ ከአምስት መቶ የሚበልጡ የመንግሥት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ የሐይማኖት ተቋማት፤ የኩባንያና የንግድ ድርጅት ተጠሪዎች፤የሰራትኞች፤ የሙያና የፆታ ማሕበራት ተወካዮች፤ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተካፍለዋል

ሎሪያል ተቋምና የተመ የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት ማለትም UNESCO በጋራ ያዘጋጁት 16ኛዉ የሳይንስ እና ሴቶች ልማት መርሃግብር ኢትዮጵያዊቷን ሳይንቲስት ዶክተር ሰገነት ቀለሙን ከዓመቱ ተሸላሚዎች አንዷ አድርጎ መረጠ።

የካቲት 29 ቀን 2006 ዓ ም፤ (08 03 2014) ከደቡብ ምሥራቅ እስያዊቷ ሀገር ማሌሺያ 239 መንገደኞችን አሣፍሮ ወደ ቤይጂንግ ጉዞ የጀመረ አኤሮፕላን፣ አቅጣጫውን ድንገት ለውጦ ከተመለሰ በኋላ እስካሁን እምን እንደገባ በይፋ ያልታወቀበት ሁኔታ

በጋምቤላ የሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የዓለም ዓቀፋ ኅብረተሰብ አስፈላጊዉ ድጋፍ ካላደረገላቸዉ በቀር በረሃብና በሽታ ምክንያት ለአደጋ ሊጋለጡ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አስተዳደር አስጠነቀቀ።