ኢትዮጵያዊቱ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ በዩኔስኮ ተሸለሙ
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ድርጅት - ዩኔስኮ ሎሬአል ከሚባል ዓለምአቀፍ የውበትና የሠውነት ጥራት መጠበቂያ አቅርቦቶች አምራች ቡድን ጋር በየዓመቱ የሚያካሂደው ሴቶች በሣይንስ ሽልማት ኢትዮጵያዊቱ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ አሸናፊ ሆኑ፡፡
ሣይንቲስቷ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ ተቀማጭነቱ ናይሮቢ - ኬንያ የሆነው የነፍሣት አካላት እና አካባቢ ጥናት ዓለምአቀፍ ማዕከል /ኢሲፔ/ (International Center for Insect Physiology and Ecology - ICIPE) ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ዶ/ር ሰገነት ከትናንት በስተያ (ረቡዕ) ፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ ላይ በተካሄደው የዓለምአቀፍ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለዘንድሮው16ኛው የዩኔስኮ እና ሎሬአል ሽልማት በአሸናፊነት ከቀረቡት መካከል አንዷ...