አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት ታስረዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. March 29, 2014)፦ ዛሬ ገዥው ፓርቲ በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ በጠራው ስብሰባ ለእያንዳንዳቸው ተሰብሳቢዎች 8ሺህ ብር ብድር በመስጠት መጭውን ምርጫ ግን ኢህአዲግን እንዲመርጡ በመቀስቀስ ላይ ባለበት ወቅት ምርጫን በገንዘብ መግዛት አይቻልም ብለው ጥያቄ ያቀረቡ አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ይፋ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሁሉንም ተቃዋሚ እንደአንድ መመልከትም ሆነ በአንድ አዕምሮ እንዲያስብ መጠበቅ የገዢው፣ የተገዢዎች፣ የተቃዋሚዎች ሁሉ የጋራ ችግር ነው። ሚሊዮን ችግሮች እና ሚሊዮን ተቃዋሚዎች ባሉበት አገር ውስጥ ተቃዋሚዎች ሁሉ አንድ ዓይነት ሊሆኑ አይችሉም። ይሁን እንጂ ሁሉም ተቃዋሚዎች ልዩነታቸውን በቅጡ ያውቃሉ ብሎ ለማለትም ያስቸግራል፤ ምክንያቱም “በስመ ተቃዋሚ ሲሳሳሙ” ማየት የተለመደ ነው። ተቃዋሚዎችን በተቃውሞ አካሔዳቸው መግባባት ላይ መድረስ እንዲያቅታቸው ከሚያደርጋቸው ችግር አንዱ ኢሕአዴግን የሚበይኑበት (define የሚያደርጉበት) መንገድ መለያየቱ ወይም ግልጽነት ማጣቱ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።

ብያኔ ለምን ያስፈልጋል?

40 ዓመት ወደኋላ መለስ ብለን የአብዮቱን ልጆች ለመከፋፈል እና ለእርስበርስ እልቂት የዳረጋቸው ዋነኛውን፣ የሚታገሉትን አካል (ደርግን) የበየኑበት መንገድ ነው። የኢሕአፓ እና የመኢሶን ዋነኛ ልዩነት፣ የኢሕአፓና አንጃ እያለ የሚጠራቸው አባላቱ መካከል የተከሰተው የሐሳብ መሰነጣጠቅ፣ ብሎም እርስበርስ መጨራረስ ደርግን የሚበይኑበት መንገድ መለያየትን ተከትሎ የተወለደው ደርግን ለማስወገድ የመረጡት መንገድ ነው። ሁለቱ (የተቀናቃኝ ወገን ብያኔ እና የመቀናቀኛ መንገድ ምርጫ) ተሰናስለው የሚኖሩ ጉዳዮች ናቸው። በጥንቃቄ ሳይጤን የሚገበቡበት ገደል አይደለም።

ኢሕአዴግ፣ በዚህ ረገድ ራሱን ግልጽ የማድረግ ችግር የለበትም። ተቀናቃኞቹን አንዱን አሸባሪ፣ አንዱን የአሸባሪ ደጋፊ፣ ሌላውን ለዘብተኛ እያለ የሚኮረኩምበትን መንገድ አስቀምጧል። ኢሕአዴግ መሣሪያ ታጣቂ እንደመሆኑ ተቀናቃኞቹን ባይበይናቸውም ቅሉ ማሽመድመጃ መንገድ አይቸግረውም። ለተቃዋሚዎች ግን ‘ኢሕአዴግ ምንድን ነው?’ የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሕልውና ጉዳይ ብቻም ሳይሆን ወዴት እና እንዴት እየሄደ እንደሆነ የሚያውቁበት ወሳኝ ጥያቄ ነው።

የበኩር ጥያቄ፤ ኢሕአዴግ ምን ያስባል?

ኢሕአዴግ እንደማንኛውም ገዢ ፓርቲ በፖለቲካዊ ብልጫ ሥልጣን ላይ የቆየ ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ የሚኖር ፓርቲ ነው? እያጭበረበረ የሚኖር ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ በሕጋዊ መንገድ ሥልጣን ላይ የቆየ ፓርቲ ነው? ሕዝባዊ ይሁንታ ባገኘ መንገድ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ኃይሉን መከታ በማድረግ ሥልጣኑን ያለመጋራት የተቆጣጠረ ፓርቲ ነው? በኃይል ሥልጣን ተቆጣጥሮ በኃይል ሥልጣኑን እያስጠበቀ ያለ ፓርቲ ነው? ወይስ ምንድን ነው?…ብዙ ዓይነት ትርጉሞች (ሁሉም እውነት ያላቸውን) ማስቀመጥ ይቻላል። የራስንና አንድ ወጥ ትርጉም ማስቀመጥ የሚበጀው የሚከተሉትን የትግል ስልት ለማወቅ እና የሚጠብቁትንም (what to expect) ለማወቅ ነው።

በአማራጭ ፓርቲዎች መካከል እና ለዴሞክራሲያዊነት  በሚደረጉ ነጻ (የአራማጆች እና የሲቪል ማኅበረሰብ) ትግሎች ምን ዓይነት መሆን አለባቸው የሚለውን መወሰን የሚቻለው የሚታገሉለትን ነገር በማወቅ (ለምሳሌ ለዴሞክራሲ በዴሞክራሲያዊ መንገድ) ከሚለው በተጨማሪ ተቀናቃኝ አካላትን በሚገባ በማወቅና በመበየንም ጭምር ነው። የኢሕአዴግን ማንነትም በቅጡ መበየን የሚያስፈልገው አላስፈላጊ ጊዜ፣ ገንዘብና ጥረት ላለማባከን እና የጠበቁትን ውጤት ለማግኘት ነው።

‘ኢሕአዴግ ሥልጣኑን በኃይል ተቆጣጥሮ በኃይል እያስጠበቀ ያለ ድርጅት ነው’ ብለን ካልን ሠላማዊ ትግል የሚባለው ሁሉ ትርጉም ላይኖረው ይችላል። ግን ይህንን ለማለት የሚያስችል በቂ መረጃ አለ ወይ? ኢሕአዴግ ብረት ታጣቂውን ደርግ ለመገርሰስ ከኃይል ውጪ አማራጭ ነበረው? የሥልጣን ባለቤት ከሆነ በኋላ ሥልጣኑን ያላስረከበው በፓርቲው እምቢተኝነት [ብቻ] ነው ወይስ የተቀናቃኞቹም እጅ (ድክመት) አለበት? ኢሕአዴግን ከኃይል መለስ ባለ ነገር ከሥልጣን ለማውረድ የሚያስችሉት በሮች ሁሉ ተዘግተዋል? ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አባላት ያሉትን ፓርቲ ‘ጠላት’ ብሎ ለመፈረጅ የሚያስችል ሁኔታ አለ? ይህ መሰሉ ድምዳሜ እና ፍረጃ በታሪክ ከተሠሩ ስህተቶች አንፃር ምን ያክል የተማረ/የታረመ ነው?

‘ኢሕአዴግ በኃይል ያገኘውን ሥልጣን በሕዝባዊ ይሁንታ (እንበል ምርጫ) ቀጥሎበታል’ ካልን ደግሞ ለስርዓት ለውጥ የሚደረጉ ትግሎች ፍፁም ሠላማዊና ግልጽ መሆን ይኖርባቸዋል ማለት ነው። ይህም እልፍ ጥያቄዎችን ይወልዳል። ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ እውን የሥልጣን ርክክብ ማድረግ ይቻላል? ከምርጫ ውጪ የሥልጣን ሽግግር የሚመጣባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ? ኢሕአዴግ ሕዝባዊ ይሁንታ ካለው ትግሉ (ለውጡ) ለምንድን ነው? በሠላማዊ መንገድ የሚመጣው ለውጥ ምን ዓይነት ነው?… ወዘተ።

እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች እንደምሳሌነት ብንወስድም፣ ሌሎችም ጥያቄዎች በተለያዩ ብያኔዎች ላይ ተመሥርቶ ማውጣት ይቻላል። በምሳሌው ውስጥ የተካተቱትን ሁለት ብያኔዎች ተንተርሶም፥ ሁለቱን ብያኔዎች የሚሰጡ አካላት አብረው ሊሠሩባቸው የሚችሏቸው እና የማይችሏቸውን ጉዳዮች አብጠርጥሮ ማውጣትም ያስፈልጋል እንጂ በብያኔ ተለያይተናልና አብረን የምንሠራበት መንገድ የለም ማለት ላይሆን ይችላል። ይህን ባለማወቅ የሚደረግ ትግል ግን መነሻውንም፣ መድረሻውንም የማያውቅ ተራ ጥላቻ የሚመራው ጉዞ ነው።

መበየን ቀላልም፣ ከባድም፤ ትንሽም፣ ብዙም ነው

ኢሕአዴግን የተለያዩ አካላት የተለያየ ብያኔ ይሰጡታል። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያዊ (ብሔራዊ) ስሜት የለውም ከሚሉት ጀምሮ ለኢትዮጵያ የመጨረሻው የመድኅን ስጦታ ነው እስከሚሉት ጽንፎች ድረስ የሚደርስ ብያኔዎች አሉት።

እኔ በግሌ ኢሕአዴግ በተለያዩ ሒደቶች ውስጥ የተለያየ ምልከታዎችን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እያጎለበተ የመጣ ቡድን ነው ብዬ አምናለሁ። ፕሮፌሰር ክላፋም እንዳሉት፥ ‘ሕወሓት በብሔር ዓይን ኢትዮጵያን እየተመለከተ መጥቶ ገዢ ሆነ፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያን ወክሎ (በኢትዮጵያዊ ዓይን) ኤርትራን ጦርነት ገጠመ፤ ይህም ሁለተኛ ዕይታ ሰጠው’። ምናልባት እዚህ’ጋ መጨመር ቢያስፈልግ ሕወሓት (የጠቅላላው ኢሕአዴግ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ እንደመሆኑ) ከምርጫ 97 በኋላ ኢትዮጵያዊ (ኅብረብሔራዊ) ስሜት ማዳበር ባይችል እንኳን ያለሱ ብዙ እርምጃ መጓዝ እንደማይችል ተረድቷል። ስለዚህ ኢሕአዴግ በሦስት ደረጃዎች ውስጥ አልፎ እዚህ ደርሷል ባይ ነኝ፤ ሁሉንም ነገር በዘውግ-ብሔር ዓይን የሚመለከትበትና የሚተረጉምበት ደረጃ (አንድ)፣ ኢትዮጵያዊ ኅብረብሔርተኝነትን ለአጀንዳ ማስፈፀሚያነት (ለምሳሌ ለጦር መቀስቀሻነት) የሚያውልበት ደረጃ (ሁለት)፣ እና ያለኢትዮጵያዊ ኅብረብሔራዊ ስሜት እና መሰል እርምጃዎች (ምሳሌ የባንዲራ ቀን) መራመድ እንደማይችል የተረዳበት ደረጃ (ሦስት) ናቸው። ይሁን እንጂ የዘውግብሔርተኝነትን እና ሕብረብሔርተኝነትን ሚዛን የሚያስጠብቅበት ግልጽ አካሔድ የለውም፤ ይልቁንም እንደ ሕዝባዊው ስሜት አነፋፈስ ተስማምቶ ለመንፈስ ብቻ እየተፍጨረጨረ ነው።

ኢሕአዴግን ከላይ ልበይነው የሞከርኩት በኢተዮጵያዊነት ስሜቱ ነው። በተመሳሳይ መንገድ ሥልጣን ላይ ያለውን አመለካከትም በአካሔዱ ለመተርጎም ብሞክርም በርግጠኝነት ልበይነው አልቻልኩም። ኢሕአዴግ ከስኒ ማዕበል በላይ አቅም የሌላቸውን ተቃዋሚዎች ይቀበላል። ከዚያ በላይ ያሉትን ግን በቀና ልቦና እንደሚቀበል አላሳየም፤ ሆኖም በሙሉ አቅም ተፈትኗል ማለትም አይቻልም። የደኅንነት፣ የኮሙኒኬሽን እና የመከላከያውን ቁልፍ ሚናዎች በሕወሓት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዲሁም ኢኮኖሚው በመንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር ስር ማድረጉም ሥልጣኑን በሠላማዊ መንገድ ለመልቀቅ ያለውን ዝግጁነት አጠራጣሪ ያደርገዋል። ይሁን እንጂ እስከመጨረሻው ድረስ ተገፍቶ ያልተሞከረ በመሆኑ ለሠላማዊ ትግል በር ተዘግቷል ሊባል በማይቻል መወላወል ውስጥ አስቁሞናል።

ብያኔ ቸኩለው የሚገቡበት ጉዳይ አይደለም። ርዕሱን ከብዙ ገጾች ማየት ያስፈልጋል። ነገር ግን ያለብያኔ ቋሚ አቅጣጫ መያዝ አይቻልም፤ ባይሆን ብያኔንም አቅጣጫንም በየጊዜው መከለስ ያዋጣል።

እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምክንያት እንደሰሞኑን በግኜ የማውቅ ኣይመስለኝም። ኣቤት ክህደታችን! እንዴት ተክነንበታልሳ ወገኖች! ረጋ ብላችሁ በጥሞና ኣንድታነቡኝ ብርታቱን ይስጣችሁ፥ 1• በዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ነባራዊ ሁኔታ ብሄር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በትክክል የሚነግራችሁ ሰው ኣታገኙም። የብሄር ፖለቲካ ኣቀንቃኞቹ ራሳቸው የሚግባቡበት ወጥ የሆነ የብሄር ትርጉም እንኳን የላቸውም። ብሄር ለኣንዳንዱ በቋንቋ ነው የሚገለፀው፤ ለሌላው በዘርና ትውልድ ሃረግ ነው […]

ሥርዐቱ በተለይም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ለሃይማኖታዊ ተልእኮ የሚጠቀሙ ሓላፊዎችና አማሳኝ የደኅንነት ግለሰቦች አሁን በተያዘው መንገድ ቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳንን አላግባብ ወደ መገዳደር ብሎም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ ተባብረው ወደ ማፍረስ የሚሸጋገሩ ከኾነ ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞው ጎራ ይጠናከራል፡፡ ይህም አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ለአርባና ኃምሳ ዓመታት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ …


(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 20/2006 ዓ.ም፤ ማርች 29/2014/ PDF)፦ ሥርዓተ ቅዳሴውን ለመምራት  ተሰይመው ለተመለከታቸው ከረጅሙ ነጭ ጽህማቸው  ጋር ውብ  የሆነውን  መረዋ  ድምጽ ሲሰማ ምድራዊ  ሳይሆን  ከሰማይ የተገለጠ መልአክ ይመስሉ ነበር፡፡ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተለየ ፍቅር ስለነበራቸው በተጋበዙበት መድረክ ሁሉ አክብረው በሰዓቱ ይገኛሉ፡፡ ለማስተማር ከተነሱም በትርጋሜ  የተዋዛ  ምስጢር አዘል ትምህርታቸውን ለምእመናን ቀምመው ያቀርባሉ፡፡ ለሃይማኖት ያላቸውን ቀናዊነት ለመረዳት በትምህርታቸው መግቢያ  የሚናገሩትን  መልእክት መስማት ብቻ በቂ ነው፡፡ ይህ የመግቢያ መልእክታቸው ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ያልተበረዘች ያልተከለሰች  መሆኛን የሚስረዱበት በተለያዩ ዘመናት የተነሱባትን መናፍቃን በመጥቀስ እነዚህ ሁሉ ያልበረዛት ያልከለሳት መሆናን የሚገልጹበት ነው፡፡ እናም በጥዑም አንደበታቸው ስለቤተ ክርስቲያን ሲናገሩ ለሰማቸው  የሊቃውንቱ ዘመን የእነ እትናቴዎስ ዘመን የሃይማኖት ቅናት በውስጣቸው እንዳለ ይረዳል፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ፡፡

በደብረ ሊባኖስ ገዳም መጻሕፍተ ሊቃውንትን ረዘም ላለ ጊዜ  በማስተማር  ቆይተው ነው  ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት፡፡ በገዳሙ ውስጥ ሲኖሩ የነበራቸውን መንፈሳዊ ሕይወት እና አንድምታውን የማስተማር ብቃት በወቅቱ የነበሩ አባቶች የሚመሰክሩት በታላቅ አድናቆት ነው፡፡ ሊቅነትን  ከመንፈሳዊነት   ጋር ይዘው በመገኘታቸውም ቤተ ክርስቲያን ለበለጠው አላፊነት አጭታ ለጵጵስና ማዕረግ በቅተዋል፡፡ መናፍቃንን  በተመለከተ ግልጽ የሆነ ቀጥ  ያለ አቃም ነበራቸው፡፡ፀረ  ማርያም  የሆነን  የተሐድሶ ጭፍራ መታገሥ አይችሉም፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነበረውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ሥሩን ነቅለው የጣሉበት የዲንነት ዘመናቸው ለዚህ ምስክር ነው፡፡ እንደእነ ቅዱስ ቄርሎስ የመናፍቃን መቀጥቀጫ መዶሻ ነበሩ፡፡ የኋላ ኋላ ይህ ቀናዒነታቸው እና  አድርባይ ሊሆኑ ያለመቻላቸው ጉዳይ  በቤተ ክህነቱ ውስጥ በተሰገሰጉ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ስላልተወደደላቸው እንዲጠሉና እንዲገለሉ አድርጓቸዋል፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ  ምርጥ ምርጡን ለወዳጆቼ በሚሉበት እንዳሻቸው ሃገረ ስብከት በሚያድሉበትም ዘመን አቃማቸውን ብዙም ስሎማይወዱላቸው ጠረፋማ ሥፍራዎች  ላይ እንዲመደቡ ሆነዋል፡፡ለነገሩ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ስለሚመደቡበት ሃገረ ስብከት ብዙም የሚጨነቁ  ስላልሆኑ ወደተላኩበት ሁሉ በደስታ  ይሄዳሉ፡፡ ፍሬም ያፈራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሰው ያለህ በምትልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ያለ አባት ማጣት ትልቅ ሀዘን ነው፡፡ ብፁዕነታቸው ወደ አገለገሉት አምልክ በክብር ቢሄዱም እኛ ግን በትልቁ ተጎድተናል፡፡
ወቅቱ በአጠገባችን ያሉ ጥቂት መንፈሳዊ አባቶችን በስስት የምንመለከትብት ነው፡፡ “አይቴ ሀለዉ ቀደምት ጳጳሳት፤ የቀደሙ አባቶች ደጋጎቹ ሊቃነ ጳጳሳት ወዴት አሉ?” እያልን ዘመን ገድባቸው የተለዩንን በሀዘንና በቁጭት የምናስታውስበት ነው፡፡ በግል ቂምና በቀል ቤተ ክርስቲያንን ለመናፍቃን አሳልፈው የማይሰጡ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚገባቸውን መከራ ሁሉ በጥብዓት የሚቀበሉ፣ ከአላውያን ነገሥታት እምነት የለሽ መንግሥታት ጋር የማይዛመዱ፣ በፍልስፍናና በምድራዊ ተድላ ተይዘው  በእምነት ጉዳይ  ቸልተኛ ያልሆኑ፣ መስሎ ለማደር ሲሉ ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጋር የማይተባበሩ፤ በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ ለትውልዱ ላለመተው የሚጠነቀቁ፤ እኔ ካልተነካሁ ሕዝቡም ሆነ አገልጋዩ ያሻውን መከራ ቢቀበል ምን አግብቶኝ ሲሉ የማይገኙ አባቶችን ተጠምተናል፡፡
እንደ ሙሴ ሕዝብህ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስስ የሚሉ፣ እንደ ነቢዩ  ኤልያስ  ስለ እግዚብሔር ክብር የሚቀኑ፣ እንደ ነቢዩ ዳዊት የተቀመጡበት ዙፋን የሚኖሩት የተድላ ኑሮ የተነሱበትን የማያዘናጋቸው፤ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ኃላፊያትና መጻዕያትን የሚረዱ፣ ሳይነገራቸው የመናፍቃንና የአላውያን ነገሥታት የጥፋት አካሄድ የሚገባቸው፡፡ እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን ተቀምጦ የሚታያቸው፣ ከምድራዊ ነገሥታት ከመዘመድ ይልቅ አደራውን ለሰጣቸው ለሰማዩ  ንጉሥ  መታዘዝ እንደሚበልጥ የሚረዱ፡፡ እንደ ሐዋርያት እስከ ሞት የሚታመኑ፡፡ እንደ ሊቃውንት መናፍቃንን የሚገስጹ፣ አልመለስ ያሉትንም የሚያወግዙ አባቶችን ተጠምተናል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አምላክ ነገን እንደ አትናቴዎስ ያለ አትናቴዎስ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የሚተካ ሌላ አባ ጊዮርጊስ  እንዲተካ አጥብቀን  እንለምነው፡፡ ለእርሱ ምን ይሳነዋል? ይህ ሁሉ ወጀብ አልፎ ደግ ዘመን ያመጣልን ይሆናል፡፡ ለሁሉም በሕይወት ያሉትን  ለተዋሕዶ ጠበቃና አርበኛ የሆኑ አባቶች ዕድሜ ያርዝምልን፡፡ ያረፉትን አባቶች በረከትም በያለንበት ያድለን፡፡ አሜን፡፡                                                                                                                        ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።  ቸር ወሬ ያሰማን።
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

በቅ/ሲኖዶሱ በይፋ ከተወገዙና በኑፋቄ አራማጅነት ከሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ ግንኙነት ያላቸውና በኅቡእ በሚንቀሳቀሱ ጥቂት ተማሪዎች የሚራመድ ነው ‹‹ችግሩን በዝምታ ለመመልከት ኅሊናችም ሃይማኖታችንም አይፈቅድልንም›› /ብዙኃኑ ደቀ መዛሙርትና የደቀ መዛሙርት ምክር ቤት አባላት ለእምነትና ሥርዓት የሚቆረቆሩ መምህራንና ተማሪዎች ‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችኹ› በሚል እንዲሸማቀቁ ይደረጋሉ (ዕንቊ፤ ቅጽ ፮ ቁጥር ፻፲፬፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን …

Image

የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።

በመለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ከማምራታቸው በፊት ኬንያ እንደነበሩ፣ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን ለምን እንደተጓዙ የዜናው ምንጮች በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲደበቅላቸው የጠየቁ የጋምቤላ አስተዳደር ባልደረባ ለጎልጉል የአካባቢው ዘጋቢ እንደተናገሩት አቶ ኦኬሎ ደቡብ ሱዳን ሆቴል በተቀመጡበት መታፈናቸውን አረጋግጠዋል።

“ወያኔ እጅ ገብቷል” ሲሉ ያከሉት እኚሁ ሰው “አቶ ኦኬሎ ብረት በማንሳት ወያኔን ለመታገል ከተነሱ ጋር ተቀላቅለዋል በሚል ስማቸው መመዝገቡንና ወደ ደቡብ ሱዳን ማቅናታቸው በመታወቁ ህወሃቶች እጅ ሊወድቁ ችለዋል” ብለዋል። ምንጩ ይህንን ይበሉ እንጂ አቶ ኦኬሎ አክዋይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑበትን ምክንያት በርግጠኛነት ሃላፊነት ወስዶ የገለጸ ወገን አልተደመጠም። ኢህአዴግም ቢሆን የቀድሞውን ሹመኛ ስለመያዙ ይፋ ያደረገው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ የኑዌር ተወላጅ ከሆኑት ሬክ ማቻር ጦር ጋር በመሰለፍ የሳልቫ ኪርን ሃይል ሲወጉ ከተገደሉ ወታደሮች መካከል የኢህአዴግን ሰራዊት መለያ የለበሱ ኑዌሮች መገኘታቸው ውዝግብ አስነስቶ እንደነበር ያመለከቱት ምንጭ “ደቡብ ሱዳን እየወጋት ካለው ኢህአዴግ ጋር አብራ የቀድሞውን የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳደር ከምድሯ ላይ እንዲታፈኑ መፍቀዷ ቅሬታ ያስነሳል” ብለዋል።

ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዛ ማቅናታቸውን ባሥልጣኑ “ታላቅ ጥፋት” ብለውታል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በቅርቡ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
goolgule.com/

የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፌዴራልም ሆነ የክልል ባለስልጣናት የተለያዩ ሕጎችን ደንቦች ሊያወጡ ይችላሉ። ነገር ግን ሕገ መንግስቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ መሰረታዊ የሕግ አንቀጾችን ማንኛዉም አካል ሊሽረው ወይንም ሊቀለብሰው አይችልም። የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 ዜጎች ነፍጥ ሳይዙ የመሰባሰብ፣ ሕዝባዊ ሰላምዊ ሰልፎች የማድረግ፣ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሙሉ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ድርጅቱ እንደሚለው በዚሁ ዓመት በዓለማችን በአጠቃላይ 778 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ። በድርጅቱ መግለጫ መሠረት በይፋ ከተፈፀሙ ከእነዚህ ቅጣቶች በተጨማሪ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቻይና በድብቅ በሞት ተቀጥተዋል ።

የወጣቶቹ አላማ ጧሪ የሌላቸውን፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ አረጋውያንንና የአዕምሮ ህሙማንን መርዳት ነው። ለዚህ ደግሞ 65 በጎ ፍቃደኞች አዲስ አበባ የሚገኘው «ሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ተቀላቅለዋል።ሶስቱን አነጋግረናቸዋል።

ስብሓት የንግግራቸው መነሻ ያደረጓቸውና ወጣት ሲሉ የጠሯቸው መነኩሴ ማን ናቸው?

Image

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም›› /አቶ ስብሓት ነጋ/
(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

አክራሪነት ይዘቱ ሃይማኖታዊ እንዳልኾነ ሕዝቡም የተገነዘበው ጉዳይ መኾኑ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ ሃይማኖትን የፖሊቲካ መድረክ የሚያደርጉት የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈጸም መኾኑ ግልጽ የኾነልን ይመስለኛል፡፡

አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ውስጥ ማስገባት የመጀመሪያው አደጋ ሲኾን በዚህ ኹኔታ ሃይማኖቱም ሃይማኖት አይኾንም፡፡ አማኞች፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነት በየሃይማኖታቸው ውስጥ ሲታይ ሃይማኖታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ) እንዳለውም፣ በጣም አስደናቂ የኾነውን የኢትዮጵያ ዕድገት ማደናቀፍ ከማንኛውም ወንጀል በላይ በሕዝብ ላይ ከባድ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ሲሠቃይ የነበረ በመኾኑ አሁንም ሕዝቡን ለሥቃይ መዳረግ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀል ነው፡፡

በማንኛውም ሃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በምንም ዐይነት ኹኔታ አንድም ሰው ለአንድ ደቂቃ እንኳ ተዘናግቶ መተኛት የሌለበት ሲኾን በተለይ ይህን ነገር በጥብቅ በሁሉም መንገድ መታገል አለብን፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት የሚቀናቀነው የውጭ ተቀናቃኝ ነው፡፡ የእነዚህን ተቀናቃኞች ዓላማ በመያዝ በአክራሪነትና በጽንፈኝነት መልክ ታላቅ ክሕደት መፈጸም ከባድ አገራዊ ክሕደት ነው፡፡ የውጭ ጠላት ቀላል ስላልኾነ አንድም ሰው ሳይቀር በጣም ተጠናክረን መመከት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የፖሊቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ሕገ መንግሥቱን የመጣስ ዝንባሌ ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መንግሥቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጸደቀው የራሱ ሕገ መንግሥት ስለኾነ ሕዝብ በመራራ ትግል ያጸደቀውን ሕገ መንግሥት መጣስ የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ግንዛቤ መያዙ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ ለውጭ ጠላት ደግሞ ሲጠብቀው የነበረ ብጥብጥ መቅረቱ ሕዝብን የሚያስደስት፣ ጠላትን ደግሞ የሚያሳፍር ነው፡፡

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነሣ ነበር፡፡ አንድ አባታችን ካነሧቸው ብዙ ነገሮች አንዱ፣ ‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን ያስገባል›› የሚል ነው፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡

ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡

ሁለተኛ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወጣት*የተነሣ ሐሳብ አለ፡፡ አክራሪነት አደጋ ነው ብሏል፡፡ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት አካባቢ በአንዳንድ ሰዎች የሚታየው አክራሪነት አደጋ ነው፤ ዋናው ግን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረው ፈንጅ ነው ትልቁ የአክራሪነት አደጋ ብሏል፡፡ አክራሪነት ማለት እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ማዋል፣ እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ መድረክ እያደረጓት ነው፤ ማኅበሩ** እንኳ ባይኾን አንዳንድ ሰዎች ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህን ተጠንቅቆ ያቀረበው ይመስለኛል፡፡ ማኅበሩ ነው አክራሪ ወይስ በማኅበሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ናቸው? መጣራት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ያሉ አንዳንድ ሰዎች ማኅበሩ ጤናው የተበከለ እንዳይኾን ማጣራት፣ ተጠንቅቆ መያዙ፣ እንደተባለው ፈንጅ ከኾነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣቱ* እና ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ሁለቱም ከባድ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደተባለው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእውነት የፖሊቲካ መድረክ እየኾነች ከኾነ፣ በዚህ አገር የትኛው አክራሪነት ነው ከተባለ፣ ትልቁ አደጋ ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው የተባለው ትክክል ነው ወይስ ትክክል አይደለም የሚለው መጣራት የሚኖርበት ቢኾንም በሁለቱ ሰዎች የተጠቆመው ግን የሚያስተኛ አይደለም፡፡ ከእምነቱ ቦታ የኾንም መተኛት የለብንም፤ የሌሎች እምነት አማኞችም መተኛት የለባቸውም፡፡

* * *

ሐራዊ ማስታወሻ፡-

*አቶ ስብሓት ወጣቱ ሲሉ የጠሯቸው የስብሰባው ተሳታፊ ከከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ከሚገኘው ሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመጡ አባ ዮናስ የተባሉ መነኩሴን ነው፡፡ እኒህ ስመ መነኮስ እንደ በጋሻው ደሳለኝ ላሉ ሕገ ወጥ ሰባክያን ዐውደ ምሕረት በመፍቀድና ምእመኑን ሰላም በመንሳት በወረዳው የማኅበሩ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ያደረጉ፣ ከትምህርቱም ከግብረ ገቡም የሌሉበት ግለሰብ ናቸው፡፡

መንግሥት አካሂደዋለኹ በሚለው የፀረ አክራሪነት ትግል አጋር መስለው የተጠጉ ግለሰቦች [የደብር አስተዳዳሪ ለማሾም 60,000 ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው 60 ጎራሽ የተባሉትንና ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተነሥተው ወደ መ/ፓ/ጠ/ቤተ ክህነት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ምክትል ሓላፊነት የተዛወሩትን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢን ርእሰ ደብር በሪሁ አርኣያን ይጨምራል] ያላቸውን አግባብነትና የሚሰጡትን መረጃ ትክክለኛነት (ቅንነት) ማጤን ይገባዋል፡፡

አቶ ስብሓት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚያራምዱትና በልዩ ልዩ ዘገባዎች ሲገለጽ የቆየው አቋማቸው በተለይ ከ፳፻፩ ዓ.ም ጀምሮ በሚገባ ይታወቃል፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም?›› ማለታቸው በአባባል ደረጃ ተገቢ ቢኾንም እርሳቸው የጠቀሱትን ሕገ መንግሥታዊ መብት ለማስከበር ቢያንስ በግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም በመጠኑ የሞከሩ ብፁዓን አባቶች ምን እንደደረሰባቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን የምንለው ሊቃነ ጳጳሳቱን ልናመሰግናቸው ፈልገን ወይም አቶ ስብሓት እንዳሉት ‹‹በሩን ከፍቶ ያንቀላፋ የለም›› ለማለት አይደለም፡፡ በሌላ መድረክ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ኹኔታው ምሬታቸውን በገለጹበት ወቅት ‹‹ብትሰየፉስ!›› ያሏቸው የመከራቸው ፍጻሜ ገና መኾኑን ስለሚያሳይ፡፡

አቶ ስብሓት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ለውጥ በቅ/ሲኖዶሱና በቀድሞው ፓትርያርክ መካከል የተደረገው የውስጥ ትግል በተጧጧፈበት ወራትና ከዚያም ወዲህ በእጅጉ ይጠሏቸው ነበር የሚባሉትን የቀድሞውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው ለማስወገድ ማኅበሩ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና ካገኘበት የአገልግሎት ዓላማና ስልት ውጭ ሚና ለመስጠትና መሣርያ ለማድረግ የገፋፉበት ኹኔታ በማኅበሩ ቀጣይ ህልውና ላይ ያላቸውን ፍላጎት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደነበር ይነገራል፡፡

ግፊታቸው በወቅቱ በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች መካከል ልዩነት ፈጥሮ እንደነበር የሚገለጽ ቢኾንም ተቀባይነት ያገኘ ግን አልነበረም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የቤተ ክህነት ዕዳ ነው›› በማለት ‹‹የተቃዋሚ ፖሊቲካ መድረክነት›› እንደሚታይበት ወዘተ ባለፈው ዓመት የፍትሕ ጋዜጣ ጽሑፋቸው የሰነዘሩበት ሒስም የዚያ ማወራረጃ እንደኾነ ይታሰባል፡፡

ማኅበሩ ከተመሠረተበት ዓላማና ከሚፈለግበት አገልግሎት አኳያ በድክመት የሚተችበትና ገና ብዙ እንደሚቀረው የብዙዎች እምነት ቢኾንም በሰሞኑ ስብሰባ አቶ ስብሓት ወጣቱ ባሏቸው አባ ዮናስ ጥቆማ በኩል አልፈውና የአባ ዮናስን ንግግር አጉነው ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሰጡት አስተያየት ወይ አቅጣጫ መነሻው ጥላቻ የወለደውና ቅንነት የጎደለው መረጃ እንደኾነ የመረጃው ጠቋሚ ሰው ስለ ማኅበሩ ባላቸው አቋምና በወረዳቸው ከማኅበሩ አባላት ጋራ ባላቸው ግንኙነት መረዳት አያዳግትም፡፡

መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘና ይህም በአክራሪነት ከተካሄደው ፍረጃ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

አባ ዮናስ ከእውነት የራቀ ጥቆማቸውን፣ አቶ ስብሓትም በዚሁ ላይ የተመሠረተ አስተያየታቸውን/አቅጣጫቸውን በሰጡበት መድረክ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ናትናአል ፣ አቡነ ኄኖክ፣ አቡነ ጎርጎሬዎስ በአጸፋ የመናገርና ምላሽ የመስጠት ዕድል ተነፍገዋል፡፡ ይኸው የስብሰባው አካሄድ ከአዳራሹ ውጭ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች መካከል በከፍተኛ ደረጃ አጠያይቆ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በውይይቱ ቤተ ክርስቲያን ከአክራሪነት አንጻር የተገለጸችበትንና ማኅበሩን አስመልክቶ የተሰነዘሩ ሐሳቦችን መንበረ ፓትርያርኩ በቀላሉ እንደማይመለከተውና በጥብቅ እንደሚነጋገርበት ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሚኒስቴሩ ሓላፊዎች እንዳሳሰቧቸውም ተገልጧል፡፡

Hara tewahdo

(የምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት – ፍኖተ ሰላም) የብፁዕነታቸው ልደትና ዕድገት ብፁዕ አቡነ ቶማስ በቀድሞው አጠራር በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በቆላ ደጋ ዳሞት አወራጃ በደጋ ዳሞት ወረዳ በመንበረ ስብሐት ዝቋላ ፬ቱ እንስሳ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ከአባታቸው ብላታ ተገኘ ይልማ ገብረ ሕይወት ከእናታቸው ከወ/ሮ ውድነሽ ቸሬ መጋቢት 14 ቀን 1935 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ‹‹ዘእንበለ እፍጥርከ አእመርኩከ ወዘእንበለ …


(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 19/2006 ዓ.ም፤ ማርች 28/2014/ PDF)፦ በዚህ የዘመነ ብላ ተባላ፣ ጸረ ሊቃውንት እና መፍቀሬ ተሐድሶ ዘመን በቤተ ክህነት ከቁንጮው እስከ ግርጌው ባሉ በልቶ አደሮች ሲገፉ ከኖሩት አባቶች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ነበሩ። አፈር ይቅለላቸው። ዕረፍታቸው እጅግ ቢያሳዝነንም ማንም ከዚያ ስለማይቀር የምንጸጸትበት አይደለም። እንዲህ የተማሩ ሊቃውንት እንደ ተርታ ሰው ወደጎን ተገፍተው ዳዊት ባልደገመ አፋቸው ነገረ ቤተ ክርስቲያንን የሚዘነጥሉ፣ ንብረቷን የሚዘርፉ፣ አሰረ ክህነታቸውን ያልጠበቁ ሰዎች የሚፏንኑበት እንዲሁም በፖለቲካ ቀረቤታቸው የቤተ ክርስቲያን ሳይሆኑ መቅደሷን የሚረመርሙ ሰዎች የሰለጠኑበት ዘመን መሆኑ ግን ያሳዝነናል። ሐዘን ብቻ ባይበቃም።

አቡነ ቶማስ አርፈዋል። ተተኪ ቶማስ እንዳይገኝ ግን የተዘራውን መልካም ዘር የሚያበላሹ ጥቃቅኑን ቀበሮዎች ማን አጥምዶ ይያዝልን? (መኃልይ 2፥15) ሊቃውንት በወንበራቸው እንደተከበሩ እንዲኖሩ የሚያደርገው ማነው? ይህ ሁሉ ፀረ ሊቃውንት ሹመኛ ሌላ የተዋሕዶ አርበኛ የሆነ ቶማስ እንዳይፈጠር ተግቶ ሲለፋ ርቱዕ እምነት የያዘው ኦርቶዶክሳዊ የአቅሙን ለማድረግ የሚተባበርበት ዘመን መቼ ይቀርባል?
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን፣
ጸሎታቸው ትድረሰን፤ አሜን
ቸር ወሬ ያሰማን።
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ሰሞኑን አንድ ኢትዮጵያዊ በቶሮንቶ የህሊና እስረኞችን ለመዘከር በግሉ አዳራሽ ተከራይቶ የአንዱዓለም አራጌን “ያልተሄደበት መንገድ” የሚለውን መጽሃፍ ለሽያጭ በአቀረበበት ቦታ ተገኝቼ ነበር። በዚህ አዳራሽ አንዱዓለምን፣ እስክንድርን፣ ርዕዮትን …ወዘተ ለመዘክር ብለው የተሰባሰቡ ሰዎች ብዛት ስመለከት “በእውነቱ እስረኞች እኛ ነን ወይስ እነ ዓንዱአለም?” የሚል ጥያቄ ጫረብኝ። አገርን ያህል ትልቅ ነገር ከራሳችን የፖለቲካና የግል ጠባብ ፍላጎት ዙርያ ቀንበበን ልንከተው […]

ወያኔ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም :: ሀገር ማለት የተለያዩ ብሄሮች ፣ የተለያዪ ጓሳዎች እና የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሎቸው ሰዎች መኖሪያ ናት :: እኛም ሀገራችን ብለን የምንጠራት ሀገራችን ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ያላት የተለያዩ ህዝቦች መኖሪያ ሀገር ስትሆን ሕዝቦቾም ለዘመናት በፍቅር፣ በመተሳሳብ ፣ በመከባባር እና በመተባባር አብሮ ሲኖር የነበሩ ህዝቦች እንደነበሩ ከታሪክ መረዳድ […]

ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ጽሁፉን በ.ፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ወያኔ ለኢትዮጵያ የቆመ መንግስት አይደለም  ወያኔ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም :: ሀገር ማለት የተለያዩ ብሄሮች ፣ የተለያዪ ጓሳዎች እና የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሎቸው ሰዎች መኖሪያ ናት :: እኛም …

ወያኔ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም Read more »

የወያኔ መንግሥት አክራሪነትን እና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ሽፋን ከተከተለው የኢትዮዽያን ህዝብ የማሸበር ዒላማ ያደረገ ፖሊሲና ይህን ፖሊሲ ለማስፈፀም ከሚሠራቸው በርካታ ፀረ ህዝብ ስራዎች አንድ ነገር መናገር ይቻላል፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢትዮጵያውያን ወደ ሁከትና ብጥብጥ፣ ብሎም ወደ ለስልጣኑ የሚያሰጋው ከሆነ እስከ መበታተን የሚደርስ እንደ እስሥት እራሱን እየቀያየረ የዘረኛ መርዙን ለ22 ዓመት ሲረጭብት ኖርዋል፡፡ ይህ የፀረ ሽብር አዋጅ ( ነፃነቱንና መብቱን የሚጠይቅ የሚታፈንበት ህግ) በህዝበ ላይ እንዲፈጠር በማድረግና በማስፈራራት “የዓለም አቀፉ ፀረ ሽብር ጦርነት” አጋርነቱን ማደስ፣ በዚህም ከአሜሪካና ከምዕራብ አውሮፓ አገራት የማያቋርጥ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ድጋፎችን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ያለፉት 22 ዓመታት ታሪክ የሚያሳየው፣ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ስለመብት መከበር የቆሙትን ሁሉ በየተራ ለማንበርከክ በፈጠራ ክሰ መወንጀል፣ ማሰርና ማሳደድ ብሎም መግደል ዋነኛ ስልቶቹ ሆነው መቆየታቸውን ነው። ይህንን የጥፋት አካሄድ ህጋዊ ለማስመሰልም ሰፊ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሥራ መስራቱ የተለመደ ነው። በአገር ውስጥ ለሚወስዳቸው ዴሞክራሲን የማቀጨጭ፣ነፃነትን የመገደብ፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ያለመቻል ችግሮች፣ በአጠቃላይም በአገሪቱ ውስጥ የሕግ የበላይነት አለመኖርን “በፀረ ሽብር ትግሉ አስገዳጅነት የተፈጠሩ” አስመስሎ ለማቅረብ ይፈልጋል፡፡ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እና የነፃነት ገደቦችን ሁሉ “የህዝብን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል በህጋዊ መንገድ የተጣሉ ገደቦች” የማስመሰል ፍላጎት እንዳለው ባለፉት ዓመታት ከወሰዳቸው ፖለቲካዊ እርምጃዎች እና እርምጃዎቹን ተገቢ ለማድረግ ካቀረባቸው ምክንያቶች መገንዘብ ይቻላል፡፡
… ምንም እንኳ ኢህአዴግ ኢትዮጵያውያን ያነሷቸውን የነፃነት ጥያቄዎች ለማፈን የ“ሽብርተኝነት” አቧራ ለማስነሳት እጅግ ቢደክምም፣ ራሱ መንግሥት ለህጋዊ እና ሰላማዊ የህዝቦች የመብት ጥያቄ ምላሽ እየሰጠ ያለው የ“ሽብርተኝነት” ተግባር በመፈፀምነው፡፡ በዚህም መሠረት በመጀመርያ የሞከረው፣ “አንድ ግደል፤ አሥር ሺህዎችን አሸብር” የሚለውን የቻይኖች አባባል ተግባራዊ ማድረግ ነበር፡፡
ኢትዮጵያውያን ወያኔ ሊገባው በማይችል ጠንካራ የአንድነት ገመድ ተሳስረዋል ፡፡ በወንጀለኛ የፌደራል ፖሊሶች የሚተኮሱ ጥይቶችና ከብረት የተሰሩ የግፈኛ በትሮች ጭቁኑን ህዝብ ለበለጠ ሰላማዊ ትግልና መስዋዕትነት ያዘጋጁታል እንጂ ከቶውኑም ከትግሉ አያሸሹትም፡፡

ከጭቆና በላይ ሽብር የለም። ምክንያቱም ጭቆና ማስፈራራት፣ ግድያ ……… ምናምን (ሰው ፈርቶና ተሸብሮ ሳይቃወም እንዲገዛ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች የሽብር ተግባራት ናቸው)። “ሽብር” ማለት’ኮ ኣንድ ኣካል ራሱ የሚፈልገውን ተግባር በሌሎች ሃይል በመጠቀም ወይ በማስፈራራት ለመጫን ሲሞክር ነው። ሌሎችን እያስፈራራ ያለው ማነው?ማነው ንፁሃን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን በየመንገዱ የገደለ ? ኣሸባሪ ማነው? ማነው ሰለማዊ ዜጎችን በማፈን እያሸበረ ያለው?

ወያኔ፣ ዓመታትን ባሰቆጠረው ግፍና የመብት ረገጣው፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በስነልቦና ሽብር አፍኖ፣ አንዱን የህብረተሰብ ክፍል በሌላው ላይ እንዲነሳ በማድረግ፣ የከፋፍለህ ግዛ መንገዱን በማጠናከር፣ የአምባገነን የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም እየጣረ መሆኑ ግልጥ ነው። ዛሬ በሀገራችን ውሰጥ፣ በወያኔ መብቱ ያልተረገጠ፣ የጥቃቱ ስለባ ያልሆነ የህብረተሰብ ክፍልን ማግኘት አይቻልም። ይህን መጠን የለሽ ረገጣ ለማስቆምና ዴሞክራሲያዊና ስብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የሚቻለው ደግሞ ሁሉም ዜጋ፣ በግልም ሆነ በጋራ፣ ለመብቱ መከበር “እምቢ አልገዛም” ብሎ ሲነሳ ብቻ ነው።
by Lemlem Kebede from Oslo Norway

[/imgwrap][/imgwrap]

በሽብር ፈጠራ ክሥ ተመሥርቶባቸው እሥር ቤት የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና የሌሎች ተከሣሾች ጠበቆች ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ጭብጦች ያልተሟሉና ግልፅነት የጎደላቸው በመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርጋቸው ፌደራል አቃቤ ሕግ ጠይቋል፡፡

የተከሻሽ ጠበቀች በበኩላቸው ለተቃውሞው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ በአፍሪካ የኢነርጂ ምርትና አጠቃቀም ዙሪያ እማኝነትን አዳምጧል።

ኰሚቴው የኦባማን አስተዳደር Powering Africa Initiative ወይም በአፍሪካ የኃይል ምንጭን ማዳረስ ጅማሮ የሚባለውን መርኃግብር እየፈተሸ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ትልቁ የአፍሪቃ ቀንድ ቤተ መፃህፍት እስከመባል በደረሰው በዚህ ተቋም ጥናትና ምርምሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የማድረግ እቅድ መኖሩን ሃላፊው ዶክተር አህመድ ሃሰን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

ባለፈዉ ሰምወን በኢትዮጵያንና በአካባቢዋ የሚገኙ ሃገራትን የእሥልምና ሥነ-ፅሁፍ ይዘትንና ታሪካዊ ፋይዳዉን የሚቃኝ አንድ ዓለም አቀፍ ጥናታዊ ጉባኤ አዲስ አበባ ዉስጥ መካሔዱ ይታወሳል። በዚህ ጉባኤ የእሥልምና ሥነ-ፅሁፍ በምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ በሚነገሩ በተለያዩ ቋንቋዎች ለረጅም ጊዜ የተለያዩ አገልግሎቶች ሲስጥ እንደነበር፤

በርስ በርስ ጦርነት በተመሰቃቀለችዉ ደቡብ ሱዳን ዉስጥ በሚሊዮኖች የሚገመቱ ዜጎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸዉ ተገለጸ። የተመድ የዝናቡ ወቅት እየቀረበ በመጣበት በዚህ ወቅት ለእርሻ መዘጋጀት በማይታሰበብት ሁኔታ የገጠመዉ የምግብ እጥረት የከፋ ቀዉስ እንዳያስከትል አስጠንቅቋል።

የግብፅ የጦር ኃይል አዛዥ አበደል ፈታህ አል ሲሲ የወታደራዊ የደንብ ልብሳቸዉን በይፋ የሚቀይሩበት ጊዜ ተቃርቧል። ትናንት ነዉ የጦር አዛዡ ከመከላከያ ሚኒስትርነታቸዉ በይፋ በመልቀቅ ለፕሬዝደንትነት ለመወዳደር መወሰናቸዉን ያስታወቁት።

ከፕሮፌሰር አለማየሁገ ብረማርያም

ትርጉም – በነጻነት ለሀገሬ

ማዳም ክላሬ አሸንፈዋል! እንኳን ደስ ያለዎት፣ ማዳም ክላሬ!

ባለፈው ሳምንት የ “አምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ሊቀ መንበር የሆኑት ማዳም ክላሬ ሾርት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም እና በማስፈራራት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የሙስና ማጋበሻ ቡድናቸው አባል እንዲሆን ለማስቻል የEITI የቦርድ አባላት ድምጻቸውን እንዲሰጡ በማድረጉ ጥረት ሲያካሂዱት የቆዩት ዥዋዥዌ ጨዋታ ተሳክቶላቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …


click here for pdf

በተፈጥሮ ካልተገኙና ሰው ልጅ ከፈጠራቸው ከማይንቀሳቀሱ የሥልጣኔ ውጤቶች አንዱ ከተማ ነው፡፡ ከተማ የአንድ ሕዝብ ሥልጣኔ የሚታይበትና የሚቀላጠፍበት ማዕከል ነው፡፡ በዚህም የተነሣ የሰው ልጅን ታሪካዊ ሂደት በመመዝገብና የደረሰበትንም ሥልጣኔ በማሳየት ረገድ የከተማን ያህል የተሻለ ቦታ የለም፡፡ የጥንታዊ ሰዎችን ሥልጣኔና ታሪክ የሚያጠኑ ባለሞያዎች የጉዞውን ሂደት የሚገልጡ መረጃዎችን የሚያገኙት በቁፋሮ ከሚገኙ ጥንታውያን ከተሞች ነው፡፡ በእነዚህ ጥንታውያን ከተሞች የሰው አነዋወር፣ ታሪክ፣ የመንግሥት አሠራር፣ የንግድና የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ ወግና ሥርዓት፣ እምነትና ባሕል በተሰናሰለና ሥርዓት በጠበቀ መንገድ ይገኝባቸዋል፡፡
በአብዛኛው የገጠሩ ማኅበረሰብ ባልተሰባሰበ፣ አንድ ወገን በሆነ፣ ግልጽ የአኗኗር መርሕ፣ አስተዳደራዊ መዋቅር እምብዛም ባልተዘረጋበት መንገድ የሚኖር ነው፡፡ የከተማ ማኅበረሰብ ግን በተወሰነ ቦታ፣ ከተለያየ ማኅበረሰብ ተውጣጥቶ፣ በአንድ ውሱን ሕግ እየተዳደረ፣ ለክዋኔዎች ቦታ ወስኖ(ለንግድ፣ ለአምልኮ፣ ለመንግሥት አስተዳደር፣ ለመኖሪያ፣ ወዘተ) የሚኖር በመሆኑ የሥልጣኔ መገለጫዎች በከተሞች የሚገኙትን ያህል በገጠር አናገኛቸውም፡፡ ሐውልቶች፣ አደባባዮች፣ አብያተ መንግሥት፣ ሳንቲሞች፣ የኪነ ጥበብ ሕንጻዎች፣ የተደራጁ ገበያዎች፣ የውኃ መሥመሮች፣ የከተማ መከለያ ግንቦች፣ የእምነት ማዕከሎች በከፍተኛ የሥልጣኔ ደረጃ ተሠርተው የምናገኛቸው በከተሞች አካባቢ ነው፡፡

በሀገራችንም የታሪክና ቅርስ ማዕከል የሆኑትን አኩስምን፣ ሮሐን፣ ሐረርን፣ ጎንደርን፣ አንኮበርን፣ አዲስ አበባን፣ ሌሎችንም ብንመለከተ የመንግሥት፣ የኢኮኖሚና፣ የእምነት መናኸሪያ ከተሞች የነበሩና የሆኑ ናቸው፡፡ በእነዚህ ቦታዎች የምናገኛቸውን እርስ በርስ የተግባቡ፣ የተሠናሠሉና የተመጋገቡ የሥልጣኔ መገለጫዎችን ያህል በሌሎች ቦታዎች አናገኝም፡፡ በሌሎች ቦታዎች የምናገኛቸው በተናጠል የተቀመጡ የሥልጣኔ መገለጫዎችን ነው፡፡
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ምክንያት ትናንትን ይጠይቃል፡፡ እንዲሁ ዛሬን ብቻ ዝም ብሎ አይቀበልም፡፡ እንደ ሥነ ፍጥረት ሊቃውንት ይህንን የሚጠይቁት መላእክትና ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ መላእክት በተፈጠሩ ጊዜ ‹‹ከየት ተገኘን? እንዴትስ ልንገኝ ቻልን?›› ብለው የጠየቁት ግእዛን ያላቸው (ማሰብና መመርመር የሚችሉና የሚያስፈልጋቸው) ፍጡራን በመሆናቸው ነው፡፡ የሰው ልጅም በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ዘመን ጀምሮ በእምነትና በፍልስፍና መስኮች ሲጠይቃቸው ከኖራቸው ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ዓለም ከየት መጣች?›› የሚለውን ነው፡፡
ሰው ትናንትን የማወቅ፣ ከትናንቱም የመማር፣ ከትናንት ተምሮም ወደፊት የመንደርደር ዕምቅ ፍላጎትና ችሎታ ስላለው መሬት እየጎረጎረ፣ ዋሻ እየበረበረ፣ ዐለት እየፈለጠ፣ ተራራ እየገለበጠ የጥንት ሰዎችን አድራሻ፣ ማንነትና ሥራ ሲመረምር ይኖራል፡፡
ሰው እንደ እንስሳ የዛሬን ብቻ ኑር ሊባል አይችልም፡፡ እንስሳ ትናንትም ነገም የለውም፡፡ ሰው ግን የሦስት ነገሮች ውጤት ነው፡፤ የትናንት አሻራ፣ የዛሬ ሥራ፣ የነገ ራእይ፡፡ ሰው ነገን ያለ ትናንት ማሰብ አይችልም፡፡ ተፈጥሮ አንድን ነገር ለብቻው በንጣሌ እንድንረዳው አልተወችንምና፡፡ ተፈጥሮ ራሷ የትይይዝ ውጤት ናት፡፡ ሊቃውንት ይህንን ለማስረዳት እንደ ቀላል ማሳያ የሚሰጡን ቀለማትን ነው፡፡ አንዱ ቀለም ከሌላ የሚግባባው ቀለም ጋር ስምምነት ፈጥሮ(harmony) ነው የሚኖረው፡፡ ይህንን የቀለማት ተግባቦት የሰዎች አለባበስ፣ የቤት አሠራር፣ የፀጉርና የሰውነት ቀለም፣ የሚተከሉ ዛፎችና እንዲፈጥሩት ይደረጋል፡፡ ምንም እንኳን እነዚህን ቀለማት አስበን ባንመርጣቸውም ተፈጥሮ ተግባቦትንና ስምምነትን ስለምትፈልግ ደመ ነፍሳዊ በሆነ መንገድ እናከናውነዋለን፡፡ 
በአንዲት ከተማ ሕይወት ውስጥም እንደ ቀለማቱ ተግባቦት ሁሉ ትናንት፣ ዛሬና ነገ ተግባብተው መገኘት አለባቸው፡፡ እንኳን እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከመቶ ዓመታት የዘለለ ታሪክ ያላቸው ከተሞች ቀርተው የቅርብ ዘመን የምሥረታ ታሪክ ያላቸው እነ ዱባይ እንኳን አንዳች ከጥንታዊነት ጋር የሚያያዝ ታሪክ ፍለጋ ሲኳትኑ፣ ያንንም ለማሳየትና የከተማቸው የሕይወት አካል ለማድረግ ሲጥሩ እናያቸዋለን፡፡
በአንድ ከተማ ሕይወት ውስጥ በሳል ነቢብ(ቲወሪ)፣ አመራርና አሠራር ከሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አንዱ ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን ከከተማዋ ዕድገት፣ ሥልጣኔና የአነዋወር ዘይቤ ጋር አጣጥሞ የመሄድ ብልሃት ነው፡፡ የከተማዋ ጥንታዊነት የዛሬ ዕድገቷንና የነገ ተስፋዋን እንዳይገታው፤ የከተማዋ የዛሬ መስፋፋት፣ ዕድገትና ሥልጣኔ የትናንት አሻራዋን እንዳያጠፋው፤ የከተማዋ የትናንት ታሪክና የዛሬ ዘይቤም የነገውን ትውልድ ድርሻና ዕጣ ፋንታ እንዳያቀጭጨው – በሳል የሆነ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ይጠይቃል፡፡
የአንዲት ከተማ መልክዐ ጠባይ፣ ሕይወትና እሴት የሚገነባው ከዚህ መሰሉ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ነው፡፡ የከተማዋ ሕንጻዎች፣ መኖሪያዎች፣ መንገዶች፣ የሕዝብ ቦታዎች፣ ገበያዎች፣ የእምነት ቦታዎች፣ ማኅበራዊ ተቋማት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ ጽዳትና ውበት፣ ከዚህ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ይወለዳሉ፡፡ የሚፈቀዱና የሚከለከሉ ነገሮች ከዚህ ይመነጫሉ፤ የሚጠበቁና ለሕዝብ ክፍት የሚሆኑ ነገሮች ከዚህ ይመሠረታሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ቁልፍ ችግሯ ትናንት፣ ዛሬና ነገን የምታግባባበት የራስዋ የሆነ፣ በዘመናት የዳበረ፣ የተፈተነና ውጤታማነቱ የተመሰከረለት ‹ነቢብ፣ አመራርና አሠራር› ማጣት ይመስለኛል፡፡ በአንድ የውይይት መድረክ አንድ የከተማ ዐቅድ ባለሞያ እንደገለጡት ‹‹አዲስ አበባ እያንዳንዱ መንግሥት የየራሱን ርዕዮተ ዓለም ያነባበረባት ከተማ ናት – The layer of different Ideologies ፡፡ ያ ነው ከተማዋን ሲምታታባት እንዲኖር ያደረገው››
አዲስ አበባ አሁን ዐሥረኛውን የከተማ መሪ ዕቅድ እያዘጋጀች ነው፡፡ እነዚህ መሪ ዕቅዶች ምንም እንኳን ሳይንሳዊ አሠራርን የተከተሉ ሞያዊ ሥራዎች ቢሆኑም የሚዘወሩት ግን በየዘመናቱ ሀገሪቱ በምትመራባቸው ርእዮተ ዓለሞች ነው፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ አዲስ አበባ ‹ወጥ፣ ለዘመናት የዳበረ፣ የተፈተነና የተመሰከረለት የከተማ ዘይቤ› እንዳይኖራት አድርጓታል፡፡
ባለፈው መንግሥት ጊዜ የቁጠባ ቤቶች የአዲስ አበባ የቤቶች መልክዕ ሆኖ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ኮንዶሚኒየምና ሪል እስቴት የአዲስ አበባ የቤት መልክዕ ሆነዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከንቲባነት ለረዥም ዓመታት በማገልገል የሚታወቁት ከንቲባ ዘውዴ እንደሚሉት በአዲስ አበባ ቀበሌ ሲቋቋም ከ2500 – 4000 የሚደርስ ሕዝብ የሚይዝ አንዳች የጉርብትና ማዕከል ለመፍጠር ነበር፡፡ ጉርብትናን ዘመናዊ ለማድረግ፡፡ ‹ከተማ ማለት የጉርብትና ሥርዓት ነውና›፡፡ ርእዮተ ዓለሙ ሲቀየር ግን ቀበሌዎች የጉርብትና ማዕከላት መሆናቸው ቀርቶ የቀይ ሽብርና የነጭ ሽብር ማዕከላት ሆኑ፡፡ ቀበሌ ማለትም የአብዮት ማራመጃ ማዕከል ሆነ፡፡ በሀገራችን መንግሥታት የሚቀያየሩት በመፍረስ በመሆኑ በመንግሥታት መካከል ርክክብ አልተደረገም፡፡
ይህንን መሰሉ በየጊዜው የሚለዋወጡ ነቢቦች፣ አመራሮችና አሠራሮች አንዳቸው ከሌላቸው ጋር ተግባብተው የሚመሠረቱ ባለመሆናቸው አዲስ አበባ ስትፈርስ ስትሠራ የምትኖር መሞከሪያ ከተማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ እንኳንስ በተለያዩ መንግሥታት ርእዮተ ዓለሞች መካከል ቀርቶ በአንድ መንግሥት ዘመናት እንኳን ሲያፈርሱ ሲሠሩ መኖር እየተለመደ መጥቷል፡፡ ከሸራተን አካባቢ የተነሡ ነዋሪዎች ለድጋሚ ተነሺነት የተጋለጡት በዚህ ያልተግባባ አሠራር ጭምር ነው፡፡ አዳዲስ ቤቶች እንደገና ለመንገድና ለሌሎች ግንባታዎች ተብለው የተሠሩበት ሲሚንቶ ሳይደርቅ እንዲፈርሱ የሚደረጉት በዚህ ወጥነት በሌለው የከተማዋ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር የተነሣ ነው፡፡ በተሠሩ በጥቂት ዓመታት ለባቡር ተብለው የፈረሱትንና 900 ሚሊዮን ብር የፈጁትን የአዲስ አበባ መንገዶችን በዚህ በበሰለ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ብቻ ነበር ማትረፍ ይቻል የነበረው፡፡ አንድም ቀድሞ በማሰብ፣ አለያም አጣጥሞ በመሥራት፡፡ 
አዲስ አበባ ዕድገቷንና ታሪኳን የማጣጣም ፈተና ገጥሟታል፡፡ ለመሆኑ ያለፉ ነገሮቿን ሁሉ እንዳሉ ይዛ መቀጠል አለባት? ያለፉ ነገሮቿንስ ሙሉ በሙሉ አፈራርሳስ መቀጠል አለባት? ለመሆኑ ታሪክና ዕድገት፣ ቅርስና ሥልጣኔ እንዴት ነው የሚጣጣሙት? ከተማዋ እነዚህን በትክክል ካልመለሰች ከተማ ሳይሆን ዘመናዊ የሰው ልጅ ማጎሪያ ትሆናለች፡፡ ዛሬ የሚሠሩት ታላላቅ ግንባታዎቻችንስ የነገውን ትውልድ ሥልጣኔ፣ አነዋወርና ፍልስፍና ከግምት ውስጥ እያስገቡ ናቸው? የዛሬ አምስት ዓመት የገነባናቸውንና ስናስመርቃቸው ጉሮ ወሸባ ያረገድንባቸውን እንዲህ በፍጥነት የምናፈርስ ከሆነ ሌሎቹን እንድንጠራጠር ያደርገናል፡፡
አሁን አሁን አዲስ አበባ ትናንትን ከዛሬ፣ ዛሬንም ከነገ የሚያጣጥም ነቢብ፣ አመራርና አሠራር በማጠቷ ምክንያት የአዲስ አበባ ከተማን ጥንታዊነት የሚያሳዩ ቅርሶች እንደ ነፍጠኛና ፊውዳል መገለጫዎች እየተቆጠሩ፣ ቀጥታና ቀጥታ ያልሆነ ሞት እየተፈረደባቸው ነው፡፡ ቀጥተኛ የሆነ ሞት የሚባለው ለዕድገት ፀር፣ለግንባታ ዕንቅፋት፣ ለመስፋፋት እንከን አድርጎ በማየት የማፍረስ ርምጃ መውሰድ ነው፡፡ በዚህ ፍርድ ምክንያት ጥንታውያን መንደሮች፣ ቤቶች፣ ድልድዮች፣ ሐውልቶች፣ አደባባዮች፣ የንግድ ማዕከላት፣ እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡
ሁለተኛውና ቀጥታ ያልሆነ ሞት የምንለው ደግሞ እነዚህን ጥንታውያን ሀብቶች የመከባከብ ኃላፊነት ያለበት አካል ክብካቤ በመንፈግና ቀስ በቀስ እንዲፈርሱ ሆን ብሎ በመተው የሚደረግ ግድያ ነው፡፡ ይህ ፍርድ የተፈረደባቸው ቅርሶች በአካባቢያቸው ለእነርሱ ሕልውና አሥጊ የሆነ ሥራ ሲከናወን የሚያስጥላቸው የለም፤ የቆሻሻ መጣያ ሲሆኑ በዝምታ ይታለፋሉ፤ ሲፈርሱና ሲበላሹ በዝምታ ይታያሉ፤ ሲዘረፉና ሲወሰዱ የሚያስጥል አያገኙም፤ ጥበቃ አይደረግላቸውም፤ ሞያ በሌላቸው አካላት እንዲጠገኑ ይደረጋል፤ ታጥረውና ተከልለው እንዲቀመጡ ይደረጋል፤ በውስጡ ነዋሪዎች ሲቀመጡባቸውና ግንባታ ሲያከናውኑባቸው ተከታታይ አይኖርም፤ በጢስና እሳት እንዲበላሹ ይተዋሉ፡፡
በአንድ በኩል ያለፈው ነገር ሁሉ መነካት የለበትም የሚሉ የታሪክና ቅርስ ወግ አጥባቂዎች (ወግ አጥባቂነት አዎንታዊ ነው) አሉ፡፡ እንደ እነርሱ ከሆነ የአዲስ አበባ ነባር ነገሮች ሁሉ ተጠብቀውና ተከብረው መኖር አለባቸው፡፡ እነርሱ የከተማዋን፣ ብሎም የሀገሪቱን ጥንት የሚመሰክሩ ናቸውና፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በቦታው ላይ የሚሠራ ሌላ ነገር እስካለ ድረስ የጥንቱ መፍረስ አለበት፡፡ የጥንቱ ጥንት አገልግሏል፡፡ አሁን ዘመኑ የዛሬ ነው፡፡ ጥንቱ ለዛሬ ዕንቅፋት ከሆነ ያለው ዕድል መፍረስ ብቻ ነው ይላሉ፡፡
እነዚህ ሁለቱም ለእኔ ጽንፎች ናቸው፡፡ ሁሉም የጥንት ነገር እንዳለ ሊቀመጥ አይችልም፡፡ በሦስት ምክንያት፡፡ አንድ ሁሉም የጥንት ነገሮች እኩል የሆነ ታሪካዊ፣ ቅርሳዊና ባሕላዊ ዋጋ የላቸውም፤ ሁለተኛ ደግሞ ሁሉም የጥንት ነገሮች ይቀመጡ ካልን ለአዳዲስ ነገሮች ቦታ ላይገኝ ይችላል፤ በመጨረሻም ሁሉንም የጥንት ነገሮች ለማቆየት፣ ለመጠበቅና ለመከባከብ ዐቅም ያስፈልጋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ለአዳዲስና ለዘመናዊ ነገሮችና ሐሳቦች ሲባል ሁሉንም የጥንት ነገሮችን በግዴለሽነት ማፈራረስ ሦስት ጉዳቶች ያስከትላል፡፡ የሰው ልጅን የጥበብ፣ የባሕል፣ የሥልጣኔና የክሂሎት አሻራ ያጠፋል፤ አንድን ነገር ምንጊዜም እንደገና እንድንጀምረው በማድረግ ተያያዥና ተደጋጋፊ ነገርን ያሳጣል፤ በመጨረሻም የከተማዋን የቱሪዝም ገቢ ያመክናል፡፡ 
እነዚህን ሁለት ጽንፎች ለማስታረቅ የሁለቱንም አዎንታዊነት የያዘ አንድ ሌላ መንገድ ያስፈልጋል፡፡ እርሱም አዳዲስ ነገሮችን ከጥንታውያን፣ ዘመናዊነትን ከነባርነት፣ ታሪክን ከዕድገት፣ ቅርስን ከሥልጣኔ ጋር አስማምቶ፣ አደጋግፎና አመጋግቦ መምራት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ወጥነት ያለው፣ በየዘመናቱ የሚዳብር በሳል ሀገራዊ ፍልስፍና ያስፈልጋል፡፡
ይህንን መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚከተሉት አካሄዶች ያስፈልጋሉ
  1. የከተማዋን ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች የመለያ መመዘኛ ማስቀመጥ
  2. በመመዘኛው መሠረት የከተማዋን ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች በዝርዝር መለየት
  3. እነዚህ የከተማዋ ቅርሶች በልዩ ልዩ መንገድ ለትውልድ የሚተላለፉበትን መሥፈርት ማውጣት
  • እንዳሉ ባሉበት ሁኔታ ለሌላ አገልግሎት ሳይውሉ ለትውልድ መተላለፍ ያለባቸው
  • መጠናቸው ተቀንሶ ናሙናቸው መተላለፍ ያለባቸው( ለምሳሌ አንድን መንደር ሙሉውን ቅርስ አድርጎ ማቆየት ከባድ ቢሆን እንኳን ያ መንደር ምን ይመስል እንደነበር የሚያሳይ አንድ ናሙና ቦታ ለይቶ ማቆየት ይቻላል)
  • በልዩ ልዩ የመቀረሻ መሣሪያዎች(ፎቶ፣ ሥዕል፣ ቪዲዮ፣ ወዘተ) ተመዝግበው መተላለፍ ያለባቸው(አንዳንድ ሠፈሮች የቀድሞ መልካቸውና አሠራራቸው በልዩ ልዩ መቀረሻ መንገዶች ቀርጸ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል)
  • ወደ ሙዝየም ገብተው መተላለፍ ያለባቸው
  • ቅርስነታቸውንና ይዞታቸውን በማይጎዳ መንገድ ለሌላ የማይጣረስ አገልግሎት ተላልፈው ግን ተጠብቀው መተላለፍ ያለባቸው(ጣይቱ ሆቴል እንደተደረገው)
  • ቦታቸውን ቀይረው በቅርስነት መጠበቅ ያለባቸው
  • ማናቸውም ከተማዊ እንቅስቃሴዎች ከእነዚህ የተመዘገቡ ቅርሶች ጋር ያላቸውን ተግባቦት በቅርብ መከታተል፣ ለክትትሉም እንዲያመች የሚመለከተው አካል ከማናቸውም ግንባታ በፊት አካባቢው ከቅርስ ነጻ መሆኑን ምስክርነት እንዲሰጥ ማድረግ
  • የከተማዋ መሪ ዕቅድ ሲዘጋጅም እነዚህን ታሪካዊ ቦታዎችና ቅርሶችን በሚገባ የለየና የእነርሱን የሕልውና መብት የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ
  • በታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች አካባቢ ይፋዊ መለያ መለጠፍ፤ ይህ ምልክት የተለየ ቀለም ወይም ዐርማ እንዲኖረው በማድረግ ማንኛውም ሰው እንዲለየው ማስቻል
  • የፌዴራል ቅርስ አዋጅ ቁጥር 209/92 ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች ምንም ዓይነት ሥልጣን ስለማይሰጥ ይህንን ማስተካከል
  • የታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች አካባቢዎች የተዛማጅ ልማቶች ማዕከል (የሆቴል፣ የጥበበ ዕድ መሸጫ፣  የዐውደ ርእይ ማሳያ፣ የባሕላዊ ገበያዎች) መጠቀም
  • በተማሪዎች፣ በአካባቢው ነዋሪዎችና በቱሪስቶች እንዲጎበኙ መርሐ ግብሮችን ማመቻቸት

  • እነዚህንና የመሰሉትን ተግባራት በጊዜ ማከናወን ካልቻልን አዲስ አበባ ‹ትናንት የሌላት ከተማ› ትሆናለች፡፡ ያውም በታሪክ አጋጣሚ ሳይሆን ሳያስቡ የሚሠሩ አመራሮችና ነዋሪዎች ስላሏት ብቻ፡፡ ከተማ እንደ ፈጣን ምግብ(fast food) ለዕለት ሆድ መሙያ የምትሠራ አይደለችም፡፡ እንደ ገጠር ጠላ ለነገም ጭምር የምትጠነሰስ ናት፡፡ ከተማዋን ለሰዎች መኖሪያነት ምቹና ተመራጭ ለማድረግ መንገድ፣ ሆቴል፣ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ፣ ባቡር፣ ሱፐር ማርኬት፣ የገበያ ማዕከል፣ የግል ኮሌጅ፣ ዓለም ዐቀፍ ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ብቻቸውን በቂ አይደሉም፡፡ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባሕላዊ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ እሴቶች፣ ቅርሶችና ቦታዎችም ያስፈልጓታል፡፡ እነዚህ ራሳቸው ነገ ታሪክና ቅርስ ስለሚሆኑ፡፡ ከተማ እንደ ላም ዱካ የሚተው እንጂ እንደ አዞ በጅራታቸው ዱካ የሚያጠፉ አመራሮች አያስፈልጓትም፡፡

     © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

    abuna tomas 2(MKWebsite):- የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዐረፉ:: የቀድሞ ስማቸው አባ መዘምር ተገኝ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ጥር 14 ቀን 1932 ዓ.ም ጎጃም ደጋ ዳሞት ዝቋላ አርባዕቱ እንስሳ ተወለዱ፡፡ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን በሚገባ ከተማሩ በኋላ ጸዋትወ ዜማን ከመሪጌታ አንዱዓለምና መሪጌታ ካሣ ይልማ ፣ ቅኔ ከመሪጌታ ፈንቴ /ዋሸራ/፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትን ከመሪጌታ ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ ፣ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከመሪጌታ ቢረሳ ደስታ ተምረዋል፡፡ በዘመናዊ ትምህርትም እስከ 6ኛ ክፍል ፣ የእንግሊዝኛን ቋንቋ በግላቸው የተማሩና የመኪና ጽሕፈት /type writing/ የሚያውቁ ነበሩ፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዲቁና ከአቡነ ማርቆስ፣ ቅስና ከአቡነ ባስልዮስ፣ ቁምስና ከብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት ተቀብለዋል፡፡

    በደብረ ሊባኖስ ገዳም መጻሕፍተ ሊቃውንትን ረዘም ላለ ጊዜ አስተምረዋል፡፡ በገዳሙ የሠራተኞች ቅርንጫፍ ማኅበር ሲቋቋምም የመጀመሪያው ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በአስተዳዳሪነትና መጻሕፍተ ሓዲሳትንና ሊቃውንትን በማስተማር የሚጠበቅባቸውን ተልእኮ ተወጥተዋል፡፡ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አንብሮተ ዕድ ተሹመው ሰፊ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመመለስ የታእካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና መንበረ መንግሥት ግቢ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሆነው አገልግለዋል፡፡
    ብፁዕነታቸው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው፤ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 16 ቀን 2006 ዓ.ም መንበረ ጵጵስናቸው በሚገኝበት በፍኖተ ሠላም ከተማ ዐርፈዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በዚያው በፍኖተ ሰላም እንደሚፈጸም ይጠበቃል፡፡
    Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

    ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

    Image

    በኢትዮጵያ የውጭ እርዳታ ይጎርፋል፤ በግርድፉ ከ40-50 ቢሊዮን ዶላር ባለፉት 22 አመታት ተለግሷል። ወደ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብም ተበድረናል፡፡ የውጭ ኢንቨስትመንትም ይፈሳል፤ ግንባታዎችም ይካሄዳሉ። በእነዚህ ፈንድሻ ዜናዎች መሃከል ግን ብዙ ችግሮችም አሉ። ውሃ ፣ መብራት፣ ስኳር እና ዘይት በፈረቃ ይከፋፈላሉ፤ ትራንስፖርት ችግር ነው፤ በቀን ሶስት ጊዜ ለመብላት ጭንቅ ነው፤ ነጻነት፣ ፍትህ፣ ሰብዓዊ መብት የሚባሉት ነገሮች ከመንግስት መዝገበ-ቃላት ተሰርዘዋል።

    የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንድ ልዩ ባህሪ አለው። እንደሚታወቀው ልማትና ድህነት ተጻራሪ ሃይሎች ናቸው። ሁለቱ ሃይሎች በአንድ አቅጣጫ መጓዝ አይችሉም። ልማት ወደ ግራ ከሄደ ድህነት የግድ ወደ ቀኝ መጓዝ አለበት። በሃይማኖታዊ ቋንቋ ሰይጣንና መላዕክ ማለት ናቸው። አንዱ ባለበት ቦታ ሌላው ድርሽ አይልም። ይሄ ህግ ተዛብቶ “ልማትና ድህነት በአንድ ላይ ተቃቅፈው ታንጎ የሚጨፍሩበት አገር የት ነው? ” ከተባለ ያች አገር ኢትዮጵያ ናት። ልማቱ አደገ ሲባል፣ ድህነቱም በዚያው ልክ ያድጋል።

    አገሪቱ ለ10 ዓመታት በ11 በመቶ እንዳደገች ከተነገረ በሁዋላ እንኳ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ( ምግብ፣ መጠለያና ልብስ) ማሟላት ጭንቅ ሆኗል። የልማቱን ኬክ ጥቂቶች ይበሉታል፣ ብዙዎች ፍርፋሪውን እንኳ አጥተው በረሃብ ያሸልባሉ። ቀኑ ይርዘም እንጅ የባስቲሌ አመጽ በአራት ኪሎ መደገሙ አይቀሬ ነው፤ ድህነትና ልማት ተጣምረው ታንጎ በሚደንሱባቸው አገሮች ማህበራዊ ምስቅልቅል የመጨረሻው ምርት ይሆናል።

    የገዚው ፓርቲ ካድሬ ኢኮኖሚስቶች “ልማቱ ጤነኛ አይደለም” ተብሎ ሲነገራቸው አይቀበሉም፤ ክርክር ሲነሳም ብዙውን ጊዜ የሚሰጡት መልስ ” የሚቀጥለው ትውልድ ያልፍለት ዘንድ ይህኛው ትውልድ መስዋትነት መክፈል አለበት” የሚል ሆኖ ይገኛል። በካድሬው አስተሳሰብ ይሄ ትውልድ ጨለማ ውስጥ ቢኖር፣ የሚቀጥለው ትውልድ መብራት እንደልቡ ያገኛል፣ ይሄ ትውልድ ውሃ ቢጠማው ፣ መጪው ትውልድ በጁስ ይራጫል፣ ይሄ ትውልድ ትራንስፖርት ቢቸግረው፣ መጪው ትውልድ በቤት መኪና ይንበሻበሻል ።

    የካድሬ ኢኮኖሚስቶች ዋና አላማ ይሄ ትውልድ የመብትና የማህበራዊ ግልጋሎት ጥያቄዎችን እንዳያነሳ የተስፋ ዳቦ እየመገቡ ማዘናጋት ነው፤ አንዳንዴ የሚገነቡ መንገዶችን እያሳዩ ” የወደፊቱ ልጅህ መኪናውን የሚያሽከረክርበት ነው፣ ዘመናዊ ህንጻዎችን እያሳዩ ” የወደፊቱ ልጅህ የሚኖርበት ቤት ነው” እያሉ ያማልሉታል። ይሄ ትውልድ የውሃና የመብራት ጥያቄ ይሟላልኝ ብሎ እስካልተነሳ ድረስ የዛሬው ካድሬ ጭንቀት የለበትም፤ ለመጪው ጊዜማ የመጪው ትውልድ ካድሬ ይጨነቅበታል። “ለመሆኑ መጪው ትውልድ የሚባለው ስንተኛው ትውልድ ነው? የሚቀጥለው ትውልድ እንደሚያልፍለትስ ማረጋገጫው ምንድነው?” እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ለካድሬ ኢኮኖሚስቶች መጠየቅ የሌለባቸው” ነውር ” ናቸው።

    “ይሄ ትውልድ ለመጪው ትውልድ ሲል መስዋትነት መክፈል አለበት” የሚለውን የካድሬ ቅስቀሳ አምነው የተቀበሉ ሰዎች አጋጥመውኛል። እነዚህም ሰዎች በፊናቸው”ልማትና ዲሞክራሲ በአንድ ጀምበር አይመጣምና ታገሱ ” ሲሉ ከካድሬው የሰሙትን ስብከት መልሰው ለሌሎች ሰዎች ለማስረዳት ሲሞክሩ አይቻለሁ። እንዲህ አይነቱ ስብከት ዜጎች ለመብታቸው እንዳይነሱ በማድረግ በኩል የራሱ አስተዋጽዎ አለው። መሰረታዊ ለውጥ በአገራችን እንዲመጣ የሚፈልጉ ሃይሎች እንዲህ አይነቱን የማዘናጊያ ቅስቀሳ ፣ በእውቀት ላይ በተመሰረተ ክርክር ሊመክቱት ይገባል። በኢትዮጵያ ስላለው ልማትና ድህነት የጠራ ግንዛቤ መያዝ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ የሚደረገውን ትግል ያግዛልና ሁሉም አስተያየቱን ሊሰጥበት ግድ ይላል።

    በቀድሞው የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ሊ ኩዋን ስም የተሰየመ “የሊ ንድፈ ሃሳብ” የሚባል በፖለቲካ ኢኮኖሚ ትምህርት ውስጥ የሚገኝ አስተሳሰብ አለ። ይህ አስተሳሰብ ዜጎችን ከብዙ ጊዜያዊ መብቶቻቸው በመገደብ ልማትን ለማምጣት የሚያልም ሲሆን፣ ዳቦን ከመብት እንዲሁም አምባገነንነትን ከዲሞክራሲ ያስቀድማል ። በዚህ አስተሳሰብ መነሻነት ኢኮኖሚያቸውን የመሩ የእስያ ነብሮች የሚባሉ አገሮች ድህነትን “ቻው” ለማለት እንደቻሉ ይነገራል ። ኢህዴግም የዚህ አስተሳሰብ ተከታይና አራማጅ ነው። አስተሳሰቡ ለብዙ አምባገነን መንግስታት የሚጥም፣ ያለ ገደብ በስልጣን ላይ ለመቆየትም እንደምክንያት ሆኖ የሚያገለግል ” ተወዳጅ” አስተሳሰብ ሆኖ ተገኝቷል- በአንባገነኖች ዘንድ። አቶ መለስም ይህን ሃሳብ መነሻ አድርገው ” ዲሞክራሲና ልማት ግንኙነት የላቸውም” የሚል የመመረቂያ ጽሁፍ መጻፋቸውን ሰምቻለሁ፣ ባላነበውም። የኖቤል ተሸላሚው አማርትያ ሴን የነጻነትና የልማት ግንኙነቶችን የሚያሳይ ውብ መጽሃፍ ባይጽፉ ኖሮ ፣ “ልማት ያለነጻነት ዋጋ የለውም” እያልን የምንጮኸውን ጩኸት ትንሽም ቢሆን የሚሰማን አናገኝም ነበር። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በዘር ተደራጅተው አገር ከሚመሩት መንግስታት በስተቀር ዛሬ አብዛኛው አለም፣ ነጻነት ለልማት አስፈላጊ መሆኑን ይቀበላል። የእስያ ነብሮች ያደጉት ከነጻነት በፊት ልማትን ስላስቀደሙ ነው የሚለው መከራከሪያም ብዙ አሳማኝ ሆኖ አልተገኘም፤ የእስያ ነብሮች እድገት የራሱ የሆኑ ብዙ ፖለቲካዊና ስትራቴጂካዊ ምክንያቶች አሉት። በተለይ ስለ ቀጣይ እደገት (sustainable development) ስናስብ፣ ነጻነት እጅግ አስፈላጊ ነገር መሆኑን ከአረብ አገራት አብዮትና ውድመት ተምረናል። ነጻነት ከሌለ ዘላቂና ለትውልድ የሚተላለፍ ልማት አይኖርም፤ ዛሬ የተጀመረው ልማት ነገ ለነጻነት በሚደረግ ትግል የሚወድምበት አጋጣሚ ከፍተኛ ነው። ለዚህ ደግሞ ሊቢያ፣ ሶሪያና ግብጽ ምስክሮች ናቸው። ቻይናም ቢሆን ፖለቲካዊ ለውጥ ካላደረገች እጣፋንታዋ መስቅልቅ ነው።

    “ከነጻነት በፊት ልማትን እናስቀድም” የሚሉ አምባገነን መንግስታት፣ ልማት በእነሱ ብቻ እንደሚመጣና እነሱ ከሌሉ ልማቱ እንደሚደናቀፍ በማስወራት እድሜ ልክ በዙፋኑ ላይ ለመቀመጥ ያልማሉ። ይህን ህልማቸውን እውን ለማድረግም ” አሳማኝ የሚመስሉ” የኢኮኖሚ ትንተናዎችንም ያቀርባሉ። ከእነዚህ ትንተናዎች አንዱ ይህን ይመስላል ፦ “የካፒታሊዝም ስርአት ለሰዎች ኑሮ መሻሻል አስፈላጊ ነው። ስርአቱ እውን ይሆን ዘንድ ደግሞ ካፒታሊስቶችን በብዛት ማፍራት አስፈላጊ ነው። ካፒታሊስቶች ሀብት እንዲያጠራቅሙ ደግሞ ሰራተኛው የደሞዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን መጠየቅ የለበትም። ባለሀብቱ ሃብት ማጠራቀም ከቻለ፣ አዳዲስ ግንባታዎች ይካሄዳሉ፣ ብዙ ሰራተኞችም ይቀጠራሉ። እድገትም ይኖራል፣ ሁሉም ተያይዞ ያልፍለታል። መንግስትም ቢሆን የህዝቡን ፍላጎት አሟላለሁ ብሎ ባለሃብቶች ብዙ ቀረጥ እንዲከፍሉ ማስገደድ የለበትም። የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሲል ባለሀብቱን ብዙ ግብር ማስገበሩ አይቀርምና የህዝቡን ጥያቄ ለጊዜው ገሸሽ ያድርግ።” አስተሳሰቡ በአጭሩ “ታገሱ፣ ይህኛው ትውልድ ባያልፍለት የሚቀጥለው ትውልድ ያልፍለታል።” የሚል ነው።

    በዚህ ንድፈ-ሀሳብ መሰረት የመብትና የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን “ያለጊዜው” መጠየቅ ጎጂ ነው፤ ህዝቡ በችግር ብዛት ቢያልቅም የሚጠበቅ ነው። መንግስት የስራ ማቆም አድማዎችንና ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን በሃይል ለመጨፍለቅ ጦሩን ቢሰብቅና ዜጎች ቢሞቱ ለካፒታሊዝም ግንባታ እስከሆነ ድረስ የተቀደሰ እርምጃ ነው። አስተሳሰቡ ኢኮኖሚውን ነጻ ፖለቲካውን እዝ የሚያደርግ፣ “ፖለቲካው ኮሚኒዝም- ኢኮኖሚው ካፒታሊዝም” ነው።

    ይህን አስተሳሰብ ወደ አገራችን ነባራዊ ሁኔታ እናምጣ እንየው። “ባለሀብቱ ሀብት ያጠራቅም ዘንድ መታገስ አስፈላጊ ነው” የሚለው ምክር አሳማኝ ነው እንበል። ይሄ ትውልድ ተበድሎ የሚቀጥለው ትውልድ ይለፍለት የሚለውም አርበኝነት ነው እንበልና እንቀበለው። ነገር ግን ይህን አስተሳሰብ በአገራችን ተግባራዊ ብናደርገው የሚፈለገውን ውጤት እናመጣለን ወይ? ብለን ስንጠይቅ ፣ የምናገኘው መልስ አሉታዊ ይሆናል። እነሆ ምክንያቶቹ-

    በቅድሚያ በእኛ አገር ሃብት እንዲያጠራቅሙ ስርአቱ የሚንከባከባቸው አዲስ-ሰዎች በአብዛኛው ከአንድ አካባቢ የመጡ ወይም የአንድ ብሄር አባላት ናቸው። እነሱ ሃብት እስኪያጠራቅሙ ሌላው ህዝብ እንዲሞት መፍረድ ከሞራል አኳያ ተቀባይነት አይኖረውም። እነሱ ብቻ ካፒታሊስቶች እንዲሆኑና ኢኮኖሚውን እንዲቆጣጠሩት ከፈቀድን ሌላው ህዝብ በባርነት ስር እንዲኖር እየፈረድንበት ነው። ኢኮኖሚውን እነሱ ብቻ ከተቆጣጠሩት ፖለቲካውንም መቆጣጠር አይሳናቸውም። ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያችን ትመሰረታለች፤ ልዩነት ቢኖር የካፒታሊስቶቹ ቀለም ብቻ ነው።

    “ግደየለም እነሱም የእኛው ሰዎች ናቸው” ብለን ብንተዋቸው እንኳ ፣ የአገር ፍቅር ስሜት አልባነታቸው ፈቅደን እንዳንገዛላቸው ያደርገናል። እነዚህ አዳዲስ ካፒታሊስቶች ገንዘባቸውን በአገር ውስጥ ባንክ አያስቀምጡም፣ ፋብሪካ ከሚገነቡ ህንጻ ቢቀጣጥሉ ይመርጣሉ፤ ህንጻ ሲሰራ እንጅ ከተጠናቀቀ በሁዋላ ብዙ ሰው አይቀጥርም። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የአገሪቱ ገንዘብ በውጭ ባንኮች መቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይህ ሃብት የማን ነው? ተከድኖ ይብሰል። ነገር ግን እነዚህ ባለሃብቶች የአገር ፍቅር ስሜት እንደሌላቸው በደንብ ያሳያል።

    የእኛ አዲሶቹ ባለሃብቶች ጉራና ልታይ ልታይ ማለትን ይወዳሉ። ደሃው እየደማ በሚያገኙት ገንዘብ አንድ ጠርሙስ ውስኪ እስከ 30 ሺ ብር እየገዙ ይራጬቡታል፤ ፈረንጆች እንኳ ለመያዝ የማይደፍሩትን ዘመናዊ መኪኖችን እያሽከረከሩ በሚሞትላቸው ህዝብ ላይ ይንደላቀቁበታል። ለጎራ ካልሆነ ሃመር መኪና በእግሩ በሚሄድ ህዝብ መሃል ምን ይሰራል? የሆላንድ ባለሀብት እኩል እንደ ነዋሪው ቅናሽ ሱቅ ውስጥ ገብቶ እቃ ይገዛል፣ ሚሊኒየሩን ከሌላው ህዝብ መለየት አይቻልም። የእኛን አዳዲስ ባለሀብቶች ለመለየት በጣም ቀላል ነው። እነዚህ ባለሀብቶች ናቸው የነገውን ትውልድ ያሳልፉለታል ተብሎ የሚጠበቀው።
    ከሁሉም በላይ እነዚህ አዳዲስ ባለሀብቶች ገንዘብ የሚያጠራቅሙት የመንግስትን ስልጣን ይዘው እንጅ ሰርተው፣ ለፍተው፣ በእኩልና በፍትሃዊ መንገድ ተወዳድረው አይደለም። የሃብት ምንጭ የሆነውን መሬት እንደልብ እያገኙ፣ ከታክስ ነጻ እቃዎችን እያስገቡ፣ ተቀናቃኞቻቸውን በተንኮል ከገበያ እያስወጡ ነው የከበሩት።

    ከእነዚህ ባለሀብቶች ውጭ ያለው ዋና ካፒታሊስት ( ባለሀብት) ደግሞ መንግስት ነው። በኢትዮጵያ እንዲያውም ዋናው ኢንቨስተር መንግስት ነው። መንግስት መሬትና ፋብሪካዎችን እየጨሸ የሚሰበስበውን ገንዘብ ከላይ ያሉት ቁንጮዎች ይመዘብሩታል። ከዝርፍያ የተረፈው ገንዘብ ለድሃው የኑሮ መደጎሚያ ይዋል ሲባልም ጦርነት ይሰበቃል። መንግስት ሃብት እስኪያጠራቅም ጥያቄዎችን ከመጠየቅ ታገሱ የሚባል ነገር ተቀባይነት የለውም ። መንግስት ሲደኸይና ዜጎች ሲበለጽጉ እንጅ ተቀራኒው ከተፈጠረ አደጋ ይኖራል።

    አሁን ያሉት አዲሶቹ ባለሀብቶችም ሆኑ አሁን ያለው መንግስት የሚቀጥለውን ትውልድ ህይወት መለወጥ የሚችሉ አይደሉም። ባለሀብቶች ሃብት ሲያጠራቅሙ ለድሃው ተንጠባጥቦ ይደርሰዋል የሚለው የ trickle-down የኢኮኖሚ አስተሳሰብ ለአሁኑዋ አገራችን አይሰራም፤ ምክንያቱም ያሉን ባለሀብቶችና መንግስት በድሃው ላይ የሚዘምቱ እንጅ ለድሃው የሚቆሙ አይደሉም። ጤነኛ ካፒታሊዝም በጤነኛ ከፒታሊስቶች ይገነባል፣ ጤነኛ ካፒታሊስት ባይኖርም፣ አገር ወዳድ ካፒታሊስት ግን አለ። የእኛዎቹ፣ ከመንግስት ጀምሮ ጤነኞችም አገር ወዳዶችም አይደሉም።
    ደሃው ኢትዮጵያዊ ዛሬ ለመብቱእና ለማህበራዊ አግልግሎት መሻሻል ካልተነሳ፣ ነገ በህይወትም ላይኖር ይችላል።

    ስደመድመው – “የዛሬው ትውልድ ተበድሎ የነገው ትውልድ ይለፍለት” የሚለው አስተሳሰብ አሁን ባለው የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ፈጽሞ የማይሰራ ፣ ሰዎች ለነጻነታቸውና ለመብታቸው እንዳይነሱ የሚያዘናጋ እንዲሁም የአንድን በዘር ላይ የተመሰረተ ስርዓት ቀጣይ ህልውና ለማረጋገጥ ተብሎ የሚነዛ አደገኛ አስተሳሰብ በመሆኑ፣ ዜጎች በዚህ አስተሳሰብ ሳይዘናጉ ዛሬውኑ ለመብታቸው መከበር መነሳት አለባቸው- ነገን ስንጠብቅ ዛሬ እንዳንሞት እንጠንቀቅ።

    በአትላንታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአዋሳ፣ በደንቬር የሚኖሩ ደግሞ በደሴ ለሚደረጉት የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነትና ለፍትህ እንቅስቃሴዎች የሚያስፈልግትን ወጭዎች ሙሉ ለሙሉ እንደሚሸፍኑ ማረጋገጣቸውን ፣ የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ማህበራት፣ ሸንጎን እና የሽግግር ምክር ቤቱን ያሳተፈው የሚሊዮኖች ድምጽ የዳያስፖራ ግብረ ኃይል ገለጸ። የመጀመሪያዉን የአዲስ አበባ እንቅስቃሴን ላስ ቬጋሶች፣ በድረደዋ ከተማ የሚደረገዉን የደብተራዉ ፓልቶክ ክፍል ፣ የቁጫ ከተማ ደግሞ […]

    ለለውጡ ዝግጅት ያስፈልጋል! እንዲህም ተብሏል ለውጥን ማዘግየት ይቻል እንደሆን እንጂ ገድቦ ማስቀረት እንደማይቻል ከትርክት አልፎ በተግባር የታየ ሀቅ ነው፡፡ በተለይ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴን አፍኖ መዝለቅ የማያዛልቅ ሙከራ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ሀገራት ታይቷል፡፡ በዓለም ላይ የማይለወጥ ነገር አለ ከተባለ ራሱ ለውጥ ነው የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን ኦፍ ኬኔዲ ‹‹እነዚያ ሰላማዊ ለውጥን የማይቻል […]

    የሀገራችን የተቃውሞ ፖለቲካ ወደ አንድ ጠንካራ የለውጥ አማራጭነት እንዲሰባሰብ እና ገዥውን ፓርቲ የሚገዳደር ወሳኝ ኃይል ሆኖ እንዲወጣ ማስቻል የብዙ ቀናት አሳቢ ኢትዮጵያውያን ፍላጎት እንደሆነ ይሰማኛል። እኔም ራሴን ይህ ዓላማ ከፍፃሜ እንዲደርስ ከሚፈልጉ ወገኖች ውስጥ እንደ አንዱ በማድረግ እቆጥረዋለሁ። ውህደት እንዲኖር መፈለግ አንድ ነገር ሆኖ፤ ማን ከማን ጋር ነው የሚወሃደው? የውህደት መስፈርቱን ምን መሆን ይኖርበታል? የሚለውንም […]

    ለፍጥረተ ዓለም(ዩኒቨርስ)መከሠት ፤ መገኘት ፤ መዘርጋት– መንስዔ ነው ተብሎ የሚጠቀሰው «ታላቁ ፍንዳታ» (BIG BANG) ከ 14 ቢሊዮን ዓመት ገደማ በፊት ማጋጠሙን የሚጠቁም መረጃ በምርምር አግኝተናል ሲል አንድ የጠፈር ሳይንቲስቶች በድን ከወዲያኛው ሳምንት መግለጹ የሚታወስ ነው።

    በዓለም ላይ ቁጥራቸው ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጥ አካል ጉዳተኞች አሉ ። አብዛኛዎቹም በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት ውስጥ ነው የሚኖሩት ። በተለይ በአፍሪቃ አካል ጉዳተኞች ብዙውን ጊዜ አድልዎና መገለል የሚደርስባቸው ሲሆን ብዙዎቹም ስር በሰደደ ድህነት ውስጥ ነው ያሉት ።

    የአሸባሪዎች ጥቃት፣ የሐይማኖት ግጭት እና ሙስና ባልተለያት ናይጄሪያ በኢኮኖሚ ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ ላይ እንደሆነች ነው የሚነገረው። ይህ እዕን ከሆነ ደግሞ በነዳጅ ዘይት ሀብታም የሆነችው ናይጄሪያ በቅርቡ በኢኮኖሚ እድገቷ ከአፍሪቃ አንደኛ ከሆነችው ደቡብ አፍሪቃ መቅደሟ አይቀሬ ነው።

    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በአዉሮጳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ቀጥሎ ዛሬ ብራስል ቤልጅግ ይገኛሉ። በብራስልስ ከአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ጋ ካደረጉት ዉይይት በኋላም ከሰዓት በኋላ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።