አፈና ከሁመራ እስከ አድዋ ከአስገደ ገ/ስላሴ (መቐለ)
http://www.ethiomedia.com/broadway/afen … e_adwa.pdf iframe
ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 5ን በ PDF ያንብቡ!
ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር – 5 ቁልፍ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ እነሆ በ PDF ያንብቧት
– መዝሙረ ኢህአዴግ!
(በላይ ማናዬ)
– የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በተደረገላቸው ግብዣ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በጉዞው ዓላማና በተለያዩ የአገራችን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
– ኢትዮጵያና የዩክሬኑ ግጥምጥሞሽ
ባለ ቀለሙን አብዮት ማን ይመራዋል?
(በጌታቸው ሺፈራው)
– አዲስ ጠብመንጃ በምንሽር፤
አገዳደሉ ሆድ የሚያሽር፡፡
(በዝክረ ታሪክ አምድ፡- አቶ ታዲዎስ ታንቱ)
– “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ”
(ግርማ ሞገስ)
– ኑሮ ሆነብን እሮሮ
(ጋሻው መርሻ)
– የኢትዮጵያ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ
(ኤልሳቤት ወሰኔ)
– ሰላማዊ ትግሉ መሪዎቹን ይሻል
(ታምራት ታረቀኝ)
– ኢትዮጵያዊነት ለእኔ!
(አፈወርቅ በደዊ)
– እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራሞች የሚተዋወቁበት ገጽ አለልዎት
መልካም ንባብ !
ቀዳማዊ ሃይለስላሴ (ተፈሪ መኮንን) :-የ“የንጉሡ ገመና” … ንጉሡ ወሬ ይወዳሉ ስስታም ;ታማኞችን አይወዱም ;አይጾሙም ;ሴሰኛ ;ተደባዳቢ… ነበሩ::

–ታላቁን ገመና የደበቀው የ“የንጉሡ ገመና”
የመጽሐፉ ርዕስ – የንጉሡ ገመና
የገጽ ብዛት – የ172
የታተመበት ዘመን – 2006 ዓ.ም
የሽፋን ዋጋ – ብር 49.75
አሳታሚ – ግርማ ለማ
የመጽሐፉ ይዘት ከታሪክ ዘውግ የሚመደብ ሆኖ አሳታሚው ሁለት ምንጮችን ተጠቅመው ነው ያሳተሙት፤ እነሱም ለ14 ዓመታት በንጉሥ አሽከርነት ያገለገሉት የአቶ ሥዩም ጣሰው መንዜው የግል ማስታወሻና የልዩ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት ቀይ ሽብርን አስመልክቶ ያሳተመው “ደም ያዘለ ዶሴ” የተሰኙ መፃሕፍት ናቸው፡፡
በተለይ አቶ ሥዩም ከልጅነታቸው ጀምረው በቤተመንግሥት ያደጉና ለድፍን 14 ዓመታት በንጉሡ አሽከርነትና አልባሽነት ያገለገሉ በመሆናቸው የንጉሠ ነገሥቱን ጓዳ ጐድጓዳ፤ የአሽከሮችን፣ የደንገጡሮችንና የወቅቱን ባለሥልጣናት ጠቅላላ ሁኔታ የማየት ብቻ ሳይሆን የማወቅ ዕድሉ ስለነበራቸው ማስታወሻቸው ተአማኒነት ይኖረዋል። አቶ ሥዩም ንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣናቸውን ተቀምተው መጀመሪያ በቤተመንግሥታቸው ቀጥሎም በ4ኛ ክፍለ ጦር እስረኛ እስከሆኑበት ድረስ ንጉሡን በታማኝነት አገልግለዋል፤ በደርግ ዘመን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ኖረው ኢህአዴግ ሲገባ በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ከጠባቂዎች አምልጠው ራሳቸውን ማጥፋታቸው ይነገራል፡፡ ወደ መጽሐፉ እንመለስ፡፡
አሳታሚው ግርማ ለማ፤ በምስጋና ገጹ ላይ የጽሑፉን ዋና ቅጅ (ኦሪጅናል) የሰጠው “በያን ናስር” የተባለ ሰው መሆኑን ጠቅሷል፤ ግን በያን የሥዩምን ጽሑፍ እንዴት እንዳገኘው ወይም የሥዩም ወኪል ይሁን፤ የገለጠልን ነገር የለም፤ የተገኘበት መንገድ ቢጠቀስ በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሥዩም የሞተው በድንገት ነው፤ የተያዘውም ሳያስበው ቤቱ በታጣቂዎች ተከቦ ነው፡፡ ስለዚህ ሃሳባችንን ወደአልተፈለገ ጥርጣሬ እንዳያመራን ግርማ ረቂቁን እንዴት እንዳገኘው ቢገልጥልን መልካም ነበር፡፡ የተጻፈልን ታሪክ ነዋ! ታሪክ ያለአስተማማኝ ማስረጃ ሊታሰብም ሊጻፍም እጅግ ይከብዳል፡፡
መጽሐፉ የምስጋናና የመግቢያ ገጾችን ሳይጨምር፣ በዘጠኝ ምዕራፎች የተዋቀረ ነው፡፡ ስምንቱ ከስዩም ጣሰው ማስታወሻ የተወሰዱ ሲሆን ዘጠነኛው ምዕራፍ “ደም ያዘለ ዶሴ” ከተባለው መጽሐፍ የተገለበጠ ነው፡፡
የመጽሐፉ ጠንካራ ጐኖች
መጽሐፉ በንጉሡ ጓዳና ቢሮ ውስጥ ስለነበረው እውነት የገለጠልን በመሆኑ፣ የንጉሠ ነገሥቱን አጠቃላይ ሰብዕና ለሚያጠና ሰው ትልቅ የታሪክ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ ንጉሡ በካህናትና ባለሥልጣናት ዘንድ ተፈርተው ይከበሩ ስለነበር፣ ድምሩ ህዝብም አባቱን እየተወ “ኃይለሥላሴ ይሙት” በማለት በስማቸው ይምልና ይገዘት ነበር፡፡ ግን እንደ ሥዩም ጣሰው ጓዳቸውን ገብቶ የማየት ዕድል ቢገጥመው ኖሮ ምን ያህል ሲታለል እንደኖረ ይገባውና ከልቡ ይቆጭ ነበር ያሰኛል፡፡ ለማንኛውም የመጽሐፉን ጠንካራ ጐኖች በአምስት ከፍያቸዋለሁ፡፡
ገመና አንድ
ንጉሡ ተደባዳቢ ነበሩ
ንጉሡ አሽከሮቻቸውን ይደበድቡ ነበር፤ “…የፀጉር ቅባት ፓንተን ሳቀርብላቸው ቀና አሉ፤ አዩኝ፡፡ አሰቡ አሰቡና ‘ማታ ማነው ፍራፍሬውን የደገሰው’ ብለው ጠየቁኝ፡፡ እኔም ራሴ መሆኔን ነገርኋቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ብድግ አሉና ተያያዙኝ፡፡ እስከሚደክማቸው ድረስ ደበደቡኝና ቁጭ ብለው ፀጉራቸውን አበጠሩ፡፡ ክራባታቸውን አሰሩና ተነሱ። ልብሳቸውን ለብሰው ሲጨርሱ ጠሩኝ፡፡ እኔም አቀርቅሬ ተጠጋሁ፡፡ አስጐነበሱና እስከሚበቃቸው ወገሩኝና እየተሳደቡ ወደ ቁርሳቸው ሄዱ” (ገፅ 11-12)
ይህን አይነት እርግጫና ጥፊ ለሥዩም አዲስ አልነበረም፤ በየጊዜው ይገረፋል፤ የስድብ ውርጅብኝ ይዘንብበታል፡፡ ሁለት ቀን ብቻ ከተገረፈ በኋላ ብር እንዲሰጠው አድርገዋል፤ ይህ አንድም ምሥጢራቸው እንዳይወጣ ማባባያ ነው፡፡ አለዚያም ካሣ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ሆኖም የሥዩም (አሽከርና የታሪኩ ፀሐፊ መሆኑን አንዘንጋ) ትልቁ ፈተና ከንጉሡ ዱላ ይልቅ የሴት አሽከሮች በእሱ ላይ ማደምና ከባለሥልጣናት ጥርስ ውስጥ ማስገባት ነበር ትልቁ ፈተና የሆነው። ለዚያ ሁሉ እርግጫ፣ ጥፊና ዱላ ሰበቡ ንጉሡ የገረዶችንና የአሽከሮችን ወሬ ስለሚሰሙ ነው፡፡ (ገፅ 14)
ንጉሡ ወሬ ይወዳሉ፤ የሆነ ያልሆነን ሁሉ የሚቀላምድላቸውን ሰው ያስጠሩትና ምንም ሳያጣሩ የተወራበትን ሰው ራሳቸው ይገርፋሉ፤ ካስፈለገም ግዞት ይልካሉ፡፡ (ገፅ 21 እና 24)
ገመና ሁለት
ንጉሡ ሴሰኛ ነበሩ
ንጉሡ ሴት በጣም አብዝተው ይወዱ ነበር፤ በዚህ የተነሳ ከጽዳት ሠራተኞች፤ ከአበሻ ወጥ ቤቶች፣ ከእንጀራ ጋጋሪዎች፣ ከቅንጬ ቤቶች፣ ከሴተኛ አዳሪዎች፣ ከሆስተስና ከባለ ትዳር ሴቶች ጋር ይቀብጡ ነበር፡፡ “ሴቶቹ አብዛኛውን ጊዜ የሚገቡት ቀን ከምሳ መልስ እረፍት በሚያደርጉበት ጊዜ ከ8-10፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ጃንሆይ ገብተው ከተኙ በኋላ ትንሽ ቆይተው ደወል ይደውላሉ፡፡ በዚያ ጊዜ በዚህ ነገር የተለየ ባለሟል የሆኑ አሽከሮች በተራቸው ይገቡና “ዕገሊትን ጥራ” ሲባል ይጠራል፡፡ ምን አልባት እርሱ ከተጠራችው ሴት ጋር ሽርክና ከሌለው ወይም ከምትወስደው ገንዘብ በብዛት ካላካፈለችው “እርሷ አሁን የለችም” በማለት የርሱ ሽርክ በየጊዜው ብዙ ገንዘብ የምትሰጠውን ሴት “ዕገሊት አለች፤ እርሷ ከሥራዋ ላይ አትጠፋም” በማለት ይቀላምድና ይጠራል፡፡ ሲገቡና ሲወጡ የተለየ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ሴቶቹ በሚያሳዩት መለዋወጥ የተቀረው ሰው እዚያ ቦታ እንደደረሰች ይገባዋል” (ገፅ 51)
“ቢሮ የሚደረገው ደሞ ሌላ ነው፤ ቢሮ በሚሠሩበት ጊዜ ረፈድ ሲልና አንዳንድ ባለሥልጣኖችን ካነጋገሩ በኋላ ገለል ብለው ቢሮ አጠገብ ካለው መኝታ ቤት ጐራ ይላሉ፡፡ ከዚያም በዚያ አካባቢ ከሚሠሩት ሴቶች ውስጥ የፈለጓትን አስጠርተው ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ ወደ ቢሮአቸው ይገባሉ፡፡ …ሆስቴሶችንና ሌሎችን ደግሞ እምድር ቤት ካለው ቢሮ ነው የሚያገኙአቸው” (ገፅ 51)
ይህ ሁሉ ሲሆን እንደየሴቶቹ የንቃት መጠን ዛቅ ያለ ገንዘብ ይከፈላቸዋል፤ ከሥራ ቤት፣ እንጀራ ቤትና ወጥ ቤት ለሚመጡት ሴቶች የሚከፈላቸው አነስተኛ ገንዘብ ሲሆን ለጽዳት ሠራተኞችና ለሌሎች ሴቶች ግን ከ70-80 ሺህ ብር ይከፍሉ ነበር፡፡ ሴቶቹ ደግሞ ወደ ንጉሡ ላቀረባቸው ሰው (ደላላው) ከ5-10 ሺህ ብር ቀረጥ የመክፈል ግዴታ ነበረባቸው። በዚህ የተነሳ ከንጉሡ ጋር የተገናኙ ሴቶች ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቆንጆ ቪላና ዘመናዊ መኪና ይገዙ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ እንዲያውም ፖለቲካዊ ሥልጣኑን ተቆጣጥረው የፈለጉትን ያስሾሙ ያስሸልሙ፤ የጠሉትን ደግሞ ያሰቃዩት ነበር (ገፅ 51)
አንዳንድ የንጉሡ ውሽሞች በጣም ቀበጦች ስለነበሩ በመንግሥት ወጭ፣ አስተርጓሚ ጭምር ተመድቦላቸው ለሽርሽር ፈረንጅ አገር ይሄዱ ነበር። በጣም የሚያሳዝነው ግን ንጉሡ የባለቤታቸውን የዕቴጌ መነን አስፋውን ጌጣጌጥ ሳይቀር ለውሽሞቻቸው መስጠታቸው ነው፡፡ ለአንዳንድ ውሽሞቻቸውም ቋሚ ደሞዝ ተቆርጦላቸው የቤተ መንግሥት አሽከሮች በየወሩ እቤታቸው ድረስ እየሄዱ ይከፍሉ ነበር፡፡ (ገፅ 56)
ይህ ድርጊት ያንገበገበው ሥዩም “ኢትዮጵያ በተለይ ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ስትገዛ የኖረችው በንጉሠ ነገሥቱ ሳይሆን በእልፍኝ አስከልካዮች፣ በጥቂት የእልፍኝ አሽከሮችና በገረዶች ነበር፡፡ …ቤተመንግሥቱ ቤተመንግሥት መሆኑ ቀርቶ ፍጹም የሰይጣን ቤት ሆኖ ነበረ” ሲል ትዝብቱን አስፍሯል። (ገፅ 20)
ገመና ሶስት
ንጉሡ አይጾሙም ነበር
ንጉሡ አክሱም ጽዮንንና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትን ስለአሠሩ ካህናት ያወድሷቸዋል፤ ይሰግዱላቸዋል፡፡ “አቤቱ ፍርድን ለንጉሣችን ስጠው” እያሉም ዘወትር ይፀልያሉ፤ እንደ ጻድቃንና ሰማዕታት በመቁጠርም መልክአ ኃይለሥላሴ ደርሰውላቸው ነበር፡፡ ሆኖም ንጉሡ የክርስቲያንን ህግና ሥርዓት በመጣስ፣ አርብና ረቡዕን እንዲሁም ሌሎች አጽዋማትን አይጾሙም ነበር፡፡ (ገጽ 25 እና 34)
ገመና አራት
ንጉሡ ጠንካራ ሰራተኞችንና ታማኞችን አይወዱም ነበር
“ግርማዊነታቸው የሚወዱት ሰው ፈጣን፣ አጭበርባሪ፣ አሳባቂ፣ በዕውቀት ያልበሰለ፣ እርሳቸውን አምታቶ የሚያታልላቸውን ሰው በጣም ይወዱታል፡፡ የጥቅም ተካፋዮቻቸው በሙሉ በዕውቀት ያልበሰሉ፣ የሰውን መብት በፍጹም ያልተረዱ፣ ሰውን ሸጠው ለመክበር ብቻ ጽኑዕ ዓላማ ያላቸው፣ ለኔ እንጂ ለኛ የሚል መንፈስ ፈጽሞ የሌላቸው ጨካኞች፣ ሰው በችግር ሲሰቃይ ሲያዩ ከማዘን ይልቅ መደሰትን የሚመርጡ ከንቱዎች ናቸው፡፡
“ግርማዊነታቸው አጥብቀው የሚጠሉት ሰው እውነትን በጣም አድርጐ የሚወድ፣ ዘወትር የሚከራከራቸው፣ በእውነት ፍጹም በሆነ መንገድ የሚወዳቸው፣ ሲዋሹ የሚያስተባብላቸው፣ የሚታሙበትን ነገር እንዲተው የሚነግራቸው፣ የማይንቀዠቀዥ፣ አዋቂ ሰው በፍጹም አይወዱም” (ገፅ 31) ይለናል፤ ሥዩም በ14 ዓመት የአሽከርነት ዘመኑ የታዘበውን ሲያካፍለን፡፡
ገመና አምስት
ንጉሡ ስስታም ነበሩ
ንጉሠ ነገሥቱ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገርና እጅግ ብዙ ህዝብ የመግዛታቸውን ያህል ስስታቸውም ያን ያህል አሳፋሪ እንደነበር በመጽሐፉ ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል፡፡ በልጅነት ዘመናችን የምናውቃቸው ንጉሥ፤ በየቦታው ሲዘዋወሩ ብር እንደጥሬ እየበተኑ የሚሄዱ መሆናቸውን ነበር፡፡
ሥዩም የሚያውቀውን እውነት ሲነግረን ግን ስስታቸው በጣም የወረደና ለማመን የሚያስቸግር ሆኖ እናገኘዋለን “…በተለይ ከኬኩ ትንሽ በቄንጠኛ አኳኋን ቆርሰው ከበሉ በኋላ በምልክት አድርገው በጥንቃቄ እንዲቀመጥ ይናገራሉ፡፡ በማግስቱ ሲመጣ ትንሽ ለውጥ ከታየበት “ማነው የተጫወተበት” በማለት ማሰቃየት ነው፡፡ አንድ ኬክ ከሶስት እስከ አምስት ቀን ድረስ እየተመላለሰ ይቀርባል፡፡ ለምሳሌ ሐሙስ ቀን ተጀምሮ እንደሆነና ቅዳሜ ደብረዘይት ቢሄዱ አብሮ ይሄዳል፤ ማሩንም በጣም አድርገው ይቆጣጠራሉ፡፡ ከማስቀመጫው ብልቃጥ ውስጥ ትንሽ ጐድሎ ያገኙት እንደሆነ “እንደፈለጋችሁ ትጫወቱበታላችሁ” ብለው መለብለብ ነው” (ገፅ 33) ሲል ያየውን ትዝብት ያካፍለናል፡፡
ከዚህ ሌላ መኝታ ቤታቸው በስጦታ ዕቃዎች፣ በቸኮላት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ስለሚሞላ ዕቃ ቤት ይመስል ነበር፤ እንዲያውም አትክልትና ፍራፍሬው፤ እንዲሁም ቸኮላትና ኬኩ እየተበላሸ የመኝታ ቤታቸውን ሽታ ያበላሸው ነበር፡፡ (47፣ 116፣ 117)
ከመጽሐፉ ውስጥ በጣም የገረመኝ ቢኖር (ገፅ 149) ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ ለንጉሡ ልክ “ልዩ ካቢኔ” ይባል እንደነበረው የስለላ ተቋም፣ በየቀኑ ለንጉሡ ደብዳቤ ይልኩ የነበሩ መሆናቸው ነው፤ ለመሆኑ ቀኛዝማች ተሥፋን ከንጉሡ ጋር ያውም በየቀኑ የሚያገናኛቸው ምን ብርቱ ምሥጢር ነበር ይሆን እንድል አድርጐኛል፡፡
የመጽሐፉ ድክመት
መጽሐፉ ከላይ በመጠኑም ቢሆን የነካካኋቸውን ጉዳዮች የዓይን ዕማኙን ሥዩም ጣሰውን ዋቢ አድርጐ የመቅረቡን ያህል ሌላ ድክመት እንዳለበትም መዘንጋት አያሻም፡፡
አሳታሚው በመግቢያው ላይ “አሽከር ሥዩም (አፈሩን ገለባ ያድርግለትና) በሰነዱ ውስጥ ጽሑፉን ለንባብ ሳያበቃው እንዳይሞት አምላኩን የተማጸነበት ፀሎት አለ” ብሎናል፡፡ ግን ይህንን ከሰነዱ ውስጥ አናገኘውም፡፡ ይህ የሚያሳየን የሥዩም ሰነድ የተነካካ ወይም የተቆራረጠ ፍሬ ነገር አለው ማለት ነው፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ፍጹም ስህተት ነው፡፡ አንድ አካል ሲቆረጥ ሌላውን ምሉዕ እንደማያደርገው ሁሉ የሥዩም ጽሑፍም የቋንቋ አርትኦት ብቻ ተደርጐለት መታተም ነበረበት፡፡
ሌላው ከወሲብ፣ ከንዋይና ከሃይማኖታዊ ገመናቸው ይልቅ የንጉሱ ፖለቲካዊ ገመና ቢታከል ኖሮ ጽሑፉን ተወዳጅ ያደርገው ነበር፤ ሰዎችን በምሥጢር መግደልና ማስገደል፣ በፍርድ አካባቢ የነበረው ሸር ሁሉ ሊገለጽ በተገባ ነበር፡፡ ይህን አይነቱን ታላቅ ገመና ሥዩም ሳይነካካው አልቀረም፤ ግን በመጽሐፉ ላይ አናገኘውም፡፡ ይህ ደግሞ ታላቁንና ለ44 ዓመታት የኖሩበትን ገመና ምስጢር አድርጐብናል፡፡ ከገጽ 141 ጀምሮ እስከ ገጽ 172 ያለውና “ደም ያዘለ ዶሴ” ከሚለው መጽሐፍ እንዳለ ተገልብጦ የቀረበልንም የመጽሐፉ ትልቅ ድክመት ነው፡፡ እንደ ትርፍ አንጀት የተለጠፈውን 32 ገጽ ከዋናው መጽሐፍ “ደም ያዘለ ዶሴ” ላይ አንብበነዋል፤ እዚህ ላይ መደረቱ ለምን አስፈለገ?
addis admass newspaper
የአፄ ምኒልክን ታሪክ ተጭበርብረናል!?

በአሜሪካ፣ በፈረንሳይና ቤልጂየም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ነበራቸው
የ25 ሚሊዮን ዶላር ባለፀጋ ነበሩ – ወደ ቢሊዬነርነት ተጠግተዋል
ቤተ-መፅሃፋቸው ራሳቸው ባሰባሰቡት 10ሺ መፃህፍት የተሞላ ነበር
በሳምንቱ ማጠናቀቂያ ግድም “ጮማ” የሆነ መረጃ እጄ ገባ፡፡ አንድ ወዳጅ ነው መረጃውን ከባህር ማዶ በኢሜይል ያሻገረልን፡፡ The New York Times የዛሬ 105 ዓመት፣ አፄ ምኒልክ ሲሞቱ ነው ዘገባውን ያወጣው – ኖቨምበር 7 ቀን 1909 ዓ.ም፡፡ “ንጉስ ምኒልክ እዚህ ኢንቨስትመንት አላቸው” በሚል ርዕስ የቀረበው ፅሁፍ፤ከአቢሲኒያ የተመለሰውን የቤልጂየም አሳሽ ባሮን ዲ ጃርልስበርግ ቃለመጠይቅ በማድረግ የተጠናቀረ እንደሆነ ኒውዮርክ ታይምስ ይገልፃል፡፡ የሚታወቁትን ታሪኮች እየዘለልኩ “ጮማ ጮማ” የሆኑትን መረጃዎች ነው የማቀብላችሁ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ከመዘጋቱ በፊት በዚህ በአዲሱ የአፄ ምኒልክ ታሪክ ላይ ትንሽ ጥናትና ምርምር ቢያካሂድ ትክክለኛው ታሪክ (ያልተጭበረበረው ማለቴ ነው!) ለትውልድ ይሸጋገራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ “የለም! የአፄ ምኒልክን ጉዳይ አጥንቼ ፋይሉን ዘግቻለሁ” የሚል ከሆነም እንዳሻው፡፡ የኒውዮርክ ታይምስ መረጃ ግን የሚያወላዳ ዓይነት አደለም፡፡ ለመሆኑ እኚህ የጥቁር ህዝብ ኩራት፣የአድዋ ጀግና—–አዳዲስ ገድሎች ምን ይሆኑ? (የተጭበረበርነው ታሪክ ማለት ነው!)
ባሮን ዲ ጃርልስበርግ ለጋዜጣው እንደተናገረው፤ ምኒልክ ከሌሎች የአህጉሪቱ ነገስታት ጨርሶ የተለዩ መሪ ነበሩ፡፡ በዲፕሎማትነት፣ በኢንቨስተርነት (ፋይናንሰር)፣ በተዋጊነት የሚስተካከላቸው አልነበረም፡፡ በተዋጊነትና በዲፕሎማትነት ያላቸውን ብቃትና ዋጋ ያስመሰከሩት ጣልያን በአቢሲኒያዎች ድል በተነሳች ወቅት ነበር ይላል – ጃርልስበርግ። በመጨረሻዎቹ የንግስና ዘመናቸው ግን ምኒልክ ይበልጥ በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸው እንደታወቁ ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡
የንግስና ዘውድ ከመድፋታቸው ቀደም ብሎ በወጣትነት ዘመናቸው የኢንቨስትመንት ዝንባሌ እንደነበራቸው የሚያስታውሰው ዘገባው፤በዚያ እድሜያቸው በፈረንሳይና ቤልጂየም የማዕድን ማምረቻዎች ውስጥ ቀላል የማይባል መዋዕለ ንዋይ አፍስሰው ነበር ይለናል፡፡ ከንግስናቸው በኋላ ግን አገር በማስተዳደር ሥራ በመወጠራቸው ከኢንቨስትመንቱ ተስተጓጉለው እንደነበር የኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ያመለክታል፡፡
“ዛሬ የአቢሲኒያው ገዢ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸውን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በማስፋፋት በአሜሪካ የባቡር ሃዲድ ሥራ ላይ ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻ አላቸው” ሲል አሳሹ የንጉሱን ወቅታዊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ገልጿል፡፡
አፄ ምኒልክ በአሜሪካ እንዲሁም በፈረንሳይና ቤልጂየም ያላቸው አክስዮንና ኢንቨስትመንት ሲደማመር ከ25 ሚሊዮን ዶላር የማያንስ የግል ሃብት እንደነበራቸው ይገመታል ብሏል- አሳሹን ጠቅሶ የዘገበው ጋዜጣው፡፡
“እኚህን ጥቁር የአቢሲኒያ ገዢ በተመለከተ በእጅጉ የሚያስደንቀው ጉዳይ ሁለ-ገብነታቸው ነው” ሲል የሚያደንቀው የቤልጂየሙ አሳሽ፤ንጉሱ የተዋጣላቸው ቋንቋ አዋቂ ነበሩ ይላል – ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ጣልያንኛ አቀላጥፈው ይናገሩ እንደነበር በመጥቀስ፡፡ ሁለመናቸውን ለአገራዊ ጉዳዮች ለመስጠት ቢገደዱም አዲስ የወጡ የአውሮፓ የስነጽሑፍ ስራዎችን ለመቃኘት ግን ጊዜ አያጡም የሚለው ጃርልስበርግ፤ ብዙ ጊዜ አዲስ የአውሮፓ ደራሲ ስም ሲጠቀስ እምብዛም አይደናገራቸውም ነበር ብሏል፡፡
እሳቸውን ከሁሉም በላይ የሚያኮራቸው ራሳቸው ባሰባሰቧቸው 10ሺ መፃሕፍት የተደራጀው ቤተመፅሃፋቸው ሲሆን መፃህፍትን በተመለከተ ዋነኛ ትኩረታቸው በአፍሪካና በእስያ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ላይ የሚያጠነጥኑ ሥራዎች ነበሩ ይላል – ለኒውዮርክ ታይምስ ምስክርነቱን የሰጠው ባሮን ዲ ጃርልስበርግ፡፡ ለካስ ምኒልክ ወደው አይደለም– ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ሥልጣኔ፣ ዘመናዊ አስተዳደር ወዘተ—-ሲሉ የኖሩት፡፡ (የንጉሱን ታሪክ ተጭበርብረናል!?)
addis admass amharic newspaper
ዋ!!! ዋ!!! ዋ!!! አደጋ አለ !!! በምእራብ ኢትዮጵያ ያልተሳካውን በምስራቅ ኢትዮጵያ ለመድገም አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል::ይህ መንግስታዊ ሽብር አደጋ አለው:: የመንግስታዊ አካላት ስውር እጆች ግፊት እየበዛ ነው፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ:- ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ ስለሆነ ሕወሓት መራሹ ገዥው ፓርቲና አማካሪዎቹ ባለስልጣኖቹ ችግሩን ዓይተው መፍትሔ ካላስቀመጡ፣ አገርንና ሕዝብን በማስቀደምና በማሳተፍ ካልተንቀሳቀሱ አደጋ አለ፡፡ ያልታሰበና ያልተጠበቀ ግጭትና ችግር በአገራችን ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለ ነው::ኢትዮጵያ ደሃ አገር ናት ተብላ ትጠቀሳለች እንጂ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ተከፋፈሉ ተጣሉ፣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተከፋፈሉ ተጋጩ፣ የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ተባሉ፣ ወዘተ የሚል አንሰማም ነበር፡፡
አሁን በዘመን ወያኔ በመስጊድም በቤተክርስቲያንም አካባቢ ይህን እየሰማን ነው፡፡ የህዝብን አንድነት ለመናድ የሚፈልገው ገዢው ኢህኣዴግ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት እና መተራመስን ለመፍጠር ፕሮፓጋንዳውን በስፋት እየነዛ ይገኛል::በምእራብ ኢትዮጵያ ያልተሳካውን በምስራቅ ኢትዮጵያ ለመድገም አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል::ይህ መንግስታዊ ሽብር አደጋ አለው::ድሮ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር ለማስታረቅ ሩጫ ነበር፡፡ አሁን ለማባባስ የሚሯሯጥ ወያኔያዊ ኃይል እንዳለም በግልጽ እየታየ ነው፡፡ መፍትሔ ከማስገኘት ይልቅ የበለጠ ብጥብጥ እንዲከሰት የመንግስታዊ አካላት ስውር እጆች ግፊት እየበዛ ነው፡፡
የኑሮ ውድነት በህዝቡ ላይ ተደራርቦ ከጭነት ልክ በላይ እየሆነ ነው፡፡ ብር እየመነመነችና እየከሳች በመሞት በየቀኑ የቀብሯ ጥሩንባ እንደተነፋ ነው፡፡ የሃገራሽን ገንዝብ ብር በራሷ ግሽበቱ ተሽኖባት አትክልትና ፍራፍሬን ፣ ስንዴና ጤፍን፣ ትራንስፖርትና ልብስን፣ የላስኪት ቤትን እና የቤት ኪራይን፣ የተማሪውን ደብተርና ስክሪፕቶን መጋፈጥ ተስኗታል፡፡ የኑሮ ውድነት የሚያስከትለው የወንጀል ድርጊት አለ፡፡ ኑሮ ውድነቱ ወንጀልን ወልዷል::ሴቶች እህቶቻችን እድሜ እና የስራ ሁኔታ ሳይለይ ስጋቸው በመሸጥ ስራ ላይ ሲሰማሪ ከተማሪ እስከ ባለትዳር ከሕጻናት እስከ አዛውንት የሚያቀርቡ የወሲብ ደላሎች በሃገሪቱ ከትመዋል::ይህም ዋነኛ አደጋ ነው::
ለፖለቲካው እና ለስልጣኑ አትኩሮት የሚሰጠው ኢህኣዴግ ተቋማትን በሚገባ አለመገንባቱና ሥርዓቱን በሁሉም ዘርፍና መስክ አለመሞከሩን ብዙ ቀዳዳዎችን እንዲፈጠሩ ከማድረጉም በላይ፣ ለችግርና ለአደጋ የሚዳርግ ሁኔታ መኖሩ በገሃድ እየተስተዋለ ነው፡፡ የሃገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት በስራ ላይ ሊውል ነው ከሚለው ዘገባ ጀምሮ እስከ ማዕድን በመገኘቱ ሀብት ተፈጠረ ብለን በሰማን ማግስት ፖታሽና ወርቅ ፍለጋው ዩራኒየም ፍተሻው ተቋረጠ:ነዳጅ የሚፈልግ ኩባንያ ሥራ እንዲያቆም ተደረገ መባሉን ስንሰማ ያሳስበናል፡፡ ሃገሪቱ ወደ አደጋ ውስጥ ሰተት ብላ መግባቷን እና እንደማትወጣውም ይጠቁመናል::
ወያኔ በፖለቲካ ታማኝነት ያደራጃቸው እውቀት እና ልምድ የሌላቸው በሙስና እና በዝምድና የተሳሰሩ አትኮሮታቸው በሰው አገር ንብረት እና ገንዘብ ማከማቸት በሆኑ ባለስልታናት የተዋቀሩ መሥርያ ቤቶች ሲልፈሰፍሱና ውሳኔ መስጠት ሲያቅታቸው ማየቱም ወዴት እየሄድን ነው የሚያሰኝ ሆኗል፡፡ ይህም ከባድ እና እስካሁን ሊፈታ ያልቻለ አደጋ ነው::
በዳያስፖራው ያለው ዘረኝነት፣ ጐሰኝነት፣ መከፋፈል፣ መራራቅ፣ ሃይማኖትን መጠቀሚያ ማድረግ፣ ከጠላት ጋር ወግኖ መሟገት፣ አገርንና የአገርን ክብር አሳልፎ መስጠትና ፖለቲካን ቢዝነስ በማድረግ ለአትራፊነት መወራጨት፣ አስፈሪ የሆነ አቋምና እንቅስቃሴ ማድረግ አሳሳቢ ነው፡፡ይህም እንዲፈጠር ከባድ ሚና የሚጫወተው ከሃገር ቤት የሚራመደው አሳዛኝ የፖለቲካ ፖሊሲ ሲሆን እንዲሁም ወያኔ እያሰለጠነ የሚያሰማራቸው የበግ ለምድ የለበሱ ቀበሮዎች የሚረጩት መርዝ ነው ይህም ሌላኛው በሃገር ላይ የተደቀና አደጋ ነው::
አንድነታችንን የሚፈታተኑ የጠባብ ጐሰኝነትና አካባቢያዊ ስሜት የተላበሱ አስተሳሰቦች እዚህም እዚያም ሲሰሙና በቦታው መሟሟቂያ ሲሆኑ ማስተዋልም የተለመደ ሆኗል፡፡ የረዥም ዘመናት አንድነት ያለውን በፍር የተሞላውን በማህበርዊ እሴቱ እና ጉዞው አለም ያደነቀውን ኢትዮጵያዊነት የሚሸረሽሩ መንግስታዊ የማፊያ እጆች ሕዝብን በማፈናቀል እና ጎሰኝነትን እና ስልጣንን የማስረዘሚያ ስልት በማድረግ ከህዝብ አናት ላይ የሚሸኑ ትናንሽ የመንደር መንግስታት እንዲፈጠሩ በማድረግ የአብሮነት ፍቅርን እና አንድነትን በማደፍረስ በስፋት እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ እያየነው ያለነውን ከባድ አደጋ በሃገሪቱ ላይ እንዲሰራፋ አድርጓል::
እደግመዋለሁ::ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ ስለሆነ ሕወሓት መራሹ ገዥው ፓርቲና አማካሪዎቹ እና ባለስልታኖቹ ችግሩን ዓይተው መፍትሔ ካላስቀመጡ፣ አገርንና ሕዝብን በማስቀደምና በማሳተፍ ካልተንቀሳቀሱ አደጋ አለ፡፡ ሃገራችን እና ህዝቧ ሊወጡበት የማይችሉት ከባድ አደጋ ከፊታችን መደቀኑን ልብ ብለን በአንድነት እና በጋራ ከላይ የተቀመጡትን አደገኛ ሽብሮች የፈጠረውን በስልታን ላይ ያለውን መንግስት በአንድነት በመታገል ወደ ከርሰ መቃብሩ ከተን ዳግም እንዳያንሰራራ ማድረግ የኢያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታ ነው::
የመስዋዕትነት ወንጌል
ከጸጋዬ ገ.መድኅን አርአያ
በአጤ ኀይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት (በ1960 አካባቢ) ኤድመንድ መሪ የተባለ አሜሪካዊ የዕለታዊው ኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ አማካሪ ሆኖ ይሰራ ነበር። እኛም እንጠረጥረው እንደነበረ ሁሉ የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ሠራተኛ (ኮንታክት ማን) ነው። (እግዜሩ ይይላቸውና ለካ በእኛም መሐል ሰዋቸውን ይተክሉ ነበር) ኤድ መሪ የሥነ ጽሑፍ ሰው ስለሆነ በማስታወቂያ ሚኒስቴር “ተረፈ ዜና” የምንለውን – የማይታተመውንና የማይታወጀውን (በራዲዮና በቴሌቪዥን) በንጥረ ነገሩ መውሰጃ ሥፍራ የተነፈስነውን ሁሉ ሰብስቦ ካገጣጠመው በኋላ ወደ አሜሪካ ሲመለስ Kulubi የሚል መጽሐፍ አወጣ። እንግዲህ ተረፈ ዜና የገባችሁ ይመስልኛል።
አቡጊዳ – የሕገ መንግስቱ መሰረት የሆነው ቻርተር በኤርትራዊዉ በረከተ ሃብተ ስላሴ በሚመራ ኮሚሽን እንደዘጋጀ ተገለጸ
ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ፣ በጎሳ የተደራጁ ድርጅቶችን በማሰባሰብ ፣ በ1991 በተደረገው የአዲስ አበባ ኮንፈራንስ ፣ የሽግግር መንግስት ቻርተር ተብሎ የሚታወቀዉን ሰነድ እንዲጸድቅ ማስደረጉ ይታወቃል። ቻርተሩ አሁን ያለውን በጎሳ ላይ የተመሰረተ ዘረኛ ፌዴራል አወቃቀር ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲገበር ያደረገ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በየትኛው አገር የሌለ፣ ጸረ-ኢትዮጵያዊ የብሄረሰቦች የመገንጠልን መብትን በሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ የደነገገም እንደሆነ ይታወቃል። ዶር ነጋሶ ጊዳዳ […]
Now I am coming back
Now I am coming back. Because of domain name renewal problems my blog was out of work for the past week. Thank You for the Almighty God. And thank you for Google support team, Brother Behailu, Yirga alem, Anteneh and Deacon Ephrem Eshete, the pro…
የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ ስለላ ያካሄዳል ሲል አንድ የሰብአዊ መብት ቡድን ገለጸ
Human Rights Watch የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን ያወጣው አዲስ ዘገባ ኢትዮጵያ በአገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ከሚኖሩት ኢተዮጵያውያን ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ለመከታተል ሲል በጣም የተራቀቀውን የሰለላ ሶፍት ዌር ይጠቀማል ይላል።
የአዲስ አበባው የእሪታ ቀን ተቆረጠ – የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል የፓርቲውን ደብዳቤ ተቀብሏል፤ – ፍኖተ ነጻነት
የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል የፓርቲውን ደብዳቤ ተቀብሏል የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ መሰረታዊ ችግሮች እየተባባሱ ከመምጣት ውጪ ለውጥ ማሳየት ባለመቻላቸው ለዚህ ተጠያቂ መሆን ያለበትን የከተማይቱን አስተዳደርና ገዢውን ፓርቲ የሚቃወም ‹‹የእሪታ ቀን››በሚል መሪ ቃል መጋቢት 28/2006 ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደርግ አስታውቋል፡፡ በዛሬው እለት የፓርቲው ተወካዩች ለአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል […]
የእሳት ፖለቲካ በኢትዮጵያ (Fire Politics in Ethiopia) – ይሄይስ አእምሮ
በሃይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች ዙሪያ ሰሞኑን አንዲት መጣጥፍ ጽፌ ለድረ ገፆች ልኬ ነበር፡፡ ለኅሊናቸው ተገዢ የሆኑ አወጡት – አስነበቡን፤ እግዚአብሔር ይስጣቸው፡፡ ለባህልና ለይሉኝታ ያደሩት እንዲሁም እነሱ በሚፈልጉት ሙዚቃ ብቻ ታንጎና ማሪንጌ መደነስ የሚፈልጉት ወደቅርጫታቸው ከተቱት – ይክተቱት፡፡ ሁሉም የመሰለውን የማድረግ መብት አለውና ያነበበም ያስነበበም፣ ያፈነም ያሳፈነም የኅሊናው ዳኝነት ይፍረደው ከማለት ውጪ በዚህ በውዥንብር ዘመን መወቃቀሱም ሆነ […]
በወላይታ የተፈፀመው መንግስታዊ ውንብድና የስርአቱን ዝቅጠት የሚያሳይ ነው!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ
በአገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም መብቶች ያለምንም ገደብ የሚከበሩበትን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ላለፉት ዓመታት በርካታ መስዋዕትነቶች ተከፍለዋል፡፡ ዜጎች የመደራጀትና ሀሳባቸውን የመግለጽ ህገ-መንግሥታዊ መብት እንዳላቸው ጧት ማታ በመንግሥት ብዙሀን መገናኛዎች ቢለፈፍም፤ ሁሉም ነገር የይምሰልና የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልፅ ነው፡፡ ከሕግ በላይ የሆነ አገዛዝ ባለበት አገር በየስፍራውና በየክልሉ የሚገኙ ካድሬዎችና የስርዓቱ ባለሟሎች እራሳቸውን ከህግ በላይ […]
የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በተፈናቃዩች ተጥለቀለቀ:: – አንድነት
ተፈናቃዩቹ ከጎንደር አካባቢ ተነስተው ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ በመውረድ በእርሻ ስራ የተሰማሩ ገበሬዎች ናቸው፡፡ከ1996ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ደረጃ ‹‹ክልላችንን ለቅቃችሁ ውጡ››ሲባሉ ቆይተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያው ወደ ግድያ፣ድብደባና ወከባ በማደጉ ለአቤቱታ አካባቢያቸውን ጥለው አዲስ አበባ ለመግባት ተገደዋል፡፡ ከተፈናቃዩቹ መካከል የተወሰኑት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃን […]
= ሥልጣንህን አድን = ኢሕአደጋዊ አጀንዳ ወደ = አገርህን አድን = ሕዝባዊ አጀንዳ ይቀልበስ።
በሕወሓት/ኢሕአደግም ይሁን በተቃዋሚዎች በረት እና ማደሪያ …….
እየከፋ ያለን ጉዳይ እየተሻሻለ ነው ማለት = እያወቁ ማለቅ …….
= ሥልጣንህን አድን = ኢሕአደጋዊ አጀንዳ ወደ = አገርህን አድን = ሕዝባዊ አጀንዳ ይቀልበስ።
እየተሻለኝ ነው እያለ ከሚሞት፣ በጣም ጥሩ ምልክት ነው እያለ ከሚገድል ያድነን ፡፡ ደግ ደጉን ማውራት የተሻለ ዓለም ለማየት ይጠቅማል የሚለው ብሂል እንደተጠበቀ ሆኖ፤ እየከፋ ያለን ጉዳይ እየተሻሻለ ነው ማለት ግን እያወቁ ማለቅ ዓይነት ነው፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ ዕውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር ለአገርና ህዝብ ይበጃል እንጂ ጐጂ አይደም፡፡ የማይሰጋ ተስፋ የሌለው ሰው ነው ፡፡ አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ጨምሪበት” የሚሉት ዓይነት::
በየኑሮ መስኩ ያለውን ህመም፣ በየሙያ መስኩ ያለውን ተወሳክ፣ በየፖለቲካ መስኩ ያለውን ወረርሽኝ በጊዜ መመርመር ዋና ነገር ነው፡፡ እኛ የወደድነውን እያጐላን በየሚዲያው ብንለፍፍ ለሀገርና ለህዝብ ፋይዳ አይኖርም።
ለምርጫ እወዳደራለሁ የሚል ፓርቲም ይሁን ፕሮፓጋንዳ የሚረጭ ሚዲያ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ሥርዓት ለመገንባትና በዚህ መንገድ ለመምራት ከፈለገ፣ ሕዝብን ማክበርና ማዳመጥ ጥበብ መሆኑን፣ አማራጭና ተለዋጭ የሌለው መርህ መሆኑን ለመግለጽና አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡
የሕዝብን ብሶት ማዳመጥና ለሕዝብ ከበሬታ የመስጠት ጉዳይ ጥበብ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ጊዜ የማይሰጥና በእጅጉ አንገብጋቢ ሕዝብ አድን እና አገር አድን አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ሥልጣንህን አድን ከሚለው ኢሕአደጋዊ አጀንዳ በላይ፡፡
በኢትዮጵያችንም እንደዚሁ ሕዝብን የማክበርና የማዳመጥ ጉዳይ ተገቢና አስፈላጊ ተብሎ ብቻ የሚታለፍ ሳይሆን፣ አንገብጋቢ ሆኖ የተግባር ያለህ እያለ በመጮህ ላይ ያለ አጀንዳ ነው፡፡ ላለው ችግር ብቸኛው ፍቱን መድኃኒትና ጥበብ ሕዝቡን ማክበርና ማዳመጥ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየጠየቀ ነው፡፡ አቤት እያለ ነው፡፡ እየጮኸ ነው፡፡ ጥያቄው ማነው ሕዝቡን እያከበረና እያዳመጠ ያለው ? የሚል ነው፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ
በወላይታ የተፈፀመው መንግስታዊ ውንብድና የስርአቱን ዝቅጠት የሚያሳይ ነው!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
በአገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም መብቶች ያለምንም ገደብ የሚከበሩበትን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ላለፉት ዓመታት በርካታ መስዋዕትነቶች ተከፍለዋል፡፡ ዜጎች የመደራጀትና ሀሳባቸውን የመግለጽ ህገ-መንግሥታዊ መብት እንዳላቸው ጧት ማታ በመንግሥት ብዙሀን መገናኛዎች ቢለፈፍም፤ ሁሉም ነገር የይምሰልና የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልፅ ነው፡፡
ከሕግ በላይ የሆነ አገዛዝ ባለበት አገር በየስፍራውና በየክልሉ የሚገኙ ካድሬዎችና የስርዓቱ ባለሟሎች እራሳቸውን ከህግ በላይ አድርገው ቢቆጥሩ የሚገርም አይደለም፡፡ በዚሁም ምክንያት በገዢው ፓርቲ ተቋማት፣ ኃላፊዎችና ባለስልጣናት የሚፈፀመው ኢ-ሰብአዊና ኢ-ዴሞክራሲያዊ ድርጊቶች እጅግ እየከፋ መጥቷል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በፓርቲያችን በአንድነት የተሰጣቸውን የተለያዩ ተልዕኮዎችን ለለማስፈፀም ወደ ደቡብ ክልል በተንቀሳቀሱት የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ም/ኃላፊው አቶ ዳንኤል ሽበሺ ላይ እና ከ32 በሚበልጡ የወላይታ ዞን አመራሮች ላይ መጋቢት 13 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም መንግስታዊ ውንብድና ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በወላይታ ዞን ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ ላሊሼ ኦሌ የሚመሩና የደህንነት ሰዎችን ጨምሮ ከ8-1ዐ የሚሆኑ መንግስታዊ ወሮበሎች የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክር ቤት አባላት የተሰበሰቡበትን ግቢ በሀይል ሰብረው በመግባት የፓርቲ ሰነዶችን፣ ሁለት ሳምሰንግ ጋላክሲ ስልኮችን ጨምር በድምሩ ከ2ዐ የሚበልጡ የሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ሄደዋል፡፡
ወሮበሎቹ ታርጋ የሌላቸው ሞተር ሳይክሎችን በመጠቀም አመራሮቻችንን ወደ ፖሊስ ጣቢያ አስገድደው ወስደዋል፡፡ ከፓርቲያችን አመራሮቻችን የተነጠቁ ስልኮች በዞኑ ፖሊስ አዛዥ ቢሮ ውስጥ ፈሳሽ ውስጥ በመጨመር ከጥቅም ውጭ በማድረግ ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮችና የዞኑን ም/ቤት አመራሮች ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳይኖራቸው አድርገዋል፡፡ አመራሮቹን አፀያፊ በሆነ ማጎሪያ ውስጥ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡30 አስረው ማደሪያ ሊያገኙ በማይችሉበት ሰዓት ለቀዋዋቸዋል፡፡ ይህ አይነቱ ከመንግስታዊ አካል የማይጠበቅ ውንብድና በሚሊዮኖች ድምጽ የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ወቅት ሐምሌ 5 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በዚሁ ዞን ተፈፅሞ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የጠራነውን ሕዝባዊ ስብሰባ ለማደናቀፍ ታርጋ የሌላቸውን ሞተር ሳይክሎች በመጠቀም በቅስቀሳ ላይ የነበሩ አባላትን በመደብደብና በመዝረፍ እንዲሁም የተከራየነውን አዳራሽ ጥበቃዎች ዘግተው እንዲሄዱ ከመደረጉም ባሻገር ከግለሰብ የተከራየነውን ሞንታርቮ ዘርፈው እስከ ዛሬም አልመለሱም፡፡
ምንም እንኳ የአንድነት ከፍተኛ አመራርና አባላት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን በሚካሄደው ትግል ውስጥ መንገላታት፣ መደብደብ፣ መታሰርና ሞትም ካለ አይናቸውን ሳይጨፍኑ አፍጠው ለመቀበል ዝግጁ ቢሆኑም ይህን አሳፋሪ ድርጊት በቸልታ የማንመለከተውና አስፈላጊውን ነገሮች አጣርተን ተገቢውን ፖለቲካዊና ሕጋዊ እርምጃ የምንወስድበት ጉዳይ መሆኑን መግለጽ እንወዳለን፡፡
ሕገ መንግሥቱ ላይ የሠፈረውን የመደራጀት መብትና እና በተሻሻለው በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2ዐዐዐ አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ‹2› የፖለቲካ ፓርቲዎች የዕለት ከዕለት ተግባሮችን ስር ፤ የሕዝቡን ፖለቲካዊ ግንዛቤ ማዳበር፣ የፓርቲውን ዓላማ ለሕዝቡ ማስረጽ፤ ዜጎች በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው መቀስቀስ፣ በሕዝቡና በመንግሥት ተቋማት መካከል ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረግ የሚሉ ግልጽ ድንጋጌዎች ሰፍረዋል፡፡ በአንፃሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዛ አባሎቻቸው ጋር በማንኛውም ጊዜ መሰብሰብ እንደሚችሉ እየታወቀ በመንግስትና በገዢው ፓርቲ የሚፈፀሙ ሕገ ወጥ ተግባሮች በየእለቱ ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ሕግ ማክበርም ማስከበርም ያልቻለው ኢህአዴግ ሠላማዊ ትግሉን የሚደፈጥጡ ድርጊቶች ፈፃሚና አስፈፃሚ ካድሬዎች እና ሕገ አስከባሪ የተባለው የወላይታ ዞን ፖሊስ አዛዥ አይነት ግለሰቦችን በማበረታታት ሕጋዊና ሠላማዊ ትግሉን ወደ ጠርዝ እየገፋ ይገኛል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮችና ለወላይታ ዞን የወረዳ አመራሮችና አባላት ያለንን ክብር እየገለፅን፣ በወላይታ ሶዶ በአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና የፓርቲያችን የዞኑ ምክር ቤት አባላት ላይ የተፈፀመው መንግስታዊ ውንብድና ስርአቱ የወረደበትን የዝቅጠት ደረጃ አመላካች እንደሆነ ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
ድል የሕዝብ ነው!
መጋቢት 16 ቀን 2ዐዐ6 ዓም
አዲስ አበባ
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ማርች 25, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
UTC 16:00 የዓለም ዜና 250314
የዕለቱ ዜና
የሙሥሊም መሪዎች የክስ ሂደት
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ችሎት በዛሬው ውሎው የሙሥሊም መሪዎችን የክስ ሂደት ተመለከተ። ችሎቱ በነአቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ ዓቃቤ ሕግ በአሸባሪነት ክስ የመሠረተባቸውን ተከሳሾች ጉዳይ ከተመለከተ በኋላ
የገቢ ግብር ማጭበርበር በጀርመን
የታዋቂው የጀርመን የእግርኳስ ክለብ ባየር ሚውኒክ ፕሬዝዳንት ኡሊኽነስ የገቢ ግብር በማጭበርበር ወንጀልከ 12ቀናት በፊት 3 ዓመት ተኩል የእስር ቅጣት ተበይኖባቸዋል ። ባለፀጋ ኽነስ ብይኑን ይግባኝ ሳይሉ ወህኒ እንደሚወርዱ አስታውቀዋል። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን በኽነስ ላይ የተላለፈው ብይንና አስተምህሮቱ ላይ ያተኩራል ።
የቡድን ሰባት ውሳኔ እና ሩስያ
የቡድን ሰባት ሀገራት መሪዎች ትናንት በዘ ሄግ፣ ኔዘርላንድ ስለዩክሬይን ውዝግብ ለመምከር በጠሩት ልዩ ስብሰባ ላይ፣ ሩስያ የዩክሬይን ግዛት የነበረችውን ክሪሚያን የግዛቷ አካል አድርጋ በመቀበሏ ፣ ሞስኮ
የግል ንፅህና እና የዓይን ሕመም
የዓይን ማዝ በሽታን በቀላሉ መከላከል ሲቻል ዛሬም ለብዙዎ የዐይን ብርሃን ማጣት ምክንያት እየሆነ ነዉ። የድህነት በሽታ በመባል የሚገለፀዉ ይህ የዐይን ህመም በዓለም 21 ሚሊዮን ሰዎችን እንደጎዳ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያ ዉስጥም ይህ የዓይን ሕመም በተለያዩ ክልሎች ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ እየተገለጸ ነዉ።
የሙሥሊም ወንድማማቾች የሞት ብይን
በትናንትናዉ ዕለት የግብፅ ፍርድ ቤት በ529 የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበር አባላት ላይ የሞት ቅጣት በይኗል። ዉሳኔዉ በተሰጠበት በዚሁ ችሎት 147ቱ ብቻ ናቸዉ በስፍራዉ ተገኝተዉ ፍርዱን ያደመጡ ሲሆን ቀሪዎቹ ከሚጠብቃቸዉ ፍርድ ለማምለጥ በሽሽት ላይ መሆናቸዉ ተገልጿል።
የደቡብ ሱዳንና የግብፅ ወታደራዊ ስምምነት
ደቡብ ሱዳን ከግብፅ ጋ የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መፈራረሟን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጁባ ተመሳሳይ መግባባት ላይ ከሁለት ዓመታት በፊት ከተነጠለቻት ሰሜን ሱዳን ጋም መድረሷ ተገልጿል።
ቤተ ክህነቱን ከሙሰኞችና ከጎሰኞች የማጥራት ዘመቻው ይሳካ ይሆን?!
ኑ! እንዋቀስ፤ ኢህአዴግንም እናፍርሰው! (ሊያነቡት የሚገባ)
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም) ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ ደርሷል። ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል። በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ እንዳላልኩ ልብ ይሏል። ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣ በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው።
አቡጊዳ – ሕወሃቶች አሰብን እናስመልሳልን እያሉ ነው !
በሕዝብ ብዛት ቁጥር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛ ከአለም ደግሞ አሥራ አምስተኛ ናት። ወደ ሰማኒያ ሚሊዮን ሕዝብ ሲኖራት፣ ያን ያህል ሕዝብ ኖሯት የባህር በር የሌላት ብቸኛ አገር ናት። ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ብዙ ሕዝብ ኖርቷት የባህር በር የሌላት አገር፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሶስተኛ የሚሆን ሕዝብ ያላት ዩጋንዳ ናት። የቀድሞ ጥቅላ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ፣ በባህር ወደብ ዙሪያ ሲጠየቁ «ለእድገት […]
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ማርች 24, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ኦባማና የውጭ ጉዳይ የፖለቲካ መርኀቸው
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ዖባማ፤ ዛሬ ኔድርላንድ እንደገቡ በሰጡት መግለጫ ፣ አውሮፓውያንን ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያ በክሪሚያ በወሰደችው እርምጃ ሳቢያ ዋጋ የሚያስከፍላትን የማዕቀብ ርምጃ በመተባበር ወስደናል አሉ። ሰፊ የጦር ኃይል አንቀሳቅሶ
በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ያጋጠመው የወረቀት ቃጠሎ
በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፣ ባለፈው ቅዳሜ ከቀትር በኋላ በደረሰው የአሳት ቃጠሎ፣ በዋናው ህንጻና ማሺኖች ላይ የደረሰ ጉዳት ባለመኖሩ፤ የማተሚያ ቤቱ መደበኛ ሥራ አለመተጓጎሉን ማተሚያ ድርጅቱ ገለጠ። በቃጠሎው የወደሙት በጓሮ በኩል የነበሩ ትርፈ
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የአዲስ አበባ ጉብኝት
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍርንክ ባልተር ሽታይንማየር በአፍሪቃ የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ጀርመናዊው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና
የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ከዉጪ ጉዞ መታገድ
የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ የሰማዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ከአዲስ አበባ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይጓዙ ታግደዋል።ኢንጂነር ይልቃል
ኢትዮጵያን በሮም የሚቋቋም አልተገኘም
በሮም አደባባይ ኢትዮጵያውያኑ ጀግኖች አትሌቶች ትናንት ድርብ ድል ተጎናፅፈዋል። በወንዶችም፣ በሴቶችም ማንም ከፊታቸው ደፍሮ መቆም አልቻለም። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ መድፈኞቹን ሰማያዊ ለባሾቹ በገዛ መድፋቸው አፈር ድሜ አብልተዋል። ማን ዩናይትድን ያሳፈረው ባቡር ግን እየተንገታገተ ነው። ሊቨርፑል እና ቸልሲ ተናንቀዋል።
የሃረር ክራሞት – “…አዘናግቶ ሊያጋየን ነው::” = ሕወሓት ሰራሾች እና ሕዝቡ ከንፈር ተነካክሰዋል።
ሸዋ በር እና አከባቢው ስጋት ነጋደው ጭንቀት እንዳጠላበት ነው።”…አዘናግቶ ሊያጋየን ነው::”
የእሳት ማጥፊያ አዘጋጁ እሳት ሊነሳ ይችላል የሚለውን ወያኔያዊ ሽብር በነጋዴዎች ዘንድ ጥርጣሬ አጭሯል::
ምንሊክ ሳልሳዊ:-በሃረር ለረዥም ጊዜ ታፍኖ የቆየው ብሶት ባለፈው ሰሞን የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ሕዝቡ አደባባይ እስከመውጣት ደርሶ ነበር::የወያኔው መንግስት ካለፉት አመታቶች ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የሃረር ነጋዴዎችን መደብሮች ሲያቃጥል እንደ ዋናው ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው አከባቢው ለልማት ስለሚፈለግ ከቦታው ተነሱ የሚለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ነጋዴዎቹ በምትኩ ቦታ ይሰጠን የሚሉትን አስታኮ የሚመጣ ቃጠሎ መሆኑ እና ከቃጠሎ በፊት ወደ መደብሮች መጋዘን የሚገቡ ነዳጅ የተሞሉ ጀሪካኖች ሕዝቡ ጣቶቹን በወያኔ ላይ እንዲጠቁም አድርጎታል::
ወያኔ የሃረር ህዝብ ላይ ያደረሰውን ሰቆቃ እና በደል ለመሸፈን ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት ነገሮችን በሙሉ አሸባሪ ብሎ በሚጠራቸው በመላከክ ህዝቡን ለመሸወድ ቢሞክርም አልተሳካለትም:: በየመንገዱ ቢያፍስ ቢያባርር ቢደበድብ ቢያስር ስብሰባ ቢጠራ ያልተሳካለት ወያኔ ከዚህ በመቀጠል ምን ሊያመጣ እንደሚችል እስካሁን የታወቀ ነገር የለም:: ምናልባት ይላሉ የሸዋ በር እና አከባቢው ነጋዴዎች ስጋታችንን እና ጭንቀታችን መደብሮቻችንን እንዳያቃጥልብን ነው ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለውናል::
በውሃ እጥረት እና በሌሎች የአገልግሎት አቅርቦት የምትታመሰው ሃረር በሕወሓት ሰራሾች ደባ እየተደረገባት ያለው የሰብኣዊ መብት ገፈፋ እና በደል እየጨመረ እንዲ እየቀነሰ አለመሆኑ የሰሞኑ ምስክር ሂደት ምስክር ነው::በዚህ ሰሞን ከክልሉ ምክር ቤት እስከ ቀበሌ ካድሬዎች ስብሰባ ከሕዝቡ እስከ ነጋዴው ቢሰበሰብም በሰብሳቢዎች እና በተሰብሳቢው ሕዝብ መካከል አለመተማመን እንደነገሰ ተበትኗል:: በትላንትናው እለት በሸዋ በር አከባቢ ጀጎል ግንቡን አስታኮ ያሉ ባለመደብሮች ስብሰባ ተጠርተው እንዲሁም የእህል እና የቅመማ ቅመም ነጋዴዎች በስብሰባው ተጋብዘው የተገኙ እና በተሰብሳቢው እና በሰብሳቢዎች ሕወሓት ሰራሽ የከተማው ባለስልታናት መካከል ስጋት እና ሽንቀት ወጥሮት የተካሄደ እንደነበር ነጋዴዎቹ ጠቁመዋል::
የሸዋ በር አከባቢ ነጋዴዎች ባለፈው በመብራት ሃይል እና በሲጃራ ተራ አከባቢ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ ከተመለከቱ በኋላ ነግ በኔን በማሰብ ንብረታቸውን ከአከባቢው በማሸሽ ስጋታቸውን በተግባር ለወያኔ ሰራሽ አካላቱ ያሳዩ ሲሆን ይህንን የተመለከተው መንግስታዊ አካል ነኝ ያለ ክፍል ነጋዴው እቃውን ከማውጣት ከመንግስት ጋር በጠረጰዛ ዙሪያ እንሰብሰብ እቃችሁን አታሽሹ ቢልም ነጋዴዎቹ አዘናግቶ ሊያጋየን ነው በሚል እቃቸውን ወደቤታቸው ጭነው ወስደዋል::
ንብረታችን ቤታችን እንዳለ ስብሰባ እንቀመጣለን ብለው የቆረጡት ነጋዴዎች በተጠሩበት ስብሰባ በመሄድ ዋና ዋና የተባሉ ነጥቦችን አንስተዋል::ከተነሱት ነጥቦች በእሁድ ቀን ማንም ሰው በገበያ ቦታዎች ውስጥ መገኘት እንደማይኖርበት;እሁድ ቀን ጠቅላላ መደብሮች ዝግ መሆን እንዳለባቸው:የዘበኞች ቁጥር መጨመር እንዳለበት:ወዛደሮች መታወቂያ እና ባጅ ሊኖረው እንደሚገባ እና መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን:በንግዱ አከባቢ ዳር ዳሩን የመኪና መንገድ ላይ ያሉ በረንዳዎች እና መደቦች መጽዳት እንዳለበት በገበያ ውስጥ እሳት ማጥፊያዎች እና የውሃ ታንከሮች እንዲዘጋጁ ተወያይተውባቸዋል:; በዚህም መሰረት ነጋዴዎቹ የመተማመን መንፈስ ባይታይባቸውም ወኪሎቻቸውን መርጠው ስራውን ሊሰሩ የተስማሙ ሲሆን እስከዛሬ ያልታሰበ የእሳት ማጥፊያ እና የውሃ ታንከር አዘጋጁ እሳት ሊነሳ ይችላል የሚለውን ወያኔያዊ ሽብር በጥርጣሬ ተመልክተውታል::ምንሊክ ሳልሳዊ
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከታች በአስተያየት መስጫ ውስጥ የምትመለከቱት ምስል ከሶስት አመት በፊት ቦታው ለኢንቨስትመት ይፈለጋል ተነሱ የተባሉ ነጋዴዎች ምትክ ቦታ ይሰጠን እያሉ ሲከራከሩ የወያነ ሰራሽ የክልሉ ባለስልጣናት በድንገት የነጋዴዎችን መደብሮች ያቃተሉት ቦታ ሲሆን ይህ ቦታ ወደ መብራት ሃይል ሂደው ባለፈው ሱቆቻቸው የተቃተሉባቸው ነጋዴዎች ቦታ የነበረ ነው:: መንግስታዊ እሳት እየተከተለን ነው የሚሉ የመብራት ሃይል መደብር ባለቤቶች እና ተጎጂዎች ከ3 አመት በፊት የተቃጠለባቸው ቦታ ሕንጻ ለማሰራት ለአንድ ኢንቨስተር ተሰቶት ጥናት ተካሂዶ ቦታው ለኮንስትራክሽን አመቺ እንዳልሆነ እና አከባቢው ውሃ የሞላበት እና ሕንሳ ሊያሰራ የማይችል አፈሩም ለሕንሳ ግንባታ ተስማሚ እንዳልሆነ ይህ ቦታ ላይ ህንጻ ለማስገንባት ከፍተኛ ወጪ እና ዲዛይን የሚጠይቅ በመሆኑ ቦታው በዚህ ምክንያታዊ ጉዳዮች ለ3 አመት ያህል በምስሉ እንደምታዮት ታጥሮ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት የተቃጠለው የሲጃራ ተራ እና የመብራት ሃይል ከቃጠሎ የተረፉ ቆርቆሮዎች እና ሌሎች ማቴሪያሎች መከመሪያ እየሆነ ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ



አቡጊዳ – የአንድነት እና መኢአድ ዉህድ ፓርቲ የመድረክ አባል አይሆንም ተባለ
መኢአድ እና አንድነት መጋቢት 11 ቀን የቅድመ ዉህደት ፊርማ ይፈረማሉ ተብሎ ሲጠበቅ ፣ ከመኢአድ ፕሬዘዳንት አቶ አበባው መሃሪ በተጻፈ ደብዳቤ፣ ላልተወሰነ ጊዜ ፊርማው እንዲዘገይ መደረጉ በስፋት ተዘግቧል። አቶ አበባዉ የቅደመ ዉህደቱን ፊርማ ላለመፈረም ሶስት ያልተፈቱ ነጥቦች የሚሏቸውን ያቀርባሉ። ነጥቦቹም የዉህድ ፓርቲው ስያሜን፣ የመሪዎች መመዘኛን እና አንድነት ከመድረክ ጋር ያለዉን ግንኙነት የሚመለከቱ ናቸው። አቶ አበባዉ ባቀረቧቸው […]
ኢህአዴግ ባደባባይ የወደቀውን ፈተና “በጓሮ” አለፈ ግልጽነትና ተጠያቂነት ፈረዱ ወይስ ተፈረደባቸው?

March 24, 2014 08:11
ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ብሎም ለህዝቦች ጥቅም ቅድሚያ እንደሚሰጥ ህግ ደንግጎ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ኢህአዴግ ያቀረበውን የይግባኝ ማመልከቻ ተቀብሎ ማጽደቁ አነጋጋሪ ሆኗል። በ2009 ኢህአዴግን “ያወጣሁትን መስፈርት አታሟላም” በማለት እውቅና የከለከለው ይህ ተቋም፣ ኢህአዴግ በሚከሰስባቸው ዋና ጉዳዮች ለውጥ ሳያደርግ የራሱን ውሳኔ የገለበጠበት አካሄድ እየተመረመረ እንደሆነ የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል።
የኢህአዴግን የእውቅና ይግባኝ ጥያቄ ተቀብሎ ያጸደቀው የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የሚባለው ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ነው። ተቋሙ ኢህአዴግ በ2009 አቅርቦት የነበረውን የእውቅና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ የሰጠው ምክንያት “የመያዶች ህግ የተሰኘው” አዋጅ ተግባራዊ እንዳይሆንና በአገሪቱ የተተከሉት አፋኝ ህጎች እስካልተወገዱ ድረስ ማመልከቻው እንደማይታይ በማሳወቅ ነበር።
በ2009 ጠ/ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ “መሰዋት” በስተቀር ኢህአዴግ አንዳችም ለውጥ ባላደረገበት ሁኔታ ባለፈው ረቡዕ መጋቢት 19፤2006 (March 19፤2014) ይኸው እውቅና ሰጪ ተቋም የራሱን ውሳኔ ቀልብሶ ለኢህአዴግ እውቅና መስጠቱ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። ከውሳኔው ቀናት በፊት በጓሮ የሚወጠን ድርጊት እንዳለ መረጃ ደርሶት የማሳሰቢያ ተቃውሞ ያሰራጨው ሂውማን ራይትስ ዎች የተሰኘውየሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳለው ከሆነ ከተገለበጠው ውሳኔ በስተጀርባ ሚስ ክሌር ሾርት ከፊት ረድፍ ተቀምጠዋል።
ማመልከቻው እንደገና እንዲታይና የቦርዱ የቀድሞ ውሳኔ እንዲገለብጥ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የቀድሞ የእንግሊዝ ዓለምአቀፍ ትብብር ሚ/ር የሆኑት ክሌር ሾርት መሆናቸውን የድርጅቱ መግለጫው ይፋ አድርጓል። እኚህ ግለሰብ የአፍሪካ አምባገነኖችን በመደገፍ የሚታወቁ ሲሆን ይህ ከጥቅማቸው ጋር የተሳሰረው ግንኙነታቸው አሁንም ኢህአዴግን እንዲደግፉ እንዳደረጋቸው ይነገራል፡፡ እንዲሁም በሌሎች ኢህአዴግ ባቋቋማቸው ዓለምአቀፋዊነት ሽፋን በተላበሱ ድርጅቶች ውስጥ የአመራር አባል በመሆን ሚስ ሾርት እንደሚያገለግሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የእንግሊዝ ፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅትም ያላወጡትን ወጪ አውጥቻለሁ በማለት በብዙ ሺዎች የሚገመት ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መሆናቸው በወቅቱ ዴይሊ ቴሌግራፍ ባወጣው መረጃ አጋልጦ ነበር፡፡ የተወሰነውን ገንዘብ የመለሱ ቢሆንም ጋዜጣው በወቅቱ ያወጣው መረጃ ግለሰቧ የሕዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው የተጠቀሙ “ሙሰኛ” መሆናቸውን ያስረዳል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከሆነ ባለፈው ረቡዕ ኦስሎ፤ ኖርዌይ ላይ ውሳኔው በተላለፈበት ወቅት ሚስ ሾርት በግልጽ የኢህአዴግ ደጋፊ በመሆን ተጽዕኖ በማድረግ ወደ ውሳኔ እንዲደረስ ግፊት አድርገዋል፡፡ ግለሰቧ ባላቸው ኃላፊነት በመጠቀም (የEITI የቦርድ ኃላፊ ናቸው) እንዲህ ዓይነቱ ግልጽና ወገናዊነት የታየበት ድጋፍ በማድረግ ከድርጅቱ አሠራር ውጪ ውሳኔ እንዲሰጥ ማድረጋቸው ለወደፊት በሚቀርቡ ማመልከቻዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የአሠራር ችግር እንደሚያስከትል ካሁኑ እየተጠቆመ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከማዕድን ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ማህበራዊ ቀውስ የደረሰባቸው አካባቢዎች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አካባቢዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባልጸዳ የሽያጭ ሂደት ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የገዙት ሻኪሶ የወርቅ ማዕድን በህዝብ ላይ እያደረሰ ችግር የሚዘገንን ነው። በየጊዜው ግልጽ ባልሆነ የማስፋፊያ ውል የሚፈናቀሉና ከፋብሪካው በሚወጣው ዝቃጭ ለከፍተኛ ብክለት የተጋለጡ ዜጎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ መታሰራቸው፣ መገረፋቸው፣ ለይስሙላ በተቋቋሙ ፍርድ ቤቶች የተፈረደባቸው እንዳሉ ታዛቢዎች ያስታውሳሉ።
በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ህዝብን እየበላ እንደሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች “ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ የሚደገፍና የሚበረታታ ተግባር ቢሆንም፣ ኢህአዴግ ፍትሃዊ በሆነ ደረጃ መጠቀም፣ ማስተዳደር፣ መምራትና ኢንቨስትመንቱን ህዝብ “የኔ” ብሎ በመቀበል እንክብካቤ እንዲያደርግ የሚያስችል ስርዓት አለማበጀቱን እንደ ዋንኛ ችግር ያነሳሉ። ኢህአዴግን ያዘጋጀው ህወሃት በራሱ ሰዎች አማካይነት ከውጪ ሰዎች ጋር እየተሻረከ ለህዝብ ጥቅም ሊውል የሚገባውን ሃብት ወደ ውስን ቋት እንደሚያግዝ የሚገልጹት እነዚሁ ክፍሎች” ይህ ዓለም የሚያውቀውን፣ ራሳቸው ህወሃቶችም የማይክዱትን እውነት ነው ብለዋል። ዜጎች የአገራቸው ሃብት ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ አካባቢያቸው ባደላቸው የተፈጥሮ ሃብት ሳቢያ መከራ ሲደርስባቸው፣ ሲሰቃዩ፣ ሲገረፉና፣ ሲገደሉ ማየት በተለመደባት ኢትዮጵያ ውስጥ ለኢህአዴግ የማይገባውን ካባ መደረብ ውሎ አድሮ የሚጋለጥ ክፉ ተግባር እንደሆነም አመልክተዋል።
አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው ቢከሽፋም በመጨረሻ ተሳክቶለታል። ስኬቱንና የስኬቱን መንገድ፣ በተለይም የዳይሬክተሯ ክሌር ሾርት ጉዳይና የተዘጋውን ፋይል በማንሳት ውሳኔው የተገለበጠበት አካሄድ ኦስሎ በሚገኘው ሃያ የቦርድ አባላት ባሉበት ተቋም ውስጥም ግራ ያጋባቸው እንዳሉ መረጃዎች አሉ።
ኢህአዴግ አጓድለሃል ተብሎ የሚከሰስባቸውን የዴሞክራሲ ግባቶችና የሰው ልጆች የተፈጥሮ መብቶች፣ አንዲሆም አፋኝ የተባሉትን ህጎች አጠናክሮ ተግባር ላይ ባዋለበት ሁኔታ፣ የዚሁ የአፈናው ሰለባዎች በተለያዩ ማጎሪያዎች ውስጥ ሆነው ድምጻቸውን በሚያስተጋቡበት ወቅት፣ EITI ከተቋቋመበት ዓላማና “መሰረቴ” ከሚለው የግልጽነትና ተጠያቂነት መርህ በተጻራሪ ግልጽነትና ተጠያቂነት በጎደለው መልኩ ለኢህአዴግ የደረበው ብሉኮ ጉዳይ እየተመረመረ አንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ጉዳዩን የሚከታተሉ “ግልጽነትና ተጠያቂነት በኦስሎ ተፈረደባቸው” ሲሉ ምጸት ሰጥተዋል፤ የክሌር ሾርትንም አካሄድ በEITI የህወሃት/ኢህአዴግ ተወካይ በማለት ተችተዋል። ይህንኑ ጉዳይ እመልክቶ ከሳምንት በፊት ለሪፖርተር አጭር መልስ የሰጡት የማዕድን ሚኒስትሩ EITI ውሳኔውን ያነሳል የሚል ጥርጣሬ እንዳለባቸው የሚያሳብቅባቸው መልስ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ዳያስፖራው እንደሚገባው አለመንቀሳቀሱ እንደ ሽንፈትና አቅጣጫ መሳት እንደሚቆጠር ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ጠቁመዋል፡፡ ዳያስፖራው ከጥቃቅንና ስሜታዊ ጉዳዮች በማለፍ በከፍተኛና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የማድረግ አመለካከቱን ማስፋት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ አለበለዚያ ኢህአዴግ እንደዚህ ዓይነቱን አጋጣሚ በመጠቀም የራሱን ገጽታ በዓለምአቀፍ መድረኮች እየወለወለ በማቅረብ የሥልጣን ዘመኑን እንደሚያራዝም ጠቁመዋል፡፡
‘Blame the Victim’: The Quest for Freedom vs. Professionalism of Media in Ethiopia?
“…Tafari and others draw three periods of the private press in Ethiopia. The first period was the chaotic period from 1991 to 1997 with a blooming of new newspapers and anarchy journalism. The second period, 1997-2005 saw the establishment of professionally and ethically integrated newspapers like Reporter, Addis Admas, Fortune and Capital. The last period goes from 2005 when press freedom again came under threat after editors and journalists were imprisoned and persecuted after alleged transgressions following the May 2005 elections…”
“David Ben-Gurion once said, ‘The test of democracy is freedom of criticism.’ Freedom of criticism has long been recognized as an essential, inalienable human right; a right that is thought to transcend political and geographical borders and applies regardless of culture, language, and national origin. In Ethiopia, as democracy begins to grow despite a history of corruption and totalitarianism, freedom of expression has proven to be an unsteady notion […]
“If Ethiopia hopes to move toward a more democratic State, it is critical to open the lines of communication between the government, media, and citizens. Freedom of expression is the only way to achieve an accountable and transparent government free from corruption and tyranny, while developing a professional and unbiased press. The press, in other words, must have the freedom to criticize the government.”
Edited by: Soleyana Shimeles
ሕወሓት መራሹ ኢሕኣዴግ አዲስ የልማታዊ ዲሞክራሲ የእቅድ ሰነድ እያዘጋጀ ነው::
መጭው ምርጫ ያሰጋው ወያኔ ሕዝቡን ለማደናበር እና ለማጭበርበር ሊረዳኝ ይችላል ያለውን አዲስ የልማታዊ ዲሞክራሲ ሰነድ እያዘጋጀ ሲሆን የባለራእዩ የሚሉት የመለስ ዜናዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በዝግታ ለማስቀረት እና ሕዝቡ አኩርፎበታል ያለውን የማንፌስቶ ሰነድ ለማዘጋጀት በአቶ በረከት የሚመራው ቡድን ስራውን መጀመሩ ታውቋል::
ተቃዋሚዎች ከፍተኛውን ድምጽ አግኝተው ከጨዋታ ውጪ ያደርጉኛል የሚል ስጋት ያደረበት ወያኔ በ1997 የተከሰተው አይነት ሽንፈት እንዳይደርስበት ከሰነዱ ዝግጅት ጎን ለጎን ስብሰባዎችን በማካሄድ ተቃዋሚዎች ከምርጫ የሚወጡበትን እና ምርጫውን የሚያጭበረብርበትን አዲስ ስልት እየነደፈ መሆኑንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል::የህዝቡ ብሶት እንደበረታ ያወቀው ሕወሃት መራሹ መንግስት በጭንቀት እና በምእራባውያን ጫና ተወጥሮ እንደሚገኝ ይታወቃል::
የመለስ ዜናዊ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በሃገሪቱ የአገልግሎት አቅርቦት ማጣትን:ሙስናን :ድህነትን:የዜጎች ስደትን :ስራ አጥነትን የኑሮ ውድነትን ወዘት ከማስፋፋቱም በተጨማሪ ምንም አይነት ውጠት እንዳልታየበት እና እስካሁን የተተገበረው የተጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ ምንም የፈየደው ነገር እንዳሌለ ኢሕኣዴግ በራሱ ድርጅታዊ ጉባዬ እና ስብሰባዎች መናገር ከጀመረ ሰነባብቷል::ምንሊክ ሳልሳዊ
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ማርች 23, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ቱርክ፥ የሶርያ ድንበር ላይ አውሮፕላን ተኩሳ ጣለች
የቱርክ የጦር ጄት በሶርያ ድንበር አኳያ አንድ የፕሬዚዳንት ኧል አሳድ ጦር ጄትን ተኩሶ እንደጣለ ተገለፀ።
የህዳሴ ግድብ ግንባታ 3ኛ ዓመት
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዕድገትና የለውጥ እቅድ ለማሳካት አስፈላጊ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የኤሌክትሪክ አቅርቦት ትልቁን ሚና ይዞዋል። በኢትዮጵያ የኤሌክትሪኩን አገልግሎት ዘርፍ የማስፋፋቱ ስራ ከተጀመረች ብዙ ዓመታት ቢሆነውም ፣ ውጤቱ እስካሁን የሚፈለገው ደረጃ ላይ ገና አልደረሰም።
መጋቢት 14 ቀን = ዝክረ- ተስፋዬ ደበሳይ
ዛሬ መጋቢት 14 ቀን ነው፡፡ የኢህአፓው መሪ ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ከደርግ ዋና ጽ/ቤት ለተላኩ ወታደሮች እጄን አልሰጥም ብሎ ከኪዳኔ በየነ ህንጻ (በድሮው አጠራር ፊሊፕስ ህንጻ) ላይ ራሱን ወርውሮ ህይወቱን ያጠፋው ልክ በዛሬዋ እለት በ1969 ዓ.ል. ነው፡፡ ኢህአፓዎች ተስፋዬ ደበሳይ ራሱን ያጠፋበትን ያንቺን ቅጽበት የቆራጥነትና የጽናት ተምሳሌት አድርገው ይዘክሯታል፡፡

በእርግጥም ተስፋዬ ደበሳይ ቆራጥ ነበር፡፡ ላመነበት ዓላማ ሺዎችን አንቀሳቅሷል፡፡ ለጠላቶቹ ሳይንበረከክ ህይወቱን ሰውቷል፡፡ በርሱ ሞት ያዘኑት ኢህአፓዎች “ተስፋዬን ከምናጣ ሌሎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቶቻችን በሙሉ ቢጠፉ ይሻለን ነበር” በማለት መሪር ሐዘናቸውን አሰምተዋል፡፡ የደርግ መንግሥት እርሱ በሞተበት ዕለት ባወጣው መግለጫ አንድ ክፍለ ጦር ሰራዊት የተደመሰሰ ያህል ነበር የፎከረው፡፡
ተስፋዬ ደበሳይ ማን ነው? በኢህአፓ ውስጥ የነበረው ሚና ምን ይመስል ነበር?… ህይወቱ የተፈጸመው እንዴት ነው? እስቲ በጥቂቱ እንየው፡፡
*****
ኢሮብ በትግራይ ክፍለ ሀገር፣ [deleted] አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ወረዳ ናት (በአሁኑ የአስተዳደር አወቃቀር በትግራይ ክልል፣ ምስራቃዊ ዞን ውስጥ ነው የምትገኘው)፡፡ በዚህች ወረዳ ከትግርኛ ተናጋሪው ብሄረ-ትግራይ በተጨማሪ ኢሮብ የሚባለው አነስተኛ ብሄረሰብ ይኖራል፡፡ ይህ ህዝብ በውስጡ ሶስት ዐይነት ማህበረሰቦች አሉት፡፡ አንደኛው ደመክኒቶ ይባላል፡፡ የዚህ ማህበረሰብ አባላት የካቶሊክ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ሁለተኛው ማህበረሰብ “ሀሳበላ” የሚባል ሲሆን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ይበዙበታል፡፡ ሶስተኛው ማህበረሰብ “ዳልገዳ” ይባላል፡፡ እነዚህኛዎቹ ደግሞ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ማህበረሰቦች የሚናገሩት ቋንቋ በኤርትራ ምድር ከሚነገረው የሳሆ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሆኖም ኢሮብ እና ሳሆ በኢኮኖሚ ስምሪታቸው ይለያያሉ፡፡ የሳሆ ህዝብ ሙሉ በሙሉ አርብቶ አደር ነው፡፡ ኢሮቦች ግን በእርሻ ስራና በአነስተኛ ዕደ-ጥበባት ነው የሚተዳደሩት፡፡ የኢሮብ ወረዳ ተራራና ሸንተረር ይበዛዋል፡፡ በአካባቢው ካሉት ተራሮች መካከል “አሲምባ” እና “አይጋ” ትልልቆቹ ናቸው፡፡
በዚህች የኢሮብ ወረዳ ውስጥ አሊቴና የምትባል አነስተኛ መንደር አለች፡፡ ይህች መንደር የአጋሜ አውራጃ ርዕሰ ከተማ ከሆነችው አዲግራት 35 ኪሎ ሜትር ያህል ትርቃለች፡፡ የመንደሪቷ ነዋሪዎች በአብዛኛው ካቶሊክ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ተሰፋዬ ደበሳይ በዚያች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው በ1933 የተወለደው፡፡ ወላጅ አባቱ አቶ ደበሳይ ካህሳይ ይባላሉ፡፡ እናቱ ደግሞ ወ/ሮ ምህረታ ዓዶ-ዑማር ነበሩ፡፡ ተስፋዬ የቤተሰቡ የበኩር እና ብቸኛ ወንድ ልጅ ነው፡፡ ከርሱ በኋላ የተወለዱት ስድስት ልጆች በሙሉ ሴቶች ናቸው (ለዚህ ጽሑፍ የመረጃ ምንጭ ከሆነው የመጋቢት ወር/2005 የኢህአፓ ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለው ከስድስት እህቶቹ መካከል አምስቱ በህይወት ይገኛሉ፤ ወላጅ አባቱም በህይወት አሉ)፡፡
አሊቴና በዚያ ዘመን ትምህርት ቤት አልነበራትም፡፡ ስለዚህ ህጻኑ ተስፋዬ የትምህርት ጉጉት ቢኖረውም እድሜው አስር ዓመት እስኪሆነው ድረስ ትምህርት ቤት ለመግባት አልታደለም፡፡ በ1943 ግን አዲግራት ከሚኖሩት አክስቱ ዘንድ ሄደና ትምህርት ቤት እንዲያስገቡት ለመናቸው፡፡ አክስቱም በከተማዋ ከሚገኝ ታዋቂ የካቶሊክ ሚሽን ትምህርት ቤት አስገቡት፡፡ ተስፋዬም እስከ ስምንተኛ ክፍል በዚሁ ት/ቤት ከተማረ በኋላ ዘጠኛ ክፍልን መቀሌ በሚገኘው አጼ ዮሐንስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀቀ፡፡ ይሁንና በወቅቱ የትምህርት ወጪውን በራሱ ሸፍኖ መማር እንደማይችል በመረዳቱ ፊት ወደ ነበረበት የካቶሊክ ት/ቤት ተመለሰ፡፡ እዚያም እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ከተማረ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ጣሊያን ሀገር ተላከ፡፡ በሀገረ ኢጣሊያ ሮም ከተማ ካለው Urbaniana University በፍልስፍና ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪውን ተቀበለ፡፡
ተስፋዬ በስራው ዓለም ሲሰማራ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራበት መስሪያ ቤት የማስታወቂያና መርሐ ብሄር ሚኒስቴር ነበር፡፡ በዚህ መስሪያ ቤት የምርምር ክፍል ሃላፊ ሆኖ እየሰራ በማታው ክፍል የአባዲና ፖሊስ ኮሌጅ አስተማሪ ለመሆን በቅቷል፡፡ በ1964 ለተጨማሪ ስልጠና ወደ አውሮጳ (ስዊዘርላንድ) ተልኳል፡፡ በዚያ እያለም በመቀጣጠል ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ልቡን ስለወሰደው ትምህርቱን ትቶ ሙሉ በሙሉ ወደዚያው ገብቷል፡፡
ታዲያ እርሱ ወደ ስዊዘርላንድ በሄደበት ወቅት በአውሮጳው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር እና በአሜሪካው የተማሪዎች ማህበር መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ይካሄድ ነበር፡፡ ሁለቱ ማህበሮች የተወዛገቡት የድርጅት ምስረታና አደረጃጀት፣ የኤርትራ ጥያቄ፣ የብሄረሰቦች መብት፣ የትጥቅ ትግል አስፈላጊነት በመሳሰሉ አርዕስተ ነገሮች ዙሪያ ነበር፡፡ በጊዜው የድርጅት አስኳል ለመመስረት ጥረት ያደርግ የነበረው የአልጄሪያው የስደተኛ ተማሪዎች ቡድን ከአሜሪካው ማህበር ጋር ተቀራራቢ አቋም አሳየ፡፡ የአውሮጳው ማህበር መሪዎች በሀገር ቤት ከነበሩ ጥቂት ተማሪዎች ጋር አንድ ዓይነት አቋም ላይ ደረሱ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይ ግን የአውሮጳው ማህበር መሪዎችን ውሳኔ በመቃወም ከአልጄሪያው ቡድን ጋር ወገነ፡፡ በዚህም መሰረት የአልጄሪያው ቡድን፣ የአሜሪካው ቡድንና አውሮጳ የነበሩት ጥቂት ተማሪዎች በድርጅት ምስረታ ሂደት ላይ መነጋገር ጀመሩ፡፡ ውይይቱ ለወራት ሲብላላ ከቆየ በኋላ በዓለም ዙሪያ ተበታትነው የነበሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ተማሪዎችንም ማካለል ጀመረ፡፡ በስተመጨረሻም በሚያዚያ ወር 1964 “የኢትዮጵያ ህዝቦች አርነት ድርጅት” (ኢህአድ) ተወለደ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይም ለድርጅቱ አመራር ከተመረጡ ሰባት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አንዱ ሆነ፡፡
*****
ኢህአድ የተወለደው በውጪ ሀገር ነው፡፡ ከ1964-1966 በነበሩት ዓመታት ዋነኛ ስራው ድርጅቱን ማስተዋወቅና አባላትን ማሰባሰብ ነበር፡፡ ከፍልስጥኤም ነጻ አውጪ ድርጅትና ከኤርትራ ግንባሮች የተሰጠውን ድጋፍ በመጠቀም የትጥቅ ትግል የመጀመር እንቅስቃሴ ሲያደርግም ቆይቷል፡፡ የድርጅቱ ቀዳሚ ዓላማ ከገጠር በሚጀመር የትጥቅ ትግል በረጅም ጊዜ የስርዓት ለውጥ ማምጣት ነበር፡፡ የኢህአድ መሪዎችም ድርጅቱ ቀዳሚ ሰራዊቱን ሊያሰማራበት ወዳሰበው የአሲምባ ተራራ በመሄድ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራር እንዲሰጡ ለማድረግ ታስቧል፡፡ ይሁንና በ1966 የፈነዳው የኢትዮጵያ አብዮት የትግሉን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ቀየረው፡፡ የአሮጌው ስርዓት መውደቅ አይቀሬ እንደሆነ ሁሉም በየፊናው አወቀ፡፡ “በርሱ ቦታ ተተክቶ ሀገሪቱን የሚመራው ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ ግን አነጋጋሪ ሆነ፡፡ በዚህም በተራማጅ አብዮተኞች መካከል ከፍተኛ ውይይት ተቀሰቀሰ፡፡ በመደምደሚያውም የፓርቲ ቅርጽ የነበራቸው ቡድኖች በከተሞች አካባቢ የፖለቲካ ትግል ቢያደርጉ ጠቀሜታው ከፍ ያለ እንደሚሆን ከስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በመሆኑም በውጪ ሀገር የነበረው የኢህአድ አመራር ወደ ሀገሪቷ ለመግባት ወሰነ፡፡
ከኢህአድ ከፍተኛ መሪዎች መካከል በቅድሚያ ወደ አዲስ አበባ የገባው ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ነው፡፡ ጊዜውም ሰኔ 1966 ነበር፡፡ በወቅቱ የወታደሮች ቡድን የሆነው ደርግ ተመስርቶ የአጼውን መንግሥት ለመጣል እያኮበኮበ ነበር፡፡ በሀምሌ ወር አጋማሽ ላይ ደርግ የልጅ እንዳልካቸውን ካቢኔ በመሻር ልጅ ሚካኤል እምሩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ መረጣቸው፡፡ ልጅ ሚካኤልም ካቢኔአቸውን ሲያቋቁሙ በስዊዘርላንድ የሚያውቁትን ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይን የመሬት ይዞታ ሚኒስትር እንዲሆን ጠየቁት፡፡ እርሱ ግን ከውጪ የመጣው ለዚያ አልነበረምና አንዳች ምክንያት ፈጥሮ አሉታዊ መልስ ሰጣቸው፡፡ በምትኩ በመስሪያ ቤቱ በኤክስፐርትነት ቢቀጠር ለመስራት ፈቃደኛ እንደሆነ ገለጸላቸው፡፡ በዚህም መሰረት ከነሐሴ 1966 ጀምሮ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ ሆነ፡፡
ተስፋዬ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ በኋላ ድርጅቱን በማስፋፋትና አባላትን በማደራጀት ስራ ላይ ነበር የተጠመደው፡፡ የድርጅቱ ልሳን የሆነችውን “ዲሞክራሲያ” ጋዜጣ ከሚያወጡ አርታኢያን መካከልም አንዱ ነበር፡፡ በድርጅቱ የመጀመሪያ ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሆኖ የተመረጠው ብርሃነ መስቀል ረዳ ከሰራዊቱ ጋር ስለነበር በርሱ ቦታ በጊዜያዊነት አመራር የሚሰጠውም ተስፋዬ ደበሳይ ነበር፡፡ በወቅቱ በድርጅቱ አመራር ላይ ከነበሩትም መካከል በዕድሜም ሆነ በትምህርት ደረጃ የሚበልጠው እርሱ ነበር፡፡
ተስፋዬ እስከ ታህሳስ 1967 በአዲስ አበባ ከተማ ከቆየ በኋላ ከመሬት ይዞታ ጋር ለተያያዘ የመስክ ስራ ወደ ትግራይ ተጓዘ፡፡ እግረ መንገዱንም አሲምባ የሚገኘውን የድርጅቱን ጀማሪ ሰራዊት ለመጎብኘት ወደዚያው ጎራ አለ፡፡ በጊዜው የነበረውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ ለሰራዊቱ ካብራራ በኋላ ግን ያልተጠበቀ ችግር ተከሰተ፡፡ ስምንት ያህል የሰራዊቱ አባላት ከጀማሪ ሰራዊቱ በመነጠል ለደርግ እጃቸውን ሰጡ (እጃቸውን የሰጡት ሰዎች ተስፋዬ መኮንን፣ ኃይለ እየሱስ ወልደ ሰንበት፣ አበበ በየነ፣ ዘከሪያ መሐመድ፣ አያሌው ከበደ፣ ጋሻው መንግሥቱ፣ ሀይሌ ወልደ ጊዮርጊስና ዳዊት አሰፋ ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች በ1968 መጀመሪያ ላይ “ማሌሪድ”፣ ማለትም “የማርክሲስት ሌኒኒስት ሪቮሉሽናሪ ድርጅት”ን መስርተዋል)፡፡ ታዲያ የነዚህ ሰዎች ከኢህአፓ አፈንግጦ መውጣት የዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይን ማንነት አጋለጠው፡፡ በመሆኑም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህቡዕ ለመግባት ተገደደ፡፡
*****
ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ህቡዕ ከገባ በኋላ የሙሉ ጊዜ አብዮታዊ ሆኗል፡፡ ኢህአድን በሙሉ አቅሙ አገልግሏል፡፡ በነሃሴ ወር 1967 ድርጅቱ ስሙን ቀይሮ “ኢህአፓ” (የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ) የተሰኘውን ዝነኛ መጠሪያውን የያዘበትን ጉባኤ በዋናነት ያዘጋጀውም እርሱ ነው፡፡ የድርጅቱ የፍልስፍና ሊቅ (ideologue) ሆኖ የሚያገለግለውም እርሱ ነበር፡፡ በኢህአፓ መስራች ጉባኤ “ዋና ጸሐፊ” የሚባል የስልጣን ተዋረድ ሲሻር በቀዳሚነት የማዕከላዊ ኮሚቴ ጸሐፊ ሆኖ ማገልገል የጀመረው እርሱ ነበር (ይህ የጸሐፊነት ቦታ በየጊዜው ይለዋወጥ ነበር፤ ጸሐፊው የሚመረጠውም በፓርቲው ጉባኤ ሳይሆን በፖሊት ቢሮው ነው)፡፡
እስከ 1968 አጋማሽ ድረስ በነበረው ጊዜ የኢህአፓ አመራሮች ማንነት በግልጽ አይታወቅም፡፡ በዚያን ጊዜ ህቡዕ ለመግባት የተገደዱት ብርሃነ መስቀል ረዳ እና ተስፋዬ ደበሳይ ብቻ ናቸው፡፡ በመሆኑም አብዛኛው የፓርቲው ስራ የሚከወነው በተስፋዬ ነበር (ብርሃነ መስቀል ለፖሊት ቢሮው ስላልተመረጠ ከፍተኛ ሃላፊነት አልተሰጠውም፤ በተጨማሪም ከሌሎች መሪዎች ጋር መነታረክ ጀምሮ ነበር) ፡፡
የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ከተመሰረተ በኋላ ግን አመራሩን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ በጽ/ቤቱ የተመረጡት ከፍተኛ ካድሬዎች የኢህአፓ መሪዎችን ስለሚያውቋቸው ለደርግ አሳልፈው ይሰጡአቸዋል የሚል ስጋት ሰፈነ፡፡ በመሆኑም በ1968 መጨረሻ ገደማ ሁሉም መሪዎች ህቡዕ ለመግባት ተገደዱ፡፡ ታዲያ የኢህአፓ የትግል ስትራቴጂም መለወጥ የጀመረው ከዚህ ወቅት ጀምሮ ነው፡፡ ከ1968 ክረምት ወራት በፊት በከተሞች አካባቢ የፖለቲካ ትግል ብቻ ያደርግ የነበረው ኢህአፓ የደርግ ፋሺስትነትን ለመከላከል በሚል የከተማ ትጥቅ ትግል የጀመረው ያኔ ነው፡፡
አንዳንድ ወገኖች የትጥቅ ትግሉ በዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ግፊት የመጣ ነው ይላሉ፡፡ ከሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማሪያም ጀምሮ መገደል ያለባቸውን ከፍተኛ የደርግና የመኢሶን ባለስልጣናት ዝርዝር እያዘጋጀ የሞት ፍርድ ያስወስን የነበረው ተስፋዬ ደበሳይ ነው በማለት ይሞግታሉ፡፡ ከዚህ እልፍ ሲል ደግሞ የተስፋዬን ትግሬነት በመጥቀስ ብቻ ሻዕቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ሽብር ለመቀስቀስ የመደበው የጥፋት ወኪል ነው የሚል መረጃ የሚያስነብቡ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ ሆኗል (ለነገሩ ተስፋዬ የኢሮብ ተወላጅ ነው እንጂ ትግሬ አልነበረም)፡፡ ይሁንና እንዲህ ዓይነቱን የተናጥል ክስ በተስፋዬ ላይ የሚያጠናክር ማስረጃ የለም፡፡ ኢህአፓ የከተማ ትጥቅ ትግል እንዲጀምር የወሰኑት ብዙሃኑ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ናቸው እንጂ ተስፋዬ ደበሳይ ብቻ አልነበረም፤ ውሳኔውን የተቃወሙት ጌታቸው ማሩ እና ብርሃነ መስቀል ረዳ ብቻ ነበሩ (በጊዜው የኢህአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የነበሩት ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ፣ ዮሐንስ ብርሃኔ፣ ዮሴፍ አዳነ፣ ክፍሉ ታደሰ፣ ክፍሉ ተፈራ፣ ዘርዑ ክህሸን፣ ኢያሱ አለማየሁ፣ ሳሙኤል አለማየሁ፣ አበራ ዋቅጅራ፣ ፍቅሬ ዘርጋው፣ ጸጋዬ ገብረመድህን፣ ብርሃነ መስቀል ረዳ፣ ጌታቸው ማሩ እና ጸሎተ ህዝቅያስ ነበሩ)፡፡
*****
መስከረም 13 ቀን 1969፡፡ በዚህች ዕለት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ለመግደል ያልተሳካ ሙከራ ተደረገ፡፡ በዚህም የተነሳ ኮሎኔሉ ኢህአፓን ለማጥፋት ቆርጠው ተነሱ፡፡ በስውር የሚያካሄዱትን ርሸና ይፋ ማውጣት ጀመሩ፡፡ በታህሳስ ወር የኮሎኔሉን እርምጃ የሚቃወሙ መኮንኖች በደርግ ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ አካሄዱ፡፡ ይሁን እንጂ ከአንድ ወር በኋላ (ጥር 25/1969) ኮሎኔል መንግስቱ ማንም ባላሰበው መንገድ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት “ለምሳሌ ያሰቡንን ቁርስ አደረግናቸው” በማለት አወጁ፡፡ “አብዮቱ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል” ተባለ፡፡ “ቀይ ሽብር” በይፋ ታወጀ፡፡ “ነጻ እርምጃ” ተፈቀደ፡፡
በወቅቱ የኢህአፓው ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ አዲስ አበባ ውስጥ እንደነበረ ደርጎች ያውቁ ነበር፡፡ ነገር ግን አድራሻውን በትክክል ማወቅ አልቻሉም፡፡ ኢህአፓም ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ እየተባባሰ በመሄድ ላይ የነበረውን የደርግ እርምጃ ለመቀልበስ እንደማይችል አውቆታል፡፡ ይሁንና የከተማውን የትጥቅ አመጽ አላቋረጠም፡፡ ደግሞም ዋና መሪውን ከደርግ አፍንጫ ስር አውጥቶ ከደህና ቦታ ለማድረስ አልሞከረም፡፡
ታዲያ ኢህአፓዎች መሪአቸው ከከተማው ወጥቶ ለደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ ቦታ ቢደበቅ ይፈልጉ ነበር፡፡ በተለይ በመጋቢት ወር አጋማሽ (1969) ከሚካሄደው የቤት ለቤት አሰሳ ነፍሱን እንዲታደግ ይመኙ ነበር፡፡ ይሁንና መሪው ከከተማው ለመውጣት ምንም ዓይነት ፍላጎት አልነበረውም፡፡ “በዚህ ክፉ ቀን ተከታዮቼን ጥዬ ከከተማ አልሰደድም” በማለት ቆርጧል፡፡ አሰሳው ከመጀመሩ አስቀድሞ በነበሩት ቀናት ራሱ ሸኝ ሆኖ በልዩ ልዩ እርከን ላይ ያሉ ኢህአፓዎችን ከከተማው ወደ ገጠር ይሸኝ ነበር፡፡ ለምሳሌ የቤት ለቤት አሰሳው ከሚካሄድበት ዕለት በፊት በነበሩት ቀናት (ከመጋቢት 10-13 ባሉት ቀናት) ተስፋዬ ደበሳይ በርካታ የኢህአፓ አባላትን ከከተማ እያስወጣ ወደ ገጠር መሸኘቱ ተመዝግቧል፡፡ በነዚያ ቀናት በርካቶች ወደ አሲምባና ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ሄደዋል፡፡ እርሱ ግን እዚያው ሆኖ አሰሳው የሚያመጣውን ውጤት ለማየት ይጠባበቅ ነበር፡፡
*****
ዕለቱ መጋቢት አስራ 15/1969 ነው፡፡ ደርግ የቤት ለቤት አሰሳውን እያካሄደ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቤት እየተከፈተ ይፈተሻል፡፡ “አናርኪስት” ተብሎ የተጠረጠረ ሰው እየተያዘ ወደ ማዕከላዊ ምርመራና የቀበሌ እስር ቤቶች ይጋዛል፡፡ ከእስራቱ ለማምለጥ የሞከረ ያለ ምንም ጥያቄ ይገደላል፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ያረፈበት የበሪሁን ማሪዬ ቤትም እንደሚፈተሽ መረጃው ለኢህአፓ አሀዶች ደርሷል፡፡ በመሆኑም የተስፋዬን ህይወት ለመታደግ ቀኑን በመንግሥት ቢሮ ውስጥ ተደብቆ ማሳለፍ አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል (በወቅቱ ቢሮዎች አይፈተሹም ነበር)፡፡ በዚህ መሰረት ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይና በሪሁን ማሪዬ አምባሳደር ቴአትር አካባቢ ባለው ኪዳኔ በየነ ህንጻ ውስጥ በሚገኘው የበሪሁን ሚስት ቢሮ ለመደበቅ ወሰኑ፡፡ በበሪሁን ማሪዬ ሾፌርነትም ከመርካቶ አካባቢ ወደ አምባሳደር ቴአትር እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ ተክለ ሀይማኖት አካባቢ ሲደርሱ ግን ተስፋዬን በሚያውቅ ሰው እይታ ውስጥ ገቡ፡፡ ያ ሰው ወዲያኑ ለደርግ ጸጥታ ሀይሎች በመደወል የተስፋዬን መገኘት አበሰራቸው፡፡ ለራሱ ደግሞ በቀስታ (እነርሱ ሳያዩት) ከኋላ እየነዳ ተከተላቸው፡፡ ደርጎች ለወራት ሲፈልጉት የነበረው አውራ ጠላታቸው ዱካ መገኘቱን ሲሰሙ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ተባለው ስፍራ አሳሽ ጦር ላኩ፡፡
ተስፋዬ ደበሳይና በሪሁን ማሪዬ ወደ ኪዳኔ በየነ ህንጻ ገቡ፡፡ ሆኖም ህንጻው እንደጠበቁት ነጻ ሆኖ ስላላገኙት ወደ መጡበት ለመመለስ ወሰኑ፡፡ ፈጠን ባለ እርምጃ ከህንጻው መውጫ በር ላይ ሲደርሱ ግን ለነርሱ የተላከው አሳሽ ጦር ህንጻውን ከቦ አገኙት፡፡ በዚህን ጊዜም ወደ ህንጻው ለመመለስ ሩጫ ጀመሩ፡፡ ሆኖም በቅርብ ርቀት ላይ የነበሩት አሳሾች ተኮሱባቸው፡፡ በሪሁን ማሪዬ ወዲያውኑ ተገደለ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይ ደግሞ ግንባሩ ላይ ቆሰለ፡፡ እርሱ ግን አልቆመም፡፡ የህንጻውን ፎቆች በትጋት ወጣ፡፡ ከስድስተኛው ፎቅ ላይ ሲደርስ አንድ ክፍት ቢሮ አየ፡፡ ከቢሮው በመግባት በመስኮቱ በኩል ወደ ውጪ ተወረወረ፡፡ ከሰከንዶች በኋላም መሬት ላይ ተፈጠፈጠ፡፡ የኢህአፓው መሪ እንዲህ ባለ አሳዛኝ ትራጄዲ ከምድር ላይ ተሰናበተ፡፡
*****
ስለዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ በኢህአፓ ወገን በይፋ የተጻፈው ታሪክ ይህ ነው፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አንዳንድ ጸሐፊዎች አሟሟቱን በሚመለከት አወዛጋቢ ታሪኮችን ማስነበብ ጀምረዋል፡፡ ውዝግቡ ለጊዜው አይጠቅመንም፡፡ የታሪክ ጸሐፊዎች ሐቁን እስከሚያወጡት ድረስ አወዛጋቢውን ታሪክ ብንዘለው ይሻላል፡፡ በጣም የምንስማማበት ጉዳይ ቢኖር ሀይሌ ፊዳ የመኢሶን ግርማ እና ኩራት እንደነበረው ሁሉ ተስፋዬ ደበሳይም የኢህአፓ አውራ የነበረ መሆኑን ነው፡፡ መኢሶንን ያለ ሀይሌ ፊዳ፣ ኢህአፓንም ያለ ተስፋዬ ደበሳይ ማሰብ አይቻልም፡፡ ሁለቱም የአንድ ትውልድ ፈርጦች ነበሩ፡፡ ሁለቱም በተሳሳተ ስሌት እርስ በርስ ተዋጉ፡፡ ሁለቱም በጨካኙ ስርዓት ተበሉ፡፡
የዶ/ር ተስፋዬ ታሪክን የማሳርገው በሚከተለው ታዋቂ የኢህአፓ መዝሙር ነው፡፡
“ቢወቀጥ አጥንቴ ቢንቆረቆር ደሜ
ለአዲስ ሥርዓት ልምላሜ
ፍጹም ነው እምነቴ
ትግሉ ነው ሕይወቴ”
*****
አፈንዲ ሙተቂ
መጋቢት 14/2006
(የትረካ ምንጮች)
1. ባቢሌ ቶላ፣ የትውልድ እልቂት፣ 1985፣ አዲስ አበባ
2. ክፍሉ ታደሰ፣ “ያ ትውልድ” ቅጽ 1፣ 1987፣ አዲስ አበባ
3. ክፍሉ ታደሰ፣ “ያ ትውልድ” ቅጽ 2፣ 1990፣ አዲስ አበባ
4. የያ ትውልድ ተቋም፣ “ዝክረ ተስፋዬ ደበሳይ”፣ መጋቢት 2005፣ ከኢንተርኔት የተገኘ
5. ገነት አየለ አንበሴ፣ የሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ትዝታዎች፣ 1994፣ አዲስ አበባ
(አፈንዲ ሙተቂ)
The writer, Afendi Muteki, is a researcher of the Ethnography and History of the peoples of East Ethiopia. He is an author of “Harar Gey”, an Ethnography book about the historical city of Harar. You can read some of his articles on his blog and his facebook page.
ጊዜ ይፈጅ ይኾናል እንጂ ለውጡ አይቀሬ ነው
(አዲስ ጉዳይ፤ ቅጽ ፰ ቁጥር ፳፻፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) ሃይማኖት ከአስተዳደሩ የተለየ በጣም ጥልቅ ነገር ነው፡፡ ሃይማኖት ማለት ከአንድ ግለሰብ ኾነ ከጥቂት ሰዎች አመራር የተለየና የራሱ የኾነ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት፣ ባህልና ሥርዓት ያለው መኾኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በሥነ ምግባር ደረጃ እኔን ጨምሮ ኹሉም ሰው ችግር ሊኖርብን ይችላል፡፡ ይኹንና ይኼ የሥነ ምግባር ጉዳይ ሊፈታ የሚችለው በመነጋገርና …![]()
እነ ዳንኤል ተፈራ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ተለቀቁ!! ወላይታ ሶዶ ነፃነት አልባዋ የማፊያ ካድሬዎች ከተማ!!
ከወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የእስርና እንግልት ማብራሪያ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ በደቡብ ቀጠና በወላይታ ዞንና በሲዳማ ዞን አዋሳ ከተማ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የፓርቲውን የትግል ስትራቴጅክ ዕቅዶች ላይ ማብራሪያ፣ ደንብና ፕሮግራም ለመስጠት እንዲሁም የስራ ጉብኝት ለማድረግ በ 12/07/06 ወደ ወላይታ ዞን ሶዶ […]
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነጻነት ጋዜጣ በግማሽ ሚሊዮን ብር የራሱን ማተሚያ ማሽን በመግዛት እና በመትከል በቅርብ ቀን ሕትመቱ ለሕዝብ በገበያ ላይ እንድሚውል ተገልጸ፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነጻነት ጋዜጣ በግማሽ ሚሊዮን ብር የራሱን ማተሚያ ማሽን በመግዛት እና በመትከል በቅርብ ቀን ሕትመቱ ለሕዝብ በገበያ ላይ እንድሚውል ተገልጸ፡፡ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሐላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተፈራ እንደገለጹት፤ የአንድነት ፓርቲ እና የፍኖተ ነጻነት የኢዲቶሪያል ቦርድ ባለፈው አመት ያሳትማት የነበረችው ጋዜጣ በ2005 ዓ. ም. በጉልበት እንድትዘጋ በመደረጉ እና የመንግስት […]

