ግርማ-ሞገሳሙ ሽማግሌ ከልብ የመነጨ ፈገግታ ለገሰኝ።ክንዱን እያያሻሸሁ ሳዋራዉ— አንዳድ ባልደረቦቹን ጠየቀኝ።ከሚጠይቀኝ ሰዎች አንዳዶቹን ከጥቂት ጊዜ በፊት አግኝቷቸዉ ነበር–» እና አከሉ ፀሐፊዋ—«ካርል የማስታወስ ችሎታዉ እየከዳዉ መሆኑን የተገነዘበ መሰለኝ።»

ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በዮጋንዳ መዲና ካምፓላ በተካሄደው 9ኛ «የኤሌክትሮኒክስ ወይም የኢ-ለርኒንግ ትምህርት በአፍሪቃ» ጉባኤ ላይ ከ68 ሀገራት የተውጣጡ 1400 የሚጠጉ ሰዎች ተገኝተዋል።

በአማካይ በያመቱ ከአምሥት ከመቶ ኤኮኖሚያዊ ዕድገት በላይ በማስመዝገብ ላይ የምትገኘዋ አፍሪቃ በዓለም የተከሰተው የፊናንስ ቀውስ ያስከተለውን መዘዝ ከሌሎች አውሮጳውያት ሀገራት በተሻለ ሁኔታ መቋቋም ችላለች። ለዚህም እርግጥ፣

እአአ ግንቦት 24፣ 2014 ዓም ቅዳሜ ከቀትር በኋላ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ብራስልስ፣ ቤልጅየም በሚገኝ አንድ የአይሁዳውያን ቤተ መዘክር ውስጥ ተኩስ ከፍቶ ሦስት ሰዎች የገደለው ተጠርጣሪ ባለፈው ዓርብ በቁጥጥር ስር መዋሉ

የገዳ ሥርዓት አራማጅ ድርጅት የተባለ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ትናንት በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባዔ አካሄደ። የአዲሱ ፓርቲ አባላት ከአመራሩ ጋ በበርካታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዩኤስ አሜሪካ የተካሄደው የዳይመንድስ ሊግ የአትሌቲክስ ጨዋታ፣ ከ50 የሚበልጡ ሀገራት የተሳተፉበት እና 21 የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የታየበት በቦትስዋና የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪቃ ወጣቶች ውድድር ፣

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት፤ በቅርቡ ያወጣው የመጠርዝር ጥናት ውጤት እንደሚያስረዳው፤ በህክምና ርዳታ የሰዎች ዕድሜ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመራዘም ላይ ነው። ባለፉት 2 ዐሠርተ ዓመታት በዓለም ዙሪያ በአማካይ የ 9 ዓመት ጭማሪ አሳይቷል።

የኢጣሊያ ባህር ኃይል ዳግም በሺ የሚቆጠሩ የጀልባ ላይ ስደተኞችን ማዳኑን አስታወቀ። እንደ ባህር ኃይሉ ከሆነ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከ3000 በላይ ስደተኞችን ከኢጣሊያ የባህር ጠረፍ ተቀብሏል። ከሰሜን አፍሪቃ በኩል እንደመጡ የተነገረዉ አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ ሲሲሊያ መወሰዳቸውም ተነግሯል።

ጽዮን ግርማ
ሦስተኛዋን ”እሁድ” - በአራዳ ምድብ ችሎት

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ተጠርጣሪዎቹን እሁድ ለሚሰየም ተረኛ ችሎት መቅጠሩን የተለመደ አድርጎታል። ከቀናት በፊት በሦስቱ ብሎገሮች ላይ በተሰጠው የዐሥራ አራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የቀጠሮው ቀን ዛሬ ነበር። ዛሬ በዚህ ፍርድ ቤት ተገኝቼ የነበረውን ሁኔታ መከታተል ባልችልም ምንጮቼ የነገሩኝን ዝርዝር እንዲህ ጽፌዋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በውህደት ጉዳይ ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ጋር ሲደረግ የነበረው ውይይት በመጠናቀቁና ሁለቱ ፓርቲዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ምክንያት የቅድመ ውህደት ፊርማ ስነ-ስርዓት ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መላኩን የመኢአድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነው ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ […]

የ ምርጫ ዘጠና ሰባት ሕልፈት ሕይወት የ አዲስ አበባን ወጣቶች ከምርጫ ወደ በርጫ በብርሃን ፍጥነት ሲመራቸው ቅንጅትም ከመንፈስነት ወደ ፈስነት የሄደበት መንገድ እንዲሁ ተመሳስይ ነብር። ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ነብር ሆነው የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች ከነብርነት ወደ ነበርንነት ፣ ቁልቁል ተንደርድረው ከዝግባነት ወደ ዘጋቢነት የተሸጋገሩበትን እጻዊ ( ምጸታዊ ጡዘት ) መንፈስ እና መንፈሰ ግስጋሴ ሳስበው ይገርመኛል። […]

የማለዳ ወግ … ካርል ሓይሰን ለሰብዕና የተጉ ብጹዕ ነበሩ ! ነፍሳቸውን ይማር ሰብዕናን መሰረት አድርገው በመላ አለም በበጎ የረድኤት እና ምግባረ ሰናይ ድርጅቶችን የመሰረቱ ብጹአን እንብዛም ባልበረከቱባት ምድር አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ በሰብአዊ ስራቸው መንፈሳዊ ቅናት ሰሜታችን የሚያጎኑ አልጠፉም። …ግን አይበረክቱም ከቀረው አለም ምልከታ ትናንትም ሆነ ዛሬ በእኛ ሃገር ለእኛ ስለሆነውና የሚሆነውን አድርገው ስላለፉት የእኔ […]

የለውጥ አስፈላጊነት ላይና ወያኔ መራሹ መንግስት ይበቃው ዘንድ ባብዛኛው ዜጋ ከተቻለ የሚለው እንዳለ ብዥታ የለም። ይህ ፍላጎት የብዙ ስረአቱ ውስጥ ያሉ ዜጎችም ጭምር መሆኑን የተለያዩ መረጃዎችን ጨምቆ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። በርግጥ የለውጡ አስፈላጊነት ላይ የሚስማሙና አይቀሬነቱን የሚያውቁ ነገር ግን ለውጡ የተረጋጋና ችግሮች ያልበዙበት እንዲሆን ይረዳል ብለው አገዛዙ ድርሻ በሚያደርግበት እንዲከወን የሚመኙ አሉ። ፈራ ተባ እያሉ […]

ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል። ይህንን ታላቅ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ኢሊባቡር ውስጥ ጉመሮ ሻይ ተክል መጥቶ በነበረበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት የተነገረን የፊልም ተዋንያን መሆኑን ብቻ […]

·         ጳጳሳት የፓትርያርኩን የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ቅድመ ኹኔታ አልተቀበሉትም::

·         ‹‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭና በሒደትም የሚያስቆም ነው›› /ታዛቢዎች/

(አዲስ አድማስ ጋዜጣ):- የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅን እንደ አንድ አጀንዳ የያዘው የዘንድሮው የሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ጉባኤ ከረቂቁ ጋር በተያያዘ በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ የፍጥጫው መንሥኤ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተሠየመው የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ አጥኚ ኮሚቴ ያዘጋጀው የማሻሻያ ረቂቅ በዝርዝር ከመታየቱ አስቀድሞ ፓትርያርኩ ለውይይቱ እንደ ቅድመ ኹኔታ ያቀረቧቸው ነጥቦች በአብዛኛው የጉባኤው አባላት የገጠመው ተቃውሞ እንደኾነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የቅ/ሲኖዶሱን ስብሰባ በርእሰ ጉባኤነት የሚመሩት ፓትርያርኩ፤ በአጀንዳው ላይ የሚካሔደውን ውይይት ቀጣይነት ይወስናል በሚል ካቀረቧቸው ቅድመ ኹኔታዎች ውስጥ÷ ለአጥኚ ኮሚቴው መመሪያ የሰጡባቸው ‹‹ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች›› አንድም ሳይቀነሱ በደንቡ እንዲካተቱና ረቂቁ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከጸደቀ በኋላ እንዲታይ የሚሉ እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡
ፓትርያርኩ በቅድመ ኹኔታ አስቀምጠዋቸዋል በተባሉት ነጥቦች ስምምነት ላይ ከተደረሰ ስብሰባው ሊቀጥል እንደሚችል በመጥቀስ፣ ኃይለ ቃልም ተማኅፅኖም በተቀላቀለበት አኳኋን መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡
ይኹንና የሚበዙት ሊቃነ ጳጳሳት በቀጥታ እንደተቃወሟቸው፣ የተቀሩትም ድጋፍ ከመስጠት እንደተቆጠቡ ታውቋል፡፡ ፍጥጫው ቀጥሎ አቡነ ማትያስ ‹‹አቋሜ ይኽው ነው፤›› በሚል አጀንዳውን መዝጋታቸውን ሲያስታውቁም፣ ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ እንዲህ ተብሎ የሚተው አይደለም፤›› በሚል ከኹሉም ሊቃነ ጳጳሳት ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ምንጮች ይገልፃሉ፡፡
የቅ/ሲኖዶሱ መደበኛ ስብሰባ የሚካሔደው ምልዓተ ጉባኤው ከጅምሩ ተስማምቶ ባጸደቃቸው የመነጋገርያ አጀንዳዎች መሠረት እንደኾነ በሊቃነ ጳጳሳቱ ተቃውሞ ተጠቅሷል፡፡
የማኅበሩ የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ እንዲቀርብ ከታዘዘበት ከጥቅምት2005 ዓ.ም. ጀምሮ እየተንከባለለ ለኹለት ዓመታት መዘግየቱን ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ የተጓተተው አጀንዳ ‹‹የማኅበሩን አገልግሎት ያቀጭጫሉ፣ በሒደትም ያስቆማሉ›› በሚል በተተቹት የፓትርያርኩ ቅድመ ኹኔታዎች ሊዘጋ እንደማይችልና ተጨማሪ ጊዜ ሳይወስድ ቅ/ሲኖዶሱ ሊወያይበት እንደሚገባ በአጽንዖት በመናገራቸው፣ ጉዳዩ ሳይቋጭ ለቀጣዩ ቀን በይደር ተላልፏል፡፡
አጀንዳው ሰኞ፣ ግንቦት 18 ቀን2006 ዓ.ም. ጥዋት መታየት ሲጀምር፣ አጥኚ ኮሚቴው በ37 አንቀጾችና በ34 ገጾች አሻሽሎ ያዘጋጀው የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብና የኮሚቴው ቃለ ጉባኤ በንባብ መሰማቱም ታውቋል፡፡ ፓትርያርኩ ‹‹ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች›› በሚል ራሱን በቻለ ርእስ በደንቡ እንዲካተት ለአጥኚ ኮሚቴው ጥብቅ መመሪያ የሰጡበት ባለ24 አንቀጽ ሰነድም አብሮ እንዲነበብላቸው መጠየቃቸው የመጀመሪያው ቀን የፍጥጫ መነሻ እንደነበር ታውቋል፡፡
በ24 አንቀጾችና በአምስት ገጾች የተዘረዘሩት የፓትርያርኩ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች÷ በአባላቱ በጎ ፈቃድ ተቋቁሞ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኘውን ማኅበር፤ ከሕገ ተፈጥሮው ውጭ የሚያደርግ፣ በቅ/ሲኖዶሱ ፈቃድ ከሚመራበት ደንብ በተፃራሪ ተቋማዊ ህልውናውን፣ የአመራር ምርጫውን፣ የአባላት አያያዙንና የሥራ ቦታውን ለውጭ ተጽዕኖ አሳልፎ የሚሰጥና አጣብቂኝ ውስጥ የሚያስገባ፣ በአርኣያነት የሚጠቀሰውን የፋይናንስ አሠራሩን ወደ ኋላ የሚጎትት መኾኑን እንደተረዱ ያብራሩ አንድ የቅ/ሲኖዶሱ አባል፣ ‹‹ቀጣዩ ቀንም የከበደ ነገር ይዞ እንደሚመጣ ግልጽ ነበር፤›› ይላሉ፡፡
በይደር የተያዘው አጀንዳ በቀጣዩ ቀን ማክሰኞ ጥዋት ተጀምሮ ለግማሽ ቀን የቀጠለ ቢኾንም ፓትርያርኩና ሊቃነ ጳጳሳቱ የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያውን በዝርዝር ለመመልከት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዳልቻሉ ታውቋል፡፡
‹‹ፓትርያርኩ በቅድመ ኹኔታ ያስቀመጧቸውን ነጥቦችና በአጀንዳው ቀጣይነት ላይ የያዙትን አቋም አልቀየሩም፤ ሊቃነ ጳጳሳቱም ባጸደቅነው አጀንዳ መሠረት ቅድሚያ ሰጥተን መነጋገር ያለብን የሠየምነው አጥኚ ኮሚቴ አዘጋጅቶ ባቀረበው ረቂቅ ላይ ነው፤ መካተት ያለበት ነገር ካለም ማኅበሩን በሚያሠራ መልኩ እያገናዘብን በሒደት እናየዋለን እንጂ አጀንዳው በቅድመ ኹኔታ መታሰር የለበትም በሚል ለማስረዳት ጣሩ፤ በመጨረሻም ፓትርያርኩ “እንግዲያውስ ስብሰባውን ለመምራት አልችልም” በማለታቸው የስብሰባው መቋጫ ኾኗል፤›› ይላሉ– ሒደቱን ለአዲስ አድማስ የገለጹ የስብሰባው ምንጮች፡፡
የማኅበሩ ደንብ በመጀመሪያ ረድፍ ከሰፈሩት የቅ/ሲኖዶሱ መነጋገርያ ነጥቦች አንዱ እንደነበር ያስተዋሉ ሌሎች የስብሰባው ተከታታዮች በበኩላቸው፤ አጀንዳው ከቅደም ተከተሉ ወጥቶ እየተገፋ በመጨረሻ መነሣቱ በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል ይህ ዓይነቱ አለመግባባት ሊነሣ እንደሚችል ጠቋሚ ነበር ብለዋል፡፡ 
ተከታታዮቹ አክለውም፣ ፓትርያርኩ ስብሰባውን ለመምራት ፈቃደኛ ባይኾኑም በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በተደነገገው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት መሠረት፣ ምልዓተ ጉባኤው በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያዎች ላይ የጀመረውን ውይይት ቀጥሎ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚችልባቸው አግባቦች እንደነበሩ ገልጸው፣ ቅ/ሲኖዶሱ በግለጫው የመጨረሻው አጀንዳው ባደረገው የማኅበሩ ደንብ ላይ “ውይይት ተደርጎበታል” ከማለት በስተቀር ስብሰባውን የቋጨበት አኳኋን ያልተለመደና አደናጋሪ ነው ብለዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን የዘመኑን ኦርቶዶክሳዊ ትውልድ አደራጅቶ ማንነቱን የሚያውቅበትንና በግብረ ገብ የሚታነፅበትን ትምህርተ ሃይማኖት ከማስተማር ባሻገር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማት አገልግሎታቸውን በብቃት የሚወጡበትን ኹለገብ ሞያዊ ድጋፍ የመስጠት ሓላፊነት እንዳለበት በደንብ አጥኚ ኮሚቴው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ መስፈሩ ታውቋል፡፡
ይኹንና ‹‹ጥበቃና ጥንቃቄ›› በሚል ፓትርያርኩ እንደ መመሪያ ያቀረቧቸው ድንጋጌዎችና ግዴታዎች እንዲሁም ከልዩ ጽ/ቤታቸው ማኅበሩን አስመልክቶ በየጊዜው የሚወጡ መመሪያዎች የማኅበሩን አገልግሎት የማቀጨጭ፣ በሒደትም አዳክሞ የማስቆም ውጤት ሊኖራቸው እንደሚችል ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡
የማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ፣ ቅ/ሲኖዶሱ የማኅበሩ ደንብ እንዲሻሻል ግንቦት 14 ቀን2004 ዓ.ም. ባካሔደው ስብሰባ÷ ማኅበሩ ከጊዜው ጋር የሚሔድ፣ አገልግሎቱና አደረጃጀቱ የደረሰበትን ስፋትና ዕድገት የሚመጥን፣ ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ልማት የሚጠቅም ድርጅታዊ መዋቅር እንደሚያስፈልገው ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት አምስት ሊቃነ ጳጳሳት፣ ገለልተኛ የሕግ ባለሞያዎችና የማኅበሩ አባላት በታከሉበት አጥኚ ኮሚቴ የጋራ ጥናት የተዘጋጀ መኾኑ ተመልክቷል፡፡
በግንቦት ወር1984 ዓ.ም. በበጎ ፈቃድ በተሰበሰቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተመሠረተው ማኅበሩ፤ እየተመራ ያለው ቅ/ሲኖዶስ በ1994 ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ አሻሽሎ በሰጠው መተዳደርያ ደንብ ሲኾን አሁን የተሻሻለው ረቂቅ ተመርምሮ ባለመጽደቁ በነባሩ ደንብ እየተመራ ለመቀጠል እንደሚገደድ ተመልክቷል፡፡
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት በሳምንቱ መጀመሪያ እንዳስታወቀው፣ በዚህ በተያዘው የግንቦት ወር ብቻ ከ66,000 የሚበልጡ ደቡብ ሱዳናውያን ከመንደሮቻቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ከነዚህ መካከል 22,000 ወደ ጎረቤት ኢትዮጵያ ተሰደዋል።

ጳጳሳት የፓትርያርኩን የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ቅድመ ኹኔታ አልተቀበሉትም ‹‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭ በሒደትም የሚያስቆም ነው፡፡›› /ታዛቢዎች/ ማኅበሩ የመተዳደርያ ደንቡ ማሻሻያ ረቂቅ እስኪጸድቅ በነባሩ ለመመራት ይገደዳል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፶፤ ቅዳሜ ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅን እንደ አንድ አጀንዳ የያዘው የዘንድሮው …

በልጅግዓሊ – ፍራንክፈርት

ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች ተከሣሾች ያቀረቧቸውን የክሥ መቃወሚያዎች በአብዛኛው ውድቅ አድርጓል፡፡

በፍርድ ቤቱ ባዘዘው መሠረት አቃቢ ሕግ የሚያሻሽላቸውን ክሦች የሚያቀርብበትን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ለዝርዝሩ የፍርድ ቤቱን ውሎ የተከታተለውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በወጣትና በጎልማሳነታቸዉ ዘመን በተጫዎቷቸዉ ፊልሞች ኦስትሪያና ጀርመን ዉስጥ ከፍተኛ አድናቆትና ያተረፉት በኧም ኢትዮጵያ ዉስጥ ችግረኞችን የሚረዳዉን ሜንሽን ፉር ሜንሽን የተሠኘዉን ግብረ-ሠናይ ድርጅት የመሠረቱና ለረጅም ጊዜ የመሩ በጎ አድራጊም ነበሩ

የናጄሪያዉ ቦኮ ሐራም፤ የማሊ ነዉጠኞች፤ በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሱ የባሕር ወንበዴዎችንም ሆነ ሌሎች «ሠላም አዋኪ» ያሏቸዉ ሐይላትን ጥቃት ለመቋቋም የማሕበረሰቡ አባላት ብቻቸዉን አይችሉትም

በፈረንሣይዋ ጥንታዊት ከተማ ካን ውስጥ ዘንድሮ በተከናወነው ዓመታዊ የካን ፊልም ፌስቲቫል ለመታደም በፊልም ሙያ የተሰማሩ አምስት ኢትዮጵያውያን ወደ ስፍራው አቅንተው ነበር፤ አራት ሴቶች እና አንድ ወንድ።

በወጣትና በጎልማሳነታቸዉ ዘመን በተጫዎቷቸዉ ፊልሞች ኦስትሪያና ጀርመን ዉስጥ ከፍተኛ አድናቆትና ያተረፉት በኧም ኢትዮጵያ ዉስጥ ችግረኞችን የሚረዳዉን ሜንሽን ፉር ሜንሽን የተሠኘዉን ግብረ-ሠናይ ድርጅት የመሠረቱና ለረጅም ጊዜ የመሩ በጎ አድራጊም ነበሩ

አስ መሐመድ ከግመልና ፍየል ጠባቂነት እራሳቸዉን ለዉጠዉ ዶቢ በተባለ በረሐማ አካባቢ ጨዉ በማልማት ከፍተኛ ሐብት ለማፍራት የበቁ፤ ለበርካታ ኢትዮጵያዉያን የሥራ ዕድል የፈጠሩና ችግረኞችን የሚረዱ ባለሐብት ናቸዉ

የ2006 ዓም ‹‹የዓመቱ በጎ ሰው›› ሽልማት በሰባት ዘርፎች የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ታውቀዋል፡፡ በልዩ ልዩ ዘርፎች ዕውቀትና ተሞክሮ ያላቸው፣ በሞያው ለረዥም ዘመን ያገለገሉ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ደራስያን፣ የዜማ ሰዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ የባሕል ባለሞያዎች፣ የሚገኙበት 21 ዳኞች የመጨረሻዎቹን ሰባት ተሸላሚዎች ለመለየት ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡ ዳኞቹ እርስ በርሳቸው የማይተዋወቁ ሲሆን በዘርፋቸው የራሳቸውን ድምፅ ብቻ ይሰጣሉ፡፡ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች የሚታወቁት በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ነው፡፡
የሽልማቱ ዲዛይን የታዋቂው ሰዓሊ የእሸቱ ጥሩነህ ነው፡፡ ‹‹ጀ›› ፊደል ኢትዮጵያዊ ፊደል በመሆኑ ኢትዮጵያዊነትን የሚወክል ሲሆን ‹በ› ና ‹ሰ› የሚሉ ፊደላት ተቀጣጥለውበታል፡፡ ይህም የበጎ ሰው ሽልማትን የሚገልጥ ነው፡፡ ከላይ ደግሞ የ‹ሽ› ምልክት አለው፡፡ ይህም ሽልማትነቱን ያሳያል፡፡ ከላይ ያለው የፊደሉ ቅጥያ የቁልፍ መክፈቻ ምልክት ያለው ይኼም የተሸላሚዎቹን ቁልፍ ማኅበረሰባዊ ሚና ያመለክታል፡፡ ከፊደሉ ሥር የሚገኘው ደረጃ ደግሞ ተሸላሚዎቹ ደረጃ በደረጃ የደረሱበትን የሰብእና  ልዕልና ያሳያል፡፡

ዕጩዎች በየዘርፉ

ኪነጥበብ ዘርፍ

  1. ሙላቱ አስታጥቄ

  2. ተስፋየ አበበ

  3. አባባ ተስፋየ ሳሕሉ

  4. ይልማ ሀብተየስ

  5. ታደሰ መስፍን

 ማኅበራዊ አገልግሎት
 1.         ዶ/ር አበበ በጂጋ
2.       ዶ/ር ሚናስ ኅሩይ

3.       ቄስ አሰፋ ሰጠኝ(ትግራይ)

4.       ብጹዕ አቡነ ዮናስ(አፋር)

5.       ደበበ ኃይለ ገብርኤል

ርዳታና ሰብአዊ ሥራ

  1. ዶ/ር ተዋበች ቢሻው

  2. ዶ/ር በላይ አበጋዝ

  3. ወ/ት ሮማን መስፍን

  4. ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ

  5. ወ/ሮ አበበች ጎበና

ግብርና፣ ኢንዱስትሪና ኢንተርፕርነርሺፕ

  1. ቤተልሔም ጥላሁን

  2. ዶ/ር ኢንጅነር ዳንኤል ቅጣው

  3. ዶ/ር ወሮታው በዛብህ

  4. አሶሴሽን ኦፍ ዉሜን ኢን ቢዝነስ

  5. ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው

መንግሥታዊ ኃላፊነትን መወጣት

1.         አምባሳደር ቆንጅት ሥነ ጊዮርጊስ

2.       ኢንጅነር ስመኘው በቀለ

3.       አቶ በድሉ አሰፋ

4.       አቶ ይርጋ ታደሰ

5.       አቶ አድማሱ ታደሰ

ቅርስ፣ ባሕልና ቱሪዝም

  1. አቶ ዓለሙ አጋ

  2. አቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ

  3. ሼህ አብዱላሂ ሸሪፍ

  4. ዶ/ር ዘረ ሠናይ ዓለም ሰገድ

  5. የኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ማኅበር

ጥናትና ምርምር

1.         አምባሳደር ዘውዴ ረታ

2.       ፕ/ር አሥራት ኃይሉ

3.       ፕ/ር ዓለም ፀሐይ መኮነን

                                            መርሐ ግብሩን ዳሽን ቢራ በዋናነት ስፖንሰር አድርጎታል

ኢሊሊ ሆቴል አዳራሹን በመስጠትና ለሌሎችም ተግባራት በመተባበር፣ ሸገር ሬዲዮና ኢቢኤስ ቴሌቭዥን የሚዲያ አጋር በመሆን፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች ማስታወቂያዎችንና መረጃዎችን በነጻ በማውጣት እየተባበሩ ይገኛሉ፡፡

ከኢያሱ ዓለማየሁ

ነገርን ነገር ያመጣዋል እንዲሉ በቅርቡ አንዲት የተበሳጨች ኢትዮጵያዊ- የኢሕአፓ ታሪክ እያሉ መጽሃፍ ጻፍን በሚሉ ዋሾዎች በመናደድ–በስም ጠቅሳኝ የድርጅቱን ታሪክ ባለመጻፌ ወቅሳኝና ውቀሱት ስትል መልዕክትና ምሬት ፈረንጆቹ ፌስ ቡክ በሚሉት አማካይነት አሰምታለች። ወጣት ናት በሚል ግምት አንቺ ብያለሁና ከተሳሳትኩ ይቅርታ። ብስጭቷ ቢገባኝም ታሪክ መጻፍን በተመለከተ የተንደረደረችበት ግምትና ሌሎችም የሚያሰሙት ትችት በመሰረቱ የተሳሳተ ነው። ላብራራ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
——–
ቃር ቃር የሚለውን የሰሞኑ የጭንቀት ሰቀቀን በምንፈልገው መጠን  እንድንጫወት ባይፈቅድልንም በተገኘችው አጋጣሚ ሩሓችን “ኢስቲራሓ” እንድታደርግ ልንፈቅድላት ይገባል፡፡ በዛሬ ውሎአችን የሚያናፍሰን ደግሞ አንጋፋው ሱዳናዊ ድምጻዊ ሰይድ ኸሊፋ ነው፡፡ ጉዞ ወደ ቢላድ- አስ-ሱዳን! ጉዞ ወደ ኻርቱም! ጉዞ ወደ ኡምዱርማን! ጉዞ ወደ ከሰላ፣ ጉዞ ወደ ዋዲ ሀልፋ፣ ጉዞ ወደ ገዳሪፍ፣ ጉዞ አል-ኡቤይድ! ጉዞ ወደ ኮርዶፋን! ዳይ!!
———
ከየትኛው እንጀምር እንግዲህ! ሰውዬው በበርካቶቻችን አዕምሮ ውስጥ የገዘፈ ምስል ጥሎብን ያለፈ በመሆኑ “ከሀ እስከ ፐ” እያሉ ስለርሱ ማውራቱ ያስቸግራል፡፡ ለማንኛውም በካይሮ ከተፈጠረ አንድ ክስተት ብንጀምር ጥሩ ይመስለኛል፡፡
ዘመኑ ራቅ ብሏል፡፡ በ1940ዎቹ አጋማሽ ነው፡፡ እውቁ የካይሮ ዩኒቨርሲቲ ለዓለም አቀፍ ተማሪዎች በሰጠው የስኮላርሺፕ እድል በመጠቀም በርካታ ሱዳናዊያን በዩኒቨርሲቲው ይማሩ ነበር፡፡ ከነዚያ ወጣቶች መካከል አንዱ በሙዘቃ ትምህርት ቤት የተመደበ ጠይም ዘለግ ያለ ኮበሌ ነው፡፡ ያ ወጣት በቤተሰቡ ወደ ግብጽ የተላከው ህግ አጥንቶ ጥሩ ዳኛ እንዲሆን ነበር፡፡ እርሱ ግን በራሱ ፍላጎት ምርጫውን ወደ ሙዚቃ አዞረ፡፡ በመሆኑም በእውቁ የዐረብ ሙዚቃ አካዳሚ ሊማር ተመዘገበ፡፡ ወጣቱ ሱዳናዊ ሙዚቃን በሀገር ቤት ያንጎራጉር ነበር፡፡ በትምህርት ቆይታውም በሀርሞኒካ እየተጫወተ ጓደኞቹን ያዝናናል፡፡
   አንድ ቀን ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቹ ባዘጋጀው ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ላይ እንዲዘፍን የተጋበዘው ፈሪድ አል-አጥራሽ የተባለው የዘመኑ ታዋቂ ግብጻዊ ዘፋኝ በሰዓቱ ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ የውሃ ሽታ ሆኖ ይቀራል፡፡ አዳራሹን ከዳር እስከ ዳር ያጨናነቁት ተማሪዎች በትዕግስት ጠበቁ፡፡ ነገር ግን ፈሪድ አል-አጥራሽን የበላ ጅብ አልጮኽ አለ፡፡ በመጨረሻም በአዳራሹ የነበረው ታዳሚ በጩኸትና በፉጨት ንዴቱን መግለጽ ጀመረ፡፡ ታላቁን ዘፋኝ ሲጠባበቅ የነበረው መድረክም በንዴተኛ ተማሪዎች ረብሻ ትርምስምሱ ወጣ፡፡
  
   የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች የተማሪዎቹን ቁጣ ለማብረድ አልቻሉም፡፡ ይሁንና ከሱዳናዊው ወጣት ተማሪ ጋር ይቀራረብ የነበረው አንድ አስተማሪ ወጣቱን እየገፋ ወደ መድረኩ አስገባውና “ዝፈን” አለው፡፡ ወጣቱ ሙዚቃን ለራሱና ለጓደኞቹ መደሰቻ ያህል ነበር የሚጫወተው፡፡ ህዝብ በተሰበሰበት አዳራሽ ላይ ቆሙ መዝፈኑን ቢመኘውም በዚያ ዕድሜው በባዕድ ሀገርና በባዕድ ታዳሚ ፊት ምኞቴን አደርገዋለሁ የሚል ሀሳብ አልነበረውም፡፡ እስከዚያን ጊዜ ድረስ በህዝብ ፊት መዝፈንን አልተለማመደውም፡፡ ስለዚህ የአስተማሪው ግብዣ በፍርሃት ማጥ ውስጥ ወረወረው፡፡
ይሁንና ወጣቱ ግብዣውን “እምቢ” ብሎ ከመድረኩ ለመውረድ አልሞከረም፡፡ እንደዚያ ቢያደርግ በፈሪድ አል-አጥራሽ መቅረት የተቃጠሉት ተማሪዎች ቁጭታቸውን በርሱ ላይ የሚወጡ መሰለው፡፡ ከተማሪዎቹ ቁጣ ለመዳን ሲልም እንደ አቅሙ ዘፍኖ ከመድረኩ ለመውረድ ወሰነ፡፡ በመሆኑም በፍርሃት እየራደና እየተርበተበተ ማይክራፎኑን ጨበጠ፡፡ የአዳራሹ ጸጥታ “ረጭ” ሲልም በቀጭን ድምጽ “አል-ማምቦ ሱዳኒ” (የሱዳን ጭፈራ) እያለ ዘፋፈነ፡፡ በፈሪድ አል-አጥራሽ መጥፋት የበገኑት ተማሪዎች ድንገት በመድረኩ ላይ በተከሰተው ሱዳናዊ ወጣት የድምጽ ቅላጼ ተማረኩ፡፡ ወጣቱ ዘፈኑን ሲጨርስ በከፍተኛ የአድናቆት ጭብጨባ አዳራሹን ቀወጡት፡፡ ዘፈኑንም ደግሞ እንዲዘፍንላቸው ጠየቁት፡፡
ሱዳናዊው ወጣት የስድብ ናዳ እንጂ የአድናቆት ጭብጨባ አልጠበቀም ነበር፡፡ የተማሪዎቹ ምላሽ የአድናቆት ጭበጨባ ሲሆንበት ግን መንፈሱ መለስ አለለት፡፡ በፍርሃት መንቀጥቀጡንም አስወገደ፡፡ እናም ዘና በማለት “አል-ማምቦ ሱዳኒን” እየደጋገመ ዘፈነ፡፡ የአዳራሹ ታዳሚ ከፊት በበለጠ ጭበጭባና አድናቆት አሞገሰው፡፡
የሱዳናዊው ወጣት ገድል በዚያ መድረክ ብቻ አልተገደበም፡፡ ስለድምጹ ማማርና ስለ ቅላጼው የሰማው ሁሉ በድግስና በሙዚቃ ኮንሰርት እንዲዘፍንለት ይጋብዘው ጀመር፡፡ በዘመኑ በካይሮ የሚኖሩት ከመቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ሱዳናዊያንም ወጣቱን የሀገር አለኝታና መታወቂያ አድርገው ወሰዱት፡፡ በየአጋጣሚው በሚያዘጋጇቸው የሙዚቃ ድግሶችም ወጣቱን ቁጥር አንድ ምርጫ በማድረግ አስዘፈኑት፡፡
ያ ወጣት የሙዚቃ ትምህርቱን በሚገባ ካጠናቀቀ በኋላ በ1946 ገደማ ተመረቀ፡፡ በታሪክ ሙዚቃን በአካዳሚ ደረጃ ያጠና የመጀመሪያው ሱዳናዊ ሆኖ ተመዘገበ፡፡ ከምርቃቱ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡
———
ይህ ነው እንግዲህ የሰይድ ኸሊፋ የዘፈን ጥንስስ! በዚህ መንገድ ነው እንግዲህ ዝነኛው ሱዳናዊ የጥበብ ጉዞውን የጀመረው፡፡ ይሁን እንጂ ሰይድ ኸሊፋ በመነሻው ላይ በካይሮ የተቀዳጀውን ዝና በሀገሪቱ ለመድገም አልቻለም፡፡ እንዲያውም መጀመሪያ ላይ የሱዳን ህዝብ “ዘፈን ሳያውቅ እዘፍናለሁ ብሎ የተነሳ መደዴ” የሚል የጥላቻ ቅጽል ለጥፎለት ነበር፡፡ ይህም የተፈጠረበት ምክንያት ሰይድ ኸሊፋ ይዞት የመጣው አዲስ የአዘፋፈን ዘውግ እና የግብጽና የኑቢያ ሙዚቃዎች ውህድ የሆነው የዘፈኖቹ ቅኝት ለሱዳናዊያን ጆሮ እንግዳ በመሆኑ ነው፡፡ ሱዳናዊያን በወቅቱ የለመዱት የአንጋፋዎቹን የነ በሺር አባስንና የነ አሕመድ አል-ሙስጠፋን የአዘፋፈን ስልት ነው፡፡ በመሆኑም እንደ ካሊፕሶ እና ዲስኮ ሞቅ እያለ የሚጓዘው የሰይድ ኸሊፋ ዘውግ ለነርሱ አልጣማቸውም፡፡
  እያደር ግን ሁሉም ነገር መስተካከል ጀመረ፡፡ ሱዳናዊያን ከሰይድ ኸሊፋ ስልት ጋር ተላመዱ፡፡ ከጥቂት አመታት በኋላ “መደዴ ዘፋኝ” የተባለው ወጣት የሁሉም ሱዳናዊ አርቲስቶች ቁንጮ ሆኖ ተገኘ፡፡ በተለይም “ኢዘየኩም” የተሰኘው ነጠላ ዜማው በኦምዱርማን ሬድዮ ሲለቀቅ ሱዳናዊያን ከዳር እስከ ዳር በአንድ ልብ አደመጡት፡፡ ስለቤተሰብና ፍቅርና ክብር የሚዘምረውን ዘፈኑን የሱዳን ብሄራዊ ዘፈን እስኪመስል ድረስ ተቀባበሉት፡፡
በ1950ዎቹ አጋማሽ ላይ የሰይድ ኸሊፋ ዝና በአባይ ግርጌ ካሉት ግብጽና ሱዳን ተነስቶ የአባይ ምንጭ ወደሆነችው ወደ ኢትዮጵያ ተሻገረ፡፡ ኢትዮጵያዊያንም ዘፈኖቹን ከመስማት አልፈው በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በሶማሊኛ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ዘፈኑት፡፡ በዚህም መሰረት ምኒልክ ወስናቸው “ጃሩ አነ ጃሩ” የሚለውን ዘፈኑን “ትዝታ አያረጅም” በሚል ቀይሮት ተጫወተው፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ደግሞ “ወጠነል ጀማል” የሚለውን ተወዳጅ ዜማውን በአማርኛ ቋንቋ “እዩዋት ስትናፍቀኝ” በማለት ተጫወተው፡፡
—–
1961፡፡ የማይረሳ ዓመት፡፡ ኢትዮጵያዊያን በድምጹ ብቻ የሚያውቁትን ታዋቂ ዘፋኝ ያዩበት ዓመት፡፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ከሱዳን ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር ባደረገው የባህልና የኢኮኖሚ ግንኙነቶች ማዳበሪያ ስምምነት መሰረት አንጋፋና ወጣት ድምጻዊያን የተካተቱበት የሱዳን የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡ ዝግጅቱንም በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ቴአትር (በአሁኑ ብሄራዊ ቴአትር) ማቅረብ ጀመረ፡፡ አሕመድ አል-ሙስጠፋ፣ በከር ሙስጠፋ፣ ኢብራሂም አውድ፣ ሳላህ ቢን ባዲያ እና ሌሎችም በታዳሚው ፊት ዘፈኑ፡፡ ከቆይታ በኋላ ግን ብዙዎች ሊያዩት የሚጓጉለት ሰይድ ኸሊፋ ወደ መድረኩ ተጋበዘ፡፡ አዳራሹ በአድናቆት ጭብጨባ ተናወጠ፡፡
ታዲያ ሰይድም ከህዝቡ ለተቸረው አድናቆትና ክብር አጸፋውን በአስገራሚ መልኩ መለሰ፡፡ በሁለት ሌሊቶች ውስጥ ያጠናቸውን የአማርኛ ቃላት ከዐረብኛ ጋር በማሰናኘት “ኢዘየኩም”ን እንዲህ ተጫወተው፡፡
 ኢዘየኩም ኬፍ ኢነኩም (2)
አነ-ሌ ዘማን ማ ሹፍቱኩም፡፡ (2)
“ጤና ይስጥልኝ እንደምን ናችሁ (2)
ከሱዳን መጣን ልናያችሁ” (2)
አነ ሌ ዘማን ማሹፍቱኩም፡፡
 በአዳራሹ የታደመው ኢትዮጵያዊ ተመልካች በሰማው ነገር እየተገረመ ጭብጨባውን አጠናክሮ ቀጠለ፡፡ በዚያች ቀን ተመልካቹን ለማስገረም ብቻ የተላከ ይመስል የነበረው ሰይድ ኸሊፋም ሌላ ዜማ ማከል አስፈለገው፡፡ እና ለሱዳናዊያን እንግዳ የሆነውን “ትዝታን” በተሰባበረ አማርኛ ተጫወተው፡፡ ተመልካቹም በሳቅ ፍርስ እያለ አጨበጨበለት፡፡
——-
አዎን! ሰይድ ኸሊፋ በኢትዮጵያዊያን ልብ ከነገሱ የሱዳን የኪነ-ጥበብ ፈርጦች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ “ሱዳን” ሲባልም ከሁሉ በፊት ለኛ ትዝ የሚሉን “ኢዘየኩም” እና የሰይድ ኸሊፋ የተሰባበረ አማርኛ ናቸው፡፡ ይህ አንጋፋ የጥበብ ፈርጥ በእጅጉ ከሚታወቅበት የምስራቅ አፍሪቃ ክልል ባሻገር በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮጳ እና በአሜሪካ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ለመቀዳጀት በቅቷል፡፡ ለዚህ ይበልጥ የረዳው ደግሞ “ኢዘየኩም”ን በሄደበት ሀገር ቋንቋ ሁሉ ለመዝፈን የሚሞክር መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም እኛ “ጤና ይስጥልን፣ እንደምን ናችሁ” እያልን የምንዘምረው “ኢዘየኩም” በሀውሳ፣ በሰዋሂሊ፣ በእንግሊዝኛ፣ በጀርመንኛና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎችም አቻ ትርጉሞች አሉት፡፡ ይህም ሰይድ ኸሊፋ ሙዚቃን ከመጫወት አልፎ የሌሎችን ቋንቋና ባህል ለማጥናት የነበረውን ጉጉት በአጭሩ ያስረዳል፡፡
——
ሰይድ ኸሊፋ እንደ ብሄራዊ መዝሙር ከሚዘፍነው “ኢዘየኩም” ባሻገር በመቶ የሚቆጠሩ ሌሎች ዜማዎች አሉት፡፡ በሀገራችን አድማጮች ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑት ዜማዎቹ መካከል “ኢንቲ ያ ጀሚላ”፣ “ሐቢበተል በለዲያ”፣ “ወሽወሾ ሀምሳ”፣ “ጃሩ አነ ጃሩ”፣ ዚድኒ ሚን ደለክ ሺወይያ”፣ “አል-ዋሒድ ኸሊ ዓለል ዋሒድ”፣ “ተዓሊ ተዓሊ”፣ “ሳምባ”፣ “መሽጉል ባለኪ”፣ “ሲደ-ንናስ ሐደር”፣ “አህላ ገራም”፣ “ያ ዒቅደል ሉሊ” የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሰይድ ኸሊፋን በመላው ዓለም ተወዳጅ ያደረጉት ግን አራት  ዜማዎች ናቸው፡፡ እነርሱም  “ዘኑባ”፣ “ኢዘየኩም”፣ “አወድዳዕኩም” እና “አል-ማምቦ ሱዳኒ” የተሰኙት ናቸው፡፡
“ዘኑባ” የፍቅር ዜማ ነው፡፡ በዘፈኑ ውስጥ “ዘኑባ” የተባለላት ወጣት የኑቢያ ተወላጅ ናት፡፡ ሰይድ ለዚያች ወጣት “ሐረቀት ገልቢ መሐባታ” (ፍቅርሽ ልቤን አቃጠለው) እያለ ልመናውን ይደረድርላታል፡፡ “ዘኑባ ያ ቢንተል ኒል”ም ይላታል፡፡ “አንቺ ኒል (አባይ) ያበቀላት የኑቢያ ወጣት” ማለት ነው፡፡ ሰይድ ኸሊፋ ይህንን ዘፈን ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅት “ዘነበች” እያለ በአማርኛ አዚሞታል፡፡ እርሱ “ቢንት ኢትዮጵያ፣ ዘነበች” እያለ ሲዘፍን ዘነበች ታደሰ (ጭራ ቀረሽ) ደግሞ ከርሱ ጎን ቆማ ትደንስ ነበር፡፡ 
   “ኢዘየኩም” የሰላምታና የናፍቆት መጠየቂያ ነው-ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት፡፡ ታዲያ ሰይድ በዚህ ዘፈን የተጠቀመው “ኢዘየኩም” የተሰኘው ቃል ሰላምታን ከመግለጽ ባሻገር ትልቅ ታሪካዊ ፍካሬን ተሸክሟል፡፡ “ኢዘይ” (እንዴት) የሚለው ቃል መሰረቱ ዐረብኛ አይደለም፡፡ ይህ ቃል ከጥንታዊው የኑቢያ ቋንቋ ተወርሶ ከዐረብኛ ጋር የተደባለቀ ነው፡፡ በግብፅና በሰሜን ሱዳን ጠረፍ በሚነገረው የዐረብኛ ዘዬ ውስጥ ጉልህ ሆኖ ይሰማል፡፡ በኻርቱም አካባቢ በሚነገረው የዐረብኛ ዘዬ ውስጥ ግን የለም፡፡ የሰይድ ኸሊፋን ዜማዎች ያጠኑ ተመራማሪዎች እንደሚናገሩት ሰይድ ይህንን ቃል በዘፈኑ ውስጥ የተጠቀመው የናፍቆት ሰላምታን ከማስተላለፍ በተጨማሪ የጥንቷ ኑቢያ በታሪክ ውስጥ የነበራትን ሚና ለማስታወስ በሚል ነው፡፡
“አወድዳዕኩም” የተሰኘው ዘፈኑ ደግሞ የ“ኢዘየኩም” ተቃራኒ ነው፡፡ ሰይድ ኸሊፋ በዚህ ዘፈን “ልለያችሁ ነው፤ ልሰናበታችሁ ነው” ነው የሚለው፡፡ ብዙ ጊዜ ሙዚቃውን ለታዳሚዎቹ ሲያቀርብ ሁለቱን ዘፈኖች መክፈቻና መዝጊያ ያደርጋቸዋል (ማለትም በ“ኢዘየኩም” የተጀመረውን ዝግጅት በ“አወድዳዕኩም” ይዘጋዋል)፡፡ ሁለቱን ዘፈኖች የሚዘፍንበት ስሜትም እንደ ዘፈኖቹ ይለያያል፡፡ “ኢዘየኩም”ን በፍልቅልቅ ፈገግታና በደስታ ተሞልቶ ነው የሚጫወተው፡፡ “አወድዳዕኩም”ን ግን ጭንቅ ጥብብ እያለ ልብን በሚነካ ስልት ያስኬደዋል፡፡ አንዳንዴም አልቅሶ ታዳሚውን ያስለቅሳል፡፡ ታዲያ ሰውዬው ሰይድ ኸሊፋ ነውና ሁለቱም ያምሩለታል፡፡ በፈገግታ ሲፍለቅለቅም ሆነ ጉንጮቹን በእምባ ሲያርስ ታዳሚውን የመነቅነቅ ሀይሉ ከፍተኛ ነው፡፡
——–
ከሰይድ ኸሊፋ ታላላቅ ዘፈኖች መካከል ጉልህ ሆኖ የሚጠቀሰው “አል-ማምቦ ሱዳኒ” ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት “አል-ማምቦ ሱዳኒ” በመድረክ ላይ የተጫወተው የመጀመሪያ ዜማው ነው፡፡ ሰይድ ኸሊፋ “አል-ማምቦ ሱዳኒን”ን በወጣትነቱ ሲጫወተው “እኛም ሀገር እንዲህ ዐይነት ተአምር አለና ተመልከቱ” ለማለት ያህል ነው፡፡ ከጊዜ በኋላ የዘፈኑ ግጥም በሙዚቃ ኤክስፐርቶች ሲጠና ግን በርካታ ተአምራትን አጭቆ የያዘ እንደሆነ ተደረሰበት፡፡  እስቲ ሙሉ ግጥሙን ልጻፍላችሁ፡፡
—– 
(አዝማቹ)
አል-ማምቦ ሱዳኒ
አልማምቦ ፊኪያኒ
ፊዑዲ ፊከማኒ
ወአጅመል አልሓኒ
ማምቡ….!
—-
(1ኛ ተከታይ ግጥም)
ያ ሐቢበ መሕላኪ
አል-ማምቦ ፊጊናኪ
አል-ለሕኑ ኸልላኪ
ቲትማየሊ ፊኹጣኪ
ዐላ-አንጋሚል ማምቡ
—-
አልማምቦ ሱዳኒ
—
(2ኛ ተከታይ ግጥም)
ያ ሐቢበ የዑዲክ
ያ ወርደ ፊኹዱዲክ
አድኔቲ መርዩዲክ
ሚን ቡክረ መውዑዲክ
የርጉስ በሃኪ ጀንቡ
—–
ዐላ አንጋሚል ማምቦ
—–
(3ኛ ተከታይ ግጥም)
ረንነት ኹጣኪ አል-ሓን
ያ ወርደ ፊ ቡስታን
አነ ቀልቢ ባት ሐይራን
ማካን ያሬት ማካን
ማዱግና ናር ሑብቡ
——
የውም ረግሰተል ማምቦ
——
(4ኛ ተከታይ ግጥም)
በረደን-ነሲም ያሌል
ያሡረይያ ናዲ ሱሄል
ኩል ኺል መዓህ ኸሊል
አነ ወሕዲ ጀመል-ሽሼል
ዐሰረል-ሀዋ ገልቡ
——
የውም ረግሰተል ማምቦ
—–
“ማምቦ” የላቲን አሜሪካ የጭፈራ ዐይነት የሚጠራበት ስም ነው እንጂ ኦሪጅናሌ የሱዳን ቃል አይደለም፡፡ ሰይድ ኸሊፋም ግጥሙን ሲጀምር በፈረንጆቹ ዘይቤ “ማምቦ” ብሎታል፡፡ በማሳረጊያው ላይ ግን ቃሉን ወደ ዐረብኛ በመጎተት “ማምቡ” አድርጎታል፡፡ ይህንንም ያደረገው አዝማቹን ከተከታዮቹ ግጥሞች ጋር ለማስማማት እንዲያመቸው ነው፡፡
  ተከታዮቹ ግጥሞች ባለ አምስት መስመር ናቸው (ስድስተኛው መስመር ዘፈኑን ለማሳመር የሚደጋገም መነባንብ ነው እንጂ የግጥሞቹ አካል አይደለም፤ ለዚህም ነው ለብቻው የጻፍኩት)፡፡ ከአምስቱ መስመሮች መካከል አራቱ በተመሳሳይ ፊደል ነው የሚያሳርጉት፡፡ በአምስተኛ መስመር ላይ ያሉት ሁሉም ስንኞች ግን “ቡ” በተሰኘው ፊደል ነው የሚያበቁት፡፡ ይህም ከአዝማቹ ጋር በሚጣጣም መልክ መሆኑ ነው (አዝማቹም ባለአምስት መስመር መሆኑን ልብ በሉ)፡፡
እንዲህ ዓይነት ግጥም በዘመናዊው ዐረብኛ ውስጥ የለም፡፡ በጥንታዊው ዐረብኛ (Classical Arabic) ግን የግጥሙን ውበት መጠበቅ ግዴታ ነው፡፡ ገጣሚዎች ስለስንኙ መልዕክት ብቻ ሳይሆን የግጥሙን ውበት በሚያበለጽጉ ቴክኒካዊ ጉዳዮችም ላይ ይጨነቃሉ፡፡ የያንዳንዱ ስንኝ ቃላትና ፊደላት ብዛት፣ ስንኙ ቤት የሚመታበት ሁኔታ፣ ከተከታይ ስንኞች ጋር ያለው ትስስር

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በፈረንሳይ የወደብ ከተማ ፤ ካሌ፣ ከተለያዩ ሃገራት ፤ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጭምር የመጡ ስደተኞች ቀልሰዋቸው የነበሩትን መጠለያ የፕላስቲክ ድንኳኖች ፖሊስ ያፈራረሳቸው መሆኑ ተገለጠ ።

« የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥታዊ መንግሥት ለጀርመን መንግሥት ከፍተኛ እርዳታ አድርጎ ነበር። በዝያን ግዜ እንደሚባለዉ ለጀርመን ወደ 200 ሽ ዶላር ርዳታ ኢትዮጵያ ሰታለች» ይላሉ ዶክተር አስፋዉ ወሰን አስራተ፤

ከሰሞኑ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ያከበረው የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት፣ በአባልነት የሚመዘግባቸው ተሳላሚዎች ፣ በኢየሩሳሌም ቅዱሳት ቦታዎችን፣ የኢትዮጵያን አብያተ ክርስትያን እና ገዳማትን ጎብኝተው

የሩስያ፣ የካዛኽስታን እና የቤላሩስ መንግሥታት በመካከላቸው አንድ የኤኮኖሚ አንድነት ህብረት ለመመሥረት በዛሬው ዕለት ውል ተፈራረሙ። በካዛኽስታን መዲና አስታና የተፈረመው ይኸው ታሪካዊ የተባለው ውል ከስድስት

በብሪታንያ በምሕፃሩ «ዩ ኬ አይ ፒ» በመባል የሚታወቀው የተባበረችው ብሪታንያ ነፃ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት በሀገሩ በተካሄደው የቀበሌ እና የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ እንዲሁም፣ የአውሮጳ ምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ በሚያስገርም ሁኔታ