የኡጋንዳ ፖሊስ የነገው ስብሠባ መታገዱን ገለፀ!!!
ትናንት አመሻሽ ላይ የካባላጋላና የሴንተራል ፖሊስ ኮማንደሮች የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ በኡጋንዳ አመራር የሆኑትን አቶ ዘለቀ ጀበሮንና የማህበራዊ ጉዳዮች ተጠሪ የሆኑትን ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻውን በጽ/ቤታቸው ያነጋገሩት አዛዦች ኮሚኒቲው የጠራው ስብሠባ በበላይ አካላት ትዕዛዝ መታገዱን እንደተገለፀላቸው ለኮሚኒቲው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቆሙ።
ከኮሚኒቲው ቦርድ አባላት መካከል አቶ ዘለቀ ጀበሮንና ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻውን ብቻ ፖሊስ ጠርቶ ማነጋገሩ ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን ኮሚኒቲው አዳራሽ ተከራይቶና ለማህበረሠቡ በበራሪ ወረቀትና በፌስ ቡክ ጥሪ አስተላልፎ ሕዝባዊው ስብሠባ ሊካሄድ ዐርባ አምስት ሠዓታት ሲቀረው በማስታወቅያው መልዕክት የተደናገጠው የወያኔ የኡጋንዳ ቆንስላ ለኡጋንዳ መንግስት ደብዳቤ ፅፎ የዕሁዱን ስብሠባ እንዳሳገደ ደብዳቤውን በፖሊስ ኮማንደር ዕጅ እንደተመለከተ ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻው ጠቁሞ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሕዝባዊ ስብሰባውን የጠራው በሠላማዊ መንገድ ለመወያየትና በሳውዲ ያሉ ወገኖችን መከራና እንግልት ለመጋራትና ወገናዊነትን ለማሣየት እንጂ ሌላ ምንም አይነት ድብቅ አጀንዳ እንደሌለው ጠቁመው የወያኔ የኡጋንዳ ቆንስላ የሕዝብን ድምፅ ለማፈን መንቀቀሱ ትzብት ላይ እንደሚጥለው ጠቁመዋል።
በመጨረሻም የፖሊስ ኮማንደሮቹ ያስተላለፉትን መመርያ በመቀበል ኡጋንዳ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ስምምነት መሠረት የፖለቲካ ጥገኝነት አግኝተን የምንኖርባት ሐገር በመሆኗ የጠራነውን ስብሰባ በመመርያው መሠረት ማቆማችንን በማሣወቅ ከፖሊስ ጋር ያደረጉት ውይይት ተጠናቋል ሲሉ ጋዜጠኛ ደረጀ ጠቁመዋል።

Image

ኢህአዴግ በብሔርና በክልል ደረጃ ከተደራጁ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚንቀሳቀሱት ቅድሚያ በመስጠት ለመደራደር የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ በማመቻቸት ላይ መሆኑን የጎልጉል ምንጮች ገለጹ። ምንጮቹ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ለዚህ ተግባሩ ወዳጅ ጎረቤት አገሮችን፣ አንጋፋ የጎሳ መሪዎችንና ያፈገፈጉ የቀድሞ ተቃዋሚ መሪዎችን እየተጠቀመ ነው።

ህወሃት አሁን በአገሪቱ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ የሄደው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው የጠቆሙት የኢህአዴግ ሰው ድርጅቱ እርቅ ላይ ከመቼውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ስትራቴጂ መንደፉን አመልክተዋል።

“ከውጥረት ለመውጣት ወይም ውጥረትን ለመቀነስ” በሚል ኢህአዴግ ትኩረት ሰጥቶ የጀመረው አዲሱ የ”ሰላም” መንገድ ህብረ ብሔር ድርጅቶችን ያላከተተበትን ምክንያት አልተብራራም። ይሁን እንጂ ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር አቋሙ ሊቀየር የሚችል መሆኑን አልሸሸጉም።

ለድርድር የተመረጡትን ብሔርና ክልል “ተኮር” ድርጅቶች ይፋ ማድረግ ለጊዜው እንደሚቸግራቸው ምንጮቹ ተናግረዋል። በድፍኑ ግን በተለይ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ክልልና ምስራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የነጻ አውጪና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ድርጅቶች በማዕቀፉ ውስጥ እንዳሉ አመላክተዋል።

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ኢንቨስተሮች ፍሰት መቀነሱ፣ ገብተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ድርጅቶችም ከጸጥታና መሰል ችግሮች አገር ለቀው ወደመውጣቱ ላይ በመሆናቸው፣ አገሪቱ ውስጥ ያለው የስራ አጥነት ችግር እየተወሳሰበ መሄዱና ድህነት በቃላት ሊገለጽ ከሚችለው በላይ መስፋቱ ህወሃቶችን እንዳሳሰባቸው ያስታወቁት የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች “የኢህአዴግ አቻ ፓርቲዎችም ለህወሃት ያላቸው የአገልጋይነት መንፈስ እየተመናመነ መሄዱ ዋንኛው የህወሃት ጭንቀት ነው” ብለዋል። በዚህም የተነሳ እርቅ ከምንጊዜውም በላይ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ነው።

ህወሃት ባደራጃቸው የብሔርና የጎሳ ድርጅቶች ጥላ ስር ለይስሙላ ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ ከሚባሉ ክልሎችና ዞኖች “እውነተኛ ውክልና አለን” የሚሉ ብሄርን፣ ክልልንና ዞንን መሰረት አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር ለማካሄድ የታሰበው ድርድር ተግባራዊ ከሆነ አተገባበሩ እንዴት ሊሆን እንደሚችልም ምንጮቹ አላብራሩም። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ኦህዴድንና ኦነግን ለማስማማት ተካሂዶ በነበረው ንግግር ኦነግን ወደ ኦህዴድ ለማጠቃለልና ለኦነግ ስልጣን ለማጋራት የታቀደው እቅድ መክሸፉን አስታውሰዋል።

መረጃ ሰጪዎቹ አያይዘው እንደተናገሩት በቀዳሚነት በተለይ ከሶስት ክልልና ብሔር “ተኮር” ድርጅቶች ጋር ኢህአዴግ ለማከናወን የሚፈልገው እርቅ በክልሉ ወይም በዞኑ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን መሪዎች እጁን ዘርግቶ እስከመቀበል የሚያደርሰው ነው። ቀጥለው ሲያስረዱም ሙሉ አስተዳደራዊ ስልጣን እስከመስጠት ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

ህወሃት ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አገሪቱን አሳንሶ አዳክሞና ቆራርጦ የማቀራመት ዓላማ ስላለው ምን አልባትም በደቡብ ክልል አዲስ ክልል ሊወለድ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ከምንጮቹ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

በማስታረቁ ስራ ላይ የተሰማሩትን ማንነት መግለጽ ለጊዜው አግባብ አይደለም በማለት ዝምታን የመረጡት የኢህአዴግ ሰዎች እርቅ በመላው አገሪቱ እንደሚያስፈልግ አብዛኛው ካድሬና የበላይ አመራሮች ምኞት መሆኑን ጠቁመዋል። ዋናው ቁልፍ ያለው በህወሃት እጅ በመሆኑ ክልሎችን ቀደም ሲል ያስቀየመ አካሄድ በመሆኑ በአሁኑ እርቅ አካሄድ ላይ የክልል ከፍተኛ ባለስልጣኖችም እንደተሰማሩበት ተመልክቷል። ሰሞኑን ግንቦት 7 የፍትህና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ኢህአዴግ ለሶስት ጊዜ ያህል የእርቅ ጥያቄ እንዳቀረበለት መግለጹና ኢህአዴግም በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኩል ግንቦት 7ን የመታረቅ እቅድ እንደሌለው በመግለጽ ጉዳዩን ማጣጣሉ ይታወሳል።

ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያና ኤርትራን ለመሸምገል በይፋ ማስታወቋ፣ ኳታርም ቀደም ሲል በተመሳሳይ ለእርቅ ላይ ታች ስትል መቆየቷ የሚታወስ ነው። የሁለቱም አገራት የሽምግልና ሩጫ ምን ውጤት እንዳስመዘገበ የሚታወቅ ኦፊሳላዊ መረጃ ከየትኛውም ወገን አልተደመጠም። ይልቁኑም ህወሃትና ሻዕቢያ አንዱ የሌላውን ባላንጣ በማደራጀት ስራ ላይ መጠመዳቸው ነው በይፋ እየተነገረ ያለው።

በሌላ በከል ደግሞ ኢጋድንና የኢጋድ አገራት መሪዎችን በይፋ ሲዘልፉ የነበሩት የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰሞኑን በሱዳን ያደረጉት ጉብኝት ተከትሎ አዳዲስ መረጃዎች እየተሰሙ ነው። ከኢጋድ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በይፋ ለማደስ እየሰሩ መሆናቸውም ተነግሯል። ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት የተጣለባት እቀባ እንዲነሳላት አጠንክራ እየተከራከረች ባለችበት ወቅት ላይ ሆና ኢጋድን በወጉ ለመወዳጀት ወስናለች መባሉ ወሬውን ሚዛን የሚደፋ እንደሚያደርገው በርካቶች ይስማሙበታል።

ኢህአዴግ በቀጠናው ብሎም በኢጋድ ውስጥ ባለው ተሰሚነት የተነሳ መድረኩ ሻዕቢያንና ወያኔን በማገናኘት ለማሸማገል ለሚደረገው ጉዞ የመጀመሪያው ርምጃ እንደሆነ ከግምት በላይ የሚናገሩም አሉ። ከካርቱሙ ጉብኝት በኋላ በኬኒያ 50ኛ ዓመት የነጻነት በዓል ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጉዳዩ ላይ ከቀጣናው አገራት ጋር እንደሚመክሩበት በመግለጽ ጉብኝታቸውን ከዚሁ ጋር የሚያይዙ አሉ። ይህን አስመልክቶ ግን ከየትኛውም ወገን በገሃድ የተሰጠ መግለጫ ግን የለም።
ጎልጉል

Image

‹‹ የሌላ አገር ዜጋ ኢትዮጵያ ውስጥ በየመንደሩ ገብቶ ዜጎችን ለስደት መለመለ ??? ››

ምንሊክ ሳልሳዊ ብሎግፖስት – በሳዑዲ የዚህ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈውንና ስንቶችን የአካል ጉዳተኛና የአዕምሮ በሽተኛ ያደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ገንዘብ አስተላላፊዎች፣ ሱቆቻቸውን እየዘጉና ሚኒባሶቻቸውን እያቆሙ ከነዚሁ መከረኞች ጋር ወደ አዲስ አበባ እየተሳፈሩና የመሳፈሪያ ጊዜያቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ በየመንም ያሉት ኢትዮጵያዊያኑን ሲያሰቃዩ የነበሩት ኢትዮጵያዊያንም እንዲሁ፡፡ አገር ቤት ያሉት ደላሎችና ኤጀንሲዎች ባለ በርካታ ፎቆችና መኪኖች ባለቤት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ታዲያ እነዚህን ሁሉ ወንጀለኞች እያወቅናቸውና በመካከላችን አቅፈናቸው እየኖርን፣ ወገንን ለባርነትና እንደ መኪና መለዋለጫ አካላቸውን እየተተለተሉ በመቸብቸብ ንግድ ሀብትና ንብረት ያለማንም ከልካይ አፍርተው በእነዚህ ተበዳዮች አገር ሲንፈላሰሱ እያስተዋልን ‹‹ይኼ ነገር ገነ አይቀጥልም›› ብለን የምናስብ ከሆነ መቼም ምን እንደምንባል አላውቅም፡፡ እስኪ ለመሆኑ የትኛው ደላላ ወይም ኤጀንሲ ነው ለኮፍ ለኮፍ ሳይሆን ለተከሰተው የሕይወት መጥፋት፣ ያአካል መጉደልና ያአዕምሮ መታወክ ተመጣጣኝ ቅጣት የተቀጣና ተመጣጣኝ ካሳ የካሰ?
መቼም አንዱን ካንዱ ማበላለጥ ቢያስቸግርም እንደ ከብት ኢትዮጵያዊያን የተቸበቸቡባቸውና የታረዱባቸው የስደተኛ ንግድ ሸሪኮች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ማወቅ ደግሞ ሐዘኑን የከፋ ያደርገዋል፡፡ ከየመን በረሃዎች አንስቶ በሳዑዲ ዋና ዋና ከተሞች ድረስ የተዘረጋው የግፍ ንግድ ምንም እንኳን በየመናውያኑና በሳዑዲያውያኑ ቢመራም በየመን በረሃዎች ውስጥ የነበሩት ገራፊዎችና በየከተሞቹ የሚገኙት ገንዘብ አቀባባዮች ግን በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ነበሩ፡፡

ምን ይኼ ብቻ? በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎችስ እነኚህን ተስፈኞች እየደለሉና እያባበሉ ወደ ሞት የነዷቸውስ እነማን ነበሩ? ‹‹የሌላ አገር ዜጋ ኢትዮጵያ ውስጥ በየመንደሩ ገብቶ ዜጎችን ለስደት መለመለ›› ብሎ የሚከራከር ያለ አይመስለኝም፡፡ በዚህ የምልመላ ሥራ ላይ ለመሳተፍ ደግሞ የግድ ባይሆንም የተመልማዩ ወገን አካባቢ ነዋሪ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ ባሻገር ደግሞ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ለዘመናት ተለጥፈው ስናነባቸው የከረምናቸው ‹‹ወደ ዓረብ አገር በነፃ እንልካለን›› የሚሉት ማስታወቂያዎች እማኞች ናቸው፡፡
http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … st_13.html

“የሰዎች ትልቁ የስህተት ምንጭ ስለቅርቡ አደጋ ሲያወሩና ሲፈሩ፤ የሩቁን አደጋ ስለሚዘነጉ ነው”
===ከሰይጣን ዱቄት የሚበደር ሳይበላው ይሞታል!! ===

በአስቸኳይ የመበልፀግ፤ በአስቸኳይ ድልን የመቀዳጀት፡፡ በአስቸኳይ የመለምለም እቅድ በአቋራጭ ህይወትን ለመለወጥ መሯሯጥን እንጂ እውነተኛ ፍሬ የማስገኘት ውጤትን መስጠቱ አጠራጣሪ ነው፡፡ መንገዶች ሁሉ ውጣ ውረድ አላቸው፡፡ በእርግብ ላባ በወርቅ አልጋ ላይ ለመተኛተ አስቀድሞ ድካምና አመርቂ ትግል ማካሄድን ይጠይቃል፡፡ ፈጣን ነው ያልነው ሁሉ ላይፈጥን ይችላል፡፡ ያቀድነው ሁሉ ወደተግባር ላይለወጥ ይችላል፡፡ ያሰብነው ሁሉ አንጀታችንን ላያርስ ይችላል፡፡ አቋራጮች ሁሉ ዋናው ጐዳና ጋ ላያደርሱን ይችላሉ፡፡

ከሰይጣን ዱቄት የሚበደር ሳይበላው ይሞታል እንደሚባለው በቀናው መንገድ ያልሄድንበት ጉዞ ማረፊያችንን ላያሳምረው እንደሚችል ማስተዋል መልካም ነው፡፡ ጊዜውም ነው፡፡ እኛ የምንሄድበት መንገድ ብቻ ቅዱስ፤ ሌሎች የሚሄዱበት ሁሉ እርኩስ እያልን አንዘልቀውም፡፡ የእኛ መንገድ ብቻ ዲሞክራሲያዊ ሌሎች የሚሄዱበት ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው እያልን ብዙ ወንዝ አንሻገርም፡፡
አበሻ “ምቀኛ አታሳጣኝ” የሚለው፤ ተፎካካሪ የለኝም ብለን አንዘናጋ፣ አንኩራራ ሊል ፈልጐ ነው እንጂ ምቀኛ ፈልጐ ወይም እንደ ንጉሥ ልብነድንግል የጦርነት ያለህ ለማለት አይደለም፡፡ የምንናገረውን በቁጥብነት፤ በጨዋነት፤ ምራቅን በዋጠ ሰው ልሳነ ማቅረብ ይኖርብናል፡፡
The more you say, the more likely you are to say something foolish. powerful people impress by saying less. ብዙ በተናገርክ ቁጥር ጅላጅል ነገር ልትናገር ትችላለህ፡፡ ሃያል ሰዎች ከአንደበታቸው በመቆጠብ ሌሎችን ይማርካሉ፤ እንደማለት ነው፡፡
በሀገራችን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በሶሻል ተራምደንባቸዋል ያልናቸው እሴቶች፤ ያሉ እየመሰሉ የሌሉ፣ የሌሉ እየመሰሉም ያሉ በርካታ ናቸው፡፡ ፈተነዋል ያልነው ችግር በሎሚ እንደተፃፈ ፅሁፍ ቆይቶ ብቅ የሚለው በብስለትና በሀቅ ሳይሆን፤ በአቋራጭና በለብ ለብ ከአንገት በላይ ስለምናደርገው ነው፡፡ የቅርብ የቅርቡን ብቻ እያየን ስለሩቁ ባለማሰባችን ውሎ አድሮ የሚያጋጥመን ነገር ይበረክታል፡፡ ማስተዋል ያንሰናል የሚባለው ለዚህ ነው፡፡
ካርዲናል ደ ሬዝ እንደፃፈው፤ “የሰዎች ትልቁ የስህተት ምንጭ ስለቅርቡ አደጋ ሲያወሩና ሲፈሩ፤ የሩቁን አደጋ ስለሚዘነጉ ነው” ይላል፡፡
የኑሮ ውድነት አደጋ በዕለት ዕለት ድጐማ የምንቋቋመው ችግር አይደለም፡፡ ብዙ በሶትን የተሸከመ በመሆኑ ማህበራዊ ምስቅልቅልን እንዳያስከትል አበክሮ መከታተልን ይጠይቃል፡፡ ፅናትን ይጠይቃል፡፡ እኔ ጠግቤ ካደርኩ ስለሌሎቹ ምን አገባኝ አለማለትን ይጠይቃል፡፡ Apre moi le deluge እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለማለትን ይጠይቃል፡፡ ገንዘብ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ለግብር ከፋዩ ምን አደረኩለት ማለትን ይጠይቃል፡፡ ሁሉን መንገድ በአቋራጭ እንዝለቀው ማለት ቢያንስ የዋህነት ነው፡፡ ችግርን ለመፍታት የቆራጥ መሪዎች ፈጣንነት ብቻ ሳይሆን የህዝብ ተሳትፎን ይፈልጋል፡፡ የአሳታፊነት መርህ ለአገር የሚበጁ ወገኖችን አሰተዋፅኦ ያጐለብታል፡፡ ብቻችንን በመጓዝ መንገዱን ሁሉ አንገፋውም፡፡ ሁሉን በራሳችን ዙሪያ ብቻ ስናጠነጥን አንደኛ የወጣን ሊመስለን ይችላልና መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ ብቻውን የሮጠ የሚቀድመው የለ፤ ብቻውን የሚሟገት የሚረታው የለ የሚባለው ምፀቱ ይሄው ነው!
#MinilikSalsawi

የዛሬይቱ ቀን በህይወቴ አዲስ ምዕራፍ የጀመርኩባት ዕለት ናት።እናት ሐገሬ ኢትዮጵያን ለቅቄ የሞያሌን ኬላ ተሻግሬ የኬንያን ምድር የረገጥኩባት ታሪካዊ እለት ።ኅዳር ሠላሣ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት ዓመተ ምሕረት ዕለተ ዐርብ ከቀትር በፊት።ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ሰሜን ኬንያ ጋንቦ ቀበሌ የገባሁበት ቀን ስምንተኛ ዓመት መታሠቢያ።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አስር ቁጥር ሃያ ሦሥትን ይመልከቱ። ባላሠቡትና ባልጠበቁት ጊዜና ሰዓት ከትውልድ ቀዬዎ ሊሠደዱ ይችላሉ።ዛሬ ምስራቅ አፍሪቃ ምድር ወገብ አቅራቢያ ቪክቶርያ ሐይቅ ዳርቻ ላይ ሆኜ የተሠደድኩበትን ምክንያት ሣሠላስል መሠደዴ አግባብነት ነበረው ወይስ እንደ ኮነሬል መንግስቱ ፍርጠጣ ነው ለማለት ህሊናዬ ዘወትር እንደጠየቀኝ አለ።
ሟቹ የወያኔ ጠቅላይ ሚንስትር የግንቦት ሠባቱን የምርጫ ውጤት በአጋዚ ጥይት ከቀለበሡትና ሕገ መንግስቱ በሕገ አራዊት ከተለወጠ በኋላ የሐገር ቤት ሠላማዊ ትግልና የፕሬስ ነፃነት ጥቅምት ሃያ ሁለት ቀን አክትሟል።
ጋዜጠኞች፣የሠብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተለቅመው ሲታሠሩ፣ወጣቱ ያለ ሀጥያቱ በየጦር ካምፑ ሲታጎር የኔ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማንም ግልፅ ነበር። ጥቅምት ሃያ ሁለት አመሻሽ ላይ ሱፍና ከረባት፣መነፅርና ፕሮቶኮል ቀርተው አልባሌ በመልበስና በመምሠል ከቦታ ቦታ ስሽሎኮለክ ብቆይም ነገሮች ከመሻሻል ይልቅ እየተበላሹ በመምጣታቸው ወደ ኬንያ ለመጓዝ ህዳር ሃያ ሁለት አካባቢ የወሰንኩ ይመስለኛል።
ጠቅላይ ሚንስትር ለገሠ ዜናዊ በኛ ላይ ጦር ሲያውጁ ያቀረቧቸው አማራጮች ት<ዝ ይሉኛል።
፩ አርፎ መቀመጥ ፪መሠደድ ፫ጫካ መግባት ፬ቃሊቲ ።
ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ለማገዝ በወቅቱ የኔ ምርጫ መሠደድ ነበር።ሠላማዊ ትግል አላዋጣ ሲል ጠመንጃ ማንሣት የግድና ተገቢ መሆኑን ከነማንዴላ ኤኤንሲ ፓርቲ ውሣኔ መማር ይቻላል።
አማርኛ ቃለ መጠይቅ ለቪኦኤ ለመስጠት የሚጠየፉት የብአዴኑ በረከት ስምዖን የማስታወቅያ ሚንስትር በነበሩበት ፩፱፱፪ የፓርላማ ምርጫ ወቅት በአፍሪቃ አዳራሽ የክርክር መድረክ ላይ ወያኔ ስልጣን በጠመንጃ እንደያዘና በምርጫ ቢሸነፍ ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ ነወይ ስል ላቀረብኩላቸው ጥያቄ ደርግ መብታችንን በመርገጡ ጠመንጃ አንስተናል ሲሉ መናገራቸውን አስታውሣለሁ።መብቱ የተረገጠ ሕዝብ ጠመንጃ ሊያነሣ እንደሚገባ በረከት የተገነዘቡ ይመስላል።
የኔ ድርሻ እንደጋዜጠኛና የሠብዓዊ መብት ተሟጋች ከሐገር ከተሠደዱ ቦኋላ የፈረንጅ ሐገር ኑሮ ለምዶ ሆዳም ዲያስጶራ መሆን ሣይሆን የተሠደዱበትን ዓላማ ባለመዘንጋት ሐገራዊና ህሊናዊ ግዴታን መወጣት ነው።
የፓለቲካ ስደተኛ ነኝ ብሎ የኬዝ ደራሲ መሆንና የስደተኛ መታወቅያ ታቅፎ ከንቱ የተስፈኛ ህይወት መምራትን ልንጠየፈው ይገባል።ሁለት ሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ ወያኔን ወያኔ ብሎ መጥራት የሚፈራ ማንነት ይዞ መንከላወስ በታሪክና በትውልድ እንደሚያስወቅስም መረዳት ያስፈልጋል።
ሁለት ልብ ሆኖ ሁለት ማልያ እየለበሡ በአንድ ሜዳ ላይ መጫወት አይገባም።እኔ የፓለቲካ ስደተኛ ነኝ።የየትኛውም የፓለቲካ ድርጅት አባል አይደለሁም።መሆንም አልፈልግም።ያ ማለት ግን የሐገሬ ጉዳይ አያገባኝም፣ካናዳ ገብቼ የስደት ኑሮ ለመኖር የመጣሁ የኤኮኖሚ ስደተኛ ነኝ፣ኬዜ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምርጥ የኬዝ ደራሲዎች የፃፉልኝን ገፀ ባህሪ በተገቢው መድረክ የምተውን ተወናይ።ካልሆነም ፍራሼ ስር የደበቅኩትን ፓስፓርት አድሼ ምሣዬን ካምፓላ በልቼ ለራቴ አዲስ አበባ የምበር ዋቴ።ዛሬ ይህን ሁሉ ያስቀባጠረኝ እንደዋዛ ከሐገር፣ከቤተሠብ፣ከጓደኛ ተለይቼ ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት ቀናት በስደት መቆየቴን በመዘከር ነው።
ህይወት ይቀጥላል።አዲስ አበባ ላይ መፃፍና መኖር ብከለከልም ካምፓላ ላይ እየፃፍኩ እኖራለሁ።ብዕሬ ዝም አትልም።እውነትን፣ነፃነትን፣ፍትህን በሐገሬ ሠማይ ላይ እስክመለከት ድረስ እፅፋለሁ።ሕገመንግስቱ ከወሬና ከመነበብ ባሻገር በተግባር እስኪፈፀም፣ሕዝቤ በነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሕዝብ የሚመርጣቸው ፓርቲዎች ስልጣን እስኪረከቡ ድረስ እፅፋለሁ ፣እናገራለሁ።
ማንዴላን የታራክ ሠገነት ላይ የሠቀላቸው ለነፃነት የከፈሉት ክቡር ዋጋ ነው።ሞት እንደሆነ አይቀሬ ነው ።እየሞቱ ከመኖር ለትውልድ ነፃነት በየመስኩ የአቅማችንን እናበርክት መልክቴ ነው።
እስክንድር፣ውብሸት፣ርዕዬት፣አንዱዓለምና በርካቶች……..የኛ ማንዴሎች ናቸው።
እንደአንዳቸውም ባለመሆኔ ባዝንም ባለሁበትም ቢሆን ስለነሡና ስለሐገሬ ልጮህ እወዳለሁ።አምላኬም ይረዳኛል።ዛሬ አዲስ የልደት ቀኔ ናት።ዕድሜዬም ስምንት ነው።አዲስ ህይወት ከኬንያ ጋንቦ ጀምሬ አሁን ካባላጋላ ላይ ነኝ።የነፃነት ትግሌ ግን እስከመቃብሬ በብዕሬ ይቀጥላል።ትግልእስከመቃብር።
ደረጀ በጋሻው<pen Ethiopian>

Image

ባለፈው ሐሙስ ምሽት ላይ ዓለማችን ታላቅ ሰው አጥታለች፡፡

የደቡብ አፍሪካ አባትና በዓለማችን ላይ የራሳቸውን አሻራ አስቀምጠው ያለፉት የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል፡፡ የእኝህ ታላቅ መሪ ሕልፈት የዓለማችን ዓይንና ጆሮ በአንድ ቦታ እንዲያርፍ አድርጓል፡፡ በአራቱም የዓለማችን ማዕዘናት ከልጅ እስከ አዋቂ በማዲባ የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ ደቡብ አፍሪካዊያን በማዲባ ሕልፈት የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን እየገለጹ ነው፡፡ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ደቡብ አፍሪካ ታላቅ ልጇን አጣች ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የማንዴላ ሕልፈት ግን ከአገሪቱ አልፎ የዓለማችንን ትኩረት መሳብ ችሏል፡፡ ማንዴላ አፓርታይድን ለማስወገድ ያደረጉት የትግል ጉዞ ወደ ፖለቲካው ዓለም እንዲቀላቀሉ ምክንያት የሆነላቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ምድራችን ታላቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ ማጣቷን ተናግረዋል፡፡ በርካታ የዓለማችን ፖለቲከኞችና ታዋቂ ግለሰቦች አርዓያ የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ ቢያልፉም፣ ስማቸው ግን አሁንም ከመቃብር በላይ ውይላል እያሉ ናቸው፡፡

ማንዴላ እንዲህ የዓለማችንን ትኩረት ሊስቡ የቻሉበት ምክንያት በሕይወት ዘመናቸው የሠሯቸው በርካታ ሥራዎች ናቸው፡፡ ማንዴላ የደቡብ አፍሪካን ፀረ አፓርታይድ እንቅስቃሴ በመምራት አገሪቱ ከቅኝ ግዛት ከወጣች በኋላ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡ ማንዴላ የሰው ልጆችን በቆዳቸው ቀለም በመከፋፈል አሰቃቂ ግፍ በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ የሚፈጽመውን የአፓርታይድ ሥርዓት ለመገርሰስ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ማንዴላም ይህንን በማድረጉ ሒደቱ ውስጥ የዘመናቸውን 27 ዓመታት በእስር ቤት እንዲያሳልፉ ተገደዋል፡፡ ማንዴላ ይህን ያህል ጊዜ በእስራት እንዲያሳልፉ የተፈረደባቸው በነጮች የተመሠረተውን የአፓርታይድ መንግሥት ሊያስወግዱ ተነስተዋል በሚል ውንጀላ ነው፡፡

ባለፈው ሐሙስ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ማንዴላ ግን በዓለማችን ጭቆናን ለሚታገሉ እንደ ምልክት የሚታዩ አርዓያ ግለሰብ ናቸው፡፡ ማንዴላ 27 ዓመታትን በእስራት በማሳለፍ ለነፃነት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ለዓለም አሳይተዋል፡፡ በ71 ዓመታቸው ከእስር ቤት የተለቀቁት ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ ተንሰራፍቶ የነበረውን የአፓርታይድ ሥርዓት ለማስወገድ ያከናወኑት ትግል ግን ሰላማዊ መንገድን የተከተለ ነበር፡፡ ለዚህም ነው በርካቶች ማንዴላን የደቡብ አፍሪካው ማህተመ ጋንዲ የሚሏቸው፡፡

ማንዴላ ምንም እንኳን አሰቃቂና ዘግናኝ የሆኑ 27 ዓመታትን በእስር ቢያሳልፉም፣ ከተቀናቃኞቻቸው ጋር እርቅ በማውረድ የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ ታላቅ መሪ ናቸው፡፡ ከባላንጣዎቻቸውም ጋር የእርቅን መንገድ በመከተላቸው የኖቤል የሰላም ሽልማትን መቀዳጀት ችለዋል፡፡

ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ በአገሪቱ ለሁሉም ዜጎች እኩልነትን በማምጣት ለብዙዎች አርዓያ መሆን ችለዋል፡፡ ይህንንም በማድረጉ ሒደት ማንዴላ የአገሪቱ አንገብጋቢ ችግር የነበረውን ድህነት በዋነኝነት ተዋግተዋል፡፡ ማንዴላ ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈልና ከራሳቸው በፊት አገራቸውንና ሕዝቡን በማስቀደም በሁሉም ሕሊና የሚታወስ ሥራ ሠርተዋል፡፡

ማንዴላ ‹‹የቀስተ ዳመና›› አገር የተባለችውን ደቡብ አፍሪካ መገንባት የቻሉት በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የመጀመሪያ ሥራቸው የሆነውን የብሔራዊ እርቅ ፕሮግራም ይፋ በማድረጋቸው ነው፡፡ በቆዳ ቀለም ልዩነት ምክንያት ክፉኛ የተጐዳው የአገሪቷ ኢኮኖሚም ሊያገግም የቻለው ማንዴላ ቅድሚያ እርቅንና መቻቻልን ማምጣት በመቻላቸው ነው፡፡

ኔልሰን ማንዴላ ከኢትዮጵያ ጋርም ቅርብ ግንኙነት አላቸው፡፡ ማንዴላ በአገራቸው ነፃነትንና ፍትሕን ለማምጣት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ የተወሰነ ጊዜ በአገራችን አሳልፈዋል፡፡ ማንዴላ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ዋናው ምክንያት ወታደራዊ ሥልጠና ለማግኘት ነበር፡፡ ማንዴላ ኢትዮጵያ ሁሌም ቢሆን ከልቤ የማትጠፋ አገር ናት ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያም ቢሆን ለማንዴላም ሆነ ለደቡብ አፍሪካ ባለውለታ መሆኗ ይታወቃል፡፡ የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሥራች ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ደቡብ አፍሪካም ሆነች መላው የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ እንዲወጡ ያደረጉት ትግል በታሪክ ሁሌም ይወሳል፡፡

ማንዴላ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩንም ሥራቸው ግን አሁንም ከመቃብር በላይ ነው፡፡ እኛም ከማንዴላ የሕይወት ጉዞ በርካታ ልንማረው የሚገባ ነገር አለ፡፡ እኝህን የዓለማችን ታላቅ ሰው ልንዘክራቸው ይገባል እንላለን፡፡

reporter amharic

Dawit Solomon
ለባቡሩ የተሰራው ሲፈርስ ምን ይባላል?
——————
የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ያላመሰቃቀለው ህይወት የለም፡፡ያልፈረሰ መንገድ ቤት አይጠየቅም፡፡ታይተው ያልተጠገቡ መኪና የናፈቃቸው መንገዶች ፈርሰዋል ባቡሩ ሊመጣ ነው ተብለው፡፡ንግድ ቤቶች የስንት ቤተሰብ ማገር የነበሩ ከቦታቸው ተነቅለዋል፡፡ስለ ባቡሩ እንጂ ባቡሩ ስላፈናቀላቸው ቤተሰቦች ህይወት ማውራት‹‹ጸረ ልማትነት›› በመሆኑም ንግድ ቤቱ ሲፈርስ ህይወቱ እየፈረሰ እንደሆነ ተንታኝ የማያሻው አባወራ የሆዱን በሆዱ አድርጎ‹‹የልማቱ ደጋፊ ነኝ››ይለናል፡፡
ባቡሩ ያፈረሳቸውን ተሻግረን ስንመጣ ከላይ ለመጥቀስ ከሞከርኳቸው መፍረሶች ጋር የማይገናኝ የመንገድ መፍረስ እናገኛለን፡፡የባበሩ ሃዲድ መዘርጋት የጀመረበት ቦታ ነው፡፡እዚሁ ሸገር ጉምሩክ ፊት ለፊት የባቡር መንገዱን ከመኪና መንገድ የሚለይ ግድግዳ ሳትመለከቱ እንዳልቀራችሁ እገምታለሁ፡፡መከለያው ከሰው ቁመት አይተናነስም የጎን ርዝመቱም የት የሌለ ነው፡፡በሲሚንቶ የተሰራው መከለያ ጠንከር ብሎ የመኪና ግጭትን ተቋቁሞ የታለመለትን አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ ብዙ የህዝብ ገንዘብ ፈሶበታል፡፡
ቻይናዊው ኮንትራክተር አበሻውን ቡልዶዘር አሽከርካሪ በእጆቹ እየጠቆመ ቡልዶዘሩ የሲሚንቶው ክምር ላይ ወጣ፡፡በጠራራ ጸሐይ ግድግዳው ተደረመሰ፣ሹፌሩ አንዱን እየናደ ወደ ሌላኛው አመራ፡፡ምን ጥፋት እንደተገኘበት ባላውቅም ግድግዳው እንዲፈራርስ ተደረገ፡፡ሌሎቹ የፈረሱት ለባቡር ተብለው ነበር፡፡ይህ ግን ለባቡሩ ተብሎ የተሰራ በመሆኑ ለምን እንዲፈርስ እንደተደረገ ሊገባኝ አይችልም፡፡አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ፣ግድግዳው በመጣመሙ፣ግድግዳው ሲሰራ የመንገዱ ውበት በመቀነሱ፣መንገዱ በመጥበቡ፣ብቻ እንዲፈርስ የተደረገው በሌላም ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
እንዴት ነው ነገሩ ግን መቼ ነው ሳንጀምር የምናስበው፣መቼ ነው ህዝብ ማክበር የምንጀምረው፣ምናልባት ይህ የኮንትራክተሮች ጉዳይ ነው ሊባል ይችላል፡፡ቢሆንስ እየሰሩ የሚያፈርሱ ከሆነ ጨረስን ያሉንን እንደማያፈርሱት አልያም ስህተት እንደማናገኝበት በምን ልናምናቸው ነው?

እነሆ ባለ ስልጣናት፣ ‹‹ልማታዊ›› አርቲስቶችና የፓርቲው የኪነት አባላት ሲጨፍሩ ሰነበቱ፡፡ ራሳቸውን ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ብለው ጠርተው፣ ኢትዮጵያንም ወክለው፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሰዎች አብረው መጨፈር መቻላቸው ራሱ አንድ ነገር ነው፡፡ ባለፉት 23 አመታት የተነዛው ጥላቻ በገንዘብና በሆድ አደርነት የሚሸፈንም አልነበረም፡፡ እንደ ቅስቀሳው ብዛት ካድሬዎች፣ የኪነት ቡድኑ አባላትና ‹‹ልማታዊ›› አርቲስቶች እርስ በእርሳቸው አለመተራረዳቸውም አንድ ነገር ነው፡፡ ችግሩ ከጭፈራ ያለፈ አለመሆኑ ነው፡፡ ጭፈራ ችግር ቢፈታ ኖሮ በአንድ ስታዲየም ውስጥ የተገኙት ፖለቲከኞች፣ የኪነት ቡድንና ‹‹የጥበብ›› ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን 90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አሸሸ ገዳሜ ከማለት ወደኋላ አይሉም ነበር፡፡ ጭፈራ ችግራችን ቢቀርፍልን ኖሮ!

ይህ የአንድ ቀን ‹‹የብሄር ብሄረሰቦች›› ጭፈራ ዳቦ መሆን ቢችል ኖሮ የባለስልጣን መኪናዎች በክረምት ጭቃ፣ በበጋ አባራ አልብሰዋቸው የሚያልፉት የጎዳና ተዳዳሪዎች በባዶ ሆዳቸው፣ በጎስቋላው አካላቸውም ቢሆን ለአንድ ቀን ይቅርና አመቱን ዳሌያቸውን መወዝወዝ ባልከበዳቸው፡፡

እውን ጭፈራ ለኢትዮጵያውያን ችግር መፍትሄ መስጠት ቢችል ሳውዲ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ዚምባብዌ፣ ኢትዮጵያም፣ ማዕከላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ጉራፈርዳ፣ ኦጋዴን…… ውስጥ ከመሰቃየት ልክ እንደ ስፖርት ጧት ጧት፣ ልክ እንደ ምግብ ወይንም ክኒን በቀን ሁለት ወይንም ሶስት ጊዜ ቅስቀሳ፣ ዝግጅት፣ ወጭ……ሳያስፈልገን ሚሊዮን ሆነን ከመጨፈር ባልሰነፍን!

ጭፈራ ውሃ ቢሆን ህጻናትና አዛውንቶች አሁን ጀሪካን የሚያጎብጠውን ወገባቸውን ‹‹ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን›› ባልለገሙ፡፡ ጭፈራ የመብራት፣ የስራ፣ የትምህርት፣ የቤት…ችግርን ቢፈታ… የህዝቡስ የህዝብ ነው፡፡ ብሄርን፣ ብሄረሰብንና ህዝብን ወክለናል የሚሉትን ተለጣፊ ፓርቲዎች ጭፈራ ከህወሓት ተመጣጣኝ ስልጣን የሚሰጣቸው ቢሆን ኖሮ ባለፈው 23 አመታት የጨፈሩት የትራንስፖርትና የሴቶች ጉዳይን እንደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲቆጥሩ ባልቆዩ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ከደብረጽዮን ስድብ፣ ከስብሃት ነጋ ቅብጠት፣ ከአባይ ጸሃዬ ግልምጫ፣ ከመለስ የሙት መንፈስ.. ቢገላግላቸው ምንም ፈቀቅ ሳይል ከነጎደው የእድገቱና… ይልቅ በጭፈራ ትራንስፎርሜሽን ወገባቸውን መቆራረጣቸው ባልከፋ፡፡

እውን ጭፈራ ለህዝብ ስልጣን መፍትሄ ቢሆን ኖሮ እነ ታማኝ በየነም በባዕዳ አገር ከመንከራተት ይልቅ ጅጅጋ ይቀርባቸው ነበር፡፡ ታማኝ እንኳ ወጣት ነው፡፡ አርጅተውም ስለ ህዝብ ስልጣን፣ ስለ ፖለቲከኞች ችግር መናገር ያላቆሙት እነ ዶክተር ሀይሉ፣ እነ ፕሮፌሰር መስፍን፣ አስግደ፣……. ሰሚ ካጣ ጩኸት የአንድና ሁለት ቀን ሆታ፣ ጭፈራና ፌሽታ ሊከብዳቸው አይችልም፡፡ ግን ምን ያደርጋል? ጭፈራ ጭፈራ ነው፡፡ የሞቅታ፣ የስካር፣ የማወናበጃ፣……

ዓለም አቀፍ የስደት ድርጅት ከሳዑዲ ዓረቢያ ለተመለሱ ቁጥራቸውም 120 ሺሕ እንደሚደርስ ለሚገመቱ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን 13.1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ድርጅቱ እንደሚለው ከስደት ተመላሾቹ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ በመሆኑ የ24 ሰዓት አጣዳፊ ዕርዳታ ያስፈልጋል፡፡ እስካለፈው ሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ከ100 ሺሕ በላይ ተመላሾችን መቀበሉን ያስታወቀው አይኦኤም፣ ከእነዚህ ውስጥ ከ90 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የስደት ተመላሾች የቀጥታ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ በየቀኑም ከሰባት ሺሕ በላይ ስደተኞች እየተመለሱ ናቸው ብሏል፡፡ አይኦኤም ለትራንስፖርት፣ ለሕክምና፣ ለምግብና ለተዛማጅ አገልግሎቶች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቆ፣ ቤተሰብ ለሌላቸው 167 ልጆች ዕርዳታ ማድረጉን ገልጿል፡፡

ሃምሳ ስምንት ሕፃናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው መሸኘቱን አስታውቋል፡፡ አይኦኤም 2.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ቢያገኝም፣ የ13.1 ሚሊዮን ዶላር ክፍተት ስላለ፣ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡ ለእያንዳንዱ ተመላሽ በነፍስ ወከፍ 130 ዶላር እንደሚያስፈልገው ገልጿል፡፡ እስካሁን ዩኒሴፍ፣ ዩኤንኤችሲአር፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴና ሌሎች አካላት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡

Image

ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ሣሙዔል መኮንን <አቡሽ> ዛሬ በዘጠኝ ሠዓት በካንፓላ መካነ ሠላም መድሐንያለም ቤተክክርስትያን በድንግል መሬት ተቀበረ።ወጣት ሣሙዔል መኮንን <አቡሽ>ከሐገሩ ተሠዶ ከወጣ አምስት ዓመታት የተቆጠረ ሲሆን ወደሌላ ሐገር ለመሻገር ሣይችል የምድር ጉዞውን በምድር ወገቧ ዩጋንዳ ጨርሷል።ከሃምሣ ያላነሡ ሥደተኞች በቀብሩ ላይ መገኘታቸውን የፔን ዘ ኢትዮጵያ ዘጋቢ የታዘበ ሲሆን ወጣቱ በጉበት ህመም ባለፈው ማክሠኞ ጧት በተኛበት ሞቶ መገኘቱን ሀኪሞች ጠቁመዎል።

የታላቁን የነጻነት ታግይ መሞት ተከትሎ ከወያኔ ጎረምሶች የሚወረወሩ ቃላቶች የፖለቲካ ብስለትን ያላገናዘቡ እና የስልጣን ጥመኝነትን የሚያሳብቁ የጭፍን ድጋፍ ሩጫዎች ሲሆኑ ማንዴላን በተመለከት ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን የሚወረወሩ የነጻነት ስሞች እና የአፓርታይድ ቃላቶች የውስጥ ህመም ሆኖባቸው ሟች አምባገነናቸውን እያነሱ መቀባጠር ጀምረዋል::

የማንዴላ ሞት አለም ያለቀሰበት የአሜሪካ ባንድራ ለ3 ቀን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ (President Barack Obama ordered American flags to be lowered immediately to half-staff until Monday in tribute to Mandela, a rare honor for a foreign leader.)የተወሰነበት ነጭ ከጥቁር ሳይል ክብሩን የገለጸበት መሆኑን በወያኔ ጎረምሶች ለምን መካድ እንደተፈለገ አይገባኝም ? የተቃዋሚ ሃይሎች ለማንዴላ ሞት ሃዘናቸውን ስለገለጹ? አሊያስ የአለም ህዝብ አትኩሮቱ ሁሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስለሆነ? ወይንሳ ለመለስ ሞት የህን ያህል …አለመደረጉ ?

ደቡብ አፍሪካ ላይ ሌጋሲ የሚባል ነገር ወላ የፖለቲካ ህዳሴ አሊያም የሚዲያ ፍጆታ ወሬ ምንምን አይሰራም:: የማንዴላ ጣኦትነት አይሰበክም :: የማንዴላ ሌጋሲ አይሰበክም :: የምንሰማው በጽናት የሃገራቸውን ነጻነት ያረጋገጥኡ በአለም አቀፍ ደረጃ የነጻነት ቀንዲል የሰላም እና የአንድነት አባት መሆናቸውን እና ፈለጋቸውን እንድንከተል እንጂ ትራንስፎርሜሽናቸውን እያጨበጨብን እንድንቀበል አይደለም::

ወያኔ የሚሰራውን ግፍና ሰቆቃ ስለሚያውቀው የነጻነት የዲሞክራሲ ጥያቄ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር ራስ ምታት ይሆንበታል:: በአለም አቀፍ ደረጃ ለዚህ የታገሉ ሰዎች ስማቸው ሲጠራ ያመዋል:; አብሶ ተቃዋሚዎች ከተናገሩ ያቃጥለዋል:: አጸ ምንሊክ … ቀኃሥ … ማንዴላ… ምናምን እየተባላ ሲተራ ያሳክከዋል ..ያራውጠዋል:….. የአገዛዝ ስልቱ በኒዎ አፓርታይድ ላይ ስለተመሰረተ የደቡብ አፍሪካው የጸረ አፓርታይድ ትግል ሲነሳ የስልጣን ማስረዘሚያው ዘዴ የተነቃበት ስለሚመስለው ይጨፍራል ለማዘናጋት ይራወጣል:: ኢትዮጵያውያን ስለእንደዚህ አይነት ነገር መስማት የለባቸውም:: አርፈው መገዛት አለባቸው ይህ ከተነሳ ወያኔ በሽታው አብሮ ይነሳል ይፈራል:ስራውን ስለሚያውቅ::

የዛሬው የወያኔ ጎረምሶች ጭፈራ በከፊል የህን የተመረኮዘ ነው::በአለም በአፍሪካ በሃገር ቤት አንድ ነገር በመጣ ሰአት ሁሉ ወያኔ የሚለቃቸውን የፖለቲካ ፍጆታ ነጠላ ዜማዎች ለማቆም መጣር እንዳለበት ልንመክረው እንፈልጋለን::

ታላቁ የነፃነት አርበኛ ኔልሰን ማንዴላ በአይቀሬው ሞት ሲረቱ ጆሀንስበርግ ብቻዋን የሀዘን ቡልኮ አላጠለቀችም።መላ ዓለም በሀዘን በረዶ ተመቷል።አፓርታይድን ወደ ከርሠ መቃብር ያወረደ ጀግና በአይቀሬው ሞት ተረታ።
እንደኔ ምኞት አፍሪቃ በየማዕዘኑ የማንዴላን አይነት መሪ ብታገኝ ምን ያህል የታደለች አህጉር በሆነች ነበር<>የተባበሩት የአፍሪቃ አንድ ገናና ስቴት በሆንን ነበረ።ነገ የሚሆነውን ለመተንበይ ነብይ መሆን ቢያስፈልግም አሁን ያለችው አፍሪቃ ከሃምሣ አራት ግዛትነት ወደ አንዲት አህጉር እንድትመጣና አንዲት ሐገር ለመሆን በየቤታችን ያለው ማነቆና የገዢ ፓርቲዎች ማቱሣላዊ ቆይታ ድቅድቅ ላይ መሆናችንን ጠቋሚ ነው።ወደ ስልሣና ሠባ ትናንሽ ሐገራት እንዳንከፋፈልም የሚያሠጉ ሁኔታዎችም መኖራቸውን መገንዘብ ይኖርብናል።
ከማንዴላ ጋር የጠበቀ ቁርኝት የነበራት የኔዋ ፀረ አፓርታይድ የነበረችው ኢትዮጵያ ጠያይም ሐገር በቀል አፓርታይዳዊ ስርዓት አራማጆች እያቆጠቆጠባት መሆኗን መደበቅ ለኔ ህሊና አይመጥንም።
የስራ ባልደረባዬ እስክንድር ነጋ በግፈኞች የተፈረደበት ጠበንጃ አንስቶ ወይም ፓርቲ መስርቶ ለስልጣን ስለታገለ እንዳልሆነ አሳሪዎቹ ጭምር የሚገነዘቡት መራራ ሐቅ ነው።
እስክንድርና ማንዴላ የነፃነት ታጋዮች ናቸው።ማንዴላ አፓርታይድን ለመዋጋት ቢያንስ ወታደራዊ ስልጠና በሐገራችን ጭምር እንደወሠዱ ከታሪክ ተገንዝበናል።እስክንድር የጦር መሣርያና የጦር ሠፈርፊትም ይሁን ወደፊት ከእስር ሲወጣ እንደማይረግጥ ስለማውቀው ላረጋግጥ እችላለሁ።የእስክንድር ኡዚ ብዕሩ ነው።ሟቹ ለገሠ ዜናዊ ጥይት በማይበሳው መኪና ታጅቦ ሲጓዝ አናቱን ብሎ ያዞረው ከእስክንድር ቀለም ተፊ ሠላማዊ ኡዚ ብዕሩ የተተኮሰ ህዝባዊ ማዕበል ቀስቃሽ ፅሁፉ ነው።ያሣሠረውም ሙያውና ሕዝባዊ አመለካከቱ ነው።
ከአሜሪካ ቅምጥል ኑሮን ንቆ የመጣው ለውጥ መጥቷል፣በሐገሬ በሙያዬ የበኩሌን ላበርክት ብሎ በመወሰኑ ነበር።ከሃያ ዓመታት በላይ ስርዓቱን በስክሪብቶ ሲፋለም የኖረው።
ማንዴላ ቢባል ኣይበዛበትም።ለሃገሩ ብሎ ያላጣው ነገር የለም።
ነገ እንደ እስክንድር ነጋ አይነት ዜጎች የሐገራችን ተስፋ ይሆናሉ።የነ ስብሐት ነጋ ስርዓት ሲመሽበትና የነብርሃኑ ነጋ ዘመን ሲመጣና እውነተኛ የሚተገበር ህገ መንግስት ሲዘርጋ ህዝቡ የመረጠው ፓርቲ ስልጣን ላይ ሲወጣ የዛሬ ስምንት ዓመት ጥያት ወደወሁባት የአፍሪቃ መዲናይቱ እትብቴ የተቀበረባት እውነተኛዎ ሪፐብሊክ ኦፍ ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያ በወጣሁበት ሞያሌ ሳይሆን በቦሌ እገባለሁ።ዘወትር የምጠብቃት ቀን ደሞ ትመጣለች።
ማንዴላ ታሪክ ሰርቶ አልፏል።ኢትዮጵያዊያን የራሣችንን ኤኤንሲ መስርተን በማቆጥቆጥ ላይ ያለውን አፓርታይዳዊ ሥርዓት በህዝባዊ ሱናሚ ኣስወግደን እስክንድርን በፍትሐዊ ምርጫ እንደማንዴላ ለመሪነት ለማብቃትና ቃሊቲ ያሉ ጀግኖቻችንን ነፃ ለማውጣት የማንዴላን ፈልግ እንከተል የሚለው መልዕክቴ በዛሬዋ ዕለት በስደት ከምማቅቅባት ሐገር ይድረሳችሁ ።
ነፍስ ይማር ለታላቁ የአፍሪቃ ብርቅዬ ልጅ ኔልሠን ማንዴላ
ደረጀ በጋሻው
የቀድሞ የአስኳል ጋዜጣ
ዋና አዘጋጅ
ምስራቅ አፍሪቃ


ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው::

Image

ምንሊክ ሳልሳዊ :-ይህን ሰሞን በሃገር ውስጥ እና በውጪው ሃገር ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመወያያ ርእስ የሆነው እና ይየወያኔ ካድሬዎችን ቀልብ የገፈፈው እና ከሰል ያለበሳቸው ወያኔ ለግንቦት ሰባት ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ነው::በስፋት አሁንም እየተከራከሩበት ያለው ይህ ጉዳይ አገሩን በጡዘት አምሶት የሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት አንድ ተስፋ የሰጠ ሁኔታ እንደሚታይ እየተተነበየ ነው::

ወያኔ በእርግጥ በማይጥም የፖለቲካ እሰጥ አገባ የተጠመደ ቢሆንም የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ለላውን ከማዘናጋት ውጪ ምንም አይነት ፋይዳ እንዳሌለው እና ራሱን እየፈተሸ እንደሆነ ያጋለጠ ጉዳይ ነው:: የድርድር ጥያቄ አላቀረብኩም ያለው ወያኔ እንደለመደው ከኦነግ ከኦብነግ ከሻእቢያ ጋርም እየተደራደረ ጥያቄውን እራሱ እያቀረበው ሲክድ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳን በኬንያ ከኦብነግ በጀርመን ከሻእቢያ ጋይ ያደረጋቸውን ድርድሮች እየታከካቸው አልፏል::

ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው:: በእርግጥ በተለያዩ ጊዜያት ለወያኔ እና ለግንቦት ሰባት የቅርብ ርቀት የሆኑ ሰዎች ይህንን ጉዳይ በግል አንስተውት የሆነ ቢሆንም ባይሆንም ግን የአና ጎሜዝ የአዲስ አበባ ምላስ ተከትሎ ግንቦት ሰባት ለህዝብ ይፋ ያደረገው ጉዳይ አሁንም ሚዛኑ ወደ ግንቦት ሰባት እንዲሆን አድርጎታል::

እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ባለስልታናት የቀን ተቀን የስብሰባ መቀመጫቸው ግንቦት ሰባት ነው:; በወታደሩ በደህንነቱ እና በታማኝ ካድሬው ዙሪያ ውይይቱ ምስጢሩ ግንቦት ሰባት ነው:: እነዚህ የሚስጥር ተወያዮች እንደሚጠቁሙት ሲሰበሰቡ በውይይት ወቅት ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ብለው አይጠሩትም:; አሸባሪ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታቸው አደባባይ ላይ መሆኑን በይፋ የተረጋገጠ መረጃ ይጠቁማል::
በቅርቡ ከአባቱ ሻእቢያ ጋር ጀርመን ላይ የተወያየው ወያኔ ግንቦት ሰባት የራስ ምታት ስለሆነበት እንዲያደራድረው አሊያም እንዲገላግለው ተማጽኖ ቢሆንስ??? ወይኔ ሻእቢያ የሚፈልጋቸውን ተቃዋሚ ኤርትራውያንን እያፈነ እንደሚሰጥ የህን ሰሞን ሃተታዎች እየጠቆሙ ነው እንዲሁም በሱዳን በኩል እያሽከረከረም እንደሚያስረክብ::ነገሩ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው ….
የአቶ ታምራት ላይኔም ወደ ፖለቲካው ለመቀላቀል ማቆብቆብ እኮ የዚሁ የድርድር አንዱ አካል ነው:; ብኣዴን ታምራት ላይኔን ይፈልገዋል:: አገሬ በፈለገችኝ ሰአት ለማገልገል ተዘጋጂቻለሁ የሚለው ታምራት ጠጋ በል እየተባል መሆኑስ የወያኔ አንድ የጭንቀት ምልክት አይደል?! … ወደ ሚዲያዎች አያሰገገ መምጣቱ ሌላ ምስጢር የለውም::

አና ጎሜዝ ከአዲስ አበባው ቆይታቸው ሁለት ንግግሮችን ከአንደበታቸው ሰምተናል:: አንዱ “ከባለስልጣናት ጋር ያደረኩት ውይይት በጎ እና ገንቢ ነው መልካም ምላሽ እንዳገኙም በእርካታ ተናግረዋል:; በመተማመን ስሜት ደሞ “አዲስ ንፋስ አለ” ሲሉ ተስፋቸውን አብርተዋል:: ይህንን የፖለቲካ ስሜታቸውን ያልተረዱ የደፈናው ጋዜጠኞች የወያኔን የሞተ እስትንፋስ ሊያበረቱ ቢሞክሩም የሚሳካ ካለመሆኑም ሌላ ወያኔም …ጌታ….ተላላኪ…;;እያለ ቢዘላብድም ታምኝነት ሊያገኝ አልቻለም:: አና ጎሜዝ ይህንን ሲናገሩ ከባለስልጣናት አንደበት የሰሙት እና የተላኩት መልእክት እንዳለ ይጠቁማል:: አና ጎሜዝ ወደ ግንቦት ሰባት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ጠያቂዎችም የብሄራዊ ድርድርን ጉዳይ አስረግጠው አዋይተዋል:;በእርግጥ ስለግንንቦት ሰባት ባያነሱም ይህ የእንደራደር ጥያቄ የመልስ ምቱን ወያኔ ለማወቅ ፈልጎ ያደረገው ሊሆን የሚችል የማጭበርበሪያ የፖለቲካ ስልት ቢሆንም የድርድሩ ጥያቄ ግን የአና ጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ እና የአዲስ ነፋስ ምልክታን ተከትሎ መነገሩ እውነታውን ያጎላዋል:; ይህ የሚያሳፍረው ወያኔን ቢሆንም ወያኔ ግን ምንተእፍረቱን አይኑን በጨው አጥቦ ቢክድም አሁንም ግንቦት ሰባትን እንዲያደራድሩት ከትን እንዲያደበጀርባ እየተለማመጠ እንደሚገኝ ለማስገንዘብ እወዳለሁ:: #MinilikSalsawiምንሊክሳልሳዊ

እነ ሌኒን በሚሉት መልኩ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የሚባለው አገራችን ውስጥ የለም፡፡ የስታሊን ጠባብ ብሄርተኝነት፣ የምዕባራዊያኑ ‹‹ካፒታሊዝምና ዴሞክራሲ›› በስም ደረጃ፣ የአልባኒያና የቻይና አምባገነንነት፣ የሻዕቢያና አረብ አገራት ጥላቻ፣ የሞሶሎኒ ፋሽዝም……ተደባልቀው የተሰራ ውጥንቅጡ የጠፋበት ‹‹ርዕዮት ዓለም›› ነው፡፡ የአሁኑ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከሁሉም ጎን የወሰደው መጥፎ ጎናቸውን እንጅ መልካሙን አይደለም፡፡ እነዚህ የየዘመኑን ትውልድ ያሰከሩ አስተሳሰቦችን መጠናቸውን ሳያውቅ የደባለቀው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከአልኮንነትም አልፎ መርዝ ወደመሆን ደርሷል፡፡ አልኮል ብቻውን ከሚወሰደው በላይ ሲደባለቅ ያሰክራል፡፡ ያሳብዳልም፡፡

ፋሽስቶች ለኢትዮጵያውያንና ለሌሎች ካልሆነ በስተቀር ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ እነ ሌኒንም ቢሆን ለአገራቸው አንድነት እንጅ ተገንጣይነት አልሰሩም፡፡ አረቦቹ ለአገራቸው ጥቅም ሲሉ ነው ኢትዮጵያን ይጠሉ የነበሩት፡፡ የአስተሳሰባቸው መርዝነት ለእኛ እንጅ ለራሳቸው ህዝብ አልነበረም፡፡ ምንም ያህል ቢያብዱና ቢሰክሩ ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ ለብሄራዊ ጥቅማቸው ይጨነቁ ነበር፡፡

ድብልቅልቁ የወጣው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ግን ኢህአዴግን ጨርቁን አስጥሎታል፡፡ ለዛም ነው ይህን ያህል ያበዱት የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠን ስንት ቢሆን ነው?›› ብየ የጠየቁት፡፡ ከወራት በፊት ለግራዚያ ሲቆም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምን ያህል እንደሚያሰክር፣ እንደሚያሰብድ አሰይቶናል፡፡ ይህ ከእነ ሞሶሎኒ የተወሰደው የአልኮል ክፍል መሆኑ ነው፡፡ ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያንን በአረብ ዱላ ገረፈ፡፡ ይህኛው ከአረቦቹ ጥላቻ የተዘነቀው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አልኮል ነው፡፡ አሁን ደግሞ የአጤ ምኒልክን ሙት አመት አታከብሩም ብሎ ከልክሏል፡፡ ይህኛው የሁሉም ውጤት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ መጨረሻ ቀላቅሎ ያለ አቅሙ አይኑን ጨፍኖ የተጎነጨው ይህኛውን አልኮል ነው፡፡ ጸረ ኢትዮጵያውይነት! የአሁኑ ጣሊያኖች የምኒልክ ታሪክ እንዳይወደስ የሚፈልጉበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡

በግራዚያኒ ላይ የጣሊያን ግራ ዘመም ፓርቲዎች በነጻነት ተቃውሞ አሰምተው በሰላም ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግንወገኖቻቸው በተጨፈጨፉበት ጎዳና እንደገና ተደብድበዋል፡፡ ታስረዋል፡፡ ይህ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተለከፈ መንግስት ከያኔው ጨፍጫፊዎችም በላይ ይሆንብኛል፡፡ ስካር ሱስ ነው፡፡ በሽታም ጭምር፡፡ እንዲህ የጠደባለቀ መርዛማ አልኮል መጎንጨትን ልማዱ ያደረገ ድሮ ሰክሮ የሚሰራውን ጉዳይ ምሎና ተዘክሮ እተዋለሁ ቢልም የሚሰራው ግን ያው የስካሩን፣ የእብደት ተግባሩን ነው፡፡ ለግራዚያኒ የቆመው ኢህአዴግ ከውስጥም ከውጭም ተቃውሞ ሲገጥመው ስህተቱ ስካሩ መሆኑን ሳይረዳው ቀርቶ አይደልም፡፡ ግን ለሳውዲዎች ቆሞ ደገመው፡፡

አሁን ደገሞ ለድሮዎቹ፣ አድዋ ላይ ለተሸነፊት ጣሊያኖች ቆሞ ከለከለ፡፡ ኢህአዴግ ከአረቦቹ፣ ከፋሽስቶቹ፣ ከእነ ስታሊን….የደባለቀውን የውስጡን ጥላቻ በአብዮታዊ ዴሞክራሲው አልኮል አወጣው፡፡ ይህን ታዲያ ከስካርና ከእብደት ውጭ ምን ይሉታል? እኔ ይህን ናላ አስቶ፣ ጨርቅ አስጥሎ በአገር ህዝብ ላይ የሚያዘምት፣ ህዝብ ላይ የሚያስጨክን፣ ብሄራዊ ጥቅምን የሚያስጠላ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠኑን መገመት አልቻልኩም፡፡ ከመጠን በላይ መሆኑን፣ መርዛማነቱ ማመዘኑን ከመገመት ውጭ! ግን ኢህአዴግ እስከመቼ እንዲህ ጨርቁን ጥሎ ይዘልብናል?

ሴራ የአምባገነኖች ዋነኛ መሳሪያ ነው፡፡

ህዝብን ለማወናበድመ ትኩረት ለማስቀየር፣ ለመከፋፈል በአጠቃላይ ዋነኛ መግዢያ መሳሪያ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ምንም ይሁን ምን ሴራ ካልሰሩ ስልጣን ላይ የሚኖሩ አይመስላቸውም፡፡ አምባገነኖች የሴራ ሱስ ጠጠቂዎች ናቸው፡፡ ከወራት በፊት ነው፡፡ ኢቲቪ ስለ ስደት ተደጋጋሚ ዘገባዎችን፣ ዶክመንተሪዎችን ማሳየት ተያይዞት ነበር፡፡ ከዛም የሳውዲ አረቢያ መንግስት ስደተኞች እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፉ ተሰማ፡፡ ይህን ተከትሎ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት በህጋዊ መንገድ የሚሄዱትንም ጭምር አገደ፡፡

ለባለስልጣናት እንደ ምትታለብ ላም የሚቆጠሩት ኤጀንሲዎችም ሳይቀር ስራ እንዲያቆሙ ተነገራቸው፡፡ በጊዜያውይነትም ታገደ፡፡ ብቻ እዚህ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት አንድ ያሳሰበው ነገር እንዳለ ማየት ይቻላል፡፡ ለስደተኞች አዝኖ እንዳልሆነ በስተመጨረሻ የደረሰውን ሰቆቃና ሰቆቃው ሲደርስ የወሰደው የረባ እርምጃ አለመኖሩ ያስረግጣል፡፡ እኔ በበኩሉ አንድ ሴራ ይታየኛል፡፡ በዓረቡ አለም የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ልክ በአሜሪካና አውሮፓ እንደሚኖረው ዲያስፖራ የተቃውሞ ምንጭ መሆን ጀምረዋል፡፡ እንዲያውም በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ድህረ ገጽ የሚንቀሳቀሱት በአረቡ አለም የሚገኙት ወገኖቻችን ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ደግሞ የአይበገሬው ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› አባላት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የዚህን ቡድን ድምጽ ሲሰማ ይበርክካል፡፡ ጭንቅ ይለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ‹‹አማካሪ›› ነን ባዮች የኢትዮጵያን ስደተኞች የድምጻችን ይሰማን ጨምሮ የተቃውሞ ጎራውን የሚያጠናክሩ መሆናቸውን አምነዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ግን መንግስት የሚወቅሰውን አክራሪነት መሳሪያ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው አስበዋል፡፡ ያው ‹‹አማካሪ›› ነን ባዮቹ የሚናገሩት መንግስት ሊሰማ የሚፈልገውን ነውና የሚፈሩትን ለጥፈውባቸዋል፡፡ ሳውዲዎች ደግሞ ስራ አጣን ብለው እያማረሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ላይ ያላቸው ጥላቻ እና ከመንግስቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ስደተኞቹን እንደ ጠላት ያዩዋቸዋል፡፡ ያም ሆኖ ኢትዮጵያውን ከስደታቸው አልቆሙም ነበር፡፡ እናም አንዳች ነገር መደገስ ነበረባቸው፡፡ ስደተኞቹ በተለይም የመንግስት አማካሪ ነን ባዮች ‹‹አክራሪዎች›› ይፈለፈሉባታል ከሚሏት ሳውዲ ‹‹አይቀጡ ቅጣት›› ተቀጥተው እንዲመሰሉ ማድረግ፡፡ ሌሎች እንዳይሄዱ ‹‹ትምህርት›› መስጠት፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለተመላሾች በሚያደርገው ‹‹ድጋፍም›› የሆነች ጥቅም እንደሚያገኝበት ገምቷል፡፡ ታዲያ ኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ለምን ደረሰ? በሳውዲ መንግስት ላይ ምንም አይነት ጫል አልተደረገም? መንግስት ለምን ትክክለኛ እርምጃ ለመውሰድ ተደናረ? ለምንስ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉትን ደበደበ? የሀይለማሪያም ደሳለኝ ዝምታስ? ሌላ ሴራ ከትናንትና በፊት መቀሌ ከአንዴም ሶስቴ መንደዷን ሰማን፡፡ ከዛም መርካቶ፡፡ አሁንም ቢሆን ይህ ለኢህአዴግ መቀመጫ የነሳው ሙስሊም የሚበዛበት አካባቢ ነው፡፡ መርካቶ የእንቅስቃሴው መሰረት ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ቢደርስ ትኩረት ሊስብ ይችላል በሚል መቀሌን ቀድመው ያነደዷት ይመስለኛል፡፡ ደግሞ በሁለቱም ከተማ የወደሙት ሱቆች ናቸው፡፡ ለምን? የንግዱን ማህበረሰብ ለማሸበር? ትኩረትን ከጅጅጋ ወደ አዲስ አበባና መቀሌ ለማስቀየስ? ‹‹አክራዎችን ገቢ ለማሳጣት››? ማን ያውቃል ‹‹አማካሪዎቹ›› የማይዘይዱት አይኖርም፡፡ ሁሉም ድራማ ነው፡፡

እሳቱ በቁጥጥር ስራ ሳይውል በቁጥጥር ስር ዋለ ማለቱን ለምን አስፈለገ? በቅርቡ ኢህአዴግ ከአማካሪዎቹ ‹‹49 በመቶ በላይ የኑሮ ውድነት ይከሰታል፡፡›› ተብሎ እንደተነገረው ተሰምቷል፡፡ በክርክር ላይ ናቸውም ተብሏል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ምክንያት ከተባሉት መካከል ደግሞ ‹‹ከ39 አይበልጡም!›› የሚባሉት የመርካቶ ነጋዴዎች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ነጋዴዎች ‹‹ድምጻችን ይሰማ››፣ በኑሮ ውድነትም ይከሷቸዋል፡፡ ብቻ ሴራው ይታየኛል፡፡ አምባገነኖች ከገቡበት ማጥ ለመውጣት ሴራን ዋናው ስልታቸው ያደርጋሉ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ውጤትና ምክንያቱን ሳይመዝኑ የተለከፉበትን ሴራ ይሸርባሉ፡፡ በተራ ግለሰባዊ ጠብ፣ በጥላቻ አገርና ህዝብ ያቃጥላሉ፡፡ ይወራሉ፡፡ ጦርነት ያስጀምራሉ፡፡ በሽታ እንዲቀሰቀስ ያደርጋሉ፡፡ ዞረው የመፍትሄው አካል መስለው ይታያሉ፡፡ ይለምኑበታል፡፡ የዜጎቻችን ሰቆቃና የከተሞቻችን ቃጠሎ ሴራ ሴራ ይሸተኛል፡፡ ይህ መንግስት እኮ ሀውዜንን ማስጨፍጨፉን የቀድሞ አባላቱ ተናግረዋል፡፡ የአበበች ደራራን አባት መግደሉን ካድሬዎቹ መስክረዋል፡፡ የደሴውን ሸክ መግደሉን ህዝብ እየተናገረ ነው፡፡ አንድ ቀን የሚወጣ ይሆናል፡፡

እሳት አደጋ ሰራቶኞች 50000 ብር ግቦ ተቀብለዋል ::
ከቀኑ በስምንት ሰአት የጀመረ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰአት ድረስ አልተቆጣተሩትም ::

የእሳቱን ጪስ መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ በያለበት በሀዘን ሲመለከተው ነጋዴዎች ንብረታቸው መቃጠሉ ሳያንስ በዱላ ተደብድበዋል ፡፡

የእሳት አደጋው መንስኤ በገለልተኝ አካላት አስኪጣራ ምንም ከማለት መቆጠቡ አስፈላጊ ቢሆንም ሀላፊነት የሚሰማው ለህዝብ መሰዋትመት የሚከፍል የድንገተኝ አደጋዎችን የሚቆጣጠር የመንግስት አካል አለሞኖሩ ህብረተሰባችንን በጣሙን ያሣዘነ ሆኖ አልፏል ፡፡ የእሳትና ድንገተኝ አደጋ ሰራተኞች እሳቱ ልክ ከቀኑ በ 8 ሰአት እንደተቀሰቀሰ መረጃው ቢደርሳቸውም ቦታው የደረሱት 9 ሰአት ላይ መሆኑ ያበሳጫቸው የአካባቢው ነዳዴዎች እቃቸውን ለማሸሽ በሚያደርጉት ትግል ብዙዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል::

በተጨማሪም በቦታው ቀደም ብለው የደረሱ የፌደራል ፖሊሶች እሳቱን ለማጥፋት ህብረተሰቡን ከማስተባበርና ይበልጥ ጉዳት እንዳያደርስ ከመከላከል ይልቅ የአካባቢውን ነጋዴዎችና
እሳቱን ለማጥፋት የሚረበረቡትን በዱላ እየደበደቡ ሲያባርሩ ተስተውለዋል ፡፡ ከዚህ በባሰ መንግስት የለም ወይ የሚያስብለው የእሳትና የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች እቦታው ደርስው መኪናቸው ውስጥ
ዝም ብለው ሲቀመጡ በንዴት ንብረጃቸውን ለማሸሽ ተንደርድረው ወደሱቃቸው የገቡትን ነጋዴዎች በውሃ ገፍትረው የጣሉዋቸው ሲሆን እነዘህም ነጋዴዎች በተክላሀይማኖት ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ ፡፡

ብር ካልተሰጣቸው እንደማያጠፉ የተረዱት 2 ነጋዴዎች ሀምሳ ሺህ ብር አዋጥተው እንደሰጦቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለአደጋው መባባስ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂው የመንግስት አካላት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው ፡፡ስምንት ሰአት ሙሉ መርካቶ በቃጠሎ ውስጥ የነበረች ሲሆን የሁለት ብሎኮች ንብረቶችም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ፡፡የእሳቱን ጪስ መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ በያለበት በሀዘን ሲመለከተው አምሽቷል፡፡ እሳቱን ማቆም የተቻለው ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ መሆኑንም
አየይን እማኞች አክለው ገልጸዋል ፡፡

የኑሮ ውድነት 40% ይጨምራል የሚል ጥናት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቀረበ::
በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ውንብድና ተስፋፍቷል::
የስራ አጦች መስፋፋት ሃገሪቱን የወንጀል መናኸሪያ እያደረጋት ነው::

የኢሕኣዴግ ኢኮኖሚስቶች በወረደላቸው መመሪያ በጋራ እና በተናጠል ባደረጉት ጥናት መሰረት በአገሪቱ በተለይ በከተሞች አከባቢ የኑሮ ውድነት በ40% ይጨምራል ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የፖሊሲ ጥናት ቡድን የጥናት ሪፖርታቸውን ያቀረቡ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::

የጥናት ሪፖርቱን ያቀረቡት የወያኔው ኤክስፐርቶች መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በድጋሚ እንዲፈተሽ እና ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ሲያሳውቁ በአገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና እንቅስቃሴ ዋነኛው የኢኮኖሚው ማነቆ ከመሆኑም በላይ የፍትህ እና የንግድ ስርኣቱ መላሸቅ የኢኮኖሚ ቁጥጥሩን ስላላው ለዋጋ ንረቱ መንስኤ ናቸው ብለዋል::መንግስት ለግሉ ዘርፍ ያለው አመለካከት ደካማ መሆኑ እና ከፖለቲካ ባለስልጣናት ጋር ቁርኝት ያላቸው ነጋዴዎች ለመክበር የሚያደርጉት ሩጫ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጣራ እንዲነካ አድርገውታል::እንዲሁም የኢኮኖሚ ውንብድና በሃገሪቱ ላይ እየተፈጸመ ነው::የስራ አጦች ቁጥር መጨመር ሃገሪቱን የወንጀለኞች መናኸሪያ እያደረጋት ነው::

በአላቂ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ይከሰታል በሃገር ውስጥ ምርቶች ላይም ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ በሚቀጥለው አንድ አመት ይመጣል ያለው ጥናት የግሉ አምራች ዘርፍ ጥሬ እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ የተወሰነ የቀረጥ ክፍያ አለመኖሩ እና የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሰኛቸው በየጊዜው እየቀያየሩ የህገር ውስጥ ምርቶች እንዲጎዱ የማኑፋክቸሪውም ዘርፍ እንዲዳከም በማድረግ ችግር እንዲፈጠር አድርገዋል::

ጥናቱ የባንኮችን መዳከም የስራ አጥነትን የስደትን የፖለቲካ ተጽእኖን የህዝቡን አስተያየት እና የገበሬውን ምሬት አጠቃሎ የያዘ መሆኑ የጠቆሙት ምንጮቹ መንግስት በሞኖፖል ንግዱን ይዞታል የውጪ ዜጎች ህገወጥ የኢኮኖሚ ስርኣት ዘርግተዋል ከፍተኛ ብዝበዛ በሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ እየተደረገ ነው የሚሉ ዝርዝር ጥናቱን አቅርቧል:: ጥናቱ ይፋ ለውይይት ይቅረብ አይቅረብ የሚለው ገና ያልተወሰነ ሲሆን የጥናቱን ዝርዝር መረጃው ከምንጮቻችን እንደደረሰን የምናቀርበው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን::

በእስራኤል ሃገር በአቶ ፋሲል ለገሰ የሚመራው IETV ወይንም ሁለተኛው ETV ሲመሰረት አላማው ኢትዮ-እስራኤሎችን በሙሉ ልቡ ህብረተሰብ ነክ ችግሮችን በማካተት ለህብረተሰቡ ይጠቅማሉ ብሎ ዓላማ ያደረጋቸውን ለምሳሌ፤- እኛ ኢትዮ-እስራኤሎችን እንዴት ከሰለጠነው ህብረተሰብ ጋር ማቀራረብ እንዳለበት እንዲሁም ባህላችንና ቋንቋችን ለ እስራኤል ህብረተሰብ በቀላሉ እንደ ድልድይ ሁኖ ለማገልገል በ እስራኤል መንግስት አመታዊ በጀት ተመድቦለት ጣቢያው አየር ላይ ከዋለ እንሆ ሦስት አመታትን አሳልፏል።
Image
ነገር ግን ዓላማውን ስቶ ለኢትዮጵያ መንግስት ፕሮፖጋንዳነት በማዋል ጭራሽ የኢትዮጵያን አምባሳደር በየሳምንቱ እያቀረበ ስለ ኢትዮጵያ “ግምታዊ” እድገት ስለ አምስት አመቱ ትራንስፎርሜሽን ስለአባይ ግድብ እና ግንቦት 7 የአሸባሪ ቡድን እንደሆነ እነሱን ከቀረብን የኢትዮጵያ መንግስት ለፍርድ እንደሚያቀርበን ፡እንደነዚህ አይነት ገደብ የለሽ ፕሮግራሞች ይቀርቡልናል ። አቶ ፋሲል ለገሰ በመጀመሪያ ይህን አስተሳሰብዎትን መቀየር መቻል ይኖርቦታል። አንድ ህብረተሰብ ወስዶ እንደህፃን ልጅ ዋ.. ብሎ የሚያስፈራሩባት ያሻዎትን የሚያደርጉበት ኢትዮጵያ አይደለችም ። እስራኤል ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሃገር ውስጥ ነው ያለነው፡ ምንም እንኳን የፓርቲው ደጋፊና አቀንቃኝ እንደሆኑ የታወቅ ቢሆንም ጋዜጠኛ በሚለው ሙያ ላይ ጋዜጠኛ ለመባል ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ ትንሾችን ለማድረግ ይሞክሩ።

ስለዚህ እኔ በግሌ የምሰጥዎት አስተያየት ቢኖር ነገሩ ለኢትዮ-እስራኤላውያን በቅቷል ። ይመለሱና ህብረተሰቡን ቃል በገቡበት መሰርት ያገልግሉ አዎ ህብረተሰቡ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ አያገባህም ከተባለ እስዎም አያገባዎትም ። ወይንም ለሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች እና ፓርቲዎች በእኩልነት አገልግሎት ይሰጥ።

የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

Image

በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡

እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?

ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!

#MinilikSalsawi

‹‹መጀመሪያ በ‹‹አማራው›› ላይ መጡ ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ‹‹አማራ›› አልነበርኩም፡፡ ቀጥለው ‹‹በኦሮሞ›› ላይ መጡ ምንም አላልኩም ምክንያቱም ‹‹ኦሮሞ›› አልነበርኩም፡፡ በመቀጠል ‹‹በሶማሊው፣ በጋምቤላው፣በትግሬው….ላይ መጡበት ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ከአንዳቸውም አልነበርኩም ከዚህ በመቀጠል በሙስሊሙ ላይ መጡ አሁንም ምንም አላልኩም ምክንያቱም ሙስሊም አልነበርኩም በመቀጠል በክርስቲያኖቹ ላይ መጡ ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ክርስቲያን አልነበርኩም በስተመጨረሻ በእኔ ላይ መጡብኝ አሁን ለእኔ የሚቆምልኝ ማንም አልቀረም፡፡ ብቻዬን ነኝ!››

ይህ በናዚዎች ስር የነበረው ህዝብ ታሪክ ነው፡፡ በአምባገነኖች ስር ያለና የነበረ ህዝብ ታሪክ ነው፡፡ የእኛው የኢትዮጵያውያን የወቅቱ ችግር ነው፡፡ኒይሞለር በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፈና የናዚ ቀንደኛ ደጋፊ የነበር የፕሮቴስታንት ፓስተር ነበር፡፡ ጨፍጫፊው ናዚ ለጀርመናውያን እቆማለሁ ቢልም በሀሳብ የተለዩትን ጀርመናዊያን ላይ ግን ጠንካራ ብትሩን አሳርፎባቸዋል፡፡ እናም ኮሚኒስት፣ ሶሻሊስት፣ ቤተ እስራኤላዊያን፣ የሰራተኛ ማህበራት….ሌላም ሌላም ከናዚ አስተሳሰብ የሚቃረኑት በሙሉ በየተራ እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ በዛ ዘመን አንዱ ላይ እርምጃ ሲወሰድ ሌላው ዝም በማለቱ ናዚዎች የሚፈልጉትን ሁሉ በግፍ ጨፍጭፈዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት የፕሮቴስታንቱ ፓስተር ማርቲን ኒይሞለር የሂትለርና የናዚ ደጋፊ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኮሚኒስት፣ ሶሻሊስት፣ ቤተ እስራኤላዊያን፣ የሰራተኛ ማህበራት… የሚባሉት መካከል ብዙዎቹ ከፕሮቴስታንት ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው እንደ ጠላት አይቷቸዋል፡፡ ፓስተሩ ሂትለር ኮሚኒስቶቹን ሲያዝር፣ ሲገድል፣ ሲያግዝ ‹‹እግዚያብሄር አይወደውም፣ እነሱም ጀርመናውያን ናቸው፣ ይቅር ተባባሉ፣ ተቀራረቡ›› ከማለት ይልቅ እግዚያብሄር የማይወደውን እግፍ በአይኑ እያየ ዝምታን መረጠ፡፡

ናዚ ያልዳሰሰው የህብረተሰብ ክፍል፣ ካድሬ ለማድረግ ያልጣረው ጀርመናዊ፣ ከጎኑ ለማሰለፍ ያልሞከረው መሪ አልነበረምና በስተመጨረሻ ወደ እምነት ተቋማት ማምራቱ የግድ ነበር፡፡ እናም ፕሮቴትታንትም ቤተ ክርስቲያንም ከመጽሃፍ ቅዱስ ይልቅ የናዚን ‹‹ዶክትሪን›› እንድትቀበል ተገደደች፡፡ ልክ እንደኛው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ማለት ነው፡፡ ናዚን አድንቆ የገባውን ካድሬ ‹‹የእምነት አባት›› እነ ሂትለር እጃቸውን ዘርግተው ተቀበሉት፡፡ በእምነታችን ጣልቃ ሊገባብን አይገባም ያሉት ግን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተዋል፡፡

ማርቲን ኒይሞለር የናዚን ‹‹ዶክትሪን‹‹ አልቀበልም ካሉት ‹‹አባቶች‹‹ መካከል አንዱ ነበር፡፡ ናዚ ሲያሰቃያቸው ዝም ብሎ ያያቸው ቤተ እስራኤላዊያን፣ ኮሚኒስቶች፣ ሶሻሊስቶች፣ የንግዱ ማህበራት…..የደረሰባቸው እጣ ፈንታ አሁን እሱ ጋ ደርሳለች፡፡ ከሌሎቹ ጋር ባለመተባበሩ ብቻውን ቀረ፡፡ ናዚዎች አስረው ሲያሰቃዩት ኖረው የተፈታው ጥምር ጦሩ ከአሸነፈ በኋላ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ፓስተር ከስቃዩ በኋላ በእጅጉ ተጸጽቷል፡፡ እ.ኤ.አ እስከ 1984 ድረስ ስለ ሰላም ሰብኳል፡፡ ይህ ሰው ከሚታወቅባቸው መካከል ዝምታ አንድ በአንድ እንደሚያስጨርስ በእስር ዘመኑ የተናገረውና መግቢያየ ላይ ወደ እኛው ሁኔታ አጠጋግቼ የጠቀስኩት ወርቃማ አባባል ነው፡፡ እሱ ቃል በቃል ያለው እንዲህ ነበር፡፡

‹‹First they came for the communists, and I didn’t speak out because I wasn’t a communist. Then they came for the socialists, and I didn’t speak out because I wasn’t a socialist. Then they came for the trade unionists, and I didn’t speak out because I wasn’t a trade unionist. Then they came for me and there was no one left to speak for me.››

ይህ አባባል ከሌላ ብሄር፣ እምነት ወይንም ሌላ ማንነት ውስጥ ነኝ ብሎ በሌሎች ላይ የሚደረጉትን ጥቃቶች በቸልታ ለሚያልፍ አሊያም ከላይ የተጠቀሱት ‹‹ማንነቶች›› ውስጥም ሆኖ ግድ ለማይሰጠው ሰው ሁሉ የሚያገለግል ነው፡፡ በሌሎች ላይ የሚደረግን በዝምታ ሲያልፍ ኖሮ በስተመጨረሻ አብሮት የሚቆም አጥቶ በብቸኝነት ለሚጨቆን ሁሉ የተነገረ ነው፡፡

በእኛ አገር በአንዱ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ችግር ሲደርስ ሌላኛው ዝምታን ይመርጣል፡፡በእምነትም ቢሆን ተመሳሳይ ነው፡፡ ሙስሊሙ ሲነካ፣ ኦርቶዶክሱ ስለ መርህ፣ ስለመብት አብሮ አይጮህም፡፡ ሙስሊሙ፣ ፕሮቴስታንቱምና ካቶሊኩም የሚያደርገው ተመሳሳይ ነው፡፡ በተቃዋሚዎቻችን ሰፈር ደግሞ ይብሳል፡፡

በአገራችን ከሚነገሩት አሉታዊ አባባሎች መካከል ዝምታን የሚያበረታቱት በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሌሎች በሚደርስባቸው ችግር ይቅርና በራሳችን ጉዳይ ዝምታን በመምረጥ ኢትዮጵያውያን ባህላችን አድርገነዋል፡፡ ዝምታ ወርቅ ነው፣ ዝም አይነቅዝም፣ ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባበትም፣ ዝምን ማን ወሰደው፣ ብንናገር እናልቃለን…. እና በርካቶች ዝምታን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ ከመናገር ይልቅ ዝምታን የሚመርጠው ይህ ባህላችን ‹‹መቻል!›› የሚባል ቃልንም በምሳሌነት፣ በስምነትና በሌላም መልኩ በስፋት ይጠቀምበታል፡፡ ገዳይ ባህል!

የጀርመኑ ፓስተር የናዚ ቀንደኛ ደጋፊ ነበር፡፡ መጨረሻ ግን የሂትለር ዱላ ያመራው ወደሱው ነው፡፡ እንዲያውም ስቃዩን በወጉ የሚያይለት፣ ለዚህ ስቃዩ የሚቆረቆርለት አላገኘም፡፡ ደጋፊ፣ ካድሬ…..ም ቢሆን ስለ አንድ ብሄር፣ እምነት፣ ቋንቋ፣ ሙያ፣ አሊያም ስለ ራሱ ከዚህም ወረድ ሲል ፈርቶ ዝም ቢል የመጨረሻው መዓት እሱ ላይ ማረፉ የማይቀር ነው፡፡ የአሁኑን ጨምሮ ከገዥው ጋር የተሰለፉ ፖለቲከኞች፣ ካድሬዎች፣ ደጋፊዎችና ሌሎች አካላትም በስተመጨረሻ በትሩ ያረፈው እራሳቸው ላይ ነው፡፡

በቃ! የዝምታችን አባዜ ይህ ነው ትርፉ፡፡ ልክ እንደዚያ ቄስ፣ ልክ እንደኛ ፖለቲከኞች፣ ልክ እንደአገራችን የእምነት ተቋማት፣ እንደ ማህበራት፣ ምሁራን፣ ልክ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተለመደ ተግባር ዝምታ፣ ‹‹ምን አገባኝ!››፣ የፖለቲካ እሳትነት ብቻችን ያስበላናል፡፡ አስበልቶናልም፡፡ ማንም ስቃያችን ሳያይልን፣ ማንም ሳይጮህልን፣ ማንም ሳይቆምልን ያስፈጀናል፡፡ ያስጨርሰናል፡፡ ዝምታ ከወርቅ ይልቅ እንደሚያበሰብስ፣ እንደሚነቅዝና እንደሚያነቅዝ የምናውቀው ብቻችን እጣ ፈንታችን ሰንጎነጫት ነው፡፡ በጣም እጅግ በጣም ከመሸ!

“እነ አቶ ልደቱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ነው ያደረጉን”

ዶ/ር ኃይሉ አርአያ

ዶ/ር ኃይሉ አርአያ በኢዴፓ በኋላም በቅንጅት አመራርነት አገልግለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአንድነት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ የ”ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ከዶ/ር ኃይሉ አርአያ ጋር ሰፊ ቃለመጠይቅ አድርጓል፡፡ በሃገር ቤት የሚታተመውን ሎሚ መጽሄት በውጭ ሃገር ለማታገኙት ወገኖች ቃለምልልሱን ዘ-ሐበሻ ትካፈሉት ዘንድ አስተናግዳዋለች።

ሎሚ፡- እርስዎ ያዘጋጁዋት የነበረችው “ፕሬስ ዳይጀስት” ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ ኢትዮጵያን በተመለከት መረጃ የሚሰጥ “ታብሎይድ” ነበር፡፡ የትንሿን ጋዜጣ ዝግጅት ለምን አቋረጡት?

ዶ/ር ኃይሉ፡- ጋዜጣዋ አሁንም እየተዘጋጀች ነው፡፡ እኔ ግን ያቋረጥኩት ጋዜጣዋ የምትፈልገውን ጊዜ እና ጥረት ማበርከት ባለመቻሌ ነው፡፡ በአጭሩ ብዙ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ዝግጅቱ ብዙ ጊዜ የመጠየቁን ያህል ደግሞ ብዙ ጥቅምም አያስገኝም፡፡ ከዚያም ባሻገር ስራው የሦስት ሰዎች ስራ ነበር፡፡ ግን የሦስት ሰዎችን ጥረት የሚጠይቅ ስራ አልነበረም፡፡ በዚያን ጊዜ ሌላ የምሰራው ስራ ስላልነበረ ሁላችንም ትንሽ ትንሽ እየሰራን ነበር የምናሣልፈው፡፡ የአንድ ሰው ስራ ነው፡፡ የአንድ ሰውም የሙሉ ጊዜ ስራ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ጊዜ ከማባከን ያንን ለአንድ ሰው ትቶ ሌሎቻችን ሌላ ስራ ብንሰራ ይሻላል በሚል ነው የተውነው፡፡
ሎሚ፡- በደርግ ዘመን “የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲቲዩት” ኃላፊ እርስዎ እንደነበሩ ይታወሳል፤ ኢንስቲቲዩቱ ምን አስተዋጽኦ አበረከተ? አሁን የብሔረሰብ መብት ተከብሯል ከሚባለው ጋር ሲያነጻጽሩት “የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲቲዩት” ሰርቶታል የሚሉትን አብይ ጉዳይ ሊገልፁልን ይችላሉ?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በመጀመሪያ የኢንስቲቲዩቱ ኃላፊ አልነበርኩም፡፡ ኢንስቲቲዩቱ ራሱ ኃላፊ ነበረው፡፡ እንደውም ኃላፊው የሚኒስትር ማዕረግ ነበረው፡፡ በኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የብሔረሰቦች ጉዳይ መምሪያ በሚባለው ቦታ በምክትል ኃላፊነት ነበር የምሰራው፡፡ ያ መምሪያ ነው ተቋሙን ያቋቋመው፡፡ ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ነበሩ፤ ጥናቶች ነበሩ፤ ሕገ መንግስቱን ለማዘጋጀት ብዙ ጥናቶች መደረግ ነበረባቸው፡፡ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የነበረው የኛ መምሪያ ብዙ ስራ ሊሰራ ስለማይችል የግዴታ ራሱን ችሎ ለመንቀሣቀስ “ኢንስቲቲዩቱን” መመስረት አስፈላጊ ነበር፡፡ ስለዚህ “የብሔረሰቦች ጥናት” ኢንስቲቲዩት ተቋቋመ፡፡ ነገር ግን በመምሪያችን ስር ነበር፡፡
የእኛ መምሪያና ኢንስቲቲዩቱ አብረው ነበር የሚሰሩት፡፡ ጥናቶች ሲካሄዱ አብረን ሁላችንም እንሳተፋለን፤ አመራር የሚሰጠው ግን ከመምሪያው ነበር፡፡ በሁሉም ዘርፍ ለአምስት ዓመት ያህል ነው ኢንስቲቲዩቱ ጥናት ያካሄደው፡፡ በዛን ጊዜ የተሰሩ ስራዎች ኢህአዴግም ከመጣ በኋላ ብዙ ጠቅሞታል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ያኔ የህግ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ሰው አሁን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሉ ይመስለኛል፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህግ አማካሪ ናቸው፡፡ ሌሎችም በሀገሪቱ አሉ የተባሉ ምሁራን ተሰባስበው ከፍተኛ ጥናት አካሂደዋል፡፡ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ጥናቶች ናቸው የተካሄዱት፡፡ ጥናቶቹ አልባከኑም ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ የተፈለገው ሕገ መንግስት በተደረጉት ጥናቶች መሠረት ተቀርጿል፡፡ መቅረፅ ብቻም አይደለም፤ ስራ ላይም ውሏል፡፡ በተለይ በብሔረሰቦች ላይ የተደረገው ጥናት በዝርዝር ነው የተካሄደው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የብሔረሰቦች መብት ምን ያህል ተከብሯል የሚለው የትኩረት መጠን ካልሆነ በስተቀር ያኔ የተደረገው የብሔረሰቦች ጥናት እና የተሰጠው የብሔረሰቦች ትኩረት በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስለ ብሔረሰቦች መብት መከበር እንደ አዲስ የጀመረ በማስመሰል ሲናገር ስሰማ በጣም አዝናለሁ፡፡ በዛን ጊዜ የነበረውን ነገር አልተከታተለውም፤ ውጊያ ላይ ስለነበር ሊከታተልም አይችልም፡፡ ውጊያ ላይ እያለ ባይከታተልም ስልጣኑን እና ኢንስቲቲዩሹኑን ከተረከበ በኋላ በዛን ጊዜ የነበሩ ሰነዶችን መመርመር ይችል ነበር፡፡ ሰነዶቹ አሁንም ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ኢህአዴግም ተጠቅሞባቸዋል ብዬ ነው የምገምተው፡፡
“የብሔረሰቦች መብት” ኢህአዴግ እንደ አዲስ የጀመረው ጉዳይ አይደለም፡፡ በባህላቸው፣ በቋንቋቸው…በሌላውም አቅጣጫ ኢህአዴግ እንደ አዲስ እንደጀመረ አድርጐ ነው የሚያወራው፡፡ ይህንን ትዝብት መቼም ለታሪክ እንተወዋለን፡፡ የደርግ ስርዓት ሌሎች ድክመቶች ሊኖሩበት ይችላል፡፡ የብሔረሰቦችን ጉዳይ በተመለከት ግን መሠረቱን ያስቀመጠው የደርግ ስርዓት ነው፡፡ ኢህአዴግ ምናልባት አጠናክሮታል፣ አስፋፍቶታል ማለት ይቻላል፡፡ አንደ አዲስ ጀመርኩት የሚለው ነገር ግን ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ይህ ሊስተካከል ይገባል፤ ምክንያቱም ታሪክ ራሱ ቁጭ ብሎ የሚመሰክርበት ጉዳይ ስለሆነ በዝምታ ማለፍ ነው የሚሻለው፡፡ የብሔረሰቦችን ጉዳይ በተመለከተ እንዲሁ ለይስሙላ ከሚደረግ በስተቀር ነፃ የሆነ ለውጥ ተደርጓል ብዬ አልገምትም፡፡ ምናልባት በጥቅም፣ በሀብት አከፋፈል በጀትን በተመለከተ ለብሔረሰቦች የሚመደበው ገንዘብ አሁን በከፍተኛ መጠን ጨምሯል፡፡ ሌላው የቅርፅ ጉዳይ ነው፡፡ ብሔረሰቦች የሕገ-መንግስት ባለቤት ሆነዋል፡፡ ህገመንግስትን መስርተዋል፤ ሕገ መንግስት አላቸው፤ ሰንደቅ አላማም ያውለበልባሉ…እነዚህ ከቅርፅ አኳያ ለውጦች ናቸው፡፡ እነዚህ የቅርፅ ለውጦች በተግባር ቢደገፉ ጥሩ ይሆኑ ነበር፡፡ ነገር ግን አልተደገፈም፡፡ ምክንያቱም ብሔረሰቦች አሁንም መሠረታዊ የሆኑ ችግሮች አሉባቸው፡፡ መሠረታዊ የምላቸው በኔ በኩል የህግ መከበር ነው፡፡
ህጐች ይጣሳሉ፤ መብቶች ይደፈራሉ፤ ምን ያህል ነፃነት እንዳላቸውም እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምንም እንኳን ስርዓቱ ፌዴራል ቢሆንም ቅርፁ ፌደራላዊ ቢሆንም በተግባር ግን “አሃዳዊ” ነው፤ ምክንያቱም በደርግ ጊዜ መንግስት “አሃዳዊ” ነበር፡፡ ክልሎች የአስተዳደር መብት ነበራቸው፡፡ ያም ቢሆን በሚገባ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ከይዘት አኳያ በደርግ አሃዳዊ መንግስትና በኢህአዴግ ፌደራላዊ መንግስት መካከል ልዩነት አለ፡፡ “ደርግ” የነበረው የውስጥ አስተዳደር ነው፤ የኢህአዴግ ግን ፌዴራል ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ብሔረሰቦች ሕገ መንግስት አላቸው፣ የራሣቸው መንግስትና ባንዲራ….አላቸው፡፡ በዛን ጊዜ የነበረው ኢሠፓ መዋቅሩን ታች ድረስ አውርዶ ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ኃይል እርሱ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ምንም እንኳን በቅርፅ “ፌደራላዊ” ቢባልም ሀገሪቱን ጠርንፎ በአሃዳዊ መልክ ነው የሚያስተዳድረው፡፡ በሁለቱ መካከል የይዘት ልዩነት የለም፡፡ ለውጡ ምንድነው? ብትለኝ ጥቂት ነው፡፡ እምቢልታና መለከት የሚያስነፉ አይደሉም፡፡ አሁንም ብሔረሰቦች ይጨቆናሉ፡፡
የሚጨቁኗቸው ደግሞ የራሣቸውን ቋንቋ የሚናገሩ የራሣቸው ወገኖች ናቸው፡፡ ስለዚህ አሁንም ከጭቆና እና ከችግር አልወጡም፡፡ ፌደራላዊ ስርዓት ጥሩ ሆኖ ከአሃዳዊ ሲለይ አልታየም፡፡ ሕዝቡ ቢጨቁነኝም ይጨቁነኝ፣ ቢረግጠኝም ይርገጠኝ፣ የኔን ቋንቋ እስከተናገረ ድረስ የሚል ከሆነ ሌላ ነገር ውስጥ ነው የሚገባው፡፡ ለኔ ቋንቋ አይደለም ትልቁ ነገር:: ከዛ ባለፈ ሕግ መከበር አለበት፤ ፍትህ መከበር አለበት፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር አለበት፡፡ እውነተኛ ነፃነት መኖር አለበት፡፡ አሁን የብሔረሰቦች ቀን ተብሎ “በዓል” ይከበራል፡፡ ሰባት ዓመት ሙሉ ተከብሯል መሰለኝ፡፡ ስምንተኛው በዓል በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ነው የሚከበረው፡፡ በአንድ በኩል ይህ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም በብሔረሰቦች መካከል ያለውን ስሜት በማጠናከር እና በራስ መተማመንን ለማምጣት የሚረዳ ነገር ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲሁ ዘፈንና ጫጫታ ሆኖ መሠረታዊ ጉዳዮች ሣይደረጉ ሲቀሩና እዛው በቦታው ሲመለስና እንደ ድሮው የሚጨቆን ከሆነ ምንድነው ትርጉሙ? የሰው ልጅ ፍላጐት ከዛ ያለፈ ነው፡፡ ይሄ ግን እየተመለሰ አይደለምና ከዳንሱና ከጭፈራው ጐን ለጐን የብሔረሰብ ነፃነት ሊከበር ይገባል፡፡ ሊሰሩ የሚችሉበት ነፃነት ይኑራቸው፡፡ ትምህርትን፣ የጤና አገልግሎትን ያየን እንደሆነ ተስፋፍቷል፡፡ “በቁጥር” ተስፋፍቷል፤ “በጥራት” ግን ገና ነው፡፡ መስፋፋቱ ጥሩ ነው፤ ግን ቁጥር ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ይሄ መንግስት አሁን እየጠቀሰልን ያለው ቁጥር ነው፡፡ ይህን ገንብቻለሁ እያለ በሁሉም ዘርፍ ይገልፃል፡፡ ያ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በጥራት መሻሻል አለበት፡፡ ቁሣዊና ሰብአዊ ልማት አለ፡፡

መንግስት እየተገበረ ያለው ቁሣዊ ልማትን ነው፡፡ ሰብዓዊ ልማት የለም፡፡ ሰብዓዊ ልማት ያለ ነፃነት፣ ያለፍትህ፣ ያለ ዴሞክራሲ ይሄን ያህል ጠቃሚ አይደለም፡፡

ሎሚ፡- በሚያዝያ 1983 ዓ.ም. ደርግ ባቋቋመው ሸንጐ የመጨረሻ ስብሰባ ላይ አባል እንደመሆንዎ ተገኝተው ለኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም የተናገሩትን ለዚህ ትውልድ መረጃ እንዲሆን ቢያስታውሱን?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ጊዜው በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ነበረች፡፡ ሀገሪቱን እመራለሁ፣ ግንባር ቀደም ነኝ የሚለው የፖለቲካ ድርጅት (ኢሠፓ) በየጊዜው እየተሰባሰበ የሀገሪቱን ሁኔታ እየገመገመ ሕዝቡ ምን እንደሚልና በሚለው መሠረት ምን መደረግ እንዳለባቸው ማወቅ ነበረበት፡፡ ግን ሳያደርግ ቀረ፡፡ ስብሰባዎች እንዲካሄዱ ነበር ብዙ ጊዜ የምንጐተጉተው፡፡ ከዛ ከፓርላማ ስብሰባው በፊት ኢሠፓ ተሰብስቦ የዚህችን ሀገር ሁኔታ እንዲገመግም፣ መፍትሄ እንዲፈልግና ተግባራዊ እንዲያደርግ በየጊዜው በሚደረጉ የመሠረታዊ ድርጅት ስብሰባዎች እንከራከር ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ውጤት አልተገኘም፡፡ ነገሮች እየተባባሱ ሄዱ፡፡
በመጨረሻ የተደረገው ተስፋ የመቁረጥ ዓይነት ሙከራ ነው፡፡ ሙከራው ቢዘገይም ከሚቀር ይሻላል፡፡ ምንም ካለማድረግ የተወሰነ ነገር ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ የግል ስሜቴ ነው፤ የግል ስሜቴን ለመግለፅ ነው የሞከርኩት፡፡ ግን አሁን መለስ ብዬ ያለንበትን ሁኔታ ሳይ ደግሞ ያን ያህል ጊዜ መዘግየት አልነበረብንም እላለሁ፡፡ ጊዜ መስጠት አልነበረብንም የሚል እምነት አለኝ፡፡ አሁን ደግሞ ለዚህ ስርዓት አላግባብ ተገቢ ያልሆነ ጊዜ እየሰጠን ነው፡፡ በስልጣን በቆየ ቁጥር እየበሰበሰ ነው የሚሄደው፡፡ በተፈጥሮው ስልጣን ያሞስናል፤ ያበሰብሳል፡፡ አንድ ወገን፣ አንድ ኃይል ስልጣን ላይ ከሚፈለገው በላይ በቆየ ቁጥር እየበሰበሰ ይሄዳል፡፡ ይሄ እኮ የተፈጥሮ ሂደት ነው፡፡ ሌሎች ሀገሮች የፕሬዚዳንትና የጠ/ሚኒስትር (በተለይ “የፕሬዚዳንት”ን) የስልጣን ቆይታ የቱንም ያህል ጥሩ ቢሆን ከስምንት አመት በላይ አያልፍም፡፡ ስለዚህ ሀገሪቱን ትጐዳለህና ቦታ ልቀቅ ነው የምትባለው፡፡ የኛ መንግስት እስካሁን ድረስ ብዙ ቆይቷል፡፡ 22 ዓመት ብዙ ነው፡፡ በኔ እምነት መበስበስ ከጀመረ ቆይቷል፡፡ የመበስበሱ ምክንያቶች በየጊዜው እየታዩ ናቸው፡፡ መቀጠል የለበትም ብለን መናገር አለብን እንጂ ዝም ማለት የለብንም፡፡ ከዚህ በፊት ዘግይተን ከነበረ እናዝናለን፡፡ በስንፍናችን እናዝናለን፤ እንቆጫለን፡፡ ነገር ግን ከዚያ ተምረን ያ መደገም የለበትም እንላለን፡፡ የሀገራችን ጉዳይ መፍትሄ ማግኘት አለበት፡፡ ገደብ የሌለው ስልጣን መፍትሄ ማግኘት አለበት፡፡ እነሱ ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ሕዝብ ስለፈለጋቸው አይደለም፡፡ በእንዴት ዓይነት ሁኔታ ስልጣን ላይ እንደወጡ የኢትዮጵያ ሕዝብም እነሱ ራሣቸውም ያውቁታል፡፡ አዲሱ ትውልድ በተለይ ወጣቱ ትውልድ መናገር መቻል አለበት፡፡ ለመብቱ ለነፃነቱ መቆም መቻል አለበት፡፡ አስፈላጊ ከሆነም ደግሞ መስዋዕትነት መክፈል አለበት፡፡
ሎሚ፡- በዚያ ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ ግድያ ሲፈጸም የድፍረት ንግግር ለመናገር የገፋፋዎት የተለየ ምክንያት ምን ነበር?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በወቅቱ ካለፈው ታሪኬ የተነሣ እንደ አደገኛ ሰው የታየሁ አልመሰለኝም፡፡ ፍራቻም አልነበረኝም፡፡ እንዲያውም የትግራይ ተወላጅ መሆኔን
ያስታወስኩት እኮ ዘግይቼ ነው፡፡ ጐሣ፣ ጐጥ… እየተነሣ ሲመጣ ነው ይሄ ነገር
መጉላት የጀመረው፡፡ እንጂ በፊት እኔ የዚህ ተወላጅ ነኝ፣ የዛ ተወላጅ ነኝ የሚል
ነገር አልነበረም፡፡ ስሜቱም አልነበረኝም፤ ትግራይ ነው የተወለድኩትና በተወለድኩበት አካባቢ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው ያደግኩት፡፡ በአጋጣሚ ትግራይ ማይጨው ራያ ተወለድሁ፡፡ የተወለድኩበትን አካባቢ እቀበላለሁ፡፡ ግን እዚያ ትግራይ በመወለዴ ልዩ ነገር ይገባኛል የሚል አመለካከት የለኝም፡፡ እዚያ መወለዴም ስጋት አላሳደረብኝም፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ሰው ነኝ፤ ከዛ በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ በዛ ምክንያት እንዲህ እሆን ወይ ጉዳት ይደርስብኝ ይሆን ወይ ብዬ አላስብም፡፡ እንደውም በዛን ጊዜ ኮ/ል መንግስቱ ፊት እንደዛ ስናገር ሰዎች በጣም ደንግጠው ከአካባቢው ለመራቅ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በኋላ ደግሞ ታስታውስ እንደሆነ ኮ/ል መንግስቱ በፃፉት ጽሁፍ /እኔ እንኳን መፅሐፉን ሣይሆን በቴፕ ነው የሰማሁት/ “ዶ/ር ኃይሉ እንደዛ የተናገረው ምናልባት ዘመዶቹ አምቦ ስለደረሱ ይሆናል፤ /ሣቅ/ ነው፤ ለኔ እንዲህ ዓይነት ስሜት ነው የፈጠረብኝ” ብለው ነበር፡፡ በጣም አሣዘነኝ፤ ምናቸው ነው ለኔ ዘመድ የሚያደርጋቸው?… በጣም አዘንኩ፤ የማንነት ጉዳይ አንዳንዴ ብወድም ባልወድም ብልጭ ማለቱ አይቀርም፡፡ ትኩረት የምሰጠው ነገር ግን አይደለም፡፡ ፍርሃት አልነበረብኝም፡፡ ያኔ የትግራይ ተወላጆች ብቻ አይደለም የሚገደሉት፤ ማንም ያንን መስመር የሚቃወም ሁሉ ነበር የሚገደለው፡፡
ሎሚ፡- ኮ/ል መንግስቱ እንደዛ ከተናገሩ በኋላ ቤትዎ ገብተው በሰላም አደሩ?… ሌሊቱን የት አሣለፉ? የኮ/ል መንግስቱ የደህንነት ሰዎች ምላሽስ ምን ነበር?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ምንም ችግር አልደረሰብኝም፡፡ ሰዎች ወስደው የት እንዳሳደሩኝ አላስታውስም፡፡ ብቻ የሆነ ቦታ ነው የወሰዱኝ፡፡ የተለየ ነገር አልገጠመኝም፡፡ አስታውሳለሁ፤ ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ስላሴ /የደህንነት ኃላፊው/ “ጐሽ ጥሩ ነው ያደረግከው” ብሎ መለስ ቀለስ እያለ እየፈራ እየቸረ ነው ያናገረኝ፡፡… /ረዥም ሳቅ/፡፡… በኋላ ጡረታ እንድወጣ ደብዳቤ ተፃፈ፡፡ በነገራችን ላይ ቀደም ብዬ ነበር ጡረታ እንድወጣ የጠየቅኩት፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ጥያቄዬ ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቶ ነበር፡፡ ወዲያው የተወሰደውን እርምጃ ሰዎች ነግረውኛል፡፡ …ኮ/ል መንግስቱ በጣም ተቆጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ለምነን አባብለን ነው ያስታገስናቸው ብለውኛል፡፡ አንደኛው የማውቀው ወዳጄ “እንዲያውም እግራቸው ላይም እስከመውደቅ ደርሰናል“” ሲል ነበር የነገረኝ፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ አላውቅም፡፡ መናደዳቸው አያከራክርም፤ እግዚአብሔር ይመስገን የከፋ ነገር ግን አልደረሰብኝም፡፡ በእሣቸው የደህንነት ሰዎችም የደረሰብኝ ነገር የለም፡፡
ሎሚ፡- እንግዲህ ውይይታችን ሰፊ ነውና ወደኋላም ወደፊትም እያልን ጥያቄ እናንሳ፤ ወደ ቅርብ ጊዜው እንመለስና ወደ ቅንጅት (ምርጫ 97) ግርግር እንምጣ፡፡ በወቅቱ አቶ ልደቱ የነበረው አቋም በእርግጥም የኢዴፓ ውሣኔ ነበር? በቅርቡ አቶ ልደቱ ከመፅሔታችን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ “የስልጣን ጥያቄ ስላልነበረን የበሰሉ ሰዎች ቢመሩት ይሻላል ብለን ነው ዶ/ር ኃይሉ አርአያን እና ዶ/ር አድማሱን ከቤታቸው አምጥተን ስልጣን እንዲይዙ ያደረግነው” ብሏል፡፡ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ መናገር አልፈልግም፡፡ ይሄ በእኔና በአንተ ቃለ መጠይቅ ላይ ብቻ ተገልፆ የሚያልቅ አይደለም፡፡ በጣም ሰፊ የሆነ ታሪክ ነው፡፡ ግን መናገር ካለብኝ አንድ ወጣት (ታምራት ታረቀኝ) የሚባል መፅሐፍ ፅፎ ነበር፡፡ ምናልባት እዚያ ላይ ያለውን ብደግመው በቂ ይሆናል፡፡ ተጠቅመውብናል ማለት እችላለሁ፡፡ በዛን ጊዜ የነበሩ የኢዴፓ አመራር /እነ አቶ
ልደቱ/ ተጠቅመውብናል፡፡ ከተጠቀሙብን በኋላ ጊዜው ሲመጣ እኛን ወደ ጐን ለማግለል ሞክረዋል፡፡ አቶ ልደቱ ብዙ ውይይት የሚከፍት ሰው ነው፡፡ መጠቀሚያ አደረገን እንጂ በምሁርነቴ ጠርቶ ይሄ ቦታ ይገባሀል ብሎ አይደለም ቦታ የሰጠኝ፡፡ በኔ ውስጥም የሚሰማኝ ይሄ ነው፡፡
ሎሚ፡- አቶ ልደቱ “ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከቅንጅት ጋር የትም አንደርስም” ብሎ
ይከራከር ነበር ሲልም ገልጿል፤ ይሄስ እውነት ነው?

ዶ/ር ኃይሉ፡- ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በተቃራኒው ነው እሱ የገለፀው፡፡ ከቅንጅት ጋር አብሮ ስለመስራት ነበር የኔ ክርክር የነበረው፡፡ አቶ ልደቱ በወቅቱ ብዙ ነገር የተወሳሰበና የተተበተበ ነገር ነበር የሚያነሣው፡፡ እንዲያውም “ቅድመ ሁኔታዎች” በሚል ይከራከር ነበር፡፡ በኔ በኩል በቅንጅት ዙሪያ መግባባት አለብን የሚል አቋም ነው የነበረኝ፡፡ በአቶ ልደቱ የተገለፀው የተገላቢጦሽ ነው፡፡
ሎሚ፡- ኢዴፓ ያንን አጋጣሚ አክሽፏል ብለው ያምናሉ?
ዶ/ር ኃይሉ፡- አዎ! አምናለሁ! በሁለት ምክንያት፡፡ አንደኛ ከምርጫ በኋላ የቅንጅት አመራር የአራቱ ፓርቲ አመራር ከልደቱ በስተቀር ለመዋሃድ ውሣኔ ሲያሳልፍ እና መሪዎቹ ፊርማቸውን ሲያሳርፉ በስምምነቱ ላይ አቶ ልደቱ በኢዴፓ ሰነድ ላይ ማህተም ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማህተሙ ሳያርፍ ቀረ፡፡ ይሄ የሆነው ማህተሙን የሙጥኝ ብሎ በመያዙ ነው፡፡ ሁለተኛ ለምርጫ ቦርድ በቅንጅት የተጠየቀው የውህደት ጥያቄ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚል ደብዳቤ በማስገባቱ ያለጥርጥር ያንን ዕድል አክሽፎታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄን ስል ግን ሌሎችም ችግሮች አልነበሩም ማለቴ አይደለም፡፡ ሌሎችም ችግሮች ነበሩ፡፡ ቀሪዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ራሣቸው አስፈላጊውን ጉባኤ አካሂደው ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች አሟልተው አንድ መሆን ሲገባቸው ሣይችሉ ቀርተዋል፡፡ ያ ብቻም ሣይሆን ያከሸፈው ሌሎች የውስጥ ችግሮችም ነበሩ፡፡
ሎሚ፡- በወቅቱ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲመረጡ በአቶ ልደቱ ላይ ምን ዓይነት ስሜት ነበር የታየው?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ብርቱካን በተመረጠችበት ጊዜ አቶ ልደቱ መበሣጨቱ ምንም የሚያከራክርና አንድና ሁለት የሚባል ነገር አይደለም፡፡ በጣም በጣም ተበሣጭቷል፡፡ በግል የተመለከትነው ነገርም ነው፡፡
ሎሚ፡- ከእርስዎ ጋር በኢዴፓም ሆነ በቅንጅት ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ ከፖለቲካ የራቁበት ምክንያት ምንድን ነው?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚገባው እሱ ዶ/ር አድማሱ ነው፡፡ እንደው ስገምተው ግን አንደኛ የትምህርትና የስራ ዕድልም ስላገኘ ይመስለኛል፡፡ ለባለቤቱም ጭምር ነው ይህ ዕድል የመጣው፡፡ ምክንያቱም የኛን ሃገር የመሰለ ፖለቲካ በሩቅ የሚከናወን አይደለም፡፡ ምናልባት አንድ ቀን ይመለስና የጀመረውን ትግል ይቀጥልበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ የዚህ ሀገር ተቃዋሚዎች ሁኔታ ደግሞ የሚያበረታታና ተስፋ የሚያጭርም አይደለም፡፡ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ አሁን አንዳንድ መሻሻሎችና መስተካከሎች የሚኖሩ ይመስላሉ፡፡ ምናልባት እነዚህ የ33ቱ ፓርቲዎች የመሰባሰብና አንድ ላይ ለመስራት የመወሰን ጉዳይ የሚያበረታታ ነው፡፡ ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራችን በፊትም ቢሆን እንኳን ሩቅ ላለና እዚህ ሀገር ውስጥ ላለም የሚያበረታታ ተስፋ የሚሰጥ አይደለምና አልፈርድበትም፡፡ እንዲህ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ወደሀገሩ ጠቅልሎ መጥቶ እገባበታለሁ ካለ መልካም ነው፡፡ ውስጡ ግን ማሰቡና መጨነቁ አይቀርም፡፡
ሎሚ፡- አቶ ልደቱ በሕይወትህ ምን የሚፀፅትህ ነገር አለ ለሚለው ጥያቄጠይቄው ነበር፡፡ ሲመልስም “በሕይወቴ ከሚፀፅተኝ ነገር አንዱ ምሁራንን ማመኔ ነው፡፡ ለምሁራን የነበረኝ ግምትና አስተሳሰብ ነው የሚጸጽተኝ” ብሏል፤ አባባሉን እንዴት አዩት?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ማንን አመነና ነው፡፡ ምንስ ተጓደለበት ነው የኔ ጥያቄ፡፡ ሣልፈልግ ወደዚህ የማልወደው ነገር ውስጥ እያስገባኸኝ ነው፡፡ የሚፀፅተኝ ሊል አይገባም፤ ምንም የሚፀፅት የተፈጠረበት ነገር የለም፡፡ የእሱን ተወውና በራሴ ግን በምሁራን ዙሪያ ከተባለ “ምሁራን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሣታፊ አለመሆናቸው ነው የሚያሣዝነኝ፡፡ የማመንና ያለማመን ጉዳይ አይደለም፡፡ አምነናቸው ጉድ አደረጉን፤ አሳልፈው ሰጡን የሚል መንፈስ ያለው
ይመስላል አባባሉ፡፡ በምን ጉዳይ ምንድን ነበር የጠበቀው? ምንስ ቀረበት?

አንድ፣ ኢሳት ፣ ኢህአዴግን እና ግንቦት7ትን የተመለከተ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ አንዳንዶች ዜናውን ሲጠራጠሩት ተመልክቻለሁ፣ ያሽሟጠጡም አልታጡም። መጠራጠርም፣ ማሽሟጠጥም የሰውልጅ ባህሪ በመሆኑ አልገረመኝም። ትንሽ የገረመኝ አንዳንድ “ጋዜጠኞች” መረጃውን ካገኙ በሁዋላ በራሳቸው መንገድ አጣርተው ሀቁን ማውጣት ሲችሉ እነሱም እንደሌላው መልሱን በማንኪያ እንዲቀርብላቸው መፈለጋቸው ነው። ጋዜጠኛ “ጥቆማ” ከተሰጠው ተመራምሮ፣ የምርምር ስራውን ይጽፋል እንጅ እንደ አንባቢ መልሱ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት አይጠብቅም፣ ጥያቄ መጠየቅማ ማንም ይጠይቃል፣ ጋዜጠኛን ጋዜጠኛ ወይም ተመራማሪ የሚያደርገው ለጠየቀው ጥያቄ ላይ ታች ብሎ መልስ ማቅረብ ወይም በአሰባሰባቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሶ ትንተና መስጠት ሲችል ነው ( በሁለተኛው መስፈርት መሰረት ተመስገን ደሳለኝን እና በእስር ላይ የሚገኘው ውብሸት ታየን አደንቃለሁ)።

ሁለት፣ ዜናውን እንደሰማሁ መጀመሪያ የመጣልኝ ጥያቄ “እና ምን ያስገርማል?” የሚለው እንጅ፣ “ድርድሩ የተጠየቀው መቼና በእነማን በኩል ነው?” የሚለው አልነበረም። የአለም የፖለቲካ ታሪክ በግጭትና በድርድር የተሞላ ነው። “ድርጅቶች ይጋጫሉ፣ ይደራደራሉ፣ ምን ያስገርማል?”፣ በፖለቲካ ትግል” በመቃብሬ ላይ ..” የሚባል ነገር የለም። “ለምን ሰበር ዜና ሆነ ታዲያ?’ እንዳትሉኝ፣ ሰበር ዜና ማለት አስገራሚ የሆነ ዜና ማለት አይደለም ።

ሶስት፣ ቀጥሎ የመጣልኝ ጥያቄ “ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር መደራደር ለምን ፈለገ?” የሚለው ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ” የፖለቲካ ድርጅቶች የእንደራደር ጥያቄ የሚያቀርቡት መቼ ነው?” የሚለውን ማየት ነበረብኝ። የፖለቲካ ድርጅቶች በአብዛኛው ለድርድር የሚቀመጡት ህልውናቸውን ለማቆየት ወይም ተደራድሮ የሚገኝ ጥቅም ሳይደራደሩ ከሚገኝ ጥቅም ( ጉዳት) የተሻለ ሆኖ ሲያገኙት ነው። በዚህ ንድፈሀሳብ ላይ ተመስርቶ ኢህአዴግ እና ግንቦት7 አሁን ያሉበትን ቁመና መፈተሽ ይገባል። ኢህአዴግ ከመለስ በሁዋላ ኢህአዴግ አለመሆኑ ይታወቃል።ሊቀመንበሩ ድርጅቱን ይዞ ለመቀጠል ተቸግሯል፣ (ምናልባትም በቅርቡ ይፋ የሚሆኑ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር አጋጥሞታል)፣ የ ህዝቡ ልብ እንደሸፈተ አውቋል፣ ወጣቱ ለውጥ እንደሚፈለግ ተረድቷል፣ ሰራዊቱ የሚተማመንበት ሀይል እስኪያገኝ እንጅ እንደሚከዳው ተገንዝቧል። በአጠቃላይ መጪው ጊዜ ለኢህአዴግ ብሩህ አለመሆኑን ግንባሩ ጠንቅቆ ያውቃል። በዚህ አደጋ ውስጥ ሆኖ ጊዜ ለመግዛትና ድርጅቱን ለማጠናከር የድርድር ጥያቄ ቢያቀርብ አይገርምም።

ግንቦት7 ለኢህዴግ “አጣዳፊ ጠላት” (immediate threat) ሆኗል እያልኩ አይደለም፣ ነገር ግን እምቅ ጠላት ( potential threat) መሆኑን አልጠራጠርም ። አንድ ድርጅት ለሌላው ድርጅት አጣዳፊ ጠላት የሚሆነው ፣ አሁን ባለበት ሁኔታ፣ ከተቃራኒው ድርጅት የበለጠ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የሀይል ሚዛን ሲኖረው ነው። ግንቦት7 ኢህአዴግን ዛሬውኑ ለማስወገድ አይችልም ምክንያቱም ከኢህአዴግ የሚበልጥ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ ሀይል የለውምና ፤ ነገር ግን በጊዜ ሂደት እንደሚያስወግደው መገመት ይቻላል፣ ከመለስ በሁዋላ ያለውን ሁኔታ ብታጠኑ የኢህአዴግ የሀይል ሚዛን ወደ ታች እየወረደ፣ በአንጻራዊ መልኩ የግንቦት 7 የሃይል ሚዛን ደግሞ ወደ ላይ እየወጣ ነው፣ የ ግንቦት7 መሪዎች በዚህ አመት የሀይል ጥቃት እንደሚጀመሩ አስታውቀዋል፣ በዚህ አመት ቀርቶ በሚቀጥሉት 3 አመታት ጥቃት ከፈጸሙ እያደጉ መሆኑን የሚያሳይ ነው ( 4 ፓይለቶች መክዳታቸውንም አንዘንጋ)። የፖለቲካ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ሁለት አይነት ሀይል አለ። አንዱ መቺው ሀይል ( hard power) ሲሆን ሌላው ደግሞ መለስተኛው ሀይል ( soft power) ነው። መቺው ሀይል የሚባለው ወታደራዊው ሀይል ነው። በዚህ በኩል ኢህአዴግ ከግንቦት7 በብዙ እጅ የሚልቅ ጉልበት አለው። ነገር ግን ግንቦት7ትም በዚያው ጎዳና እየተጓዘ መሆኑን መርሳት የለብንም።

መለስተኛ ሀይል (soft power) የሚባለው ደግሞ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎችን፣ ጥራት ያለው የሰው ሀይልን ( መሪም ተከታይም)፣ ህዝባዊ ድጋፍ ፣ የካፒታል አቅም ፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የመሳሰሉትን ያካትታል። ግንቦት7 በዚህ በኩል ከፍተኛ ጉልበት መገንባቱን መመስከር ይችላል። ከኢህአዴግ ተመጣጣኝ የሆነ ካፒታል ባይኖረውም፣ ከሌሎች ድርጅቶች የተሻለ ካፒታል( ገንዘብ)እንደሚኖረው ከስራዎቹ መገመት ይቻላል ። የተማሩ ሰዎችን በመያዝ በኩልም፣ ከኢህአዴግ ቢበልጥ እንጅ አያንስም። በፕሮጋንዳውና በህዝብ ድጋፍ በኩልም እንዲሁ። እንዲያውም የግንቦት7 የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ከኢህአዴግ የተሻሉ ለመሆናቸው ብዙ አስረጅ አይጠይቅም፣ የግንቦት7 ራዲዮና ዌብሳይት እስከዛሬ ሳያቋርጥ እየሰራ ነው፣ ጠንካራ የፓልቶክ ደጋፊዎችም አሉት። ኢህአዴግ ራሱ የሚሰራላቸው ፕሮፓጋንዳም ቀላል አይደለም። ኢህአዴግ ቢያንስ በውጭ ያለውን ድጋፉን፣ በተለይም ለጀመራቸው የአባይ እና ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ ለመለመን ሲል ግንቦት7ን ለድርድር ቢጠይቀው አይገርምም። ኢሳት የግንቦት7 ነው ብሎ ስለሚያስብም፣ ኢሳትን እንዲያስቆምለት ልደራደርህ ቢል አሁንም አይገርምም። (በኢሳት ላይ እንኳ ቀልድ የለም፣ መደራደር ከፈለገ ከኢሳት ጋር እንጅ ከግንቦት7 ጋር ሊሆን አይችልም፣ ምክንያቱም ግንቦት7 ስለኢሳት ምንም የሚያገባው ነገር የለምና፣ ከኢሳት ጋር ድርድር ከተጀመረም ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ዙሪያ እንጅ፣ ከስራው ጋር የተያያዘ እንደማይሆን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ)

አራት፣ ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር ብቻ ነው ወይ ድርድር የመረጠው? እኔ ባለኝ መረጃ ኢህአዴግ በእነ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅ በኩል ላለፉት 4 ወራት ከእነ አቶ ሌንጮ ለታ ድርጅት ጋር ሲነጋገር ነበር። ይህን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ከኦብነግ ጋርም እንዲሁ ተደጋጋሚ የድርድር ጥያቄዎች ቀርበዋል። እነዚህ ድርጅቶች በፓርላማ “አሸባሪ” የተባሉ ናቸው። እና ለግንቦት7 ጥያቄ ቢያቀርብ ምን ይደንቃል? ፖለቲካ እኮ ፊት ለፊት የምትናገርውና በውስጥ የምታደርገው የተለየ ነው። That is politics. በነገራችን ላይ ” አንደኛው የአለም ጦርነት የተጀመረው በድብቅ በሚካሄድ ፖለቲካ የተነሳ ነው” ተባለና ፖለቲካ ግልጽነት እንዲኖረው ተብሎ አዲስ አስተሳሰብ ለረጅም ጊዜ ተራመደ። ፖለቲካ ግን ዛሬም ፊትና ጀርባ እንደያዘ ቀጥሎአል።

አምስት፣ “ጥያቄው በእነማን በኩል ቀረበ?’ የሚለውንም ለራሴ አንስቻለሁ። የድርጅቱ መሪዎች መልሱን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ነገር ግን የራሴን ግምቶች አስፍሬአለሁ። አንድ፣ በቅርቡ በእነአቦይ ስብሀት የተመራ ቡድን አሜሪካ ከርሞ ሄዷል። ሁለት፣ ፕ/ር ኤፍሬም አሜሪካ ከርመዋል፣ ኦነጎችን ለማስታረቅም ላይ ታች ሲሉ ከርመዋል። ሶስት፣ በቅርቡ የአውሮፓ እና የካረቢያን አገሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፣ ብዙ ዲፐሎማቶችም አዲስ አበባ ነበሩ። አራት፣ ኖርዌይና ሆላንድ ሁሌም ተቃዋሚዎችን ለማቀራረብ ይሰራሉ። ይዋል ይደር እንጅ ትክክለኛውን መልስ እናገኛለን። መልሱ ግን ከጠቀስኳቸው ሰዎች ወይም አገሮች በአንዱ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። የእንደራደሩ ጥያቄ ለመቅረቡ ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ። እስከዛው እንደ ጋዜጠኛ መላ ምት በማስቀመጥ ምርምራችን መቀጠሉ ተገቢ ነው።

ስድስት፣ ግንቦት7 ለምን ይህን ድርድር ይፋ ማድረግ ፈለገ? ኢህአዴግ አስቀድሞ በኢቲቪ ” ከግንቦት7 ጋር ሲያደርግ የነበረው ድርድር ከሸፈ” ብሎ መግለጫ ቢሰጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? የግንቦት7 ደጋፊዎች የድርጅቱን መሪዎች በጥሩ አይን የሚያዩዋቸው አይመስለኝም፤ ግንቦት7ትም ውስጥ አለመተማመን ይፈጠርና ድርጅቱን ከሁለት ሊከፍለው ይችል እንደነበር መገመት ይቻላል፣ ዲሞክራሲያዊ ነኝ የሚል ድርጅት ከአባሎቹና ከህዝቡ የሚደብቀው ነገር መኖር የለበትም። ግንቦት7 በመግለጫው “ድርድር መደረግ ካለበት ከሁሉም ድርጅቶች ጋር ነው፣ ሁሉንም ነገር ግልጽ እናደርጋለን የምንደብቀው የለንም” ብሎአል። ትክክል ነው። እውነተኛ ድርድር ሲጀመር ለጊዜው ይፋ የማይወጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ድርድር ተጠየቅሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱ ግን የሚገርም አይመስለኝም። ግንቦት7 መረጃውን ከኢህአዴግ ቀድሞ ይፋ ማድረጉ ድርጅቱን ከመከፋፈል ማዳን ብቻ ሳይሆን ንቅናቄው ከኢህአዴግን አንድ እርምጃ ቀድሞ የ ሚያስብ መሆኑን ለማሳየትም ጠቅሞታል።

በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች በኢህአዴግ በኩል ያለውን መልስ ይዘውልን እንደሚቀርቡ ተስፋ እናድርግ።

http://www.goolgule.com/we-shall-arise-again/

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡ መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡ ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣ እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው” ብለዋል፡፡ መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣ እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡ በቃለ-መጠይቁ ሰላማዊ ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣ እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡ እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣ በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን? ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?

ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣ የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡ የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ ሽማግሌዎችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ ከፖለቲካ ልዩነትም፣ ከአምባገነንነትም በላይ ሰዎቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡ በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣ እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣ የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡ እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡ አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሻለ ልገልጸው አልችልም፡፡

አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋናው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡

ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡ መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣ እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣ እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡

ለምሳሌ ኢቲቪ ስለ ጉዳዩ ሲያወራ ህገ ወጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው? ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡

ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው? ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ ኤምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣ አፈነን፡፡ በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡

ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣ እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::

እንዴት!

በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡ የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ ሳውዲዎችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡ በዚህ ክፉ ጊዜ ስለሰብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡

መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡ በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡ የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡ በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡

እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ ጩኸቱ ግን ይቀጥላል… ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡ አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣ በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣ የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣ እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡ እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡ እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ ቸልታንም አስበለጡ፡፡ በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)

ሳውዲ አረቢያ ጎዳና ላይ የኢትዮጵያውያን ደም ብቻ ነው የሚፈሰው፡፡ የሚያለቅሱትም ኢትዮጵያውያን ሆነዋል፡፡ ኦጋዴን ታነባለች፤ ጋንቤላ ውስጥ ተወላጆቹ ለአረቦቹ እትብታቸው የተቀበረበትን መሬት ትተው እየሸሹ ነው፡፡ በኦነግ ስም መታሰር አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ቀድሞ የታሰሩትንም ማዕከላዊ፣ ዝዋይ፣ቃሊቲ….እየማቀቁ ነው፡፡ ከየ አካባቢው ኢትዮጵያውያን መሬታችሁ አይደለም ተብለው ያፈሩትን ተነጥቀው እየተባረሩ ነው፡፡ ሙስሊሞቹ ታስረዋል፡፡ መስጊድ ውስጥ ፖሊስ ገብቷል፡፡ ገዳማት ለሸንኮር አገዳ ተከልለዋል፡፡ ወጣቱ ስራ አጥቷል፡፡ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ‹‹አሸባሪዎች›› ተብለው እየተሰቃዩ ነው፡፡ ህገ መንግስቱን ጠቅሶ መብትን ማስከበር ያስደበድባል፡፡ ያሳስራል፡፡

ኢትዮጵያ እንዲህ ሆነች፡፡ እምነት ምኑም ባይሆን በኢኮኖሚው ያስለቅሱታል፡፡ ከእነሱው ተጠግቶ ለኢኮኖሚው ግድ ባይኖረው በእምነቱ ይመጡበታል፡፡ ይህንም ቢሆን ‹‹ዝም›› ብሎ ቢያልፍ እህቱ ሳውዲ ውስጥ ተደፍራ ስትሞት ‹‹ህገ ወጥ ስለነበረች ነው›› ይሉታል፡፡ ለዚህ ሰቆቃ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ይደበደባል፡፡ ይታሰራል፡፡ ብቻ በአንድም ሆነ በሌላ ኢትዮጵያ ታነባለች፡፡ የሚያሳዝነው ግን እንዲህ እያነባች መጨፈሯ ነው፡፡

አንድ የአማርኛ ፊልም ላይ ነው፡፡ ተዋናዮቹ ‹‹ጥሮ ግሮ›› የሚለውን ቃል ወደ እንግሊዘኛ ለመተርጎም ሞክረው መጣር መጋር በኢትዮጵያ እንጅ ሌላ አገር እንደሌለ አምነው ይተውታል፡፡ እንደ እኔ ኢትዮጵያ እያነባች የምትዳንስ ብቸኛዋ አገር ትመስለኛለች፡፡ እያነቡ እስክስታ የእኛው ብቻ መገለጫ ይመስለኛል፡፡ ሰቆቃ ተለይቷት የማታውቀው አገር እያረረች ትስቃለች፣ እያነባች እስክስታውን ታስነካዋለች፡፡ ይህ የሚደረገው በገዥዎቿ ትዕዛዝ ቢሆንም የሚያለቅሱትም የሚዳንሱትም ግን ምስኪኖቹ ህዝቦቿ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ለህዳር 29 ዳንስ እየተለማመዱ ነው፡፡ ይህ ሁሉ በሆነበት ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› የሚባሉት በተድላና በደስታ እንደሚኖሩ ሲነገር ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እየራጠራለሁ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ህቡዕ ይሆኑብኛል፡፡ መቼም ብሄር ብረሰቦችና ህዝቦች የሚባሉት ሳውዲ፣ ኦጋዴን፣ ጉራፈርዳ፣ ነቀምት፣ አዲስ አበባ……ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰቃዩትን ውጭ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሳውዲ ውስጥ እህቱ የሞተችበት እንባውን በቅጡ ሳይጠራርግ ይጨፍራል፡፡ መሬቱን የተነጠቀው፣ ወንዱሙ የታሰረበት፣ ከክልል የተባረረ…..እርር ድብን እያለም ቢሆን በትዕዛዝ እስክስታውን ይመታል፡፡ እያረረ ይስቃል፡፡

ህዳር 29ኝም ሆኑ ሌሎቹ በዓላት ለእኔ እንደዚህ ናቸው፡፡ ቋንቋህ ተከብሮልሃል ተብሎ መብቱን በአፍ መፍቻው መናገር ሳይጀምር ሰቆቃ የደረሰበት ህዝብ፣ የብሄርን መብት ተከብሮልሃል ተብሎ ከስም ያላለፈ ጥቅም ያላገኘ ‹‹ብሄርና ብሄረሰብ›› ከልቡ የሚያከብረው በዓል ሊሆን አይችልም፡፡ አዎ ህዳር 29 መብገኛ፣ እያረሩ የሚጨፈርበት፣ ህገ መንግስታዊ መብት ከጭፈራና ማስመሰል ያለለፈበት እያረሩ የሚስቁበት ቀን ነው፡፡

Image

ኢትዮጵያ ግራ በሚያጋባና ሊተነበይ በማይችል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መገኘቷን ያመኑ የህወሃት ሰዎች መካካል የእርቅ ሃሳብ ላይ ለማተኮር እቅድ እንዲያዝ ሃሳብ ማንሳታቸው ተሰማ። ኢህአዴግ የቀድሞው የአፈና ገመዱ መንተቡን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸውና አለመተማመን መንገሱ ተጠቆመ።

ለጎልጉል መረጃ በመስጠት የሚታወቁ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራርና ዲፕሎማት እንዳሉት ህወሃት ውስጥ “እርቅ አስፈላጊ ነው” በሚል እቅድ እንዲያዝና እንዲሰራበት ሃሳብ ቀርቧል። በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመተማመን ሳቢያ ስጋት የገባቸው የህወሃት ሰዎች የእርቅ ሃሳብ እንዲሰራበት ያቀረቡት ሃሳብ ግን በመደበኛ ስብሰባ አይደለም።

በህወሃትና ህወሃት በሚያዛቸው አቻ ፓርቲዎች መካከል ያለው የመከባበርና የመገዛት ስሜት ከመለስ ሞት በኋላ መበላሸቱ፣ በኢህአዴግም ሆነ በህወሃት ደረጃ የተፈጠረው ልዩነትና በሙስና ስም የተጀመረውን ዘመቻ ተከትሎ የተነሳው አለመግባባት አደጋ እንዳያስከትል ተፈርቷል። የመረጃው ምንጭ እንደሚሉት በጣም ጥቂት ካልሆኑ በስተቀር ከሙስና የጸዱ አለመኖራቸው “ማን ንጹህ ሆኖ ማንን ይጠይቃል?” የሚል ቅሬታ አስነስቷል።

ህወሃት ባሰበው በሁሉም መንገድ የበላይ ሆኖ ሊቀጥል እንደማይችል ከየድርጅቶቹ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በስፋት እየተነገረ መሆኑንን ያነሱት እኚሁ ሰው፣ ይፋ ባልሆነ መንገድ የቀረበው እርቅን የመቀበል ጥያቄ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የተነሱት አስደንጋጭ ችግሮች ተከትሎ መሆኑን አልሸሸጉም።

ሊታመን በማይችልና ባልተለመደ መልኩ የሃይማኖት አባቶች ኢህአዴግን አንደበታቸውን ከፍተው በግልጽ ማውገዛቸውን፣ “አገሪቷን ገደላችኋት” በማለት መኮነናቸውን ተከትሎ በኢህአዴግ ዘንድ መደናገጥ እንደተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል። የእምነት ጉዳይ ጥንቃቄ የሚያሻው በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ዲፕሎማት “ኢህአዴግ በቀድሞው ፓትሪያርክ ፈቃድና ውዴታ ያደርግ እንደነበረው አሁንም በደኅንነት ሃይሎች ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠርና አመራሮቹን አንደበታቸውን ማፈን የማይችልበት ደረጃ መድረሱን አምኖ ተቀብሏል። በዚህ ላይ ደግሞ እስካሁን ምላሽ ያላገኘ የድምጻችን ይሰማ ጉዳይ አለ” ኢህአዴግ እንደተምታታበት አመላክተዋል።

ሲኖዶሱ በጉባኤው ያነሳቸው ነጥቦች ኢህአዴግ ነገሮች ቀስ በቀስ ከእጁ እንደወጡበት የሚያሳይ እንደሆነ ያመለከቱት የኢህአዴግ ሰው “ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኢህአዴግ አባላት በልብ ከድርጅቱ ጋር እንደሌሉ ሪፖርት ቀርቧል። አብዛኛው አባልና ደጋፊ ባለሃብቶች የሚባሉትን ጨምሮ ሰላማዊ ለውጥ እንዲካሄድ ኢህአዴግ ወደ እርቅ መንገድ እንዲሄድ ይፋ (ኦፊሴላዊ) ባልሆነ መልኩ ያነሳሉ” በማለት ድርጅቱ የገባውን ስጋትና መሸርሸር ያስረዳሉ።

እርቅ ከተፈለገ ለምን በግልጽ አይቀርብም በሚል ለቀረበላቸው ሃሳብ ዲፕሎማቱ ምላሽ ለመስጠት አልፈለጉም። ይሁን እንጂ “ከማን ጋር ነው የምንታረቀው? እነማንን ነው ለእርቅ የምንጋብዘው? እርቅ ጠያቂ መሆን ያለበትስ ማን ነው?” የሚሉት በግልጽ ባይቀርቡም ተመሳሳይ የስጋት ጥያቄዎች እንዳሉ ሳይገልጹ አላለፉም።

በቅንጅት ጊዜም በተመሳሳይ የዕርቅ ፍላጎትና “ሥልጣን እናስረክብ” የሚል አቋም ተነስቶ እንደነበር ያስታወሱት ምንጫችን፤ በወቅቱ ሃሳቡ ተግባራዊ ያልሆነው “ወያኔዎችን ወደመጡበት ጠራርገን እንመልሳቸዋለን” በማለት አንድ የቅንጅት አመራር ለሕዝብ መፈክር ሲያወርዱ ከተሰማ በኋላ ነበር፡፡

በመከላከያ አዛዦችና በደህንነት የተለያዩ መምሪያዎች የሃላፊዎች ለውጥ እያካሄደ ያለው ኢህአዴግ ከአቻ ፓርቲዎች ጋር ውህደት በማድረግ ብሔራዊ ፓርቲ ለማቋቋም በሁለት ጉባኤዎች ሃሳብ ቢቀርብም ተግባራዊ አላደረገውም። ፓርቲው ህብረ ብሔር ከሆነ ህወሃት የገነባቸው የንግድ ድርጅቶችና በሞኖፖል የያዘውን ቁልፍ ስልጣን እንዲያጣ ስለሚያደርገው ጊዜ ሲያጓትት መቆየቱን ያመለከቱት የመረጃው አቀባይ “ይህ ፍርሃቻ አሁንም ሆነ ወደፊት ለሚፈለገው በሃሳብ ደረጃ ያለ እርቅ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል የውስጥ ለውስጥ ሃሜት አለ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ሆኖም እጅግ የተወሳሰበ የፖለቲካ ትወና ውስጥ ያሉት ካልሆኑ በስተቀር በማናቸውም መልኩ እርቅን ለመቀበል የማያቅማሙ እንደሚበዙ ግን አልሸሸጉም፡፡

በኢህአዴግ ውስጥ አለመተማመን መንገሱን የሚናገሩ ወገኖች “ለራሳቸው መተማመን ያቃታቸው ክፍሎች እንዴት ሌላውን አስማምተው ይመራሉ” በማለት መጠየቅ ከጀመሩ ቆይተዋል። በተለይም አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ መንበሩ ከመጡ በኋላ አገሪቱ በደቦ መመራቷ የኢህአዴግን መሽመድመድ የሚያሳይ እንደሆነም እየተቹ ነው።

sebhat negaሁሉም ሰላም ነው፤ ልማት ነው፤ ዕድገት ነው፤ ህዳሴ ነው … በማለት አንድም ችግር የሌለበት ለመምሰል የሚሞክረው ህወሃት ደግሞ በውስጡ የመከፈል አደጋ አጋጥሞት እንደማያውቅ ምንነታቸውና የስራ ደርዛቸው በውል በማይታወቀው አቶ ስብሃት አማካይነት እያስታወቀ ነው። እሳቸው እንደሚሉት ችግር የህወሃት “ሰማያዊ ስጦታውና በረከቱ ነው” አቶ ሃይለማርያምም በበኩላቸው “ኢህአዴግ መካከል መከፋፈል አለ የሚሉ የዋሆች ናቸው” ሲሉ አንድነት የሰፈነበት አመራር እንዳለ ለማስተጋባት ሞክረዋል።

የእርቅ ሃሳብ ተሰንዝሯል በማለት መረጃውን የሰጡን ዲፕሎማት ግን ይህንን አይቀበሉም። “በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚታይ ነው። አንዱ እኔ ነኝ። ሌሎችም አሉ። ብዙዎች ሰላማዊ ህይወት ናፍቆናል። የተወሳሰበውን አገራችንን ፖለቲካ አካሄድ ለመተንበይ ተቸግረናል። መፍትሔው የእርቅ ሃሳብ ብቻ ነው” በሚል ተከራክረዋል።

በድርጅታቸው ውስጥ የበላይና የበታች መጥፋቱን፣ የበታቹ የበላዩን እንደሚያዘው፣ አንዳንዴ የበላይ መስለው ምንም ዓይነት የውሳኔ ሰጪነት ሚና የሌላቸው ክፍሎች መኖራቸው የአደባባይ ምስጢር እንደሆነ የሚናገሩት እኚሁ ሰው፣ “እርቅና ዋስትና የሚሰጥ አግባብ ቢያገኝ የመጀመሪያው ስምምነት ፈራሚና ደጋፊ ስብሃት ነው። ቀሪውን የጡረታ ዘመኑንን በትዝታ ያለውን እየበላ መኖር ይፈልጋል። እሱ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች ተመሳሳይ ፍላጎት አለን። አስከማውቀው ድረስ ችግሩ ከራስ ምግባርና ከድርጅት ተልዕኮ በመነጨ የተሰሩት ጥፋቶችና ሃጢያቶች መብዛታቸው ከለውጥ በኋላ የሚያመጣቸው የተጠያቂነት ጣጣዎች ናቸው” ብለዋል፡፡

በኢህአዴግ ውስጥ ንጹህ ሰዎች አሉ ለማለት የማይቻልበት ደረጃ መደረሱን የሚያመለክቱት ዲፕሎማት፣ ህወሃትም ሆነ ኢህአዴግ አሁን የጋራ ነጠብ የሌላቸው፣ የርስ በርስ ትስስራቸው የላላና የተለያየ፣ አንዱ ሌላውን ለመንካትና ለመገምገም የሞራል ብቃት ያጣበት፣ እርስ በርሱ በወንጀል የሚጠቋቆምበት የውድቀት ጫፍ ላይ መድረሱን የውጪ አገር ወዳጆቹም ተረድተውለታል፤ አሁን ለእነርሱም ችግር የሆነባቸው ቁጭ ብለው ሥልጣን ላይ የሰቀሉትን ህወሃት አሁን ቆመው እንዴት ማውረድ እንደሚቻል መቸገራቸው ነው ብለዋል። የእርቅ ሃሳቡ ከውጪ አገር ወዳጆቻቸው ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ግን ፍንጭ አልሰጡም።

በህወሃትም ሆነ በኢህአዴግ ደረጃ የውስጥ ስጋት ቢኖርም “ሕዝብ እስኪ ዛሬን ልደር” በሚል የሞራል ውድቅት ውስጥ በከተተው ድህነት የተመታ በመሆኑ ለጊዜው ያምጻል የሚል ግምገማ አለመኖሩን ዲፕሎማቱ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ህዝብ በኢህአዴግ ደስተኛ አለመሆኑ፣ የጥበቃና የቁጥጥር መረቡ እንደወትሮው ትጋት ማጣቱ፣ የአካባቢ ስሜትና “ወገኔን ለምንና እስከመቼ አሳልፌ እሰጣለሁ?” የሚል አስተሳሰብ መበራከቱ፣ አጋጣሚ ተቃውሞ ቢነሳ መቋቋም እንደማይቻል፣ ረብሻ ከተነሳ የስርዓቱ ባለሟሎች ህልውና ጉዳይ አስጨናቂ እንደሚሆን ግንዛቤ ስለመኖሩ አላስተባበሉም። በማያያዝም እሳቸው በዚህ ደረጃ ስርዓቱን ከገመገሙና ችግሩን ከተረዱ በይፋ የማይከዱበትን ምክንያት ተጠይቀው “ለጊዜው በምስጢር ጠባቂነት የዝግጅት ክፍሉ ቃሉን ይጠብቅ። የቀረውን ወደፊት እናየዋለን” የሚል ድፍን መልስ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሰጥተዋል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ምንሊክ ሳልሳዊ :- ወገኖቼ መቸም የወያኔን እኩይ ምግባር የቱን ጥለን የቱን አንስተን እንደምንናገር አናውቅም ሙሉ ሰውነቱ በመጥፎ የፖለቲካ ፈንጂዎች እና በቀሎች የተሞላ በማዘናጋት እና በማደናበር በማጭበርበር የተሞላ መሆኑ ሳይታለም በይፋ የተፈታ እውነት ነው::

የዛሬ ትኩስ ወሬ የሆነው የወያኔው ጁንታ ከግንቦት ሰባት ጋር እንደራደር የሚለው ጥያቄ እጅም አስገራሚ የማይደንቅ ሆኖም በጭንቅ ሰአት የተጠበቀ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ አሊያም ማጭበርበር ሲጨመርም ማዘናጋት የታከለበት ጠማማ አክሄድ መሆኑ ለማንም አይጠፋውም:: ወያኔ ከበረሃ ጀምሮ በአባቱ ሻእቢያ በኢሕኣፓ በደርግ በኢሕዴን እና ተመሳሳይ አንጃዎች ላይ ሲሰራ የነበረው የማጭበርበር እና የማዘናጋት ፖለቲካ አልፎ እስከ ሽብር ተግባር ድረስ የሚፈጽም አደገኛ አሸባሪ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል::ወያኔ በአሲምባ ኢሕኣፓን በሮም እና ሎንዶን ደርግን እንዲሁም በበረሃ ሻእቢያን እና ኢህዴንን… ከዛም የሽግግር መንግስት ከተባለ ጀምሮ እንደ ኦነግ ኦብነግ የመሳሰሉ ድርጅቶችን በድርድር ስም ሲያጭበረብር የነበረ ከመሆኑም በላይ በትልቁም የኢትዮጵያን ሕዝብ ያጭበረበረ እና እያጭበረበረ እያዘናጋ ያለ ቅስም ለመስበር የሚራውጥ የሽብር ጀሌ ነው::

ወያኔ አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ግንቦት ሰባት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ አንድም ቀልድ ነው አንድም ማዘናጊያ ስልት ነው:: ወያኔ በሃገር ውስጥ ያለውን ሕዝብ እና ከሃገር ውጪ ያለውን ዲያስፖራ ለማዘናጋት እና ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት የመጀመሪያውን ዳገት በመቧጠጥ ላይ ይገኛል::የወያኔው ጁንታ ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ወጥሮ የያዘውን ከፍተኛ አደጋ ለመወጣት ሲሆን ከዚህም መሃል

-በሃገሪቱ ይከሰታል ተብሎ የሚሰጋው እና በጥናት ሪፖርት የቀረበበት የኑሮ ውድነት
-በሰራዊቱ እና በደህንነቱ ተቋማት ውስጥ እየተነሱ ያሉ ህገመንግስታዊ ጥያቄዎች
-በተለያዩ ሃገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ብሄራዊ ውርደቶች
-የሃይማኖት መሪዎች ወቀሳ እና የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ
-በሃገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው የትውልዱ ስራ ማጣት እና ስደት
-የፖለቲካ ምህዳኡ መጥበብ ያስነሳው አለማቀፍ ጫና
-በየእስር ቤቱ ያሉ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ይፈቱልን ጫና
-እንዲሁም ተመሳሳይ የሆኑ የዲሞክራሲያዊ መብቶች እና የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ለውጦች ጥያቄዎች ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ሲሆን በየጊዜው በሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች እና በማይገናኚ የሃሰት እይታዎች የሚዲያ ፍጆታ የፖለቲካ ውሸቶች ሕዝብ በጁንታው ላይ ያለውን እምነት በማጣቱ እና ተስፋው በመሟጠጡ ወያኔ በውጥረት ውስጥ በመሆኑ ይህንን ለማዘናጋት እና የፖለቲካ ማጭበርበር ለመፈጸም የድርድር ጥያቄዎች ማቅረቡ ምንም አዲስ ነገር ካለመሆኑም በላይ የሚጠበቅ እና የማዘናጊያ ደውል ነው:; ከዚህ ቀደም ተደራደርኩ ካላቸው ድርጅቶች ላይ ያመጣው ታጣ እና ውጤት ቢኖር ስደት እና ሞት ለድርጅቶቹ አባላት እንዲሁም አሸባሪ የሚል ታርጋ መለጠፍ ብቻ ነው::

በግንቦት ሰባት ውስጥ ያሉ ታጋዮች በኢህኣፓ በኢሕኣዴግ በቅንጅት እና በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥ በመሆን የተለያዩ እውቀቶችን እና ልምዶችን የቀሰሙ እንደመሆናቸው ለወያኔ የማዘናጊያ እና የማጭበርበሪያ ደውል መልስ አይጠፋቸውም ትግሉም ስልጠናውንም ሃገር እና ወገን የማዳን ስራውም ከበፊቱ በበለጠ መልኩ እየተጠናከረ እንደሚሄድ እንተማመናለን::
‪#‎MINILIKSALSAWI‬
ለወያኔ የማደናበሪያ እና የማዘናጊያ ስልቶች የሚራራ ልብ የለንም!! ድል ለተጨቆኑ ሕዝቦች!!እናቸንፋለን!!!

Image

ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ የግንቦት 7 ምርጫ መሆኑን ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። ግንቦት 7ን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው።

የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰሞኑ የወያኔ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያደርገው ትግልና እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው። በመሆኑም፤ ለቀረበልን ጥያቄ ግልጽ መልስና፤ ድርድር ስለሚባለው ጉዳይም ያለንን አቋም ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ አድርገን ወስደነዋል። በዚህም መሠረት ለቀረበልን ጥያቄ የሰጠነዉን መልስና አቋማችንን በድርጅታችን ድረ ገጽ ላይና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን በኩል በይፋ ለመግለጽ ወስነናል።

በድርድር ስለሚመጣ ለውጥ ያለን የመርህ አመለካከት:

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዳደረግነው ድርጅታችን ከምሥረታው ጀምሮ የትግል ስልቱን ሲወስን እምነቱ አድርጎ የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን በሰላማዊ መንገድና በድርድር ቢመጣ በእጅጉ የሚፈልገውና የሚመኘው መሆኑን ነው:: ድርጅታችንን ወደ ሁለንተናዊ ትግል የገፋው በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው የወያኔ እብሪት ብቻ ነው:: የቀረበልን ምርጫ በባርነትና በውርደት መኖር ወይም ለነፃነት እየታገልን መሞት ቢሆን ኖሮ ንቅናቄያችን የሚመረጠው ምን ግዜም ለነፃነትና ለአገር አንድነት ታግሎ በክብር መሞት መሆኑን በተደጋጋሚ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል። ይህ የማይናወጥ አቋማችን ደግሞ ለይምሰል የተቀመጠ አቋም ሳይሆን ከልባችን የምናምንበትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቻችንን ያሰባሰብንበት አቋም ነው። ዛሬ በትግሉ ግንባር የምንንቀሳቀሰውና ወደ ግባችን የሚወስደንን ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰድን ያለነውም በዚሁ አቋማችን ዙሪያ ነዉ።

ይህ አቋማችንና እምነታችን በአንድ ላይ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁለት መርሆችን አጣምሮ የያዘ ነዉ። አንደኛው፣ ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ዋና ውጤቱን፤ ማለትም ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት መሆኑን ነው::

በእኛ በኩል ድርድሩን አስፈላጊና ጠቃሚ የሚያደርጉት መነሻ የፖለቲካ እሳቤዎችም ከእነኝሁ ሁለት መንታ ገጽታዎች የሚመነጩ ናቸው:: በድርድር ለሚገኝ ፍትሀዊና እውነተኛ ውጤት ክፍት መሆናችንን ሁሌም እናሳያለን፤ ነገር ግን ይህን የምናደርገው የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት መከፈል አለበት የሚለውን መሠረታዊ የአካሄድ መርህ በመመርኮዝ እንጂ መርሀችንን ለድርድር ለማቅረብ እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል::

ስለዚህም:

ሀ) የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆን ይኖርበታል:: ይህ ዋናው ግብ ሆኖ ከዚህ በመለስ የሚኖሩ በሂደት የሚገኙ አነስተኛ ግቦች ሊኖሩ ይችላሉ (ለምሳሌ የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታት…ወዘተ):: ሆኖም በምንም አይነት ለእነኝህ መለስተኛ ግቦች ተብሎ ዋናውን ግብ የሚያሳጣ ወይንም ጊዜውን ያላግባብ የሚያስረዝም ድርድር፣ ድርድር ነው ብሎ ድርጅታችን አይቀበልም። ስለዚህም ዋናው የድርጅታችን ዓላማና ግብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ፣ በፍጹም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም::

ለ) በግንቦት 7 እምነት ማንኛውም ድርድር ወያኔ ከግንቦት 7 ጋር በተናጠል የሚያደረገው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያካተተ መሆን ይኖርበታል:: ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም:: ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል:: የሚደረገው ድርድርም ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት::

ሐ) ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አንድን ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው:: ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ አይነት ድርድር ከሕዝቡ በተደበቀ ሁኔታ በሚስጥር የሚካሄድበት ምንም ምክንያት የለም::

2) ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋር ከተደረጉ ድርድሮች ያገኘናቸው ተመክሮዎችና ከዚህ በመነሳት ወደፊት በሚደረጉ ምንም አይነት ድርድሮች እንዳይደገሙ ለመጠበቂያ የሚሆኑ ከአሁኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች

ከማንኛውም ወገን ጋር የሚደረግ ድርድር የተደራዳሪዎቹ ምንነት፤ ውስጣዊ ባህርያቸውን፤ ከተለምዶ ተግባራቸው ያላቸውን ተአማኒነትና ወደዚህኛው ድርድር ያመጣቸውን ምክንያቶች በበቂ ከመገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ነው:: ቃሉን አክባሪና ተዓማኒ ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ድርድርና ያለፈው ታሪኩ ምንም አይነት የተዓማኒነት ባህርይ ከማያሳይ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ለድርድሩ የሚደረግ ዝግጅት ለየቅል ናቸው:: ይህ ማለት ግን ተዓማኒነት ካለው ኃይል ጋር ብቻ ነው ድርድር የሚካሄደው ማለት አይደለም:: በፍጹም ተዓማኒ ካልሆነ ኃይል ጋር የሚደረግ ማንኛውም ድርድር ግን ድርድሩ በእርግጥም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ጠንካራ መጠበቂያዎች (System of Verification) እንዲሁም ግልጽ የመተግበሪያ ሥርዓቶች (Implementation Mechanism) ሲደረጉለት ብቻ ነው ከምር ሊወሰድ የሚችለው:: ከዚህም ባሻገር ግን መጀመሪያውኑ ወደ ድርድር የሚመጣው ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሳይሆን በእዉነተኛ መንፈስ ከድርድር የሚመጣውን ውጤት በመፈለግ መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” ምልክቶች ሲያሳይ ነው በእርግጥም ወደ ድርድር የመጣው ከልቡ ድርድሩንና ከድርድሩ የሚመጣዉን ዉጤት ፈልጎ መሆኑን ለማመን የሚያስችለው::

ወያኔ ከተቀናቃኝ ወገኖች ጋር “ድርድር” ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜዉ አይደለም:: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ምናልባት በኃይል ይበልጡኛል ብሎ ከሚያምናቸው ወገኖች ጋር ካልሆነ በስተቀር፣ በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ጊዜ ለቃሉ ታማኝ፤ ለመርሁ እውነተኛ፤ ለደረሰበት ስምምነት ተገዢ ሆኖ አያውቅም:: ይልቁንም ሶስተኛ አደራዳሪ ወገኖችን በሚያሸማቅቅና በሚያሳፍር መልኩ ውሸትን እንደ አዋቂነት፤ ማጭበርበርን እንደ ብልጠት፤ የተስማማበትን በገሀድ ማፍረስን እንደ የአመራር ብልሀት አድርጎ የሚያይ፤ ምንም እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት እኩይ ኃይል ነው:: ከራሱ የድርጅት ጥቅምና በስልጣን ከሚገኝ የዝርፊያ ሀብት ማካበት ባሻገር፤ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ብሎ የራሱን ጥቅም አሳልፎ የሚወስደው ምንም እርምጃ እንደሌለ በተግባር በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን ኃይል ነው:: በግንቦት 7 ውስጥ ያለን ወገኖች ይህንን የወያኔ ባህርይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሌሎች ጽፈውት ያነበብነው ሳይሆን፣ እራሳችን በተግባር በተሳትፈንበት ሂደት ያገኘነው ጥልቅ ግንዛቤ ነው:: ይህንን ደግሞ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከድርጅቱ ታሪክ ጋር የተጣበቀ፤ በአመራር አባላቱ ላይ እንደ ግል ባህርይ የሰረጸ መሆኑን እስክንገነዘብ ድረስ በተደጋጋሚ የተመለከትነው ነው:: ስለዚህም ከዚህ ኃይል በኩል የሚመጣን የ “እንደራደር” ጥያቄ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት በፍጹም አንፈቅድለትም:: ስለዚህም ከላይ በመርህ ደረጃ ከጠቀስናቸው ሶስት ጉዳዮች በተጨማሪ ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት ወያኔ ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን::

እነኝህም፣

ሀ) ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት:: ይህ ደግሞ በግልጽ የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ማጠቃለል አለበት።

ለ) በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ ወያኔ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር አለበት።

ሐ) በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብዮ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።

መ) ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።

ሠ) ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ አለበት።

እነኝህ ከላይ ያስቀመጥናቸው በወያኔ በኩል የሚወሰዱ “የመተማመኛ” እርምጃዎች ለተቃዋሚዎች ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም:: ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም ስለማንችል ነው ::

እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የምንታገል ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን የምንገፋበት እንጂ በምንም አይነት ለአንድ አፍታም ቢሆን በድርድር ስም የማንዘናጋ መሆኑን አበክረን እናስታውቃለን::

የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣

ኅዳር 23፣ 2006 ዓ:ም
http://www.ginbot7.org/2013/12/02/%E1%8 … %E1%89%80/

የእፎይታ ጊዜው የኮሚቴዎቻችንን የፍርድ ቤት ውጤት ተምርኩዞ እንደሚያበቃ ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ::

መንግስት በኮሚቴዎቻችን ላይ የጥፋተኝነት ብይን የሚሰጥ ከሆነ የእፎይታ ጊዜው እንደሚያበቃ እና በአዲስ ጉልበት ሰላማዊ ተቃውሞው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ፡፡

ሙሉውን መግለጫ ከዚህ በታችን እንደሚከተለው ይቀርባል፡

ከዒደል ፊጥር አስቀድሞ የታወጀው የእፎይታ ግዜ ማብቂያ ከኮሚቴዎቻችን የፍርድ ሂደት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኖረዋል፡፡ በርካታ መስዋእትነት በከፈልንበት ሰላማዊ ትግላችን ውስጥ ኮሚቴዎቻችንን ነፃ ማውጣት አንዱ ጥያቄያችን መሆኑም ይታወቃል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ደጋግሞ እንደገለፀው ለዚህ ጥያቄው መሪዎቻችንን በነፃ ከማሰናበት ውጪ ምንም አይነት መልስ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ መሪዎቻችንን በቀጠሮ ዳግም ማጉላላት ወይም በሃሰት ተመስርቶ መፍረድ በእፎይታ ጊዜው ርዝመት እና ከዚያ በኋላ በሚኖረው ትግላችን ጥልቀት ላይ ግልፅ ተፅእኖ ይኖረዋል፡፡ ይህ ማለት ግን ከእፎይታ ጊዜው በኋላ ለሚኖረን ረጅም ጉዞ የመንግስትን እግር እየተከታተልን መሪዎቻችንን በመያዣነት እንዲጠቀምባቸው እንፈቅዳለን ማለት አይደለም፡፡

በእፎይታ ጊዜው ሰላማዊ ትግላችን በሚገባ ተገምግሟል፡፡ ብዙሃኑ የተሳተፈበት የቀጣይ አቅጣጫ ቀረፃ እና የአካሄድ ስልትም ተነድፏል፡፡ በዚህ ረገድ የእፎይታ ጊዜው ለተገቢው ስልታዊ ጥቅም ውሏል፡፡ በዚህ ወቅት የተከናወኑ አበይት ተግባራት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚገለፁ ይሆናሉ፡፡ ቀጣይ አቅጣጫችን እና የትግል ስልታችን የእፎይታ ጊዜው ማብቂያ እስከሚታወጅ ድረስ ይፋ ባይሆንም በነዚህ ጊዜያት መንግስት እየመረጠ ያለው አካሄድ የህዝቡም አቅጣጫ ምን ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ የሚሰጥ ነው፡፡

በቀሪው ጊዜ የመሪዎቻችን የፍርድ ሂደት እንደመጨረሻ ግብአት ተወስዶ የእፎይታ ጊዜው ማብቂያ እና የቀጣዩ ጉዞ ጅማሬ ይሆናል፡፡ የመሪዎቻችን የፍርድ ሂደት ላነሳናቸው ጥያቄዎች መፍትሄ የማፈላለጉ ሂደት ቀጣይ ጉዞ ወይም በጥያቄዎቻችን መልስ ማጣት ማግስት የሚጠነሰሰው ሌላው ትግል መጀመሪያ ይሆናል፡፡

ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡

ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ህዝቦች ይልቅ የሚያመሳስሉን፣ የምንጋራቸው በርካታ እሴቶች አሉን፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያውይነታችን (ዜግነታች) የጋራችን ነው፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ ተብሎ በጅምላ ዜግነት ሊሰጠው አይችልም፡፡ አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ለመሆን መደራጀት አይጠበቅበትም፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ‹‹ኦሮሞ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ግለሰብ አማርኛ ተናጋሪዎች ‹‹አማራ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ሶማልኛ ተናጋሪዎን ‹‹ሶማሊ››…….እያሉ ነው ኢትዮጵያውያንን ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› በሚል አዲስ ማምነት የሚደረድሩን፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ የሚባለው ከግለሰቦች እንጅ ከምንም የመጣ አይደለም፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር ካለበት መጀመሪያ መቅደም የሚገባው የስሪታቸው የግለሰቡ መብት ነው፡፡
‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ትግሬ….› እየተባሉ የተቦደኑት ህዝቦች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ እንዲያውም ኦሮምኛ ተናጋሪው ‹‹ኦሮሞ›› ከሚባለው ውጭ ከአማርኛ ተናጋሪው ጋር የሚጋራው በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ አማርኛ ተናጋሪው ‹‹አማራ›› ከተባለው ይልቅ ከኦሮምኛ ተናጋሪው ጋር የሚያመሳስሉት በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ ለአብነት ያህል ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ፣ ….ተናጋሪው ህዝብ ከቋንቋውም በላይ አንዱ የሌላውን ድንበር ተሸግሮ ከሌላኛው ቋንቋ ተናጋሪ ጋር በእምነት፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ገመዶች ይገናኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአንድ ብሄር ሰዎች አይደሉም፡፡ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እንዲህ እስካሁን በጥንካሬ የዘለቀው በድንበር ተሸጋሪው ማንነቱ እንጅ በጠባብ ‹‹የብሄር›› ማንነት ታጥሮ አይደለም፡፡ ኦርቶዶክሶቹ፣ ፕሮቴስታንቶቹ፣ ካቶሊኮቹ በ‹‹ብሄር›› የታጠሩ አይደሉም፡፡
የአንድ ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ…መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ በ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ሶማሊ…….›› ስም በጅምላ ከመነገድ ያለፈ ስለ እያንዳንዱ ህዝብ አያስጨንቀቃቸውም፡፡ 30 ወይንም 40 ሚሊዮን የአንድ ‹‹ብሄር›› ህዝብ በአንድ ጉዳይ ሊከፋ አይችልም፡፡ ቢያንስ ከገዥዎች ጋር ሆኖ የሚጠቀም አይጠፋም፡፡
ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን ግን የሚድበሰበስ ነገር አይኖርም፡፡ ሁሉም የግለሰብ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የአገሪቱ ህዝብ መብት ይከበራል፡፡ የግለሰብ መብት ካልተከበረ ግን የማንም መብት ሊከበር አይችልም፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡
Getachew Shiferaw

Image

ጥሪው የማህጸን ነበር። ምላሹም የዕትብት ሃዲድነት ነበር።

ጤና ይስጥልኝ ሞገደኛው ተክሌ እንደምን ሰነበትክ? ደህና ነህ ወይ? የብዕር አጣጣልህ እንደ አቤ ቶኬቻው ውብ ስለሆነ ለረጅም ጊዜ እያደንኩ አነባለሁ። ጠረባህንም አክሎ። በጠረባህ ዙሪያ አንድ ቀን የምለው ይኖረኛል …. ዛሬ ግን ልታገሰው ስላልቻልኩት ማለት ፈለግኩ ….. በሦስት ነገሮች ዙሪያ …. እንዲህም እላለሁ …. እኔው ….

ሳውዲ አረብያ ላይ ለደረሰው ውርደት ተጠያቂው አረሙ ወያኔ ነው። የወያኔ ፖሊሲ ነው ለዚህ የትውልድ ፍልሰት በይፋ የፈቀደው። ሙጃው ወያኔ የተመሰረተበት ይህ ነውና። እኛ ጊዜ እዬጠበቀ ወያኔ በሚያፈነዳው ፈንጅ ዙሪያ ጥቃቱን ለመመከት ዕለታዊ ሰልፍ ስለምነደርግ ነው እንጂ የወያኔ መሰረታዊ ፍጥረት ትውልድን ከማፍለስ ላይ በመሆኑ መርዙ የማይነካውና የማያካተው አንዳችም ነገር የለም። ይህ የጥፋት አዟሪት የሚነሳው ኢትዮን ቅኝ ለማደረግ ህልማቸው ካልተሳከ ሀገሮች ምኞት ነው። ስለሆነም ዒላማችን ሊነሳ የሚገባው ከጥንስሱ መሰረት ላይ መሆን አለበት እላለሁ እኔ። ይህን መሰረት ያያዘ የኢትዮጵያዊነት የጥላቻ ፖሊሲ ከሥሩ ለመንቀል ደግሞ ከበቀለበት ማንፌስቶ ነው የትግሉ ወላፈን መነሳት ያለበት የሚል ጠንካራ አድምታ ነው ያለኝ በግሌ። መዳህኒቱም የወያኔ ማንፌስቶ ግብዕተ – መሬት ሲፈጸም ብቻ ነው። የፈውሱ ፍሬ ነገር ከሃርነት ትግራይ ህልፈት ላይ ነው። እያንዳንዱን የወያኔ የጥፋት ሆነ የቅጣት የበቀል እርምጃ በሥርዓት በተጠና ሁኔታ ቢመረመር ቢተነተን – ቢነበብ – ቢፈታታሽ ድርጀቱ ከተፈጠረበት እንቁላል አስኳል ውስጥ ይመነጫል።

ለማንኛውም በሳውዲ ላይ የተሰነዘረብን የጥቃት እርምጃ ለመቃወም እልፎችን ያስቆጣው ሰላማዊ ሰልፎች ወያኔ ኢትዮጵዊነትን የቀማበት ወይንም የነጠቀበት አልነበረም። በጭራሽ።“ኢትዮጵያዊያንን ለማስተባበርና ሳኡዲዎችን ለመጀንጀን የምናቁዋቁመውን ኮሚቴ መለየት ያለብን ይመስለኛል፡፡ሰልፎቹንግንተቀምተናል፡፡ ከልጅ ተክሌ ጹሑፍ የተወሰደ”

ልጅ ተክሌ …. ምን አልባት አንተ በላህበት ሀገር ሆኖ ከሆነ ከተጠያቂዎቹ ውስጡ አንዱ ትሆናለህ። ከማንም በተሻለ ተደማጭነቱም፤ ተቀባይነቱም አለህና! ሁልጊዜ አንተ ታንከባላለህ ድክመቶችን ወደ ሌሎች። …. አንተ እኮ ምርጥ፤ ልዑቅ ከሚባሉ ኢትዮጵውያን ውስጥ አንዱ ነህ። የፖለቲካ ተንታኝ …. በታኝ፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ሃያሲ፤ የምትፈልገውን ጽፈህ ተከብረህ የሚወጣለህ፤ ያልታገድክ፤ ገድብ ያልተሰረባህ፤ አንቱ የተባልክ ሚሊዮኖች በምታገኘው መድረክ ሁሉ በአክብሮት የሚያዳምጡህ ዕድለኛ ወጣት ነህ …. እና ካናዳ ላይ ወያኔ ኢትዮጵያዊነት ለመቀማት መድረክ ሲያገኝ አንተ የት ነበርክ? ምንስ ትሰራለህ? ….. እራስህን ጠይቅ።

እኔ ሲዊዘርላንድ ነው የምኖረው። ሰላማዊ ሰልፉን ማን እንደጠራው አላወቅም። ከኢሳት ሰምቼ ነበር የሄድኩት። እንዲህ ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ ሲዊዘርላንድ ውስጥ አላዬሁም። እጅግ በጣም ብዙ ሰው ነበር። ቁጭቱ፤ እልሁ፤ እንባው፤ መቃጠሉና መንደዱ … የነጠረው ሰንደቅዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ካለምንም ቅይጥ በነፍስ ወከፍ ተይዞ ነበር …. እኔ በሰዓቱ እጠረት ነድጃለሁ። ምክንያቱም እዛው ባድርም አልጠግብኩትም ነበርና። ወንድምዓለም ጊዜው ከኖረህ እንዲህ ሰርቸዋለሁ አዳምጠው www.lora.ch.tsegaye ዬ 21.11.2013 ወይንም … በዚህኛው ሊንክም ይቻላል ….

…. ይገርማል። ለመሆኑ ለዛውም ውጭ ሀገር ወያኔ በምን ሞራሉና አቅሙ ነው እኛነታችን፤ ማንነታችን፤ ውስጣችን የመቀማት አቅሙስ ሞራሉስ የሚኖረው። ወንድሜ ሆይ! በአባይ ቦንድ ምን ያህል አረሙ ወያኔ እንዴት እንደ ተራገፈ አላዬህንም? አይታሰብም! ተዎው እኛን ወያኔ ከመጠበት ዘመን ጀምሮ የተወለዱት አዲስ ፈርጦች እኮ ናቸው የኢትዮጵያዊነት መሪና አደራጅ የሆኑት። ይህ ከድንቅ በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት እኮ ገና በሥነ – ምርምር ብዙ የፈካ ተግባር ከፊት ለፊቱ የሚጠብቀው የሰማይ ጥበብ ነው። ተቀማን? አፈርኩልህ ስለቃሉ ….. አኔ የብዕርህ ፍቅረኛ። ጥሎብኝ ደግሞ ድምጽህንም እወደዋለሁ።

ሳውዲ ላይ ለዛውም የውጭ ዜጋ በሳውዲ መሬት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሲደርግ እኮ ሰማዕት ኢትዮጵያውያኑ የመጀመርያ ናቸው። በማይቻልበት ቦታ ችለው ግን የተሰውበት የተጋድሎ ልዩ ታሪክ …..። የበቀል አምላክ እንደሚበቀለው የሳውዲን መንግስት ቀን ይናገራል …. አምላካችን እንደ ቻይነቱ ቁጡ ነውና።

ሰላማዊ ሰልፉ በመላ ዓለም የኢትዮጵውያን የአትንኩን አኅታዊ ድምጽ … ደመ – ነፍሱን ወያኔን ያራጋፈ፤ ያደናበረ፤ ከእንቅልፉ የቀሰቀሰው፤ ያተራመሰው፤ ከእንሰሳነት፤ ከአራዊትንት አስተሳሰቡ ተግ ብሎ ሰው ስለመሆኑ እራሱን እንዲጠይቅ ያፋጠጠበት፤ ወያኔ ከዛቀጠበት አርንቋ ለመውጣት እፍ ግብ ያለበት በፍጹም ሁኔታ የተዋረደበትና ማንነቱ ያጋለጠበት ነበር ማለት ይቻላል። እውነቱን ልንገረህ ትናንት የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ ከወያኔ አስተዳደራዊ ተቋም በላቀ ሁኔታ ዕውቅና ያገኘበት። ኢትዮጵያዊነት የወያኔን የ40 ዓመት ሴራ አክሽፎ የተሞሸረበት – የተመሳጠረበት ታላቅ አብነታዊ የኢትዮጵውያን የወል የጥሪት ውጤት ነበር። ካፒታላችን ቅርሳችን ነው ለዛሬ። ለነገ ደግሞ ትውፊታችን …..

ሌላው አንተ እንዳትቀማ በራስህ ላይ ማተኮር እንዳለብህ የሚያመለክት ነገርም ከጹሑፍ አዬሁ …. እንዳላዬሁ ሆኜ ላላፈው አልፈለግሁም። ምን? ምን አልክ ወንድምዓለም …. „„…የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ፤ ከዚህ ከሳኡዲ ችግር ጋር በተያያዘ ያቁዋቁዋምነው አለማቀፍ ኮሚቴም፤ አስር ሀያ አመት ከምናደርግበት የትግል ስልት ብዙ ፈቀቅ ያለ አይመስልም፡፡ የኮሚቴው ሙሉ ዝርዝር ባይኖረኝም፤ የሶስቱ ሰዎች ስም እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ኮሚቴው ዘመኑን ያልዋጀ፤ የአንድ ብሄር ስብስብ ነው የሚመስለው፡፡ ስብስቡ አለማቀፍም አገርአቀፍም ደረጃውን እንዲጠብቅ አልተደረገም፡፡ “ …. „ብንቀበለውም ባንቀበለውም፤ በአደባባይ እንደዚያ ብለን ባናውጅም፤ ይሄንን የሳኡዲን ግፍ ለማለስለስና ለማስቀልበስ የምናቋቁማቸው ተቁዋማትና ስብስቦችም ሁኑ ሌሎች መሰል ፖለቲካዊና ሲቪክ ማህበራቶቻችን፤ በተዘዋዋሪ ይሄንን የሀይማኖትና የብሄር ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገቡ መሆን አለባቸው፡፡ ከልጅ ተክሌ ጹሑፍ የተወሰደ” ዬት የት እዬተጓዝክ ነው እናትዬ …. አዬህው በወያኔ የጎጥ ፖሊሲ ምን ያህል እንደ ሰመጥክ፤ እዬተጠቃህም እንደሆነ …. እጅም እንደ ሰጠህ። „እናስተውል“ ይላሉ አባቶቻችን …. እኔ ስለተደራጀው ግብረኃይል እራሱ በነፍሱ ስላለ የሚለውን ይበል ….

ነገር ግን እንደ አንተ ዓይነት ወንድም ግን በብሄረሰብ ስብጥር ላይ ማተኮሩ በጣም መውረድ ነው። ይህ የሚመችህና የሚደላህ ከሆነ ከቶ ስለምን ተሰደደክ? አልገባኝም። የእኔ እናት ጎሰኝነት፤ መንደርተኝነት እኮ ኋላቀርነት ነው። ኋላቀርንት በኢኮኖሚያዊ ስሌቱ ያልተመጣጠነ እድገት ማለት ነው። በአስተሳሰብ ስሌት ስንሄድም ያው ያልተመጣጠነ እድገት ነው …. በ21ኛው ምዕተ ዓመት ከቤተሰብ ቀጥሎ ካላው ጎሳ ላይ መቆም ምን ሊሉት ይቻላል ከኋላቀርነት ውጪ

እባክህ እያንዳንዱን ነገር በዚህ ዝርዝርና ምንዛሬ አታሰባጠረው …. ከዚህ መጠራቅቅ መውጣት አለብህ። አዎና! በአንድ ወቅት አንድ ቅዱስ አባታችን ከዚህዓለም ስደት ላይ እንዳሉ ሲያርፉ ዬእምነት ልዩነት ሳይኖር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቀብር ሥርዓቱ ላይ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን ስሜቱን አድንቀህ ተከታታይ ጹሑፎች በኢትዮ ዛሬ ላይ አስነብበህን ነበር። ያን ጊዜ ስትጽፍ ጎሰም አድርገህ የጻፍካት ነበረች። ሊቀ ሊቃውንቱን ብታገኛቸውና ልምዳቸውን ቢያካፍሉህ ግን ሸንቆጥ አድርገህ ያለፍካት ነገር „ላም ባለወለበት መሆኑን ትረዳ በነበረ“ ለማንኛውም ሁላችንም ….. በዚህ ስሌት ከተጓዝን …. ምን አልባት ያን የፍቅር ቤት ደርመሾቹ እኛው ሆነን እናርፋለን። የወያኔን የተጠያቂነት ጠቀረማ ዘመንም የመሸከም ግዴታ ሊኖርብን ነው። በዚህ የፋደሰ መንገድ ከተጓዝን። ከወያኔም እንሻል ቢያንስ እኛ …. በስተቀር ግን ዛሬም ጭቃ ነገም ረግረግ …. መዛገጥ … መዝገጥም – ኪሳራ መከዘን ይሆናል ዕጣ ፈንታችን።

ሌላው ያነሳህው …. እንዲህ ላሉ ድንገተኛ ችግሮች ቋሚ አካላት አለመኖራቸው …. እንዳሳዘንህም ጽፈኃል። አንተ እንዲህ ያለ የቀደመ ሃሳብ ከነበርህ ባለህበት ሀገር ማቋቋም ትችል ነበር አኮ። ማን ጌታ አለብህ። አቅሙ እንዳለህም አስባለሁ። በሌላው ድርጅት ላይ ካለይሉኝታ የምትሰንዝራቸው ወቀሳዎች እዳይደገሙ ጥርት ያለ ብቁ ተቋም። ከስህተት የጸዳ፤ ምርጥ ዘር የሚያፈራ፤ ፍጽምና ሸማው የሆነ ድርጀት የማቋቋም ሙሉ መብት ነበረህ። አለህም። እንዲህ በዬጊዜው እርር ድብን ከምትል …. ልጅ ተክሌ የአንተ ጹሑፍ አምልጦኝ አያውቅም፤ ቃለ ምልልሶችህም ከሌላ ድርጀቶች ጋር አንተ የደረካቸውም ሆነ አንተም በኢሳት ባለህ ቦታ …. ከሌሎች ጋር ያደረከውም …..

እኔ እንደማስበው ወያኔ ብዙ ቢፈታታነውም የኢትዮጵያ ሰብዕዊ መብት አስከባሪ ጉባኤ በፕሮፌሰር መስፍን ይመራ የነበረው፤ እስረኞችን ለመታደግ ውጭ ሀገር የተቋቋመው፤ የአዲሱቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ፤ ሌሎቹም … በተጨማሪም በኢሳትም ሰብዕዊ መብት በሚመለከት ራሱን ያቻለ መመሪያ መኖሩ …. ጅምሩ መልካም ነው። በዬጊዜው እስር ቤት የሚማቅቁት ጋዜጠኞች፤ ከዚህም ባለፍ ሥምና ዝና የማይፈልጉ፤ ድምጻቸውን አጥፈተው ከዬሀገሮችም ሆነ በድንበር ዘለልም ከዓለም ዓቀፍ የሰብዕዊ መብት ድርጅቶች ጋር የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉም አውቃለሁ። ይደክማሉ። ይሰራሉ።

እኔ በምኖርበት ሲዊዘርላንድ የሰብዕዊ መብት ረገጣ በኢትዮጵያ የቆረቆራቸው ወጣቶች ሶሎቶርን በሚባል ከተማ በ2010 የመሰረቱት አንድ ግብረኃይል አለ። ጥቅምት 12/2012 አቶ ኦባንግ ሜቶ ከአዲሲቱ ኢትዮጵያ የክብር እንግዳ የነበሩበት፤ ከግንቦት 7 ዶር. ታደሰ ብሩ፤ አቶ ወንድምአገኝ ጋሹ ከኢሳት በተገኙበት በዙሪክ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ

አካሄዶም አይቻለሁ። ስብሰባው ጥሩ መንፈስ ነበረው። ሃሳቦች በሚገባ ተንሸራሽረዋል። ከጀርመን ሙንሽን የመጡ ወገኖችም ነበሩ። …

…. እኔ እንደ አንተ ሃያሲ ስለሆንኩ ከልብ የተደሰትኩበት ስብሰባ ነበር … ማለት እችላለሁ። ያው አልጻፍኩትም። ልመናው ሆነ ድጅ ጥናቱ ገደለኝ። በዬድህረ ገፆች አውጡልኝ በማለት መንከራተት እንጂ …. ያን የመሰለ የወጣቶች ጥረት ወሼኔ ተብሎ በተፃፈለት ነበር። በሌላ የሚዲያ ሽፋን ማግኘቱን ባላውቅም …. እኔ ግን በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜ በዜና ሰርቸዋለሁ ….. ከዚህ ጋር በተያዬዘ መልኩ በሰብዕዊ መብት ዙሪያ ጠንከር ያሉ ተግባራት በሲዊዲንም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዳለ ይሰማኛል።

…. በተጨማሪ በዬሀገሩ የሚስማሙ፤ የሚግባቡ፤ የሚደማመጡ ሰዎች የራሳቸውን የግልና የወል ጥረት እንደሚያደርጉም አስባለሁ። ሌላው ቀደም ባላው ጊዜ አዲስ ድምጽና የሲዊዲን እንዲሁም ሌሎች የነፃነት ትግሉ ቤተኛ የሆኑ የኮሚኒቲ ራዲዮኖች ሆነ ማህበራዊ ድሀረ ገፆች በርካታ ተግባራትን ከውነዋል በዚህ ዙሪያ ። እንዲሁም የኢትዮጵውያን የመወያያ ሩሞች የራሳቸውን ሁለገብ ተግባር ሲከውኑ ቆይተዋል። የትኛው የአፍሪካ ሀገር ነው እንደ ኢትዮጵውያን በሀገሩ ጉዳይ ትርጉም ያለው ተግባር ውጭ ሀገር የሚከውነው። እውነት ለመናገር ተጽፎ አያልቅም ….

ልጅ ተክሌ … ችግራችን ከቁጥር በላይ ነው። በሁሉም ቦታ ሁሉም ሊሆን ስላማይቻል ክፍት ቦታ እዬፈለጉ ቀዳዳ መሸፈን የእኔም የአንተም ግዴታ ነው። ሲናሪዮ ሆነ ፕሮቶኮል የማይጠይቁ ብዙ የተግባር መስኮች አሉና። ሌላው ግን እኛም ስደተኞች ነን። ብዙ መከራና ፈተና በግል ህይወታችን እዬፈተለን ነው። ይህም ሆኖ ውጪ ያለነው ኢትዮጵውያን ሁሉንም ሆነናል በአቅማችን ልክ። ከነድክመቶቻችን ለበርካታ ነገሮች በባለቤትነት ስሜት የምንችለውንም አድርገናል እያደረግነም ነው።

ስለሆነም በማናቸው ጊዜ በድንገተኛ የእናት ሀገር የእማ ጥሪ፤ ጠሪም ተጠሪም ወቃሽም ተወቃሽም የለም። ሊኖርም አይገባም። መወቀስ ካለብን ሁላችን። መመስገን ካለብን ደግሞ ሁላችን። ቁስሉም ህምሙም ስቃዩም እኩል ነው። በእናት ሀገር የችግር ቀን የድረሱልኝ ጥሪ አንዱ የክት ሌላው የዘወትር፤ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ሊሆን አይችልም …. ከወያኔ በስተቀር …. ወያኔ ይህን ለማጥፋታ 40 ዓመት ቢሰራበትም ንጉሥ ዳዊት በወጣትነቱ ማህልዬን፤ በጎልማሰነቱ ምሳሌን በእርጅና ዘመኑ ደግሞ ሁሉም ኖሮት ዓለምን ፈትሾና አይቶና መርምሮ ከመንፈስ ቅዱስ በተሰጠው መክሊት ከንቱነትን አመሳጠረ …. በሳውዲ የኢትዮጵያዊነት መከራ የወያኔን ከንቱነት ያነበበ፤ የተረጎመና ያመሳጠረ ነበር ዓይንም ህሊናም የለውም እንጂ …. ሙጃው ወያኔ።

እናሳርገው …. በወሳኝ ጉዳይ። …. አንድ ነገር ኢህድግ …. የሚባል ኑሮ ያውቃልን? ከዚህ የወያኔ ሸንኮፍ ተጠቂነትም መውጣት ያለብን ይመስለኛል። የልጅ ተክሌ ጹሑፍ ለወያኔ የጥፋት ሴራ ዕውቅና የሰጠ መሰለኝ። ሀገር ትውልድ ታሪክ ባህል እምነት ያጠፋ ወያኔ ነው። መነሻው መድረሻውም ተልዕኮውም በመሆኑ …. ቅርጽ ነው ኢህድግ ይዘቱ TPLF ነው ትናንትም ዛሬም …. በሌለ ነገር ላይ ምስክርነት …. መስጠት —- ትዝብት ነው … ይበቃኝ። ጨረስኩ።

እኔ እኔ ነኝ የምለው፤ እኔ በእኔ ውስጥ ሳይሾልክ እኔን ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው።

እኔ እኔ ነኝ የምለውም የጠላቴ ዒላማ ተጠቂ አለመሆኔን በፍጹም ሁኔታ በእኔ ውስጥ ሳረጋግጥ ብቻ ይሆናል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Image
ሥርጉተ ሥላሴ

ምንሊክሳልሳዊ-በሰራዊቱ ውስጥ የተነሳውን ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ተከትሎ የቀድሞ የኢሕዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ እንደሚቀነሱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:: በየቀኑ ለስብሰባ የሚቀመጠው ሕወሓት መራሹ የጄኔራል መኮንኖች የአንድ ብሄር ቡድን ተጠንቷል ባለው እና የተወያየበት ሰነድ እንደሚያመለክተው በሰራዊቱ ውስጥ የሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች የሚፈጠሩት ከአማራው እና ከኦሮሞው ወገን ከሆኑት መኮንኖች ሲሆን ይህንንም የሚመሩት የውስጥ መዥገር የሆኑት የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ስለሆኑ ከሰራዊት ውስጥ በመቀነስ በተለያዩ መንገዶች በወንጀል ለማጥመድ እና ከነማን ጋር እንደሚገናኙ አስፈላጊውን የደህንነት ክትትል ማድረግ ይገባል ሲል ተነጋግሮበታል::

እነዚሁ የለውጥ ጥያቄ ያነሱት የሰራዊቱ መኮንኖች ከተለያዩ የታጠቁ የጠላት ሃይሎች እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በመገናኘት የመንግስትን ህልውና እየተፈታተኑት ከመሆኑም ባሻገር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከቀድሞ ስርኣት የተወረሱ እና ለዲሞክራሲው እና ለልማቱ እንቅፋት ስለሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ተብሏል::ከግንቦት ሰባት እና ከተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘት በሰራዊቱ ውስጥ ያለነበሩ እና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በመፍጠር ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ሰዎችን በማስኮብለል መረጃ በማቀበል እንዲሁም አለመተማመን እንዲኖር በመስራት ከፍተኛ ደንቃራ ሆነዋል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ እንደገለጹት የቀረበው ሰነድ ለጄኔራል መኮንኖቹ ያልተበተነ ሲሆን የስብሰባው መሪ የሆኑት ኢታማጆር ሹሙ እጅ በመሆን ሰነዱ እየተነበበ የተወያዩበት እና ይህም የሚያመለክተ በሕወሓት ጀኔራሎች መካከልም መተማመን አለመኖሩን ያሳያል ብለዋል::በሙስና ከአስተዳደርዊ ባለስልጣናት በበለጠ የተዘፈቁት የሕወሓት ጄኔራሎች በስብሰባ እና አብዛኛው ንብረቶቻቸን በተዘዋዋሪ በመሸጥ ስራ ላይ እየተንቀሳቀሱ ሲገኝ በሱዳን በኢምሬት እና በአውሮፓ አገሮች እንዲሁም በአሜሪካ በቤተሰቦቻቸው ስም የተለያዩ ንብረቶችን በመግዛት ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮሽ ጨምረው ገልጼዋል::

Image

ምርጫ 97ን ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረትን የምርጫ ታዛቢ ቡድንን የመሩት አና ጐሜዝ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ መንግሥትና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ በመሰንዘር ይታወቃሉ፡፡

ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ በ26ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የመጡትን አና ጐሜዝን በዴሞክራሲ፣ በእስረኞች አያያዝ፣ በሰብአዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ነአምን አሸናፊ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ምርጫ 97ን ተከትሎ በእርስዎና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት ጥሩ የማይባል ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ያቀረቡት የቪዛ ጥያቄ እንዴት ነበር? ቪዛ መስጠት ያለመፈለግ አልያም ሌላ ነገር አጋጥሞዎታል?

አና ጐሜዝ፡- በፍጹም፡፡ ምንም ዓይነት ክልከላ ወይም እምቢታ አላስተናገድኩም፡፡ ለነገሩ የአውሮፓ ኅብረት የሰብአዊ መብተት ንኡስ ኮሚቴ ባለፈው ሐምሌ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት በአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር እኔም መሄድ እፈልግ እንደሆን ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔም መሄድ ብፈልግም ባልፈልግም ቪዛ አትሰጡኝ ምን ያደርጋል አልኩት፡፡ እርሱ ግን የለም እንሰጥሻለን አለኝ፡፡ እሺ ለአሁን የሥራ ባልደረቦቼ ይጓዙ የእኔ ጊዜው ሲደርስ አመለክታለሁ አልኩ፡፡ ስለዚህ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የአፍሪካ ፓስፊክ ካሪቢያንና የአውሮፓ ኅብረት ጥምር ስብሰባ ላይ ለመካፈል የቪዛ ጥያቄ አቀረብኩ፤ እነርሱም ያለምንም ቅድመ ሁኔታና ያለምንም ችግር ቪዛውን ሰጥተውኛል፡፡ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በማለፋቸው የተለየ የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ እንደሆነ የሚያሳይ ነገር ነው፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ለማምጣት ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ተረድቻለሁ፡፡ በተለይ ሙስናን በመዋጋት የጀመሩት ዕርምጃ ከፍተኛ የሥርዓቱን ባለሥልጣናት ሳይቀር ወደ እስር ቤት አስገብዋል፡፡ ይህም መልካም ጅምር ነው፡፡

ነገር ግን በኢትዮጵያ ከፍ ያለ ለውጥ ማየት እሻለሁ፡፡ ይህ የእኔ ብቻ ፍላጐት አይደለም፣ የኢትዮጵያውያንም ጭምር እንጂ፡፡ እዚህ በመምጣቴ ከስብሰባው ጐን ለጐን ሌሎች ሰዎችን በማናገር ለውጡ በእንዴት ያለ ሒደት ላይ እንዳለ ለመመልከትም እሞክራለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን በመምራት በ1997 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ውስጥ ስለነበሩ የአገሪቱን የምርጫ የዲሞክራሲና ሰብአዊ መብትንና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ያውቋቸዋል፡፡ አገሪቱ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንዴት ይገመግሙታል?

አና ጐሜዝ፡- እንደሚመስለኝ ድኅረ ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ያለው ዲሞክራሲያዊ ምህዳር ጠቧል፡፡ ከምርጫ 97 በፊት ከነበረበት ገጽታ አንፃር ብሶበታል፡፡ ምርጫውን ተከትሎ እልቂቶችን አይተናል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሲታሠሩ አይተናል፣ ለሲቪል ማኅበራት ምህዳሩ ሲጠብ አይተናል፡፡ እንደሚመስለኝ በበጐ አድራጐት ማኅበራት ላይ የወጣው ሕግ አሉታዊ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አላግባብ ጥቅም ላይ ሲውል አስተውለናል፡፡ ሕጉ እጅግ የተለጠጠ ትርጓሜ እየተሰጠው የተለየ ሐሳብ ያላቸውንና የሚቃወሙ ግለሰቦችን ለማጥቃት አገልግሎት ላይ ለማዋል እየሞከረ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ የተነሳ ሁኔታው የባሰበት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ምርጫ 2002 በቀዘቀዘ ሁኔታ ተከናውኖ አልፏል፡፡ የሥራ ባልደረባዬ ቴስ በርማን ምርጫውን ለመታዘብ በአውሮፓ ኅብረት ተወክሎ ነበር፡፡ ምርጫው መቀዛቀዙን ገልጿል፡፡ ምክንያቱም በምርጫ 97 ኅብረተሰቡ በስፋት ከመሳተፉ በተጨማሪ በምርጫው ለውጥ ይመጣል የሚል ተስፋ ነበረው፡፡ ይህ ተስፋውም እስከ ድምፅ ቆጠራው ድረስ የዘለቀ ነበር፡፡ ነገር ግን ሕዝቡም ሆነ እኔ ምርጫው መጭበርበሩን ተረድተናል፡፡ ስለዚህ በምርጫ 2002 ኅብረተሰቡ በአብዛኛው ወደ ምርጫ አልሄደም፡፡ እኩለ ቀን ላይ ሁሉም ነገር የተጠናቀቀበት የምርጫ ጣቢያዎች ነበሩ፡፡

የአውሮፓ ኅብረትን የወከለው ቴስ በርማን የምርጫውን ሪፖርት ለማቅረብ እንኳን ወደ አዲስ አበባ መመለስ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ሪፖርቱ ሒስን የያዘ ስለሚሆን ነው፡፡ ሒሱ ግን ገንቢ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ይህን ከልብ የመነጨና ቀና ሒስ መቀበል አልፈለጉም፡፡

እንደሚመስለኝ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ካለፉ በኋላ ነገሮች በሚገርም ሁኔታ ተለውጠዋል፤ የሚለወጡም ይመስለኛል፡፡ ይህም የመነጨው አመራሩ በመለወጡ ነው፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ለማምጣት እየሠሩ ይመስለኛል፡፡ ነገሮች ተጠናክረው እንዲጓዙ እንፈልጋለን፡፡ በፀረ ሙስና ላይ የተጀመረው ትግል፣ የዲሞክራሲያዊ ምህዳሮች መስፋፋት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች እንዲስፋፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲጠናከሩ፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ማየትን እንሻለን፡፡

እርግጥ ነው በተደጋጋሚ በመንግሥት በኩል የሚነገር መከራከሪያ አለ፡፡ ይህም እነዚህ ግለሰቦች የታሰሩት ጋዜጠኞች በመሆናቸው ሳይሆን በሽብርተኝነት ወንጀል ነው ይላል፡፡ እኔ ግን ይህን አልቀበለውም፡፡ ምክንያቱም አሁን አሁን ሽብርተኝነት የሚለው ሐሳብ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ዝም ለማሰኘት እያዋሉት ነው፡፡

ከአሁን በፊት በአገሬ የነበረው አምባገነን መንግሥት ይጠቀምበት የነበረው ቃል አመፀኛ የሚል ነበር፤ አሁን ግን ቃሉ ሽብርተኛ ሆኗል፡፡ እንደሰማሁት እነዚህ ሽብርተኛ የተባሉ ግለሰቦች ያለፉበት የፍትሕ ሥርዓቱ ፍትሐዊ አልነበረም፡፡ ግለሰቦቹ የሽብር እንቅስቃሴን ማድረጋቸው የሚያስረዳ በቂ መረጃ አልቀረበም፡፡ ለኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ጥሪ ማስተላለፍ ፈጽሞ የሽብር ተግባር ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የትኛውም ዲሞክራሲ ሊጠብቀው የሚገባ እውነተኛ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ድኅረ ምርጫ 97 ኢትዮጵያን አሁን ካለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር እንዴት ያነጻጽሩታል?

አና ጐሜዝ፡- አዲስ አበባ የቆየሁት ከመጋቢት ጀምሮ እስከ ምርጫው ድረስ እንደሆነ ማስታወስ ጥሩ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ጥቂት ተስፋ ሰጪ ነገሮች ነበሩ፡፡ መንግሥት በተወሰነ መልኩ የፖለቲካ ምህዳሩን ክፍት ለማድረግ ይሞክር ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የብዙኃኑን ሐሳብ ተቆጣጥሮት የነበረው ለአምስት ጊዜያት በቀጥታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው የፓርቲዎችን ክርክር ነው፡፡ ይህ ክርክር የሕዝቡን ሐሳብ ተቆጣጥሮት የነበረ ሲሆን፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ያንን በመፍቀዳቸው እንደ ተጸጸቱ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም ኅብረተሰቡ አማራጮችን በአግባቡ የተረዳበት ክርክር ነበርና፡፡

ድኅረ ምርጫ የተፈጠረውን ሁኔታም አስታውሳለሁ፣ በምርጫው ዕለት ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለምንም በቂ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ፡፡ ይህም ምን ያህል እንደ ተሸበሩ የሚያሳይ ነበር፡፡ ምርጫው በአጠቃላይ በሰላምና በሥርዓት ተካሂዷል ብሎ የሚያምን ከሆነ እንዲህ ያለ ውሳኔ ለምን አስፈለገ? ለምን ሕዝቡን አያማክሩም ነበር፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፣ ምርጫውን ለማጭበርበር በመታሰቡ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መሠረት አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የማወዳድረው ከቅድመ 97 ሁኔታ ጋር ነው፡፡ በዚያን ወቅት ቢያንስ በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በፓርላማ ውስጥ መቀመጫ ነበራቸው፡፡ አሁን ግን በፓርላማው መቀመጫ ያለው ተቃዋሚ አንድ ብቻ ነው፡፡

እርግጥ ነው አንዳንድ የማውቃቸው ግለሰቦች የሚዲያው ዘርፍ በትንሹም ቢሆን እየተከፈተ እንደሆነ ገልጸውልኛል፡፡ ነገር ግን እየተከፈተ ያለው የሚዲያው ዘርፍ ዋናው ሳይሆን አማራጭ የሆኑት ማኅበራዊ ሚዲያዎች ናቸው፡፡ እርሱም የሚመነጨው ደግሞ ሕዝቦች ከቴክኖሎጂ ጋር ባላቸው ቅርርብም ጭምር ነው፡፡ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የቴክኖሎጂ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ አሁን ያለውን ቴክኖሎጂ ለማገድ ከአውሮፓም ይሁን ከእስራኤል የምታመጣው ባለሙያ ለመቆጣጠር የሚሆንለት አይሆንም፡፡ በምትቀጥራቸው ባለሙያዎች ፌስቡክንም ሆነ ትዊተርን መቆጣጠር እጅግ አዳጋች ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ የተነሳ ባለሥልጣናቱም ወደ እዚያው ለመቅረብ እየሠሩ ይመስለኛል ምክንያቱም መንግሥት ሚዲያውን በሥነ ሥርዓት ካልከፈተው ሕዝቡ የራሱን መንገድ ይፈልጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ዲሞክራሲን፣ የሰብአዊ መብት አያያዝን እንዲሁም ስለ እስረኞች ጉዳይ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል?

አና ጐሜዝ፡- አዎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት አባዱላ ገመዳ ምሳ ጋብዘውኝ ነበር፡፡ ከእርሳቸውም ጋር አቶ ተሾመ ቶጋ ነበሩ [የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች አፈ ጉባኤ፣ በአሁን ሰዓት በብራሰልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር] ከእነዚህ ባለሥልጣናት ጋር በጣም ግልጽ የሆነ ውይይት ከማድረጋችን በተጨማሪ በግልጽ ያሉኝን ጥያቄዎች፣ ቅሬታዎችና ሒሶች ሰንዝሬያለሁ፡፡ ምንም ግለሰባዊ ችግር እንደ ሌለብኝም አስረድቻለሁ፡፡ በግሌ የማገኘው ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌላ ጥቅም የለኝም፤ ሥራዬን ግን በቁርጠኝነትና በትጋት እሠራለሁ፡፡ ስለዚህም ያየሁትንና የሰማሁትን የመናገር ግዴታ አለብኝ፡፡ በዚህም መሠረት ውይይታችን እጅግ በጣም ግልጽና ገንቢ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- ከባለሥልጣናቱ ያገኙት መልስ ምን ይመስላል?

አና ጐሜዝ፡- ይህን እንኳን በዝርዝር አልነግርህም፡፡ የውይይታችን አንዱ ጠቀሜታም በግል መያዙ ነው፤ ምክንያቱም ውይይታችን የተካሄደው በግል ስለነበር፡፡ ነገር ግን ላረጋግጥልህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ውይይታችን የፖለቲካ ምህዳሩን ስለማስፋት፣ የታሠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ስለማስፈታት፣ ለበጐ አድራጐት ማኅበራት ምቹ ሁኔታን ስለመስጠትና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማጠናከርና መሰል ጉዳዮች የተዳሰሱበት ከመሆኑም በተጨማሪ ግልጽና ገንቢ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- ከባለሥልጣናቱ ባገኙት መልስ ረክተዋል?

አና ጐሜዝ፡- እንደሚመስለኝ እኔን ለመስማት መፍቀዳቸውና መወያየታችን አንድ ጥሩ ምልክት አድርጌ እመለከተዋለሁ፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች በሙሉ የኢትዮጵያ ጉዳዮችና ሒደቶች ናቸው፡፡ የትኛውም አካል ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ማሳደር አይችልም፡፡ ነገር ግን ከእኔ ጋር ለመወያየትና እኔን ለመስማት መፍቀዳቸው እንደ ጥሩ ጐን አድርጌ እመለከተዋለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሚወቅሱበት ጉዳይ አንዱና ዋነኛው የእስረኞች ሁኔታ ነው፡፡ እዚህ በመጡበት ወቅት ወደ ቃሊቲ ተጉዘው እስረኞችን ለመጠየቅ ጥያቄ አቅርበዋል?

አና ጐሜዝ፡- ጥያቄ አቅርቤያለሁ፡፡ ጥያቄዬ ግን በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን የጋራ ስብሰባው የፖለቲካ ኮሚቴ ወደ ስፍራው ተጉዞ እስረኞችን እንዲጐበኝ ባለፈው ቅዳሜ ጥያቄ አቅርቤያለሁ፡፡ (ይህ ኢንተርቪው የተካሄደው ሰኞ ዕለት የነበረ ሲሆን ረቡዕ ዕለት በሌዊ ሚሽል የተመራ ቡድን እስረኞችን ጐብኝቷል)

ከእስረኞች ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የሚደመጥ ነገር አለ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የታሰሩት ጋዜጠኛ ወይም ሌላ ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቅስ አሸባሪ በመሆናቸው ነው የሚለውን አስተሳሰብ የሚጋሩ የአውሮፓ ተወካዮችም እንዳሉ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ እኔ ግን በዚህ አስተያየት ፈጸሞ አልስማማም፡፡ ምክንያቱም የስዊድን ዜግነት ያላቸው ሁለት ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ተከሰው መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በበርካታ ወንጀሎች ክስ ተመሥርቶባትና ተፈርዶባት መፈታቷ ይታወሳል፡፡ የእነዚህ ሰዎች ጉዳይም የተለየ አይደለም፡፡ የታሰሩት ግለሰቦች የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምልክቶች ናቸው፡፡ የወጣቱ ትውልድ ምልክቶች ናቸው፤ ምናልባትም ያቋቋሙት የፖለቲካ ሥርዓትም የላቸውም፡፡

ሪፖርተር፡- መንግሥት በሽብርተኝነት ነው ያሰርኳቸው የሚለውን የሚያምኑ ከሆነና እነዚህ ሰዎች አሸባሪ አይደሉም ብለው የሚያስቡ ከሆነ የእርስዎን ሐሳብ የሚያጠናክር ምን መረጃ አለዎት?

አና ጐሜዝ፡- ኢትዮጵያ ከሽብርተኝነት ጥቃት ሥጋት ነፃ ነች እያልኩ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያና የአውሮፓ አገሮች ከሽብርተኝነት ጥቃት ሥጋት እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡ ነገር ግን በስመ ሽብርተኝነት የዲሞክራሲ ምህዳሩን ማጥበብ፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውንና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን የሚጠይቁ ግለሰቦችን ፀጥ ማሰኘት፣ ሽብርተኝነትን መታገል አይደለም፡፡ ይህ እንዲያውም ግለሰቦችን በይበልጥ ወደ ሽብር ተግባር እንዲሰማሩ መመልመል ነው፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን የሽብር ሥጋት ደረጃ ለማሳነስ እየሞከርኩኝ አይደለም፤ ነገር ግን የታሳሪዎቹን የፍርድ ሒደት የታዘቡ ግለሰቦች እንደነገሩኝ የፍርድ ሒደቱ ፍትሐዊ ካለመሆኑም በተጨማሪ የቀረቡት ማስረጃዎች የግለሰቦቹን የሽብርተኝነት ተግባር የሚያሳዩ አልነበሩም፡፡ ለዚህ ነው እነዚህ ሰዎችን አሸባሪ ብሎ መጥራትን የማልቀበለው፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ የሰጡኝ ማብራሪያ ትክክል እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሁነኛ ትንታኔ ሊሰጡኝ ይችላሉ?

አና ጐሜዝ፡- አላውቅም፡፡ እኔ እኮ ታሳሪዎቹን በግል አላውቃቸውም፡፡ ለምሳሌ የብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳይን ያነሳህ እንደሆነ በግል እንተዋወቃለን፡፡ እንዲሁም ከብርሃኑ ነጋ ጋር የግል ትውውቅ አለን፡፡ እነዚህ እስረኞች ግን በግሌ አላውቃቸውም፡፡

ሪፖርተር፡- በቅርበት እንደሚያውቋቸው ከገለጹት ግለሰቦች መካከል አንዱ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው፤ እርሳቸው ያቋቋሙት የፖለቲካ ድርጅት በኢትዮጵያ መንግሥት እንደ አሸባሪ ይቆጠራል፡፡ እሳቸውም ሥርዓቱን ለመለወጥ ከምርጫ የተለየ መንገድ ያስፈልጋል እያሉ ነው፡፡ እርሳቸው አቅጣጫቸውን ይቀይራሉ ብለው አስበው ያውቃሉ?

አና ጐሜዝ፡- ብርሃኑ ነጋን የማውቀው በምርጫ 97 ወቅት ነው፡፡ ቅድም የገለጽኩት በቀጥታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር የተነሳ በአገር አቀፍ ደረጃ ተቃዋሚ ጐራ ወኪል እንዲሆን አስችሎታል፡፡ በክርክሩ የተነሳ በአገር አቀፍ ደረጃ ተቃዋሚ ጐራውን በመወከል ስሙ የሚነሳ ግለሰብ ቢኖር ብርሃኑ ነጋ ነበር፡፡ እርግጥ ነው በየምርጫ ወረዳቸው የታወቁ ግለሰቦች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳና ወዘተ፡፡ በነገራችን ላይ ብርሃኑ ነጋ በምርጫ 97 ወቅት ባይታሰር ኖሮ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ይሆን ነበር፡፡ ከእስር እንደተፈታም ወደ ስደት አመራ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች አቅጣጫውን እንዲቀይር ያደረጉት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በአገሪቷ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ሊኖረው የሚችለው ሚና በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓት በመበላሸቱ የተለወጠ ይመስለኛል፡፡

ሪፖርተር፡- እርስዎ በስፋት የሚታወቁት የኢትዮጵያ መንግሥትንና የአውሮፓ ኅብረትን ከዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፋፋት ጋር ባለባቸው ችግር በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ነው፡፡ አሁን በእርስዎ ላይ የተፈጠረ የአቋም ለውጥ አለ?

አና ጐሜዝ፡- ኢትዮጵያን በተመለከተ ከፍተኛ ትችትና ሒስ እሰነዝራለሁ፡፡ አውሮፓ ኅብረት ላይ የምሰነዝረው ሒስ ደግሞ የባሰ ነው፡፡ የአውሮፓ ኅብረትን በተለያዩ ጉዳዮች እተቻለሁ፡፡ በተለይ በኅብረቱና በኢትዮጵያ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ትችት እሰነዝራለሁ፡፡ ምክንያቱም የአውሮፓ ከፍተኛና ጠንካራ ተፅዕኖ ማሳረፍ ሲችልና በኢትዮጵያ ጉዳይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ሲችል ዝምታን ይመርጣል፡፡ ይህን አይቻለሁ፡፡

አንዳንድ ሰዎች የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲ የተሻለ እንደሆነ ይገልጹልኛል፡፡ እርሱን እጠቀምበታለሁ፤ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውልም አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከፍተኛ ጫና የማሳደር ዲፕሎማሲ (ሜጋፎን) መጠቀም ይኖርብናል፡፡

ባልደረባዬ ሊዊ ሚሸል ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ሁለት የስዊድን ዜግነት ያላቸውን ጋዜጠኞችን አስፈትቶ ስለ ኢትዮጵያውያን እስረኞች ጉዳይ አንዳች ሳይሠራ ወደ አውሮፓ በመመለሱ በጣም ተናድጄ ነበር፡፡ በተለይ ለኢትዮጵያውያንና በአጠቃላይ ለአፍሪካውያን የምናስተላልፈው መልዕክት ምንድነው? እኛ የምንጨነቀው ለዜጐቻችን ብቻ ነው፡፡ ይህ ተግባር ተራና ማዳላት ያለበት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ በነበሩበት ወቅት ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት እንደነበሮት ይታወሳል፤ እዚህ ከመጡ ያገኟቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አሉ?

አና ጐሜዝ፡- እስከ አሁን ያገኘሁት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የለም፡፡ ነገር ግን እንደማገኛቸውም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከዚህ በላይ ግን በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የትውልድ ችግር አለ፡፡ በግሌ በተቃዋሚ ፓርቲና በውጪ አገሮች ባሉ ኃይላት መካከል ግንኙነት ቢፈጠር መልካም ይመስለኛል፡፡ ይህም ለፖለቲካው ምህዳር መከፈትና ለውይይት መዳበር ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ እውነተኛ ለሆነ የዲሞክራሲ ግንባታ እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ መጠላላትን አስወግዶ ወደ ፊት ለመጓዝ ይረዳል፡፡

ሪፖርተር፡- ምርጫ 97ን ተከትሎ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በተደጋጋሚ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዴት ይገልጿቸዋል?

አና ጐሜዝ፡- ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እስከ ምርጫው ድረስ የነበረኝ ግንኙነት መልካም የሚባል ነበር፡፡ ከእርሳቸው ጋር ግልጽ የሆኑ ብዙ ውይይቶች አካሂደናል፡፡ ተለዋዋጭ ባሕሪ እንዳላቸው ለመታዘብ ችዬ ነበር፡፡ በግንኙነታችን መጀመሪያ አካባቢ አምናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ ሊያሞኙኝ እየሞከሩ እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ እርሳቸው በጣም ክፉ ነበሩ፡፡ በጣም ክፉ የሆነ አእምሮ የነበራቸው ናቸው፡፡ ብልህ ናቸው ግን ክፉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ ላይ የጻፉትን የምንጊዜውም ረዥሙን ርእሰ አንቀጽ አልረሳውም፡፡ መጨረሻ ላይ ግለሰባዊ ጥቃት በመሰንዘር ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ገንዘብ ተቀብላለች የሚል ዘመቻ ጀመሩ፡፡ ፈጽሞ ተራ የፈጠራ ውሸት ነው፡፡

እኔ በግሌ ከእርሳቸው ጋር ምንም ዓይነት ችግርም፣ ጸብም ባይኖረኝም እኔን በመክሰስና በመዝለፍ ጉዳዩን ግለሰባዊ አደረጉት፡፡ እርግጥ ነው ያኔ በጣም በጣም ብናደድባቸውም አሁን ግን የሉም፤ ሄደዋል፡፡
reporter amharic

Image

ይህ ቀን በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት በመንግስት አቃቤ ህግ በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ የተከፈተውን የሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ክስ የመጨረሻ ብይን የሚሠጥበት ቀን ነው፡፡

በዚህ ቀን ፍርድ ቤቱ ሲመለከት የቆየውን አቃቤ ህጉ ያቀረበውን መረጃ በማየት ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች በቀረበባቸው የሽብር ድርጊት ፈፃሚነት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው አግኝቻቸዋለው በመሆኑም እራሳቸውን ይከላከሉ አልያም ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው አላገኘዋቸውም በማለት በነፃ እንዲሰናበቱ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች የሽብር ክስ ተምስርቶብን ከ አንድ አመት በላይ በእስር ቤት ስቃይ ላይ እያሳለፍን ብንገኝም ለቆምንለት አላማ ግን ፍፁም በፅናት ላይ እንገኛለን፡፡

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ወኪሎች ናቸው፡፡ ኮሚቴው ማለት ኢትዬጰያውያን ሙስሊሞች ማለት ነው፡፡ ህጋዊ የሆነ ውክልና ያላቸው በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ የሚገኙ የኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች አንድ አካል ናቸው፡፤

ህዳር 23 የሚበየነወ የጥፋተኝነት ብይን በኮሚቴው ላይ ሳይሆን በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ ነው፡ ለዚህም ነው ህዳር 23 በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ በሽብር ድርጊት ፈፃሚነት የቀረበው ክስ ብይን የሰጥበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምንገልጸው፡፡

ኮሚቴውን እና ህዝብን ፈፅሞ መለየት አይቻልም፡፡ ለቀሩት 10 ቀናቶች የኮሚቴዎቻችን የፍርድ ሂደት ሳይሆን መባል ያለበት የኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች የፍርድ ሂደት መባል እንደሚኖርበት እሙን ነው፡፡

በመሆኑም ኮሚቴው ማለት የኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ማለት በመሆኑ በዚህ ክስ አንተም፣እኔም፣ አንቺም፣እነሱም መወንጀላችን በመገንዘብ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት የሚሰጠው ብይን በሁሉም ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ፍትህ ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!!
BY:- ABU DAWD OSMAN

Source Addis Admass local newspaper addis abeba

Image

ራውዳ ጀማል ትባላለች፡፡ የሃያ ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለራስዋም ሆነ በሳኡዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ስታወራ እያለቀሰችና እየተወራጨች ነው፡፡ ለማነጋገር ስቀርባት “ወንድ ከሆናችሁ ጋዜጠኞች ነን፣ የህዝብ አፍ ነን ካላችሁ፤ እዚህ ተቀምጣችሁ፣ “ሁለት ሰው ሞተ” እያላችሁ ከምታቅራሩ ሳኡዲ ሂዱና በየቀኑ ሁለት ሶስት ሰው የሚሞትበትን እልቂት ተመልከቱ፣ “ሰዎቹን ምን እየሰራችሁ ነው?” ብላችሁም ጠይቁልን” አለችኝ። መቅረፀ ድምፄን ሶስት አራት ጊዜ ያስጠፋችኝ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ሆነችልኝ፡፡
ስንት ዓመት ቆይተሽ መምጣትሽ ነው?
ከሁለት ዓመት በኋላ ነው የመጣሁት፡፡ እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩት አዲስ አበባ ቢሆንም፤ የኮምቦልቻ ልጅ ነኝ፡፡
እንዴት ነበር የሄድሽው?
በፓስፖርት… በኮንትራት ነበር የሄድኩት … ካላስ! የሰውየው ልጆች ግን “የማይሆን” ፊልም ተመልከቺ እያሉ ያስቸግሩኝ ነበር፡፡ ሲመረኝ ጠፍቼ ወጣሁ፡፡ ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር በነፃነት ቤት ተከራይተን እየኖርን፣ በ1800 ሪያል ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ፡፡ ቤተሰቤንም ገንዘብ እየላኩ እረዳ ነበር፡፡
ወደ አገርሽ እንዴት ተመለስሽ?
ውጡ ሲባል… ረብሻ ሲነሳ.. ጓደኞቻችን ሲሞቱ.. ሲደፈሩብን.. ‘ድሮም ስደተኛ ክብር የለውም’ ብዬ ተመልሼ መጣሁ..ከሚገሉኝ ከሚያበለሻሹኝ ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵውያኖች ችግር ላይ ናቸው.. እባካችሁ ድረሱላቸው፡፡ ብርዱም ፀሃዩም ሲፈራረቅባቸው.. ያሳዝናሉ፡፡ ብዙ ያልመጡ አሉ፤ መምጣት እየፈለጉ፡፡ ስቃይ ላይ ናቸው፡፡ እኔ አሁን አስራ ሶስት ቀን ታስሬ ነው የመጣሁት፡፡ እስቲ ስለ እስሩ ንገሪኝ … ሁለት ቀን ያለ ምግብ ያለ ውሃ ነው የታሰርነው። ከዛ በኋላ ግን ጥሩ ምግብ ሰጥተውናል፣ ጥሩ መኝታም አግኝተናል፡፡ ብዙዎቹ ግን ከእኛ የባሰ ችግር ላይ ናቸው፡፡ መጠለያ ያላገኙ አሉ… ኤምባሲያችንም አይሰማም እንጂ ስንት ጊዜ ደውለን ተናግረናል መሰለሽ፡፡ ግን የሚሰማ የለም፡፡ ከአገራችን ውጡ ካሉ በኋላ ትዕግስት ያጡና መልሰው ይዩዙናል፡፡ በዛን ጊዜ አበሻው፣ ሻንዛ/ጩቤ ይመዛል፡፡ ፖሊስ ራሱን ለማዳን ይተኩሳል። እኔ እንደውም ደህና ነኝ፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው። በምድረ ዱርዬ እየተደፈሩ ነው ያሉት /ለቅሶ/ ስንት ህፃናት አሉ የሚሞቱ፣ የሚታመሙ፡፡ ስንመጣ ደሞ፤ ሻንጣ አትያዙ ተብለን ተመናጭቀን…በጥፊ ተመትተን..መከራችንን በልተናል፡፡
ወንዶችና ሴቶች ለብቻ ነበር የተቀመጣችሁት?
የተቀመጣችሁት አትበይ! የታሰራችሁት በይ፡፡ … የሴት እስር ቤት ለብቻው ነው በሴቶችና በህፃናት ለቅሶ የተሞላ ነው፡፡ እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ…/ለቅሶ/
አሁን ቤተሰብ እየጠበቅሽ ነው?
ነበረ ግን ሻንጣዬ ጠፋብኝ፡፡ በርግጥ ጤነኛ ሆኖ መምጣትም ቀላል አይደለም፡፡ እዛ ያሉትን ጥለናቸው ስንመጣ እያለቀስን ነው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ አንድ እርጉዝ ሞታብናለች፡፡ እዛው እስር ቤት እያለን ምጥዋ መጣ፤ ግን የህክምና እርዳታ ባለማግኘትዋ ሞተች፡፡
እስር ቤት ያሉት ምን ያህል ይሆናሉ?
ሰማኒያ ክፍል አለ..በየክፍሉ ስልሳ አምስት ስልሳ አምስት ሰው ነው ያለው፡፡ መካሲመሺ እስር ቤት ይባላል፡፡ የወንድና የሴት እስር ቤት የተራራቀ ነው፡፡ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ በመኪና እንጂ በእግር አይሞከርም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማው ያለው እስር ቤት ሞልቶ የመዝናኛና የስብሰባ አዳራሹን ሁሉ እስር
ቤት አድርገውታል፡፡ የተደፈሩት የሞቱት..ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዷን እርጉዝ ለሶስት ሲደፍሯት ሞታለች፡፡
የሌሎች አገር ስደተኞችም እየወጡ ነው ተብሏል…
አዎ፡፡ ኢትዮጵያዊው ከበደሉ ብዛት የተነሳ እየተናነቀው እኮ ነው ግጭቱ የሚከረው፡፡
ሚስቱን እህቱን ከእጁ መንትፈው ሊወስዱበት ሲሉ ነው ጦርነት የሚነሳው፡፡ አበሻ ወንድ እየሞተ ያለው ‹‹ሴቶቻችንን አትንኩብን..›› ስለሚል እኮ ነው፡፡ ኤምባሲው ሊደርስላቸው ይገባል፡፡
አዲስ አድማስ ጋዜጣ

ምንሊክ ሳልሳዊ :-በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት መፈተሩን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ተሰምቷል:: በወታደራዊ ጥቅማ ጥቅም እና በህገመንግሥቱ ዙሪአ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ አካል መጥፋቱ እና ዝም መባሉ ዉስጥ ውስጡን እየተብላላ ያለው የመኮንኖቹ ጥያቄ እንዳይፈነዳ የተሰጋ ሲሆን ከፈነዳ ሰራዊት ለሶስት ቦታ እንደሚከፈል ለምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

መኮንኖቹ በትምህርት በስራ እና በማእረግ እድገት በቤተሰብ እንክብካቤ በደሞዝ ጭማሪ እና በሕገመንግስታዊ የህዝብ መብቶች ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞች ለአንድ ብሄር አባላት ብቻ ተመድበው እየተሰራባቸው ነው ከተማ ውስጥ ታጥቀው የመሸጉ እና ህዝብን እያጠቁ የሚገኙት የአንድ ብሄር አባላት ናቸው እንዱሁም ከሃገራዊ ጥቅም ይልቅ የፓርቲ ጥቅም እየተስተዋለ ነው:ወታደሩ የጦር ሳይንስን እና ዲሲፕሊን በጎደለው መልኩ እየተስተዳደረ ነው በሰራዊቱ እና በሃገሪቱ ሁሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ሽፋን እና ማዘናጊያ በማድረግ የሙስና እና የዘረፋ መስፋፋት መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ጄኔራል መኮንኖች አላቸው የተባለው ንብረት ይጣራ በሃገሪቱ የፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማንሳታቸው ታውቋል::የመከላከያ አባላቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሱት ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው::

ይህ ከዚህ ቀደም የተጀመረው እና አሁንም በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በሁሉም የሰራዊት እዞች ውስጥ ጥያቄው መነሳቱን ምንጮቹ አመልክተዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጮቹ ገልጸው ነበር::

ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ ጡረታ ወቶ በምትኩ የብኣዴን ሜ/ጄ አበባው ይተካሉ ሲባል ወያኔ በድንገት የመለስ የቅርብ ሰው የነበሩትን እና በአንድ ወቅት የአማር ክልል አቶ አያሌው ጎበዜን ላንቻ አከባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ለ3 ወር አግተው ሲያሰቃዩ የነበሩት ሌ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀልን በማእረግ ሾሞ ሳሞራ የኑስን ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ የብኣዴን አባላት መቃወማቸውን ተከትሎ ጄኔራል አባባውን ጨምሮ የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ የሕወሃት አባላት የሆኑ ጄኔራሎች ብቻ የተሳተፉበት በትግሪኛ የተመራ ስብሰባ መደረጉን ውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ተናግረዋል::በስብሰባው ላይ ቀሪ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች እና የመምሪያ ሃላፊዎች ለምን አልተሳተፉም የሚል ጥያቄ ከአንድ ስማቸው ካልተጠቀሰ ብርጋዴር ጄኔራል መነሳቱን ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

ይህ ስብሰባ ዋና አትኩሮቱ የነበረው በብሄር አደና ላይ ሲሆን እንደ ምንጮቹ መረጃ በአማራ እና በኦሮሞ መኮንኖች እየተመራ ያለውን የለውጥ ጥያቄ በማክሸፉ ዙሪያ እንደነበር እና አሁንም በስፋት የሕወሓትን የፓርቲ አቋም የሚቀበሉ እና የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለመሾም የታቀደ ሲሆን እንዲሁም ከፖለስ ሰራዊት በከፍተኛ የማእረግ ሹመት ወደ ጦር ሰራዊቱ ለማምጣት የታሰበ ሲሆን በወታደራዊ ደህንነት ዙሪያ ሌላ ተጨማሪ ሰልጣኞችን ከፖሊስ ወስዶ በማሰልጠን ወደ ሰራዊት ማዘዋወር የሚሉ ውይይቶች ተካሂደውበታል:: አሁንም ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እንለቃለን::

Image

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው መጠን የለሽ የመብት ጥሰት ለመቃወም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በየአገራቱ የሚገኙ የሳውዲን ኢምባሲዎችን በተቃውሞ እያጨናነቁ ነው። በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ዘግኛኝ በደል የተሰማቸውን ጥልቅ የመጠቃት ስሜት ኢትዮጵያን በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በሚያሰሟቸው መሪር የሐዘን እንጉሮችና የቁጭት ንግግሮች እየገለፁ ነው። ከሐዘንና ቁጭት ባለፈም ለበደል ለተጋለጡ ወገኖቻችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ እና የዲፕሎማሲ ድጋፍን ለማሰባሰብ ዓለም ዓቀፍ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራውን ጀምሯል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህንን ዓለም ዓቀፍ ጥረት ለመደገፍ በውጭ አገራት የሚገኙ አባላቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል።

ይህ ሁሉ በውጭ አገራት እየተደረገ ያለ ጥረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ባሉበት አገራትና ከተማዎች ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድነት መንቀሳቀሳቸው የሚያስደስት ነገር ነው። ሌላው ቀርቶ በሳዉዲ ዋና ከተማ ሪያድ ውስጥ እንኳን ኢትዮጵያውያን የሳውዲን መንግሥት ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል።

የሳውዲ መንግሥት በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ የያዘውን ጨካኝ አቋም እና በመንግሥት እውቅና በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል መቃወም ያልተቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ!!! ይህ እጅግ ያማል፣ ልብን ያደማል።

ወያኔ የሳውዲ የንግድ ሸሪኮቹን ለማስደሰት የፈንሳይን ግማሽ የሚያህል ለም መሬት በነፃ መስጠቱ በቂ አልመሰለውም። በአገራቸው ኢትዮጵያዊያንን ሲጨፈጭፉ፣ ሲገሉና ሲደፍሩ በቸልታ መመልከቱ በቂ የወዳጅነት ስጦታ መስሎ አልተሰማውም። እናም ሸሪኮቹ የበለጠ እንዲደሰቱና ከእስከዛሬ በበለጠ ገንዘብ እንዲደጉሙት ለማበረታታት አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲያቸው ፊት ለፊት ኢትዮጵያንን ደበደበላቸው።

ወያኔ ከሳውዲ ጋር ያለው ግኑኝነት “የቢዝነስ ሽርክና” ነው። ቢዝነሱም ኢትዮጵያዊያንን በቁማቸው መሸጥንም ያጠቃልላል። የወያኔ ሹማምንት እና የሳውዲም ቱጃሮች በዘመናዊ ባርነት ንግድ ውስጥ አቀባይና ተቀባይ ናቸው። ለዚህም ነው እየተነገደበት ያለው ምስኪን ኢትዮጵያዊ እጣ ፈንታ በአዲስ አበባና በሪያድ አንድ ዓይነት የሆነው። እዛ ዱላ፤ እዚህም ዱላ። እዛ እስር፤ እዚህም እስር። እዚያ ስድብ፤ እዚህም ስድብ። እዚያ ቶርቸር፤ እዚህም ቶርቸር። በባርያ ንግድ ውስጥ አቀባዩም ተቀባዩም ባርያዉን መግዛታቸው፣ መስበራቸው፣ መግደላቸው የማይቀር መሆኑ የታወቀ ነው።

ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ ደግሞ የወያኔ ድኩማን ሹማምንት የሚሰጡት አስተያየት መስማት ነው። በሳውዲ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍትህ ለመጠየቅ በመላው ዓለም እና በአዲስ አበባ ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት ወደ ጎዳና በወጡ ኢትዮጵያዊያን የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ተብየው “የፋሺሽት መፈክር አንግቦ በተጎሳቆሉ ዜጎች ስም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መጣር ብሎም መንግሥት በዜጎቹ ግዴለሽ እንደሆነ አስመስሎ ማቅረብ” ሲል ተሳልቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተብየው ጨምሮ ሁሉም የወያኔ ሹማምንት “ሳውዲዎች በግዛታቸው ውስጥ ያሻቸውን የማድረግ “ሉዓላዊ” መብት አላቸው፤ መንግሥታችን የሳውዲ አረቢያን ሉዓላዊ መብት ያከብራል” እያሉ ይከራከራሉ። ለመሆኑ ይህንን የሚሉት ከልባቸው ነው? ፈጽሞ። ኢትዮጵያዊያንን ማሰቃየትና መግደል የቢዝነሳቸው አካል ስለሆነ ነው እንጂ የሉዓላዊነት ትርጉም ይህን ያህል ተምታቶባቸው አይደለም።

ሰብዓዊ መብቶች አገር፣ ድንበር፣ ዜግነት፣ ወይም ሌላ ማናቸው ሰው ሠራሽ ህግጋት ሊጥሷቸው እንደማይገቡ የወያኔ ሹማምንት ቢያንስ ሲነገር ሰምተው ያውቃሉ። ማንኛውም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገደል፤ ሰቆቃ (ቶርቸር) እንዲደርስበት ማድረግ፤ ጾታዊ ጥቃት እንዲደርስበት ማድረግ እንደማይቻል ሰምተው ያውቃሉ። ሰብዓዊ መብቶች ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ ሊያገኙት የሚገባ ክብር መሆኑ በተሳተፉባቸው በርካታ ዎርክ ሾፖች ሰምተዋል። ያም ሆኖ ግን በዘመናዊው ዓለም እንስሳ እንኳን ያገኘውን ክብር ኢትዮጵያዊያን ተነፍገው በሪያድ ጎዳናዎች ሲታረዱ፤ በጭካኔ ሲደበደቡና ሲገረፉ፤ ሴቶች ሲደፈሩ፤ ሕፃናት በረሀብና በእርዛት ሲቀጡ የወያኔ ባለሥልጣኖች የበዳዮች አፈቀላጤ ሆነው የሚከራከሩት በዳዮቹ ሸሪኮቻቸው ስለሆኑ ነው።

ይህ ድርጊት በወያኔ እየደረሰብን ያለው በደል ምን ያህል ሥር የሰደደ እንደሆነ እና የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ ምንጭ የት እንዳለ አመላካች ሆኗል።

“ትግላችን የነፃነት ትግል ነው” ስንል “ከማን ነፃ ለመውጣት?” እያሉ የሚሳለቁ እንደነበሩና እንዳሉም ይታወቃል። በወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያን ወደ ባርነት ማሽቆልቆላቸው ይህ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ከወያኔ የባርነት አገዛዝ ነፃ እስካልወጣን ድረስ ሌሎች አገሮች መብቶቻችን የሚያከብሩልን በየአገራቱ ልምድ እና ከወያኔ ጋር ባላቸው ሽርክና መጠን ነው።

ለሳውዲ መንግሥትና ቱጃሮቹ ከነዳጅ ቀጥሎ የሀብታቸው ምንጭ ከየአገሩ የሚመጣላቸው የድሀ ጉልበት ነው። የሳውዲ ቱጃሮች ድሆችን ከባርነት ባልተሻለ መንገድ ረግጠው በመግዛት ኑሮዓቸውን ያደለቡ ናቸው። ለወያኔ አገዛዝ ደግሞ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛው የገቢ ምንጩ ዜጎቹን በመሸጥ የሚሰበስበው ነው። ለወያኔ፣ ኢትዮጵያዊያን ወንዶችና ሴቶች ትርፍ አምጪ ሸቀጦች ናቸው። ወያኔና ሳውዲ – ሻጭና ገዢ ናቸው።

ባርያ ከሻጩ ነፃ ሳይወጣ ከአንድ ገዢ ነፃ ቢወጣ ሌላ ገዢ ስለሚመጣ ዘለቄታነት የለውም። እኛም ከወያኔ ነፃ ሳንወጣ ከሳውዲ ነፃ መወጣት አይቻለንም፤ ቢቻልም ነፃነታችን ዘላቂነት አይኖረውም።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሳዉዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በሚደርሰው ጥቃት ክፉኛ ተቆጥቷል። በዚህ የመከራና ጭንቅ ሰዓት ለወገኖቻችን ለመድረስ የሚቻለውን ጥረት ሁሉ ማድረግ እንዳለብን ያምናል። አባላቱ በነብስ አድን ርብርብ በግንባር ቀደምትነት እንዲሳተፉ መመሪያ አስተላልፏል። ይህ አጣዳፊ ሆኖም ጊዜዓዊ መፍትሔ ነው። በግንቦት 7 እምነት የችግሮቻችን ሰንኮፍ ያለው አዲስ አበባ ነው። ሰንኮፉን ሳንነቅል የሚደርስብንን ውርደት በዘላቂነት መቀልበስ አንችልም። ስለሆነም በችግር ላይ የወደቁትን ወገኖቻችን እየረዳን፤ የችግሮቻችን ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይ የተባበረ ክንዳችንን እናንሳ ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የጋራ ላይ ፉጨት!!
//ደመቀ ከበደ – ጣና ዳር//

‹‹ሀበሽ አባ ደፋር – አባ ሰው አይፈሬ
ጫማ የለም ከእግሩ – ተሰርቶ ጎፈሬ፤
ሀበሽ አባ ሞጋች – አባ ጎበዝ ጤፉ
ጋራ ላይ ያቅራራል – በጎቹ ሲጠፉ››
የሚሉት ቀረርቶ – የሚሉት ሽለላ
ስንት ወንድ ገደለ – ስንት ጎበዝ በላ፤
‹‹ደፋር ነው እያሉ – ጀግና ነው እያሉ
የሞት ሞቱን ሲሞት – ዳር ቆመው ያያሉ፤
ተውት ይሄን ሶታ – ይሄንን ጠንበለል
ጀግና ነህ አትበሉት – እንዲያው ይንጎማለል፤››
የሚሉት የእናት ወግ – የአባት ማስፈራሪያ
ስንት ወንድ አከሸፈ – እንደ ዘመን ድሪያ፤

እኔ ግን እላለሁ፤
ተውት ይኸን ጀግና – ይውጣ ወደ ጋራ
ይሸልል ይፎክር – እንዳሻው ያቅራራ
እንዳሻው ‹‹ቡ!›› ይበል – ያሻውን ይጣራ
ሰው እንዴት ይኖራል – እያየ መከራ!!

Image


በዚህ 20 አመት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን የማይወጣ ዳገት የሆነው የኢህአዴግ ስርዓት ብቻ አይደለም፡፡ የተቃዋሚዎች መጠላለፍም ህዝብን ተስፋ ሲያስቆርጥ ኖሯል፡፡ እንዲያውም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገዥውን ለመቃወም ከሚያደርጉት በላይ እርስ በእርስ ለመጠላለፍ በርካታ ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ሆነዋል፡፡

Image
ሰሞኑን ፌስ ቡክ ላይም የምናነበው ይህን መጠላለፍ ነው፡፡ ሳውዲ ውስጥ ዜጎቻችን ሰቆቃ እየደረሰባቸው ባለው ወቅት ሳይቀር ተቃዋሚዎች እርስ በእርሳቸው ይናቆራሉ፡፡ ምንም እንኳ ጭቅጭቁ ፌስ ቡክ ላይ ቢሆንም የፓርቲዎቹን አቋም ግን የሚያንጸባርቅ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የሚያስገርመው ደግሞ የሚናቆሩት ይህ ነው የሚባል የፖሊሲም ሆነ ሌላ የሚያጨቃጭቅ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች አለመሆናቸው ነው፡፡
ተጨቃጫቂዎቹ የዚህ ትውልድ ወጣቶች መሆናቸው ደግሞ ይበልጡን ያስገርማል፡፡ አብዛኛዎቹ ደግሞ ሁለቱ ፓርቲዎች የተቀራመቷቸው የባለ ራዕይ ወጣቶች አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ በእድሜ ከገፉት ፖለቲከኞች ይልቅ ወጣቶች ከመግባባትም አልፎ ሁለቱን ፓርቲዎች ማቀራረብ ነበረባቸው፡፡ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲ ያደረገውን ሰልፍ ሲነቅፉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ደግሞ አንድነት መንግስትን ገፍቶ መሄድ እንዳልቻለ ይተቹታል፡፡ መተቻቸት አንድ ነገር ነበር፡፡ ሆኖም በሁለቱ አባላት መካከል የሚደረገው እሰጣ ገባ ከምክንያታዊነት ይልቅ በመጠላለፍ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ጭራሹን ጥላቻም ይታከልበታል፡፡ ከአሁኑ ካድሬያዊ ባህሪም ይታይበታል፡፡
እንደ እውነት ከሆነ ሁለቱ ፓርቲዎች አብረው ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ነበረባቸው፡፡ ሆኖም በመካከላቸው ባለው የመጠላለፍና የመጠላላት ችግር ለየብቻቸው አድርገውታል፡፡ አንድነት ደግሞ ጭራሹን አልቻለም፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አንድነትና ሰማያዊ ክፍተቶች ታይቶባቸው ይሆናል፡፡ ግን እነዚህ ክፍተቶች ኢህአዴግ የፈጸመውን በደል እያለ ሁለቱን መነታረክ አልነበረባቸውም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የመጨረሻው አይደለም፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች (ወጣቶቻቸውም) ሌሎች በርካታ ትግሎች ይጠብቃቸዋል፡፡ ባለፈው የታየውን ስህተት በሚቀጥሉት ማረም ይችሉ ነበር፡፡ አሁን የሚታየው ግን አንዱ የሌላውን ስህተት ሲያገን፣ አንዱ ውድቀቱን በሌላው ላይ ሲያላክክ፣ አሊያም በማይተቸው ሲተች ነው፡፡
በበኩሌ ‹‹ተባበሩ አሊያም ተሰባበሩ›› የሚለው መርህ አይመቸኝም፡፡ ቢያንስ ለገዥው ባለመተባበር ላይ ግን መተባበር የግድ ይላቸዋል፡፡ እርስ በእርሳቸው ሲናቆሩ ተስፋ የሚያስቆርጡት፣ የሚያስገዙት ህዝብን ነው፡፡ ከ97 በኋላ የተፈጠረው መከፋፈል፣ መናቆርና መጠራጠር በርካታ ዋጋ አስከፍሎናል፡፡ የፓርቲዎቹ አባላት ደግሞ ቀዳሚ ተጠቂዎች ናቸው፡፡ እናም መጠላለፉ ለገዥው ካልሆነ በስተቀር ለማንም የሚጠቅም አይደለም፡፡ ሀሳብን በነጻነት መናገር አንድ ነገር ነው፡፡ የሀሳቡን ጥቅምና ጉዳት ሳይመዝኑ መዘላለፍ፣ መናቆር ግን ፖለቲካችን በብስለት ላይ ያልተመሰረተ ለመሆኑ አመላካች ነው፡፡
በሚያስማማቸው መተባበር ቢችሉ መልካም ነገር ነው፡፡ መተባበር ባይችሉ እንኳን አንዱ ሌላውን ባለመጥለፍ ቢተባበር መልካም ይመስለኛል፡፡ አይደለም በአሁኑ ዘመን ፖለቲካ በ1970ዎቹ ታጣቂዎች ለገዥዎች ክፍተት ላለመፍጠር ልዩነታቸውን በሰላም ፈትተዋል፡፡ ሳይግባቡ ሲቀሩ እርስ በእስር ላለመጠላለፍ ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህ እንዴት በዚህ ዘመን ያቅታል?
የፓርቲዎች ድክመት ለፖለቲካ ትግሉ እንቅፋት እየሆነ ነው ከተባለ እንኳ ችግሩ መፈታት ያለበት በመጠላለፍ አይደለም፡፡ በሰከነ መንገድ ተወያይቶ መፍታት፣ ተነጋግሮ መግባባት ካልተቻ የየራሱን ትግል አጠናክሮ ትክክለኝነቱን በማሳየት የሌላው መንገድ ስህተት መሆኑን ማሳየት ይገባል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት እነዚህ ሁለቱ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ኢህአዴግን መቃወም ብቻ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ ህዝብ ተቃዋሚዎች የትግሉ ዳገት ላይ ሲደርሱ እርስ በእስር ተጓትተው እንደገና ተስፋ እንደማያስቆርጡት፣ ዋጋ እንደማያስከፍሉት፣ እንደገና ተከፋፍለው እንደማያስገዙት ካወቀ ብቻ ነው ሊከተላቸው የሚችለው፡፡ እንዲያው ቢከተላቸው እንኳ እነዚህን ስህተቶች ላለመድገም መዘጋጀት ይሆርባቸዋል፡፡ ከሁለቱም ፓርቲዎች አባል ባልሆንም ለመጠጋት ስሞክር ይች መጠላለፋቸው እምነት አሳጥጣ እንደገና ትገፈትረኛለች፡፡ ይህ ለሌሎችም ተመሳሳይ ይመስለኛል፡፡ ህዝብ ትግሉን በሙሉ ልብ ለመቃለቀል የሚፈራውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡
በቅርብ ጊዜያት እንደምናየው መጠላለፍ ከሆነ አሁን የሚጠላለፉት ፓርቲዎች መካከል አንዱ ስልጣን ቢይዝ ከኢህአዴግ ባልተነሰነሰ ሌላኛውን ለማፈን ወደኋላ እንደማይል ነው፡፡ መሳሪያ ቢኖራቸው ደግሞ ተጨፋጭፈዋል፡፡ ህዝብ ተቃዋሚን የሚደግፈው ገዥውን ስለሚቃወም ብቻ ሳይሆን ገዥው የፈጠሩትን ስህተት የማይደግሙ ከሆኑ ብቻ ነው፡፡
ብዙውን ጊዜ ‹‹ብሄራዊ እርቅ›› ሲወራ በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል ስላለው አለመግባባት ነው የሚወራው፡፡ ኢህአዴግ ለብሄራዊ መግባባትም ሆነ ለሌሎች ጉዳዮች እጁን ያልሰጠው ተቃዋሚዎች መካከል ባለው መጠላለፍ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ይህ የተቃዋሚዎች መጠላለፍ ኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎች ከሚሰሩለት በላይ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቶለታል፡፡ ስለሆነም ከገዥው ጋር ከሚደረገው ትግል ቀድሞ ተቃዋሚዎች እርቅ፣ መግባባት…ብቻ ትግሉን ወደኋላ ከመጎተት የሚታደግ አንዳች መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን እንደተለመደው በትኩሳትና ሰሞነኛ ፖለቲካ ዳገቱ ላይ ደርሶ እርስ በእርስ ተከፋፍሎ፣ ህዝብን ተስፋ አስቆርጦ፣ ገዥዎችን አጠናክሮ ከመመለስ ያለፈ ውጤት ጠብ ሊል አይችልም፡፡ ይህ ደግሞ ትውልዱን ለማይወጣው ተገዥነት አሳልፎ ይሰጠዋል፡፡

‹‹ዘረኝነት›› እና ኢትዮጵያ ምን አገናኛቸው? /Minillik Salsawi/

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በፌስ ቡክና በሌሎች አጋጣሚዎች ታዋቂና አንቱ የተባሉ ፖለቲከኞች ሳይቀር በኢትዮጵያ ያለውን ልዩነት ‹‹ዘር፣ ዘረኝነት፣ ዘረኛ›› እያለ ሲገልጹ ማየትና ማንበቤ ነው፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹ዘር፣ዘረኝነት፣ዘረኛ›› አሉ? ለሰው ልጅ አመጣጥ ሳይንሳዊ አሊያም መለኮታዊ አመጣጥ ይሰጠዋል፡፡ አንደኛው ሰው ከዝንጀሮ መሰል እንሰሳ መጣ ሲል ሌላኛው አሁን ያለውን አካል ይዞ ነው የተወለደው በሚል ‹‹አምላክ ሰውን በአምሳያው ፈጠረ!›› ይለናል፡፡ የዓለም ህዝብ ከዝንጀሮ መጣ የሚሉት መነሻውን ወደ አፋር ሲጎትቱት በመለኮታዊው ግምገማቸው ወደ መካከለኛው ምስራቅ የተጠጋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በሁለቱ አመለካከቶች መሰረት የሰው ‹‹ዘር›› ምንጩ አንድ መሆኑንእንረዳለን፡፡ ግን ሰዎች በዚህ አልተወሰኑም፡፡ ሰውን ለመነጣጠል የሚያስችል ፖለቲካ ጨመረበት፡፡ በቆዳ ቀለሙ፣ በአኗኗሩ፣ በሰውነትና አካል ቅርጹ፣ እና በመሳሰሉት አናሳ ወይንም የበላይነቱ! ይህን መሰረት በማድረግ በ18ኛው ክፍለዘመን ጆሃን ብሉሜንባች የተባለ ጀርመናዊ የህክምና ባለሙያ አምስት ዋና ዋና የሰው ‹‹ዘር›› አይነቶችን አስቀምጦ ነበር፡፡ አውሮፓን ማዕከል አድርጎ የምዕራበዊያንን ነጮች ካውካሳይድ ብሎ ጠራቸው፡፡ የኤሲያዎቹን ‹‹ብጫ›› ህዝቦች ሞንጎሎይድ ብሎ አንድ ‹‹ዘር›› ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡ አውስትራሊያና ኦሺኒያን ደግሞ ማሌዠያ የሚል ስያሜ ሰጣቸው፡፡ አሜሪካኖቹን አሜሪካውያን በሚል ሰየማቸው፡፡ ጥቁር አፍሪካውያንን በሙሉ ደግሞ ኢትዮጵያውያን የሚል ‹‹ዘር›› ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡ ይህን አምነን እንቀበል ብንል እንኳ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አፋር፣ እና ሌሎች አፍሪካውያን አንድ ‹‹ኢትዮጵያ›› የሚባል ‹‹ዘር›› ውስጥ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከቀለም፣ የቅርጽና ሌሎች ፖለቲካ ያልተላቀቀው ‹‹ታሪክ›› የሚያስተምረው ሶስት የሰው ‹‹ዘር›› አሉ ብሎ ነው፡፡ ነጮቹን በድፍን ካውካሳይድ ይሏቸዋል፡፡ ጥቁሮቹን ኔግሮይድ ብለው ይሰይሙታል፡፡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከዚህ ውስጥ እንገኛለን፡፡ ሞንጎሎይድ የሚሉት ደግሞ ወደ ቢጫ ይጠጋል የሚሉትን የኤሲያ ህዝብ ነው፡፡ ዘር ምን ያህል እውነት ነው? ………… በዘመናችን ‹‹ዘረን›› ከፖለቲካ መቀስቀሻነት ባለፈ ‹‹ሳይንሳዊ›› ትንታኔው የሚሰጡት ባይጠፉም በቆዳ ቀለም፣ አካላዊ ቅርጽና በመሳሰሉት የሚለየዩ ሰዎች በስነ ህይወታዊ ይህ ነው የሚባል የጎላ ልዩነት እንደሌላቸው የሚከራከሩት ተበራክተዋል፡፡ ለአብነት ያህል ዘር ከስነ ህይወታዊ በተለይም ከዘረመል ጋር የረባ ግንኙነት የሌለው መሆኑን በርካታ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ ለፖለቲካ መቀስቀሻም ቢሆን በአይን ቀለሙ ለማመሳሰል የተሞከረ ህዝብ በቆዳ ቀለሙ አይገናኝም፡፡ አሊያም በአፍንጫው፣ ወይንም በሌላው ነገሩ ይያያል፡፡ በመሆኑም ፖለቲከኞች አሊያም ሰውን የሚከፋፍሉት ‹‹አጥኚዎች›› ‹‹ዘር›› ብለው ሲመድቡ ለራሳቸው አስተሳሰብ ወይንም ጥቅም ቅርበት ያለውን በማጠጋጋት ብቻ ነው፡፡ በምዕራበዊያን አገራት ከእናቱ ወይንም ከአባቱ አንዱ ጥቁር የሆነው ጥቁር ይሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ የእሱ የልጅ ልጆች ምንም ያህል ከነጭ ጋር ቢወላለዱና ነጭ ቢመስሉም ‹‹ኔግሮ›› የሚል ዘር ውስጥ መመደባቸው የግድ ነው፡፡ የኦባማ ልጆች ምንም ያህል ከነጭ ጋር ቢወላለዱ የልጅ ልጆቻቸው ጥቁር እንጅ ነጭ አይባሉም፡፡ ይህም የበላይ ነን የሚሉት ነጮች ለጥቁር ህዝብ ባላቸው የተሳሳተ አለመካከት የመጣ እንጅ የቀለም፣ የቆዳ አጠቃላይ የአካል ቅርጽ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ የሚያሳየን አብዛኛዎቹ ዘር ጥቃቅን ስነ ህይወታዊ ጉዳዮችን በማጋነን የመጣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፈጠራ መሆኑን ነው፡፡ ዘር የፖለቲካ ፈጠራ በመሆኑ ፓስተር፣ ቄሱ፣ ሹሁና ሌላው የ‹‹ሀይማኖት›› አባት የሰው ልጅ ከአንድ አዳምና ሄዋን መጣ ብሎ ሳይጨርስ ስለተለያዩ ‹‹ዘሮች›› ፖለቲካዊ ትርጉም ያወሩልናል፡፡ ስለ ጥንታዊ ሰው የሚያጠናው ሳይንቲስት የሰው ዘር መገኛ ‹‹አፍሪካ ነች›› ብሎ ሳያበቃ ፖለቲካው በጎተተው መጠን ስለተለያዩ ዘሮች ከማውራት አይቆጠብም፡፡ እንደ አብዛኛዎቹ የወቅቱ ሀቀኛ ምሁራን ከሆነ የቆዳ ቀለም ልዩነትን ለመፍጠር ከዘረመል ይልቅ የአየር ንብረት ትልቅ ቦታ አለው፡፡ በአፍሪካ በርሃማ ቦታዎች የሚኖርና በአውሮፓ ግግር በረዶማ ቦታዎች የሚኖር ህዝብ አንድ አይነት የቆዳ ቀለም ሊኖረው አይችልም፡፡ ሆኖም በሂደት ተላምዶዊም ሆነ በሌላ ምክንያት ዘረመልም በቆዳ ቀለምና በመሳሰሉት ምንም አስተዋጽኦ የለውም ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ የቆዳ ቀለምንና የመሳሳሉትን ልዩነት በመፍጠር ሚና የሚኖረው ዘረመል በጣም ጥቂትና በሰዎች መካከል ለመሰረታዊ ልዩነት መነሻ የሚሆን አለመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹‹ተመሳሳይ›› በሚባሉ ህዝቦች መካከል ያለው ስነ ህይወታዊ ልዩነትም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ከደም አይነት ጀምሮ ከቤተሰብ፣ ከጎሳና ብሄር፣ እንዲሁም ዘር የሚባለው በሙሉ የተለያዩ ናቸው፡፡ የአሜሪካን አንትሮፖሎጅ ማህበር እ.ኤ.አ በ1998 ባወጣው ጥናት ‹‹የሰውን ዘር በስነ ህይወታዊ ጥናት ድንበር ለይቶ መከፋፈል አይቻልም፡፡ 94 በመቶ ያህል የሰዎች ስነ ህይወታዊ ልዩነት አንድ ‹ዘር›› ውስጥ ናቸው በሚባሉት ውስጥም ይከሰታል፡፡›› የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ማለትም አብዛኛው ልዩነት አንድ ዘር በሚባሉትም መካከል እንዳለ ነው፡፡ በተለያዩ ወቅቶች ‹‹ዘር›› ለሚባለው የተሰጠውም ይህንኑ ጥላቻ አዘል ፖለቲካ የሚያሳይ ነው፡፡ ለአብነት ያህል በ18ኛውና 19ኛው ክፍለ ዘመን በነጮቹ ዘንድ ጥቁር ግማሽ እንሰሳ እንደሆነ ሁሉ ይታመን ነበር፡፡ በ19ኛው እና 20ኛው ክፍለ ዘመን ለዚህ አሉታዊ አስተሳሰብን የሚቃረን የማርክሲዝም አስተሳሰብ ብቅ ብሏል፡፡ በ20ኛው ክፈለ ዘመን በተለይም በ1930 ጀምሮ ደግሞ ዘር ለጦርነት ምክንያት ሲሆን አካላዊ ሳይሆን ፖለቲካዊና በፖለቲከኞች ፈጠራ የመጣ ልዩነት መሆኑን አስመስክሯል፡፡ ይህም ዘር የሚባለው ‹‹ፈጠራ›› መሆኑን እንደሚያሳይ በርካቶች በመከራከሪያነት ያቀርቡታል፡፡ ኢትዮጵያና የዘር ጉዳይ ………… ዘር መኖሩን አምነው በጉዳዩ ጥናቶችን የሚያደርጉ ‹‹ምሁራን›› ዘርን የሚያስቀምጡት ከጎሳና ብሄር በላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ጎሳ የሚባለው ‹‹አንድ አይነት አኗኗር፣ ስነ ልቦናዊ ሁኔታ፣ አለባበስ፣ ቋንቋ›› ውስጥ ከሚገኝ ‹‹ብሄር›› ከተባለው ማንነት በታች የሚገኝ ማንነት ነው፡፡ ሆኖም በርካቶች ዘርን ከጎሳና ከብሄር ጋር በማቀላቀል የቃሉን አውድ ሲያዛቡ ይስተዋላል፡፡ ፖለቲከኞች ዘር ሲሉ ምክንያቱን ስነ ህይወታዊ ምክንያት ይሰጡታል፡፡ እነ ሂትለር በጸጉር፣ በአይን ቀለም ጀርመናዊያንን ከሌሎቹ ሲያነጻጽሩ እንደነበሩት ማለት ነው፡፡ አሊያም ነጮቹ ራሳቸውን ከአፍሪካውያን፣ ከአረቦቹ አሊያም ከህንዶቹ ወይንም ከደቡብ አሜሪካውያን ጋር አነጻጽረው ልዩ እንደሚያደርጉት፡፡ ይህ ዘርን ከጎሳና ከብሄር ጋር የመቀላቀል አባዜ በኢትዮጵያም ከተለመደ ሰነባብቷል፡፡ በብሄር አሊያም በጎሳ የሚያምኑ የፖለቲካ ሀይሎችን የትኛውንም የፖለቲካ ጥበት ‹‹ዘረኝነት›› ብሎ መፈረጅ ለኢትዮጵያውያን አዲስ አይደለም፡፡ የኢህአዴግ መንግስት በሚያራምደው የብሄር ፖለረቲካ ‹‹በዘረኝነት›› ይወቀሳል፡፡ ሌሎችም ይህን የፖለቲካ ስልት በራሳቸው መልክ ይዘው ብቅ ሲሉ ‹‹የዘር ፖለቲካ›› ብለው የሚፈርጁት በርካቶች ናቸው፡፡ በአገራችን ከብሄርና ጎሳም ወረድ ሲልም ከእናት፣ አባትና ቤተሰብ የሚሳብን ዝምድና እና የ‹‹ደም›› ትስስር ለመግለጽ ‹‹ዘር›› ብሎ መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ሆኖም ዘር፣ ዘረኝነት.. የሚባለው ፖለቲካዊ ፍች ከቤተሰባዊ ትስስር ይልቅ ‹‹race›› ከተባለው ጥቅል (ግን የተሳሳተ የፖለቲካ ፈጠራ) ማንነት የመጣ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰረጸው ጣሊያን ካደረሰችው ምስቅልቅል ጋር ተያይዞ እንደሆነ በርካቶች ይገልጻሉ፡፡ ጣሊያኖች ኢትዮጵያ ውስጥ በራሳቸው የሰለጠነ ልዩ ዘርና በኢትዮጵያ ኋላ ቀር ዘር መካከል ከፈጠሩት ንቀት አዘል ክፍፍል ባለፈ ኢትዮጵያውያንን በ‹‹ብሄርና ጎሳ›› ከፋፍለዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ፖለቲካ አዋጭ መሆኑን የሚያምኑት አካላትን ከጣሊያኑ ከፋፋይ ስርዓት ጋር በማዛመድ ‹‹ዘረኛ፣ ዘር፣ የዘር ፖለቲካ›› ብለው ይፈርጇቸዋል፡፡ ‹‹ዘር›› ፈጠራ መሆኑን ለጊዜው ረስተን ከአገራችን ህዝብ አኳያ ብንገመግመው ሰህተት መሆኑን እንረዳለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር አሊያም ጎሳ የሚባለው የቋንቋ ልዩነት ሲጠቀስ በዘር መክፈልም ሆነ ጎሰኛ አሊያም ጠባብ ብሄርተኛን ‹‹ዘረኛ›› ማለት የተሳሳተ ነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹በየዘረኝነት›› ስም የሚያወግዙት አካላት ኢትዮጵያ በጠባብ ማንነት መከፋፈል የለባትም የሚሉ ናቸው፡፡ ሆኖም ‹‹ዘር፣ዘረኛ፣ ዘረኝነት ፖለቲካ›› አለ የሚሉ ከሆነ በአካልም ቢሆን እጅጉን የተለያየ ነን ወደሚል እጅግ የሚቃረንና የተሳሳተ አመለካከት ያደርሳቸዋል፡፡ በጸጉር፣ በአይን ቀለም፣ በቆዳ ቀለም፣ በቁመት እጅጉን የተለያየን ነን እንደማለት ነው፡፡ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡ የስርዓቱን ከፋፋይነት ለመግለጽ ከተፈለገ እንኳ ከጠባብ ብሄርተኝነት፣ጎሰኝነትና ጎጠኝነት ያለፈ ስም ሊሰጠው አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ብሎ በዓይን ቀለም፣ በጸጉር፣ በአፍንጫ፣ በቆዳ ቀለም፣ በቁመት፣ በቅርጽ….መለየት አይቻልም፡፡ አሊያም አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ… የሚባለው ህዝብ ውስጥ ተመሳሳይ የዓይን ቀለም፣ የቆዳ ቀለም፣ የአፍንጫ ርዝማኔና ቅርጽ…..ብቻ አካላዊ ማንነት አይኖርም፡፡ እንደ ሁመራና መተማ ያሉ በርሃማ አካባቢዎች የሚኖረው ህዝብ በአለባበስ፣ በአመጋገብና በአካል ገጽታ ከደጋው ትግርኛና አማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ይልቅ በቆላማው አካባቢ ከሚኖረው የአፋርና የሶማሊ አካባቢ ህዝብ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በደጋው አካባቢ የሚኖረው ኦሮምኛ፣ አፋርኛ፣ሶማሊኛ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ…..ተናጋሪ ህዝብ ተመሳሳይ ቋንቋ ከሚናገው ቆለኛ ህዝብ ይልቅ ሌላ ቋንቋ ከሚናገረው ደገኛ ህዝብ ጋር ተመሳሳይ ገጽታ፣ የኑሮ ዘይቤ፣አለባበስ…..ያለው ነው፡፡ ዘር ከፖለቲካ ፈጠራው አልፎ የደም ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ኦሮምኛ ተናጋሪው አንድ አይነት ደም፣ አማርኛ ተናጋሪው ከኦሮምኛ ተናጋሪው የተለየ ሌላ የደም አይነት በኖረው ነበር፡፡ በዓለም ደረጃም ቢሆን ተመሳሳይ ነው፡፡ ዘር የተሳሰተ የፖለቲካ ቀመር ነው፡፡ ይህን የተሳሳተ የፖለቲካ ቀመር እንጠቀም ካልም ደግሞ ‹‹ዘርን›› ካመጡት ‹‹ምሁራን›› ምድብ ልንወጣ አንችልም፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያውያንን የግድ በዚህ በተሳሳተ ቀመር እንክፈላቸው ከተባለ በጥቁር ማንነት ስር እኩል ከጋና፣ ከሞዛምቢክ፣ ከኬንያ፣ ከአንጎላ፣ ከጥቁር አሜሪካና ጃማይካኖቹ ጋር ይመደቡ ይሆናል እንጅ ሌላ ‹‹ዘር›› አይገኝላቸውም፡፡ እንዲያውም ጆሃን ብሉሜንባች የተባለው ጀርመናዊ ለመላው ጥቁር ህዝብ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› የሚል ዘር ነው የሰጠው፡፡ ከዚህ ባለፈ ኢትዮጵያውያንን በቋንቋና ሌሎች ጥቃቅን መሰረቶች ‹‹ዘር›› ብሎ መፈረጅ ግን በጥላቻ ከተሞላው ጀርመናውይም በላይ እንድንሳሳት ያደርገናል፡፡ እናም በበኩሌ ፖለቲከኞቻችን ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ሲወራ ‹‹ዘር›› የምትባለዋ ቋንቋ የተሳሳተች መሆኗን ተረድታችሁ ባትጠቀሙባት ይሻላል እላለሁ፡፡ ካልሆነ ግን ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛ፣ አገውኛ፣ አርጎብኛ…..ተናጋሪው አንዱ ከሌላው በአይን ቀለሙ፣ በጸጉሩ፣……….እንደሚለይ መረጃ ልታቀርቡልን የግድ ነው፡፡ ዝም ብሎ መከፋፈል አለ እንዴ?

http://66.147.244.58/~theethio/harartub … %E1%8A%93/

Abraha Desta
November 19
“ከህወሓት የባስክ ትሆናለህ” አሉኝ
———————————–

“ጨቋኝ ስርዓት አልፈልግም” ብዬ በፃፍኩት ላይ አንድ የፌስቡክ ወዳጄ “አንተ ራስህ ስልጣን ብትይዝ ከህወሓት የባስክ አምባገነን ትሆናለህ” አለኝ።

እኔም እላለሁ፣

ከህወሓት የተሻልኩ እንደምሆን እርግጠኛ አይደለሁም (ራሴ ለግዜው እንደ ፓርቲ ልቁጠር)። ስለ አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ። እኔ ሰለማዊ ታጋይ ነኝ። ስልጣን የምይዘው በህዝባዊ ምርጫ እንጂ በጠመንጃ አይደለም። የምወዳደረው በሐሳብ እንጂ በሃይል አይደለም።

ስለዚህ ስልጣን ስይዝ የራሴ ወታደር፣ ፖሊስ፣ ዳኛ ወዘተ ይዤ አልመጣም። ስልጣን የምይዘው በሕገመንግስት መሰረት እስከሆነ ድረስ በኔና በወታደሮቹ ያለ ግንኙት ሕገመንግስታዊ ይሆናል። ስለዚህ ወታደሮቹ እንደፈለኩ የግሌ የስልጣን ጥም ለማርካት አላዝዛቸውም። ዳኞችም ነፃ ይሆናሉ።

ስለዚህ እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ከህወሓት ካልተሻልኩ በህዝብ ምርጫ እንደወጣሁ ሁሉ በሚቀጥለው በህዝብ ምርጫ ከስልጣን እወርዳለሁ። ከስልጣን ላለመውረድ ምንም ዓቅም የለኝም፤ ምክንያቱም በምርጫ ስልጣን የያዘ አካል የግሉ ወታደርና ፖሊስ የለውም። የስልጣን መሰረቴ የህዝብ ድምፅ ከሆነ በስልጣን ለመቆየት ስል ህዝብን አልጨቁንም። ከጨቆንኩ ደግሞ ህዝቡ ያወርደኛል።

የኢህአዴግ መንግስት ሰለማዊ ትግልን አጨልሞብኝ በትጥቅ ትግል ስልጣን ከያዝኩ ግን አምባገነን የመሆን ዕድል አለኝ። ምክንያቱም የስልጣን ምንጬ ጠመንጃ እንጂ ህዝብ አይደለም። ለህዝብ ታማኝና አገልጋይ የምሆንበት ዕድል ይጠባል። ስለዚህ በምርጫ ስልጣን የያዘ መንግስት ቢያበላሽ እንኳ በምርጫ ይወርዳል። አሁን የቸገረን በጠመንጃ የመጣ መንግስት ነው።

ዓላማችን ስልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ስልጣን በጠመንጃ ከመያዝ በምርጫ የምያዝበት ስርዓት መገንባት ጭምር ነው።

(ስልጣን የመያዝ ዕቅድም ፍላጎትም የለኝም። የኔ ፍላጎት በነፃነት የፈለኩትን ማድረግ ነው። እኔ የሌሎችን መብት ሳልዳፈር የፈለኩትን የማድረግ ነፃነት እንዲኖረኝ የህዝብ መንግስት ወይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አለበት። ስልጣን መያዝ ነፃነትን ይገድባል)።

It is so!!!