“የኢትዮ-ኤርትራ ችግር መፍትሄ፣ ድንበር ማስመር ሳይሆን ድንበር ማፍረስ ነው”
——————————–

ኤርትራዊው ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ እንዲህ ተጠየቀ;

አዲስ አድማስ ጋዜጣ : የኤርትራ ህዝብ አሁን ያሉበትን የነፃነት ሁኔታ ከቀድሞው ጋር ሲያስተያዩት ምን ትርጉም ይሰጥዎታል?

ተከስተ ነጋሽ: እኔ እኮ በመጀመሪያም ኤርትራውያኖች ከማን ነው የሚገነጠሉት የሚል አቋም ነው ያለኝ። ማነው ከማን የሚገነጠለው? የደቡብ ወይም የኦሮሞ ህዝቦች እንገነጠላለን ቢሉ ኖሮ ምክንያት ነበራቸው፡፡ የኤርትራ የነፃነት ጥያቄ በተነሳበት ወቅት ኤርትራውያኑና ከላይ የጠቀስኳቸው ህዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ያገኙትን እድል (Comparative advantage) ስናይ፣ ኤርትራውያኑ በጣም ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ (በጣሊያን፣ በእንግሊዝ፣ በፌዴሬሽኑ ዘመን) በ1960ዎቹ የአዲስ አበባ ሀብታሞቹ እነሱ ነበሩ። በትምህርት መስክ ሃያ አምስት በመቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች ኤርትራውያን ነበሩ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችንም ካየሽ 25 በመቶ የሚሆኑት ኤርትራውያን ነበሩ፡፡ ከተማረው ሰላሳ አምስት በመቶው ክፍል ኤርትራውያን ነበሩ፡፡

Image
ልሂቃን ለስልጣናቸው ሲሉ ሊሰብሩት የሚጥሩትን ድልድይና ገመድ አጠናክረነው በሰላም አብረን መኖር የምንችለው፡፡

በእርግጥ እኛም ከኤርትራውያን የምንሻልበት ደረጃ ላይ አይደለንም፡፡እነሱም እንደኛው ናቸው፡፡ መከራ ውስጥ ሆነውም ቢሆን ግን በሳውዲ አረቢያ ሰቆቃ የደረሰባቸውን ዜጎች ድምጽ ከጎናችን ሆነው አሰምተዋል፡፡ በደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ከጎናችን ሆነው የአገራችን ቡድን አበረታትተዋል፡፡
ድሮም ቢሆን ህዝብ በራሱ ተሳስቶ አያውቅም፡፡ ህዝብን የሚያወናብዱት ልሂቃን ናቸው፡፡ ኤርትራ በጣሊያን እጅ በነበረችበት ወቅት በርካቶቹ ወደ እናት አገራቸው ጠፍተው ገብተው በከፍተኛ ስልጣን አገራቸውን አስተዳድረዋል፡፡ እነ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስግዶም ስለ እናት አገራቸው መስዋትነት ከፍለዋል፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌደራል ስርዓት ስትቀላቀል ጨፍረዋል፣ ደስታቸውን በእምባ ሳይቀር ገልጸዋል፡፡ ይነሱም ይብዙም ኤርትራውያን በኢትዮጵያ መከራ ጊዜ ከጎናችን እርቀው አያውቁም፡፡
አጼ ኃይለስላሴ ፌደሬሽኑን ሲያፈርስ በኢትዮጵያውያን ድጋፍ ወይንም ግፊት አልነበረም፡፡ መንግስቱ ኃይለማሪያም በኤርትራውያን ላይ እርምጃ ሲወስድም ቢሆን እንዲሁ፡፡ ጀብሃና ሻዕቢያ በአረብ አገራት ድጋፍ ኤርትራን ለመገንጠል የጣሩት በህዝቡ ትዕዛዝና ግፊት አሊያም ድጋፍ አልነበረም፡፡ እንዲያውም ይህንን ተገንጣይነት ኤርትራውያን ‹‹እናት አገር ወይንም ሞት›› ብለው ተዋግተውታል፡፡ በኢትዮጵያ የነበሩት አስተዳደሮችም ሆነ ‹‹ወንበዴዎቹ›› ስህተት ግን ሁለቱን ህዝቦች መካከል ያለውን ድልድይ ለመስበር ሳይታክቱ ሰርተዋል፡፡
ህወሓትና ሻዕቢያ ስልጣን ከያዙ በኋላም ቢሆን የሁለቱ ህዝቦች ትስስር እንደፈለጉት ሊበጠስላቸው አልቻለም፡፡ የሻዕቢያና የህወሓት ካድሬዎች ሁለቱን ህዝቦች እየደበደቡ፣ እየዘረፉ፣ እያሰቃዩ ከአስመራና አዲስ አበባ ሲያስወጡ ህዝብ የተለያየው በእንባ ነበር፡፡
በእርግጥ የመንግስታት ፕሮፖጋንዳ፣ ካድሬዎች የሚፈጥሩት መከራና ኢኮኖሚያዊ ወይንም ሌላ ግንኙነት በመቋረጡ ምክንያት ህዝቦች ሊቆራረጡ ይችላሉ፡፡ ሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመስበር የተደረገው ሙከራ ግን አልተሳካም፡፡ አዎ! ኤርትራውያን የአገሪቱ ‹‹መንግስት›› ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ባሰረበትና በደበደበበት ወቅት ከጎናችን ሆነው ገመዱ ኃይለስላሴ፣ መንግስቱ ኃይለማሪያም፣ ኢሳያስ፣ መለስ፣ ህወሓት፣ ሻዕቢያ ሊበጥሱት የማይችሉ የደም ገመድ መሆኑ በድጋሜ አሳይተውናል፡፡
እናም እንደነሱው ከጎናቸው መቆም ይገባናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢሳያስ ጠፋ፣ ታመመ እየተባለ ነው፡፡ አምባገነን መሪ ሲሞት፣ ሲታመም፣ ወይንም አምባገነኑ ስርዓት ምክንያት ስርዓት ሲናጋ የሚጎዳው ሀብትና ጥበቃ የሌለው ምስኪን ህዝብ ነው፡፡ ሀብት ያላቸው የኤርትራ ባለስልጣናት በፈለጉት አገር ሄደው ይኖራሉ፡፡ ጥበቃ ያላቸው አገር ውስጥም ቢሆን አንጻራዊ ሰላም ይኖራቸዋል፡፡ ድሃውና ሲጨቆን የነበረው ህዝብ ግን አምባገነኑ እያለም ሆነ ሞቱ ስጋት ውስጥ ነው፡፡ የአገር አደጋ አደጋ የሚሆነው ለድሃው ነው፡፡
ኢትዮጰያውያን መለስ ዜናዊ ጠፋ፣ ታመመ፣ ሞተ በተባለበት ወቅት አምባገነንነቱን ረስተን ‹‹አገር ትፈራርሳለች›› ብለን ተጨንቀናል፡፡ ኤርትራውያንም አሁን ተመሳሳይ ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡ ሁለቱ ህዝብ በተለያየ ጊዜ ይከሰቱ እንጅ ተመሳሳይ መከራ፣ ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡ ችግራቸው መሰረት ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም እነዚህን ችግሮች መፍታት የሚችሉት አንዱ ከአንዱ ጎን በመቆም ብቻ ነው፡፡
ለችግሮቻቸው መፍትሄ ማምጣት እንኳን ባንችል ልክ እንደወትሮው፣ ልክ እንደባህላችን፣ ልክ እነሱ እንዳደረጉት ከጎባቸው መሆናችንን ማሳየት አለብን፡፡ ሲሆን ታሪክ፣ ደም፣ አምሮ መኖር በደመነፍስ እያነጋኘን እንደሆነ በቅርቡ አይተነዋል፡፡ የሁለቱ አምባገነን ስርዓቶች ፕሮፖንዳና መሰሪነት በርካቶቹን እሴቶቻችን ሸርሽሮት አብሮ መስራት እንደማይቻል የሚያስብ የዋህ (ካድሬ ቢኖር እንኳ) ጎረቤቶች ነን፡፡ የኤርትራ ችግር መቼም ቢሆን የኢትዮጵያውያን ችግር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ችግር የኤርትራውያን ችግር ነው፡፡ ከሁለቱ አገራት መካከል አንዱ እንደ ሰው ተሰዶ ወይንም ሸሽቶ፣ አሊያም አጥሮ መኖር አይችልም፡፡ የሶማሊያና የሱዳን ችግር እንኳን ችግራችን ሆኗል፡፡
እናም በችግራቸው ጊዜ አብረናቸው መቆማችን ለእነሱ ብቻ ሳይሆን ለእኛም ጥቅም ነው፡፡ ስለሆነም ከኤርትራውያን ወንድምና እህቶቻችን ጎን አብረን መቆም ይኖርብናል፡፡ እንዲህ ሲሆንም ነው ልሂቃን ለስልጣናቸው ሲሉ ሊሰብሩት የሚጥሩትን ድልድይና ገመድ አጠናክረነው በሰላም አብረን መኖር የምንችለው፡፡ — with Getachew Shiferaw and 2 others.

በውጪ ሐገር በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው የካምፓላ መካነሰላም መድሃንያለም ቤተክርስትያን በዩጋንዳ የህዳር ሚካዔልን የንግስ በዓል ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አንዳከበሩት በስፍራው የነበረው የፔን ዘ ኢትዮጵያ ዘጋቢ ገለፀ።
ከለሊቱ አስራአንድ ሠዓት ጀምሮ በማህሌት የጀመረው ክብረ በዓል በደብሩ መሪጌታ ይህይስ ዓለሙ ያሬዳዊ ዝማሬ ቀርቧል።<ውእቱ ሚካዔል መልዓከ ኃይለ ልዑል።ውእቱ ልዑለ መንበር ይስአለነ……>
በዕለቱ ቅዳሤ በርካታ ምዕመናን የታደሙ ሲሆን ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አስራ ስምንት ከቁጥር አስራአምስት እስከ ሃያ አንድ በቆሞስ አባ ኃይለማርያም ተነቧል። ስርዓተ ቁርባን ከተከናወነ በኋላም በቆሞስ አባ አብዩ የዕለቱን በዓል በማስመልከት ኦሪት ዘፀአት ምዕራፍ አስራ አራት ከቁጥር አስራ ዘጠኝ ጀምሮ ያለውን ቃል በተመለከተ የወንጌል ማዕድ ቀርቧል።
የቅዳሤ ስርዓቱ እንዳበቃም ታቦተ ህጉ በካህናትና ምዕመናን ታጅቦ በክብርና በምስጋና ዜማ ታጅቦ በአውደ ምህረቱ ላይ መሪጌታ ይህይስ <አንተኑ ሚካዔል መና ዘአወረድከ።ወአንተኑ ለእስራዔል መና ዘአወረድከ።>በያሬዳዊ ዜማ ወረብ አቅርቧል።
የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ፀሐይ ደስታ በበዓሉ ፍፃሜ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እግዚአብሔር አምላክ እስራዔላዊያንን ከግብፅ የባርነት ቀንበር ነፃ የወጡበትን ዕለት በመዘከር ይህንን ታላቅ በዓል ቤተክርስትያን በድምቀት እንደምታከብረውና በዓሉ የስደተኞች በዓል ሊባል እንደሚችል ጠቁመው ስደተኞች ሁላችን እግዚአብሔር አምላክ እስራዔላዊያንን ከግብፅ የፈርዖን አገዛዝ እንዳዳናቸው ሁሉ እኛንም ለሐገራችን ያብቃን ሲሉ ቃለ ምዕዳን ሰጥተዎል።
በመጨረሻም የአምልኮ ነፃነት በተረጋገጠባት ዩጋንዳ ኤርትራዊያንና ኢትዮጵያዊያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የፖለቲካ ድንበር ሣያግዳቸው በአንድ ደብር ፈጣሪያቸውን ሲያመሠግኑ የዚህ ዜና ዘጋቢ ተመልክቷል።
Pen Ethiopian

Image

በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ጥቃት እና የፈዘዘው ስርኣት የፖለቲካ ክስረት
መፍትሄው ኢሕኣዴግ የማይደፍረው ስር ነቀል ለውጥ ነው::

ምንሊክ ሳልሳዊ:-ኢትዮጵያውያን በመካከለኛው ምስራቅ በስፋት መሰደድ የጀመሩት ባለፈው 20 አመታት የወያኔው ጁንታ መንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በህዝቦች ላይ በተለየ መልኩ የፈጠረውን አደገኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ መሆኑ እሙን ነው::ይህ ቀውስ የደረሰባቸው ወገኖቻችን ከተሰደዱባት ሃገር አንዷ ሳኡዲ አረቢያ ተጠቃሽ ናት::ሳኡዲ አረቢያ ከሃብቷ ብዛት የመጣ የስራ ፍቅር ባሌለው ወጣት ዜጋ የተሞላች እና ፔትሮ ዶላር ባሰከራቸው ቱጃሮች የምትተዳደር አገር መሆኗ እና የዜጎቿ የስራ አለመስራት የስራ እድሎችን ስላሰፋ የወያኔ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጠቂዎች ወደዚሁ መሰደድን መርጠዋል:: ይህንን ተከትሎም ይህን ሰሞን የአለም ዋና አጀንዳ የሆነው የኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረቢያ እየደረሰባቸው ያለ ስቃይ ነው::

ሰቆቃው ያደረሰው የሰብኣዊ መብት ጥያቄ ከሳኡዲ መንግስት ላይ ይልቅ ወደ ወያኔው ጁንታ ላይ እንዲተኮር ያደረገ ሲሆን የወያኔው ጁንታ ለከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ተዳርጓል::በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው አስደንጋጭ እና ሰብኣዊነትን ያለፈ ድርጊት በመንግስት ባለስልጣናት መሃከል የፈጠረው መረበሽ እስከአለመግባባት አድርሷቸዋል::ይህንን የወያኔን አቋም የተመለከተችው ሳኡድ አረቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ የበላይነት ተቀናጅታለች::በከፍተኛ ደረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ አትኩሮት አግኝቶ የአለም ጎዳናዎች ሳኡዲን እና ወያኔን በሚቃወሙ በሰላማዊ ሰልፍ እየተጥለቀለቁ ነው::ህገመንግስታዊ መብቶችን አለመከበሩን እና ለዜጎች አለመቆርቆርን በማሳየቱ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል::ሚዲያዎች ከዜጎች የሳኡዲ ሰቆቃ ይልቅ በኢትዮጵያውያኑ ሰልፎች ላይ አትኩሮት ሰተዋል::

ከወያኔው መንግስት የሚንጸባረቁ አጀንዳዎች ለዘብተኛ አቋሞች በስህተት እንደተፈጠሩ ወቅታዊ ሁኔታኦች እያሳዩ ሲሆን ስርኣቱ አጣብቂኝ ውስጥ እና የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ እንደገባ ተረጋግጧል:: የሌላ ሃገር እምባሲዎች ዜጎቻቸውን በመጠበቅ ላይ ሲያተኩሩ የወያኔው ዲፕሎማቶች የዜጎች ንብረት የሆነውን ኤምባሲ በመዝጋት አገልግሎት አቁመዋል::
የደረሰውን ሰቆቃ ተከትሎ ስርኣቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ለሉአላዊ የዜግነት ክብር መነሳሳት ሲኖርበት እና ህዝብን ማቀፍ ሲኖርበት ለብሄራዊ ውርደት ዜጎችን ዳርጓል::የፖለቲካ ፓርቲዎች የጠሩትን ሰልፍ በሃይል እና በደብዳቤ በትኗል::የወያኔው ስርኣት የህዝቡን ቁጣ ባለማንበቡ በችኮላ ያልበሰለ ሃሳብ በማራመዱ የፖለቲካ ኪሳራውን አስፍቶታል::ህገመንግስታዊ መብቶችን አለመከበሩን እና ለዜጎች አለመቆርቆርን በማሳየቱ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል::ሚዲያዎች ከዜጎች የሳኡዲ ሰቆቃ ይልቅ የወያኔን ስርኣት ጋጥወጥነት አትኩሮት ሰተውታል::

ለዚህ ሁላ ችግር መንስኤው ስርኣቱ በልማት ሽፋን የሚከተለው የፖለቲካ እና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግሮች እንደሆኑ አግጥጦ ገሃድ ከመውጣቱም በላይ የአደባባይ ሃቅ ሆኖ ለለውጥ እንትጋ የሚሉ ድምጾች በመላው ሃገሪቱ ተንጸባርቀዋል:; የወያኔ ስርኣት ህዝብን የሚያሳትፍ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ እስካልተከተለ ድረስ እና አሁን ባለው ሂደት ላይ ለውጥ እስካላደረገ ድረስ የስደት ችግሩ በስፋት እየቀጠል ይሄዳል:;ዛሬ ሳኡዲ ላይ የደረሰው ሰቆቃ ነገ በሌሎች ሃገራትም ይቀጥላል::ይህ ብሄራዊ ውርደት በታሪካችን አይተነው የማናውቅ ነው:;ኢትዮጵያውያን ከቀድሞው ጀምሮ በፖለቲካ ቢሰደዱም እንደዚህ አይነት ውርደትን አስተናግደው አያውቁም::የአሁኑ ውርደት ያለው ስርኣት ለዜጎቹ ደንታ ቢስ በመሆኑ የተወለደ ችግር ነው::በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ተመዘገበ ከመባል ውጭ የተባለው እድገት ምንም አይነት ህዝባዊ ጠቀሜታ እንዳላሳየ በይፋ አስመስክሯል::የተማረው እና የሚሰራው ሃይል መሰደዱ ኢኮኖሚው እንደኮላሸ እንጂ እንዳደገ አያሳይም::የዚህ ሁላ መንስኤው ስርኣቱ የሚከተለው አፋኝ የፖለቲካ እና የእኮኖሚ ፖሊሲ ስለሆን ድጋሚ ሊከለስ እና ሊፈተሽ ይገባዋል::

የነቃ እና የተደራጀ አዲስ ፖሊሲ አስፈላጊ መሆኑ እሙን የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል::ስርኣቱ የሚከተለውን ፖሊሲ በአስቸኳይ ካልቀየረው የሚመጣው አደጋ ከፍተኛ ነው::በሃገሪቱ በልማት ስም እና በፖለቲካ ባላንጣነት በዜጎች ላይ የሚደርሰው ችግር የሙስና መንሰራፋት ሚዛናዊነት የጎደለው የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ የግሉን ሴክተር የማዳከም ውስጣዊ ሴራ ዘር ተኮር የሆነ ፖለቲካ እና አድሎኣዊ አሰራር የትምህርት ጥራት መውረድ እና የስራ አጡ ቁጥር እንዲስፋፋ የሚደረጉ ደባዎች ዜጎች ምንም አይነት ጥያቄ እንዳያነሱ የሚደረጉ የፖለቲካ ዱላዎች ለድህነት መፈጠር እና የስደት መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል::የህዝብ ቁጥርን ተከትሎ የሚደረግ የእድገት ፖሊሲ አለመመጣተን የሃገሪቱ ዜጎች ተዘዋውረው እንዳይሰሩ የተደረገ የጎሳ ፖለቲካ የተማሩ ዜጎችን የስራ እድል አጥብቦታል::አለ ተብሎ የሚወራለት የኢኮኖሚ እድገት ጥቂት የስርኣቱን ካድሬዎች ተጠቃሚ ያደረገ በመሆኑ ማንኛውም ነገር በካድሬዎች ዙሪያ እና በፓርቲ ስራዎች ዙሪያ ያተኮረ በመሆኑ ዜጎች በሃገራቸው ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል::

ያለው ስርኣት ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ፖሊሲዎቹን እና የደረሱ የዜጎችን ችግር ከስሩ መሰረቱ መመርመር አለበት:: በፓርቲው አመራር ደረጃ ያሉ የስርኣቱ ባለስልጣናት ለስርነቀል ለውጥ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው::በግል የንግድ ተቋማት ላይ ስርኣቱ ያለው አቋም ከመጀመሪያ ለውጦች አንዱ ነው የግል የንግድ ተቋማት መዳከም ምክንያቱ የስርኣቱ መራሽ የንግድ ድርጅቶች እና አድሏዊነት የፈጠረው የኢኮኖሚ ችግር ሲሆን መፍትሄውም የተዳከመውን የግሉን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያንሰራራ ማድረግ እና ለዜጎች በርካታ የስራ እድሎች እንዲከፍት ማበረታታን አንዱ ሲሆን የተለየ የፖለቲካ አቋም ያለው ዲያስፖራው በሃገሩ ጉዳይ እንዲሳተፍ እድሎችን ማመቻቸት እንዲሁ ለፖሊሲ ለውጥ ጅማሮ ሊሆን ስለሚችል ስደትን በስፋት ለመቀነስ እና ዜጎች ከሃገራቸው እንዳይወጡ ለማድረግ ይችላል::

በአሁን ሰአት ስርኣቱ እየተተቀመበት ያለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ከመሆኑም ባሻገር ባልተማሩ እና ባልሰለጠኑ የፖለቲካ ታማኞች ስለሚተገበር በአግባቡ እየተተረጎመ ባለመሆኑ ውድቀትን አምጥቷል::የሃገሪቱ አጠቃላይ ሃብት እና የኢኮኖሚ ምሶሶ በጥቂት የፓርቲ ድርጅቶች እና ባለስልጣናት እጅ በቁጥጥር ስር ስለሆነ የግሉ ኢንቨስትመት በመዳከሙ እና ስርኣቱ ከዚህ አይነት የንግድ እንቅስቃሴ ካልወጣ በቀር ምንም አይነት ለውጥ መምጣት እንደማይቻል እሙን ሲሆን መፍትሄው የተቆጣጠረውን እና በግል መያዝ ያለባቸውን የንግድት ተቋማት እና የአገልግሎት ዘርፎች መልቀቅ ካልቻለ ችግሩ እየከፋ ዜጎችን ምንም ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል::በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚታየው መንግስታት ህግ የማውጣት እና የማስፈጸም አቅም እንጂ ከትልቅ እንስከተራ ንግድ ድረስ እጃቸውን አስገብተው ሲሰሩ አይታይም::ያለው ስርኣት ወደ ቸርቻሪ ነጋዴነት በመቀየሩ ለዜጎች የስራ እድሉን አጥብቦታል::

ኢኮኖሚውን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች እና የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች በሞኖፖል ስለተቆጣጠሩት ዜጎች በስርኣቱ ፖለቲካ ካልተጠመቁ ድረስ ስራ የማግኘት እድል የላቸውም::ይህ ኢኮኖሚውን የመቆጣጠር የፖለቲካ ጭብርብሮሽ የኢንቨስትመት ሂደቱን ከማዳከሙም በላይ ዜጎች በሃገራቸው እና በስርኣቱ ላይ እምነት እንዲያጡ አድርጓል::ስርኣቱ ከነጋዴነት መውጣት ሰፊ የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ እና ስደት እንዲቀንስ የሚረዳ ሲሆን ዜጎች በሃገራቸው ተሳፋ እንዳይቆርጡ ያደርጋል:: እንዲሁም የመንግስት የመገናኛ ቡዙሃን በሃሰት የተሞሉ መሆናቸው እና አስፈላጊውን መረጃ መስጠት አለመቻላቸው ሌላኛው የኢኮኖሚ ድቀት እና የስደት መንስኤ ናቸው:: በነጻነት የማይሰሩት እና ለፖለቲካው የእድሜ ማስረዘሚያ የሆኑት የመገናኛ ብዙሃን ቀረጥ የሚከፍላቸውን ህዝን እንዳያገለግሉ ከመደረጉም በላይ በሃሰት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ወንጀሎችን በመፈብረክ የታወቁ ሆነዋል::

ሕዝቡ ስርኣቱ እስካልተመቸው ድረስ ስደትን ማቆም አይቻልም ጊዜአዊ እገዳውም ውጤታማ አይሆንም:: ሀገሪቱ ብዙ ሴቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሊሰደዱባት የቻለውም ከሴቶች እኩልነት ጋር በተያያዘም ችግር በመኖሩና ብዙ ስራ አለመሰራቱን የሚያሳይ ነው::በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችም በነፃነት አለመቋቕውማቸው ሴቶችም እንደሰው አለመታየታቸው ነው::የፓርቲ ፖለቲካ መስበክ ሳይሆን በሴቶች እኩልነት እና ተሳትፎ ዙሪአ ኢኮኖሚው መዳበር ሲኖርበት አስፈላጊውን ኦረንቴሽንም መስጠን የስርኣቱ ግዴታ ነው::አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ስራ የሚገባውን ወጣት የሚሸከም ኢኮኖሚ አልተፈጠረ:: የግል ሴክተሩም በርካታ ዜጎች እንዳይፈጥር ሆኖ እየሞተ መሆኑን ከዓለም ባንክ ሪፖርቶች ማየት ይቻላል::በዓለም ደረጃ በመንግስት ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ በዓለም ሦስተኛ ስትሆን፤ በግል ኢንቨስትመንት ከመጨረሻዎቹ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ነን። ስለዚህ የግል ሴክተሩ ካልተስፋፋና ካላደገ ስራ ሊፈጠር አይችልም። በየዓመቱ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቀው ወጣት በዓመት ወደ መቶ ሺህ ሊጠጋ ነው። ይሄንን ኃይል መጦ የሚያስቀር የሚያደርግ ኢኮኖሚ መፈጠር የሚቻለው የግል ሴክተሩ ሲነቃቃ ነው። አሁን የግል ሴክተሩ በኮንስትሪክሽን ዘርፍ ላይ ውር ውር እያለ ነው። ይሄም ሴክተር ቢሆን፤ የቀን ሰራተኛ ከመሳብ ባለፈ ሙያተኛውን መቅጠር አልቻለም። ለዚያውም ትንሽ ሲሚንቶ መለሰን ሲጀምሩ ወደ መካከለኛው መስራቅ በተከበረ ወርሃዊ ደመወዝ ሲቀጠሩ ይታያል። ሀገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል የላትም። ያሉዋትም ለባዕድ አገር እያገለገሉ ነው። በአንፃሩ የአገሪቱን የባቡር መንገድ እና ግድብ የሚሰሩት ቻይናና ሕንድ ናቸው። ስኳር ፋብሪካውንም የሚሰሩት ሕንዶች ናቸው። በሚያሳዝን መልኩ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የተማሩም ሆነ ያልተማሩ ችሎታቸውን እየሸጡ ያሉት ለባዕድ ሀገር ነው። ከአፍሪካ እስከ ደቡብ ሱዳን፣ ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ሳይቀር በርካታ ኢትዮጵያውያን ችሎታቸውን በጥሩ ዋጋ እየሸጡ ነው። ይሄን አሳዛኝ ታሪክ ለመቀየር የግል ሴክተሩ ማደግ ወሳኝ ነው ።

የግል ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይረከብ ማለት ግድብ ይገንባ፣ የባቡር መንገድ ይዘርጋ ማለት አይደለም ነገር ግን የግል ዘርፉ ሊሰራቸው የሚችሉ ስራዎች ተለይተውና ተጠንተው መሰራት አለባቸው። የኅብረተሰብ ችግርም እየተበራከተ ስለሆነ ችግሩን መመርመር ያስፈልጋል ። የግል ዘርፉ ከካፌና ሆቴል ላይ ብቻ የሚሯሯጠው ለምንድነው? የቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት ችግር በገፍ የማይመጣው ለምንድነው፣ አነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀት ምን ያህል ውጤት አምጥቷል? የተደራጀ ጠንካራ የግል ዘርፍ መፍጠር ነው ወይስ አነስተኛ ጥቃቅን ድርጅቶች የሚለው መታየት አለበት። የትኛው ነው ብዙ ኀሳብ የሚያመነጩት፣ የገበያ ሁኔታስ? ባንኮች አካባቢ ያለው ችግር ምንድነው? ለምን አያበድሩም ይሄ ሁሉ መፈተሽ አለበት ።የኢትዮጵያ የአረብ ገረድ አምራች ሆና መቅረት የለባትም ።

http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … st_21.html

ዐረቢያ፥ ረቢያ፥ የቄዳር ግፊያና ግፍ።
ኅዳር ፱ ቀን ዓ. ም.
ከእስልምና እምነት መምጣት በፊት ዐረቦች የሚኖሩት መካ፣ ያትሪብ፣ መዲና ወዘተ ተብለው ይጠሩ
በነበሩ ሠፈሮች አካባቢ ነበር። ዐረቦች የአስተዳደር ሥርዓት ፣ የህግ ሥርዓት ወይም የእደ ጥበብ
ስምሪት አልነበራቸውም። መንግሥትና መንግሥታዊ አስተዳደር የሚባል ነገርም አያውቁም ነበር።1
ቁሬሺ፣ ባኑ ሃሺም፣ ባኑ ኡማያ ወዘተ በሚባሉ ጎሳዎች ተለያይተው ግን ይጣሉ ነበር።2 ጣዖት
አምላኪዎችም ነበሩ። ካባ የተባለ ድንጋይም ያመልኩ ነበር። እስከ አራት መቶ ዓ.ም. አካባቢ ዐረቦች
ለሚናገሩት ቋንቋ መፃፊያ ፊደል አልነበራቸውም። ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ በንግግር ግጥም
መፎካከር የዐረቦች ባህል ነበር።3 እጅግ በጣም ግጥም የሚገጥመውን ሰው መጅኑን እያሉ ይጠሩት ነበር። ዐረቦች
ከእስልምና በፊት የነበረውን ዘመን ጃሂሊያ ወይም የድንቁርና ዘመን ብለው ይጠሩታል።
በዚህ ጊዜ ነበረ አንድ ሙሀመድ የሚባል ዐረብ መካ አጠገብ በሚገኜው የሂራ ኮረብታ ላይ ሳለሁ ጅብሪል ነገረኝ
ብሎ አዲስ እምነት በአቅራቢያው ላሉ ሰዎችና ለዘመዶቹ የሰበከው። በልዩ ልዩ የምዕራባዊ ትረካዎች እንደሚነገረው
ሙሀመድ በሂራ ኮረብታ ላይ ጅብሪል ነገረኝ ካለበት ጊዜ በፊት እሱ በሚኖርበት አካባቢ ክርስትናን ለማስፋፋት
ክርስቲያኖች ብቅ ይሉ እንደነበረ ይነገራል። ከነዚህም ውስጥ ዋናዎቹ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ከኢትዮጵያውያንም
መካከል የሂመራ (የየመን) ንጉሥ አብርሃ ዐረቦች ወደ ሰንዓ መጥተው በሰንዓ የተገነባውን ትልቁን የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በግቢው ተደብቀው በመጸዳዳት ባረከሱ ጊዜ ዐረቦቹን ለመቅጣትና የመካን የካባ
ጣዖት ለማፍረስ ሥንቅ በዝሆኖች ጭኖ ያደረገው ዘመቻ ይታወሳል።4 ሙሀመድ ይዞት ለተነሳው እምነት መሠረተ
ሃሳቡን ያገኘው ክርስትናን ለማስፋፋት እሱ ወደሚኖርበት አካባቢ ከሄዱ ኢትዮጵያውያን የወንጌል አስተማሪዎች
መሆኑን በእስልምና እምነት በተለይም በቁርአን ውስጥ ያሉ ጭብጦች ያመለክታሉ።
የእስልምና እምነት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ “ኢሳ” የሚባል ስም ነው የተሰጠው። በሌሎች አገሮች የነበሩ
ወንጌላውያን ኢየሱስ ክርስቶስን፥ “የሽዋ” ወይም “ሄሱስ” ወይም “ጀሽዋ” ወይም “ጂሰስ” ወይም “አየሱስ” እያሉ
ነበር የሚጠሩት። በእስልምና ውስጥ ላለው “ኢሳ” ለሚለው ቃል በጣም የሚቀርበው የግዕዙ “ኢየሱስ” ሲሆን
ቀጥሎም የግሪኩ “አየሱስ” ነው። ሙሀመድ ቃሉን ከግዕዙ ወይም ከግሪኩ መውሰዱን ለመለየት ቀላሉ ማነጻጸሪያ
ሙሀመድ “ማርያም” የሚለውን ቃል ከየት እንዳገኜው መለየት ነው። በእስልምና “ማርያም” የሚለው ቃል ድንግል
ማርያምን ለመጥራት የሚጠቀሙበት ሲሆን ቃሉ በግሪክ “ማሪያ” የሚል ሲሆን በግዕዝ ደግሞ “ማርያም” ነው።
ለድምዳሜ በቂ ባይሆኑም ከዚህ አጠራር በቀላሉ ሙሀመድ ቃሉን ከግዕዝ ሰዎች እንዳገኘው መንገዱን ያሳያል።
እብራይስጥና ግዕዝ ተቀራራቢ በመሆናቸው ምክንያት አጋጣሚውን በመጥለፍ አንዳንድ ታሪክን ለመሠሪ ዓላማ
ለመጠቀም የተነሱ ምዕራባውያን እና አይሁድ ነን ባዮች ሙሀመድ የእስልምና እምነትን መሠረተ ሃሳብ ያገኘው
ከአይሁዶች ነው ለማለት ይቃጣቸዋል። ነገር ግን ሙሀመድ ሃሳቡን ከአይሁዶች እንዳላገኘው ብዙ ማስረጃወችና
አመልካቾች አሉ። በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሱስ ክርስቶስ አያምኑም። ስሙንም አይጠሩም። እንኳን አምላክ ነቢይ
ነውም አይሉም። ቅድስት ድንግል ማርያምንም በእምነታቸው አያውቋትም። በተጨማሪ “ኤልያስ” የሚለውን
መጠሪያ እስላሞች የሚጠሩት እንደ ግዕዙ “ኤልያስ” ብለው እንጂ እንደ እብራይስጡ “ኤልያሁ” ብለው
አይደለም። በተለይም ደግሞ የእስላሞች ቁርአን መጠሪያው “መጽሐፍ” ተብሎ ነው። “መጽሐፍ” የዐረብኛ ቃል
አይደለም ከግዕዝ ውጭ በሌላ ቋንቋ ውስጥም አይገኝም። እስልምና ይህን ቃል የወሰደው ከግዕዝ ነው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ አዲሱን እምነቱን እንዳያስፋፋ በመካና በመዲና ተቃውሞ ሲያጋጥመውና በዳሩል ናድዋ
የተሰበሰቡት የቁሬሺ ጎሳ ባላንጣዎቹ ተከታዮቹን ሊገድሉ ሲያሳድዷቸው ፥ ሙሀመድ ለተከታዮቹ፣ “ፍትህን
ሳያጓድል የሚያስተዳድር ደግ ንጉሥ በእውነት ምድር በሐበሻ አገር ይገኛልና ወደ እርሱ ሂዱ። ያስጠጋችኋል።”5
አላቸው። ተከታዮቹም ወደ አክሱም ተሰደዱ። ንጉሠ ነገሥቱም ተቀብለው አስትናገዷቸው። እዚህ ላይ ትኩረት
የሚያስፈልገው “የሐበሻው” ንጉሥ ደግ መሆናቸውን ማን ነገረው? ፍትሕን ሳያጓድሉ የሚፈርዱ መሆናቸውንስ
እንዴት አወቀ? የሚለው ጥያቄ ነው። ከአይሁድ ወይም ከግሪክ ወይም ከፋርስ ወደ ዐረብ አገር የሚመጡ ሰዎች ስለ
“የሐበሻ” ንጉሥ ደግነት ሊነግሩት አይችሉም። ስለ ኢትዮጵያ ንጉሥ ደግነት ለሙሀመድ ሊነግሩ የሚችሉት
ከኢትዮጵያ ወደ ዐረቦች ሠፈር የሄዱ ኢትዮጵያዊ የክርስትና ተከታዮች ወይም የወንጌል መምህራን ናቸው።
እንግዲህ እነዚህ መረጃዎች የሚያሳዩት ሙሀመድ እስልምናን ለወገኖቹ ለመስበክ መነሻ የሚሆነውን ትምህርት
ያገኘው ከኢትዮጵያውያን መሆኑን ነው።
2
የሙሀመድ ተከታዮች አክሱም እንደደረሱ መልካም መስተንግዶ እንደተደረገላቸው የዐረብ ተራኪዎች
እራሳቸው ዘወትር ይመሰክራሉ። በተለይም ደግሞ ቁሬሺ የሚባሉት የሙሀመድ ተቃዋሚዎች አክሱም ድረስ
ለንጉሠ ነገሥቱ እጅ መንሻ ይዘው በመምጣት በሽሽት የመጡት የሙሀመድ ተከታዮች ወንጀለኞች ናቸውና
ስጡን፣ ወደ ዐረብ አገር መልሰን እንውሰዳቸው ብለው ሲጠይቋቸው ንጉሠ ነገሥቱ የሁለቱንም ወገን ቃል ካዳመጡ
በኋላ ስደተኞቹን አሳልፌ አልሰጥም ማለታቸው እስካሁን ይነገራል። እነዚህ የሙሀመድ ተከታዮች የሆኑ ስደተኞች
ወደ ዐረቦች አገር ቢመለሱ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ያዩት ነጉሠ ነገሥቱ ስደተኞቹ በሂመራ (የመን) እንዲሠፍሩና
እንዲኖሩ ፈቀዱላቸው። አሁንም እዚህ ላይ ከላይ የተጠቀሱት ነዳጅ ፈላጊ ሃሰተኛ ምዕራባዊ ተራኪዎችና አይሁድ
ነን ባዮች ከእስልምና በፊት የመንን ፋርሶች አጥቅተው ይዘዋት ነበር የሚል ሃሰት ይተርካሉ። ከነሱ የሃሰት ትረካ ሌላ
እነሱ ለሚሉት ነገር ጭብጥ ማስረጃ የለም። የመን የኢትዮጵያውያን ምድር እንደነበረችና በውስጧም
ከኢትዮጵያውያን በቀር ዐረብ የሚባል ጎሳ እንዳልነበረባት፣ ዐረብኛ ቋንቋም እንዳልትነገረባት፤ ይልቁንስ የሂመራ
ሰዎች የሚናገሩት ቋንቋ፣ የሚጽፉትም ጽሁፍ ግዕዝ እንደነበረ፣ ባህላቸውም “የሐበሻ” እንደነበረ የሚያረጋግጡ
በጣም በርካታ ማስረጃዎች አሉ። የሙሀመድ ተከታዮች በኢትዮጵያ ከተሰደዱ በኋላ ጊዜው ሲረጋጋ አንዳንዶቹ
እየተመለሱ እስልምናን አስፋፉ። ከሞት አፋፍ ላይ ደርሶ የነበረው እስልምና በኢትዮጵያው ንጉሥ ደግነት ምክንያት
እንደገና አንሰራራ።
እንግዲህ ይህን የመሰለ መስተንግዶ የተደረገላቸው ዐረቦች ግን እስልምናቸውን ሲያስፋፉም ሆነ ሲገድሉ፣ በመሬት
ንጥቂያም ላይ ሲሰማሩ ርኅራኄ ያደረገችላቸውን ኢትዮጵያ በርኅራኄ ዐይን አይተዋት አያውቁም። ብዙ ዐረቦች
“ኢትዮጵያ ስላስጠጋቻችሁ እሷን አትንኩ” ብሎ ሙሀመድ ተናግሯል ሲሉ ይደመጣሉ። ይሁንና ከእስልምና በኋላ
ዐረቦች ኢትዮጵያን ሳይነኩ የሰነበቱበት ዘመን የለም። ከእስልምና ማንሰራራት በኋላ ኢትዮጵያ በእስልምና
የደረሰባትን ውድቀት ሲመለከቱ ንጉሠ ነገሥቱ ለነዛ ለተሰደዱ ዐረቦች ያደረጉላቸው መስተንግዶ ከደግነትም አልፎ
የየዋህነት እንደነበር አዙሮ ለሚያይ ሁሉ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ንጉሠ ነገሥቱ እጃቸውን ዘርግተው ዐረቦቹን
መቀበላቸው ለኢትዮጵያ ተናዳፊ እባብን እጅ ዘርግቶ እንደመቀበል ነው የሆነባት።
የመንን ወሰዱ። ኢትዮጵያውያንን አረዱ። የቀሩትንም መንገድ ላይ ጣሏቸው።
ከተደረገላቸው ከዚህ ሁሉ ቸርነት በኋላ ዐረቦች እስላምናን
ለማስፋፋትና የሌሎችን መሬቶች ለመንጠቅ ሲሰማሩ የመጀመሪያ ሰለባ
ያደረጉት የኢትዮጵያን አውራጃ ሂመራን (የመንን) መውረርና የራሳቸው
ማድረግ ነበር። ዐረቦች በሂመራ ኢትዮጵያውያን ላይ የሠሩት ግፍ
ምዕራባውያን አፍሪካውያንን በባርነት ቀንበር ከገዙበት ግፍ ቢበልጥ
እንጂ አያንስም። ዓረቦች ሂመራን (የመንን) ሲወሩ መጀመሪያ በሰንዓ
የሚገኘውን እጅግ የተዋበውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ህንፃ
ቤተክርስቲያን ነበር ያፈረሱት። ክርስቲያኖችንም አረዱ። የቀሩትን
ኢትዮጵያውያን አስገድደው አሰለሟቸው። በባርነትም ገዟቸው።
የመንንም አጥለቀለቋት። እጅግ የሚዘገንኑ ግፎችንም በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጸሙባቸው። ልጆቻቸው
ታሪካቸውን እንዳያውቁ አደነቆሯቸው። የሚበሉት፣ የሚጠጡትና የሚለብሱትም አሳጧቸው። አክሃዳም
(ጠራጊወች) የሚል ስምም አወጡላቸው። አክሃዳሞች ከሽንት መጥረግና ከጫማ ማጽዳት ውጭ ሌላ ሥራ
አይፈቀድላቸውም፡፤ ልጆቻቸውም አይማሩም። ዐረቦች “እቃህን ውሻ ቢነካው እጠበው፤ አክሃዳም ከነካው ግን
ጣለው”¶ የሚል ፈሊጥ አወጡላቸው። ዐረቦች አክሃዳም እያሉ የሚጠሯቸውን ሥራና ትምህርት ብቻ ሳይሆን
የከለከሏቸው ሰው መሆንን ጭምር ነው።
ከየመን ወረራ በኋላ ዐረቦች እስልምናን በማንገብ የሌሎች ሰዎችን
መሬቶች ለመንጠቅ ወደ ሰሜን አፍሪካ፣ ወደ መካከለኛው
ምስራቅና ወደ ፋርስ ዘመቱ። የተከላከሏቸውን በጎራዴ እያረዱ
ገደሉ፣ የቀሩትን እስላም አደረጓቸው፣ መሬታቸውንም ሁሉ
ወሰዱ። በተለይ ጥቁሮችን በማጥፋት ከሲሶ በላይ የሚሆነውን
የአፍሪካ መልክዓ ምድር በንጥቂያ ወሰዱ። ኢትዮጵያን በዙሪያዋ
ከበቧት። በግድም በውድም ብዙ ኢትዮጵያውያንን አሰለሙ። በዳር ድንበርም በማህል አገርም ያሉ
ኢትዮጵያውያንን ካሰለሙም በኋላ የክርስቲያን መንግሥት ስለሆነ ለመካከለኛው መንግሥት አትገዙ፣
ጎጦቻችሁንም ከመካከለኛው መንግሥት ገንጥሉ የሚሉ ፋትዋዎችን በመደንገግ ሙስሊም የሆኑትን
3
ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ላይ ለጦርነት በማነሳሳት ኢትዮጵያን በአመጽ ለብዙ መቶ ዓመታት አስጨነቁ።
የባህር በሮቿንም ያዙ።
ዐረቦች ቆስጠንጥኒያ ተብሎ የሚጠራውን አገር በንጥቂያ ከወሰዱ በኋላ ኦስማንየ የሚባል የቱርክ የእስልምና
መንግሥት ተቋቁሞ እሱም በመስፋፋትና እስልምናን በማስፋፋት ብዙ የዓለም ክፍሎችን ይቆጣጠር ጀመር።
ኦስማንየ የተባለው የእስልምና ቀንበር ጫኝ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን መሣሪያ
በማስታጠቅ ኢትዮጵያን ለብዙ አመታት በአመጽና በጦርነት አደቀቁ። በተለይም አህመድ ግራኝ በመባል
የሚታወቀውን ሙስሊም በማስታጠቅ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ በጦርነት አመሷት።
አብያተ ከርስቲያናትን አወደሙ። ቅዱሳን መጻሕፍትን አቃጠሉ። ካህናትን እና ምእመናንን አረዱ። የኢትዮጵያ
ንጉሠ ነገሥት የዐረብ ስደተኞችን ካስተናገዱ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በችግር፣ በጦርነትና በሰላም ማሳጣት
ዐረቦች እንዳመጡት እስልምና ኢትዮጵያን ያዎካት የለም። የዐረቦች እስልምና አዋኪነቱ በማበጣበጥ ብቻ የተገታ
አይደለም። ታሪክንም በመበረዝ ጭምር ነው።
በተለይ ባለፉት ሃምሳ አመታት በዐረባዊው በግብጽ መንግሥትና ካይሮ በሚገኘው የዓለም ሙስሊሞች
እንዲከተሉት የእስልምና መመሪያ ወይም ፋትዋ ማፍለቂያ ማእከል በሆነው በአል አዛር ተቋም አበረታችነት
በኢትዮጵያ የተኪያሄዱት ሁከቶች ኢትዮጵያን ትልቅ አደጋ ላይ የጣሉ ነበሩ። ይህ የዐረቦች የአመጽ ጥንስስ
በኢትዮጵያ ብዙ ደም ካፈሰሰ በኋላ “ኤርትራ” ተብላ የምትጠራውን የኢትዮጵያ አካል ከነነዋሪዎቿ ከኢትዮጵያ
ገንጥሏል። በእስልምና ስም የሚመጣው የዐረቦች የብጥብጥ እርሾ በማሀል አገር፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ
ኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ ወዘተ እስካሁን ድረስ ጥፋቱን እንደቀጠለ ነው።
ዐረቦች እስልምናን ተጠቅመው በሚፈጥሩት ሁከት ምክንያት ኢትዮጵያ በመታመሷና ድህነትም ላይ በመውደቋ
በተለይ ባለፉት አርባ አመታት ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ኢትዮጵያን ትተው በመሰደድ በተለያዩ
የዓለም አገሮች ተበታትነዋል። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ወደ ዐረቦች አገር ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ተሰድደው በዛ እስከ
አሁን ይኖራሉ። ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም በታህሳስ ወር &frac12; ዓ.ም. ሰላሳ አምስት የሚሆኑ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን የክርስቶስን ልደት በቤታቸው ተሰብስበው ስላከበሩ የሳዑዲ ዐረቢያ መንግሥት
እነዚህን ክርስቲያኖች በእሥራትና በድብደባ ካንገላታቸው በኋላ ክሳዑዲ ዐረቢያ አባሯቸዋል።6 ዐረቦች
የመጀመሪያው ሂጅራ እያሉ በሚያስታውሱት ስደታቸው ከዐረብ አገር ተሰድደው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው
ኢትዮጵያውያን ላደረጉላቸው አቀባበል፣ የተሰደዱትንም ችግር እንዳያገኛቸው በኢትዮጵያ እንዲኖሩ መልካም
መኖሪያ ለሰጧቸው ኢትዮጵያውያን የከፈሉት ውለታ እነሆ ኢትዮጵያውያን በዐረቢያ በተሰደዱ ጊዜ ዱላ፣
እሥራትና ካገር ማባረር ሆነ። ዛሬም እንደትናንትናው ዐረቦች
ኢትዮጵያውያንን የማጥቃትና የማዋረድ ሥራቸውን
ቀጥለውበታል። በተለይ ሰሞኑን በሳዑዲ ዐረቢያ
ኢትዮጵያውያንን እያሳደዱ በመያዝ እየደበደቡ አጉረዋቸዋል።
አንዳንዶችንም ገድለዋቸዋል። ኢትዮጵያውያን ሴቶችን
ከቤታቸው እያወጡ አስራ አምስት እና ሃያ እየሆኑ ሰብአዊነት
በሌለው ሰይጣናዊ ሁኔታ ደፍረዋቸዋል። ከቤታቸውም
ከተሰደዱበትም ቦታ እያወጡ ጥለዋቸዋል። የርኅራኄ መስተንግዶ
የተደረገላት ቄዳር ግፍን መለሰች። በቄዳር ድንኳኖች ውስጥ
ያላችሁት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያውያን
ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ተመልከቱ። ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍስ ብዙ ጌዜ ኖረች። ኢትዮጵያ ማረፊያ ሰጥታ
ሰላምን ለቄዳር ልጆች ሰጠች፣ የቄዳር ልጆች ግን ስላምን ነሷት። መኖርያቸው ለራቀ፣ በቄዳር ድንኳኖች ላደሩ
ወዮ፥ እግዚአብሔር ተናግሯልና እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋልና።
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
1 Muller, Herbert J.: The Loom of History, 1958
2 Grunebaum, G. E.: Classical Islam – A History 600-1258 – 1970
3 Margoliouth, D.S.: Mohammed and the Rise of Islam, 1931
4 Discover True Islam: free-minds.org
5 Safieddine, Shahnaze: Migration to Abyssinia & Wikipedia, the free encyclopedia
6 Nazret.com: Saudi Arabia Deports 35 Ethiopian Christians for Praying, August 4, 2012

Image

በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም አጋማሽ በኤርትራ ጎዳና መታየታቸው የተነገረላቸው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአደባባይ እና ከኤርትራ ቴሌቪዥን ዕይታ ውጪ መሆናቸው በአስመራ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የሆነ መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።
የሰንደቅ ጋዜጣ ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለፁት “ከዚህ በፊት ፕሬዝደንቱ ከሚሰቃዩበት የጉበት በሽታ ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ ሕመም ተዳርገዋል። በአሁን ሰዓት በኳታር ሆስፒታል ሕክምና እየወሰዱ ይገኛሉ” ብለዋል።
በአስመራ ከተማ ውስጥ እየተናፈሰ ያለው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከበሽታቸው አገግመው ሀገር ሊያስተዳድሩ ይችላሉ የሚሉ በአንድ ወገን በሌላ ወገን ያሉት ከዚህ በኋላ ፕሬዝደንቱ ሀገር በሚያስተዳድሩበት ቁመና ውስጥ ሊገኙ አይችሉም የሚሉት ይገኙበታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግስት እ.ኤ.አ. በግንቦት 10 ቀን 2013 ወደ ኤርትራ የሚጓዙ የአሜሪካ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያርጉ የሚያሳስብና ከተቻለ ወደ ኤርትራ ጉዞ እንዳያደርጉ የሚመክር የማሳሰቢያ መልዕክት በዚሁ ሳምንት በድጋሚ ለዜጎቹ አስተላልፏል።
“የኤርትራና የአሜሪካ ጥምር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስራቸዋል። ስለታሰሩ ዜጎች ከአሜሪካ መንግስት ማብራሪያ ሲጠየቅም ምላሽ አይሰጥም። አስመራ የሚገኘውም የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ መታሰራቸውን ሰምቶ ማብራሪያ ለአስመራ መንግስት ቢያቀርብም ምላሽ አይሠጥም” ሲል መግለጫው ተቃውሞውን አሰምቷል።
በተለይ እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ የኤርትራ መንግስት በግለሰብ ደረጃ ዜጎቹን አውቶማቲክ መሳሪያ በማስታጠቁ በቀላሉ የአሜሪካ ዜጎች ለአደጋ ተጋላጭ ይሆናሉ ከሚል ስጋት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ታጣቂዎች በአስመራ ከተማ ሚሊሽያ በሚል ስለሚታወቁ ማንኛውንም ሰው በፈለጉት ቦታና ሰዓት መፈተሽ ይችላሉ። በዚህም የተነሳ በአስመራ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻና የሃይማኖት ቦታዎች ለመጎብኘት የሚመጡ የአሜሪካ ዜጎች በእነዚህ ታጣቂዎች ላይ ሊደርስባቸው ከሚችለው ስጋት ለመዳን ከአሜሪካ መንግስት ዕውቅና ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ መግለጫው አሳስቧል።
በኦክቶበር 3 ቀን 2013 በላምባዱሳ ለተሰውት 350 ኤርትራዊያን ማስታወሻ በተደረገ ስነ-ስርዓት በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አካባቢ ኤርትራዊያን በመንግስታቸው ላይ ባሰሙት ቅሬታ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱ የሚታወቅ ነው።፡
የኢሳያስ አፈወርቂ ጤና መሻሻል ካላመጣ በአስመራ ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል የስልጣን ሹኩቻ መነሳቱ አይቀርም ሲሉ የዲፕሎማቲክ ምንጮቻችን ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ገልፀዋል። አያይዘውም፤ ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምም የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት እ.ኤ.አ. 2009 የአስመራ መንግስት በሚከተለው የትርምስ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መነሻነት በኤርትራ መንግስት ላይ ባስተላለፈው ማዕቀብ የተነሳ እስከ ዛሬ ድረስ የአስመራ መገናኛ ብዙሃን በአሜሪካ መንግስት ላይ ከፍተኛ የስም የማጥፋት ፕሮፖጋንዳ እየፈጸመ መሆኑ ይታወቃል።&frac34;

Written by ኤልያስ, AddisAdmassNews.com
“በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ሙሉ በሙሉ ተከብሯል” – የጋዜጠኞች ማህበራት
“በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ለውጥና ማሻሻያ እናደርጋለን” መንግስት
ኢህአዴግ ሌሊት ሌሊት የምረጡኝ ቅስቀሳ እያጧጧፈ ነው!

እንደኔ አላጋጠማችሁ እንደሆነ አላውቅም እንጂ ኢህአዴግ ሌሊት ሌሊት የምርጫ ቅስቀሳ ጀምሯል (ህገ መንግስታዊ መብቱ እኮ ነው!) እኔን የገረመኝ ግን ቅስቀሳው ሳይሆን ቀኑን ትቶ ሌሊትን መምረጡ ነው፡፡ (ቀንማ “ቢዚ” ነው!) ባለፈው ሳምንት ነው፡፡ ሰኞ ወይም ማክሰኞ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሌሊት ላይ እንቅልፍ እምቢ አለኝና ኢቴቪን ከፍቼ ቁጭ አልኩኝ (ብቸኛ “አጫዋቼ” ነው አላልኳችሁም!) ምናልባት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ወይም 10 ሰዓት ገደማ ይሆናል፡፡ ኢቴቪ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ አባላትን የልማት እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ፕሮግራም ማቅረብ ጀመረ፡፡ (“የሴቶች ሊግ” የተሰኘ አዲስ ፕሮግራም ሳይሆን አይቀርም!) በኋላ ሲገባኝ ግን የልማት ሳይሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ነገር ነው፡፡ እኔ የምለው … በህዝብ ንብረት ቅስቀሳ ይቻላል እንዴ? (ኢህአዴግም እኮ የህዝብ ንብረት ነው!) አንድ ጥያቄ ግን አለኝ፡፡ የ2007 ምርጫ ወደ 2006 ተዛወረ እንዴ? ለቀጣዩ ዓመት ምርጫ ዘንድሮ ቅስቀሳ አይጀምርም ብዬ እኮ ነው! እናላችሁ … በኮብልስቶንና በሌሎች “ደሃ-ተኮር” ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሴቶች አስተያየት ሲሰጡ፣ እንደሌላው ጊዜ ስማቸው ወይም የሥራቸው ዓይነት አይደለም ቲቪ ስክሪኑ ላይ የተጠቀሰው፡፡

ለእያንዳንዱ ተናጋሪ “ሊግ አባል” የሚል መግለጫ (Caption) ነው የተሰጠው። (መቼ የተጀመረች ግልፅነት ትሆን?) አንደኛዋ የሊግ አባል፤ ኢህአዴግ ከጓዳ (ማጀት) አውጥቶ ለአደባባይ እንዳበቃት ገለፀች፡፡ እሷም ብትሆን በጥቃቅን ሳትደራጅ በፊት ነው የሊጉ አባል የሆነችው፡፡ (ባለውለታ ናት ማለት ነው!) ቀጠለች-ሴትየዋ፡፡ “ለሴቷ አማራጭ ያለው ፓርቲ ነው” ስትል አውራ ፓርቲውን በደንብ አሞካሸችው (በእሷ ዓይን “ሲያንሰው” እኮ ነው!) ትንሽ ቅር ያለኝ ግን ምን መሰላችሁ? አባል ለመሆን መዘግየቷ ነው። “በ2001 ዓ.ም ነው አባል የሆንኩት” ብላናለች፡፡ (ያን ሁሉ ዓመት የማን አባል ነበረች?) በነገራችሁ ላይ …ከሴቶች ሊግ አባላት ውስጥ 99 በመቶ ያህሉ በሥራ ላይ የተሰማሩ (employed ወይም self employed) ሲሆኑ በቅርቡ አንድም ሥራ አጥ (zero unemployment) የሊግ አባል እንደማትኖር የሊጉ ሊቀመንበር ተናግረዋል፡፡

Image

(ልብ አድርጉ! “አንድም የሊግ አባል” ነው የተባለው!) በነገራችሁ ላይ … ሊጉ የሚመራው “ሰጥቶ መቀበል” (ፈረንጆቹ Give and take ይሉታል) በሚለው መርህ ነው፡፡ በአበሽኛ “እከክልኝ ልከክልህ” የሚባለው መሰለኝ፡፡ እናላችሁ … የሊጉ አባላት በ2002 እና በአካባቢና ማሟያ ምርጫዎች ኢህአዴግን በመምረጥ ብቻ ሳይሆን እንዲመረጥ በመቀስቀስም ለፓርቲያቸው ያላቸውን የማይናወጥ “ታማኝነት” አሳይተዋል ብላለች – የሴቶች ሊግ ሊቀመንበሯ፡፡ (ካላሳዩማ አለቀላቸው!) እኔ የምለው … የሊግ አባል የመሆን ዕድል ላላገኙ የጦቢያ ሴቶች የሥራ ዕድልና ብድር የሚሰጣቸው ማነው? (ጥያቄ እኮ ነው!) እንደው ለጨዋታ ያህል ነው እንጂ… በኢቴቪ በውድቅት ሌሊት የተላለፈው የሴቶች ሊግ የምርጫ ቅስቀሳ ምንም ክፋት የለውም (አሳቻ ሰዓት ከመቅረቡ በቀር!) የሊጉን ቅስቀሳ ኮምኩሜ ልተኛ ስል ግን አንድ ሃሳብ መጣልኝ። “Drink Responsibly” ወይም “በሃላፊነት ስሜት ተጐንጩ” የሚለውን የቢራ ማስታወቂያ ታውቁታላችሁ አይደል? ኢህአዴግን ጨምሮ ሁሉም የጦቢያ ፓርቲዎች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁና ሲቀሰቅሱ “Support Responsibly” ወይም “በሃላፊነት ስሜት ይደግፉ!” የሚል ማስታወቂያ ቢያክሉበት አልኩ-ለራሴ፡፡

(እንዴ … የፖለቲካ የአልኮል መጠን እኮ ከቢራ የአልኮል መጠን በብዙ እጅ ይልቃል፡፡) እኔ የምለው … ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ህብረት የተካሄደውን የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም እንዴት አያችሁት? የአፍሪካ ነገር ሁሌ ችግሯን ሁሉ በፈረንጆቹ ላይ ማላከኳ አናደደኝ እንጂ ጋዜጠኞቹ መወያየታቸውና መወቃቀሳቸው የሚበረታታ ነው። አንድ ቀን ከምዕራባውያን ላይ ወርደው ራሳቸውን መቻላቸው አይቀርማ! የእኔን ትኩረት የበለጠ የሳበው ግን ጉባኤው እንዳይመስላችሁ! በፎረሙ መጠናቀቂያ ላይ ሦስት የጦቢያዋ “የጋዜጠኞች ማህበራት” ያወጡት “ድንቅ” የአቋም መግለጫ ነው። (ሦስቱ ማህበራት ለኢትዮጵያ ብቻ ነው ወይስ ለሶማሊያም?) እናላችሁ … የማህበራቱ መግለጫ የጋዜጠኞች ሳይሆን የ“አብዮታዊ መንግስት” ወይም “ድርጅት” ነበር የሚመስለው፡፡ ከአቋም መግለጫቸው መካከል አንደኛው ደግሞ ከኢህአዴግ ቃል በቃል የተኮረጀ ነው (ኮማ ሳይቀር!) ልዩነቱ ምን መሰላችሁ? ኢህአዴግ በተደጋጋሚ “በኢትዮጵያ ውስጥ ከሙያቸው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞች የሉም” የሚል ምላሽ ሲሰጥ ደንፍቶ አያውቅም። እነሱ ግን ቀላል ቀወጡት! አገር ይያዝልን እኮ ነው ያሉት፡፡ ቦታው ስላልተመቻቸው ነው እንጂ ሽለላና ቀረርቶ ሁሉ ዳድቷቸው ነበር፡፡

(ኢህአዴግ ራሱ እኮ ሳይታዘባቸው አይቀርም!) እኔማ ምነው በገመገመልኝ ብዬ ነበር፡፡ ለካስ የኢህአዴግ አባል አይደሉም (ናቸው እንዴ?) የጋዜጠኞች ማህበራቱ ሁለተኛው የአቋም መግለጫ ደግሞ “በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ከየትኛውም የአፍሪካ አገራት የበለጠ ተከብሯል” የሚል ነው፡፡ ይሄኛውም በድንፋታና በጩኸት የታጀበ ነበር፡፡ ይሄን የሰሙ የአፍሪካ ጋዜጠኞችና የሚዲያ መሪዎች አገራቸው እስከሚገቡ እንዴት እንደሚቸኩሉ አልታያችሁም? (ለመሳቅ እኮ ነው!) እንኳን እነሱ ኢህአዴግም ይሄኔ በመግለጫው ፍርስ ብሏል (አይነግረንም እንጂ!) እውነቴን እኮ ነው … መንግስት ራሱ “በአገራችን የፕሬስ ነፃነት ሙሉ በሙሉ ተከብሯል” ብሎ አያውቅም፡፡ (ከየት አመጡት ታዲያ?) በነገራችሁ ላይ … የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ … መንግስታቸው፤ በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ለውጥና ማሻሻያ እንደሚያደርግ ተናገሩ እንጂ “የፕሬስ ነፃነታችን እንከን የለሽ ነው!” ብለው አልተመፃደቁም፡፡ “ዲሞክራሲውም … ነፃ ፕሬሱም … የሰብአዊ መብት አያያዙም ወደፊት ከልማቱ ጋር እየተሻሻለ ይሄዳል” ነው – የኢህአዴግ አቋም፡፡ (“ከጳጳሱ በላይ አማኝ” አሉ!) የጋዜጠኞች ማህበራቱ ጉዳይ በዚሁ ቢያልቅ “ተመስገን” ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ምሽት ደግሞ “የነፃ ጋዜጠኞች ማህበር” ፕሬዚዳንትና ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ይሄንኑ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያብራሩ ተጋብዘው ነበር – በኢቴቪ፡፡

የሚገርመው ታዲያ የምሽቱ አጀንዳ “በኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞች አሉ የሉም” ወይም “የፕሬስ ነፃነት ተከብሯል አልተከበረም” የሚለው አልነበረም። የአገር ሉዓላዊነት ማስከበር፣ አንድነትና ነፃነትን ማስጠበቅ ወዘተ … ሆነና አረፈው (የአቋም መግለጫ በማውጣት “አርበኝነት” የለም እኮ!) የኢቴቪ ጋዜጠኛው (ጋባዡ ማለት ነው) ታደሰ ሚዛን፤ ለጋዜጠኞች ማህበሩ ፕሬዚዳንት አስገራሚ ጥያቄ አቀረበ (ሃሳቡን እንጂ ቃል በቃል አይደለም!) “በቀጣይ እንደ CPJ ያሉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ነን ባዮች ‘በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ታስረዋል፣ የፕሬስ ነፃነት ታፍኗል’ እያሉ የሚያወጡትን መግለጫ እንዴት መከላከል ይቻላል?” ፕሬዚዳንቱም አስገራሚ ምላሽ ሰጠ፡፡ “ፅናትና መስዋዕትነት ይጠይቃል” በማለት፡፡ የምን ፅናት ነው? የምንስ መስዋዕትነት? እውነቱን መናገር እኮ በቂ ነው – እንደ ኢህአዴግ፡፡ (እውነት አንፃራዊ መሆኗ እንዳይረሳ!) ሁለቱን ጋዜጠኞች ወይም የ “ነፃ ጋዜጠኞች” ተወካዮች በኢቴቪ የጋበዘው ጋዜጠኛ፤ አንድ ነገር ግን ሳይሸወድ አልቀረም፡፡ (“አውቆ በድፍረት ሳያውቅ በስህተት” ሊሆን ይችላል!) ምን መሰላችሁ? የጋዜጠኞች ማህበራት ያወጡትን መግለጫ፣ የአገርን አንድነት (ዳር ድንበር) እንደማስከበር ነው የቆጠረው፡፡

(በአቋም መግለጫ “አንድነት” ተከብሮ አያውቅም እኮ!) እናም … ማህበራቱ ወደፊትም ተመሳሳይ መግለጫ በማውጣት የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ ይጥሩ እንደሆነ ጠየቀ – ወደ ውይይቱ መጠናቀቂያ ላይ፡፡ (ወይ ፍሬን መበጠስ!) መልሱም “ፍሬን የበጠሰ” ስለሆነ ትቼዋለሁ፡፡ አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ሦስቱ የጋዜጠኞች ማህበራት ዓላማ ምንድን ነው? (የጋዜጠኞችን መብት ማስከበር እንዳይሉኝ ብቻ!) “ኢህአዴግ ማረኝ” ማለት ይሄኔ ነው፡፡ (“የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ” አሉ!) እናንተ … እኔም ፖለቲካዊ ወጌን በአቋም መግለጫ ልቋጨው ዳድቶኝ ነበር፡፡ (አንድዬ እኮ ነው ያዳነኝ!) በሉ ሰሞኑን በቴክስት የደረሰኝን “ቧልት” ላካፍላችሁና ልሰናበት፡- “ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ዕቅድ ጉባኤ ላይ የተሳተፈችና የቡራዩን የስነ ተዋልዶ ጤና ኤክስቴንሽን የጐበኘች አንዲት አሜሪካዊት፣ በተለይ ለኢቴቪ በሰጠችው ቃለ ምልልስ፤ ‘ምነው እኔም ኢትዮጵያ ውስጥ በወለድኩ’ ስትል አድናቆቷን ገለፀች” (ማንም ምንም ቢል የምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ እንደሆነ መሳካቱ አይቀርም!!) ድል ለዋልያዎቹ!!

የፊታችን ዕሁድ ፆመ ነቢያት ይጀመራል።የገና ፆምን ለመፆም ተዘጋጅተዎል?ዘንድሮ ፆም ለነፍስ ብቻ ሣይሆን ለስጋም ጠቃሚ እየሆነ ነውና ሀኪም ቀይ አብርቶ በስጋ ምክንያት ሥጋት ላይ መሆንዎን ሣያረዳዎ በንስሃ አባትዎ ምክር ፆሚ ይሁኑ።
ቢፆሙ ሸንቃጣ ይሆናሉ።ስጋዎ ፈተና ላይ አይወድቅም።መንፈስዎ ይረጋጋል።ባይፆሙ ኪሎዎ ይጨምራል።ከሀኪም ፊት አይርቁም።ቁና ቁና ይተነፍሣሉ።ወጪዎ ይጨምራል።አልጋና ብልግና ሊያዘወትሩ ይችላሉ።
ኪስዎ ከመጀመርያው ፆሚ ከሆነ የኔ ምክር እርስዎን አይመለከትምና ዘና ይበሉ።ፆም ሲፆሙ ሆድዎን ብቻ ማዕቀብ አይጣሉበት። ምላስዎን አደብ አስገዟት።ዓይንዎን ከዳሌና ጭን ላይ ይንቀሉ።ጆሮዎ የአመት ረፍት ያስወጡት።እግርዎ አይንጦልጦል።ያኔ የወጣልዎ ምርጥ ፆሚ ይሆናሉ።አንድ ነገር ረሣሁ።በልብዎ ግርግዳ ያከማቹትን የቂምና የጥላቻ ዶሴ ፈጥነው ይደልዙ።ልብዎ በቂም ኔትወርክ ተጨናንቆ ወደ ፈጣሪዎ የሚያደርጉት ማንኛውም ጥሪ አይሠማምና ውዝፍ ሂሣብዎን ያወራርዱ።ያኔ የገናን ፆም ለመፆም ሚኒማውን ያሟላሉ።
ዕሁድ ጧት ቸርች ሲመጡ ልብስዎ ብቻ ሣይሆን ልብዎም ፀዳ ብሎ ይምጣ።እኔ እንዲህ ብያለሁ ።እርስዎስ??
አክሊለ ሠማያት ዘ መካነ ሠላም

ምንሊክ ሳልሳዊ :- ይህ በአለም ላይ የማይካድ እውነት ነው:: ምንም ከሃገሩ ካለምክንያት አይሰደድም የአንድን ሃገር ድንበርም ጥሶ ካለምክንያት አይዘልቅም:: ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ወደ አረብ አገራት ገብተዋል:: የይልፍ ወረቀት ገዝተው በአየር የወጡትን ጉዳይ ለጊዜው ተወት እናድርገው እና በዛሬው ወቅት ህገወጥ እየተባሉ በአረቦቹ እና በስርኣቱ መሪዎች ስለሚወነጀሉት ኢትዮጵያውያን አጠር ያለ ነገር እናንብብ::

ወደ አረብ አገራት የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን በሁለት ይከፈላሉ እነዚህ ስደተኞች አብዛኛዎቹ በባህር አቋርጠው እና አስቸጋሪ ፈተናዎችን አልፈው በሰላም ወደ ፈለጉበት የደረሱ የሸሹ የተደበቁ እጅግ አሳዛኝ ዜጎች ናቸው:: በሁለት ከፍለን ስናያቸው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስደተኞች ብለን እናስቀምጣቸዋለን :; እነዚህ የሁለት ፈርቅ ስደተኞች በጅቡቲ እና በሱማሌላንድ ወደቦች በጀልባዎች ተጭነው የተረፈ ተርፎ የገባ ገብቶ አሁን ላሉበት ሁኔታ ደርሰዋል::እስኪ ከፍለን እንመልከታቸው::

የፖለቲካ ስደተኞች
እንዚ የፖለቲካ ስደተኞች በብዛት የተሰደዱት ከኦሮሚያ ክልል ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች በተለያየ ጊዜ የእነግ አባላት ናችሁ የኦነግ ጦር ረዳቶች ናችሁ ኦነግን ትደግፋላችሁ በሚል የተለያዩ ችግሮች እና መከራዎች ሲደርሱባቸው ድብደባ እና እስር ሲፈጸምባቸው ይህንን በመሸሽ እንዲሁም የቤተሰቦቻቸውን እና የራሳቸውን የእርሻ መሬት ሲነጠቁ የስራ እድላቸው በፖለቲካ እምነታቸው ሲጋረድባቸው ስርኣቱ በፈጠረው የፖለቲካ ጫና ቤተሰብ ማስተዳደር ሲሳናቸው ወደ የመን ሳኡድ አረቢያ ደቡብ አፍሪካ እና የተለያዩ አገሮች በምድር ጉዞ ይሰደዳሉ:; እንዲሁም ሴት ልጆች በቤተሰባቸው ላይ ፖለቲካው የፈጠረን ጫና ለማሸነፍ ሲሉ እንዲሁ ይሰደዳል:: እንዚህ የፖለቲካ ስደተኞች ራሳቸውን ለማሸነፍ ሲፍጨረጨሩ ህገወጥ ወይንም ወንጀለኛ አድርጎ ማየት ሃላፊነት የጎደለው አስተሳሰብ ነው::

የኢኮኖሚ ስደተኞች
በሃገሪቱ የተንሰራፋው የዘረኝነት ጁንታ አብዛኛው ህብረተሰብ እንዳይሰራ ግሬጣ ከመሆኑም በላይ የፖለቲካው አናት የንግድ ድርጅቶቹን በማስፋፋት በሃገሪቱ አንጡረ ሃብት እየተጫወታ ዜጎችን ለድህነት አገሪቱንም ለድቀት ዳርጓል::የሃገሪቱ የትምህርት ጥራት ትውልድ እንዳያፈራ ተደርጎ አመድ ከተለወሰ በኋላ የስራ አጥ ቁጥሩ በእጥፍ ጨምሯል:: የምእራባውያኑ የገንዘብ ተቋማት የአፍሪካን እድገት ስለማይፈልጉ አምባገነንነትን በማበረታታት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ይነዛሉ::እንዲሁም እንደ ቻይና የመሳሰሉት አገራት ከቀን ሰራተኛ ጀምሮ በተለያዩ ለውጪ ዜጎች በማይፈቀድ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው የአገሪቱን ወጣት በስራ አጥነት እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ አድርገውታል:: ይህ አይነቱ መንግስት ባለስልጣናት ነጋዴነት ሙሰኝነት የውጪ ዜጎች ካለደረጃቸው ዝቅ ብለው የሚበጠብጡት የስራ እድል አሻሚነት ተደማምሮ በአመት ከ 800.000 በላይ ስራ አጥ ስለሚፈጠር የስደት መንስኤ ሊሆን ችሏል::ወደ አረብ አገራትም የሚሰደዱ ዜጎች የዚህ እና የተያያዥ የኢኮኖሚ ችግሮች ሰለባ ከመሆናቸውም በላይ ይህ ደግሞ የስርኣቱ ለዜጎች የኑሮ እድገት ግዴለሽነት ያመለክታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብሄራዊ እፍረት መንስኤ የሆነው ስርኣት በሚከተለው የፖለቲካ እና የእኮኖሚ ፖሊሲ ምክንያት ዜጎች አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እና ለሞት ለእስር ለስቃይ እና ለመንገላታት እንዲዳረጉ ሚናውን ተጫውቷል:: ይህንን መፍትሄ ለማምጣት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገናል በጋራ አገር ላይ በጋር እንድንሰራ እኛ እናውቅላቹዋለን የሚል ስርኣት ከነአካቴው ሊቆም እና ሃይ ሊባል ይገባዋል: ኢትዮጵያውያን በአረብ አገራት እየደረሰ ያለው መከራ የምን ውጤት ነው መፍትሄውስ ምንድነው ብለን ቆም ብለን የምናስብበት ጊዜ ነው:: ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ስርኣቱ አሁንም ካለው እኩይ አድራጎቱ ሊቆጠብ ስለማይችል ነገ በሌላም አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን ችግሮች ቢደርሱብን የገዛ ዜጎቼ ሳይሆን የሚለው አብሮ ህገወጥ እና ወንጀለኛ ብሎ በመፈረጅ ለሞት እና ለስቃይ ከመዳለግ ወደኋላ ስለማይል የትግል አድማሳችንን በማስፋት ወንጀለኛው ህገወጡ በሃገሪቱ የተንሰራፋው ስርኣት መሆኑን የማጋለጥ ግዴታ አለብን;;ጎን ለጎንም የመፍትሄ ሰዎች እየሆንን ባለው ስርኣት ላይ ጫና በማሳደር መትጋት ድርሻችን ነው::

Image

ምነው ሰቆቃችን በዛ?
ሐገር እንደሌለው በዋዛ።
ለውጡ ሆኖብን ከድጡ ወደማጡ
ስንቶች ሐገራቸውን ጥለው ወጡ?
ብልሹ አገዛዝ ነግሶብን
ኢትዮጵያዊያን ተዋረድን።
ያዋረድን ግን ወያኔ ነው
ዓይን እያለሁ የማያየው
ጆሮ እያለው የማይሰማው።
ሴቶቻችን ሲደፈሩ ክብራችን ሲንኮታኮት
ኢቲቪ የወያኔ የውሸት ቋት።
አንቺ ያልታደልሽ ሐገር
አኬልዳማ የደም ምድር።
አምላክ ሆይ እንባችንን አብስና
ገላግለን ከዚህ ዘመን ፍጠንና
ሐገር እያለን እንደሌለን
በጣም እናሣዝናለን።
በርጉማን እየተመራን እስከመቼ
በሣውዲ እያለቁ ወገኖቼ
ዱሮ ግንደበረት የቀረው
ሣውዲ ላይ ባርነታችን የነገሠው
በወያኔ የተነሣ ነው።
ለአፍሪካ የምትተርፍ ሐገር
እንዲህ ሆና ስትቀር?
ጌታ ሆይ ገላግለን ከእዬዬ
መሪ ስጠንና እንደ እምዬ።
*በሣውዲ መከራ ላይ ለወደቁ ወገኖቼ መታሠቢያ
18/11/2013
penethiopian

በዩጋንዳ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ!!!
በሳውዲ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ በማውገዝ የሳውዲ መንግስት ለዓለም አቀፉ የሠብዓዊ መብቶች መከበር የፈረመውን ስምምነት እንዲያከብርና ዜጎቻችን ላይ እያደረሠ ያለውን ኢሞራላዊ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያቆምና ለሠው ልጆች ሰብዓዊነት እንዲያሳይ ለመጠየቅና በቀጣይ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን የስደተኞች ሁኔታ ለመምከር የወገኖቻችን መከራና ስቃይ ነግ በኔ ሊሆን ይችላል ብሎ በማሠብ በአንድነት ሆነን ለመምከር አንዳንድ ቅድመ ዝግጅቶች ለማድረግ ከጎናችን እንዲቆሙ እንጠይቃለን።
ቀጣይ እንቅስቃሴያችንን በ<efjaehrco>ፌስ ቡክ ላይ ማስታወቅያችንን ይከታተሉ።
በህዝባዊ ተቃውሞ ለመሣተፍ በ<[email protected]>ይመዝገቡ።
በዩጋንዳ ነግ በኔ የወገን ለወገን ደራሽ የጋራ ድምፅ አስተባባሪ ኮሚቴ
[email protected]>

ኢትዮጵያዊ ባልሆነ መንግስት መገዛት ይብቃን! ጌታቸው ሽፈራው

አንድ የኢህአዴግ ታጋይ አሊያም ሲቪል ካድሬ ሲሞት በቴሊቪዥን ሳይቀር ይለፈፍለታል፡፡ በሳውዲ እየሞቱ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ግን አንድም ነገር አልተደረገም፡፡ ሌላው ይቅርና መሰሎቹ አጭበርብረው ‹‹ምርጫ አሸነፍን›› ሲሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለማጉረፍ ማንም የማይቀድማቸው እነ ኃ/ማሪያም አሁን ምንም አላሉም፡፡ በተቃራኒው ድምጽ ለማሰማት የወጡትን በጨካኝ ፖሊሶቻቸው አስደበደቡ፡፡

ወደ ጣሊያን ሲያቀኑ ያለቁት የአፍሪካ ስደተኞችን ሞት አስመልክቶ ሰንደቅ አላማው ዝቅ ብሎ ተውለብልቧል፡፡ የኢትዪጵያውያንን ነፍስ ምን ያህል አርክሰው ቢያዩት ነው? ለአንድ ቀን ሀዘን፣ ለአንድ ቀን ሰንደቅ አላማውን ዝቅ ለማድረግ አልፈቀዱም፡፡ ስለዛ አምባገነን መሪያቸው ግን ሁሌም ይቆዝሙብናል፣ ይለምኑብናልም፡፡ ኢትዮጵያን እንደነጠቁን ሰላማዊ ሰልፉን በመከልከል ዳግመኛ አረጋግጠውልናል፡፡ በተቃራኒው ከኤስያ፣ እስከ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ የእኛዎቹ ወገኖች እንደልባቸው ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው፡፡

እንዲያውም ድጋፍ እየተደረገላቸው፡፡ ትናትና ፌስ ቡክ ላይ እንዳነበብኩት አንድ የአውሮፓ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ የድምጽ ማጉያ የመሳሰሉ መሳሪያዎች ከሌሏቸው ማዘጋጃ ቤቱ ሊያውሳቸው እንደሚችል አረጋግጦላቸዋል፡፡ እንደ ሳውዲ ካሉት ውጭ ለኢትዮጵያውያን አገራቸው ካለው ይልቅ የተሰደዱበት መንግስታት ደግና ርሁሩሆች ናቸው፡፡ ለእኔ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊ ላለመሆኑ ከዚህ ውጭ አስረጅ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ የግድ እንደ ግራዚያኒ በየ ቤታችን ገብቶ በቆጨራ እስኪቆርጠን መጠበቅ የለብንም፡፡ ካድሬ ሆነ ተቃዋሚ፣ አማራ ሆነ ኦሮሞ፣ ትግሬ ሆነ ወላይታ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን እስካለሰበ ድረስ ከስቃዩ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ መለስ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ኢህአዴግ ገንዘብ ሲያሰባስብ የነበረው እንደ ሳውዲ ባሉ አገራት ከሚገኙት ዜጎቻችን ጭምር ነው፡፡ የልመና ጊዜ በሮ የደረሰው የውጭ ጉዳይ አሁን በቲውተር ከሚቀልደው ያለፈ ሊፈይድ አልቻለም፡፡ ካድሬም ብትሆን አይቀርልህም፡፡

Image
በጊዜያዊ ጥቅም ከሆነማ ጣሊያንም ለባንዳዎቹ ከፍተኛ ጥቅም ሰጥታለችኮ፡፡ እነ ራስ ሀይሉ በወር 175 ሺህ ሊሬ ይከፈላቸው ነበር፡፡ የፋሽስቱን ስርዓት ያልተቃወመ ወጣት አሁን ኢህአዴግ ከሚያደርገው በላይ ተከፍሎታል፡፡ እናቶች፣ ካድሬ ቄሶችና ሌሎችም ኢህአዴግ አሁን ከሚያደርግላቸው በላይ ጣሊያንን እንዳይቃወሙ ጥቅማጥቅም ተሰጥቷቸዋል፡፡ በኋላ ግን በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡ እናም ይህን ኢትዮጵያውይ ያልሆነ መንግስት ኢትዮጵያዊ ማድረግ አይቻልም፡፡ በቃ! ከዚህ በላይ በደል መሸከም አንችልም፡፡ ከዚህ በላይ ባይተዋር መሆን አንፈልግም፡፡ ከዚህ በላይ ማንባት አንሻም፡፡ ኢህአዴግን በግልጽ በቃህ የምልበት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ አዎ! ኢትዮጵያዊ ባልሆነ መንግስት መገዛት ይብቃን! Getachew Shiferaw.

Image
Ethiopian migrants sleep out in the open near a transit centre where they wait to be repatriated in the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia, (REUTERS/Khaled Abdullah) dailystar.com
********************************************************************************************************************

በአብዛኛው የኢህአዴግ ድርጅቶችን ብቻ በማሳተፍ የምዝገባ ዘመቻው ቀጥሏል
ዛሬ መልካም ዜናን ከሪያድ መጠለያዎች ሰማሁ !
* 66 በሚደርሱት መጠለያ የሚገኙት ኢትዮጵያን ይዞታ መሻሻል ጀምሯል
* የምግብ የውሃና የህክምና አገልግሎቱ ሽፋን አበረታች ነው ፣ አቅርቦቱ ሙሉ በሙሉ በሳውዲ መንግስት የሚሸፈን ነው
* ለህጻናትና ለአቅመ ደካማ ሴቶች ትኩረት እየተሰጠ ነው
* የተሻለ መጠለያ ለማስተላለፍ የተደረጉ ሙከራዎች በተጠላዮች ፍርሃቻ ከሽፈዋል
* ተጠላዩ ግን ፍርሃት አለበት ፣ ከመጠለያው ውጭ ያሉ ዜጎች በሚሰጡት ነዋሪው ሊያረጋገው አልቻለም

የጅዳው አስጊ ሁኔታና የቆንስል መስሪያ ቤቱ የሽሜሲ ዘመቻ፡-

* የጅዳ ቆንስል ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቷል
* የመረጃ እጥረት አሁንም አለ
* በጅዳ አንዳንድ አካባቢዎች ህገ ወጥ ወገኖች በመረጃ እጥረት ወደ ሁከት እንዳይሸጋገሩ ያሰጋል
* መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ነዋሪዎች እንዲታገሱ ህጋዊ ነዋሪዎች እየተማጸኑ ነው
* የቆንስላው ሃላፊዎች ትኩረት ወደ ሽሜሲ ጊዜታዊ እስር ቤት ሆኗል
* በአብዛኛው የኢህአዴግ ድርጅቶችን ብቻ በማሳተፍ የምዝገባ ዘመቻው ቀጥሏል
* በቆንስሉ መዘጋት ብዙዎችን አስቆጥቷል ” የታመመ ቢሞት እንደጰት እንቅበር? ፖስፖር ቢታደስ ማስተካከል ቢያስፈልግ ምን እናድርግ? የጋብቻ ወረቀት ማረጋገጫና እና ተመሳሳይ ግልጋሎት ስንፈልግ የት እንሂድ? ” ሲሉ በማጠየቅ በአስቸኳይ ቆንስሉ እንዲከፈት ነዋሪዎች መንግስትን ተማጽነዋል

* የሰው ሃይል እጥረት አለ፣ ሶስት ኢኒስፔክተሮች ከሃገር ቤት ጅዳ ገብተው ስራቸውን ጀምረዋል
* በጎ እናድርግ የሚሉ ነዋሪዎች ተበራክተዋል ፣ የቆንስሉን መልስ እየጠበቁ ነው

Image

በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው መከራ መስማት ህሊና መሸከም ከሚችለው በላይ ሆኗል። ኢትዮጵያዊን እህቶቻችን ወንድሞቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ፤ አካሎቻቸው በስለት እየተቆራረጠ፤ እየተደበደቡና እየተደፈሩ ነው።

ይህ ሁሉ የሚፈፀው በሪያድ፣ ጂዳና አዲስ አበባ የሚገኙ የወያኔ ዲፕሎማቶች መልካም ፈቃድና ሙሉ ተባባሪነት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ የሚያንገበግብ ነው። ወያኔ ለአረብ ሀብታም ሸሪኮቹ ለም መሬቶቻችንን ሰጥቶ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ሠርቶ የእለት ጉርሱን መሸፈን የማይችልበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ አደረገው። ቀጥሎ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጃገረዶችና ወጣት ኢትዮጵያንን እየደለለ ከባርነት ላልተሻለ ግርድና አሳልፎ ሰጣቸው። ይህ ሁሉ ግፍ አልበቃ ብሎ “በሏቸው፤ ቀጥቅጧቸው፤ ህገወጦች ናቸው” እያለ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ በአጋፋሪነት እያስተናገደ ነው።

በኩየት በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ ተመሳሳይ ሰቆቃ ሊደርስ የሚችል መሆኑ ምልክቶች እየታዩ ነው። በኩዌት ያለአንዳች ምክንያት ቁጥራቸው በአንድ ሺህ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በድንገት ከሥራ ተባረዋል። እዚህም የወያኔ እኩይ እጆች እንዳሉት መረጃዎች አሉ። በሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ሕይወታቸው በዘወትር ስጋት ላይ ወድቋል።

የኢትዮጵያዊያን እጣ ፈንታ በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ሰቆቃና እንግልት መሆኑ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስቆጭ፤ ለመራራ ትግል የሚያነሳሳም ነው። ለአገሩ ሕዝብ የሚቆረቆር መንግሥት ኑሮን ቢሆን ኖሮ ሕይታችን እንዲህ የተመሰቃቀሰ ባልሆነም ነበር።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም የመካከለኛ ምሥራቅ አገራት መንግሥታት ለኢትዮጵያዊያን እህቶቻንና ወንድሞቻችን ሰብዓዊ ክብር እንዲሰጡ አበክረን እናሳስባለን። ሰብዓዊ መብቶችን መድፈር ዓለም ዓቀፍ ወንጀል መሆኑን ልንነግራቸው እንፈልጋለን። በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ አሁኑኑ ይቁም!!! ሰቆቃ ፈፃሚዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

በተቻለው ፍጥነትና ባገኘነው እድል ሁሉ ተጠቅመን ሕይወታቸው አደጋ ላይ ላሉት ወገኖቻችን እንድንደርስ ግንቦት 7 ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ያደርጋል።

በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በዘላቂነት የሚወገደው ወያኔ ከሥልጣን ተባሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠው መንግሥት ሲያስተዳድር በመሆኑ ለዚህ ታላቅ ግብ በኅብረት እንነሳ።

በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ይቁም!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡

እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡

Image

የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ፓርቲያችን እንዲህ አይነቱን የለየለት የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከተው መሆኑን እየገለፅን፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐናችን እንዲቆም በአፅንኦት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም

Image

Getachew=Shiferaw-
በጧቱ ነበር ወደ ወሎ ሰፈር ለማቅናት መንገድ የጀመርኩት፡፡ መሃል ላይ አንድ ስልክ ደረሰኝ፡፡ ‹‹የሰማያዊ ፓር አመራሮችና አባላት ታግተዋል›› የሚል፡፡ ለማረጋገጥ ወደ ቢሮ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ቢሮ ስደርስ የአካባቢው ሰዎች ሰብሰብ ሰብሰብ ብለው ስለ ታሳሪዎቹ፣ ሳውዲ ውስጥ ስለሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያን፣ ስለሰላማዊ ሰልፉ ያወራሉ፡፡

በርካታ ፖሊሶች በቢሮው አካባቢ ተሰባስበዋል፡፡ ግቢው ውስጥ ግን ማንም የለም፡፡ ቢሮው በር ላይ ሳውዲ ውስጥ ለሚሰቃዩት ወገኖች በምልክትነት የተሰቀለው ጥቁር ምልክት እንዳልተነሳ ስመለከት ፖሊሶቹ ስለ ጉዳዩ እውቀት እንደሌላቸው ገባኝ፡፡ አመራቹን በአንዳች ነገር ከሰው ብቻ እርምጃ እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ማለት ነው፡፡

ከሰዎች መረጃ እያሰባሰብኩ እያለ ሌላ ስልክ ደረሰኝ፡፡ ‹‹ወደ ጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል›› የሚል ነው፡፡ ወደዛው መሄድ አለብኝ፡፡ አንድ ጓደኛየን አግኝቸው ከእሱ ጋር አመራሁ፡፡ ኤምባሲው ጋር የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀላቀል እየረፈደብን ቢሆን ስለ ታሳሪዎቹ መረጃ ማግኘት ነበረብን፡፡

ጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ስንደርስ ኢንጅነሩንና ሌሎች ጥቂት አመራሮችን ከርቀት አየናቸው፡፡ ሌሎቹን አስገብተው እየደበደቧቸውም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ውስጥ ገብተው አይታዩም፡፡ ፖሊሶቹ ወደ እኛ ሲመጡ ሳውዲ ኤምባሲ ያለውን ጉዳይ ከመታሰር ብለን ታሳሪዎቹን ከእርቀት ሰላም ብለን ወደ ኤምባሲው እየተቻኮልን አቀናን፡፡

ሰዓቱ እየሄደ በመሆኑ ላንደርስ እንችላለን ብለን ሰግተናል፡፡ በእርግጥ የኢህአዴግ አንዱ ስልትም እንዲህ በተለያዩ ጉዳዮች በመወጠር ዋናውን ነገር ማሳት ነው፡፡ ወሎ ሰፈር አካባቢ ወደ 6 ሰዓት አካባ ስንደርስ ጥቁር የለበሱ ሰዎች ከኤምባሲው አቅጣጫ እየተመለሱ ነው፡፡ ሌላው ህዝብ ደግሞ በየ መንገዱ ዳር ቆሞ ይመለከታል፡፡

ይበልጥ እየቀረብን ስንሄድ የምናውቃቸውን ሰዎች አገኘን፡፡ እስካሁን አልተደበደብኩም የሚል ሰው አላጋጠመንም፡፡ አንዲት ምን አልባትም ሳውዲ ውስጥ የምታውቀው ሰው ጥቃት የደረሰበት ዘመድ ያላት የምትመስል ሴት ስቅስቀስ ብላ ታለቅሳለች፡፡ ሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሳለች፡፡ ይህች ሴት እንዲህ የምታለቅሰው ከድብደባው ይልቅ ለዜቾቻችን ክብር ያልተሰጣቸው መሆኑ ነው፡፡

ሌላኛዋ ደግሞ የምታለቅሰው በጣም በመደብደቧ ነው፡፡ አንድ ሌላ ወጣት (ጓደኛየ ጋር ይተዋወቃሉ) ሰላም ካለን በኋላ በየ ቦታው ይቀመጣል፡፡ ምኑን እንደመቱት ስንጠይቀው ኩላሊቱ አካባቢ የተገመደለ አዲስ ቁስል አሳየን፡፡ ልጁ በንዴት ይቁነጠነጣል፡፡

በርካቶች መታሰራቸውን ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የነበሩት ነግረውናል፡፡ አብዛኛው የተበተነው ወጣት እያማረረ ነው፡፡ አንደኛው ‹‹ሰላማዊ ትግል አያስፈልግም›› ይላል፡፡ ለጎኑ ካሉት ክርክር ይገጥመዋል፡፡ ሌላኛው ‹‹ ነገ ኳስ ላይም ቢሆን ይህን ጮከታችን እናሰማለን››፣ ሌላኛው ‹‹እኔ የተደበደብኩት አገሬ ውስጥ ነው ወገኖቹ ሳውዲ ውስጥ እየሞቱ ነው፡፡››፣ ሌላኛዋ ‹‹እሁድም መጥተን መደብደብ አለብ›› ……

እኔም ቢሆን ኢህአዴግ ይፈቅዳል የሚል ተስፋ አልነበረኝም፡፡ ሰማያዊዮች ሲታሰሩም ማረጋገጥ የቻልኩት ይህን ነው፡፡ ግን መታሰርም ሆነ መደብደብ አንድ ነገር ነው፡፡ ይህ ለዜጎቻችንም ሆነ ለራሳችን ያለንን ክብር የምናሳይበት ነው፡፡ ኢህአዴግ ዳግመኛ ከገዳዮቻችን፣ ከጠላቶቻችን ጎን ቆሞ፡፡ ጸረ ህዝብነቱንም አስመሰከረ፡፡
አንዳንዴ ስትደበደብ ወይንም ስትሰታሰር ይወጣልሃል፡፡ እኔ እየዞርኩ ሳይ የዋልኩት የዜጎችን ሰቆቃ ብቻ ነው፡፡ እናም ቅጥል ብያለሁ፡፡

ዩጋንዳ ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በሕይወት አለ?
ይህን ጥያቄ ለመመለስ ካምፓላን ማዳረስ ኣያስፈልግም።የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሚሊኒየሙ አከባበር ግዜ ነበረ። ከዛ ተሽመደመደ።ጁላይ ኢለቨን ካምፖላ በአልሻባብ አጥፍቶ ጠፊዎች አሰቃቂ ፍንዳታ በደረሠ ግዜ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አለሁ ብሎ ሲሯሯጥ ታየ።ከዛ በኋላ ነበር ኖቬምበር አስራአራት ቀን ሁለት ሺ አስር የኢትዮጵያ ኮሚኒቲን
ኖቬምበር አስራአራት ከሚሊኒየሙ በፊትና በኋላ ኮሚኒቲው ያከናወናቸውን ተግባራት የሚያትት ዝርዝር የስራና የሂሣብ ሪፖርት ቀርቦ የነበረው።ለአንድ ዓመት ያህልም በወገኖች ድጋፍ ቢሮ እስከመክፈትና የአባልነት መታወቅያም ለማህበረሠቡ አዳርሶ ነበር።ኮሚኒቲው በወቅቱ ያሣየው ፍጥነት የወያኔን ወኪሎች አስግቶአቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንት ቢሮውም ተዘጋ ፣አመራሩም ላይገናኙ የተማማሉ መሠለ።ከወያኔ ቆንስላ ሃላፊዎች ጋርም ምስጢራዊ ስብሰባ የተወሰኑ የኮሚኒቲው አመራሮች አደረጉ የሚል ወሬ ተሠማ።ያኔ ኮሚኒቲው ተሸረሸረ።
ዩጋንዳ ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መተዳደርያ ደንቡ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ አባል መሆን እንደሚችል ስለሚገልፅ የወያኔ ቆንስላ ሠራተኞች ካሣደዱዋቸው የፖለቲካ ስደተኞች ጋር የአንድ ኮሚኒቲ አባል ለመሆን ሲመዘገቡ ታይተዋል።በየትኛውም ስፍራ የፅዋ ማህበርም ቢሆን ወያኔዋቹ በይፉም ሆነ በህቡህ ያን ማህበር ካልተቀላቀሉ፣
አልያም ካላፈረሱና ወይም በነሡ ሣንባ የሚተነፍስ ተለጣፊ ካልመሠረቱ ሞታቸው ነው።
የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በዩጋንዳ ዛሬ ስሙ ከመኖሩ ባሻገር ተሽመድምዶ ያለው ፖሊዮ ይዞት አይደለም።የኮሚኒቲው አመራሮች የያዙትን ቦታ ለመልቀቅ ፈቃደኝነት ያላቸውም አይመስልም።የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ከሚሊኒየሙ በፊትም ሆነ በኋላ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሚያደርጋቸውን ተግባራት በቅርበት ያውቃል።እንደዜጋም አቅሙ የፈቀደውን በማድረግ በወያኔ ቆንስላ ጥቁር መዝገብ በጠላትነት ተፈርጆ እንደሚገኝ የካምፓላ ሰማይ የሚያውቀው ዕውነታ ነው።
ወያኔ የሚሊኒየሙን በዓል በሱ ፊታውራሪነት ካምፓላ ላይ ለማክበር ሲሯሯጥ በወቅቱ ወያኔ ንፁሀንን እስር ቤት አጉሮ በዓሉን በጋራ እንድናከብር ሊያግባባና ሊያስፈራራ ሲሞክር የታሠሩት ይፈቱ፣ብሔራዊ ዕርቅ ይደረግ ብለን የተወሰንን ወገኖች በመናገራችንና ሚሊኒየሙን ያለወያኔ ተሣትፎ በደመቀ ሁኔታ በማሣለፋችን ነበረ የወያኔ ጥርስ ውስጥ የገባነው።
ባለፉት ሦሥት አመታት የወያኔ ቆንስላ ዩጋንዳ ካምፖላ ላይ እውነተኛ የፖለቲካ ስደተኞችንን በማሳደድ፣በማሠለልና መፈናፈኛ በማሳጣት ሕብረተሠቡን በዘር እስከማደራጀት ሠርቷል።
ኮሚኒቲውን አሽመድምዷል።ከአመራሩ የተወሠኑትን ፖስፖርት በመስጠት ከስደተኛነት አላቋል።የወያኔ ቆንስላ ቤተኛ የሆኑም እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
በርካታ ወገኖች ኮሚኒቲው ባይቀበርም እንደሞተ ያምናሉ።እንደገና ለማጠናከርም ቢሞከር አሁን ካሉት የአመራር አባላት መካከል ከወያኔ ጋር በግልፅም ይሁን ውስጥ ለውስጥ የሚሞዳሞዱትን ለይቶ ለማውጣት አስቸጋሪ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።
ከሁለት ዓመት በፊት በሕጋዊው ሲኖዶስ የሚመራውን የካምፖላ መካነ ሠላም መድሐንያለም ቤተክርስትያን የወያኔ ቆንስላ ካህናትና፣ ዲያቆናት እንዲሁም መዘምራንን በስውር አደራጅቶ ያካሄደው ትርምስ በእውነተኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ከከሸፈና የአመፁ መሪ የነበሩት የቀድሞ አስተዳዳሪ የስደተኛ እስታተሳቸውን ወርውረው በወያኔ ፖስፖርት የአምስት ኪሎውን ቤተክህነት ከተቀላቀሉ ወዲህ ነገሮች እየጠሩ መጥተዎል።
ካምፖላ ላይ የፖለቲካ ስደተኛ መታወቅያ በደረታቸው ፣የወያኔ አክቲቭ ፓስፖርት ትራሳቸው ስር ሸጉጠው ትክክለኛ ስደተኞችን የሚሠልሉና ለአደጋ የሚያጋልጡትን ሆድ አደሮች ለማጋለጥ በዩጋንዳ የሚኖሩ ስደተኞች ለህልውናቸው ሲሉ በህብረት ሊቆሙ ይገባል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥቂት የፖለቲካ ስደተኞች ስደተኛውን ብቻ ያቀፈ የስደተኞች ማህበር ለመመስረት እንቅስቃሴ እየተከናወነ ሲሆን ለስደተኛው መብት መከበር የሚሠራ ከማናቸውም የፖለቲካ ሃይሎች ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ማህበር ለመመስረት የበኩሌን እገዛ ሳደርግ ብቆይም ለደህንነቴ ስጋት የሚፈጥሩ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ከማናቸውም ማህበረሠቡን ከሚመለከቱ ጉዳዮችራሴን አግልዬ እንደምገኝ ለመጠቆም እወዳለሁ።በተቻለ አቅም ስደተኛው የራሱን ማህበር ከወያኔ ሠርጎ ገቦች እንዲጠብቅ አሳስባለሁ።
የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እስከዛሬ የታመሙትን ወገን በማስተባበር ለማሣከም ያደረገው መልካም ተግባር ፣
የሟች ወገኖችን አስከሬን ከቤተሠብ ጋር መክሮ ለሐገራቸው አፈር እንዲበቁ በመስራቱ፣ምስኪን ስደተኞች ሲሞቱ በመቅበር የሠራውን ስራ በመዘከር ወደ ወያኔ ጉያ የተሸጎጠውና ፖራላይዝዱ ኮሚኒቲ እኔም ልክ የዛሬ ሦሥት አመት በተከናወነው የማሟያ ምርጫ የቦርድ አባል ሆኜ እስከዛሬ መቆየቴን እየጠቆምኩ በመላ ዓለም የምትገኙ ኮሚኒቲዎች ልምዳችሁን እንድታካፍሉኝ እንደ አንድ ዩጋንዳ ላይ በሚኖር ሐገር አልባ ስደተኛ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ ሁሉ ፀሀፊው በንፁህ ህሊና እውነቱን ብቻ ለመግለፅ ህሊናው ዝግጁ መሆኑን ይጠቁማል።
ጋዜጠኛ ደረጀ በጋሻው
ከኮሚኒቲው ቦርድ አባላት አንዱ

ድምጻችንን ከማሰማት አንቆጠብ..የኢትዮጵያ መንግስት ማላገጡን በሳዑዲም ዜጋችን መሞቱ ቀጥሏል..
በግሩም ተ/ሀይማኖት
ሪያድ ውስጥ ወገኖቻችን ላይ ዛሬም ጥቃት ተፈጸመ፡፡ ብጥብጥ ተፈጥሯል እባክህ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውልልኝ ብሎ ቁጥር አስቀምጦልኝ አገኘሁ፡፡ 9665533…አደረኩና ደወልኩ፡፡ ከወዲያ ማዶ ምላሽ ስጠብቅ ኮለል ያለ የመደፈር ጥቃት የአትንኩኝ ባይነት ግርማ ሞገስ ባለው ድምጽ ‹‹ሀሎ!›› ተባልኩ፡፡ ሰላምታዬን አደረስኩና ብጥብጡ ምንድን ነው አልኩት፡፡ ‹‹..ይሄውልህ ግሩሜ በሪያድ መንፉሃ አውራ መንገዶች ሃገራችን ውሰዱን ብለን እቃችንን ሸጠን ወጥተናል፡፡ አምባሳደሩ መጣና ምንም ችግር የለም ወደ ሀገር ትገባላችሁ ብሎ ሄደ፡፡ ዛሬ ከቀትር በኋላ ወደ ብጥብት ተነሳ….(ዛሬ የሚለው ትላንት ማታ ስላውራሁት ነው)
Image
(እኔ እሱን ላቋርጥና የምለው ስላለኝ ቅንፌን ከፍቻለሁ፡፡ አምባሳደሩ በሉ ተብለው የታዘዙትን ነው ያሉት፡፡ ያ-ሳይሆን የሚያሳዝነው ቤታቸውን ጥለው ወጥተው አደባባይ መሆናቸውን እያዩ አላግጤ ንግግራቸውን ተናገው እና በአፍ ደልለው መሄዳቸውን ሌላ ምንጮቼ ገልጸውልኛል፡፡ ዜጋዬን..ያለው መንግስትም 25 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር መመለሱን በዜና እወጃው አሰውቋል፡፡ የተመለሱት ሰዎችን ምንነት በዜናው ላይ ከተደረገላቸው ቃለ-ምልልስ ማወቅ ይቻላል፡፡ የኢህአዴግ ካድሬዎች ዘውትር የሚያንቆረቁሩት ስልቹ ቃላትን ሲደግሙት ለሰማ ‹‹..አሀ! የእንትን ልማት ማህበር አባል…›› ብሎ መጥራቱ አይቀሬ ነው፡፡ ይህን ጥርጣሬዬን ይዤ ለአንዱ እንዴት ነው ለመግባት ያለው ሂደት አልኩት፡፡ ‹‹.1000 ሪያል ካለህ በአፋጣኝ ትጨርሳለህ….›› በስመአብ የደነገጥኩትን አትጠይቁኝ፡፡…እኔ በአረቡ አለም ያሉት ኤምባሲዎች ኮሙኒቲ ካልተመዘገብክ የአማራ ልማት ማህበር፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣የጉራጌ..ምናምን አባል ካሆናችሁ እያሉ አገልግሎት ስለማጓተታቸው ስጠይቀው ይባስ ለፈጣን አገልግሎት 1000 ሪያል ጉቦ መባሉ እንዴት አያስደነግጠኝ? አሁን ለደወልኩለት እና እያናገርኩት ላለው ልጅም ይሄን ጥያቄ አቀረብኩለት…ወደ ዘገባዬ ተመለስኩ፡፡)

ወደ ሀገራችን መልሱን የሚለው ጥያቄያችንን ለማደናቀፍ ፖሊስ ሸባቦቹን ይዞ መጣ፡፡ (ሸባብ ማለት ወጣት ነው፡፡ ፖሊስ እነዚህን የመንደር ጎረምሶች ይዞ በመዞር ነው ዜጋዎቻችን ላይ ጥቃት የሚፈጽመው) ‹‹ለምንድነው እንደዚህ የምትሆኑት ሂዱ ብላችኋል መሄድ እንፈልጋለን ብለን ነው ቤት ንብረታችንን ጥለን የመጣነው ብለን ለማረጋጋት ሞከርን፡፡ በፊት ሲመጡ አሰር (የዘጠን ሰዓት ስግደት) እየሰገድን ነበር፡፡ በተፈጠረው ግርግር ሲያሰግደን የነበረውን ልጅ በጩቤ ወጉት፡፡ ከዛ ከፍተኛ ግርግር ነበር፡፡ ወደ ታፋው አካባቢ ነው የወጉት፡፡ እንግዲህ ኤምባሲው ምንድን ነው ስራው…(ወዳጄ የኤንባሲው ስራ እናንተን ማስደብደብ እና ከሳዑዲ የሚፈልጉትን ማግኘት) እንዴት ነው በዚህ ጭንቅ ሰዓት ኤምባሲው የሚያስከፍላችሁ ነገር አለ እንዴ? አልኩና ጥያቄ በስልክ ወረወርኩ፡፡ ቀበል አለና አይ! ጉዳዩን ቶሎ እንዲጨርሱልህ ላለመጉላላት ከፈለክ 1000 ሪያል የይጠይቁሀል….(ጉቦ መሆኑ ነው ወገኖቼ በዚህ የጭንቅ ሰዓት እነዚህ የኤምባሲ ሰራተኞች ጉቦ ይበላሉ…..የወገናቸውን ደም ይጠጣሉ፡፡ ኧረ!!!!…እባካችሁ እንተዛዘን….) ሌላው አሁንም የገዚው ፓርቲ አሸርጋጆች በድርጅታዊ አወቃቀር ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊን እንደ ዜጋ በማየት ማስተናገድ እንጂ በዚህ ሰዓት አባል የሆና ያልሆነ እያላችሁ እና ከዜጋ ህይወት ገንዘብ አስበልጣችሁ ኪሳችሁን ማደለብ ስታስቡ አሁንም ወገኖቻቻንን ለእልቂት አትዳርጉ፡፡

በዙሪያው የምንገኝ የመንፉሃን ግጭት ተከትሎ በተሰጠው ወደ ሃገር የመግባት እድል ለመጠቀም በቡዙ ሺህ የሚቆጥሩ ኢትዮጵያዊ መጠለያዎችን እያጨናነቀ ነው። በመካ ያለው ከባድ ሁኔታ ቢሆንም ያለው የባሰ ያስገረመው በሁለት ኢትዮጵዊያን መካከል በተፈጠረ ግጭት አንደኛው አንዱን ደጋግሞ በጩቤ በመውጋቱ አንደኛው ኢትዮጵያው ለህልፈተ ህይወት በቅቷል፡፡ ይህ ወገን ወገኑን የሚጎዳበት ሂደት በእንደዚህ አይነት አጣብቂኝ የስቃይ ህይወት ውስጥ ሆኖም መቀጠሉ ያሳዝናል፡፡

አሁንም በሽዎች የሚቆጠሩ ወደ መጠለያ ለመግባት እየጎረፉ ነው ። በመጠለያው ትናነት አንዲት የ9 ወር እርጉዝ ሞታ ተቀብራለች ። በመጠለያው የምግብና የመጥ እጠረቱ ደግሞ ኢትዮጰያውያኑነ አጥር ሰብረው እንዲወጡ እያስገደደ ነው ተብሏል። በሳዑዲ ያለው ሁኔታ መንግስት ቀዝቅዟል በማለት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በኩል ቢናገርም ቢገልጽም፡፡ሁኔታው የከፋ እና ፖሊስ አሁንም ወጣቶችን ይዞ በየቦታው እየዞረ ማስደብደቡን እንደቀጠለ መሆኑን ሳዑዲያ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ይናገራሉ፡፡ በጣም አሳፋሪ መረጃ እየሰጡ ያሉት የመንግስት ተቋማት ዛሬም ይህንኑ እየደገሙት መሆኑ አሳዛኝ ኢ-ሰብአዊነት እየፈጽሙ መሆኑን ልብ ሊባል ይገባዋል፡፡

ከከተማው አርቀው ያስቀመጧቸው ካምፐ ውስጥ የምግብ እና ውሀ እጥረት መኖሩን አንድ መረጃ ሲያቀብለኝ የከረመ ወዳጄ አድርሶኛል፡፡ ሴቶች፣ ህጸናት፣.የስኳር በሽተኞች፣ አሉ፡፡ ካምፕ ውስጥ አስገብተው ከቀን አንዴ ብቻ ነበር እህል የሚሰጠን፡፡ አሁን ድንገት ሁለት ነው ማለት ከተቻለ ሁልቴ አንዴ የምትበላውን የሚያህል ያበሉሀል፡፡ የመጠለያው ሁኔታ እጅግ አስከፊ መሆኑን ነግሮኛል፡፡ በተጨማሪም በእስር እና ከእስር ወደ እስር ቤት መቀየር ላይ አስካሁን ብቻ 5 ሰዎች መሞታቸውን ይሄው የአይን እማኝ የሆነው የመረጃ ምንጬ ገልጾልኛል፡፡ በግሩም ተ/ሀይማኖት

እንደ ኢህአዴግ ፈሪ ፓርቲ ከወደየት አለ? ጌታቸው ሺፈራው

beዚህ ጽሁፍ መግለጽ የምፈለግው የኢህአዴግን መጠነሰፊ ፍርሃት ያሳያሉ ያልኳቸውንጥቂት ምሳሌዎች ነው፡፡ እስካሁን እንደ ኢህአዴግ ፈሪ ፓርቲ አጋጥሞኝ ስለማያውቅም እንደ ኢህአዴግ ፈሪ ድርጅት ከወደየት አለ? ብሎ መጠየቁ አግባብ መስሎ ታይቶኛል፡፡ ፈሪው ድርጅት ‹‹የለም ከእኛ በላይ ፈሪ ድርጅቶች እዚህ እዚህ…አገር ይገኛሉ›› የማለት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲያውም እስካሁን የነበረበትን ከፍርሃት የመነጨ ድብቅነት በጥቂቱም ቢሆን እንደቀነሰ እንረዳለታለን፡፡ በድፍኑ ‹‹አይ እኛ ፈርተን አናውቅም!›› ቢል ግን ያው የተለመደ ስለሆነ የሚያምነው አያገኝም፡፡ ደግሞስ እየፈሩ ‹‹አልፈራንም›› ማለት ምን ማለት ነው? ‹‹አልፈራንምንስ ምን አመጣው? ኢህአዴግ የሚፈራውን ከመዘርዘር ይልቅ ራሱ የማይፈራቸው ነገሮች ካሉ ቢነግረን የተሻለ ነበር፡፡ እኔ ግን ከሚፈሯቸው ነገሮች መካከል በጣም ጥቂቶቹን ብቻ በመጥቀስ የፍርሃቱን መጠን ለማሰየት እሞክራለሁ፡፡ ህገ መንግስቱን ለብሄር ብሄረሰቦች መብት መከታ ነው የሚባለው የወቅቱ ህገ መንግስት የአቶ መለስና ለንጮ ለታ የፖለቲካ ማህተም ያረፈበት እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ይህ ህገ መንግስት እንደ አንቀጽ 39ን ያሉትን ጨምሮ ስለ የመሬት ፖሊሲ፣ አንድነትና ሌሎች ጉዳዮች ያለው ህጸጽ እንዳለ ሆኖ ከነ ድክመቱም ቢሆን ቢተገበር አሁን ካለንበት ብልሹ ፖለቲካ የተሻለ ስርዓት ሊመሰርት እንደሚችል ይታመንበታል፡፡ በተለይ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የአመለካከትና ሌሎች ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን ከዳር ዳር ከማጨቅ ውጭ ተግባራዊ ሲሆኑ አይታዩም፡፡

Image

ከተግባራዊነቱ ይልቅ ለይስሙላህነቱ እንዲውል ተደርጓል፡፡ ይህም የሆነው ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈሩት አብዛኛዎቹ መርሆች ተግባራዊ ቢሆኑ የገዥውን ፓርቲ ስልጣን የሚያሳጡ መስለው ስለሚሰሙት ነው፡፡ እናም ኢህአዴግ ‹‹ባለ ራዕዩ›› መሪ በበላይነት መርጠው ያጸደቁትን ህገ መንግስቱንም ቢሆን ለመተግበር ይፈራዋል፡፡ ስለሆነም በተቻለ መጠን ህገ መንግስቱ ላይ ያሉት መርሆች ተግባራዊ የማይሆኑበትን አጋጣሚ ሁሉ ይጠቀማል፡፡ ለዚህ አተገባበሩ የዳኝነት ሰርዓቱን ጨምሮ በጉዳዩ ተያያዥነት ያላቸውን አካላት የገዥውን ፖሊሲ የሚያቀነቅኑ እንዲሆኑ ጥሯል፡፡ ይህ ግን በቂ አልነበረም፡፡ በተለይ በ1997 በኋላ ኢህአዴግ እንደ አንዳች ነገር የሚፈራቸው ወሳኝ የህገ መንግስቱ መርሆች በጸረ ህገ መንግስት አዋጆች ታጥረው ተቀምጠዋል፡፡ የጸረ ሽብር፣ የሶቪክ ማህበራት፣ የፓርቲዎች የስነ ምግባር፣ የሚዲያ…..አዋጆች ህዝብን ብቻ ሳይሆን ህገ መንግስቱን አሽገው ለህዝብ እንዳይቆም ያደረጉ አዋጆች ናቸው፡፡ ተወዳዳሪ ፓርቲን ኢህአዴግ መድብለ ፓርቲን መርህን እቀበላለሁ እያለ የጠንካራ ፓርቲዎችን መኖር ግን በእጅጉ ይፈራል፡፡ ለዚህም ሲባል ከፓርቲዎች ጋር አብሮ ከመስራት ይልቅ ተገንጣዮችን በመፈልፈል የኢትዮጵያን ፓርቲዎች ከ80 በላይ አድርሷቸዋል፡፡ በእርግጥ ይህ የጠንካራ ፓርቲ ‹‹ፎብያ›› የጀመረው ህገ መንግስቱ ላይ ‹‹የበድብለ ፓርቲ›› በስምም ቢሆን ከተፈቀደ በኋላ አይደለም፡፡ ህወሓት በዱር እያለም ፓርቲዎችን ከዚህም በላይ ይፈራቸው እንደነበር ታሪኩ ያስረዳል፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ኢህአፓ ከህወሓት ጎን ለጎን አብሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ይሁንና የኢህአፓ ህብረ ብሄርነት ህወሓት የቆመለትን የመገንጠል ፖሊሲ አደጋ ላይ በመጣሉ ህወሓት ‹‹ከትግራይ መሬት ውጡልን ይህ የትግራይ ህዝብ መሬት ነው›› ብሎ አባረረው፡፡ የትግራይ አርነት ግንባርን (TLF)ንም የትግራይ ህዝብ ከአንድ በላይ ፖለቲካ ፓርቲ መሸከም አይችልም ብሎ አጥፍቶታል፡፡ እንዲያውም የትግራይ አርነት ግንባር አባላት ከህወሓት ጋር ለመደራደር ከተስማሙ በኋላ በተኙበት በህወሓት መጨፍጨፋቸውንና ይህን ዘግናኝ የጭፍጨፋ ሂደት አንዳንድ የህወሓት አባላት ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡ እንደራደር ብሎ የመጡትን ፖለቲከኞች መጨፍጨፍ መቼም ጀግንነት፣ ድፍረት ሊሆን አይችል፡፡ ኢህአዴግም እየተጠቀመበት የሚገኘው ይህን የህወሓትን የፍርሃት ልምድ ነው፡፡ ገና ስልጣን እንደያዘ ጠንካራ ከሚባሉት ኦነግ፣ ኦብነግና ሌሎች የብሄር ድርጅቶችን ጋር ከጥርጣሬም አልፎ አለመግባባት ውስጥ ገባ፡፡ በምትካቸው ደግሞ እንደ ኦህዴድ፣ ሶዴፓ ያሉ ደካማ ፓርቲዎችን ተገን ማድረግ ጀመረ፡፡ ለጠንካራ ፓርቲዎች በርካታ ደካማ ተገን ፓርቲዎችን የሚፈጥረው ኢህአዴግ ከመቼውም በላይ ስለፈራ 80 ያህል ደካማ ፓርቲዎች አገሪቱን ተፍልፍለዋል፡፡ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎቹን ብቻ ሳይሆን አብረውት እየሰሩ የሚገኙትንም ቢሆን ‹‹በአጋር ፓርቲነት›› ስም ብቻ ፖለቲካውን ከእርቀት እንዲመለከቱ እያደረገ ነው፡፡ በአገሪቱ የረባ የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን እነዚህ ፓርቲዎች ያፈነግጡብኛልበማለትም የህወሓት/ኢህአዴግን አማካሪዎች በተቆጣጠሪነት ከማስቀመጥ ጀምሮ መረዎቻቸውን በተለያየ መንገድ ማግለል የተለመደ የፖለቲካው እቃ እቃ ጨዋታ ሆኗል፡፡ የሶማሊ፣ ጋንቤላና ቤንሻንጉልን ህዝቦች ስም ‹‹አጋር›› የሆኑት እነዚህ ፓርቲዎች መሪዎቻቸው ከአዲስ አበባ በተላከ ትዕዛዝ በተደጋጋሚ ገለል የሚደረጉት ያፈነግጡብኛል ብሎ ስለሚፈራቸው ነው፡፡ የአገር አንድነትን ኢህአዴግ የአንድነት ፍርሃት የሚጀምረው እስካሁንም ድረስ የትግራይን ህዝብ ነጻ ለማውጣት የቆምኩ ነኝ የሚለውን ስሙን ለመቀየር ከሚፈራው ህወሓት ነው፡፡ የህወሓት የተገንጣይ ስምም ቢሆን እስካሁን የማይቀየረው አንድነት ይቅርና ፌደራሊዝሙም ላይ ፍራቻ ሳላለው ይመስላል፡፡ ከዚህ ውጭ የትኛውም አንድነትን የሚወክል ወይንም የሚያንጸባርቅ ነገር ለህወሓት/ኢሀአዴግ ያስበረግገዋል፡፡ ልክ እንደ ህወሓት/ ኢህአዴግ ሁሉ የኢትዮጵያ አንድነትን የሚጠላው ሻዕቢያ መጀመሪያ የተረባረበው የአንድነት ዋነኛው መገለጫ የሆነው ሰንደቅ አላማው ላይ ነበር፡፡ ሻዕቢያ ባልታጣ መቋጠሪያ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ዋነኛው የዱቄት መቋጠሪያው አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ በለስ (ቁልቋል) ሳይቀር የሚሸመጥጡት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንደነበር ይነገራል፡፡ ህወሓት በተለይ መጀመሪያ አካባቢ ትጥቅም ሆነ ስንቅ (ዱቄት) ይቀበል የነበረው ከሻዕቢያ ነውና ከሻዕቢያ የተለየ ተግባር ሊፈጽም እንደማይችል መገመት ቀላል ነው፡፡ አቶ መለስ ስልጣን ከያዙ በኋላ ስንደቅ አላማውን ጨርቅ ያሉት ከሻዕቢያ በወረሱት የአንድነት ፍርሃት መሆኑን እንረዳለን፡፡ ሁለቱም ድርጅቶች ይህ በደል የፈጸሙት ከሰንደቅ አላማው በስተጀርባ ያለውን አንድነት በእጅጉ ስለሚፈሩት ነው፡፡ ኢህአዴግ ለዚህ የረዥም ጊዜ ፍርሃት መሃል ላይ ያስቀመጠው ኮከብም ፍርሃቱን ሊያስወግድለት አይቻለም፡፡ አቶ መለስ ከመሞታቸው ከወራት ቀደም ብለው ሰንደቅ አላማውን የዘቀዘቁት አሁን ባለው ቅርጹም ቢሆን ስለሚፈሩት ይመስለኛል፡፡ ዛሬም ቢሆን ኢህአዴግ ራሱ መጥኖ በጠራው ጉዳይ ካልሆነ በስተቀርሰ ህዝብ በስፋት ባለኮከቡን ሰንደቅ አላማ በክብር ሲያነሳም ብርክ ይይዘዋል፡፡ አማራጭ ሚዲያን ኢትዮጵያ በሚዲያ ወደኋላ ከቀሩት አገራት መካከል የመጀመሪያዋ ናት፡፡ ለ90 ሚሊዮን ህዝብ ያለን አንድ ፕሮፖጋንዳ የሚሰራጭበት ቴሊቪዝን ጣቢያ ብቻ ነው፡፡ በአንጻሩ 6 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ላኦስ፣ ሁለት ሚሊዮን ህዝብ ያላት ጃማይካ፣ አንድ ሚሊዮን ህዝብ ያላት ትሪንዳድና ቴቪጎ እያንዳንዳቸው የግልን ጨምሮ ባለ ሰባት ጣቢያዎች ናቸው፡፡ 400 ሺህ ህዝብ ያላት ማልታ 8፣ 36 ሺህ ህዝብ ያላት ሞናኮ 5 ጣቢያዎች ለህዝባቸው አማራጭ መረጃ ያስተላልፋሉ፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር የሚነጻጸር ህዝብ ያላቸው አገራት ደግሞ በርካታ ጣቢያዎች ባለቤቶች ሆነዋል፡፡ ለአብነት ያህል ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ በኩል የምትተሳሰረው ግብጽ 98 ያህል ጣቢያዎች ባለቤት ነች፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ ከግማሽ ያነሰ ህዝብ ያላት ጎረቤት ኬንያ እንዲሁም 34 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ዩጋንዳ እያንዳንዳቸው 8 ጣቢያ ያላቸው ሲሆን አብዛኛዎቹ የግል ሚዲያዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ሚዲያ ይህን ያህል ከአገሪቱ ታሪክም ይሁን ህዝብ ጋር የሚቃረን የሆነው ኢህአዴግ በእጅጉ ስለሚፈራው ነው፡፡ ሚዲያ ህዝብን ያነቃል፣ ሙስናንና ሚስጥርን ያጋልጣል፣ አንድነትን ያጠናክራል፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት አማራጭ ሀሰብ ህዝብ ዘንድ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ ይህ የነቃ ማህበረሰብ የሚፈጥረው ሚዲያ ደግሞ ለአንድ ፓርቲና ግለሰብ የበላይነት ጸር ነው፡፡ ለህዝብ ልዓላዊነት እንጅ ለ‹‹አውራ ፓርቲ›› አያመችም፡፡ ስለሆነም ኢህአዴግን ከምንም በላይ ያስፈራዋል፡፡ ለዚህም ነው 90 ሚሊዮን ህዝብ አሰልች ፕሮፖጋንዳ በሚነዙ የመንግስት (ፓርቲ ሚዲያዎች) ብቻ የተወሰነው፡፡ በፍርሃቱ ምክንያትም የህትመት ሚዲያው አሳሩን ሊበላ የግድ ሆኖበታል፡፡ ህገ መንግስቱም ሆነ አዋጁ አማራጭ (የግል) ሚዲያን አይከለክልም፡፡ እንዲያውም በአዋጁ የብሮድካስት ሚዲያም በግል እንደሚፈቀድ ሁሉ አስቀምጧል፡፡ ይህ በሆነበት ግን አንድም የግል ቴሊቪዥን ጣቢያ የለንም፡፡ ሚዲያ ህዝብን እንደሚያነቃ የሚያውቀውና ይህንን የሚፈራው ኢህአዴግ ኢሳትን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎችን ለመዝጋት አገሪቱን ከፍተኛ ገንዘብ በማባከን ላይ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አልጀዚራም ጭምር የታገደበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡ አማራጭ ሀሳብ የሚተላለፍበትን ሚዲያ እንዲህ የሚጠላው ‹‹አብዮታዊ›› ፓርቲ ፌስ ቡክን እንኳ ንቆ አልተወውም፡፡ በርካታ ፌስ ቡክ ላይ የሚጽፉ አካላት ጽሁፋቸው አገር ውስጥ እንዳነበብ ይደረጋል፡፡ እስክንድር ከታሰረባቸው ምክንያቶች ቀዳሚው ፌስ ቡክ ላይ በሚጽፋቸው ትንታኔዎቹ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ልክ የቻይና እና የኢራን አምባገነን ፓርቲዎች በአንድ ወቅት እንዳደረጉት ፌስ ቡክን ሊዘጋ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍና የአደባባይ ሰልፍ በኢህአዴግ ዘንድ የሚፈራ ብቻ ሳይሆን የሚጠላም ተግባር ለመሆን ደርሷል፡፡ ታይቶ ከጠፋው የ1997 ምርጫ በኋላ ለአለፉት 8 አመታት ከድጋፍ ሰልፍ ውጭ የህዝብ ሮሮ የሚሰማባቸው ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽም ሆነ በተዘዋዋሪ ታግደው ቆይተዋል፡፡ ባለፉት ስድስትና ሰባት ወራት የሰላማዊ ሰልፍ መብት እንደገና ተመልሶ የነበር ቢሆንም አሁን ግን እንደገና ታግዷል፡፡ ኢህአዴግ ሰላማዊ ሰልፍን ብቻ ሳይሆን አደባባዮችንና ጎዳናዎችን ኢትዮጵያዊ ታህሪር እንዳይሆኑ አብዛቶ ፈርቷል፡፡ ለአብነት ያህል 97ት ላይ ክፉኛ የደነገጠበት መስቀል አደባባይ ለድጋፍ ሰልፍ እንጅ ለሰላማዊ ሰልፍ ክልክል ሆኗል፡፡ ከዚህ አለፍ ሲልም ኢትዮጵያውያን ኳስ እንዳያዩበት ሁሉ እየተደረገ ነው፡፡ የናይጀሪያንና የኢትዮጵያን ጨዋታ መስቀል አደባባይ ላይ ለመመልከት ሰንደቅ አላማ ለብሰው የጎረፉ ኢትዮጵያውያን ደጋፊዎች ተደብድበው ተመልሰዋል፡፡ ሀይማኖት፣ ግለሰባዊነት፣ ነጻ ተቋም… ብቻ ኢህአዴግ የማያስፈራውን ነገር ቢናገር ይሻል ነበር፡፡ በእርግጥ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ‹‹አንፈራም!ፓርቲው እንደማይፈራ ታሪኩ ይናገራል፡፡›› ብለውናል፡፡ እዚህ ላይ አቶ ሃይለማሪያም እንደተለመደው ተሳስተው ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም እሳቸው አይፈራም ብለው ለመከራከር የፈለጉት አርሳቸው ያልነበሩበትን የኢህአዴግን የጠብመንጃ ታሪክ ነው፡፡ መሳሪያ ያነሳ ሁሉ ግን ደፋርም ጀግናም አይደለም፡፡ እንዲያውም ፈሪ ዱላው፣ ጠብ መንጃው፣ መሳሪያው፣ መሰሪነቱም ከልክ በላይ በርካታዎች ናቸው፡፡ ከእነ ተረቱም ቢሆን የፈሪ ዱላ ይባላል እኮ፡፡ ፈሪ ይህን ያህል ጉዳት ሊያደርስበት የማይችለውን አካል ሁሉ ያለ አቅሙ ይደበድባል፡፡ በራሱ አይተማመንምና እንደገና እንዳያስፈራራው ያወድመዋል፡፡ አይደለም አንዳች የሚንቀሳቀስን አካል ይቅርና ጥላውን እንኳ አያምንም፡፡ የመዋጋት፤ የማሰር፣ የመፈረጅ ታሪክ ከዚሁ ከፈሪነት ባህሪው የመነጩ ናቸው፡፡ በአንጻሩ ደፋር ለመርህ ይታገላል፡፡ ለአቆመው ህግና ስርዓት ራሱንም የሚሰዋ ታማኝ ነው፡፡ ያቆመውን ስርዓት፣ አብሮት የሚኖረውን አካልና ራሱን ያምናል፡፡ በህዝብና በአገሩ ስለሚያምን፣ በራሱ ስለሚተማመን ህዝብን በፍቅር ያቀርባል፣ ተቀናቃኙን በፍቅር ይስባል እንጅ በግድ ወደኔ ካልመጣህ ብሎ ለማጥፋት ከሆነ አንዳች ነገር ፈርቷል ማለት ነው፡፡ ያኔ ፈርቷል፣ ተፍረክርኳል፣……ይባላል፡፡ ልክ እንደ ኢህአዴግ!

Image

ጥቁር ሽብር ወያኔ ቁምጣ የለበሰ ደርግ ነው ! እመኑኝ በየትኛውም የታሪክ ገጠመኝ የሳወዲ መንግስት የዚህ አይነት ድፍረት ያውም በአደባባይ በዜጎቻችን ላይ አሳይቶ አያውቅም ፡፡ ነገሮችን ተመልሰን ከተመለከትን ይህ ግፍና በደል የእኛው ባለስልጣናት ሳውዲወችን አደፋፍረው ያስፈፀሙት ጉዳይ ነው፡፡
ይህም ሁለት ፖለቲካዊ ምክንያቶች አሉት ፡፡ የመጀመሪያው ፡- የወያኔ ባለስልጣናት በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ቦንድ እንዲገዙ በሰበሰቡበት ወቅት ተደጋጋሚ ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደነበር የሚታወቅ ነው ፡፡ ይህም ድምፃችን ይሰማ ባሉ ሙስሊሞች ላይ በሃገር ውስጥ የሚደርሰው በደል ይቁም ለጥያቂያቸውም አጥጋቢ መልስ ይሰጥ በሚል ምክንያት ነበር ፡፡ ቂመኛው መንግስታችን ይህን እንደበደል በመቁጠር በእጅ አዙር ዜጎቻችንን እያስጋዘ ይገኛል ፡፡ ለዚህ በደሉ ሽፋን እንዲሆነው በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያወቹ አረብ አገራት ላይ ያተኮሩ ወሬወችን ሲነዛ ቆይቷል ፡፡ የሳዲ መንግስት በሰጠው የጊዤ ገደብ የሚያስፈልጋቸውን መረጃ ሊጠይቁ ወደ ‹‹ኢትዮጲያ ኤምባሲ ›› የሄዱ ሚስኪን ለፍቶ አደሮች ቦንድ ግዙ እየተባሉ ሲመላለሱ የጊዜ ገደቡ አልቆላቸዋል ፡፡ ሁለተኛው ምክንያቱ ፡- አገር ውስጥ ያለው ‹‹የድምፃችን ይሰማ ›› እንቅስቃሴ አረብ አገራት ባሉ ኢትዮጲያዊያን የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል በሚል ፍርሃት ነው ፡፡ፍርሃት ብቻ ሳይሆን በግልፅም በወቲቪ (የ ወያኔ ቴሌቪዥን ) በተደጋጋሚ ተናግሮታል ፡፡ በመሆኑም ይህን የራሱን ስጋት ለማስታገስና መመለስ ያልቻለውን የማይችለውንም የመብት ጥያቄ ለማፈን የገቢ ምንጭ ናቸው ያላቸውን በአረብ አገር የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ሰላም ደህንነትና ሂወት ጭምር በእጅ አዙር እየነጠቀ ነው ፡፡ (እዚህ ላይ ሳውዲወች የቴውድሮስ አድሃኖም ስምምነት አለበት ማለታቸውን እንዳንዘነጋ) አሁን ከወደኪዌት እንደምንሰማው ደግሞ ከስራቸው በገፍ የተፈናቀሉ ኢትዮጲያዊያን ሰልፍ እንወጣለን አልያም ስራ ይሰጠን እያሉ ነው ፡፡ እኒህ ኢትዮጲያዊያን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከስራቸው የተፈናቀሉ ናቸው ፡፡
ወያኔ እና የወያኔ ጭፍን ደጋፊወች ማወቅ ያለባችሁ ጉዳይ ድህነት ትግልን ያባብሳል እንጅ አያዳፍንም ‹‹አፈር እየቃምን ድንጋይ እየቆረጠምን ደርግን ጣልነው ›› እንደምትሉት ይህም ህዝብ ሆነ ብላችሁ የምትጭኑበትን ድህነትና እንግልት ተቋቁሞ ድል ማድረጉ የማይቀር ነው ፡፡ ታውቁታላችሁ እናውቀዋለን ! ወያኔ ማለት ቁምጣ ለብሶ የመጣ ደርግ ነው ፡፡ ደርግ ቀይ ሽብር ብሎ ህዝብ ፈጀ ፤ ወያኔ በተዳፈነና የህዝብን መብት ፣ ነፃነትና ሂወት ጭምር በጋረደ ጨለማ አገዛዙ ጥቁር ሽብሩን አወጀ፡፡ እነሆ አገራችን በጥቁር ሽብር ውስጥ ወድቃለች ንጋትን ናፍቆ የተሰደደ ህዝብ በገፍ እየተሰቃየ ነው ፡፡ https://www.facebook.com/photo.php?v=286230021510610
Information for Ethiopia blog

የቀጣፊዎቹ ልሣን የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትናንት ማታ በመስኮቱ ሦስት ሆዳም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር አመራሮች አቅርቦ ነበር።ሦስቱ ሆድ አደሮች በበረከትና በሺቀጥል ከማል ተጠፍጥፈው የተሠሩ የጋዜጠኞች ማህበር መሆናቸው ነው።
ኢነጋማ አባላቱና አመራሩ ተጠራርገው ከሐገር ከተባረሩበት የጥቅምቱ መሬት አንቀጥቅጥ ሕዝባዊ ማዕበል በአግአዚ ጭፍጨፋ ከከሸፈ ወዲህ የነበረከት ስሪቶቹ በቀቀኖች አይናቸውን በጨው አጥበው ዕአንድም ጋዜጠኛ በሙያው ምክንያት አልታሠረም።የምዕራቡ ሚዲያ የኢትዮጵያን ሚዲያ ገፅታ አለአግባብ እየኮነነ ነው።የኢትዮጵያ ሚዲያ ነፃ ነው ዕዕሲሉ ለፈጣሪዎቻቸው ታማኝነታቸውን አረጋግጠዋል።
ጋዜጠኛ ባንዳ ሆኖ ህሊናውን ሲያመክን ማየት እንዴት ያሣዝናል፧
በእስክንድር፣በርዕዬትና በውብሸት ኮራሁ።በአብርሐም፣በወንደሠንና በመሠረት አታላይ አፈርኩ።ሦሥቱም አታላዮች መሆናቸው ነው።ያታለሉት ግን ራሣቸውን ነው።ህሊናቸውን ነው።
የሐገራችን ሚዲያ መቃብር ከወረደ ስምንተኛ ዓመቱን በምንዘክርበት በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኞችን አሸባሪ እያለች ዘብጥያ የምትወረውር ሐገር ውስጥ የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች መድረክ በመባል የሚታወቀው አኅጉር አቀፍ የሚዲያ ባለድርሻዎች የውይይት መድረክ ስድስተኛ ጉባዔውን ሲያከናውን በመለስ ዜናዊ ሚስጥራዊ መመርያና የተፈቀደ በጀት አማረ አረጋዊ ባለ ቀይ ጃኖው የሪፖርተር ጋዜጣ አሣታሚና የ ኤም ሲ ሲ ባለቤት እንዳለውዕየአፍሪካ ሚዲያ መሠረታዊ ችግሮች ሁለት ነጥቦችን አንስቷል፡፡ በዋናነት የጠቀሱት የሚዲያ ተቋማቱ አቅም ማነስና የሚዲያ ነፃነት ችግሮች መሆናቸውን፣ ሌላኛው ደግሞ የውጭ አገሮች አድልኦና ፍላጐት ነው ፡፡ በኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነት ችግር ቢኖርም ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ቢሆንም፣ ነገር ግን በሰፊው እየተዘገበ ያለው ስለኢትዮጵያ ብቻ ነው ዕአማረ አረጋዊ ዕበኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነት ችግር ቢኖርምዕሲሉ መናገራቸው የግሉ ፕሬስ የነፃነት ችግር እንዳለበት ከመሸም ቢሆን ያመኑ ይመስላል።
በቀጣይ ልጅ ደመቀ መኮንን አሉት እንደተባለው ጋዜጠኞቹ በሙያቸው ምክንያት አለመታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡

ዕጋዜጠኞቹ በተግባር በሽብር እንቅስቃሴ ውስጥ ተገኝተዋል ለዚህም ተገቢውን ሕጋዊ ሥርዓት የተከተለ ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፤ዕዕ

ዕኢትዮጵያ ካለችበት ቀጣና አንፃር የሽብር እንቅስቃሴ ዋነኛ ሥጋቷ ነው፡፡ በመሆኑም መንግሥት የህልውና ጉዳይ አድርጐ ይመለከተዋል፤ዕ ብለዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በጋዜጣዊ የሙያ ተግባሩ የተከሰሰ አንድ ግለሰብ ብቻ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡
ዕበጋዜጣዊ የሙያ ተግባሩ የተከሰሰ አንድ ግለሰብ ብቻ ነው።ዕያሉት ጋዜጠኛ ስሙ ማን ይሆን፧በረከት ለምን ይህን ተናገሩ ብሎ እንደማይቆጣዎ ተስፋ እናድርግ፧ተላላኪው ቢሆኑም ቅሉ።
የኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣በወርቃማ ቃላት ይህን ብለዋል። ዕሙያዊ ተግባራቸውን በመወጣታቸው ጋዜጠኞችን ማሰርና መቅጣት ኋላ ቀር የሆነ አስተሳሰብ ነው፤ዕ ሲሉ ገልጸውታል፡፡

የሚዲያ ነፃነት በኬንያ መሠረቱ እንዲስፋፋ መንግሥታቸው የሚያምን መሆኑን የሚናገሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ይህንን የሚያደርጉት ለሚዲያ ተቋማቱ ሲባል ብቻ ሳይሆን ኬንያውያን ሥልጣን ላይ ያስቀመጧቸው መሪዎች እንዴት እያስተዳደሯቸው እንደሆነ የማወቅ መብት ስላላቸውና ስለሚገባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አንዳንድ የጉባዔው ተሳታፊዎች የአኅጉሪቱ የፖለቲካ አመራሮች ወይም መንግሥታት የሥልጣን ቆይታቸውን ለማራዘም የአኅጉሪቱ የሚዲያ ነፃነትን በሚያወጧቸው የተለያዩ አፋኝ ሕጐች ገድበዋል፡፡ የሚዲያ ባለሙያዎችም በእነዚህ ሕጐች ሰለባ ሆነዋል በማለት ጋዜጠኞች ተከራክረዋል፡፡ በርካቶችም ሙያዊ ተግባራቸውን በመወጣታቸው ሕይወታቸውን እስከማጣት ደርሰዋል በማለት በውይይቱ የተሳተፉ ጋዜጠኞችና የመስኩ ባለሙያዎች የአኅጉሪቱን የፖለቲካ አመራሮች ወቅሰዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ የሚዲያ ባለሙያዎች ባገኟቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በሙያቸው ምክንያት በርካታ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እስር ቤት እንደሚገኙ በማሳያነት ይጠቅሳሉ፡፡
ይህን የመሠለ መድረክ መዝጊያ ላይ ነው የነበረከት በቀቀኖች ዕበኢትዮጵያ አንድም ጋዜጠኛ በሙያው ምክንያት አልታሠረም።የምዕራቡ ሚዲያ የሐገራችንን ሚዲያ ገፅታ አለአግባብ እየኮነነ ነው።የኢትዮጵያ ሚዲያ ነፃ ነው።ዕየሚሉን።

ህሊና ከሌላቸው ሆዳምና አድርባይ ጋዜጠኞች ይሠውረን።

ፔን ዘ ኢትዮጵያ

እንደ ሰው አንድ የሚያደርገን ባሕርይ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት የማይነጣጥለው በደል በሳዑዲ አረብያ ግዛት እየተፈጸመ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። ይህ ዛሬ በሳዑዲ አረብያ የሚደረገው ጥቃትን ማስቆምና ቁጣችን መቆምያ እንደማይኖረው ማሳየት ለነርሱ ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ደህንነትም ጭምር የምናደርገው ነው። ምክንያቱም ነገ ተመሳሳይ ጥቃትና በደል በመላው አለም ይስፋፋል። በአፍሪካ ሀገሮች የተበተኑ ኢትዮጵያን ከሶማሌና ኤርትራ ከሚሰደዱት በተለየ ይዘረፋሉ፣ ይደፈራሉ ይዋረዳሉ። እንደ አገር ልጅ አብረው እንዳይቆሙ በዘር በሀይማኖትና በፖለቲካ አቋም ምክንየት የተበተኑ ናቸው። ለሰላሳና አርባ አመት አምባገነኖች ያደረጉት ጭፈጨፋና በደል ፍርሃትን ሰማይ ጥግ አውጥቶታል። እናም ኢትዮጵያዊ በየተበተነበት ሁሉ ተኛ ሲሉት የሚተኛ አውልቅ ሲሉት እርቃኑን የሚቆም ፈሪ እንዲሆን ተደርጓል። ሲቸግረው የሚጮኸውን ያህል ሲመቸው ለወገን የሚደርሰው ጥቂቱ ነው። ይህ ሊቀጥል አይገባም!

ቀደም ባለው ጊዜ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥቃት ቢደርስበት ባገኘው መሳርያ ዘነጣጥሎም ቢሆን ይገድል ስለነበር ማንም አይደፍረውም ነበር። በዘመነ ኮሎኒያሊዝም ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ አንገት የማይደፉና ክብራቸውን የማያስነኩ ነበሩ። ዛሬ ጠቁመው የሚያስይዙ፣ ወገናቸውን የሚያሻሽጡና የሚሰልሉት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የዚህ ጽሁፍ መነሻም ሆነ መድረሻው የድሮውን አሁን እየሆነ ካለው ጋር ማወዳደር አይደለም። ለዚህ የሚሆን የቅንጦት ጊዜም የለንም። ዓላማው አሁን እየደረሰብን ያለውን በደል በቁርጠኛነት አንታገለው ነው። ይህ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ከዳር እስከዳር ማስነሳት ካልቻለና ቁጣቸውንም ለመላው አለም ማሳየት ካልቻለ እውነትም አገራችን እያበቃላት ነው ማለት ይቻላል።

የዱር አውሬ እንኳን ከዚህ የተሻለ ክብር አለው። እነዚህ አጅግ ሁዋላ ቀር የሆኑ አረመኔዎች ከእንስሳ እንኳን አንሰው አንዲት በፍርሃት ነብሷን የሳተችን ሴት አስር ሆነው የሚደፍሩትን እያየን የተደፈሩት ህጋዊ ናቸው ህገወጥ የሚል የሕግ አንቀጽ መረጣ ውስጥ ልንገባስ እንዴት ይቻለናል? በመላው አለም ያለ የሳዑዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ ሊደረግና የሳዑዲ ወሮበሎች በወጣት ሴቶች ላይ እያደረሱ ያለው ግፍ በመረጃም ተደገፎ በበራሪ ወረቀትም ተዘጋጅቶ ለአለም ሕዝብ ሊበተን ይገባዋል። ተፈጥሮ ዘይትን ስትቸራቸው አእምሮ ግን እንደነፈገቻቸው ከዚህ በላይ መረጃስ ከየት ይመጣል?
እንደ ትውስታ ከወሰድነው በኬንያ ያሉ ስደተኞች ላይ በደል ይደርስ በነበረበት ወቅት ያ በጨካኝነቱ የሚታወቀው መንግሥሰቱ ሀይለማርያም አንኳን “ኢትዮጵያውያኑ የተሰደዱት የምናራምደውን ፖለቲካ እንጂ ሀገራቸውን ጠልተው አይደለም…” በሚል ኬንያን ማስጠንቀቁን መስማቴ ትዝ ይለኛል። በየወሩ 40 ሺህ ሴቶችን እንልካለን እያለ እንደ እንቁላል በየአረብ ቤቱ ሲያከፋፍል የነበረው መንግስት ዛሬ ዜጎቹ እንዳይሆን መጫወቻ ሲሆኑ ዝም ብሎ መመልከቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ኢትዮጵያውያኑ ምናልባትም ኤምባሲውን ራሱን መቆጣጠር የሚገባቸው እስኪመስል ያስቆጣል።
Image
በኢትዮጵያዊነት ላይ የተነጣጠረን ክፋት እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ካላስቆምነው በሳዑዲ የተጀመረው መረን የጥላቻ ሰደድ ሊቀጣጥል የሚችልና የየሀገሩ የፖለቲካ ኪሳራ ማስተንፈሻ የሚሆነው አገር አጥቶ የተሰደደው ኢትዮጵያዊው ላይ ሁሉ ይሆናል። ይህንን በአስቸኳይ ለመቃወም ያሉ የትግል መንገዶች ሁሉ ክፍት ሊሆኑ ይገባል። እኔ አዘጋጀሁ እኔ ጠራሁ የሚል ደካማ የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ መንቀሳቀስ ሳይሆን ለሰብዓዊ ክብርና የመከራ ማጥ ውስጥ ሆነው የወገን ያለህ ለሚሉት እህት ወንድሞቻችን የድረሱልን ጥሪ ምላሽ እንስጥ። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኞቹ ለስራ የሚሄዱት ወጣቶች የትምህርት ደረጃቸው አነስተኛ የሆነና በድህነት ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት የሆነው ይሁን ብለው ከቤታቸው የወጡ ናቸው። አንዳንዶቹም ግሩም እድል አንደሚገጥማቸው በደላላዎች እየተነገራቸው ከቤት ወጥተው የቀሩ ናቸው። ለኒህ አጋር መሆን ለሀገር እንኳን ደንታ ባይኖረን ለነብስ የሚበጅ ስራ ነው። የኢትዮጵያ ኮሙኒቲዎች፣ በኢትዮጵያ ስም የተቋቋሙ የሀይማኖት ማዕከላት፣ ሲቪክ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ ለዚህ ዓላማ ቢቻል አደራጆች ካልተቻለም ዋንኛ ተሳታፊዎች ሊሆኑ ይገባል። ይህ በደል እጅ ለእጅ ሊያስተሳስረንና አንድ ላይ እንድንቆም ሊያደርገን የሚችል የጋራ ጉዳይ ነው። ዛሬ ነገ ሳንል በተደራጀና አለም አቀፍ ትኩረት ሊኖረው በሚያስችል አቅሙ እንነሳ ለወገንም አንድረስ።የመከራ ቀናችንን ለማሳጠር እንደ ሕዝብም ከአንገታችን ቀና እንድንል በያለንበት እንትጋ!

የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል!
===========
በኃይሉ አርአያ (ዶ/ር) – የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት አባል

ሰሞኑን የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል አይፈራም የሚል ጉዳይ ከፓርላማ ተነስቶ ወደ መገናኛ ብዙኃንም ደርሷል። ጉዳዩ የተነሳው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ አዲሱ ፕሬዚዳንታችን በፓርላማ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ

ባቀረቧቸው የማማሻሻያ ሐሳቦችና ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡት ምላሽ ዙሪያ ነው። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዝ ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓም በአወጣው ዕትሙ ‹‹’ፈሪ’ መንግሥት?›› በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ ጥሩ ትንተና አቅርቧል። የፍርኃት ነገር ከተነሳ ጋዜጠኛው ያነሳውን ለማዳበር በእኔም በኩል የምለው አለኝ። የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል። የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል ስል ግን በደፈናው አይደለም። በርካታ የማይፈራቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ጦርነትን አይፈራም። በተለይ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ጥርሱን ነቅሎ ያደገበት ጉዳይ ነው። ሕግ መጣስን አይፈራም። ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መጣስን አይፈራም። መዋሸትን አይፈራም።

የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል ስል በተለይ የማተኩረው በአንድ ጉዳይ ላይ ነው። እውነት ላይ። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ይፈራል። እውነትን ስለሚፈራ እሱ ራሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲታወቅ ከሚፈልገው ውጪ ሕዝቡ እውነቱን እንዲያውቅ አይፈልግም። ይህ ደግሞ የአምባገነን አውራ ፓርቲዎች መንግሥታት አንዱና ዋናው የደባቂነትና የሸማቂነት መገለጫ ባህሪ ነው። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ለመፍራቱ በርካታ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለጊዜው ግን አራቱን ብቻ በምሳሌነት እንደሚከተለው ልጥቀስ።

1. ከቅርቡ የሶማሊያ ጦርነት ጋር በተያያዘ የእውነት መረጃን ከሕዝብ መደበቁ

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጎረቤት ሶማሊያ ውስጥ ገብቶ ከአክራሪና ከሽብር ኃይሎች ጋር ተዋግቷል። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ አሁንም እየተዋጋ ነው። ከማን ጋር ነው የተዋጋውም ሆነ የሚዋጋው? ለምንድን ነው የተዋጋው/የሚዋጋው? ጣልቃ ገብነቱ ሕጋዊ ነው አይደለም? ወደሚሉት ውስብስብ ጥያቄዎች አልገባም። እኔ የምገባው ወደ እውነት መረጃ አስፈላጊነት ነው። ጦርነት ነውና ወታደሮች ሞተዋል፣ ቆስለዋል። ገንዘብ ወጪ ሆኗል። የሞቱት የሕዝብ ልጆች ናቸው። ወጪ የሆነው የሕዝብ ገንዘብ ነው። ጦርነቱ የተካሄደው በውጭ ዕርዳታ ገንዘብ ነው እንዳልል፣ ነፍሳቸውን ይማርና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን አቶ መለስ ዜናዊ ጦርነቱን በተመለከተ ፓርላማ ፊት በመቅረብ የአውራ ጣታቸውንና የሌባ ጣታቸውን ጫፎች አነካክተው ዜሮን በማሳየት ‹‹ሳንቲም ዕርዳታ አላገኘንም›› ማለታቸውን አስታውሳለሁ።

የሞቱት የሕዝብ ልጆች ናቸውና የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት ልጆቹ እንደሞቱ እውነቱን ለማወቅ ይፈልጋል። እውነቱን የማወቅ መብትም አለው። የወጣው የሕዝብ ገንዘብ ነውና ሕዝቡ ያወጣውን ለማወቅ ይፈልጋል። እውነቱን የማወቅ መብትም አለው። እኔ እስከማውቀው ድረስ በተለይ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ የኢሕአዴግ መንግሥት የጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ሕዝብ በይፋ የሰጠው መረጃ የለም። ምናልባት ለአሜሪካ፣ ለአፍሪካ ኅብረትና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ‹‹እኔ እንደ መንግሥት እየከፈልኩ ያለሁትን መስዋዕትነት ዕወቁልኝ›› በሚልና የባለውለተኛ ወሮታ ለማግኘት በሚስጥር አሳውቆ ሊሆን ይችላል። ይህ መደረጉ አይከፋም። መጀመሪያ መስማት ያለበት ግን ባለጉዳዩ ሕዝብ ነው። ለምንድን ነው ባለፈው እውነታውን ለሕዝብ ያላሳወቀውና አሁንም ቢሆን የማያሳውቀው? እውነትን ስለሚፈራ ነው። መደበቅና መሸመቅ ዓይነተኛ ባህሪው ስለሆነ ነው። ለሕዝብ የማወቅ መብት አክብሮት ስለሌለው ነው።

ጦርነቱን በበጎ ጎኑ አይተነው፣ ሠራዊታችን ሶማሊያ የገባው ሉዓላዊነታችንን ላለማስደፈር፣ ድንበራችንን ለማስከበር፣ የአገራችንንና የአካባቢያችንን ሰላም ለመጠበቅና ከዚያም ባለፈ የዓለማችንን ሰላም ለማስከበር ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው እንበል። ታዲያ እንደዚህ ላለ ‹‹የተቀደሰ›› ዓላማ የተከፈለን መስዋዕትነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀርቶ ዓለም እንዲያውቀው ይደረጋል እንጂ ይደበቃል?

ይህን አጭር ጽሑፍ ለማዘጋጀት ሳስብ እስቲ አሜሪካ በቪየትናም ጦርነት የሞቱባትን ወታደሮች ለሕዝብ በይፋ አሳውቃ እንደሆነ ልይ ብዬ ኢንተርኔት ውስጥ ገባሁ። “Us Soldiers Killed in Vietnam” በሚል ‹‹ጉግል›› ሳደርግ ያገኘሁት መረጃ ብዛትና ዝርዝር የሚገርም ነው። በአጭሩ ግን 58,220 ወታደሮች እንደሞቱ፣ የሟቾቹ ቁጥርም በዘር፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በመጡበት ‹‹ስቴት››፣ በሠራዊት ምድባቸው (አየር ኃይል፣ ምድር ጦር፣ መርከበኛ፣ ወዘተ.)፣ በአሟሟታቸው ሁኔታ (በውጊያ፣ በድንገተኛ አደጋ፣ በሕመም፣ እርስ በርስ መገዳደል፣ ወዘተ.)፣ በጦርነቱ መጀመሪያ የሞተ ወታደር ስም፣ ጦርነቱ ሊፈጸም ሲል በመጨረሻ የሞተ ወታደር ስም፣ ወዘተ፣ ተዘርዝሮ ተቀምጧል። በተመሳሳይ ሁኔታ የኢራቅንና የአፍጋኒስታንንም አየሁ። መረጃው ከሞላ ጎደል በታመሳሳይ ሁኔታ ተቀምጧል። ወጪ የሆነው የገንዘብ መጠን ሁሉ ተቀምጧል። ከዚያ በኋላ እስቲ መንግሥታችንም ምናልባት ሳናውቀው መረጃ አስቀምጦ እንደሆን ብዬ ለማየት ሞከርኩ። የውጭ ጋዜጦችና ሌሎች የዜና ምንጮች በዜና መልክ ካስቀመጧቸው ጥቂት ተባራሪ መረጃዎች በስተቀር ምንም ነገር የለም።

ለምንድን ነው የአሜሪካ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱትን ጦርነቶች በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለሕዝቡና ለተቀረው ዓለም ሲሰጥ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሊያ ያካሄደውን ጦርነት በተመለከተ መረጃ ትንፍሽ ያላለው? ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ብዙ ማለት ይቻላል። በአጭሩ ግን የአሜሪካ መንግሥት መረጃ የሰጠው እውነትን ስለማይፈራ ነው። በራሱ ስለሚተማመንና ሕዝቡንም ስለሚያምን ነው። የሕዝቡን መረጃ የማግኘት መብት ስለሚያከብር ነው። የኢሕአዴግ መንግሥት መረጃ ያልሰጠው በእኔ እምነት እውነትን ስለሚፈራ፣ በራሱ ስለማይተማመንና ሕዝቡንም ስለማያምንና መረጃ የማግኘት መብቱንም ስለማያከብር ነው።

በዲሞክራሲ የዳበሩ መንግሥታት ምንጊዜም እውነትን አይፈሩም፣ አይደብቁም፣ አይሸምቁም ማለቴ አይደለም። አልፎ አልፎ እውነትን ይፈራሉ፣ ይደብቃሉ፣ ይሸምቃሉ። ሆኖም እውነትን መፍራት፣ መደበቅና መሸመቅ እንደ አምባገነን መንግሥታት ዓይነተኛና መገለጫ ባህሪያቸው አይደለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ በእነዚህ አገሮች ውስጥ ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ነፃና ጠንካራ ፕሬስ፣ ነፃና ጠንካራ ሲቪክ ማኅበራትና ንቃተ ህሊናው የዳበረና ለመብቱ ቀናዒ የሆነ ሕዝብ ስላሉ እውነትን የሚፈራ፣ የሚደብቅና የሚሸምቅ መንግሥት ይዋል ይደር እንጂ ይጋለጣል። የአሜሪካው የዋተርጌትና የቢል ክሊንተን-ሞኒካ ለዊንስኪ ቅሌት እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጁሊያን አሳንጅና በኤድዋርድ ስኖውደን እንዲሁም በሌሎች ንቁና ተቆርቋሪ ዜጎች አማካይነት እየጎላ የመጣው የመረጃ ፍልፈላና ፍትለካ የዚህ አንድ ማስረጃ ነው። በዚህም ምክንያት ዲሞክራሲያዊ መንግሥታት እውነትን ከመፍራት፣ ከመሸመቅና ከመደበቅ ድርጊት በተቻላቸው መጠን ይቆጠባሉ። በአምባገነን ሥርዓት ግን የመንግሥት ፕሬስ አድር ባይ በመሆኑ፣ ነፃው ፕሬስ፣ ተቃዋሚዎችና ሲቪክ ማኅበራት ደካሞች በመሆናቸው፣ ሕዝቡም የታፈነና በፍርኃት ድባብ ውስጥ የሚኖር በመሆኑ መረጃ የመፈልፈልና እንዲያፈተልክ የማድረግ አቅም ያንሳቸዋል። ስለዚህ መንግሥት በእነዚህ ኃይሎች ድክመት ምክንያት በማናለብኝነት እንደፈለገው ይሆናል፣ እንደፈለገው ያደርጋል።

2. የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንን በሞኖፖል መያዙ

የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን የሚፈራ ለመሆኑ ሌላው ዋና ማስረጃ በሕዝብ ገንዘብ የሚሠሩ መገናኛ ብዙኃንን (ጋዜጣ፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን) በሞኖፖል መያዙ ነው። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ ‹‹ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሐሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሠራር ነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል፤›› ይላል። በተጨማሪ በዚሁ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 5 ‹‹በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አመለካከቶችን ለማስተናገድ በሚያስችል ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል፤›› ይላል። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ከመፍራቱ የተነሳ በእነዚህ ንዑሳን አንቀጾች ውስጥ የተካተቱ መሠረታዊ መብቶች ፍርክስክሳቸውን አውጥቶታል። ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሐሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ይፈራል። እውነትን ይፈራል። ለዲሞክራሲ ሥርዓት መልካም አሠራር ሲባል የተለያዩና ጥርስ ያላቸው አስተያተቶች ማስተናገድን ይፈራል። ከመፍራቱ የተነሳ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንን ዘግቶ ይዟል።

አልፎ አልፎ የተለያዩ አስተሳሰቦችን ያቀረበ ለማስመሰል በቤት ልጆች እዚያው ተፈጭተው፣ እዚያው ተቦክተው፣ እዚያው ተጋግግረው የሚቀርቡ ፕሮግራሞችን ያይራል (Air) ያደርጋል። በምርጫ ሰሞንም ነፃነት ያለ ለማስመሰል የሚዲያ በሩን ለስሙ ገርበብ አድርጎ በመክፈት የተለያዩ ሐሳቦች ይቀርባሉ ለማስባል ይሞክራል። በዚህም ቢሆን የቀረቡ ሐሳቦችን በቅድሚያ ቀርፆ የሚፈራቸውን ሐሳቦች ቆርጦ (ሳንሱር አድርጎ) ነው የሚያቀርበው። በጋዜጣና በሬዲዮ የሚቀርቡ ሐሳቦችን ደግሞ ‹‹ይህን ካላስወጣችሁ››፣ ‹‹ይህን ካላስተካከላችሁ›› እያለ በቅድሚያ ሳንሱር የማያላውስ እንቅፋት ይፈጥራል። እንደ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አካሄድ ከሆነ፣ እንዲሁም በጎረቤትና በሩቅ አገሮችም እንደሚታየው ከሆነ ብዙ የግልና ነፃ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም ጋዜጦች መኖር ነበረባቸው። የመንግሥት የሚባል ቴሌቪዥንም ሆነ ሬዲዮ መኖር አልነበረበትም። ትላልቅ የሚባሉ፣ በዲሞክራሲ የዳበሩና በራሳቸው የሚተማመኑ አገሮች የቴሌቪዥንም ሆነ የሬዲዮ ጣቢያዎች የሏቸውም። (ያሏቸው የሉም ማለት ግን አይደለም)። የእኛ መንግሥት ግን ሲጀመርም እውነተኛ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር ስላልተዋሀደው፣ እንዲሁም በግል ቴሌቪዥና በግል ሬዲዮ ጣቢያዎች ሊንሸራሸሩ የሚችሉ እውነታዎችን ስለሚፈራና እውነትን በእውነት ለመጋጠም ችሎታውም፣ ድፍረቱም ስለሌው እነዚህ ተቋማት እንዳይኖሩ ከልክሏል። ተረጋግተው፣ በነፃነታቸው ተማምነው የሚሠሩ ነፃ ጋዜጦችም የሉም ማለት ይቻላል። ስለዚህ ሥራዬ ብሎ የመረጠው መንገድ የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃንን የሕዝብን የተለያየ መረጃ የማግኘት መብትን በሚፃረር ሁኔታ በሞኖፖል በመያዝ እሱ የመረጠውን እውነታ ብቻ፣ እሱ በመረጠው ጊዜና መንገድ ለሕዝብ ማንቆርቆር ነው። የዚህ ዓይነት መንገድ የፍርኃት አካሄድ ነው።

ጽጌረዳና ዲሞክራሲ አንድ ናቸው። ጽጌረዳ አበባዋ ውብ ነው። ከውብ አበባዋ ጋር ግን እሾህ አላት። እሾሁ የተፈጠረው ለክፉ ነገር አይደለም። የአበባዋን ውበት ከጉዳት የሚጠብቅ የተፈጥሮ መከላከያ ነው። እሾሁም የውበቷ አካል ነው። ስለዚህ ጽጌረዳን ስንወድ የተፈጥሮዋ አካል ከሆነው ከእሾህዋ ጋር ነው። ዲሞክራሲም ‹‹እሾህ›› አለው። የዲሞክራሲ ‹‹እሾህ›› ነፃነቱ፣ ሙያዊ ብቃቱና ትጋቱ ካለው ፕሬስ፣ ብቃቱና ቁርጠኝነቱ ካላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ነፃነቱና ጥንካሬው ካላቸው ሲቪክ ማኅበራት፣ ንቃቱ ካላቸው ዜጎች የሚሰነዘሩ ገንቢና ሂሳዊ እውነታዎች ናቸው። የኢሕአዴግ መንግሥት ከእነዚህ አቅጣጫዎች የሚመጣውን እሾህ ስለሚፈራ እውነተኛ ዲሞክራሲን በሩቁ ብሏል።

3. ኢትዮ ተሌኮምን በሞኖፖል መያዝ

ቴሌኮሙዩኒኬሽን በዘመናዊ መልኩ ቴክኖሎጂ የወለደው የእውነት መረጃ መንሸራሸሪያ ጎዳና ነው። በሌላው ዓለም እንደ ፀጋና እንደ ልማት መሣሪያ ሲወሰድ በአምባገነን ሥርዓቶች ግን እንደ አደገኛ መሣሪያ ይወሰዳል። በዚህ ምክንያትም በአገራችንም ይህን ‹‹አደገኛ›› መሣሪያ ለመቆጣጠር ሲባል መንግሥት በሞኖፖል ይዞታል። መንግሥት እንደሚለው ኢትዮ ቴሌኮምን በሞኖፖል የያዘው ለልማት የሚውል ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ (‹‹የምትታለብ ላም››) ስለሆነ ብቻ አይደለም። የመረጃ መንሸራሸሪያ ጎዳናና የእውነት ምንጭ ስለሆነ ነው። እንዲያውም የኢሕአዴግ መንግሥት ኢትዮ ቴሌኮምን በሞኖፖል ለመያዙ ዋናው ምክንያት የከፍተኛ ገንዘብ ምንጭ ከመሆኑ ይልቅ የመረጃ መንሸራሸሪያ፣ የሕዝብ መገናኛና የእውነት ምንጭ የመሆኑ ፍራቻ ነው ብዬ አምናለሁ። የኢሕአዴግ ምንግሥት መረጃ ኃይል የመሆኑን እውነታ ጠንቅቆ ያውቃል። ይህንን እውነታ ይፈራል።

4. በአሳሪና አስፈሪ ሕጎች ራሱን ማጠሩ

የኢሕአዴግ መንግሥት ዙሪያውን በአስፈሪና አሳሪ ሕጎች በማጠር የእውነት ፍርኃቱን ለመቀነስ ይሞክራል። የእውነት መምጫ መንገዱ ብዙ ነው። ለምሳሌ በነፃ ፕሬስ አማካይነት ይመጣል። በጠንካራ ሲቪክ ማኅበራት አማካይነት ይመጣል። የጠያቂነትና የለምን ባይነት መንፈስ ባላቸው ዜጎች አማካይነት ይመጣል። እውነትን የሚፈራው የኢሕአዴግ መንግሥት አንዱ ዋነኛ ሥራው ሆኖ የተገኘው የእውነት መንገዶችን የሚዘጉ አስፈሪና አሳሪ አዋጆችን ማውጣት ነው። ነፃው ፕሬስ የእውነት መምጫ መንገድ እንዳይሆን በአሳሪና አስፈሪ የፕሬስ አዋጅ ታጥሯል። ሲቪክ ማኅበራት የእውነት መምጫ መንገዶች እንዳይሆኑ በሲቪክ ማኅበራት አዋጅ ታስረው እንዲሽመደመዱ ተደርገዋል። የጠያቂነትና የለምን ባይነት መንፈስ ያላቸው ዜጎች የእውነት መንገድን እንዳያሳዩ በሽብር ሽፋን በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ እንዲሸማቀቁ ተደርገዋል። ከዚያም ባለፈ ወደ ወህኒ እንዲወርዱ የተደረጉም አሉ።

ኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ሥጋት የለባትም ማለት አይደለም። የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ ስታወጣም የመጀመሪያ አገር አይደለችም። ሌሎች አገሮችም አውጥተዋል፣ በተለይ በዲሞክራሲ የዳበሩ አገሮች። ትልቁ ጥያቄ ‹‹የወጣው ፀረ ሽብር አዋጅ በማን እጅ ነው? በምን ዓይነት መንግሥት እጅ ነው?›› የሚለው ነው። በዲሞክራሲ በዳበሩ አገሮችና በእኛ አገር ያለው ሁኔታ የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል። በዲሞክራሲ የዳበሩ መንግሥታት ራሳቸው የዜጎቻቸው መብቶች እንዳይነኩ በከፍተኛ ደረጃ የሚጨነቁ፣ የሚጠበቡና የሚጠነቀቁ ናቸው። አርባ ዓመት ለመግዛት ዕቅድ በማውጣት ቸክለው የተቀመጡና ሥልጣናቸውን ለመከላከል ከፀሐይ በታች ባለ በማንኛውም ዓይነት ስልት ከመጠቀም ወደ ኋላ የማይሉ አይደሉም። የፍትሕ ተቋሞቻቸው ነፃ ናቸው፣ የአስፈጻሚ አካላት ትእዛዝ ፈጻሚዎች አይደሉም። ፖሊሶቻቸውና የደኅንነት ሰዎቻቸው በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠኑ፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች የሚያከብሩ፣ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ሕግን በሚገባ የሚያውቁና የሚያከብሩ ናቸው። ስንዝር ሥልጣን ሲሰጣቸው ክንድ የሚወስዱ አይደሉም። ፀረ ሽብር አዋጆቻቸውም በአመዛኙ የሚያተኩሩት ከውጭ በሚመጡ አደጋዎች ላይ ነው። በእኛ አገር በአሁኑ ጊዜ የአዋጁ ዋና ሰለባ የሆኑት በአመዛኙ የአገሪቱ ዜጎች ናቸው። ስለዚህ የኢሕአዴግ መንግሥት በፀረ ሸብር ሽፋን አዋጁን ተቃዋሚዎችንና የጠያቂነትና የለምን ባይነት መንፈስ ያላቸውን ዜጎች ለማጥቃትና በአጠቃላይ ሕዝቡን ለማሸማቀቅና ለማሸበር በመሣሪያነት ይጠቀምበታል የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለ።

የኢሕአዴግ መንግሥት አፈ ቀላጤዎች ‹‹የፀረ ሸብር ሕጉን የሚፈሩት ሕገወጦች ብቻ ናቸው›› ይሉናል። አዎ፣ እውነት ነፃ በምታወጣበት አገር አባባሉ ያስኬዳል። በእኛ አገር ግን እውነት ነፃ ታወጣለች ብሎ መተማመን አይቻልም። በዚህ ምክንያት ንፁኃን ዜጎችም ፀረ ሽብር ሕጉን ይፈራሉ፣ ሽብርተኞች ሆነው ግን አይደለም። ዜጎች ሽብርተኝነትን ያወግዛሉ። የሚፈሩት የኢሕአዴግ መንግሥት አዋጁን እንደሚፈልገውና እንደሚያመቸው በመለጠጥ ያለ ኃጥያታችን ሊወነጅለንና ሊጎዳን ይችላል ከሚል ሥጋት በመነሳት ነው። ሥጋታቸው ደግሞ ያለመሠረት አይደለም። እንግዲህ የኢሕአዴግ መንግሥት ከነፃው ፕሬስ፣ ከነፃና ጠንካራ ሲቪክ ማኅበራት እንዲሁም የጠያቂነትና የለምን ባይነት ባህሪ ካላቸው ዜጎች የሚመጣ እውነትን ለመከላከል በተደራራቢ አዋጆች ዙሪያውን አጥሯል። ይህ ደግሞ እውነትን ለመፍራቱ ግልጽ ማሳያ ነው። ለመሆኑ የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን መፍራትና መበርገግ የጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው? መፍራት የጀመረው እውነትን ፊት ለፊት ያየ ዕለት ነው። ያ ዕለት ደግሞ ሚያዝያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም. ነበር። በዚያን ዕለት ያየውን እውነት በሳምንቱ ግንቦት 7 ቀን 1997 ደግሞ አየው። ይህ ዕለት ደግሞ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሳይሆን በሕዝብ ድምፅ መሸነፉን የተረዳበትና ይበልጥ የበረገገበት ዕለት ነበር። የአቶ መለስ ዜናዊ የግንቦት 7 ምሽት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም የዚህ መበርገግ ዓይነተኛ ምልክት ነበር። ከእነዚህ የእውነት ቀናት ጀምሮ እስካሁን ድረስ የኢሕአዴግ መንግሥት እንደበረገገ አለ። የእነዚያን ቀናት የሽንፈት እውነታ ዳግም ላለማየት የማይፈነቅለው ድንጋይ፣ የማይወስደው ዕርምጃ፣ የማያወጣው ግልጽም ሆነ ስውር መመርያ፣ የማይቀይሰው ስትራቴጂ፣ የማይደነቅረው መሰናክል፣ የማያወጣው ወጪ፣ የማይጥሰው እሴት የለም። በምርጫ የመሸነፍ እውነታን ሲያስበው ስለሚያስበረግገው፣ ለ2007 ምርጫ ዝግጅት የጀመረው በ2002 ምርጫ ማግሥት ነው። የ2002 ምርጫ ዝግጅት የጀመረው በ1997 ምርጫ ማግሥት ነው። (ይህ አካሄድ በእንድ ጎኑ ሲታይ የሚደነቅ ነው። ምርጫ ወራት ብቻ ሲቀረው የሚንደፋደፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከዚህ ብዙ ትምህርት ሊቀስሙ ይችላሉ፣ እስካሁን አላደረጉትም እንጂ)።

ለማጠቃለል የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል። አልፈራም ካለ አለመፍራቱን በድርጊቶቹ ያሳይ። በሶማሊያ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ የከፈለውን መስዋዕትነት በተመለከተ ትክክለኛና ይፋዊ መረጃ በመስጠት የሕዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ያክብር። የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንን ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች (እውነተኛ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ) ለሚመጡ ሐሳቦች መንሸራሸር በአምስት ዓመት አንድ ጊዜ ሳይሆን ዓመቱን በሙሉ ክፍት ያድርግ። በተጨማሪ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉንና ኢትዮ ቴሌኮምንም ለግሉ የንግድ ዘርፍ ክፍት ያድርግ። አሳሪና አስፈሪ ሕጎችን በመሰረዝ ወይም በማሻሻል እንደ ምሽግና እንደ ማጥቂያ መሣሪያ መጠቀምን ያቁም። የኢሕአዴግ መንግሥት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ ለውጥ ካላመጣ አሥር ጊዜ በቃል ‹‹አልፈራም!›› ቢልም እውነትን ለመፍራቱ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ተጽፈው የሚታዩ ጉልህና ተጨባጭ ማስረጃዎች ሆነው ይቀጥላሉ።
Image

Image
Getachew Shiferaw VIA Minilik Salsawi
ከጓደኞቼ ጋር በጠየቅነው ወቅት እንድናስተላልፍ አደራ ብሎናል፡፡ ድምጻችን ይሰማዎች ሆይ! እስክንድር አድንቋችኋል፡፡ ከሁለትና ሶስቱ ውጭ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው የሚውሉት ከ70 በላይ ፓርቲዎች ጉዳያችን አይደለም ቢሉትም እስክንድር ግን ቃሊት ሆኖ እያንዳንዱን እንቅስቃሴያችሁን ይከታተላል፡፡

መልዕክቱንም እንዲህ አስተላልፏል፡፡ ‹‹ድምጻችን ይሰማ ብለው የተነሱት ወጣቶቻችን ለፖለቲካው እንቅስቃሴም ትልቅ ተምሳሌት ናቸው፡፡ ሌላው ማህበረሰብም ሊደግፋቸው ይገባል፡፡ ወጣቶቹ ኢትዮጵያ ውስጥም አምባገነንን ሊያስጨንቅ የሚችል ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደሚቻል በቀላሉ አስመስክረዋል፡፡ መብቱን በቀላሉ አሳልፎ የማሰጥ ወጣት እንዳለው አሳይተዋል፡፡ እስኪ አስቡት ይህ የወጣት እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ቢሆን ምን ታዕምር ሊፈጥር እንደሚችል? እውነቴን ነው የምላችሁ ፓርቲዎችን ጨምሮ በፖለቲካው ዘርፍ እንቀሳቀሳለሁ የሚል አካል ድምጻችን ይሰማን ሞዴል ማድረግ ይኖርበታል››፡፡

እስክንድር እውነት አለው፡፡ እኔ በበኩሌ የማይዋዥቅ እንቅስቃሴ ያየሁት ድምጻችን ይሰማን ነው፡፡ ለሌላኛው የፖለቲካ እንቅስቃሴም ቢሆን ቀላል የማይባል ድምቀት ሰጥቶታል፡፡ በፖለቲካው ዘርፍ ብቻ ያተኮረው እንቅስቃሴን በተለይ በፌስ ቡክ በቅርብ አመታት ጠንከር እያለ ቢሆንም አጀንዳ ቀረጻው፣ አደረጃጀቱና እንቅስቃሴው አዝጋሚ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ሲኖር፣ ባለሰልጣናት ሲመረጡ፣ ሲሻሩ፣ ሙስና ተከሰተ፣ መሬት ተሸጠ ሲባል ዜና ማስተላለፍ፣ ወቅታዊ ጉዳይን ማስተላለፍ ላይ የተጠመደ ነው፡፡ በእርግጥ ይህም አንድ በጎ ጅምር ነው፡፡

ሆኖም ትኩስ ጉዳይ ካላገኘ እንደገና ይቀዘቅዛል፡፡ አንዱን አጀንዳ ጥሎ ሌላ ከማንሳት ያለፈ ዳር የማድረስ ችግር ይታይበታል፡፡ ቀደም ብሎ የያዘው ጉዳይ (እስራት፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ሙስና……) ዳር ሳይደርስ ሌላ አዲስ ወሬ ከመጣ ዋና አስመስሎት የነበረውን አጀንዳ በትኖ አዲሱን ይቀበላል፡፡ ያው ዋና አጀንዳው አልነበረውም ማለት ነው፡፡ አሊያም አጀንዳ ለመያዝ አቅም አልነበረውም፡፡ በዚህ ረገድ ድምጻችን ይሰማ የተለየ ነው፡፡ ኳስም ይኑር ሩጫ፣ ሙስናም ይሁር ሹምሽር በድምጻችን ይሰማ ሰፈር የሙስሊሙ ጉዳይ፣ የኮሚቴዎቼ ዜና አይደበዝዝም፡፡ በፖለቲካው ጉዳይ ግን በወረት አጀንዳዎች ዳር ሳይደርሱ ሌላኛውን ማንሳት የተለመደ ነው፡፡ አዲስ ዜና ያጠቃናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለጭቆና ራሱን መስዕዋት ያደረገውን የኔሰው ገብሬን እያስታወስነው አይደለም፡፡ ውብሸት ታዬን እኛ እረስተነው ያስተወሱት ፈረንጆቹ ናቸው፡፡ ከክልል የሚባረሩት ኢትዮጵያውያን የአንድ ሰሞን ጉዳይ ነው፡፡ ታሰረ፣ ተፈታ፣ ተገደለ፣ ሙስና…….ዜና ሆነው ያልፋሉ፡፡ ከሳምንት በኋላ በሳውዲ የሚሰቃዩትን ዜጎቻችንን ጉዳይ ረስተን ሌላ ጉዳይ እናነሳለን፡፡ ከዋናው ጉዳያችን ልቅ የኢህአዴግ ካድሬዎች የሚያነሷቸው ማስቀየሻዎች ላይ በርካታ ጊዜያችን እንገድላለን፡፡ እንደገና ሌላ ዜና ይመጣል፡፡

እኔ እንደሚመስለኝ ዋናው ችግራችን የተበታተንን በመሆናችን ነው፡፡ ፌስ ቡኩንም ሆነ ሌላውን እንቅስቃሴ በተደራጀ መለኩ፣ በሙያ፣ በስነ ምግባር የሚመራው አልተገኘም፡፡ ዲያስፖራውና አንዳንድ ፓርቲዎች አካባቢ የሚገኙ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች (በግል) ብቻ እንቅስቃሴ የትም ሊያደርሰው አይችልም፡፡ ማህበራዊ ድህረ ገጹ፣ ፖለቲካ እንቅስቃሴው የመሪ ያለህ እያለ ነው፡፡

በ1960ና 70ዎቹ ትውልድ በብጫቂ ወረቀት፣ በመልዕክተኛ፣ አልፎ አልፎም በቤት ስልክ ተገናኝተው ለራሳቸው ሳይሆን ለሰፊው ህዝብ ታግለዋል፡፡ በዛን ወቅት ፌስ ቡክ ቢኖር በየ ካፌና ጠባብ ቤቶች ተሰብስቦ የራሱን አገራዊ ፖሊሲ መቅረጽ የቻለው ያ ትውልዱ ምን ያህል ሊጠቀምበት ይችል እንደነበር መገመት አያዳግትም፡፡

ይህ ግን የአሁኑ ትውልድ በአጠቃላይ ችግር እንዳለበት የሚያሳይ አይደለም፡፡ ጥቂቶችም ቢሆኑ የአሁኑ ትውልድ በሙሉ የባከነ እንዳልሆነ እያሳዩን ነው፡፡ ድምጻችን ይሰማን በዚህ በፈዘዝነው መካከል ሆኖ መደራጀት፣ መጠየቅ፣ አጀንዳና ማንሳትና ዳር ማድረስ፣ አምባገነንን ማስጨነቅ ችሏል፡፡ ስለሆነም ድምጻችን ይሰማን መመልከቱ አዋጭ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ድምጻችን ይሰማ ሆይ! የኢትዮጵያውያን ድምጽ ጮህ ብሎ ይሰማ ዘንድ እናንተም አርዕያነታችሁን ተወጡ፡፡

የድሮው ትውልድ ፍልስጤም ድረስ ተጉዞ ሰልጥኗል፡፡ የሌሎች አገር ዜጎች እንኳን ስል አብዮት ብለው ኢትዮጵያ ድረስ መጥተው አሰልጥነዋል፡፡ አሁን ፌስ ቡክ የሚባል አውላላ ሜዳ ትልቅ ማሰልጠኛ ጣቢያ ሆኗል፡፡ እናም የዳሌ ምስል እየተከተለ ‹‹like›› የሚያደርገውን ወጣት፣ አንዱን ዜና ይዞ ሌላኛውን የሚያነሳውን፣ በአገር ጉዳይ አያገባኝም ብሎ ራሱን የሚሸነግለውን ስለ ትግል ስልት፣ ስል መደራጀት፣ ስለ አጀንዳ ቀረጻ ስልጠና ብትሰጡት፣ ‹‹ዱብ ዱብ›› እንዲል ብታደርጉት ምን ይመስላችኋል? —

በግንቦት 7 አና በአርበኞች መካከል ያለው ልዩነት እየጎላ መጥቷል:: ጀነራል ፍፁም አርበኞች ወደ ገንቦት 7 እንዲቀላቀል ግዳጅ ቢሰጥም ከአረበኞት ተቀባይነት አላገኘም:: በትናቸው(አንዳርጋቸው) ጥጌ በወያኔ የግድያ ሙከራ ተፈፅሞብኝ ነበር የሚለው ከሃቅ የራቀ አውነቱን ለመሸፈን የተደረገ ፕሮፓጋንዳ ነው:: ዋናው ቁምነገሩ አርበኞች በጉራጌና “በጋላ” (አንዳርጋቸው) አንመራም እያሉ ነው:: አርበኞች በብዛት ከጎንደር የመጡ ሲሆን ከመቶ አይበዙም:: ግንቦት 7 በአሁኑ ሰዓት ምላስ እንጂ ምንም ጡንቻ የለውም:: የአንዳርጋቸው ጥጌ የአስመራ ጉዞ ስኬታማ አልነበረም:: በአስመራ ያሉት የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በጎሪጥ ነው የሚተያዩት:: አይተማመኑም::

በእኛ አገር መንግስትና ፓርቲን መነጠል አይቻልም፡፡ህገ መንግስቱ ሳይቀር በብዙ አንቀጾቹ የገዢው ፓርቲ ፕሮግራም ግልባጭ መሆኑ ትስስሩን ላቅ ያደርገዋል፡፡ስለዚህ መንግስት ሲለወጥ ባንዲራ፣ህገ መንግስት፣ብሄራዊ መዝሙር እንቀይራለን፡፡የመንግስት ስርዓት መዘርጋት አለመቻላችን ያመጣብን ጣጣ ልንለው እንችላለን፡፡
ህዝቡ በፓርቲው እምነቱን አጣ ማለት መንግስትንም አያምነውም ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የመንገስታት ታሪክ አመኔታ በማጣት ረገድ ግምባር ቀደሙ ይመስለኛል፡፡እምነት የጠፋበት አጋጣሚም ከኢህአዴግ የትጥቅ ትግል ቆይታ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ደርግ የያኔዎቹን አማጺያን ወንበዴ፣አገር አስገንጣይ በማለት ይፈርጃቸው ነበር፡፡ከተሜው የደርግን ፕሮፓጋንዳ ሲጋት በመቆየቱ ተጋዳላዮቹ ወደ ከተማ ሲገቡ የተቀበላቸው በፍርሃት ድባብ ታስሮ ነበር፡፡
ትግራይን ነጻ ለማውጣት በረሃ የገቡት የትግራይ ልጆች የህዝቡን አመኔታ ለማግኘት የሐውዜንን ድብደባ ለደርግ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የቪዲዮ ካሜራ በማዘጋጀት የተዋጣለት ፊልም መቅረጻቸውና ለጊዜውም ቢሆን በዚህ ምክንያት የትግራይ ህዝብን ድጋፍ ለማግኘት ቢበቁም እያደር ግን የሐውዜን ምስጢር አፈትልኮ መውጣቱ ተአማኒነታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጥሯል፡፡በግሌ እምነት የሰጧቸው ዋና ዋና ተግባሮቻቸው የሚከተሉት ናቸው
—- በትግራይ መንግስት የወረሳቸውን ቤቶች በመመለስ ለሌሎቹም ይህንን እንደሚያደርጉ ቃል ቢገቡም ቃላቸውን መጠበቅ አለመቻላቸው
—- የአልባንያን ሶሻሊዝም ተጋዳላዮቹን ይግት የነበረው ኢህአዴግ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ከጫፍ በደረሰበት ወቅት የምዕራባዊያንን ድጋፍ ለማግኘት ራሱን ነጭ ካፒታሊስት በማድረግ መጥራት መጀመሩ ርዕዮት አልባ አድርጎታል፡፡ይህም በሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና አቋመ ቢስ ስላደረገው የገዛ ታጋዮቹን እምነት አሳጥቶታል፡፡
—–በበደኖ፣በአርባጉጉና በአሰቦት በተፈጸሙ አንድ ብሄር ላይ ያነጣጠሩ ጭፍጨፋዎች ኦህዴድና/ኦነግ ሃላፊነት በመውሰድ መጠየቅ ይገባቸው የነበረ ቢሆንም ኢህአዴግ የኦህዴድን እጅ እንደ ጲላጦስ በማጠብ የደሙን ዋጋ ኦነግ ላይ መጣሉ በኦሮሚያ አማኝ አሳጥቶታል፡፡
—– የመምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት የነበሩትን መምህር ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትን የ17 ዓመት እስራት ሲያከናንብ በዜና ያስደመጠው ‹‹ታጣቂ ቡድን እያደራጁ ነው››ብሎ የነበረ ቢሆንም በፍርድ ቤት ይህንን ማስመስከር አልቻለም፡፡
—–እነ ርዕዮት አለሙ በታሰረበት ቅጽበት ምሽቱን በኢቴቪ የተደመጠው ዜና ‹‹በመንግስት መሰረተ ልማቶች ላይ አደጋ ለማድረስ ሲያሴሩ ተገኝተዋል፡፡››ተብሏል፡፡ፍርድ ቤት ጋዜጠኞቹ በቀረቡበት ወቅት ግን በኢቴቪ የቀረበው በክሳቸው ውስጥ አልተካተተም፡፡ይህም አመኔታን የሚያሳጣ ድርጊት ሆኖበታል፡፡
—-የ1997 ምርጫን ነጻና ፍትሃዊ አደርጋለሁ በማለት ቃል የገባው ኢህአዴግ ለ200 ሰዎች ዕልቂት መንስኤ የሆነን ኮሮጆ ግልበጣ ፈጽሟል፡፡
—-የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቢሮን ለአመታት ተቆጣጥረውት የነበሩት አቶ ስዮም መስፍን የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ፍርድን ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስደመጡበት ወቅት ‹‹እንኳን ደስ አለን ብዙ ሺህ የህይወት ዋጋ የከፈልንባት ባድመ ለእኛ ተፈረደች››በማለት ህዝቡ ደስታውን በሰላማዊ ሰልፍ እንዲገልጽ ቢያደርጉም እውነታው ግን ባድመ ለኤርትራ መወሰኗ ነበር፡፡
—- በተለያዮ ቦታዎች ስለተፈጸሙ የቦንብ ፍንዳታዎች መንግስት ተቃዋሚዎችን ተጠያቂ ቢያደርግበትም ዊኪሊክስ በቅርቡ በለቀቀው መረጃ መንግስት ሆን ብሎ እንዲህ አይነት ድራማዎችን እነደሚሰራ አጋልጧል፡፡እስከ እናንተ ለምን መንግስትን እንደማታምኑ ምክንያታችሁን አካፍሉን፡፡

ምንጭ :- START – UNIVERSITY OF MARYLAND – የአሸባሪዎች አጥኚ ቡድን

የአሸባሪ ድርጅቶች መዝገብ
በሃገሩ ቋንቛ መጠሪያው .. አልተገለጸም

የድርጅቱ ስም …..የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (TPLF)

የሚንቀሳቀስበት አከባቢ … ኢትዮጵያ

የተቋቋመበት ጊዜ ….. አልተገለጸም

የአባላቶቹ ቁጥር/ጥንካሬው … አይታወቅም

መለያው ….. ኮሚኒስት/ሶሻሊስት/ብሄርተኛ/ተገንጣይ

የገንዘብ ምንጩ …. አይታወቅም

የተነሳበት የፖለቲካ ፍልስፍና
ራሱን የትግራይ ንቅናቄ ወይንም ወያኔ በማለት በ1970ዎቹ መጀመሪያ በመንግስቱ ሃይለማርያም አገዛዝ ላይ የተጀመረ ተቃውሞ
በ1975 አከባቢ የትግራይ ነጻ አውጪ በማለት ተመስርቶ በኤርትራ ነጻ አውጪ ስር እየተዳደረ ውጊያ የከፈተ ድርጅት ነው::አላማቸው የአልቤንያን ሞዴል የተከተለ የኮሚኒስት ስርኣት በማስፈን የታለመ…የትግራይን ህዝብ ከደርግ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የተነሳ ነበር::በሜይ 1989 የደርግን ሰራዊት በማሸነፍ ሙሉ ትግራይን መቆጣጠር ችሎ ነበር::በተለያየ ጊዜ ከሻእቢያ ጋር እና በተናጠል በተለያዩ አከባቢዎች የአሸባሪነት ድርጊት ፈጽሟል::
ዝርዝር መረጃውን ከዚህ ድህረገጽ ያገኙታል:- http://www.start.umd.edu/start/data_col … sp?id=4287

ለሸገር ልጆች፦፦፦
የድሮ አራዶች እነ ድንጋይ ኳሱ
ቦርቸሌን ከርቸሌን በደንብ ያዳረሱ።
ለወሬ ነጋሪ ካሉ የተረፉ፧
ምን አለ ቢያወጉን፧ምን አለ ቢጽፉ፧
ያዲሳባ ልጆች አብሮ አደጎቼ፣
በናፍቆት ባዘኑ እያነቡ አይኖቼ።
ድንገት ሣናስበው እንደተለያየን፣
በሞያሌ ሾልከን በቦሌ እንገባለን፣
አይቀርም አንድ ቀን፦እናወራዋለን፣
በአመቺው ዘዴ እንተርከዋለን፣
ዕድሜና ጤናውን አምላክ ካልነፈገን።፧
ሁል ግዜ ድሪሜ፣
የዘወትር ህልሜ፣
እንዳይነፍገን ዕድሜ።
እስከምንገናኝ በአካል በዐይነ ስጋ፣
ፌስ ቡክ ያገናኘን እርሱም እስኪዘጋ።
*ድንገት ለተለያየነው አብሮ አደጎቼና ወዳጆቼ ሁሉ መታሠቢያ ተፃፈ።
ተዱ ዘአራዳ ከዩጋንዳ