Man accused of spying for ESAT sentenced to four years in prisonMikiyas Nigatu of the Ethiopian Airports Enterprise’s Gambella Airport Security personnel, who was charged by the federal prosecutor for delivering sensitive information to the ESAT journalist named Fasil Yenealem for 4,460 Br is sentenced to four years in prison by the Federal High Court’s Fourth Criminal Bench on January 20, 2014.

Mikiyas who has failed to defend himself against a 10 page written document from his e-mail and three pictures from his cell phone has been giving various information to the ESAT television station which was deemed by the Ethiopian government as “a media outlet for the terrorist group Ginbot 7” The charge indicates that Mikiyas has provided information about foreign investors who were killed in the Gambella region and other very sensitive security related materials.

ፍትህ ለበቀለ ገርባ!
የእስር ጊዜውን ያጠናቀቀው አቶ በቀለ ገርባ አልተፈታም::
‹አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው› የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች

በእስር ቤት የሚገኘው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በባለፈው እሁድ የእስራት ቅጣቱን አጠናቆ የነበረ እና መፈታት የነበረበት ቢሆንም እስካሁን ድረስ በእስር ቤት ነው የሚገኘው:: በቅርቡ ከጓደኞቼ ጋር ሆነን ቃሌቲ ሄደን አግኝተነው ነበር፡፡ አመክሮ ለማግኘት እንደ መስፈርት የሚወሰደው፤ በቆይታው ወቅት የነበረው ስነ ምግባር በበቂ ሁኔታ እንዳሟላ እንደተገለፀለት ነግሮናል፡፡

ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቱ በፊት ማእከላዊ ያሳለፋቸው 41 ቀናት ሲደመሩ ነው ባለፈው እሁድ መውጣት የነበረበት፡፡ ማእከላዊ በእስር የቆየባቸው ቀናት መያዝና እና አለመያዝ የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር የይሁንታ ፈቃድ ማግኘት እንደሚያስፈልግ ተነግሮታል፡፡ በህጉ መሰረት ከሆነ ግን ማንም መፍቀድ ሳይጠበቅበት ሊደመርለት ይገባ ነበር፡፡ትላንት ይህን ጉዳይ ይዘው የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ለጠየቁ ቤተሰቦቹ ‹አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በቀለን ለመጠየቅ የሚፈልግ በስራ ቀናት ጠዋትና ከሰዓት፤ በእረፍት ቀናት ደግሞ ጠዋት ብቻ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን 2 ሄዶ ማግኘት ይችላል፡፡

ፍትህ ለበቀለ ገርባ!

60ኛው የ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› በራሪ ወረቀት አቢይ ጽሁፍ እነሆ!
በጠንካራ ወኔ ዛሬም ጥሪያችንን እናስተጋባለን!!

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሆይ! ‹‹ሀይማኖታዊ መብታችን ይከበር!›› ስንል የምናደርገው ሰላማዊና ህዝባዊ ትግል ዛሬ ወሳኝ ምእራፍ ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም የምንገኝበት የእፎይታ ጊዜ ሊነሳ አጭር ግዜ በቀረበት በዚህ ሰዓት ሰላማዊ ትግሉ የተጀመረበት ሁለተኛ ዓመት የሚታወስበት ወቅት ላይ መድረሳችን ነው፡፡ ከፊታችን ጁሙዓ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት ሁለተኛ ዓመት የሞላውን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ የ‹‹መብቴ ይከበርልኝ!›› ጥያቄ በተለያዩ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች መዘከር እንጀምራለን፡፡ በዚህ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በዝምታችን ውስጥ አልፈው የሚያስተጋቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እናደርጋለን፡፡ የእፎይታ ጊዜው ዝምታ አንዱ የሰላማዊ እንቅስቃሴያችን መገለጫ ሆኖ ላለፉት 6 ወራት ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ በዚህ የእፎይታ ጊዜው የመጨረሻ እድሜ ላይ የምናደርገው የሁለት አመቱን የሰላማዊ ጥያቄያችንን ሂደት የምናስታውስበት እንቅስቃሴ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም የሁለት አመት ጉዟችንን በምናስታውስበት ሂደት ሁሉም የሙስሊም ማህበረሰብ ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርግ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ሰላማዊ እንቅስቃሴያችን ሰላማዊ ሆኖ በመጓዝ ሰላማዊነቱን ለማደፍረስ መንግስትና ህገ ወጡ መጅሊስ የሚሰነዝሩትን የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ የሚያሴሩትን ሴራ ወጥመድና እና ህገ መንግስቱን ክፉኛ የሚሸረሽሩ ህገ ወጥ ተግባራት ሁሉ በአላህ ፈቃድ እያከሸፈ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ኢንሻላህ ወደፊትም በሀያሉ ጌታችን አላህ ፈቃድ የእምነት ነፃነታችን ተከብሮ በሀገራችን ፍትህን እንደምንጎናፀፍ እምነታችን ሙሉዕ ነው፡፡ ይህን የምንለው ሀያሉ ጌታችን አላህ የተበደለን የሚክስ፣ በህዝብ ላይ ግፍ የሚፈፅምን መሪ የሚያስተካክል አልያም የሚቀይር ሁሉን ቻይና ተመልካች በመሆኑ ነው፡፡ ጌታችን አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል ‹‹…… ምእመኖቹንም መርዳት በእኛ ላይ ተገቢ ሆነ፡፡›› (ቅዱስ ቁርዓን 30፡47)

ዛሬ ላይም ቆመን ለሚመለከተው ሁሉ የምናረጋግጠው እውነታ ትግላችን ከስሜታዊነት ርቆ በሀቅ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው፡፡ ትግላችን ‹‹የሀይማኖት ነፃነታችን ይከበር! በገዛ ሀገራችን በሀይማኖታችን የሚፈፀምብን ግፍ ይቁም!›› ነው፡፡ ትግላችን ‹‹ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በሀገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶች የህግ ታራሚዎች የሚቆዩበት ስፍራ መሆናቸው ቀርቶ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ማሰቃያና ማጎሪያ ስፍራዎች እስኪመስሉ ድረስ እየተደረገብን ያለው ዓይን ያወጣ የመብት ረገጣና የህገ መንግስት ጥሰት ይቁም!›› ነው፡፡ ‹‹የህዝብን መብት እንዳሻቸው ረግጠውና የሀይማኖት ነፃነትን ነፍገው ሲያበቁ ይህን ፍፁም ህገ ወጥና ክፉ ስራቸውን ለመሸፈን በማሰብ በተቃራኒው በሚዲያ ቀርበው በየእለቱ ‹አክራሪ፣ አሸባሪ፣ ፅንፈኛ፣ ህገ መንግስቱንና የሌሎችን እምነት መኖር የማይቀበሉ› ሲሉ የሚያቀርቡት የተገላቢጦሽ ልፈፋና ድራማ ህዝብ አንቅሮ የተፋው እዚህ ግባ የማይባል ከንቱ ድካም መሆኑን ደግመው ይገንዘቡ›› ነው፡፡ ‹‹ለልማት መዋል የሚገባው የሀገር ሀብት እና ጊዜ የንፁሁን ህዝበ ሙስሊም ስም ለማጥፋት፣ የህዝበ ሙስሊሙን ሀይማኖታዊ ነፃነት እና ህገ መንግስታዊ መብትን ለመገደብ፣ ህዝብ በይፋ ያወረዳቸውን የመጅሊስ ሹመኞች ከህዝበ ሙስሊሙ ተቃራኒ ተሰልፈው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ በማዋል ሀገርን ወደ ፊት ከማራመድ ይልቅ ወደ ኋላ የሚጎትት አካሄድ ላይ መጠመድ ይቁም!›› ነው ጥያቄያችን፡፡ ‹‹እነዚህ ሁሉ ህገ ወጥ ድርጊቶች ቆመውና ጥፋተኞችም በፍትህ ፊት ታርመው የጠየቅናቸው ሰላማዊና ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች ይመለሱልን!›› እንጂ ሌላ አልነበረም ጥያቄያችን፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እነኚህን ሁሉ ለግርግር የሚጋብዙ ህገ ወጥ ድርጊቶች እና በደሎችን በእልህ አስጨራሽ ትእግስትና ፅናት ተሻግረው ዛሬ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህን ያደረግነው ከምንም ነገር በላይ ዲናችን የሚያስተምረንን ሰላማዊነት ለማንፀባረቅ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ እንዲሁም በተመሳሳይ ምንም እንኳ ለሀገር ሰላም እና ለህዝብ ደህንነት መጨነቅ ያለበት አካል በተቃራኒው ተሰልፎ የህዝብን ሰላም እና የተረጋጋ ህይወት፣ እንዲሁም የሀይማኖት እና የግለሰብ ነፃነቶችን በሚያደፈርሱ ተግባሮች ላይ ሲጠመድ ብናስተውልም ነገር ግን እንደ ህዝብ ለሀገራችን እና ለህዝቦቿ መረጋጋት በማሰብ፣ ለሰላሟ እና ደህንነቷ በመጨነቅ፣ በሰከነ ልቦናና በተገራ የሀላፊነት ስሜት እልህ የሚያስጨርሱ ክስተቶችን በሚያስደንቅ ፅናት፣ አንድነት እና ትእግስት አልፈናል፡፡ ይህ እንደ ህዝብ በአላህ እገዛ የተቸርነው ፀጋ ነውና አልሐምዱሊላህ!!

የእፎይታ ጊዜውም ቢሆን የተቀመጠበት ዋነኛ ዓላማ ይህንኑ ከግንዛቤ በማስገባት መንግስት ከስሜታዊነት ወጥቶ በሰከነ መንፈስ ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሄ እንዲያስቀምጥ የማሰቢያ እና የማሰላሰያ ጊዜ መስጠት ነበር፡፡ በተመሳሳይ ‹‹ተቃውሞ ቢቆምና ሙስሊሙ ዝም ቢል መንግስት ምን ሊያደርግ እንደሚችል በተግባር በማየት ማረጋገጥ›› የሚሉና መሰል ዓላማዎችም ነበሩት፡፡ በመሆኑም መንግስት በዚህ የእፎይታ ጊዜ ከፈፀመው ስህተት ከመመለስ ይልቅ በዚያው የስህተት መስመር መጓዙን እንደቀጠለ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ተቃውሞ የሌለበት አየር ቢመጣም እንኳ እስሩ፣ ድብደባው፣ እንግልቱ፣ የኢማሞች መባረርና መንግስታዊ ኢማሞች መተካቱ፣ የመስጂድ ነጠቃው፣ የሀሰት ክሱና የሀሰት ፍርዱ ሁሉ እንደሚቀጥሉ እንጂ እንደሚቆሙ የእፎይታ ጊዜው አላሳየንም፡፡

በመሆኑም በዚህ የእፎይታ ጊዜው የመጨረሻ እድሜ ላይ የትግላችንን የሁለት ዓመት ጉዞ ስናስብ በሙሉ መነቃቃት ላይ በመሆን ነው፡፡ በጠንካራ ወኔ ዛሬም ጥሪያችንን እናስተጋባለን፡፡ ዛሬም እንደ ትላንቱ ሁሉ ለዲናችን መከበር ዘብ በመቆም ሀይማኖታዊ ነፃነታችንን እስክንጎናፀፍ እና የፈጣሪያችንን አምልኮተ ህግጋቶች እንዳንተገብር፣ ብሎም እንድንርቅ በማሰብ የሚደረጉብን ጫናዎች እስኪቆሙ ድረስ ሰላማዊ ሆነን ከመታገል አንወገድም፡፡ ዛሬም አንድነታችን እንደጠበቅን ለዲናችን መከበር ያለንን ጠንካራ ወኔ አጉልተን እናሳያለን፡፡ ሂደታችን ሰላማዊና ከግብታዊነት የራቀ፣ ሀይማኖታዊ መብት እንዲከበር የመጠየቅ ሂደት ነውና የጠየቅነው መብት እስኪከበር በተለያዩ ሰላማዊ መንገዶች መታገላችንን እንቀጥላለን፡፡

የምንከፍለው መስዋእትነት ለዲናችን መሆኑን ጠንቅቀን መረዳታችን በሰላማዊ ትግሉ ላይ አላህ ወፍቆን በምንከፍለው መስዋእትነት ሳቢያ የምናገኘውን ደረጃ ማሰብ ምንኛ የሚያጓጓ ፀጋ መሆኑን ግፍ የሚፈፅሙብን አካላት በጥልቀት እንዲረዱት ደግመን የምናስመሰክርበት ሂደት ላይ ነን፡፡ ውድ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች! ከኛ የሚጠበቀው ዲንን በመጠበቁ ሂደት ላይ ሁሉም በሚችለው አቅም መረባረብ ነው፡፡ ይህን ስናደርግ ውስጣችን በሚከተለው የሀያሉ ጌታችን አላህ ቃልኪዳን ይረጋጋል፡-

‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሀይማኖቱን) ብትረዱ ይረዳችኋል…›› (ቅዱስ ቁርዓን 47፡7)

አዎን! እስልምናችንን ለመጠበቅ በምናደርገው እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ያለጥርጥር የአላህ አርዳታ ከጎናችን ይሆናል፤ በንፁህ ልቦና በአላህ መንገድ ላይ እስከቆምን ድረስ፡፡ አላህ ባዘዘው መንገድ ላይ መቆም ምንኛ መታደል ነው!!

በሌላ መልኩ ለዲናችን የምንከፍለው እያንዳንዱ መስዋእትነት ዋጋው አላህ ዘንድ እንጂ የትም አይደለም፡፡ ሺዎች ታስረናል፤ አልያም የግፍ በትር አርፎብናል፡፡ ከእስር የተረፉ ብዙ አሊሞቻችን፣ ዱዓቶቻችን እና ወጣቶቻችን ተሰደዋል፤ ተወልደው ካደጉባት፣ ኖረው ከከበዱባት የገዛ ሀገራቸው ሰላምን ፍለጋ እንዲሰደዱ ተገደዋል፡፡ ወጣት አዛውንት፣ ወንድ ሴት ሳይለይ የከፈልናት እያንዳንዷ መስዋእትነት ጌታችን ዘንድ ተመዝግባ ለምንዳ ትቀመጣለች፡፡ አዎን! ዛሬን ስለ ዲኑ እና ህብረተሰቡ በመቆርቆር፣ ሀቅን በመናገር፣ ሙስሊሞችን ወደ አንድነት በመጣራት ጊዜውን ያሳለፈ ወጣት ነገ ጌታው ዘንድ ትልቅ ክብርን ይጎናፀፋል፡፡ ጌታችን አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

‹‹… እነዚያም የተሰደዱ፣ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ፣ በመንገድም የተጠቁ (በአላህ መንገድ ላይ ግፍ የተፈፀመባቸው)… ክፉ ስራዎቻቸውን በእርግጥ አብሳለሁ፤ በስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አስገባቸዋለሁ፤ ከአላህ ዘንድ የሆነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፤ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለ፡፡›› (ቅዱስ ቁርዓን 3፡195)

ዛሬም አንድነታችንን እንደጠበቅን ለዲናችን መከበር ያለንን ጠንካራ ወኔ አጉልተን እናሳያለን!! የፈጣሪያችንን አምልኮተ ህግጋቶች እንዳንተገብር ብሎም እንድንርቅ በማሰብ የሚደረጉብን ጫናዎች እስኪቆሙ ድረስ ሰላማዊ ሆነን ከመታገል አንወገድም!! ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

ሽንፈትን መቀበል ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ ሽንፈትን ለመቀበል ዝግጁ የሆነ ሲያሸንፍ ጉራ አይነዛም፡፡ንቅዘት ብቻ ነው ጉዞው፡፡ የዓለም ታላቅ ኃይለም ያሸንፍ አገራዊ ኃይል፤ በምን ሁኔታ አሸነፈን እንጂ፤ አልሸነፍም ማለትን መመርመር አለብን፡፡ የማረከውን ሰው በሰብዓዊ መንገድ ለመያዝ የሚችል ተዋጊ ጀግንነትን ከጭካኔ በመለስ ማየት አይሳነውም፡፡ ምህረት ለማድረግም ፍርሃትና ሥጋት አይኖርበትም፡፡ “የተጠማ ከፈሳሽ፣ የተበደለ ከነጋሽ” የሚለው ምሣሌያዊ አነጋገር በቀላሉ ይገባዋል፡፡ ምርጫ፣ በተለይም በአገራችን፣ በሚካሄድበት ጊዜ የሚያጋጥመን የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽ፤ 1ኛ/ የተሸናፊው ሽንፈትን አለመቀበል እና 2ኛ/ የአሸናፊው ዘራፍ ባይነት ነው፡፡ ይህ ማለት ከምርጫው በኋላ አሸናፊና ተሸናፊ አይጥና ድመት ናቸው ማለት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ዐይን መተያየት ቀርቶ እንደ ዜጋ መተሳሰብም ይቀራል፡፡ “የማትወልደውን ሶሻሊዝም ሲያማምጡዋት፤ ከነ ካፒታሊዝሟም አስወረዳት!” እንደተባለው ነው፡፡ አዲስ ሥርዓት መፍጠር ቀርቶ አሮጌውንም ማጣት አለ፡፡ ቁልቁል ማደግ የሚባለው ዓይነት!

ዲሞክራሲ በምርጫ ሳጥን ብቻ ሳይሆን፤ በኑሮአችን ድርና ማግ ውስጥ ሁሉ የሚኖር መሆን አለበት፡፡ ሁሉን ጐራሽ የሆነ አሠራር ከተከተልን ፖለቲካውም ሆነ ባህሉ ልሙጥ ይሆናል፡፡ ይህም ህዝብን ሽባ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ይሰውረን፡፡ ሥልጣንን ማጋራት፣ ሥራን ማከፋፈል ይቻለን ዘንድ ትምህርታችንን ይግለጽልን! የችግር ጊዜ ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ፡፡ የላዩ ታች የታቹ ላይ ቦታ ሊቀይር ይችላል፡፡ በደስታው በተድላው ጊዜ የሚደረገው ሁሉ ይቀራል፡፡ ድህነት ጥላውን ሲጥል ማጀት ጓዳው መራቆቱ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብም ይራቆታል፡፡ ዕምነት ይመነምናል፡፡ ጀግንነት ይኮሰምናል፡፡ ቆራጥነት ይከሳል፡፡ የሌለው ላለው ያድራል፡፡ ተገዢ ገዢውን ከልኩ በላይ እጅ ይነሳል፡፡ አድር ባይነት የዕለት የሠርክ ጉዳይ ይሆናል፡፡

ሁሌ በተለመደው የፖለቲካ መንገድ መሄድ ለህዝብ ዕድል አይሰጥም፡፡ ሌላው ይቅርና ለፖለቲከኛው ለራሱም ዕድል አይሰጥም ፡፡ እስከንቅዘት ብቻ ነው ጉዞው፡፡ ወደ አዲስ አይን መክፈት አያመራም፡፡ የትኛውም ዘመን በየትኛውም ፓርቲ አንድና አንድ መንገድ ብቻ ልከተል ባለ ሰዓት የሚከሰት ችግር ነው፡፡ የታየ፣ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው!! “እወርካ ሥር የገደለ፣ ዘወትር እወርካ ሥር ያደፍጣል” የሚባለው እንዲህ ሲሆን ነው! ጦርነት ሰልችቶናል፡፡ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ጦርነታችን ብዙ ሰው አልቆብናል፡፡ ብዙ ንብረት ወድሞብናል፡፡ ኢኮኖሚያችን ደቅቋል፡፡ ስለዚህ ሌላ ጦርነት ይጎዳናል እንጂ ምንም አይፈይደንም!

እንቢኝ ለመብቴ እንታገላለን ያሉት የደሴ ሙስሊሞች ደሴን በበራሪ ወረቀት አሸብርቀዋት አደሩ::

መንግስት የደሴን ሙስሊም በሀይል ቀጥቅጨ ተቆጣጥሬዋለሁ ብልም ፉከራውን መና የሚያሰቀር ሁኟን:: በተያያዘ ዜናም በዚሁ ድርጊት የተደናገጡት የመንግስት ደህንነቶች እና አቀንቃኝ ካድሬወች በሌሊቱ ተነስተው በስራ ተጠምደው እንዳደሩም ለማወቅ ተችሏል::

በበራሪ ወረቀቱ ላይ ጎልተው ከሚታዩት መፈክሮች መካከል 1.ኮሚቴወቻችን ወንጀለኝ አይደሉም ንፁህ ናቸው ይፈቱልን 2.መንግስት በሙስሊም እና ክሪስቲያን መካከል ግጭት ለመፍጠር ድራማ እየሰራ በ Etv የሚያቀርበው ፕሮፓጋንዳ ይቁም 3.አሸባሪ አይደለንም 4.ትግሉ ይቀጥላል 5.ድምዻችን ይሰማ እና ኮሚቴው በፍጥንነ ትይፈታ አለያ አንደራደርም የሚሉት ይገኙበታል::

የደሴ ሙስሊም በኮሚቴወቹ ላይ መንግስት የጥፋት እጁን ከሰነዘረ እንደማይደራደሩ ዛሬ ተበትኖ ባደረው 50000 ሺ በራሪ ወረቀት አስረግጦ አሳስቧል:: ሲቀጥልም ዱላ እስር እና ግድያ የማይበግረው የደሴ ሙስሊም ትግሉ እስከ ድላችን ድረስነው በቀይ ይሰመርበት ሲሉ አሳስበዋL:: ድል ፍትህ ለተጠማው ሙስሊም አላህ አክበር!

ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ግንባታ ማንኛውንም ዓይነት ሕግ የጣሰ አይደለም በማለት መንግሥት የግብፅን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡

አል ሞኒተር የተባለ የግብፅ ሚዲያ የተለያዩ የአገሪቱ ባለሥልጣናትን በመጥቀስ፣ ግብፅ በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ተቃውሞ ዓለም አቀፍ ማድረግ እንደምትፈልግ ዘግቧል፡፡

‹‹የህዳሴው ግድብ አሁን ባለው የግንባታ ደረጃ ተገንብቶ ዕውን የሚሆን ከሆነ በግብፅ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከባድ ነው፡፡ በመሆኑም ጉዳዩን ወደሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መውሰድ እንደሚገባ፣ ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው፤›› ያሉት የአገሪቱ የመስኖና ውኃ ሀብት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ካህሊድ ዋሲፍ ናቸው፡፡

‹‹ግብፅ የህዳሴው ግድብ ግንባታን ፈፅሞ አትፈቅድም፡፡ ይህንን ለማሳካትም ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የውጭ ዕርዳታ ለግድቡ እንዳታገኝ ግፊት እናደርጋለን፤›› ሲሉ በይፋ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ የኢትዮጵያን ግድብ በማውገዝ ከግብፅ ጐን እንዲቆም አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ በዓለም አቀፍ ሕግ የተከበረና የተረጋገጠ መብት አላት፡፡ ነገር ግን ይህ የግብፅ መብት በኢትዮጵያ እየተጣሰ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ሕጋዊ መብት አላት የሚሉት ቃል አቀባዩ፣ ማናቸውም የተፋሰሱ አገሮች ተፋሰሱን በመጠቀም ወደ ልማት መግባት ሲፈልጉ በቅድሚያ ግብፅን የማማከርና ይሁንታ የማግኘት ግዴታ አለባቸው ሲሉ የአገራቸውን አቋም አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን ግዴታ በመጣስ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ መጀመሯ በራሱ ሕግን የጣሰ መሆኑን፣ ነገር ግን የግብፅ መንግሥት ጉዳዩን በወዳጅነት በመያዝ ሲወያይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ምንም ዓይነት ጉዳት በግብፅ ላይ እንደማያደርስ ኢትዮጵያ ለማረጋገጥ እንቢተኛ በመሆኗ ግብፅ ከውይይቱ ራሷን እንዳገለለች አስረድተዋል፡፡

የግብፅ የቀድሞ የመስኖና የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሙሐሙድ ናስር አል ዲን አላም በበኩላቸው፣ ግብፅ ከዚህ በኋላ በህዳሴው ግድብ ላይ ሌላ አማራጭ የላትም ብለዋል፡፡ የቀረውና በፍጥነት ተግባራዊ መሆን የሚገባው አማራጭ ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው ማድረግ፣ በዋናነትም ይፋዊ ቅሬታና ተቃውሞ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማቅረብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

‹‹ማንኛውም የዓባይ ተፋሰስ ተጋሪ አጋር በወንዙ ላይ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የግብፅን ይሁንታ ማግኘት አለባት የሚለው ስምምነት ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለው ነው፤›› በማለት የሚከራከሩት የቀድሞው ሚኒስትር ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት በመጣስ ለጀመረችው ግንባታ በተባበሩት መንግሥትት ድርጀት ልትጠየቅ ይገባታል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል አሁን ያለውን አለመግባባት በተመለከተም ዓለም አቀፍ እውነት አፈላላጊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ማጥናት ይኖርበታል በማለት ተከራክረዋል፡፡

የግብፅ ባለሥልጣናት እያንፀባረቁት ስላለው አዲስ አቋም የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ፣ ‹‹ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ውል አይመለከታትም፣ ምክንያቱም አልፈረመችም፤›› ሲሉ የግብፅ ባለሥልጣናት መግለጫን አጣጥለዋል፡፡ የቅኝ ግዛት ውሉ የተፈረመው በግብፅና በእንግሊዝ መካከል መሆኑን ያስታወሱት አቶ ፈቅ፣ እንግሊዝ ቅኝ የገዛቻቸውን ኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ በመወከል ስምምነቱን ፈርማለች፡፡ ይህ ግን ኢትዮጵያን ፈፅሞ አይመለከትም ብለዋል፡፡

የግብፅ የቀድሞው የመስኖና የውኃ ሀብት ሚኒስትር በተደጋጋሚ ይህንን መሳይ ነገር ያነሳሉ በማለት ያስታወሱት አቶ ፈቅ፣ ‹‹ሰውዬው ከሳይንስ ውጭ ነው የሚናገሩት፣ ከእሳቸው የሚጠበቅ አይደለም፤›› ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ የጀመረችው የህዳሴው ግድብ ግንባታ የትኛውንም ዓለም አቀፍ ሕግ የጣሰ አይደለም፡፡ ወደፈለጉበት ቢሄዱ የሚመጣ ነገር የለም፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡ ጉዳዩን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ መምራት ሊያተርፍ የሚችለው በሁለቱ አገሮች ያለውን የትብብር መንፈስ ማጥፋት ነው ሲሉ የግብፅ ባለሥልጣናትን የሰሞኑን ዘመቻ አውግዘዋል፡፡ Reporter

ከኡጋንዳ ኢንቴቤ ተነስቶ ወደ ሰንዓ የመን በመብረር ላይ የነበረ ንብረትነቱ የዩክሬን የሆነ አንቶኖቭ 28 የመንገደኞች አውሮፕላን ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ አቅራቢያ ለገዳዲ አካባቢ ተከሰከሰ፡፡

ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ የአውሮፕላኑ አብራሪዎች ሰኞ ማለዳ ከባለሥልጣኑ ጋር ባደረጉት የሬዲዮ ግንኙነት ከኢንቴቤ ተነስተው በኢትዮጵያ በኩል ወደ የመን ለመብረር ፈቃድ ጠይቀው ነበር፡፡ ባለሥልጣኑም የበረራ ፈቃድ ሰጥቷቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ኤር ናቪጌሽን ክፍል ለአብራሪዎቹ የሚበሩበትን ከፍታ ሰጥቷቸዋል፡፡ አውሮፕላኑ የኢትዮጵያን አየር ክልል አቋርጦ በማለፍ ላይ ሳለ አዲስ አበባ አካባቢ ሲደርስ የሞተር ብልሽት ያጋጥመዋል፡፡ ይህንኑ ለአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ መቆጣጠሪያ ማማ አሳውቆ ‹‹ኢመርጀንሲ ላንዲንግ›› እንደሚያደርግ (በድንገተኝነት እንደሚያርፍ) ሪፖርት አድርጐ፣ ከጠዋቱ 3፡35 ሰዓት ላይ ለማረፍ ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በማምራት ላይ ሳለ ለገዳዲ አካባቢ ተከስክሷል፡፡

አደጋው እንደደረሰ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፈልጐ ማዳን ቡድን ወደ ሥፍራው ተንቀሳቅሶ የአውሮፕላኑ አብራሪዎችን ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ሕክምና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፋሪዎች እንዳልነበሩ ታውቋል፡፡ በአደጋው አብራሪዎቹ የተጐዱ ቢሆንም፣ ሕይወቱ ያለፈ ሰው እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአውሮፕላን አደጋ መከላከልና ምርመራ ክፍል ባለሙያዎች የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ምርመራ ጀምረዋል፡፡ ባለሙያዎቹ አውሮፕላኑ ወደ ወደቀበት ሥፍራ በማምራት መረጃ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሩሲያ ሰራሽ የሆኑ አንቶኖቭ አውሮፕላኖች ከተመረቱ ረዥም ጊዜ ያስቆጠሩ በመሆኑ በየጊዜው እክል እየገጠማቸው በተለያዩ አገሮች በመከስከስ ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ ዕድሜ ጠገብ አውሮፕላኖች ዋጋቸው ርካሽ በመሆኑ በአፍሪካ አገሮች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ያረጁ በመሆኑና ተገቢ የሆነ ጥገና ስለማይደረግላቸው በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በተደጋጋሚ አደጋ እንደሚያደርሱ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ Reporter

በምስራቅ ሃረርጌ ከ59 ሰዎች በላይ መገደላቸውን መንግስት ግጭቱን ሆን ብሎ መቀስቀሱን የኦሮሞ ጥናት ማህበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ገለጡ:: የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ኢሌሞ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ጥቂት ወራት በአንያ፣ ማቶ እና ሙለቄ ቆላማ ወረዳዎች ላይ በፌደራል መንግስቱ እውቅና የተቋቋመውና ስልጠና የሚሰጠው ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ሃይሎች በኦሮሞዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት 59 ገድለው፣ 42 አቁስለዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከልም ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል።

“በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ሰላም ካገኙ ለተቃዋሚዎች ምቹ ቦታ ሊፈጥሩ ይችላል በሚል እሳቤ የሁለቱን ክልል ህዝቦች እያጋጨና እርስበርስ ተጠባብቀው እንዲኖሩ ለማድረግ ” መንግስት ግጭቱን ሆን ብሎ መቀስቀሱን የገለጡት ዶ/ር ኢብራሂም ፣ በግጭቱም እድሜውን ለማራዘም እንደሚያስብ ተናግረዋል። ማህበሩ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ለሌሎችም አገራት ደብዳቤ ማስገባታቸውን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል ። ኢሳት ዜና

ምንሊክ ሳልሳዊ
እኛ ሃገራችንን የምንወድ ኢትዮጵያን ስለ ፖለቲካ ድርጅቶች አያገባንም::እንዲያድጉ እንዲለሙ እንዲመነደጉ እናበረታታለን እንጂ በነዙ ስትራቴጂ አልባ ድፍን ደረቅ ፖለቲካ ውስጥ ገብተን አብረን በጭቃቸው መቡካት አንፈልግም::የወደደ ይውደድ የጠላ ይጥላ እትዮጵያ ውስጥ ወያኔን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ጎራ ጥያቄው የስልጣን እና የአገዛዝ ሩጫ ነው::የእኛ የዜጎች ጥያቄ ግን ፍትህ መልካም አስተዳደር የአገልግሎት አቅርቦት እና ሰላም ነው::

ወያኔ የሚያደፈርሳቸው ተቃዋሚ ነን የሚሉትም በአቅማቸው የሚያደፈርሷቸው ሰላሞቻችን ይመለሱልን::ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የሚበጅ አስተዳደር ለማምጣት መጀመሪያ የህዝቦች ጥያቄ መመለስ የለውጥ እርምጃ መምጣት አለበት::
ለዘላቂ ልማት እንሰራለን በሚል ስርኣት ውስጥ የመሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች በጊዜያዊነት መኖር እና እንደመነገጃ መጠቀም ህዝብን አገለግላለሁ ሳይሆን አጭበረብራለሁ እንደማለት ይቆጠራል:: የወያኔ ስርኣት ባለስልጣናት በፍርሃት ተውጠው በሚኖሩባት በዚች ኢትዮጵያችን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አሁንም እጅግ መልስ የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው::ዜጎች በሃገራቸው እንዳይኮሩ በመኖር ደህንነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ እየተደረገ ስለሆነ ይህ ደሞ ወያኔ በዘላቂነት የያዘውን ስልጣን ላለመነጠቅ የሚሰራው ፖለቲካዊ ደባ ውጤት መሆኑ እሙን ነው::

ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን ወደ እውነት ያመጡ ህጎች በኢትዮጵያ አሉ የሚለው ወያኔ ህዝቦች ግን በተግባር ተጠቃሚ ሲሆኑ አላየንም::ህጎቹ በተግባር ይዋሉ ይህንን ህጎች በመመሪያ በደብዳቤ እና በስልክ የሚቀይሩ የሚደፈጥጡ በጥቅም የሚሸጡ የሚረጋግጡ የሚለውጡ ከየወንበራቸው ተሽቀንጥረው ይጣሉ:: የቀን ተቀን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ሂደት ውስጥ እጃቸውን እያጠለቁ ፍትህን የሚያዛቡ አስተዳደራዊ በደሎችን የሚፈጽሙ ባለስልጣናት የህዝብን ማህበራዊ ህይወቶች ከማፋለሳቸውም በላይ ፖለቲካው እንዲጭበረበር ኢኮኖሚው እንዲደቅ ሃገር በብድር እንድትዘፈቅ ህዝብ እንዲደኽይ ከባዱን ሚና እየተጫወቱ ነው::

ህዝቦች ህግ እየጸደ ህግ እየተሽሞነሞነ እና እየተብለጨለጨ ቢቀመጥ ምንም የሚጠቅማቸው ነገር እንደሌለ መታወቅ ያለበት ሲሆ አንድ ህዝብ ባላረቀቀ ባልተወያየበት እና ባላጸደቀው ህግ እየተገዛ ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እንዴት ማስፈን ይቻላል??? መተማመን እና የዜግነት ኩራቱን በሚሰብሩ ባለስልጣናት እየተሰበረበት ያለ ህዝብ ፍትህን እና አስተዳደራዊ እንዲሁም አገልግሎቶችን በተግባል ለማየት እና ለመጨበጥ አልቻለም:: ለተበደለና ፍትሕ ላጣ ዜጋ፣ መልካም አስተዳደር አጥቶ ለሚንገላታ ዜጋ ፍትሕና መልካም አስተዳደር እንዲኖር በአንቀጽ ተደንግጓል እያልን ብናወራ ዋጋ የለውም::

ህዝብ ባለው ስርኣት ላይ እምነት የለውም:; ይህ ደግሞ ራሱ ስርኣቱ ያረጋገጠው ነገር ነው ኢትዮጵያውያን የስርኣቱ ታጣቂ ሃይሎች በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚያደርሱትን የሰብኣዊ መብት ጥሰት እያዩ በሃገሪቱ ህግ የለም እኔም ነገ እደበደባለሁ እታሰራለሁ ንብረቴን እነጠቃለሁ መብቴን እነፍርጋለሁ እጠቃልሁ እገደዳለሁ እሰደዳለሁ እገደላለሁ በሚል በስርኣቱ ላይ ያላቸው እምነት የተሟጠጠ ከመሆኑም በላይ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከሃገር የመውጣት ንብረትን እና ሃብትን የማሸሽ ተግባር ላይ በመሰማራት በዜግነት አለመተማመን እንዲፈጠር በሩን በርግዶ ከፍቷል ይህ ደሞ ህጎች በተግባር ህዝብን አለማገልገላቸው እና በባለስልጣናት የመደፍጠጣቸው ውጤት ነው::

በተግባር ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት የተነሳ ማንም የለም::ስርኣቱም በጥቅመኞች የሚመራ ህዝቡም ላላወጣው ህግ በዝምታ ደንታቢስነቱን እየገለጸ ነው; ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን የሚጥስና የሚያደናቅፍ የስርኣቱ ባለሥልጣን፣ ዜጋም ሆነ ግለሰብ፣ በማስረጃ ሲታይና ሲረጋገጥ ዕርምጃ ለመውሰድ ሕግ ፊት ለማቅረብ ምንም አይነት የተሰራ ስራ ካለመኖሩም በላይ በባሰ መልኩ በይፋ ህጎች ሲደፈጠጡ እያየን ነው:: ባለሥልጣንም ሆነ ባለ ሀብት፣ ታዋቂም ይሁን ተራ ዜጋ፣ ከፈለገው ብሔር ብሔረሰብ ይምጣ፣ የፈለገውን ሃይማኖት የሚከተል ይሁን፣ የጾታና የዕድሜ ልዩነት ሳይኖር ተቃዋሚም ይሁን ደጋፊ ሁሉም ሕግ ፊት፣ ፍትሕ ፊት፣ መልካም አስተዳደር ፊት እኩል መሆኑን አምነን በተግባር ለማዋል ቁርጠኝነት በፍጹም የለም:: ፍትህ እና መልካም አስተዳደር እንዴት ሊረጋገጡ ይችላሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየተጓዝን ነው ጥያቄያችን ;ስለዚህ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል::

ምንሊክ ሳልሳዊ አገር በኔ ብቻ ተመርታ አገር አትሆንም ብሎ፤ ኃይለኛውና አሸናፊው ከወጣበት መሠላል ዝቅ ብሎ፤ ግማሽ መንገድ ወርዶ እንነጋገር፣ እንወያይ የማለት ባህል፤ ተሸናፊውም ከቁጭቱ፣ ከቂሙ፣ ለመጣል እንጂ አብሮ ለመቀመጥ አልፈልግም የሚልበትን ግትር አቋም ትቶ፤ እኔም የሀገር ጉዳይ ያገባኛል፣ “እንድትሰፉ እንጂ እንደትጠፉ አልፈልግም” ብሎ፤ መንገድ መሻት ያሻዋል፡፡

ቤት ንብረት በሀራጅ ከሚያስሸጥ ድህነት ይሰውረን፡፡ በሎተሪ ከሚያሳምን የገጠመኝ ዘመን ያውጣን፡ ከሁሉም በላይ ግን ለመለመን እንኳ ጥቂት የራስ መንቀሳቀስ እንደሚያሻን መገንዘቢያ የሚሆነን ልብ ይስጠን!!በሀገራችን ከድህነት እኩል የሚፈታተነን ችግር፤ ቢያንስ ግማሽ መንገድ እንኳ ሄዶ ለመደራደር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን አሊያም ቀና ልቡናውን ማጣታችን ነው፡፡ ግማሽ መንገድና የመቻቻል፣ ልዩነትን የማስተናገድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመልመድ ትልቅ ፀጋ ነው፡፡

የኋላ ታሪክ የሌለው የሚያውቀው ዛሬን ብቻ ነው፡፡የአንድ ቀን ታሪክ የሌለው የሚያውቀው ዛሬን ብቻ ነው፡፡ አንድ ቀን ባዶነት መሰማቱ አይቀርም፡፡ ከሌላ አካል ተከፍሎ መፈጠር ዕድሜ ልክ ሙሉነት ሳይሰማን እንድንኖር ማድረጉ አሌ አይባልም፡፡ ራስን ችሎ፤ በራስ ተማምኖ ለመኖር ራስን ሆኖ መፈጠርን ይጠይቃል፡፡በሀገራችን በፖለቲካ መከፋፈል እንጂ ተስማምቶ መጓዝ አይሆንልንም፡፡ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ እንደባህል የተያዘ ፈሊጥ ነው፡፡

አይጥና ድመት የታረቁ ለታ ባለግሮሰሪው/ባለንብረቱ ወዮለት! አይጥና ድመት እንኳ ታርቀው ጠላታቸውን የሚያጠቁበት ቀን ይመጣል ነው የሚሉን፡፡ “የማይለወጥ ነገር የለም – ከለውጥ ህግ በስተቀር” ታሪካችንን ወደኋላ ብንመረምር ምን ያህል እንደተለወጥን ወይም እንደተለዋወጥን መገንዘብ ቀላል ነው፡፡

ስለተሰሩ መንገዶች፣ ስለፈረሱ ቤቶችና ስለተሠሩ ህንፃዎች፣ ስለታሰሩ ሰዎችና ስለተፈቱ ሰዎች፤ ስለተፃፉ ደንቦችና ስለተጣሱ ህጐች፤ ስለማይሸጡ መሬቶችና በሊዝ ስለተወሰዱ መሬቶች፤ ስለማይነኩ ሰዎችና ኋላ ስለተወረወሩ ሰዎች፡፡ ለውጥ አይቀሬ ነው፡፡ ህገመንግስቱን እንኳን “የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም ሰው ነው የፈጠረው ሰው ይለውጠዋል፡፡” ብለው ነበር የቀድሞው መሪ፡፡ የብሔር ብሔረሰብ አካሄዳችንም ወደ ኢንዱስትሪ ልማት የሚሸጋገርበት ቀን ሊመጣ ይችላል፡፡

“ዘለዓለም ውሻ ሆኖ ከመኖር አንድ ቀን አንበሳ ሆኖ መሞት” የሚለውን መዘንጋትም ተገቢ አይሆንም፡፡ ሁሉም ወቅት ወቅት አለውና! ሁኔታዎችን እንደየአመጣጣቸው መመዘን፣ እንደየልኬታቸው ዓይነተኛ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ በደስታ ሰዓት ደስታችንን መግለጽ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የሚያዘናጉንን ሁኔታዎች፤ ይሆነኝ ብሎ ማሰብ ወሳኝ ነው! ይሄ በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም፣ በባህልም፣ በሥነ አዕምሮአዊ ሂደትም፤ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ መንግሥትም፣ ፓርቲም፣ ግለሰብም ተሁኖ ቢታሰብ፤ ዋናው ነገር ይሄው ነው፡፡

የአባይ ጉዳይ ላይ ያጠላበት የፖለቲካ ድባብ አሁን ሊገፈፍ ይገባል!! ግርማ ሠይፉ ማሩ

የውሃ፣ ኢነርጂና መስኖ ሚኒስትር በአባይ ተፋሰሰ ሀገሮች መካከል በተለይም በግብፅ፣ በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረውን ውይይት እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ያለበትን ደረጃ አሰመልክቶ ለምክር ቤት አባላት በባለሞያ የታገዘ ገለፀ ለማድግ ህዳር 22/2006 በምክር ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡ ይህ ገለፃ እና ማብራሪያ ከዚህ ቀደም ለዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ቀርቦ የነበረ መሆኑ በሚዲያ ተከታትለናል፡፡ በእኔ እምነት ቀድሞ መቅረብ የነበረበት ለምክር ቤቱ ሆኖ ከዚያ ቀጥሎ በየደረጃው ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ቢቀርብጥሩ የፕሮቶኮል አካሄድ ነው ለማለት እችል ነበር፡፡ ለማነኛውም ፕሮቶኮሉን እነተው እና በዚህ ደረጃ ለህዝብ ለማቅረብ ተነሳሸነቱ መፈጠሩ የዘገየም ቢሆን ተገቢ ነው ብዬ መውሰድ አልቸገርም፡፡ “ዘገዬ” የሚለውን ቃል ኢህአዴግና ሹሞቹ በጓዳ ግምገማ ካልሆነ በአደባባይ ውይየት ጊዜ ደስ አይላቸውም፡፡

በነገራችን ላይ ይህ ማብራሪያ አሁን መቅረቡ ጥሩ መሆኑን፤ ነገር ግን ዘግይቷል በሚል ለውሃ፣ መሰኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ለሰጠሁት አስተያየት ሚኒስትሩ “አልዘገየም ድርድሩ እዚህ ጋ የደረሰው በጥቅምት ወር ነው፡፡” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በእኔ እምነት ኢትዮጵያዊያን ማወቅ ያለባቸው የሶስትዮሽ ድርድሩን ሳይሆን አጠቃላይ መንግሰት ግድቡን ለመገንባት የሄደበትን መንገድ ነው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያዊ ምሁራን እና ጋዜጠኞች ከግብፅ እና የግብፅ ወዳጆች በተለያየ መልክ በሚያስረጩት መረጃ ሳይሆን በቀጥታ ከሀገራቸው ታማኝ መረጃ አግኝተው ጠንካራ አቋም እንዲይዙ ማድረግ የግድ የሚል ነው፡፡ የምሁራኑ እና የጋዜጠኞች መረጃ ማግኘት ያለጥርጥር ህዝቡ ሀገር በቀል መረጃ እንዲያገኝ ዋናኛ መንገዶች ናቸው፡፡ የዘገየ ማብራሪያ የምለውም ስለግድቡ አጠቃላይ ሁኔታ ነው እንጂ ስለ ሶስትዮሽ ውይይት ሂደትና ውጤት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በአባይ ተፋሰስ ላይ ቀደም ሲል በአሜሪካ ድጋፍ ቀጥሎም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2005/6 በተፋሰስ አገሮች ትብብር ሱዳን እና ግብፅ ጨምሮ በተደረገው ጥናት ሶሰት የግድብ ቦታዎች ተመርጠው የአሁኑ “ቦርደር ሳይት” በመባል የሚታወቀው የግንባታ ቦታ በሁሉም ተመራጭ እንደነበር ብዙ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ በአቶ አለማየሁ ተገኑ አገላለፅ “ፕሮጀክቱ ግማሽ
ድረስ በትብብር የተሰራ ነው”፡፡ ይህን የትብብር ስሜት ያፈረስው ምን አልባትም የግብፅ ከልክ ያለፈ አልጠግብ ባይነት እና በኢትዮጵያ ምድር ላይ የሚገኝ ቢሆንም አባይን የሚመለከት ፕሮጀክት በባለቤትነትን የመያዝ እና የማስተዳደር ፍላጎት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመጣው ከንቀት ጭምር ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከግብፅ ጋር በሽግግር መንግስት ወቅት የገቡት ቃል ወይም ስምምነት ለመናቃችን አንዱ የቅርብ ምሳሌ ነው፡፡ ኦቶ መለስ ይህን ቃላቸውን አጥፈው፣ ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያዊያን ቁጥጥር እና ባለቤትነት እንዲካሄድ የወሰዱት አቋም ተገቢም ትክክል ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ተመሳሳይ አቋሞች በብዙ ሁኔታዎች የታዘብን ቢሆንም
በዋነኛነት “ባንዲራ ጨርቅ ነው” በባንዲራ ቀን አከባበር፤ “የአክሱም ሀውልት ለወላይታ ምኑ ነው” በብሔር ብሔረሰቦች በዓል አከባበር ቀጥሎም በብሔር መለያየትን “ልዩነታችን ውበታችን” በሚል መፈክር መታጀቡ እና በሌሎች ሁኔታዎችን የተገነዘብን ሰዎች የሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ መታጠፍ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡ ለማንኛውም ኢትዮጵያን እና ህዘቦቿን ወደሚጠቅም አቋም በፈለጉት ዲግሪ መታጠፍ ቢዘገይም በአዎንታ መቀበል ይኖርብናል፡፡

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ጥሩ አካሄድ ሊባል የሚችለው የውጭ ዜጎችን በመጠቀም ዙሪያ በመንግሰት የተያዘው አቋም ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከወንድሞቻችን ኤርትራዊያኖች ጋር በመሪዎች ፍላጎት በገቡት “የድንበር” ተብዬ ግጭት፣ ችግሩን ለመፍታት በተለይም የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ የሀገር ውስጥ ባለሞያዎችን እና ታሪክ አዋቂዎቸን ባለመጠቀም የደረሰባትን ኪሳራ በደንብ የተረዱት ይመስላሉ፡፡ በአባይ ጉዳይ ዋናዎቹ ተዋናዮች ኢትዮጵያዊያኖች እንደ ነበሩ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም በቀጣይ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በሚደረግ ውይይት ከውጭ የሚባል አይኖርም፤ የሚያስፈልግ ባለሞያ ቢኖር ቀጥረን አገልግሎት ከመስጠት በዘለለ ገብቶ መፍተፈት አይፈቀድም፡፡ የሚል አቋም ኢትዮጵያ ይዛለች የሚለው መስመር እሰይ የሚያስብል ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አቋም የሚመራው በኢህአዴግም ቢሆን መደግፍ የግድ ይለናል፡፡

በዚህ አጋጣሚ እሰከ ዛሬ በነበረው ውይይት ከውጭ ሀገር ማለትም ከጀርመን፣ ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ እና ከደቡብ አፍሪካ ተወክለው ምክረ ሃሳብ ያቀረቡት ባለሞያዎች ጥንቅር “ለምን ከወዳጆቻችን ከነቻይና አልመጣም?” የሚል ፈገግ የሚያሰኝ በዚያውም የህውሃት አባላት አሁንም መንግሰት ሶሻሊሲት እንደሆነ የሚያሳብቅ ጥያቄ አንድ የምክር ቤት አባል ሰንዝረዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጭ ካፒታሊዝም ነው የምንከተለው ይበሉ እንጂ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በዚህ የሚስማሙ እንዳልሆነ በተለያየ መግለጫ ታዝበናል፡፡ እኛም ብንሆንን የምንስማማው አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በሚገልፁት መስመር ነው፡፡ የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከካፒታሊዝም ሳይሆን ወደ ሶሻሊዝም የሚጠጋ ርዕዮት እንደሆነ ነው የሚገባን፡፡ መድበለ ፓርቲ ስርዓት፣ ነፃ ገበያ፣ የግል ሀብት፣ ወዘተ ለእርዳታ ሰጪዎች ሲባል የሚቀርቡ ሹፈቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሹፈቶች ግን ይዋል ይደር አንጂ ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

በግሌ የኢህአዴግ በደል ከፍቶ ፅዋው ሞልቶ ቢፈስ እንኳን የሀገሬን ጥቅም አሳልፌ የምሰጥበት ምንዳም ሆነ የግፍ መጠን እንደሌለ በተደጋጋሚ ይፋ አድርጊያለሁ፣ ከዚህ የግል እምነቴ ጋር የሚፃረር ፓርቲም ሆነ ሌላ ስብስብ ጋር እንደማልሰራ አውቃለሁ፡፡ እንደዚያም ሆኖ የመንግሰት ሹማምንት የአባይ ግድብን ያህል ትልቅ ፕሮጀክት ይዘው ተቃዋሚና ገዢ ፓርቲ የሚል ክፍተት መፍጠር እንደሌለባቸው ሲነገራቸው፣ በተግባር የሚሰሩትን ሀቅ ወደ ጎን ትተው ጉዳዩን በሙሉ ፕሮፓጋንዳ ያደርጉታል፡፡ ኢህአዴግ ለፕሮፓጋንዳ የሚከፍለው መሰዋዕትነት የፈለገ ውድ ቢሆን ለመክፈል ዝግጁ ነው፡፡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስለግድቡ በቂ መረጃ በሌላቸው እና ይልቁንም ግርማ ሠይፉ ማሩ በመንግሰት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ፍፁም ደስተኛ ባልሆኑበት ሁኔታ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መንግሰትን ደግፈው ገንዘባቸውንያለምንም ጥያቄ እንዲቸሩ ይጠይቃል፡፡ በሀገር ውስጥም ቢሆን ሁሉን ተዉት ገንዘብ አምጡ ዘመቻ የሚያስገርም ነው፡፡ በውጭ የሚኖሩኢትዮጵያዊያን ይህን ግድብ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሊገነቡት የሚችሉበት አቅም እንዳለ ተገንዝቦ ግብፅን አንገት የሚያስደፋ መንገድ ከመቀየስ ይልቅ አሁንም በውጭ የሚገኙትን ዜጎች መከፋፈል ተገቢ አይደለም የሚል እምነት አለኝ፡፡ መንግሰት ከዚህ አንፃር
የሚጠበቅበት ለውጥ፤ ግብፅን አና ወዳጆቿን እሞኑኝ ብሎ ለልምምጥ ከሚያጠፋው ጉልበትና ሀብት የሚበልጥ አይደለም፡፡ መንግሰት ከዚህ አንፃር የሚከተለውን የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂ እንደገና መገምገም እና ሁሉንም በሚያሳትፍ መልኩ መቀረፅ እንዳለበት ማስገንዘብ ቢዘገየም የረፈደ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ግን የሚሰማ አይመስልም፡፡ ማን ነው ኢህአዴግ ሀፍ እንጂ ጆሮ የለውም ያለው?

በአባይ ዙሪያ በኢየትዮጵያ ለሚታሰብ ማንኛውም እንቅስቃሴ በቂ ተቃውሞ በግብፅ ስለ አለ በሀገር ውስጥ ሌላ ጠላት ለምን ትፈልጋላችሁ? ለሚል ጥያቄ ኢህአዴግ ሆደ ሰፊ መሆን አይችልም፡፡ ኢህአዴግ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ማግኘት የሚፈልገው፣ ለአብታዊ ዲሞክራሲ እግረ መንገዳቸውን ገብረው እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ እኔ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ አባል ለስልጣን ነው ትግል የማደርገው፡፡ ስልጣን ብንይዝ ይህች ሀገር ኢነርጂ እንደሚያስፈለጋት ለማወቅ ስልጣን መያዝ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ የአባይን ግድብ ለመገንባት መንግሰት የሚያወጣውን ዕቅድ በተመለከተ የተሟላ መረጃ እንዲኖረኝ የግድ ይላል፡፡

የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከዚህ አንፃር በጭፍን የአባይን ግድብ እንዲደግፉ እንጂ መረጃን መሰረት አድርገው ትንተና እንዲሰሩ እና የራሳቸውን ምክረ ሃሳብ እንዲሰጡ እድል የላቸውም፡፡ ለዚህ ጉዳይ የሚፈለጉት ልማታዊ የሚባሉት ጋዜጠኞች ብቻ ናቸው እነርሱም መንግሰት የሚለውን እንደ በቀቀን መድገም ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ በግብፅ ግን የግልም ሆነ የመንግሰት ሚዲያዎች ለሀገራቸው ይጠቅማል ያሉትን እንዲዘግቡ መረጃ ይስጣቸዋል፡፡ ማግለል ይቅር ስንል የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን
ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን ሚዲያውንም ጭምር ነው፡፡ አሁንም የአባይ ጉዳይ እና መረጃ ሁሉም ሚዲያዎች በሚያሳትፍ መልኩ ለሚዲያዎች መሰጠት ይኖርበታል፣ ሚዲያዎችም ይህን ኃላፊነት እንደሚወጡ ጥርጥር የለኝም፡፡ ለዚህም ማሳያ የ “ፋክት” አምደኞች ቤተሰብ የነበረችው መፅሄት አዲስ ታይምስ ከዓመት በፊት የአባይን ጉዳይ በልዩ ዕትም ቅፅ 1 ቁጥር 9 ህዳር 2005 ማውጣቷ እና በዚህ ዕትም ያስተላለፈችው መልዕክት ድጋሜ መነበብ የሚገባው ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ በኤክሰፐርቶች ፓናል ውስጥ ተሳታፊ ለሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ሁሉ ከመቀመጫዬ ብድግ ብዬ አድናቆቴን መግለፅ እፈልጋለሁ፡፡

ግብፆች የአባይ ጉዳይ ሲነሳ የፖለቲካ ልዩነታቸውን ትተው እንደ ግብፅ ሲያስቡ እኛን መለያየት ለምን ያስፈልጋል? የአባይ ግድብ ፕሮጀክት በተግባር የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮጅክት አንዲሆን የፖለቲካ ድባቡ ላይ ያጠላው የፕሮፓጋንዳ አዚም ሊገፈፍ ይገባል፡፡ አንድነት ፓርቲ ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን መጠቀም ተፍጥሯዊ መብቷ ነው ይላል፡፡ ይህ የማይገሰስ መብት ላይ ምን ፕሮፓጋንዳ ያስፈልጋል፡፡ የዛሬው መልዕክቴ ዋና ማጠንጠኛ በሀገር ጉዳይ እንዳንግባባ አዚም ያደረገብን ማን ነው? የዚህ አዚም መፍቻ ቁልፍ መተማመን እና ሀገራዊ ዕርቅ ይመስለኛል፡፡
መልካም በዓል ቸር ይግጠመን !!!!!!

[email protected]

‹‹የሕዝብ መብት ከሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ጋር መሥራት አስቸጋሪ ነው›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
‹‹የአንድነትን አቋም ሳያውቁ የፓርቲው አባል ሆነዋል ለማለት ያስቸግራል›› m አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ

ላለፉት ሁለት ዓመታት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር የነበሩትና ለ45 ዓመታት በፖለቲካ ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ከጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም.
ጀምሮ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት የወሰኑት አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ስላልተመቻቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ምላሽ ባለማግኘታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ እንደገለጹት፣ መድረክ ግንባር ከመሆኑ አስቀድሞ ባነሳቸው ሐሳቦች ላይ ሁሉም ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባዔ በማድረግ ከተወያዩባቸው በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ መስማማታቸውንም ለመድረክ በመግለጽ መድረክ ወደ ግንባር መሸጋገሩን አስታውሰዋል፡፡

በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. በአንድነት ፓርቲና በእሳቸው የአመለካከት፣ የአቋምና የአቅጣጫ ልዩነት መፈጠሩን የገለጹት ዶ/ር ነጋሶ፣ አንድነት ፓርቲ መድረክ ወደ ግንባር የተቀየረው በጠቅላላ ጉባዔውና በብሔራዊ ምክር ቤቱ እምነትና ውሳኔ ሳይሆን በአመራሮች መሆኑን በመጥቀስ፣ እንደማይስማማ በዚያን ወቅት ባደረገው ግምግማ ላይ በመግለጹ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

መድረክ ወደ ግንባር ከመቀየሩ አስቀድሞ ይፋ ባደረገው ፕሮግራም ላይ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተወያይተውና ተመካክረው በሕገ መንግሥት ጉዳይ፣ በቤት ጥያቄና በሌሎችም በተነሱ ነጥቦች ላይ መስማማታቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ነጋሶ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ላይ ብቻ ልዩነት እንዳለው አንድነት ገልጾ የሽግግር ሒደቱ በሰላም መፈጸሙን አስታውሰዋል፡፡

ሽግግሩ ወራትን ካስቆጠረ በኋላ በሕገወጥ መንገድ እንደተደረገ በማስመሰል ወደኋላ መመለስ አሳፋሪ ድርጊት ከመሆኑም በተጨማሪ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትና የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት፣ ፓርቲው የማይስማማበትን ነጥብ ይዞ ወደ መድረክ በመሄድ መወያየት ሲገባቸው፣ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠታቸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የነበሩትን የተሳሳቱ ሒደቶች በመጥቀስ እርማት እንዲደረግ ዶ/ር ነጋሶ ለአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ቢሆንም፣ ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላው ዶ/ር ነጋሶ የሚያነሱት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ላይ የተጠቀሰውን ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት የራስን ዕድል በራስ ከመወሰን እስከ መገንጠል›› የሚለውን የሕዝቦች የመብት ጥያቄ አንድነት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አለመሆኑን ሲሆን፣ ‹‹የሕዝብን መብት ከሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ጋር መሥራት አስቸጋሪ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አንድነት የመድረክን ወደ ግንባር መቀየር የማይቀበለው ‹‹የውህደት›› ኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ መመሥረት እንዳለበት ስለሚፈልግ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ነጋሶ፣ በሕጋዊና በትክክለኛ መንገድ ስምምነት የተፈጸመበትን ‹‹ግንባር›› ‹‹ውህደት›› ካልሆነ ማለት የማይሆንና የማያስኬድ መንገድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ያልተስማሙባቸውን ነጥቦችና ስምምነት ከተደረገ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አግባብ አለመሆኑን በመጠቆም ላቀረቧቸው ጥያቄዎች የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ምላሽ በመንፈጉ ምክንያት፣ ዶ/ር ነጋሶ ከፖለቲካው ዓለም መሰናበታቸውን ይፋ ቢያደርጉም፣ ቀደም ብሎም ከፖለቲካ ሥራና ተሳትፎ ለመልቀቅ በማኮብኮብ ላይ እንደነበሩ አልሸሸጉም፡፡

ምክንያታቸውንም ሲገልጹ ነሐሴ 3 ቀን 2005 ዓ.ም 70 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡ ከዕድሜያቸው ከግማሽ በላይ ለ45 ዓመታት በፖለቲካ ውስጥ ቆይተዋል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብን የፖለቲካ ባህል ሲያስታውሱ፣ በኦሮሞ ገዳ ዲሞክራሲ አንድ መሪ ዕድሜው 48 ሲሆነው የአመራር ሥልጣኑን ለወጣቱ መልቀቅ እንዳለበት የሚገልጸውን ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ መሆኑንም ማሰባቸውን አብራርተዋል፡፡

ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ዓለም ራሳቸውን ማግለላቸውን ከዚህ በኋላ በማንኛውም መንገድ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በአባልነትም ሆነ በመአራርነት እንደማይሳተፉ ያረጋገጡት ዶ/ር ነጋሶ፣ ‹‹ጆሮዬ ለፖለቲካ ክፍት ይሆናል፤ የማስበውን በጽሑፍና በአፌ እናገራለሁ፤ አንድነትንም ሆነ ሌሎችንም በመዋቅራዊ መልክ ሳይሆን እደግፋለሁ፤ ሲያስፈልግ እተቻለሁ፤ ሲያስፈልግ እቃወማለሁ፤›› ብለዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ ለዶ/ር ነጋሶ ከፖለቲካ መገለል ምክንያት ስለመሆኑ ለተነሳለት ጥያቄ በሕዝብ ግንኙነት አማካይነት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ፓርቲው በቅርቡ አዲስ አመራር መምረጡንና ቀደም ሲል በሊቀመንበርነት ሲመሩ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ፣ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሥልጣን ሽግግሩን ፈጽመው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አቅርበው ሽግግሩን ማፅደቃቸውን የገለጹት የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ናቸው፡፡

ለብሔራዊ ምክር ቤቱ የአዲሱን አመራር ቀጣይ የሥራ የሽግግር ጊዜ ሲያቀርቡ፣ ከዕድሜያቸው ጋር በተገናኘ ለቤተሰቦቻቸው ራሳቸውን ከፖለቲካ እንደሚያገሉ ቃል መግባታቸውን የተናገሩት አቶ ሀብታሙ፣ በመድረክ ላይ ያላቸውን አቋምም ግልጽ ማድረጋቸውን አክለዋል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ አንድነት መድረክን መገምገሙና ማጥናቱ ትክክልና ተገቢም ነው፡፡ የግንባሩ አባል የሆነ ድርጅት ፖለቲካውን አግባብ ባለው መንገድ እየመራ ነው? አይደለም? የሚለውን ጥናት ማድረግ ተገቢ ነው ካሉ በኋላ፣ መድረክ አሁን ባለው ሁኔታ የሚታየውን ነገር ሁሉ ማሻሻያ በማድረግ ሊቀጥል ይገባል የሚል አቋም እንዳላቸው መናገራቸውን አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ መድረክ ወደ ውህደት በማደግ አንድ ግዙፍ ብሔራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር ያቀረበውን ሐሳብ በቀላሉ ሊሳካ የሚችል ባለመሆኑ፣ ሐሳቡን እንደማይደግፉም ዶ/ር ነጋሶ ማሳወቃቸውን አቶ ሀብታሙ ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ያነሱትን የልዩነትና የድጋፍ ሐሳብ አንድነት ፓርቲ እንደሚያከብር የገለጹት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው፣ ፓርቲው ግን ግልጽ የሆኑ የፖለቲካ አማራጮች እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግልን ወደፊት ለመግፋት ብሔራዊ ምክር ቤቱና ጠቅላላ ጉባዔው አስቀድሞ ባዘጋጁዋቸውና በሚያሻሽሉዋቸው ነጥቦች ትግሉን እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡

አንቀጽ 39ን በሚመለከት አንድነት የብሔር ብሔረሰቦችን መብት በተመለከተ ሕገ መንግሥቱ የሚያነሳቸውን ነጥቦች ፍፁም በሆነ ሁኔታ እንደሚያከብር የተናገሩት አቶ ሀብታሙ፣ ዶ/ር ነጋሶ የአንድነት ፓርቲን አቋም በግልጽ ሳያውቁ የፓርቲው አባል ሆነዋል ለማለት እንደሚያስቸግር አክለዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ ከአንቀጽ 39 የማይቀበለው በመጨረሻው ንዑስ አንቀጽ ላይ የተቀመጠውን ‹‹እስከ መገንጠል›› የሚለውን ሐረግ መሆኑን ይህንንም በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት ላይ የተቃጣ አደጋ በመሆኑ፣ መቼም ቢሆን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማንም ለድርድር እንደማያቀርብ በግልጽ ሊታወቅ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ላለፉት 45 ዓመታት በቆዩበት የፖለቲካ ሕይወታቸው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል፣ እንዲሁም የኢሕአዴግ አባል የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) አመራር እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ከኢሕአዴግ ጋር ከመለያየታቸው በፊት ለስድስት ዓመታት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ከቀድሞ የአገር መከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ ጋር በመሆን የአንድነት ፓርቲ አባል ከመሆናቸውም በላይ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የፓርቲው አመራር አባልና ሊቀመንበር መሆን ችለው ነበር፡፡

ዓለም አቀፍ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ብድርና ዕርዳታ እንዲያቆሙ ግብፅ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን መንግሥት መረጃ እንዳለው አስታወቀ፡፡

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው የሦስትዮሽ ድርድር ሦስተኛ ስብሰባ በቅርቡ ያለውጤት ከተበተነ በኋላ፣ በግብፅ በኩል አፍራሽ የሆኑ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓርብ ረፋድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና፣ በግብፅ በኩል የቀረበውና በኢትዮጵያና በሱዳን ውድቅ የሆነው ሐሳብ፣ እስካሁን ግድቡን አስመልክቶ የተጀመሩ ውይይቶችን ወደኋላ የሚመልስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ ባለሙያዎች ያሉበትና ከሦስቱም አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የኤክስፐርቶች ፓነል ለአንድ ዓመት በግድቡ ዙሪያ ጥናት አካሂዶ ባወጡት ሪፖርት፣ ከተወሰኑ ቴክኒካዊ ማስተካከያዎች ውጪ ግድቡ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሟላ መሆኑን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የፓነሉ ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ የሚያደርግ ከሦስቱ አገሮች የተውጣጡ የውኃ ባለሙያዎች ያሉበት ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑን፣ ግብፆች አዲስ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ የኮሚቴውን ሥራ በበላይነት እንዲከታተል የሚል ሐሳብ ነው ያቀረቡት፡፡

እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ፓነል መቋቋም ላይ ሳይሆን፣ ሚናውን በተመለከተ ነው፡፡ በዚህ ልዩነት የተነሳ ያለውጤት ስብሰባው ከተበተነ በኋላ፣ ግብፆች በሚዲያዎቻቸው ‹‹ኢትዮጵያ ለመተባበር እምቢተኛ ሆነች›› እያሉ እያቀረቡ መሆኑንና ከዓለም ባንክ፣ ከአይኤምኤፍና በሌሎች ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በምንም ምክንያት ኢትዮጵያ በገንዘብ እንዳትደገፍ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን መንግሥት መረጃ እንደደረሰው አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል፡፡

የግድቡ ግንባታ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ይቋረጣል የሚል እምነት ያላቸው ግብፃውያን፣ የገንዘብ ተቋማቱ ኢትዮጵያ የዚህን ግድብ ግንባታ ካላቆመች በማንኛውም መንገድ የሚያደርጉትን ዕርዳታ እንዲያቆሙ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡ ግብፃውያን ከዚህ አፍራሽ ድርጊታቸው ተቆጥበው በኤክስፐርቶች ፓነል ሪፖርት መሠረት መተባበራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ ከተለመደው አፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማስታወቅ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሑመራና በመተማ አካባቢ ኢትዮጵያ ለሱዳን መሬት ስለመስጠቷ እየተነገረ ስላለው ጉዳይ መንግሥት አስተባብሏል፡፡ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሱዳን በግድቡ ላይ ባሳየችው አዎንታዊ አቋም ምክንያት፣ ሲያወዛግብ የቆየውን ሰፊ የድንበር መሬት መስጠቷ የተዘገበ ቢሆንም፣ አምባሳደር ዲና ግን፣ ‹‹እንኳን መሬት ሊሰጥ ይቅርና በጉዳዩ ላይ የሚደረገው ውይይትም አልተቋጨም፤ እስካሁንም ስምምነት ላይ የተደረሰ ነገር የለም፤›› ብለዋል፡፡

ላለፉት አሥር ዓመታት ድንበሩን በተመለከተ ሲሠራ የቆየው የጋራ ኮሚሽን፣ በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር እንዲካለልና የግጭት መንስዔ የሆነውን ጉዳይ ለመፍታት እየሞከረ መሆኑን፣ በቅርቡ ‹‹ለሱዳን መሬት ተሰጠ›› ተብሎ የተነገረው ግን መሠረት የሌለው ወሬ መሆኑን አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል፡፡

ሐበሾቹ ነገ ጠዋት የጌታን ጥምቀት በዩጋንዳ በልዩ መንፈሣዊ ስርዓት ያከብሩታል!!!

መንበረ ፓትርያኩን በሰሜን አሜሪካ ባደርገው በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው የካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የደብሩ ማሕበረ ካህናትና ማህበረ ምዕመናን በዩጋንዳ ነገ ጠዋት ጥር ዐሥራ ዐንድ ቀን የጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓልን በከፍተኛ መንፈሣዊ ሥነ ሥርዓት እንደሚያከብሩ ተገለፀ።
ከሠንበት ቅዳሤ በኋላ የመድሃኒያለምና የቅዱስ ሚካዔል ታቦታት በምዕመናን ታጅበው በመሪጌታ ይህይስ ዓለሙ መሪነት ያሬዳዊ ዝማሬ የዕለቱ ምልጣን<ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ወልደነ ዳግመ እማየ ወእመንፈሠ ቅዱስ እሙነኮነ ለፀሐየ ፅድቅ አስተርዕዮቱ አማን መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ > የሚቀርብ ሲሆን የደብሩ ማሕበረ ካህናት ከማህበረ ምዕመናን ጋር ፈጣሪ አምላካቸውን በያሬዳዊ ዜማ ያመሠግናሉ። ጥምቀተ ባሕሩም ይባርካል።
አስተማማኝ የፖሊስ ጥበቃ ስለሚደረግ ምዕመናን መኪናቸውን ደብሩ ባዘጋጀው የማቆሚያ ስፍራ በማድረግ ያለስጋት በዓሉን እንዲያከብሩ የቤተክርስትያኒቱ አስተዳደር ጽ /ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
ሐበሾቹ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በዩጋንዳ በጋራ በመሆን ፈጣሪያቸውን በተለይ ዘወትር ዕሁድ እንደሚያመሠግኑ ይታወቃል።አባ ኃይለማርያም በአሉን በማስመልከት የወንጌል ማዕድ የሚያቀርቡ ሲሆን የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ፀሐይ ደስታ በበበዓሉ ፍፃሜ ላይ ቃለ ምዕዳን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

የካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ማህበረ ካህናትና የደብሩ አስተዳደር ጽ /ቤት ለመላ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ጥምቀቱ አደረሣችሁ እያሉ መልካም ምኞታቸውን እንዳስተላለፉ የዚህ ዜና ዘጋቢ ጨምሮ ገልጿል።
አክሊለ ሠማዕት
penEthiopian

በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡

በአደባባይ የሚጽፉ ሰዎች ሁለት ነገሮችን ለይተው መገንዘብና ለሌሎችም ሲየያስተላልፉ ለይተው ማስተላለፍ አለባቸው፤ አንዱ የሆነና የተረጋገጠ ሁነት ነው፤ይህንን ሳይበርዙና ሳይከልሱ እንዳለና እንደተገኘ ማስተላለፍ ግዴታ ነው፤ ሁለተኛው የራስ አስተያየት ነው፤ የጠራውንና የነጣውን አውነት ከጎደፈ የግል አስተያየት ጋር አጋብቶ ማቅረብ ወይ አለማወቅ ነው፤ አውቀው ከሆነም ለማታለል ከመሞከር የሚቆጠር ነው፤ በአለንበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ የምናየው ፊደሎቹን ማወቅ እንደሙሉ እውቀት ይቆጠራል፤ ወይም በሌላ አነጋገር ፊደልን ማወቅ የመጻፍ ችሎታን ይሆናል፤ ይህ ትልቅ ስሕተት ነው፤ ፊደሎችን ማወቅ ትልቅና መሠረታዊ የእውቀት ጎዳና ላይ መግባት ነው፤ ጎዳናው ግን በጣም ረጅም ነው፤ በእውቀት ጎዳና ላይ መግባት የእውቀት ባለቤት ከመሆን ጋር እንዳይደባለቅ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአገራችን ፊደልን ማወቅ ሌላም አደጋ አለው፤ ፊደልን ማወቅ ከሥልጣን ጋር ሲጋባ የሚያስከትለውን ውድቀት ከአንዴም ሁለቴ አይተናል፤ እያየንም ነው፤ ስለዚህም ፊደል ኃላፊነትን ያመጣል፤ አለዚያ በአለፉት ሠላሳ ዓመታት ያየነው ውድቀት እየተከበረ ይቀጥላል፡፡

መጻፍ እንደመናገር ሊቆጠር ይቻላል፤ሆኖም በመጻፍና በመናገር መሀከል ትልቅ ልዩነት አለ፤ በንግግር ላይ ከሰዎች በሚቀርበው ጥያቄም ሆነ ተቃውሞ እንዲህ ማለቴ ነው ብሎ የተናገሩትን እዚያው ለማረምና ለማስተካከል ይቻላል፤ በተጻፈ ነገር ላይ እንዲህ ዓይነቱ ወዲያው የመታረም ዕድል የለም፤ ስለዚህም ለመጻፍ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው፤ ከላይ እንደተገለጸው ፊደልና ሥልጣን ሲጋቡ ሰንደቅ ዓላማው ጨርቅ ነው ከማለትም ሊያልፍ ይችላል፤ ለምሳሌ የደርግን የትርፍ ቤቶች አዋጅ ብንመለከተው ‹‹ትርፍ ቤት›› ሲል ትርፍን እንተወውና ‹‹ቤት›› ለሚለው ትክክለኛ ትርጉም አልሰጠም፤ ስለዚህም በጭራሮ የተያያዘ ምንም ‹‹ቤት›› የሚያሰኘው (መኝታ ቤት፣ ወጥ ቤት፣ መታጠቢያ ቤት፣ … የሌለው) በሃምሳ ሳንቲም የሚከራይ ነገር ‹‹ቤት›› ተብሎ በሺህ ብር ከሚከራይ ቤት ጋር ተወረሰ! ያፈረ የለም እንጂ አሳፋሪ ነው!

እንዲህ ዓይነቱ ችግር ከየት የሚመጣ ነው? አንድ አጠቃላይ የአስተሳሰብ ችግር አለ፤ ለየት ያለውን ከጅምላው፣ ግዙፉን ከረቂቁ፣ አንዱን ከብዙው ያለጥንቃቄ ማደባለቅ በአማርኛ በጣም የተለመደ እየሆነ ነው፤ የአስተሳሰብ ችግር ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ (አበሻና ሆድ የሚለው ጽሑፍ ባሕር ተሻግሮ የአበሻን ነገር-ዓለም ትቶ የተጠበሰ ውሻ (ሆት ዶግ) የሚበላውንም አስቀየመውና ሌሎች ስለአበሻ የጻፍኋቸውን ተውኩት እንጂ አበሻና መናገር የሚለው በተለይ ለባሕር ማዶው ዘሎ-ጥልቅ ተስማሚው ነበር፤) በማናቸውም ነገር ላይ ለመቀባጠር በጣም ኃይለኛ ምኞት አለው፤ አንዱ ያስተሳሰብ ችግር ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፤ ሳያስቡና ሳይጨነቁ አፍ እንዳመጣ ከመናገር ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፤ አሁን ደግሞ የጎሠኛነት ሥርዓት ካመጣብን ጣጣ ዋኖቹ የአስተሳሰብ ችግሮች እነዚህ ናቸው፤ የቡድን መብትን መሠረታዊ አድርጎ የግለሰብን መብት ጨፍልቆ የተነሣው የወያኔ የጎሣ ሥርዓት ከሃያ ዓመታት በኋላ በስንት ጥረት የደረሰበት አሁንም የተዛባ ድምዳሜ የቡድን መብትንና የግለሰብ መብትን ጎን ለጎን አቁሞ እኩል ናቸው ማለትን ነው፤ ለውጡ የተጣራ ባይሆንም ሃያ ዓመታት መፍጀቱ የወያኔን የመማር ፍጥነት የሚያመለክት ነው፤ የሥልጣን ጉልበትና የሥልጣን ምኞት ተጽእኖ እንደአንድነት ያለውንም የፖሊቲካ ፓርቲ ፐሮግራሙን እንዲለውጥና የግለሰቦችንና የቡድን መብቶች በአንድ ደረጃ ላይ እንዲያስቀምጥ ተደርጎአል፤ ከቡድን ውስጥ ግለሰቦች ሁሉ ሙልጭ ብለው ሲወጡ ስለቡድን መብት የሚያወራ ምን እንደሚባል እንጃ! ከቀኝ ወደግራ የዞረ? ወይስ ከግራ ወደቀኝ? ወይስ … ቀኝ ፖሊቲካ ባዶ ከረጢት ይዞ ይቀራል።

በተደጋጋሚ እንዳየሁት ለግለሰብ መብቶች የቆመ ቀኝ-ዘመም፣ ለቡድን መብቶች የቆመ ግራ-ዘመም የሚባል ይመስላል ይህ ስሕተት ነው።

ቀደም ሲል የታወቀው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እኔን ቀኝ-ዘመም እያለ ጽፎ ሳይ ይህ ሰው በአውነት አንድ መዝገበ ቃላት ማየት አቅቶት ነው? ወይስ እኔን በተለየ ዓይን ለማየት ከመፈለግ የተነሣ ነው? ወይስ የሲአይኤውን መልክተኛ ፖል ሄንዜን ሰምቶ ነው? የሱ ጎሣ አባል መሆንንና አለመሆንን እኔ የምመርጠውና የምወስነው አይደለም፤ ታምራት በኢትዮጵያዊነት ወይም በዜግነት ዓይን ሊመለከተኝ አለመቻሉም የእኔ ጥፋት አይደለም፤ ሁሉም ቢቀር በሰውነት ደረጃ ሊያየኝ ይችል ነበር፤ ይህንንም አልቻለም፤ እንግዲህ ወይ እኔ ሰው አልሆንኩለትም፤ ወይ እሱ ወደሰውነት ደረጃ አልደረሰም፤ በታምራት ነገራ ቀኝ-ግራ መጋባት እንደኔው ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ የነበረው ክፍሉ ሁሴን ወደጥናት ተመልሶ የታምራትን ስሕተት አረጋገጠ፤ እኔም እንዲሁ አደረግሁና የታምራት ነገራን ግራ መጋባት አረጋገጥሁ፤ ታምራት ነገራ የጎሣ ቀኝ ገብቶት ግራ ፖሊቲካ ቀኝ ሆኖበታል! ቀኝ-ግራ ፖሊቲካ በጎሣ አባልነት የሚገኝ ወይም የሚታጣ ይመስለዋል፤ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ሀብትና ሌላ ማናቸውንም ነገር ከቁም-ነገር ሳይቆጥሩ ለማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ ማግኘት የሚገባውን መብት እንዲያገኝ ቆሞ መከራከር ለታምራት እንግዳ ነገር ይመስለኛል፤ ገና እሱ ሳይወለድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር በተደረገ ስብሰባ ላይ ለምን የኢትዮጵያ ራድዮ በኦሮምኛ አይናገርም? በማለት ጌታቸው ኃይሌ ጋር ሆነን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሰዎችን ሞግተን ነበር፤ ይህ ለታምራት የቀኝ ፖሊቲካ ነው፤ የሱ ጎሣ-ዘመም ፖሊቲካ ግራ መሆኑ ነው! ጎሠኛነት ምን ጊዜም የትም ቦታ እንደግራ ፖሊቲካ ተፈርጆ አያውቅም።

አሁን ደግሞ ሰሎሞን አብርሃም ይህንኑ የታምራት ነገራን ስሕተት ለመድገም የዳዳው ስለመሰለኝ በዝምታ ለማለፍ አልፈለግሁም፤ ሰሎሞን (liberalism) የሚለውን የአንግሊዝኛ ቃል በባሕርዩ የሌለበትን ትርጉም ሊሰጠው ይዳዳዋል፤ ሰሎሞን አብርሃም ሊጽፍበት የተነሣው ጉዳይ በእኔ ግምት በጣም ወቅታዊና አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን የግል ስሜትን ከሁነት ጋር፣ ያልተጣራ የተውሶ ሀሳብን (‹‹ፊዩዳሊዝም፣ ሊበራሊዝም››…) ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር በማያያዝ አስተሳሰቡን ያጎደፈው ይመስለኛል፤ ያነሣው ጉዳይ በተለይም እንደሱ ላለ ፖሊቲከኛ ከስሜተኛነትና ከወገንተኛነት የጸዳ ቢያደርገው (‹‹ወግ አጥባቂ፣ቀኝ አክራሪ›› ..)፣ወይም ደግሞ ያልተጣራ (‹‹የሊበራል ዴሞክራሲን ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ይመስላሉ፤›› እያለ በጎን ከሚጎሽም የጸዳውን እውነት ፊት ለፊት እያቀረበ ድካማቸውን ቢተነትን የሚጠቅም ይሆን ነበር።

ግራና ቀኝ ፖሊቲካ የሚባለውን ከጎሣ ፖሊቲካ ጋር ለማገናኘት የሚፈልጉ ሰዎች ወጣቶችን ወደአስከፊ ስሕተት እንዳይመሩ መጠንቀቅ ያለባቸው ይመስለኛል፤ የጎሣ ሥርዓትን የሚቃወሙትን ወገኖች በሌላ መንገድ ለመቋቋም ቢሞክሩ የተሻለ ነው፤ በጎሣ ክፍፍል ማመን ሌላው ቀርቶ በሰውነት ደረጃ ለመሰለፍም ያስቸግራል፤ ለማናቸውም የጎሣ ፖሊቲካን ከግራ ፖሊቲካ ማዛመዱ እሳትና ውሀ ነው።

የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባፈለግ፣ ቁሸት ሕኖይቶ) ህዝብ የከፈተው ዓመፅ ዛሬ (ዓርብ 09/05/06 ዓም ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ከአስር ደቂቃ (12:10) ላይ ቆሟል። ህዝብ ወደየቤቱ ተመልሷል። የፀጥታ ሃይሎች ግን ከአከባቢው አልራቁም።
አስተዳዳሪዎች ህዝቡን በፌደራል ፖሊስ አስከብበው ሲያስፈራሩት የዋሉ ሲሆን የህዝቡን ጥያቄ (ካሳ የመክፈሉ ጉዳይ) ለመመለስ ተስማምተዋል። ስለዚህ ህዝቡ በጠየቀው መሰረት መንግስት ተገቢውን ካሳ ይከፍላል። የታሰሩት የአከባቢው ኗሪዎች ግን አይፈቱም። ህዝቡ “የታሰሩትን ይፈቱልን” ብሎ ሲጠይቅ “እርምጃ እንወስድባችኋለን፣ ማንም መጥቶ አያድናችሁም” የሚል ማስፈራርያ ደርሷቸዋል። ስለዚህ መንግስት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የታሰሩትን ዜጎች ለመልቀቅ ዝግጁ አይደለም።
የመንግስት አካላት ህዝቡን ካሳ ለመክፈል ሲስማሙ የህዝቡን ጥያቄ ትክክለኛነት ተቀብለውና አምነው እንደሆነ አቅርበዋል። ጥያቄው ያነሱት ዜጎች ከእስር ለመፍታት ግን ፍቃደኛ አይደሉም። በትግራይ ዜጎች መብታቸው ሲጠይቁ ለእስር ይዳረጋሉ። የአፅቢ ወንበርታ ጠያቂዎች ምሳሌ ናቸው። ታሳሪዎች የዛሬን ጨምሮ ስምንት ናቸው።
ጥያቄ የጠየቀ ዜጋ ለምን ይታሰራል? ጥያቄ የመጠየቅ መብት የለውም? መንግስት የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ለምን ወደ ሃይል እርምጃ ይሄዳል? አምባገነኖች በራስ የመተማመን ባህሪ ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።
አብርሃ ደስታ

የወያኔን የሚዲያ አፈና ማመከን የጊዜው አጣዳፊ ተግባር ነው::

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የአገራችንን በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝባችን ስለራሱና ሰለአገሩ ምንም አይነት መረጃ ከአማራጭ የመገናኛ ብዙሃን ምንጮች እንዳያገኝ ያሉትን ዕድሎች በሙሉ ድርግም አድርጎ ዘግቶ ኖሮአል።

የወያኔ መሪዎችና ተሿሚዎች በየግላቸው ምንም ቁብ በማይሰጡትና ተቃዋሚዎች እንዲያከብሩት ነጋ ጠባ በሚወተውቱት የአገሪቱ ህገመንግሥት አንቀጽ 29 ዕውቅና ካገኙ የዜግች መብቶች አንዱ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ተፈጥሮአዊ መብት ሆኖ ሳለ እየተካሄደ ያለውን የሥልጣን ብልግናና አገሪቱን እያራቆተ ያለውን ዘረፋ በመተቸታቸው ብቻ በአንድ ወቅት እንደ አሸን ፈልተው የነበሩ የነጻ ጋዜጣ አዘጋጆችና አሳታሚዎች በሽብርተኝነት ተወንጅለው ከፊሉ ከአገር እንዲሸሽ ሌላው አፉን ዘግቶ እንዲቀመጥ አለያም የፈጠራ ክስ እየተመሰረተባቸው እስር ቤት እንዲማቅቁ ተደርገዋል። አሁንም በመደረግ ላይ ናቸው። በወያኔ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት አፈና የአሜሪካና የጀርመን መንግሥታት በየግላቸው የሚያስተዳድሩዋቸው የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮኖች እንኳ ከጥቃቱ ማምለጥ ስላልቻሉ እነሆ እስከዛሬ ያልተቋረጠ የማጥላላት ዘመቻ ይካሄድባቸዋል።

ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ከቻሉና ከየትኛውም መዲያ መረጃ የማግኘት መብታቸው ከተረጋገጠ ሥልጣን ላይ ውሎ እንደማያድር ጠንቅቆ የተረዳው የወያኔ አገዛዝ በዚህ የሚዲያ አፈና ተግባሩ በመቀጠል ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮን እንዲሁም ህዝብ አልፎ አልፎ ሃሳቡን ለመግለጽ በሚገለገልባቸው ጥቂት የአገር ውስጥ ህትመቶች ላይ የተለመደውን የጥቃት ጅራፉን ለማሳረፍ ታጥቆ ተነስቶአል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በመረጃና ደህንነት መሥሪያ ቤቱ ተዘጋጅቶ የህወሃት ቀድሞ ታጋዳላዮች በሚቆጣጠሩትና እንደግል ንብረታቸው በሚፈነጩባቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የተሰራጨው ዘገባ እንደሚያመለክተው ከአሁን ቦኋላ ማንኛዉም የመንግስት ባለስልጣን፤ የገዢዉ ፓርቲ አባላትና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ምንም አይነት ቃለመጠይቅ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ እንዳይሰጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአል። ማስጠንቀቂያውን ተላልፎ በተገኘ ማንም ሰው ወይም ድርጅት ላይ የአሸባሪነት ወንጀል ክስ እንደሚመሰረትበትም ዛቻና ማስፈራሪያ በተለመደው የቃላት ጋጋታ ተገልጾአል።

ይህ ከሰሞኑ የወያኔ ብሄራዊ መረጃ ደህንነትና ኮሚኒኬሽን መስሪያቤት ያወጣዉ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎች የሚናገሩትን ፤ የሚጽፉትን፤ የሚያነቡትንና የሚሰሙትን ብቻ ሳይሆን የሚያስቡትንና ሊደግፉት ወይም ሊቃወሙት ይችላል ተብሎ የሚጠረጠረውን ሁሉ አስቀድሞ ለመቆጣጠር ፍላጎቱ ያለው መሆኑን ነው።

ከሰሞኑ መግለጫ የተለየ ነገር ቢኖር ህዝባችንን በፍርሃት አንገት ለማስደፋት ሲባል የወያኔ ፓርላማ በሽብርተኝነት የፈረጀውን ንቅናቄያችንን ግንቦት 7ንና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንን በአንድነት የመፈረጅ ስልት ይፋ መደረግ መቻሉ ብቻ ነው።

የወያኔን ቁንጮዎች ጨምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይገነዘበዋል ብለን እንደምናምነው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት የተቋቋመው የአገራቸው ጉዳይ የሚያንገበግባቸው ቅን ዜጎች ባዋጡት የገንዘብ መዋጮና በሚሰጡት ያልተቋረጠ የእውቀትና የፋይናንስ ድጋፍ ነው። ተቋሙ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 22 አመታት በወያኔ የሚዲያ ሞኖፖሊ ተይዞ የኖረውን የአገራችንን አየር ክልል ሰንጥቆ በመግባት ህዝባችን ስለ አገሩና ስለራሱ ጉዳይ በቂ መረጃ እንዲያገኝ በመጣር ላይ ያለ ብቸኛ መገናኛ ብዙሃን ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኝ ነው።

ሃቁ ይሄ ሆኖ ሳለ ለምንድነዉ ታዲያ ላለፉት ሁለት አመታት ስብሀት ነጋን ጨምሮ የተለያዩ የገዢዉ ፓርቲ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ሳይቀሩ በተደጋጋሚ ቀርበዉ በስነ ስርኣት የተስተናገዱበትን ይህንን ሚዲያ የወያኔ ፓርላማ ቀደም ሲል በአሸባሪነት ከፈረጀው ንቅናቄያችን ግንቦት 7 ጋር መወንጀሉ ለምን ይሆን ? መልሱ ቀላል ነው። ከአገዛዙ ያልወገኑ ማናቸውም ሚዲያዎች እንደሚያደርጉት ኢሳት ስርጭቱን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነጋ ጠባ በኢትዮጵያ ቴለቪዥንና ሬዲዮ የሚደሰኮረው ልማትና ዕድገት ተጠቃሚው ሥልጣንን የሙጥኝ ያሉ የቀድሞ ታጋዳላዮችና የቅርብ ዘመዶቻቸው እንጂ ህብረተሰቡ አለመሆኑን በግልጽ ከማጋለጥ ባለመቆጠቡ ጥርስ ውስጥ ገብቶአል። ከዚህም በተጨማር ለምዕራባዊያን ፍጆታና ድጋፍ ማግኛ በየአምስት አመቱ የሚደረገው የምርጫ ተውኔት ወቅት ስለተቃረበ ተቃዋሚዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው በዚህ ሚዲያ ያብጠለጥሉኛል፤ የስልጣን ብልግናውንና የሙስናውን ጉዳይ ይዘከዝኩታል የሚል ፍርሃትና ስጋትም አለው። በእርግጥ ዝክዘካው በይስሙላ ምርጫው ላይ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ እኛ የጉዳዩ ባለቤቶች ቀርተን ምዕራባዊያን ለጋሾችም አያጡትም። ሆኖም ግን ወያኔ ፈርቶአል ተረብሾአል። ስለዚህም ኢሳትና አሁን በአክራሪ ድርጅቶች ልሳንነት የተፈረጁት የአገር ውስጥ ህትመቶች ከምርጫው በፊት መጥፋት ይኖርባቸዋል። ያ ካልሆነ በመላው አገሪቱ የሰፈነው የሥልጣን ብልግናና የሃብት ዘረፋ የፈጠረው የኑሮ ውድነት ያስመረራቸው ሚሊዮኖች የመጪውን ምርጫ ውጤት አስታከው ሆ ብለው አደባባይ ሊወጡና የአገዛዙን የሥልጣን እድሜ ለማሳጠር ተቃዋሚዎች ለሚያካሄዱት ትግል መሳሪያ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ተፈርቶአል። ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከብዙ የወያኔ ጥቃትና አፈና ተርፈው አገር ውስጥ በመታተም ላይ በሚገኙ 8 መጽሄቶች እና ለኢትዮጵያዊያን ብቸኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ በማገልገል ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ ላይ የተጀመረውን አዲሱን ዘመቻ በቸልታ አይመለከተውም።

መረጃ ሃይል ነውና አገራችን ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ሥር እየሰደደ የመጣው ድህነት እንዲቀረፍና ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የሚሻ ዜጋ ሁሉ ወያኔ በሚዲያ ላይ የጀመረውን ጥቃት ለማስቆም ከጎናችን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል።

ወያኔ በመረጃና ደህንነት መሥሪያቤቱ አማካይነት ያስተላለፈው የሰሞኑ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ በተለይም በሰላማዊና ህጋዊ ትግል ወያኔን መቀየር ይቻላል በማለት አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች መተንፈሻ ለማሳጣት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ህዝባችን እንዲረዳና በህዝባዊ እምቢተኝነት ሴራውን ለማክሸፍ መነሳት ጊዜው ግድ የሚል የወቅቱ አንገብጋቢ የትግል ጥሪ መሆኑን ግንቦት 7 የፍትህና የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያስገነዝባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የአማራ ክልል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ይኖራቸል ብለው የሚጠረጥሩትን ሁሉ እንዲይዙ ታዘዙ::

ባለፈው ወር በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር የተካሄደውን የብአዴን እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዞን እና የወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ኢህአዴግ አሸባሪ እያለ ከሚጠራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ በሚጠረጠሩት ወጣቶች ላይ የቁጥጥር ዘመቻ እንዲካሄዱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል።

ጥር 8፣ 2006 ዓም በሁሉም የአማራ ክልል ወረዳዎች በተደረገው የብአዴን ስብሰባ ላይ ወጣቶች መረጃ በማስተላለፍ እና ለአሸባሪዎች መሳሪያ የሚሆኑ ሰዎችን በመመልመል ላይ በመሆናቸው የግንኙነት ሰንሰለቱን ለመበጠስ አባላቱና አመራሩ ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው ተገልጾላቸዋል። እያንዳንዱ አባል በአሸባሪዎች ፕሮፓጋንዳ ሳይዘነጋ ጠንክሮ እንዲሰራም ትእዛዝ ተላልፎለታል።

“ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ወጣቶች ባላይ የአማራ ክልል ወጣቶች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ አለኝ” ያለው ኢህአዴግ በክልሉ እነዚህን ወጣቶች የመቆጣጠርና የመከታተል ዘመቻ በዘርፈ ብዙ ስልቶች ታጅቦ መካሄድ እንዳለበት አሳስቧል።

“በመሰረተ ቢስ አሉባልታዎች ከኢህአዴግ የኮበለሉና ወስጣቸው የሸፈተ የብአዴን አባላትም ሀቁን ተገንዝበው ከኢህአዴግ ጋር እንዲቀጥሉና ሀገሪቱን ወደ ላቀ እድገት እንዲያሸጋግሩ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊዎች በስብሰባው ላይ ተናግረዋል፡፡

የመወያያ አጀንዳዎች ትምህርትና የመኖሪያ ቤት ሊዝ ጉዳይ ቢሆኑም የስብሰባው ውሎ ግን ከአጀንዳዎች ውጭ አሸባሪዎች በሚሏቸው አካላት ላይ ነበር ያሉት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የድርጅት አባላት፣ መንግስት በመኖሪያ ቤት ሊዝ ያቀረበው ጉዳይ ግን ከፍተኛ ተቀዋውሞ አስነስቷል ብለዋል፡፡ ህጉ የማንንም ኢትዮጵያዊ ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ያላገናዘበ፣በአሰራር ውጣ ውረድ የተበተበና በዘፈቀደ እንዲወጣ የተደረገ ይመስላል ያሉት አባላቱ በተለይ የመንግስት ሠራተኞችን ከጨዋታ ውጭ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከብአዴን እየኮበለለ የሚጠፋውንና ለአሸባሪዎች መጠቀሚያ እየዋለ ነው ያሉትን ሃይል እንቅስቃሴ ለመግታት እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአማራ ክልል የሚገኙ ወጣቶችና የብአዴን አባላት ” ብአዴን የህወሀት በቅሎ መሆኑ ያብቃ” በማለት ጥያቄዎችን እያነሱ ነው።

በክልሉ ውስጥ የተንሰራፋው ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና አፈና መባባስ አባላቱን ለተስፋ መቁረጥ መዳረጉንም ወጣቶች ይናገራሉ።

“መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ”

መቼም በኢትዮጲያ ብጥብጥና ሁከት የሚባለውን አባባል የማያቅ አለ ለማለት ያሰቸግራል። ምክንያቱም የመብትና የፍትህ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር የህወሃት መንግስት “ ብጥብጥና ሁከት ሊያሰነሱ ሲሉ” ማለቱ የተለመደ ነው። ምንም አይነት መብትን የተመለክቱ ጥያቄዎች በድርጅት ወይም በግለሰብ በተነሱ ቁጥር “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ሲሉ ይባልና እስር ቤት ይወረወራሉ። እዚህጋ በርካታ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነገር ይታያል። በኢትዮጲያ መብት ማለት ምንድነው? አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን የመብት ጥያቄዎቹን ለመንግስት እንዴት ነው ማቅረብ ያለበት? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ግን አንድ መራራ እውነት አለ እሱም መብት ማለት በኢትዮጲያ መንግስት መጥኖና ለክቶ ለራሱ በሚስማማ መልኩ ለማህበረሰቡ መብቶች ብሎ የተዋቸው ናቸው። መብት ሲባል በወያኔ ካድሬ አመለካከት ያው ሁሌ ንፅፅሩ ከዛ ከፈረደበት ደርግ ነው “በደርግ ጊዜ ሰአት እላፊ ነበር አሁን ግን የለም” ፣ “በደርግ ጊዜ ብሄራዊ ውትድርና ነበር አሁን ግን የለም” ስለዚህ ወያኔ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው እንባላለን።
ብጥብጥና ሁከት ምን ማለት እንደሆነ ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን ነገር ግን በአሁኑ ሰኣት በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የሚገኙት ወጣቶች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ነው እንጂ በጥብጠው እንዳልሆን ለማንም ግልፅ ነው። ደሞ ሌሎች አባባሎች አሉ “የተወሰኑ” ፣ “አንዳንድ” የሚባሉ ለምሳሌ ባለፈው ምስኪኖቹ የኢትዮጲያ መምህራን ደሞዝን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋነት የተሞላው የመብት ጥያቄ ሟቹ አቶ መለስ “አንዳንድ ብቃት ያነሳቸው መምህራን ብጥብጥና ሁከት ሊያስነሱ ሲሉ” ብለው በአነስተኛ ገቢ በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩትን ምስኪን የኢትዮጲያ መምህራን በሃዘን አንገታቸውን አስደፏቸው። እብሪት ከተሞላው ስድብና ማስፈራሪያ ውጪ ላነሱት ጥያቄ በአግባቡ እንኳን ማብራሪያ አልተሰጣቸውም።
የኢትዮጲያ ሙስሊም ማህበረሰብም ከህፃን እስከ ሽማግሌ እምነታቸውን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋ የመብት ጥያቄ “አንዳንድ ብጥብጥና ሁከት ፈጣሪዎች” እየተባለ ይዘገባል። ባለፈው የብራዚል ማህበረሰብ ላነሳው የመብት ጥያቄ ፕሬዝዳንቷ ዲልማ ሩሴፍ የተናገሩት ንግግር እጅግ ያስቀናል “መብታችሁን ለማስከበር በመነሳታቹ ኮራሁባቹ” ነበር ያሏቸው። አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው በወያኔ አገዛዝ ይህንን በፍፁም አንሰማም። ለምን? የኢትዮጲያ ህዝብ በጥባጭ ስለሆነ? ወይም መንግስትን አጉል ጥያቄ ስለሚጠይቅ? አይደለም። ህወሃት ራሱ የሰራውና እየሰራ ያለው ኢሰባዊ የሆን ግፍና የመብት ረገጣ ስለሚያስበረግገው ሰው ሲሰብሰብ አይወድም። እጅግ በሚያስገርም መልኩ በቅርቡ የሳውዲ መንግስት በኢትዮጲያዊያን ላይ ያደረሰውን አስከፊ ግፍና የመብት ረገጣ ለመቃወም የወጣውን ህዝብ እንኳን “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ተብሎ እየተደበደቡ ተበተኑ። ኧረ ሌላም ብዙ አይተናል።
ነፃና ዲሞክራሲያዊ መንግስትማ የህዝቡን የመብት ጥያቄ እንዴት እንደሚመልስ እናያለን። እንደውም የኢትዮጲያ ህዝብ ሲበዛ የዋህ ነው ባለፈው ውጥንቅጡ በወጣውና መላቅጡ በጠፋው የኢትዮጲያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የተነሳ ተሰደው በሳውዲ ሲሰቃዩ ቆይተው ወደሃገራቸው ከተመለሱት ስደተኞችጋ አንድ ሁለት ፎቶ ስለተነሱ ብቻ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን የሚያደንቁም ተነስተው ነበር። ምን ስላደረጉ? ምንም። እንደው ህዝባችን ትንሽ ሲያረጉለት ወዲያው ለምስጋና አንገቱን ስለሚያጎነብስ ነው እንጂ። ይህን የመሰለ የዋህ ምስኪን ህዝብ በዘርፈብዙ ችግር ሲሰቃይ ማየት እጅግ ያበሳጫል።
ለምሳሌ የመብት ጥያቄ ማንሳት “ብጥብጥ” መባሉ ቀርቶ ለማንኛውም ኢትዮጲያዊ ተፈቀደ እንበልና ምስኪኑ የኢትዮጲያ ህዝብም “ኧረ ተው ከዚህ ሀገር ንቀለኝ” እያለ አማልክትን ከማስቸገር መብቱን ለማስከበር ቢነሳ ምን ያህሉ የሃገራችን ህዝብ የመብት ጥያቄ እንደሚያነሳ ሁላችንም መገመት አያቅተንም።
አንዳንዴ ሳስበው መንግስት ዝም ሲባል የተወደደ ይመስለዋል መሰለኝ ምናልባትም አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ቦታ የሚሰሩ ካድሬዎች የህዝቡን ሮሮ ትተው “ህዝቡ ለመንግስት ፍቅር አለው” ብለው ሪፖርት ስለሚያቀርቡ ይሆናል። እውነታው ቢገለፅ ግን ሪፖርታቸው የሚሆነው “መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ” ነበር።
ታስታውሱ እንደሆን አቶ መለስ “ይህ ማዕበል” ብለው አለወትሮአቸው ድምፃቸውን ሞቅ አርገው የተናገሩት መንግስታቸው የተወደደ መስሏቸው ነበር ወዲያው በነጋታው መልሱን አገኙት እንጂ። ግን እንዴት እንደዛ አሰቡ? በትክክል ቁጥሩን የማያውቁትን ህዝብ ፣ መንግስት በስርአቱ መዝግቦ ያልያዘውን ህዝብ ፣ በኑሮ ውድነት ፣ በነፃነት እጦት እያሰቃዩት ያለውን ህዝብ እንዴት ይወደኛል ብለው አሰቡ። ያስገርማል።
ወደዋናው ሃሳቤ ስመለስ ማንኛውም የሰው ልጅ መብቱን መጠየቅ ማስከበር አለበት ማንኛውም ኢትዮጲያዊም እንድዚሁ። ይህን ስል ግን የግድ መስቀል አደባባይ መሰብሰብ ላይቻል ይችላል ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚኖርበት ፣ በሚሰራበት ፣ በሚማርበት ፣ አገልግሎት በሚያገኝበት ቦታ መብቱን ማስከበር አለበት። ባገኘው አጋጣሚ እምቢ ማለት አለበት።
ናትናኤል ካብቲመር ኦስሎ ኖርዌይ 5 ጥር 2006

በጋምቤላ እና በሸካ አዋሳኝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል 100 ሺ የሚሆኑ የሸካ ተወላጆች 3012 የሚደርስ ሄክታር መሬት ከአካባቢያችን ጥብቅ ደን ተወስዶ ቨርዳንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ለተሰኘ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱን በመቃወማችን ጉዳት እየደረሰብን ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ምሬታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለጹ። በክልሉ እንደተካተቱት ሌሎች አምስት ብሔሮች ስድስተኛ ሆነን አልተመዘገብንም፤ ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር አልቻልንም፤ በክልሉ ተገቢ የሆነ የመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ አልሆነም፤ ለዚህም አካባቢው የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት ተቃዋሚ እንደሆነ ተደርጎ መታሰቡ አግባብ አለመሆኑን የሸካ ህዝቦች ተወካይ በመሆን አቤቱታቸውን ለማሰማት የመጡት አቶ ታምሩ አምበሉ አስረድተዋል።

በጋምቤላ ክልል የመጀንግ ዞን አመራር የሆኑት አቶ ይማም ቃሪስ በበኩላቸው ይህንን አቤቱታ የሚያሰሙት ጥቂት ግለሰቦች የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውና ተጨፈጨፈ የሚሉትም ጥብቅ ደን ሳይሆን ቁጥቋጦ ነው ብለዋል። አክለውም እንደጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ደንብና አሰራር መሰረት የህንዱ ኩባንያ መሬቱን እንዲያለማ መፍቀዳችን ትክክል ነው ይላሉ።

የሸካ ህዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ባቆዩት ጥብቅ ደን ውስጥ ማር በማምረት እንደሚተዳደሩ ያስረዱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ የአካባቢውን ህዝብ ባላማከለ መልኩ ጥብቅ ደኑን እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ከውስጡ የሚመነጩትን ወንዞች መጉዳት ነው ሲሉ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ። ይህንንም አስመልክተው በ1999 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተጠቃሚዎች አይደለንም በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ1200 ሰዎችን ፊርማ አሰባስበው የመብት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ፤ የመብት ጥያቄያቸው ሳይመለስ እስከ 2002 ዓ.ም መጠበቃቸውንና አልፎም የህዝቡን ዋና መተዳደሪያ የሆነውን ጥብቅ ደን ለማጥፋት ምክንያት ሆኖብናል ይላሉ።

በተለይም የህንዱ ቨርደንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ የጎማሬ ቀበሌ አስተዳደር በሸካ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን 3012 ሄክታር ጥብቅ ደን ለሻይ ልማት መፈቀዱ አግባብ አይደለም ሲሉ በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “እኛ ምንም አይነት ኢንቨስትመንትን የመቃወም ኀሳብ እንደሌለን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን” የሚሉት የህዝቡ ተወካዮችና አቤቱታ አቅራቢዎች፤ ይህ ቦታ አማራጭ ቢፈለግለት ይሻላል። ደን ከጠፋ ዘራችን የአኗኗር ባህላችን ሁሉ ይጠፋል የሚል እንደሆነም ተናግረዋል። ያም ሆኖ ለኩባንያው ግንባታ ሲባል በ67 ሄክታር ላይ የሚገኝ ደን ተጨፍጭፎ 1640 በላይ ጣውላዎች ወጥተው ተገኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በወቅቱ ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ በፃፉት ደብዳቤ፤ በጋምቤላ አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ደን ያለበት ሰፊ መሬት ደኑ በጣም ጥቅጥቅ ያለና ለአየር ጥበቃ ሊቆይ የሚገባው ሆኖ ሳለ ለሻይ ልማት ኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ሊመነጠር ስለመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ይህን ችግር ለማሳወቅ ሰዎች ወክሎ መላኩን በመግለፅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።

በበርካታ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎለት የአካባቢው የደን ሀብት እንዲጠበቅ ቢወሰንም አሁንም ድረስ የተሰራ ስራ አለመኖሩንና የአካባቢው ህዝብም ስጋት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ህዝብና መንግስት ጉዳያችን ተረድቶ ጥብቁን ደን ከጥፋት ይከላከለው ዘንድ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል፤ አቤቱታ አቅራቢዎቹ።
የመጀንግ ዞን አመራር በሰጡት ምላሽ ቦታው ጥናት ተደርጎበት ለልማት የተመራ መሆኑን በመግለፅ፤ ኩባንያው የሻይ ልማት ስራውን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየሰራ እንደሚገኝና ነገር ግን ጥቂት የግል ፍላጎት ያላቸው ግሰቦች እንቅፋት የሚሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።
ሰንደቅ ጋዜጣ

የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸው ያታወሳል።

ኦዴፍም በኢትዮጵያ አንድነት እንደሚያምን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮዮጵያዉያን ሁሉ እንቆማለን የሚል አቋም ፣ ድርጅቱ በተመሰረተ ሰሞን በስፋት ሲያንጸባርቅ ነበር። እንደዉም በፓልቶክ በተደረጉ ዉይይቶች፣ የኦዴፉ አቶ ሌንጮ ባቲ፣ «ካስፈለገም፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተነጋግረን፣ ኦሮሞ ከማለት ኢትዮጵያ የሚል ስም ለመያዝን እንሞክራለን » እንዳሉም የሚረሳ አይደለም።

ሰሞኑን ኦዴፍ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በመጪው ምርጫ ሊወዳደር እንደሆነ የሚገልጹ ዘገባዎች በስፋት እየተነገሩ ነዉ። የኦዴፍ ሊቀመንበር ፣ ነዋሪነታቸዉ በኖርዌይ የሆኑት፣ አቶ ሌንጮ ለታ (ሌንጮ ባቲ አይደለም) «ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ሊገባ ነዉ» በተባለውና በሌሎሽ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በጀርመን ድምጽ ራዲዮ ቀርበዉ በአማርኛ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ሌንጮ አሁን በኢትዮጵያ ያለዉ በዘር ላይ የተመሰረተዉ ፌደራል አወቃቀር መቀጠል እንዳለበት አጠንክረዉ ይናገራሉ። «ችግሩ በአፈጻጸሙ ላይ እንጂ በፌደራል አወቃቀሩ ችግር የለም » ያሉት አቶ ሌንጮ፣ ኦዴፍ በተመሰረተ ጊዜ በፌደራላዚም ዙሪያ ፣ ኦዴፍን ወክለው ዶር በያን አሴቦ፣ በፓልቶክ፣ ከሰጡት አስተያየት ጋር ይቃረናሉ። በወቅቱ ዶር በያን፣ «አንዴ ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ መንግስት በተቀየረ ጊዜ የማይለወጥ፣ ሁሉም የሚስማሙበት አዲስ ፌደራል አወቃቀር እንዲኖር ነው ኦዴፍ የሚፈልገው» የሚል አስተያየት ነበር የሰጡት።

የአቶ ሌንጮ በፌደራል አወቃቀሩ ዙሪያ በጀርመን ድምጽ የተናገሩትን ያዳመጡ፣ ኦዴፍ በፖለቲካ አቋሙ ፣ ከኦህዴድ ጋር በጣም የሚቀራረብ እንደሆነ በመግለጽ ኦዴፍ በአገር በት ገብቶ ምን የተለየ ነገር ሊያመጣ እንደሚችል ይጠይቃሉ።
የአገሪቷ ችግሮች በሰላምና በዉይይት እንዲዲፈታ ድርጅታቸው ፍላጎት እንዳለዉ አክለው የገለጹት አቶ ሌንጮ « እኔ እዚህ ኖርዌይ ተቀምጬ ምን አደርጋለሁ ? ሕዝቡ ጋር ሆን ካልታገልን በዉጭ ሆነ የምናደርገዉ ምንም ነገር የለም» ሲሉ ከሕዝብ ርቆ በዉጭ የሚደረግ ትግል ዋጋቢስ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል። ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ፣ አገር ዉስጥ ገብተዉ፣ በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት አቶ ሌንጮ፣ በዚያ ዙሪይ ከኢሕአዴግ ጋርም ሆነ ከተቃዋሚዎች ጋር ለመወያየት ድርጅታቸው ዝግጁ እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህ ዙሪያ፣ ከኦዴፍ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላቸው፣ አንድ ምሁር፣ ኦዴፍ ከጅምሩ አገር ዉስጥ ገብቶ በሰላም ለመታገል ፍላጎት እንዳለው ሚስጠር እንዳልሆነ ካስረዱ በኋላ፣ ኦዴፍ ለመደራደር ጥያቄ ያቀረበዉ፣ ኢሕአዴግ ለምርጫ የሚያስፈልጉ የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን እንዲያስተካክልና ለፍትሃዊ ምርጫ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች መሆኑን ይገልጻሉ። «በኦዴፍ ዘንድ ኢትዮጵያ የመግባትና ለምርጫ የመወዳደር ዉሳኔ በፍጹም የለም» ያሉት እኝሁ ምሁር ኦዴፍ አገር ቤት ሊገባ ነዉ ተብሎ የሚዘገበዉን «ከእዉነት የራቀ» ብለዉታል።

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ፣ ኦዴፍ ኢትዮጵያ የመግባት ፍላጎትና አላማ እንዳለው እንጂ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ እንደሆነ አያመላከትም።

በቅርቡ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ኀሳቦች እየተነሱ ነው። በተለይ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ካርቱምን ከጎበኙ በኋላ ከሌሎች ጉዳዮች በበለጠ የድንበሩ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።

የካርቱም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የድንበር ማካለል አለመግባባት (Demarcation disputes) በቅርቡ መፍትሄ እንደሚያገኝ ዘግበዋል። የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዓሊ ከርቲ ሁለቱ አገሮች የድንበር ማካለል ችግራቸውን ለመፍታት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሱዳኖቹ “ፍሻጋ” በማለት በሚጠሩት አካባቢ ያለው የድንበር ችግር ይፈታል ብለው እንደሚያስቡ እየገለፁ ነው። በሌላ ወገን በርካታ ኢትዮጵያውያን መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ነው በሚል ቅሬታ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሁለቱም አገሮች ሰላማዊ የድንበር ቀጠና እንዲኖራቸው እየሰሩ ነው ከማለታቸው ባለፈ፤ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በቀጣይም በሀገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እውነታውን ይገልፃሉ ተብሎም ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ይሄው ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመሳቡ በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገሮች ድንበር ችግር ያለበት መሆኑን በመጥቀስ የማካለል ስራው እንደሚከናወን መግለፃቸው አይዘነጋም። ይኼው የድንበር ማካለል ከጥቂት ወራት በኋላ ሊከናወን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ነገር ግን የማካለል ሂደቱ በምን መልኩ እንደሚፈፀም የታወቀ ነገር የለም።

በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ግን የድንበር ማካለሉ ሂደት ግልፅነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ በመንግስት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ አረናም ሆነ አንድነት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብርሃ ደስታ ጉዳዩን በተመለከተ ፓርቲው እንደ ፓርቲ መረጃ እንደሌለው ገልፀዋል። ነገር ግን በግል በሁመራ ከሚገኙ ነዋሪዎች መረጃውን ለማጣራት ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። በሁመራ የሚኖሩ አንዳንድ ግለሰብ ነዋሪዎች “መሬቱ ለሱዳን ይሰጣል” ተብሎ እየተወራ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል። በተጨማሪም የአካባቢው ባለስልጣናትን ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ሙከራ ማድረጋቸውንም የሚገልፁት አቶ አብርሃ ባለስልጣናቱም “የምናውቀው ነገር የለም” እንዷላቸውም ነው የገለፁት።

ፓርቲው ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ እንደመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እያጣራ መሆኑን የገለፁት አቶ አብርሃ፤ ከስርዓቱ ባህሪ በመነሳት በድንበር ማካለሉ ላይ እምነት መያዙ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። “ሥርዓቱ ለስልጣን ብሎ እንጂ የሀገር ድንበር ለመጠበቅ አይደለም። ከዚህ ጉዳይ ተነስቶ የኤርትራን ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የሱዳንም ጉዳይ ሊያጠራጥር ይችላል። ምክንያቱም ሥርዓቱ ለኢትዮጵያ ያለው ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬ አለን። ሥርዓቱ ዳርድንበር ከመጠበቅ ባለፈ፤ የውጪ ኃይሎችም ጋር ቢሆን በስልጣን የሚቆይበትን መንገድ ሊያፈላልግ ይችላል” በማለት ጥርጣሬአቸውን ገልፀዋል።

የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ በመደገፉ በምትኩ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ተሰጥቶት ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥርጣሬም በተመለከተ አቶ አብርሃ ሲመልሱ፤ “የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩ ነው። ነገር ግን የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ ቢደግፈውም፣ ባይደግፈውም የእኛ ግድብ ነው። የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩና የምንፈልገው ቢሆንም፤ ስለደገፈ ተብሎ የሚሰጥ መሬት ሊኖር አይገባም። ከአባት፣ አያቶቻችን የተረከብነው መሬት ለሌላ አካል ሊሰጥ አይገባም። ድርጊቱ ተፈፅሞ ከሆነ እንታገለዋለን” ሲሉ መልሰዋል።

“መንግስት በጉዳዩ ላይ ግልፅ መሆን አለበት” የሚሉት አቶ አብርሃ፤ በጉዳዩ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግልፅ መደረግ አለበት ብለዋል። ድንበሩ ሲካለልም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍ አለባቸው ብለዋል።

“የድንበር ጉዳይ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። ኢህአዴግ በመንግስትነቱ ሳይሆን በፓርቲነቱ ስለሚሰራ ጥርጣሬ አለን” የሚሉት አቶ አብርሃ ስለሆነም ለጉዳዩ ማረጋገጫ የሚሆን ግልፅ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ቀጠናው የተረጋጋ ባለመሆኑ የድንበር መካለል እንደሌለበት የጠቀሱት አቶ አብርሃ የድንበር ማካለሉ ሂደት ተጀምሮም ከሆነ መቆም አለበት ብለዋል። በደቡብ ሱዳንና በሰሜን ሱዳን አንዳንድ አካባቢዎች መረጋጋት በሌለበት በድብብቆሽ ወደ ድንበር መካከል መገባት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ጫኔ ታደሰም እንደ አቶ አብርሃ በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ግልፅ የሆነ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀው፤ ነገር ግን መንግስት በውጪ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ዙሪያ ላይ ጠንከር ያለና ኢትዮጵያውያንን ለሚጠቅም ተግባር ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የድንበር ጉዳይ የሕዝብ ጉዳይ እንደመሆኑ ግልፅ አሰራርን መከተል አለበት ብለዋል። ከመንግስት ባለፈ ሚዲያውም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

አቶ ጫኔ በመንግስት በኩል የሀገር ድንበርን በተመለከተ የመድበስበስ አካሄድ መኖር የራሱ አደጋ እንዳለው ይገልፃሉ። ፓርቲያቸውም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊና እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚያሳስበው እንደሆነና በጉዳዩም ላይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት እየጣረ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ ፓርቲም በአካባቢው ከሚገኙ አባሎቹም መረጃ የማሰባሰብ ስራም እያከናወነ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ኢዴፓ ከኢህአዴግ ጋር የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ልዩነት እንዳለውም ጠቅሰዋል። ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘም ያሉ ችግሮች የኢህአዴግ የውጪ ፖሊሲ ችግሮች የሚመነጭ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም በመንግስት በኩል የኢትዮ ሱዳንን ድንበር ማካለል ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚጎዳ መልኩ የሚፈፀም ከሆነ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመን የማጋለጥና የመቃወም ስራ እንሰራለን ብለዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በጉዳዩ ላይ አቋም መወሰዱን ይናገራሉ። ፓርቲው የወሰደው አቋም፤ ጉዳዩን የማጋለጥና ሕዝቡ እንዲያውቀው የማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።

“የኢትዮጵያ መንግስት ከሕዝቡ ጀርባ ሆኖ ድንበር የማካለል ስራ እየተሰራ በመሆኑ እንቃወመዋለን። ጉዳዩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያውቀው አይመስለንም። ምን ያህል መሬት ለሱዳን ይሰጣል? ለምንስ ይሰጣል? ታሪካዊ ባለቤትነቱ የማነው? የሚለው መታየት አለበት የሚሉት አቶ ስለሺ፤ ድንበሩን በድብብቆሽ የማካለሉ ተግባር ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ፓርቲው ከልዩ ልዩ ምሁራንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሰዎች እንደተረዳው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል ባለፉት ሰርዓቶች ቢነሳም ጉዳዩ ሳያስተናግዱት መቆየታቸውን አስታውሰው ኢህአዴግ ግን መነሻው ግልፅ ባልሆነ መንገድ የድንበር ማካለል ጥያቄውን አሁን ማንሳቱን ጠቅሰዋል። ያም ሆኖ ኢህአዴግ በሱዳን ድንበር አሸባሪ የሚላቸው ወገኖች ተደራጅተው እንዳይመጡበት ገዢ መሬት ለማሳጣት ድንበሩን ለድርድር አቅርቦ እንደሚሆንም እንገምታለን ብለዋል።

ፓርቲውም ይሄንኑ ጉዳይ እንደ አጀንዳ በመያዝ የፓናል ውይይት በማዘጋጀት ከፓናል ውይይቱ በሚነሳው ኀሳብ ደግሞ ሕዝቡ አቋም እንዲይዝና እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ወደ አካባቢው በማቅናት በጎንደር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ተናግረዋል።

“በአሁኑ ወቅት መሬቱ በእርግጥም ለሱዳን አልተሰጠም” ያሉት አቶ ስለሺ፤ ሆኖም ግን በድንበር ማካለሉ ላይ ድርድር ተካሂዶ በወረቀት ደረጃ ሁለቱ አገሮች መስማማታቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም በኀሳብ ደረጃ ተስማምቶ በመጪው መጋቢት የመሬት ርክክብ እንደሚፈፀም የሱዳን የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት እንደሆነም ተናግረዋል።

“ጉዳዩን እየደበቀው ያለው ኢህአዴግ ብቻ ነው” የሚሉት አቶ ስለሺ፤ “ነገሩ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ ነው” ብለውታል። የድንበር ማካለል ጉዳይ የሉአላዊነት በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሊፈፀም አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል። ኢህአዴግ ለሀገሪቱ ታሪካዊ ሉአላዊነት ደንታቢስ በመሆኑም የድንበር ማካለሉን ለስልጣኑ ብሎ ከመፈፀም ወደኋላ አይልም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ፓርቲያቸው ሕዝቡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ከማድረግ ባለፈ ኢህአዴግ በድርድር የተስማማባቸው ስምምነቶች በመጪው ትውልድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ ነው ጨምረው የገለፁት።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪም እንደሌሎቹ የፓርቲ አመራሮች ጉዳይ የሚያሳስበው መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ተናግረዋል። አጣሪ ቡድኑ በሚያመጣው መረጃ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ መኢአድ እንደ ፓርቲ ድንበሩ በቅድመ አያቶቻችን አባቶቻችን የተካለለ በመሆኑ እንደገና መከለል የለበትም የሚል አቋም እንዳለው ገልፀዋል። የፓርቲው አቋም የአከላለል ሂደቱ ግልፅ ይሁን አይሁን ከማለት ባለፈ ድንበሩ እንደገና መከለል አይገባውም የሚል እንደሆነ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ድንበር ማካለል ቀደም ሲል በነበሩ ስርዓቶች ሳይነሳ አሁን የተነሳበት ምክንያት የአማራውን ብሔር በመልከአምድር እና በቁጥር ለማሳነስ የሚደረግ ሴራ ነው የሚሉት አቶ አበባው፤ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሁም በሕዝብ እኩልነት የሚያምን ሁሉ ሊቃወመው ይገባል ብለዋል።

በመንግስት በኩል የድንበር ማካለሉን ሂደት ለሕዝብ ግልፅ ማድረግ በተለይ ጎንደር አካባቢ ሱዳኖች ይገባናል ስለሚሉት መሬት ግልፅ አቋም መያዝ አለበት የሚሉት አቶ አበባው፤ “ሕዝቡ ድምፁ ሊሰማና የታሪክ አዋቂዎችና አባቶች በጉዳዩ ሊጠየቁ ይገባል። ሽፍንፍን ባለ ሁኔታ ድንበር ማካለል ተገቢ አይደለም። ይህ አካሄድ ለሱዳንም ሆነ ለኢህአዴግ አይጠቅምም” ሲሉ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን አድርጎ እና እያደረገ ከሆነም እንደገና ነገሩን እንዲያጤነው” ሲሉ አሳስበዋል።

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው የፓርቲው አዲሱ የስራ አስፈፃሚ እየተወያየባቸው ካሉ ሦስት አስቸኳይ ዋና ርዕሰ ጉዳዮች የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማከለል ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ኢህአዴግ በሉአላዊ ግዛት ማስከበር ጉዳይ የላላ አመለካከት ያለው በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅማችንን ሊጐዳ የሚችል እርምጃ ሲወስድ በመቆየቱ አሁንም በዚህ ተግባሩ ሊቀጥል እንደሚችል የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ ከዚህ በፊትም የሀገሪቱን ታሪካዊ ባለቤትነት በጣሰ መንገድ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መደረጓን አቶ ሀብታሙ አስታውሰዋል። አሁንም የኢትዮ-ሱዳን ድንበር የኢትዮጵያን ጥቅም ባላስጠበቀ መንገድ ሊፈፀም ስለሚችል ከፍተኛ ሰጋት አድሮብናል ብለዋል።

“በሱዳን በኩል እየተጠየቀ ያለው መሬት የኢትዮጵያ ነው” የሚሉት አቶ ሀብታሙ፤ ይሄንን ሉአላዊ ግዛት ለሱዳን መስጠት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ግዛት ላይ እንደገና ከተደራደረበት ከሕዝብ ጋር በመሆን የምንታገለው ነው ብለዋል።

እስካሁን በመንግስት በኩል ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ፓርቲያቸው ደጋግሞ እያሳሰበ መሆኑን የጠቀሱት ህዝብ ግንኙነቱ የድርድሩ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሂደቱም ለህዝቡ ግልፅ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

“ከዚህ በፊት ከ60ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የረገፉበት የባድመ ጉዳይ መፍትሄ አላገኘም። የአሰብ ወደብን በተመለከተም ኢህአዴግ ቸልተኛ አቋም በመከተሉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ጎድቷል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ አሁንም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል በተመለከተ ኢህአዴግን እንድንጠራጠረው አድርጎናል ብለዋል።

ኢህአዴግ በተፈጥሮአዊ ባህሪውን እና ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚመነጭ አስተሳሰብ መረዳት እንደሚቻለው ግንባሩ በሉአላዊነት ላይ የተዛባ አቋም ያለው በመሆኑ አሁንም የሀገሪቱን ሉአላዊነት በመጠበቅ ላይ ስጋት አለን ሲሉ አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል።

“ሀገር ማለት ሕዝብ ነው ነው ብለው ለኢትዮ-ኤርትራ ድንበር 60 ሺህ ሰው አስጨርሰዋል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ጤናማ ለማድረግና የአባይን ግድብ መደገፉን ተከትሎ መሬት ቆርጦ ለመስጠት ከታሰበ ተገቢም፣ ትክክል አይደለም ብለዋል። ድንበር እየሰጡ ግድብ መገደብ ሰጥቶ መቀበል አይደለም በማለት ተቃውመውታል። ግድብ መገደብ የሀገሪቱ መብት እንደሆነም መታወቅ አለበት ሲሉ አጠቃለዋል።

በዚሁ አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ለማነጋገር ጥረት አድርገናል። ነገር ግን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦፊሴላዊ ጉብኝት ጋር በተያያዘ ስራ ስለበዛባቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። በተመሳሳይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች በኩልም መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገናል። በመስሪያ ቤቱ አሰራር በቃል አቀባዩ በኩል መረጃ ስለሚሰጥ ሊሳካልን አልቻለም።

በተጨማሪም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማልን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ቴሌፎናቸው ስለማይሰራ ልናገኛቸው አልቻልንም። በጠቅላይ ሚኒስትር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ደስታ ተስፋውን አነጋግረን አቶ ሽመልስን ወይም አምባሳደር ዲናን ብቻ ማነጋገር እንደምንችል ገልፀውልናል። በቀጣይ ሳምንት የመንግሥትን ምላሽ ይዘን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ረቡዕ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በ 2004 በመኪና ሰው ገጭተው አምልጠዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ቡሃላ አቃቤ ህጉ ክሱን ለፍርድ ቤቱ በንባብ ያሰማ ሲሆን ሀምሌ 8 2004 ላይ በተለምዶ ሶማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ላይ በንብረት እና በሰው ሂወት ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል መልኩ ከተገቢው ፍጥነት በላይ አሽከርካሪውን በማሽከርከር በአንድ ሰው የእጁ አውራ ጣት ላይ የስብራት አደጋ አድርሰው ጥለውት ሄደዋል የሚል ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡

ይህም ድርጊት ተፈፀመ የተባለው ሃምሌ 8 ቀን የደህንንንት ሃይሎች የኮሚቴውን አመራሮች ከመንገድ ላይ በማገት ወደ ሚፈልጉት ቦታ የብልግና ስድብ እየሰደቡ ይዘዋቸው በሚወስዱበት ሰአት መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ ቀን መታቂያቸውን አናሳይም ያሉት ደህንነቶች ጋጠወጥ በሆነ መልኩ ብልግና እየተሳደቡ ለማገት ያደረጉትን ሙከራ በማክሸፍ ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ አምልጠው መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ወቅት ነው ሰው ገጭታችሁ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ወንጀል የቀረረበባቸው፡፡

ኡስታዝ አበቡበከር አህመድ ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወንጀል መርማሪ ፖሊሶች ወደሳቸው በመሄድ ይህን ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከርም የተባለውን ድርጊት አለመፈፀማቸውን በወቅቱ መኪና ሲያሽከረክሩ እንዳልነበር፣መኪናውም የሌላ ሰው እንደነበር እና በሹፌር ሲሄዱ እንደነበር ብሎም ከፊት ለፊት በነበረው የመኪና መቀመጫ ላይም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተቀምጠው እንዳልነበር እና በደህንነቶች ጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ የእገታ ወንጀል ሲፈፅምባቸው ከወንጀል ድርጊቱ ማምለጣቸውን በዝርዝር ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህንንም በማስመለከት ዛሬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ሰአት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተው እንደሆነ ለማረጋገጥ የጠየቃቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድም ቃላቸውን መስጠታቸውን እና የዚህ አይነት ድርጊት በወቅቱ አለመፈፀሙን ብሎም የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የጠየቀ ቢሆንም አለመገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን ምስክር የተባለ አንድ ግለሰብ ብቻ ግን ችሎት የቀረበ ሲሆን ሁሉም ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 28 ቀነ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ይህ ክስ ሆን ተብሎ የኡስታዝ አቡበከር አህመድን ፅናት ለመፈታተን እና ተስፋ ለማስቆረጥ ሆን ተብሎ የተደረገ ተግባር ሲሆን በተጨማሪም ኮሚቴው በእስር ላይ ሆነው ባወጡት መግለጫ በመበሳጨታቸው እና የተፈጠረው መነቃቃት ወደሌላ አቅጣጫ ሆን ተብሎ ለማስቀየስ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሆነው ህወሃት በሀገራችን ሰላምና ፍትህ፣ ልማትና እድገት እየመጣ ነው እያለ የተረጋጋ መሆኑን በማስመሰል በየጊዜው ይናገራል። ነገርግን የሀገሪቱን ገንዘብ በተዘዋዋሪ በውጪ በሚኖሩ የስርአቱ አግልጋዮች ስም የቦታና የንግድ ግዢ በውጪ ሀገር የማድረግ ስራ በሰፊው እየተፋፈመ መሆኑን የውስጥ ዜና ምንጮቻችን ገልፀዋል።

በተለይም በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች በጉብኝት ስም ታማኝ ሰዎችን በመላክ የሀገሪቱን ገንዘብ በማሸሽ ቦታና የንግድ ማእከሎችን እንዲገዙ እየተደረገ ነው። ህወሃት ራሱ ያልተረጋጋ እና አደጋ ያንጃበበት በመሆኑ ውስጣቸው መረጋጋት እንደሌለበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

ታዲያ ይህንን ፍርሃት በመሸፈን በበላይነት የህወሃት ኤፈርት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን ገንዘብ የማሸሽን ዘዴ እንደ አንድ አማራጪ ወስደው ራሳቸውንና ንብረታቸውን ለማሸሽ እየተዘጋጁ ነው ሲል መረጃውን የላከልን ዘጋቢያችን አስታውቋል። በቅርቡ ከሁለት ወር በፊት የኤፈርት ልኡክ ቡድን ወደ አሜሪካ ተልእኮ እንደነበርም አስረድቷል። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የህወሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው ሲል የግንቦት 7 ሬዲዮ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል። (አባይ ሚዲያ)

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለአንድነት ፓርቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና ከ22 ከሚበልጡ የህብረቱ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተነፃነት እንዳስታወቁት ትላንት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው በዚህ ውይይት የአንድነት ፕሬዝዳንት ፣የህዝብ ግንኙነትና የውጪ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ሀገራትን የወከሉት የህብረቱ ዲፕሎማቶች አሁን ስለሳለው አጠቃላይ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ፣አንድነት እንደ ፓርቲ ያለበትን ሁኔታ በዝርዝር ለማወቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የፓርቲው ፕሬዝደንት በፕሮጀክተር የታገዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድነት ከግንኙነት ስትራቴጂ አንፃር በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ማለትም ከኢትዮጵያ ዳያስፖራና ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት የተብራራ ምላሽ ተሰጥቷቻዋል፡፡

ኢንጅነት ግዛቸው አንድነት በሚመለከት ባቀረቡት ገለፃ የፓርቲውን ርዕይ፣ተልዕኮና አላማ በሰፊው አብራርተዋል፡፡በመቀጠልም ስለአንድነት ፖሊሲዎችና መርሆዎች ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አክለውም የአንድነት ፓርቲን ተቋማዊ አደረጃጀት በሚመለከት ገለፃ ሰጥተዋል፡፡ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከትም የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት አመታት አንዳችም አይነት የለውጥ አዝማሚያ እንዳላሳየ ይልቁኑም ተቋማዊ የአፈና ስርአትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ፕሬዝዳቱ ማሳያዎችን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት የተዘፈቀበትን ሙስና ግዝፈት የዘረዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፀረሽብር ህጉ ከመንግስት የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ለማጥቃት የተቀመጠ መሆኑን በአንድነት አመራሮችና በሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ላይ የደረሰውን እስርና እንግልት በማሳያነት አስረድተዋል፡፡ አንድነት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለውና በበርካታ ሀገራትም የተቋቋሙ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮች እንዳሉጠቁመዋል፡፡

ወደፊትም በተጠናከረ ደረጃ በሀገራቸው ፖለቲካ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉበትን መንገድ እንደተቀየሰና የዲያስፖራው አባላትን በአባልነትና በድጋፍሰጪነት በንቃት ለማሳተፍ መታቀዱን ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከፓርቲው ፕሬዝደንት ከኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ጋር የተገኙት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሀብታሙ አያሌውና የውጪ ግንኙነት ሀላፊው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠታቸውም ታውቋል::

የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ ከሚኒስትሮች እና ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትና ግምገማ ላይ «ህዝቡን ለመምራት የሚነደፉ ንድፈ ሀሳቦች ( ቲዮሪዎች) በየጊዜው ካልተሻሻሉ የሚዝጉ በመሆናቸው አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲ እንዲተካ ተደርጓል» ብለዋል። «የኢህአዴግ መንግስት ይበልጥ የሚገለጸው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሳይሆን በልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው» በማለት አቶ በረከት ገለጽዋል።

አቶ በረከት አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ከመተካቱ በፊት ፣ ግንባሩ ለ3 ተከፍሎ እንደነበር ገልጸዋል። አንደኛው የአመራር ወገን «ችግራችን የውስጥ ነው እና በቅድሚያ የውስጥ ችግራችንን እንፈትሽ የሚል» አቋም ሲይዝ ፣ ሌላው ወገን ደግሞ ዋናው ችግራችን ሻዕቢያ በመሆኑ በቅድሚያ ሻዕቢያን እንውጋ የሚል አቋም ይዞ እንደነበር፣ እና ሻእቢያን ከወጋን በኋላ ወደ ውስጥ ችግራችን እንመልከት የሚለው ሶስተኛው አማራጭ አሸንፎ መውጣቱን ገልጸዋል። «በ1997 ዓ.ም ዋናው የአመጽ ሀይል የነበረው ስራ ያጣውና ተስፋ የቆረጠው ወጣት ነው» በማለት የገለጹት አቶ በረከት ለወጣቱ ስራ ካልተፈጠረለት በመንግስት እና በአገር ላይ እንደሚያምጽ ገልጸዋል። መንግስት የምርጫ 97ትን አመጽ ያስነሱት ተቃዋሚዎች ናቸው ብሎ ሲከስ መቆየቱ ይታወቃል።

ኢህአዴግ ከባለሀብቱ ነጻ የሆነ መንግስት ለመመስረት መነሳቱን የገለጹት አቶ በረከት፣ ስልጣን ላይ የሚያመጣን አርሶአደሩና በከተማ ያለው ጭቁኑ ህዝብ ነው እንጅ ባለሀብቱ አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በባለሀብቱ ገንዘብ የሚተዳደር አይደለም ያሉት አቶ በረከት፣ ገንዘብ ከፈለገ ከባላሀብቱ በግብር መልክ መውሰድ እንደሚችል ተናግረዋል። ይህ መንግስት ለህልውናው የራሱ የገቢ ምንጭ እንዳሉት የጠቀሱት አቶ በረከት፣ አየር መንገድን ባንኮችን እና መብራት ሀይልን በምሳሌነት አንስተዋል። የመንግስትን አስተዳደር ያለምንም ችግር ለማስኬድ የባለሀብቱም የውጭ ድጋፍም እንደማያስፈልግ አቶ በረከት አክለዋል።

አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ ምርጫውን ያለባለሀብቶች ድጋፍ ማሸነፍ እንደሚችል እየገለጹ ባለበት ጊዜ በድንገት የመንግስት ተቋሞችን በመግለጽ በቂ ገንዘብ አለን ማለታቸው ተሰብሳቢዎችን ማስገረሙን ስብሰባውን የተከታተሉት አንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራር ገልጸዋል። አመራሩ እንዳሉት ኢህአዴግ ለምርጫ ማስኬጃ ከመንግስት ገንዘብ እንደሚወሰድ የአቶ በረከት ንግግር በቂ ማሳያ ነው ።

መንግስት የራሱ ገንዘብ ከሌለው እንደምእራብ የአፍሪካ አገራት ይሆናል ያሉት አቶ በረከት፣ የኮትዲቩዋር ሚኒስትሮች ደሞዛቸውን የሚወስዱት ኮትዲቯር ከሚገኘው የፈረንሳይ ኢምባሲ ነው ይላሉ። በኬንያም ሁኔታው ተመሳሳይ መሆኑን አቶ በረከት አክለዋል ኢህአዴግ በ2002 በተደረገው ምርጫ ከግል ባለሀብቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወቃል። በባቡር ግንባታ፣ በመንገድ ቁፋሮና በትራንሰፖርትና እጥረት የተነሳ በአዲስ አበባ መኖር ያስጠላል ያሉት አቶ በረከት ያም ቢሆን ግን ህዝቡ ልማት ነው በሚል እንደሚቀበለው ገልጸዋል።ኢሳት ዜና

መንግስት የግል መጽሄቶች የህትመት ቁጥር መጨመር ስጋት ላይ እንደጣለው ታወቀ::

መንግስታዊዎቹ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በአሁኑ ወቅት በመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ስር በአንድ መመሪያነት የሚሰራውና በአዋጅ በፈረሰ ስም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እየተባለ የሚጠራው ድርጅቶች በጋራ አጥንተናል ባሉትና ሰባት ያህል መጽሄቶች ሕግና ስርዓትን በመተላለፍ እየሰሩ መሆኑን የሚያውጀው ጥናት መነሻ የመጽሄቶቹ ቁጥር መጨመር ገዢውን ፓርቲ ስጋት ላይ በመጣሉ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደጠቆሙት በጽንፈኝነት ከተፈረጁት ሰባቱ መጽሔቶች ማለትም ሎሚ፣ፋክት፣አዲስጉዳይ፣ዕንቁ፣ቆንጆ፣ሊያ እና ጃኖ መጽሔቶች መካከል አብዛኛዎቹ ሳምንታዊ የህትመታቸው መጠን ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣትና የሚጽፉአቸውም ርዕሰ ጉዳዮችም ገዥውን ፓርቲ አጠንክረው የሚተቹ መሆን በተለይ ከመጪው ዓመት አገር አቀፍ ምርጫ ጋር በተያያዘ ኢህአዴግን ስጋት ላይ ጥለውታል፡፡

መጽሄቶቹ ለጥናት ሲመረጡ ቀድሞውኑ ውጤቱ ይታወቅ ነበር ያሉት ምንጮቹ ፣ በጥናቱ ተገኘ የተባለው ውጤት ባለስልጣናቱ በየጊዜው ሲሉት የነበረና በአዲስዘመን ጋዜጣ አጀንዳ ኣምድ ላይ በተከታታይ ሲጻፉ የነበሩ ትችቶች ናቸው ብለዋል፡፡ መንግስታዊ ተቋማቱ የጀመሩት ጥናት ገና አለመጠናቀቁንና ከጅምሩ ተቆንጥሮ እንዲለቀቅ የተደረገው በሁዋላ መንግስት ለሚወስደው እርምጃ ከወዲሁ ህጋዊነትን ለማላበስ ታስቦ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ጥናቱ ገና ሳይጠናቀቅና ድምዳሜው ሳይታወቅ ውጤቱ ይፋ መደረጉም መንግስት ሚዲዎቹን ለመወንጀል የቱን ያህል እንደቋመጠ የሚያሳይ ነውም በማለት አክለዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በአዲስዘመን ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ የታተመው ዘገባ እንደሚሳየው ሰባቱ መጽሔቶች ከመስከረም እስከ ህዳር 30/2006 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ባወጡዋቸው ዘገባዎች የጽንፈኛ ድርጅቶች ልሳናት መሆናቸውን፣ሕገመንግስቱን እንደሚጥሱ፣ሽብርተኝነትን እንደሚያበረታቱ፣የተሳሳቱ መረጃዎች ሕዝቡ በስርዓቱ ላይ እምነት አጥቶ ለአመጽ እንዲነሳሳ እንደሚደርጉ በጥናት ደርሰንበታል መባሉና ኢሳትም ይህንኑ በዕለቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
የብሮድካስት ባለስልጣን በታህሳስ ወር 2006 ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፋክት መጽሔት በወር 62 ሺ ኮፒ በማሳተም የሚመራ ሲሆን ሎሚ 55ሺ፣ አዲስጉዳይ 51 ሺ ኮፒዎችን በማሳተም ይከተላሉ፡፡ ቆንጆ 7ሺ፣ ዕንቁ 6ሺ 400፣ጃኖ 4ሺ ሲያሳትሙ ሊያ የተባለችው መጽሔት በታህሳስ ወር ምን ያህል ኮፒ እንደታተመች ባለስልጣኑ በመረጃው አላካተተም፡፡
ምንም አይነት ግሳጼ ካልደረሰባቸው ሳምንታዊ ጋዜጦች መካከል ሪፖርተር የእሁድ እትሙ 11 ሺ፣ ፣ አዲስ አድማስ 8 ሺ 700፣ ሰንደቅ 1 ሺ 933፣ ኢትዮ ቻናል፣ 1 ሺ 737 ያሳትማሉ። ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና

የመከላከያ መኮንኖች በአ.አ ፖሊስ ተመደቡ::
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም ::
በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት ተቀየሩ ::

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስሩ ክፍለ ከተሞች የመከላከያ መኮንኖች ተዛውረው መመደባቸውን ታማኝ የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባላት የሆኑትና ከመቶ አለቃ እስከ ሻለቃ ደረጃ ያላቸው የመከላከያ መኮንኖች የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲቆጣጠሩ በአስሩም ክፍለ ከቶሞች የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች “ኮሚኒቲ ፖሊስ” በሚል አዳዲስ የፌደራል ፖሊሶች እንደመተደቡ ምንጮቹ አያይዘው ገለፀዋል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ሃይል እምነት ያጣው ገዢው ፓርቲ ሕወሐት/ኢህአዴግ ታማኝ በሚላቸው መኮንኖችና የፌደራል ፖሊሶች እየተካና አፈናውን እያጠናከረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም አሁን በተጀመረው የክልሉን ፖሊስ የማፍረስ ተግባር በቅርብ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል።

ገዢው ፓርቲ ራሱ በደነገገው ሕገ-መንግስት ላይ ፖሊስ ፀጥታውን እንደሚቆጣጠር እንዲሁም መከላከያ ገለልተኛ ሆኖ የአገሩን ሉአላዊነት እንደሚጠብቅና ከማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት ነፃ ሆኖ እንደሚቆም አዋጁ የሚገልፅ ቢሆንም ነገር ግን ራሱ ላወጣው ሕገ መንግስት ተገዢ መሆን እንዳልቻለ የሕወሐት መኮንኖች ከመከላከያ ተዛውረው የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ መመደባቸው የህግ ጥሰት እያካሄደ እንደሆነ በቂ ማስረጃ ነው ብለዋል ምንጮቹ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት እየተቀየሩ መሆኑን ምንጮች አጋልጠዋል። በአዲስ አበባ የካና አራዳ ክፍለ ከተሞች “ኬርና ፕላን” በተባሉ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተሰሩት ጤና ጣቢያዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀይረው እስረኞች እየታሰሩባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06/07 ቤላ፣ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ቀበሌ 11 እንዲሁም ጃንሜዳ ቀበሌ 05 የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች በከፊል እንደሚጠቀሱ ያስታወቁት ምንጮቹ በተጠቀሱት ቦታዎች እስረኞች በብዛት ታስረው እንደሚገኙ አያይዘው ገልፀዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በእንግሊዝኛ ምህጻሩ «ኦ ዲ ኤፍ» ወደ ኣገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑን ኣስታወቀ። ‪የግንባሩ ፕሬዝደንት አቶ ሌንጮ ለታ እንደገለጹት ግንባሩ ከምስረታው ኣንስቶ ወደ ኣገር ቤት ለመመለስ ግልጽ አቐም ይዟል። ለኢትዮጵያ ህዝቦች አዲስ ራዕይ ኣለኝ የሚለው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ህጋዊ መሰረት ያለው ኣገራዊ ኣንድነትን ለመመስረት እንደሚሰራም ኣስታውቐል። «ኦ ዲ ኤፍ» በይፋ ከተመሰረተ ገና ኣንድ ዓመቱ ሲሆን ፕሬዝደንቱ አቶ ሌንጮ ለታ ለረጅም ጊዜ የዓማጺው ኦሮሞ ነጻነት ግንብር ከፍተኛ ዓመራር አባል እንደነበሩ ኣይዘነጋም።

object Podcast

Image

«በሕገ መንግስቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም።ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገዉ ስርዓቱን ወይንም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም ፣ ነገም ፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነዉ።»ኢቲቪ በቅርቡ በ«ሽብርተኝነት» ላይ፣ በቅርቡ ባቀረበዉ አሳዛኝ ዶኩሜንተሪ ላይ ፣ የፌደራል መንግስት አቃቤ ሕግ፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ የተናገሩት ነበር።

እኝህ የሕግ ባለሞያ እየደጋገሙ ሕግን ስለማክበርና ስለ ሕገ መንግስቱ ነግረዉናል። ስለሕገ መንግስት ካነሳን አይቀር አንድ ነገር ጣል ላድርግ። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ 4 «በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይንም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል» የሚል ድንጋጌ ያካትታል። ኢቲቪ በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደር እንደመሆኑ ይህ የሕገ መንግስት አንቀጽ ይመለከተዋል። ነገር ግን ኢቲቪ በቀጥታ፣ ሕግ መንግስቱን ሲንድ፣ ገለልተኛነት በጎደለው መልኩ የአንድ ድርጅትን የፖለቲክ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ሲሆን ነው እያየን ያለነዉ። እነ አንዱዋለም አራጌ ላይ፣ ኢቲቪ የአንድ ወገንን አቋም የያዘ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲያዥጎደጉድ፣ ቢያንስ ቢያንስ ጥቂት ሰኮንዶች፣ የአንዷለምን ጠበቃዎች፣ ወይንም ቤተሰብ፣ አሊያም የትግል አጋሮቹ የሆኑት የአንድነት አመራር አባላትን ለማነጋገር አልተሞከረም። እንግዲህ ከዚህ የምንረዳዉ፣ ሕግን በማክበር አኳያ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴጎችና ኢቲቪ፣ አንድ ጣታቸዉን ወደሌሎች ሲጠቁሙ፣ አራቱ ጣቶቻቸው ወደ እነርሱ መዞራቸውን፣ ሕገ መንግስቱን እየጣሱ ያሉ እነርሱ መሆናቸውን ነዉ።

«አንዱዋለም አራጌን በተመለከተ፣ የግንቦት ሰባትን ተእልኮ ለማስፈጸም አገር ዉስጥ በሕቡእ (ስዉር) ይንቀሳቀሳል በሰላማዊ ትግል እንታገላለን የሚሉ የፓርቲዎችን ሽፋን አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረ በመሆኑ በቂ ማስረጃ አቅርበናል» ሲሉ ነበር የፌደራል አቃቤ ሕጉ ለኢቲቪ አክለው የገለጹት። ምን አይነት መረጃ እንዳቀረቡ ግን አልነገሩንም። ለምን ቢባል ምንም ስለሌለ።

አንዱዋለም ያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ሲያደርግ የነበረው በግልጽና በገሃድ ነዉ። ለተለያዩ ፓልቶክ ክፍሎች፣ አገር ዉስጥና በዉጭ ለሚገኙ ሜዲያዎች በርካታ ቃለ መጠይቆችን ሰጥቷል። በአገር ቤት፣ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ዉይይቶችና ስብሰባዎች ያቀረባቸው ንግግሮች በሙሉ የተደበቁ አይደሉም። ዉጭ ካሉ ኢትዮጵያዊያን ጋር (አንዱም እኔው ነበርኩ) ፣ ብዙ ጊዜ በስልክ ሃሳቦችን ተለዋዉጧል። በስልክ ያደረጋቸው ንግግሮችም፣ 24 ሰዓት የሰላማዊ ተቃዋሚ መሪዎችን ስልክ በሚጠልፈው ቴሌ ዘንድ የተሰሙ ናቸው። ቤቱና ቢሮዉ ከላይ እስከ ታች ተበርብረዉ ፣ የሚስጥራዊ የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች፣ ቦምቦች፣ ፈንጂዎች፣ ሚስጥራዊ ሰነዶች አልተገኙም። ኤሜሎቹ በሙሉ ተነበዋል። አንዱዋለምን ከግንቦት ሰባት ጋር የሚያገናኝ፣ በሕቡእ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ የሚያመለክት አንዳች መረጃ አቃቤ ሕግ አላቀረበም። መረጃዎች ቢኖሩ ኖሮ፣ «እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ» እንደተባለ፣ ዜጎችን በማዋረድና በማሳነስ የሚታወቀዉ ኢቲቪ፣ ይሄን ጊዜ በስፋት ያወራልን ነበር።

ኢቲቪ ግን አንዱዋለምን ለመክሰስ ያቀረበው፣ አንድ የአንድነት አባል የነበሩ፣ ተስፋሁን አናጋዉ የተባሉ ሰው የተናገሩትን ነዉ። አንዱዋለም ከታሰረ በኋላ አቃቤ ሕጎች መረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው፣ የዉሸት መረጃዎች ማሰባሰቡ የግድ ሆነባቸው። የታሰሩ ሌሎች የአንድነት አባላትን ማግባባት ጀመሩ። «በአንዱዋለም ላይ እኛ ተናገሩ የምንላችሁን ከተናጋራችሁ እንፈታቹሃለን» ብለው እጆቻቸዉን ጠመዘዙ። ብዙዎች በአንዱዋለም ላይ የዉሸት መረጃ ማቅረቡ ሕሊናቸውን ስለከበደው ፍቃደኛ አልሆኑም። ነገር ግን እንደ ተስፋሁን አናጋው፣ የሚባሉ ደካማ ሰዎች ተገኙና የዉሸት ምስክርነት ቀረበ። እንግዲህ በአገዛዙ ካድሬዎች ተቀናብረው ከቀረቡ የዉሽት ምስክርነቶች ዉጭ፣ ቅንጣት የምታክል፣ አንዱዋለምን ሽብርተኛ ወይንም ከግንቦት ስባት ጋር የሚሰራ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ አልቀረበም።

«ግንቦት ሰባት ፣ ግንቦት ሰባት ……» እንባላለን። ከጅምሩ በግንቦት ሰባት ላይ ጠንካራ ተቃዉሞ ያለኝ ሰው ነኝ። የግንቦት ሰባት ፖለቲካ አይመቸኝም፣ ለአገርም ይጠቅማል ብዬ አላስብም። ግንቦት ሰባቶች ከያዙት የተሳሳተ መንገድ እንዲመለሱ፣ በሻእቢያ ድጋፍ ሳይሆን፣ በሕዝብ ጉልበት በመተማመን ወደ ሰላሙ መንገድ እንዲመጡ መክሪያለሁ። በተለያዩ ጊዜያት ለአንባቢያን ያቀረብኳቸውን ጽሆፍችን መመልከት ይቻላል።

ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በአገር ዉስጥ በሰላም ለዉጥ ለማምጣት የሚሰሩ ድርጅቶችን ደግፊያለሁ። በተለይም የአንድነት ፓርቲ በጣም የሚመቸኝ ፓርቲ እንደመሆኑ፣ አንዱዋለም አራጌን ጨምሮ፣ ከፓርቲዉ አመራር አባላት ጋር ሃሳብ የተለዋወጥኩባቸው በርካታ ጊዜያት ነበሩ። አንዱዋለም አራጌ፣ እግዚአብሄርን የሚፈራ፣ የልጆች አባት፣ የሰላማዊ ትግል አርበኛ ነዉ። አንዱዋለም ስለ ትጥቅ ትግል ያለዉን አመለካከት አውቃለሁ። በየትኛዉም መድረክና ፍርድ ቤት፣ መጽህፍ ቅዱስ ላይ እጄን ጭኜ የምመሰክረዉ ነዉ። አንዱዋለም አራጌ የግንቦት ስባት አባል ወይንም ሽብርተኛ ነው የሚለውን፣ በምን መስፈርትና መልኩ ልቀበለው አልችልም። በርግጥ አንዱዋለም የግንቦት ሰባት አባል ከተባለ፣ እኔም የግንቦት ሰባት አባል ነኝ እንደ ማለት ነዉ።

በጣም ያሳዝናል። እንደ አንዱዋለም አራጌ አይነት አገር ወዳድ ዜጎች፣ አገራቸዉን በመዉደዳቸው፣ የሕዝብ መብት ይከበር በማለታቸው፣ «ሽብርተኞች» በሚል አሳዛኝ ክስ ሲታሰሩ ማየት፣ አገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች ቀና ብለው የሚራመዱባት ሳይሆን ፣ አሳፋሪ ድራማ የሚካሄድባት፣ ሕግ መቀለጃ የሆነባት አገር መሆኗ፣ በርግጥ ልብን የሚያደማ ነው።

እንግዲህ፣ ሁሌ እንደማደርገዉ፣ ጥሪ ለኢሕአዴጎች አስተላልፋለሁ። ኢሕአዴግ ዉስጥ፣ ለአገርና ለሕዝብ የሚያስቡ ካሉ፣ በድርጅታቸው ዉስጥ እየተደረገ ያለውን አፈናና ግፍ በቃ የማለት አቅምና ጉልበት ሊኖራቸው ይገባል ባይ ነኝ። ድርጅታቸው ዉስጥ ያሉ ጥቂቶች ድርጅታቸውን ይዘው ገደል እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነ አንዱዋለምን በማሰር ኢሕአዴግ ምንም የሚጠቀመው ነገር የለም። እነ አንዱዋለምን በዉሸት ክስ ከሶ፣ በቴለቭዥኝ ደግሞ ስማቸውን ማጉደፍ፣ ነዉር ነዉ። ኢሕአዴግ የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርግ ነዉ። የአረና ትግራይ አመራር አባል አብርሃ ደስታ አንዴ ሲጽፍ፣ የሕወሃት እምብርት በነበረችው የትግራይ ክልል፣ አንዱዋለም አራጌ በጣም ተወዳጅ ፖለቲከኛ እንደሆነ ገልጾ ነበር። አንዱዋለም አራጌ፣ በክልሎች ሁሉ ሕዝብ የሚያውቀዉ ጀግና መሪ ነዉ። በርሱ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ፣ የበለጠ አንዱዋለምን ከፍ የሚያደርግ፣ ኢሕአዴግን ደግሞ የሚያሳንስ ነዉ። አንዱዋለምን እና ሌሎች የሕሊና እስረኞች፣ አለመፍታት በቀጥታ ከሕዝቡ ጋር እንደመላተም ነው። አይጠቅምም። ጉዳት አለው።

ለኢሕአዴጎች ጥሪ ባቀርብም፣ የነአንዱዋለም ጉዳይ፣ የኢሕአዴጎች ጉዳይ ብቻ ግን አደለም። ኢሕአዴጎች ወደ ሕሊናቸው ተመልሰው መልካም ነገር ያደርጉ ዘንድ እነርሱን ማነጋገርና ለማሳመን መሞከር፣ ማበረታታት ተገቢ ነዉ የሚል እምነት ቢኖረኝም፣ ሁሉንም ነገር ከነርሱ ጠብቆ ቁጭ ማለቱ ግን፣ እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። እነርሱ ቢሰሙ መልካም ነዉ፤ ካልሆነ ግን እያንዳንዳችን መብታችንን የማስከበር ሃላፊነት ያለብን ይመስለኛል። ዛሬ እነ አንዱዋለም ናቸው። ነገ እያንዳንዳችን ቤት ይንኳኳል ። ዛሬ ሊመቸን ይችላል። ነገር ግን ለሕይወታችን ምንም ዋስትና አይኖረንም። አንድ የመንግስት ባለስልጣን ፊታችንን አይቶ ከጠላን፣ በቀላሉ ወደ ወህኒ ሊወረወረን የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ማወቅ አለብን። አለን የምንለውን ቢዝነስ አንዱ ከፈለገዉ፣ «ያለ የሌለዉን እያመጡ፣ ይሄን ያህል ግብር ክፈል» ተብለን ከጨዋታ ዉጭ በቀላሉ ልንሆን የምንችልበት አገር ነዉ ያለችን። አቤት የምንልበት የሕግ ስርዓት የለም። አብዛኞቹ ዳኞች በመመሪያ የሚፈርዱ ካድሬዎች ናቸው። በመሆኑም፣ ኢትዮጵያ፣ ሕግ የበላይ የሆነባት፣ ለሁሉ ዜጎቸ እኩል የሆነች፣ ኢትዮጵያዊያን ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የሚችሉባት፣ መቀባባል፣ ይቅርታ፣ ፍቅር፣ ሰላም ፣ ፍትህና ወንድማማችነት የሰፈነባት፣ የበለጸገች አገር እንድትሆን፣ እያንዳንዳችን የድርሻችንን መወጣት አለብን። ዳር ሆኖ ተቀመጦ ማውራት ይብቃ። ሌሎች ለምን እንዲህ አላደረጉም ብሎ መክሰስ ይብቃ። ሌሎች ሞተው በነርሱ አስክሬን ላይ ተረማመደን ለመሻሻል መሞከር ይብቃ። አገራችን የእስክንደር፣ ወይንም የአንዱዋለም፣ ወይንም የበቀለ ገርባ፣ ወይንም የርዮት አለሙ ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ናት፣ ሁላችንም ተስፋ ሳንቆርጥ፣ ሌሎች ነጻ እንዲያወጡን ሳንጠብቅ፣ የድርሻችንን እንወጣ።

መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች እያቀረቡላቸው መሆኑ ታወቀ::

የሃያሰዎስተኛ ክ/ጦ ኣዛዥ ብ/ጀነራል በላይ ስዩም፤ የሰላሳ ኣንደኛ ክ/ጦ ኣዛዥ ብ/ጀነራል ድሪባና፤ የሰላሳ ሰዎስተኛ ከ/ጦር ኣዛዥ ብ/ጀነራል ከበደ ፍቃዱ እኛ ኣዲስ ቶሻሚ በመሆናችን ብዙ ተቀባይነት የለንም::

የማእከላዊ እዝ የበላይ ኣመራሮች በተገኙበት ስብሰባ ላይ እንደ ኣንድ ትልቅ ኣጀንዳ ሆኖ የቀረበ። ኣብዛኛው የሰራዊቱ ኣባል ማግኘት የሚገባው ጥቅም ባለማግኘቱ በሰራዊቱ ውስጥ የመቀጠል ፍላጎቱ ያበቃና የሞተ በመሆኑ ምክንያት ክውትድርና ኣለም ተሰናብቶ የግል ሂወቱ መምራት እንደሚፈልግ ላቀረቡት ጥያቄ በስብሰባው ውስጥ የተካፈሉት የበላይ ኣመራሮች የቀረበው ጥያቄ ሰምተው እንዳልሰሙ በመምሰል ተገቢ መልስ ሳይሰጡበት እንዳለፉ ለማወቅ ተችለዋል::

መረጃው በማስከተል በስብሰባው ውስጥ የተገኙ የሃያሰዎስተኛ ክፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል በላይ ስዩም፤ የሰላሳ ኣንደኛ ክፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ድሪባና፤ የሰላሳ ሰዎስተኛ ከፍለጦር ኣዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ከበደ ፍቃዱ እኛ ኣዲስ ቶሻሚ በመሆናችን ብዙ ተቀባይነት የለንም ኣታስቸግሩን ብለው መልስ እንደሰጥዋቸው ለማወቅ ተችለዋል::

ይህ በንዲህ እንዳለ ከሰራዊቱ ውስጥ ለመኪና ሾፌርነት ስልጠና ተመልምለው ኣዲ ቡኽራይ ወደ ተባለው ቦታ የታላኩ ወተሃደሮች ስልጠናውን በመተው ወደ ክፍላቸው ተመልሰው የ 7 ኣመት ኣገልግሎታችን ስለ ጨረስን ከሰረዊት የመሰናበት መብታችን ይረጋገጥልን ብልው ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ::

ወደ ስልጠናው ከተላኩ ቦሃላ ተመልሰው ወደ ክፍላቸው ከተመለሱ ምልምል ወተሃደሮች ስም ለመጥቀስ። ወ/ር ማእርግ ሰፍየ፤ ወ/ር ተሻለ ኣየነው፤ ወ/ር ክብሮም ኣስረስና ሌሎች ሲሆኑ። በተለይ ከ 1990 ኣ/ም ባሃላ የተቀጠሩ የሰራዊቱ ኣባላት የደሞዝ ይሁን የማእርግ እድገት መብታቸው እንዳላገኙና በላዩ ላይ ለኣባይ ግድብ፤ ለትምህርት ቤትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እየተባለ ደሞዛቸው እየተቆረጠ በመሆኑ ምክንያት ተማርረው ከሰራዊቱ ለመልቀቅ ስንብት እየጠየቁ መሆናቸው መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል::

የኢሕኣዴግ ፍራቻ የወለደው እቅድ ምርጫውን ሊያጭበረብር ነው::የድምጽ ማጭበርበሮች እንኳን ቢከሰት ተቃዋሚዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም።
ኢህአዴግ ከምርጫ 2007 በሁዋላ ረብሻ ሊነሳ ይችላል አለ::

ኢትዮጵያን ላለፉት 23 ዓመታት የገዛው ኢህአዴግ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በአዲስ አበባና በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች ረብሻዎች ሊነሱ እንደሚችሉ ፓርቲው ድምዳሜ ላኢ መድረሱን አስታውቋል።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ተብለው የተፈረጁት በተለይ ግንቦት7 እና ኦነግ ምርጫውን ተከትሎ በምርጫ 97 የታየውን አይነት የህዝብ አመጽ ለማስነሳት እየሰሩ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰው ኢህአዴግ፣ ከአሁኑ ጀምሮ በአንድ ለአምስት አደረጃጀትና የከተሞችን ነዋሪዎች ስለ አሸባሪዎች አላማ እና ግብ በማስረዳት ህዝቡ በአመጹ ተሳታፊ እንዳይሆን እንደሚያስተምር አስታውቋል።

አሸባሪ የተባሉ ድርጅቶች በመልካም አስተዳደር፣ በሙስና እና በኢኮኖሚ ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ተጠቅመው ህዝቡ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ሊያደርጉ ይችላሉ አለው ኢህአዴግ፣ ለዚህ አላማ እንዲረዳቸው ደግሞ ኢሳትንና ቪኦኤን የመሳሰሉ የመገናኛ ብዙሀንን በአገር ውስጥ ደግሞ አንዳንድ ጽንፈኛ አስተሳሰብ ያላቸውን መጽሄቶች ሊጠቀሙ ይችላሉ ብሎአል። በአገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ ለአመጽ ጥሪው ህጋዊ ሽፋን ለማሰጠት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ ።

በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ የአሸባሪዎች ኢላማ እንዳይሆን ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ኢህአዴግ ገልጿል።

በሚቀጥለው አንድ አመት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች በሽብረተኝነት ዙሪያ ተከታታይ ትምህርት የሚሰጣቸው ሲሆን፣ ግንባሩም ከእዚህ ስልጠና የአካባቢ የሰላም ጠባቂዎችን እንደሚመለምል ፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ገዢውን ፓርቲ አይደግፉም የሚባሉትን የመለየት ስራም እንደሚሰራ ታውቋል።

ኢህአዴግ ምርጫውን ተከትሎ ሊነሳ የሚችል ማንኛውም ተቃውሞ ሽብርተኝነት ነው ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። በምርጫ ሂደቱ ላይ ፍትሀዊ ያልሆኑ አሰራሮች እንዲሁም የድምጽ ማጭበርበሮች እንኳን ቢከሰት ተቃዋሚዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ አይፈቀድላቸውም። ኢሳት ዜና

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እሁድ ጥር 4 ቀን 2006 ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሄድ የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እና አብረዋቸው የታሰሩትን የኢስላም ልጆች መዘየራቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በዚያራውም ከኮሚቴው አባላት ጋር የተነጋገሩ ሲሆን የፓርቲው አመራሮች በኮሚቴው አባላት ላይ የሚታየውን ፅናት አድንቀዋል፡፡

በህዝብ ግንኙነት ክፍሉ የተመራው የከፍተኛ አመራር አባላት
– የፓርቲው ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር አቶ ተክሌ በቀለ
– የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ
– የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው
– የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ
በማረሚያ ቤቱ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ከኮሚቴው አባላት ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ ከሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የቅሊንጦ እስረኞች –
1-ሼህ መክት ሙሄ – የሼሪዓ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ
2- አቡበከር አህመድ
3- ካሚል ሸምሱ
4- አቡበከር አሊ
5- ሙባረክ አደም
6-አህመድ ሙስጠፋ
7- አብዱራዛቅ አክመል
እና ሌሎችም ሲሆኑ እነ አቡበከር ከፍተኛ የመንፈስ ጥንካሬ የሚታይባቸው ዛሬም ዛሬም ከፊታቸው ፅናት የሚነበብባቸው እንደነበር የአንድነት አመራሮች ገልፀዋል፡፡
የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠንከር ያለ ምክርና መልዕክትም አስተላልፏል፡፡ ሀገሪቷ በነፃነት ደረጃ እንዲህ ባለ ሁኔታ ላይ መድረሷ እንዳሳዘናቸውም ለፓርቲው አመራሮች ገልፀዋል፡፡

ኮሚቴዎቻችንን ህጋዊ ወኪሎቻችን መሆናቸውን ሳር ቅጠሉ የመሰከረው ጉዳይ ቢሆንም ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ግን በእስር ቤት እንዲማቅቁ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

አላህ ፍትህን ያስፍንላቸው!!!
ፍትህ ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች !!!

ቁጥራቸው ወደ 40 የሚጠጋ የእሕኣፓ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሰራዊት ጎንደር እና ጎጃምን በተቆጣጠረ ጊዜ በውጊያ ከተማረኩ በኋላ በ1983/84( በ1991)ከተረሸኑ በኋላ በጣና በለስ ፕሮጀክት አቅራቢያ በጅምላ መቀበራቸውን ምንጮች ለኢትዮ ሚዲያ ገልጸዋል::

የጅምላ መቃብሩን የቆፈረው ቡልዶዘር የጣና በለስ ፕሮጀክት ንብረት የነበረ ሲሆን ቡልዶዘሩን ሲያንቀሳቅስ የነበረውም ኦፕሬተር ግድያውን እና የጅምላ መቃብሩን በተመለከት ህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ ምስጢር ለመጠበቅ ሲባል ወዲያው የተገደለ መሆኑ ምንጮቹ ገልጸው የግድያው ትእዛዝ የሰጡት እና እንዲፈጸም ያደረጉት ሟች መለስ ዜናዊ እና አኦ ስብሃት ነጋ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሳይ ሁኔታ ስምንት የኢሕኣፓ ሰራዊት አመራሮች የነበሩት በሕወሓት ሰራዊት ተይዘው በ ባዶ 6 እስር ቤት ትግራይ መታሰራቸው እና የግድያ ቅጣት ተላልፎባቸው እንደነበር ይታወሳል:: ይህ የኢሕኣፓ ከፍተኛ አመራሮች ጸጋዬ ደብተራው ሃጎስ በርሄ ይሳቅ ደብረጺሆን እና ሌሎችም የተላለፈባቸው የግድያ ቅጣት የተፈጸመው በትግራይ ይሁን በጎንደር አሊያም በጎጃም እስካሁን መረጃው እንዳሌላቸው ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::
http://www.ethiomedia.com/14store/5563.html

የምርጫ 97ን ቀውስ ተከትሎ ወደ እስር ቤት ከገቡት የቀድሞዎቹ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው፣ በቅርቡ የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ስለአዲሱ ሊቀመንበርነታቸው፣ ስለመጪው ዓመት ምርጫና ሌሎች ጉዳዮች ነአምን አሸናፊ አጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን አመራሩ ላይ ወጣቶች አይታዩም በማለት የሚተቹ አሉ፡፡ የእርስዎን ዳግም ሊቀመንበር ሆኖ መመረጥንም እንደ ምሳሌ ያነሱታል፡፡ ለምንድነው ወጣቶች ወደ አመራር የማይመጡት?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ያለባቸው መራጮች ናቸው፡፡ መራጮችንና የአንድነት አባላትን መጠየቅ ነው፡፡ በመሠረቱ አንድነት የወጣቶች ፓርቲ ነው፡፡ ባለፈው ሥራ አስፈጻሚም ሆነ በብሔራዊ ምክር ቤቱ የወጣቱ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር፡፡ በጠቅላላ ጉባዔው ሰባ በመቶ አካባቢ ወጣት ነው፡፡ የተወዳደርኳቸው ሰዎችም ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ነገር መጠየቅ ያለባቸው አባላትና ጉባዔው ናቸው፡፡
መጠየቅ ያለበት እኔ ፍላጎት ኖሮኝ ወጣቶችን ወደታች ገፍቼ ድርጅታዊ ሥራ ሠርቼ ብመጣ ኖሮ ነበር፡፡ ወጣቶችን ወደታች ተጭነሃል ማለት ይቻል ነበር፡፡ ዋናው ማየት ያለብን ጠቅላላ ጉባዔውና አጠቃላይ ሒደቱ ዲሞክራሲያዊ ነበር ወይስ አልነበረም ነው፡፡ በእኔ ግምት አንድነት ፓርቲ ለዲሞክራሲያዊ አሠራር ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ፓርቲዎች የሚበልጠው ያለ አይመስለኝም፡፡ ለዚህም የምገልጸው በምክር ቤታችንም በሕገ ደንባችን መሠረት የምንሰበሰበው በሦስት ወር አንዴ ነበር፡፡ ምክር ቤቱ ግን በዓመት እስከ 20 ጊዜ ይሰበስባል፡፡ ምክንያቱም የጀመርነውን አጀንዳ በምናደርገው ሰፊ ውይይት መጨረስ አንችልም፡፡ አጀንዳ ጨርሰን አናውቅም፡፡ አራት አጀንዳዎች ቀርበው እንደሆን ሁለቱን ጨርሰን ሁለቱን ደግሞ ለሚቀጥለው ጊዜ እናስተላልፋለን፡፡ ይህ ደግሞ የዲሞክራሲያዊ ውይይት ነፀብራቅ ነው፡፡
እኔ እንዲያውም ቅስቀሳ አላደረግኩም፡፡ የእኔ ተወዳዳሪዎች ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ነው ወይም አይደለም? የሚለው ነው ጥያቄው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ነበር፡፡ ለምን ወጣቶች አልመጡም ለሚለው የእነሱ ምርጫ ነው፡፡ እኔ በአብዛኛው የተመረጥኩት በወጣቶች ነው፡፡ ምናልባት ከዚህ በፊትም እንዳደረግኩት ወጣቶችን የማሳተፍ አመለካከትና ባህሪ አለኝ፡፡ እኔ አመራር በነበርኩበት ጊዜ በሕገ ደንቡ መሠረት በሥራ አስፈጻሚ 13 አባላት ነው የሚኖሩት፡፡ እኔ ግን ወጣቶች ወደፊት እንዲቆጠሩ ስድስት አባላት ድምፅ የመስጠት ሥልጣን ሳይኖራቸው አስገብቻለሁ፡፡ ደንቡ ስለማይፈቅድልኝ ነው እንጂ ባለድምፅ ሆነው መግባት ይችሉ ነበር፡፡ ደንቡ ግን አይፈቅድም፡፡ ስለዚህ ድምፅ አልባ ከመሆናቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ የአመራር አባል ነበሩ፡፡
አቶ ግርማ ሰይፉም የዚያ አባል ነበሩ፡፡ ሌላው ወጣቱን ለዚህ ቦታ ማንም አልከለከለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ ሜካኒካል ይሆናል፣ ኮታ ይሆናል፡፡ ወጣቶች መምጣት አለባቸው፡፡ የኮታ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ የመብት ጉዳይ ነው እንጂ የሚሰጣቸው ስጦታ አይደለም፡፡ ስለዚህ በአንድነት ፓርቲ ለወጣቶችም ሜዳው ክፍት ነው፡፡ ነገ ጠዋት የላቀ ከመጣ ምክር ቤቱ በወጣት ሊተካ ይችላል፡፡ ከፖለቲካም አንፃር መታየት ያለበት ስብጥሩ ነው፡፡ ከወጣቶችም፣ ከጐልማሶችም፣ ከአዛውንትም ያ ስብጥር ነው መሆን ያለበት፡፡ ወጣትም ሆኖ ሽማግሌም ሆኖ የራሱ የሆነ ችግር አለበት፡፡ ያንን የሚያቻችለው መቀላቀሉ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በተቃዋሚውም ሆነ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያሉት የ60ዎቹ ትውልድ አባላት አመራርነት የሚያበቃውና ወጣቶች በሰፊው ወደ መሪነት የሚመጡት መቼ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- በእኔ በኩል በአመዛኙ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ፖለቲካ የሚለው አይሠራም፡፡ ባለፈው አላየነውም አሁንም አይታይም፡፡ የአንድነት ዕድሜ ስድስት ዓመት ነው፡፡ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራት ፕሬዚዳንቶችን ለውጧል፡፡ የመጀመሪያዋ ብርቱካን ሚደቅሳ ነበረች፡፡ የወጣቶች ተወካይ ነበረች፣ የ60ዎቹ አይደለችም፡፡ ከዚያ እርሷ ስትታሰር እኔ ተጠባባቂ ሆኜ ኃላፊነቱን ተረከብኩ፡፡ ከዚያ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሆነ፣ አሁን እኔ መጣሁ፡፡ ማንም ፓርቲ በስድስት ዓመት ውስጥ አራት ፕሬዚዳንት የቀየረ የለም፡፡ ይህ የሚያሳየው የአንድነትን ዲሞክራሲያዊነት ነው፡፡ በመሠረቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብቃት ባለው ከ60ዎቹ በኋላ ባለው ትውልድ መተካት አለበት፡፡ ያ የእኔ እምነት ነው፡፡ የ60ዎቹ ፖለቲከኞች መጪውን ትውልድ አብቅተው መተካት እንዳለባቸው እምነቴ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን አንድነትን እንደ ምሳሌ ከወሰድነው መጀመሪያ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወጣት መሪ ነበሩ፡፡ ከዚያ እሳቸው ሲታሰሩ እርስዎ መሪ ሆኑ፡፡ ቀጥሎ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አሁን ደግሞ ተመልሰው እርስዎ መጡ፡፡ በአንድነት ውስጥ ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ውጪ ያው የ60ዎቹ ትውልድ አባላት ስለሆናችሁ ከዚያ አንፃር ለማለት ፈልጌ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ትክክል ያልሆነ ምዘና ነው፡፡ ምንድነው የ60ዎቹ ፖለቲከኞች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ቅድም እንዳልኩህ ስብጥሩን ነው ማየት ያለብን፡፡ ብርቱካን በነበረችበት ጊዜም ሆነ አሁን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች ጥቂት ናቸው፡፡ ምናልባት በጣት የሚቆጠሩ [እኔ፣ ነጋሶ፣ አስራት]፡፡ ነገር ግን ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ የነበሩት አብላጫዎቹ ከ60ዎቹ በኋላ የመጡ ትውልዶች ናቸው፡፡ በአሁኑ ብሔራዊ ምክር ቤት ውስጥ ከ35 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉት 72 በመቶ ናቸው፡፡ የ60ዎቹ አሉበት፡፡ ነገር ግን በአብላጫው ወጣቶች ናቸው፡፡ በእኔ ካቢኔ ውስጥ የ60ዎቹ ትውልድ ያለነው ሁለት ሰዎች ነን፡፡ ከ15 ሰዎች አንድ ሰው የ60ዎቹ ሆኖ ላይ ስለተቀመጠ የ60ዎቹ ተፅዕኖ አለ ለሚባለው ምዘናው ትክክል አይመስለኝም፡፡ መታየት ያለበት ይዘቱ ነው፡፡ የ60ዎቹ ትውልድ አባላት እንዲያውም የት እንዳሉ ግራ ይገባኛል፡፡ አንዳንድ ቦታ መሪ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ የፓርቲው መዋቅር መፈተሽ ካለበት የ60ዎቹ የፖለቲካ ተሳፊዎች ወጥተው ዳር የቆሙ ይመስለኛል፡፡ ደግሞም የተፈጥሮ ሒደት ነው፣ የፖለቲካም ሒደት ነው፣ የታሪክም ሒደት ነው፡፡ መታየት ያለበት የግለሰቦች የ60ዎቹ ትውልድ መሆን ሳይሆን ስብጥሩ ውስጥ ስንት አሉ የሚለው ነው፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን እንደ አዲስ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው መጥተዋል፡፡ ለፓርቲው ምን አዲስ ነገር ይዘው መጡ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኛ ፓርቲያችንን የምንመራው በሥርዓት ነው፡፡ ፓርቲው በ2002 ዓ.ም. የስትራቴጂ ዶክመንቱንና የአምስት ዓመት ዕቅዱን በመጽሐፍ መልክ አውጥቶታል፡፡ የአነድነት ፓርቲ መሠረታዊ ራዕይና ግብ በዚያ ውስጥ ነው የሚታየው፡፡ እዚያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ነው ሁላችንም በቀጣይነት እየገነባን የምንሄደው፡፡ ነገር ግን በ2002 እና በ2003 ዓ.ም. ያወጣነው የስትራቴጂ ግንባታ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር መዛመድ አለበት፣ መቀነባበር አለበት፡፡ ስለዚህ በዚያ መንገድ አንዳንድ ለየት ያሉ ሙከራዎች አካሂዳለሁ፡፡
የመጀመሪያው ሙከራዬ አንድነት ምናልባት ካሉት ፓርቲዎች በጉልህ ጠንክሮ የሚታይና መዋቅሩ ታች ድረስ የወረደ ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲያው እንደ ሌላው ጉልበት ወይም አቅም አለን ባንልም በቂ የመንቀሳቀስ ችሎታ አለን የሚል ግምት አለኝ፡፡
ይህንን የአመራር መርህ ከአንድነት አቅምና ሕዝባዊ ገጽታ አንፃር የተለየ (Rebranding) እንዲሆን አደርጋለሁ፡፡ ለምሳሌ አንዱ ያደረግኩት ሥራ አስፈጻሚውን በአብዛኛው ወጣትና አዲስ ነው ያደረግኩት፡፡ በትምህርታቸው ብቁ የሆኑ ናቸው፡፡ በትምህርት ብትሄድ አሁን ከ15 ሰዎች ስድስቱ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሰባቱ የመጀመርያ ዲግሪ አላቸው፡፡ ሁለቱ ደግሞ ዲፕሎማ አላቸው፡፡ አሁን ይኼ አዲስ ምልክት (New Branding) ነው፡፡ ሁለተኛ እነዚህን ሰዎች ስመድብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ችሎታ እንዲኖራቸው አንዱ መሥፈርት ነበር፡፡ አሁን ዘመኑ ወደዚያው እያመራ ነው፡፡ ስለዚህ በኢንፎርሜሽን ግንኙነታችን ከውጭው መረጃ እኩል አንድነት መራመድ አለበት፡፡
ሌላው ትኩረት የምሰጠው ወጣቶችን የማብቃት ሥራ ነው፡፡ ወጣቶች በቅተው ፓርቲውን እንዲመሩ አደርጋለሁ፡፡ አሁን እኔ እዚህ ሆኜ ወጣቶችን ነው ወደፊት እንዲሮጡ የማደርገው፡፡ ይህን ካደረግኩ በኋላ በእኔ እምነት ክርክርም መካሄድ አለበት፡፡ እስካሁን የተካሄደው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ውጤት አላስገኘም፡፡ ይኼ ምንም የምንክደው አይደለምና ይህ ለምንድን ነው የሚለው ብዙ ጊዜ ይረብሸኛል፡፡ ወይ ማቆም አለብን ወይ መሥራት አለብን፡፡ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተበጣጠሱ ዘጠና ፓርቲዎች አሉ፡፡ ከዘጠናዎቹ ደግሞ ጉልህ የሆኑት አሥር አይሆኑም፡፡ አሥሩም አብረው መሥራት አልቻሉም፡፡ በጥምረትም በግንባርም አልተቻለም፡፡ ለምንድን ነው? ለአሥሩም ቢሆን አሥር መሪዎች አሉ፣ አሥር ፕሮግራሞች አሉ፡፡ አሥሩም እንግዲህ አሥር መሪ ኖሮዋቸው ፖለቲካ ይመራሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ ስለዚህ በብሔራዊ ምክር ቤትና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስገኛለሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡
በእኔ እምነት እንግዲህ አንድነት ፓርቲ ግንባርና ጥምረት ውስጥ አይገባም፡፡ ወደ ውህደት አንድ አመራር አንድ ፕሮግራም ወዳለው እንቅስቃሴ እንገባለን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህ የእኔ ሐሳብ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ስብሰባ ላይ ፈንጥቄያለሁ፡፡ ይህ መሆን አለበት፡፡ የተጀመሩት ውህደቶች በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ማለቅ አለባቸው ብሎ ጠቅላላ ጉባዔው ወስኗል፡፡ ወይ እንዋሀዳለን ወይ እንለያያለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁኔታ አንድ የማየው እስከ 2007 ዓ.ም. ወይም በዚህ ዓመት ለእኔ የውህደት ዓመት ነው ብዬ የምገምተው፡፡ ወይ እንዋሀዳለን አለበለዚያ በሰላም ተለያይተን ሁላችንም ጉልበታችንን በየአካባቢው በትብብር እናጠናክር የሚል አመለካከት አለኝ፡፡
ይህን ካደረግኩ በኋላ ከኢሕአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) እንዲኖረን እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት፡፡ ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያያቸው እንደ ጠላት ከዚያም አልፎ እንደ ሽብርተኛ ነው፡፡ ይኼንን ነገር ለሚያስብ ሰው እኮ በጣም ነው የሚያስደነግጠው፡፡ በእኛም በኩል ኢሕአዴግን የምናየው እንደ አውሬ ነው፡፡ ምናልባት የሠራውን ሥራ ሁሉ ዋጋ (Credit) ያለመስጠት አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖለቲካችን ኢሕአዴግን መቃወም ብቻ ሆኖአል፡፡ ያ መቆም አለበት፡፡ ትልቁ ኳስ ያለው ኢሕአዴግ ዘንድ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ወደፊት በማደርገው እንቅስቃሴ ገንቢ ግንኙነት አድርገን ያለውን የፖለቲካ ምኅዳር ለሁላችንም እኩል ማድረግ አለበት፡፡ ኢቴቪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡ ለምንድነው የኢሕአዴግ ብቻ የሚሆነው? መብት እኮ አለን፡፡ ለኢቴቪ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡ የጻፍነው ምንድነው የኢሕአዴግን ኮንፈረንስ ከባህር ዳርና የኢሕአዴግን ብሔራዊ ምክር ቤት በቀጥታ ስታስተላለፉ ነበር፡፡ የእኛን ግን አልዘገቡም፡፡ ለኢሕአዴግ 99 በመቶ ሰጥተው ለእኛ ግን አንድ በመቶ እንኳን አይሰጡንም፡፡ ይኼ ሁሉ ቁልጭ አድርጐ የሚያሳየው የኢሕአዴግን ድክመትና ስህተት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ለብዙ ፓርቲዎች የእንዋሀድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም እንደታየው ብዙ ውህደቶች ምርጫ ሲደርስ ከመሰባሰብ በዘለለ ብዙም ሲገፉበት አይስተዋልም፡፡ የ97ቱን ቅንጅት ማስታወስ ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን እርስዎ የሚያቀርቡት ሐሳብ በምን ይለያል? ከዚህ ቀደም ተሞክረው እንደከሰሙት እንደማይሆንስ ማረጋገጫው ምንድነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የቅንጅት ራሱን የቻለ ጉዳይ አለው፡፡ ቅንጅት አልተዋሀደም ነበር፡፡ ለዚህም ነው ቅንጅት ግንባር ደረጃ አልደረሰም የሚባለው፡፡ ለቅንጅት ከፍተኛውን ድቀት ያስከተሉት የኢሕአዴግና የቅንጅት መሪዎች ናቸው፡፡ በወቅቱ ኢሕአዴግ ያልጠበቀው የፖለቲካ አድማስ ነው የመጣበት፤ በ97 ምርጫ አልጠበቀውም ነበር፡፡ አራቱ ፓርቲዎች ማለትም መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ቀስተ ደመናና ኢዴሊ ሆነው ቅንጅት የተመሠረተው ኅዳር ላይ ነበር፡፡ ኅዳር ላይ ተመሥርተን ግንቦት ላይ ነው ከፍተኛ ዕርምጃ ያሳየነው፡፡ ያ ሁኔታ ኢሕአዴግ ያለውን ግምት በጣም ነው ያዛባው፡፡ ኢሕአዴግ አቅም አይፈጥሩም የሚል ግምት ነበረው፡፡ ገና ስንፈጠር በምርጫው አካባቢ አዲስ አበባን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠርን፡፡ የምርጫው ዕለት ምሽት በአጠቃላይ የምርጫው ሒደት ተናጋ፡፡ በዚያ ምክንያት ቅንጅት ከፍተኛ ውድቀት ውስጥ ገባ፡፡ ኢሕአዴግ ትኩረት አደረገብን፡፡
በዚያ ምክንያት እኛም ወደ እስር ቤት ገብተን ከዚያ ደግሞ ወጣን፡፡ ያው ነገሩ ትክክል ስላልነበር መውጣት እንደነበረብን እኔ አምናለሁ፡፡ ከወጣን በኋላ ደግሞ እኛ አንድ መሆን አልቻልንም፡፡ በእስር ቤት ውስጥ ብሶት ተፈጠረ፡፡ እንደገና ቅንጅትን ለአቶ አየለ ጫሚሶ ሰጡት፡፡ በዚያ በዚያ በመካከላችን ችግሩን በሰከነ ሁኔታ ለማራመድ አልቻልንም፡፡ በዚህ በኩል የራሱ የኢሕአዴግም የእኛም ድክመት ነበር፡፡ ከዚያ በፊትም በተፈጠሩት ስብስቦች እንደዚሁ የመሪዎች ብዛት ነው ችግሩ፡፡ አሁን እኔ የምለው ውህደት ከሆነ አንድ መሪ ሊኖር ይችላል፡፡ ውህደቱም መፈጸም ያለበት በዲሞክራሲያዊ መርሆዎች መሆን አለበት፡፡ ውህደት ላይ ዲሞክራሲያዊ ባህል መፍጠር አለብን፡፡ አመራር አንድ መሆን አለበት፡፡ ሕግ፣ ሥነ ሥርዓትና ደንቡ መታየት አለበት፡፡ እናም ዲሲፕሊን ሊኖረን ይገባል፡፡ የባህሪ ለውጥም ያስፈልገናል፡፡ ከዚህ አንፃር አንደኛ እኛ አመራሮች የባህሪ ለውጥ ያስፈልገናል፡፡ ያ እስከሆነ ድረስ እኔ ውህደት ይወድቃል ብዬ አላስብም፡፡ አልተሞከረም፡፡ በተጨባጭ ብሔራዊ ዕይታ ያለው ውህደት እኮ እስካሁን አልተካሄደም፡፡
ሪፖርተር፡- ከዚህ ከውህደቱ ጋር በተያያዘ የርዕዮተ ዓለም ጉዳይስ እንዴት ነው የሚታየው? ብሔራዊ የሆነ ፓርቲ ይኖራል፤ ኅብረ ብሔራዊ የሆኑ ፓርቲዎችም ይኖራሉ፡፡ ይህስ ለውህደቱ እንቅፋት አይሆንም?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- እኔ ሁላችንም ወደ ብሔራዊ ምክክር መምጣት አለብን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለምሳሌ ብሔር ተኮር የሆነ ፓርቲ ከእኛ ጋር ሲዋሀድ ብሔራዊ ቅርፅ መያዝ አለበት፡፡ አለበለዚያ ብሔር ተኮርና ኅብረ ብሔር ሊዋሀዱ አይችሉም፡፡ ምንድነው ጠቃሚው ነገር? ዲሞክራሲ እስከሆነ ድረስ ለምሳሌ የእኛ ፕሮግራም የግለሰብንም የቡድንንም መብት ያከብራል፡፡ የብሔረሰብ ጉዳይ ከሆነ የቡድን ጉዳይ ነው፡፡ ያ እስከተጠበቀ ድረስ ማንኛውም የብሔር ፓርቲ እኛን ይቀላቀላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ያ ነው ጠቃሚው ነገር፡፡ የፕሮግራሙ ዕይታ ብሔር ተኮር የሆኑትን ፓርቲዎች ፍላጐት ማሟላት አለበት፡፡ የብሔረሰቡ ቋንቋ፣ የብሔረሰቡ የመወሰን መብትና ባህል ማሟላት አለብን፡፡ ይኼ የኢትዮጵያ ነፀብራቅ ነው፡፡ አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች የምንልበት ጉዳይ አይደለም፡፡ እኩልነት እስካለ ድረስ የብሔረሰብ ጉዳይ አይነሳም ባይ ነኝ፡፡ ፍትሕ፣ እኩልነት፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እስካሉ ድረስ ችግር ያለ አይመስለኝም፡፡
ሪፖርተር፡- አንድነት አሳካዋለሁ ወይም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አመጣዋለሁ የሚለው የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ምንድነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- የእኛ ሊበራል ዲሞክራሲ ነው፡፡ ሊበራል ዲሞክራሲ ሆኖ የቡድንና የግለሰብ መብትን አንድ ላይ እናከብራለን፡፡
ሪፖርተር፡- በሊበራል ዲሞክራሲ የቡድንም የግልም መብት ይከበራል ብለዋል፡፡ ነገር ግን የፍላጐት መጋጨት አይኖርም? በቡድን መብትና በግለሰቦች መብት መካከል ማለት ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ነው የሚወሰነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ስንት ሰዎች ናቸው እንደዚህ የሚሉት? ሊኖርም ይችላል፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ አሥር ሰዎች ሁለቱን አባረው ማካሄድ አይችሉም የሚል ይኖራል፡፡ 90 በመቶ ከደገፈው የ90 በመቶ ይሆናል ለሚለው የዲሞክራሲ ውሳኔ ነው የሚጠይቀው፡፡ እኛም ተወያይተንበታልና የሚወሰነው በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄድ አገር አቀፍ ምርጫ አለ፡፡ አንድነት እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በምርጫው ለመሳተፍና ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ምን ምን ሥራዎችን እየሠራ ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- አንደኛ የራሳችንን አቅም እየገነባን ነው፡፡ ከጠቅላላ ጉባዔያችን ዕይታ አግኝተናል፡፡ በዚያ ዕይታ ለምሳሌ የውህደቱ አንዱ ዓላማ በምርጫ የማሸነፍ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድነት ብቻውን ከሚሮጥ ሦስትና አራት ፓርቲ ሆነን ልክ እንደ ቅንጅት ብንሮጥ የተሻለ ውጤት እናገኛለን በማለት፣ በውህደቱ ለምርጫው አንድ የጐለበተ አቅም ለመፍጠር የምናደርገው ስትራቴጂ ነው፡፡ ሁለተኛው ፕሮግራማችንንና ርዕዮተ ዓለማችንን ልክ እንደ ሚሊዮኖች ንቅናቄ ወደታች እናወርደዋለን፡፡ አንድ የሕዝብን ዕይታ የሚስብ ከምርጫ 2007 ጋር የሚገናኝ ፕሮግራም እናወጣለን፡፡ ሕዝብን ለማንቀሳቀስ ከዚህ በተጨማሪ አንድነት የዲሞክራሲ ምርጫ ፓርቲ ነው፡፡ ለማንኛውም ሁልጊዜ ለምርጫ ይዘጋጃል፡፡ አሁን ስትራቴጂያችንን ከልሰን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር አማራጭ ፖሊሲዎችን እንቀርፃለን፡፡ ከአማራጭ ፖሊሲዎች በመነሳት የምርጫ ማኒፌስቶ እናዘጋጃለን፡፡ በእኔ ዕይታ እስከ ሰኔ ድረስ ካለፈም እስከ ነሐሴ ድረስ አንዱና ትልቁ ሥራችን ይህንን የምርጫ ፖሊሲና ማኒፌስቶ ማዘጋጀት ነው፡፡ ከዚያ ብቁ የሆኑ ዕጩዎችን ከካቢኔያችን ውስጥ እንመለምላለን፡፡ ከየቦታው ብቁ የሆኑ ታዛቢዎችንም እንመርጣለን፡፡ ይህ ሒደት ነው፡፡ ሕዝባዊ ስብሰባ እናካሂዳለን፡፡ እንደዚሁም ሕዝባዊ ንቅናቄ ይኖረናል፡፡ እየሄድን ራሳችንን ወደ ሕዝብ የምናወርድበት፡፡ ይህን ሁሉ ለማድረግ ግን የምርጫ ፓርቲ ብንሆንም ምርጫ ውስጥ ጥልቅ ብለን አንገባም፡፡ ሜዳው ለሁላችን እኩል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ስለዚህ ከላይ እንዳልኩት ለዚህ ነው ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) ከገዥው ፓርቲ ጋር የምናደርገው፡፡ ይኼ ሜዳ ለሁላችንም እኩል እንዲሆን ነው የምንፈልገው፡፡ ኢትዮጵያ የጋራችን ነች፡፡ ኢሕአዴግ አንድ ፓርቲ ነው፡፡ እኛም አንድ ፓርቲ ነን፡፡
የምርጫው ሕግ በሕገ መንግሥቱና በምርጫ ቦርድ ሕግ መሠረት መካሄድ ስላለበት ያንን እንጠይቃለን፡፡ ምርጫ ቦርድ የኢሕአዴግ ከሆነ፣ ሚዲያው የኢሕአዴግ ከሆነ፣ የፍትሕ አካላቱ የኢሕአዴግ ከሆኑ እኛ ያን ጊዜ የምንወስነው ውሳኔ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከትዝብትም ጭምር እስካሁን ያሉት ተቋማት ለእኔ ዲሞክራሲያዊ አልነበሩም፡፡ የ2002 ምርጫ በጣም ያዘንኩበት ምርጫ ነበር፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን 99.6 በመቶ የሚያገኝ ፓርቲ የለም፡፡ በዓለም ላይ ዲሞክራሲያዊ በሆነና ውድድሩ በእኩል ሜዳ ላይ ተካሂዶ በእዚህ ውጤት ማሸነፍ አይቻልም፡፡ በዓለም ዙሪያ በአብዛኛው መንግሥት በቅንጅት እየተፈጠረ ነው፡፡ እንግሊዝን ውሰድ የኮንሰርቫቲቭና የሌበር ፓርቲ ቅንጅት ነው፡፡ ጀርመን፣ ጣሊያንና ኖርዌይም እንዲሁ ቅንጅት ነው፡፡ ምክንያቱ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ውድድሩ ነፃ ነው፡፡ እናም ስለዚህ 99.6 በመቶ በጭራሽ ሊሆን አይችልም፡፡ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ያለ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና የኅብረተሰብ ክፍል ባህሪ ባለበት አገር ይኼ አይቻልም፡፡ ይኼ ነገር መለወጥ አለበት፡፡ እናም ለምርጫ እንዘጋጃለን፡፡ ነገር ግን ሜዳው ሁላችንንም እኩል ማስተናገድ አለበት፡፡
ሪፖርተር፡- የመጫወቻ ሜዳው ለሁላችሁም እኩል መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ ትችላላችሁ?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- ለምሳሌ በምርጫ 97 ሚዲያው ትንሽ ወደ ኢሕአዴግም ቢያደላ ተከፍቶ ነበር፡፡ እንዲያውም የእነሱ ሜዳ ከፍ የእኛ ሜዳ ዝቅ ቢልም፣ ነገር ግን የመወዳደርያ ቦታ ነበረው፡፡ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ክርክሮች ለሕዝብ የወጡት በ97 ምርጫ ነበር፡፡ በ2002 ምርጫ ሚዲያው ታፍኖ ነበር፡፡ ሚዲያው የሕዝብ ጥያቄ አላስተናገደም፡፡ ዝም ብሎ ለይስሙላ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተሂዶ አንዳንድ ነገሮች መነጋገራችንን ሕዝብ ሊሰማው ይችላል፡፡ ነገር ግን በሆነ እጅ ቁጥጥር ሥር የወደቀ ነበር፡፡ ያ መሆን የለበትም፡፡ እናም ትልቁ ምሳሌ የ97 ምርጫ የሚዲያ ጉዳይ ነበር፡፡ ሚዲያው ያን ጊዜ ተከፍቶ ነበር፡፡ በእኩልነትም ባይካሄድም ያን ጊዜ እንደ እኩል ነው የወሰድነው፡፡ እንደዚያ መሆን አለበት፡፡
ሪፖርተር፡- ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ አንድነት የፀረ ሽብር ሕጉ ይሰረዝ የሚል አቋም ይዞ እየተከራከረ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በመላው ዓለም ሽብርተኝነት ትልቅ ሥጋት ሆኗል፡፡ በእኛ አገር የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አጠቃቀም ተቃዋሚዎችን ፀጥ ለማሰኘት ነው የሚለው እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት እንደ ፓርቲ አማራጭ የፀረ ሽብር ሕግ አለው ወይ ይሰረዝ ሲል ምን ማለት ነው?
ኢንጂነር ግዛቸው፡- መጀመርያ ሽብርተኝነትን መዋጋት የኢሕአዴግ ብቻ አይደለም፡፡ የማንኛውም ዜጋ ነው መሆን ያለበት፡፡ ይኼ ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴው አስከፊ፣ ከሰው ልጅ ባህሪ በተለየ የሰው ልጅን መንፈስ የሚሰብር፣ የሰው ልጅነትን የሚቀንስ ነው፡፡ አንድነትም ሆነ እኔ እንደ አንድነት አመራር እንደዚሁም እንደ ዜጋም እንዋጋለን&#496

በአሁኑ ወቅት 30 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀውና በሦስት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ፣ ‹‹ቴክኒካዊ›› በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ድርድሮች እየተደረጉ ነው፡፡

በእያንዳንዱ ድርድር ከሚስተዋሉ አቋሞች ግን ለዘመናት የቆዩ ሴራዎች መልካቸውን ቀይረው እየመጡ ይመስላል፡፡

በታላቁ የዓባይ ግድብ ላይ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ጥናት ውጤት የያዘው ሪፖርት አሁን እየተደረጉ ላሉት ድርድሮች መሠረት የሚጥል ነው፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው፣ የግድቡ ግንባታ እንዲቋረጥ ምንም መሠረታዊ ምክንያት ባለመኖሩ፣ በተቻለ መጠን በታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አገሮች ላይ ሊያስከትለው የሚችለው የውኃ ፍሰት መጠን መቀነስና ቴክኒካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሦስቱም አገሮች ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በጋራ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው ነው፡፡ በተረፈ የግድቡ ግንባታ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ሪፖርቱ አጽንኦት ይሰጣል፡፡

የግብፅ ዥንጉርጉር አቋሞች

ኢትዮጵያና ሱዳን ሪፖርቱን በፀጋ የተቀበሉት በመሆናቸው ሚስጥርነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይም የሚቻላቸውን ጥረት አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ግብፅ በሪፖርቱ ላይ የተዘበራረቀ አቋም እያንፀባረቀች በመሆንዋ ሪፖርቱ ይፋ በሆነበት ወቅት በተጠራው ብሔራዊ ምክክር፣ በተለይ የግብፅ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ ጦር ኃይሉ እንዲዘምት ድምፃቸው ተሰምቷል፡፡ ግብፅ ባጋጠማት ቀውስ ምክንያት እየተደረጉ ያሉት የባለሥልጣናት መቀያየር የግብፅ መንግሥት አቋም ለትንተና የማይመች ቢሆንም፣ አንዱ የሌላውን ስህተት እየደገመ ይመስላል፡፡ አንዱ ከሌላው ስህተት እየተማረ አይመስልም፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የሽግግር መንግሥት ከአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታ ጊዜ በኋላ የተባረረውን የፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ መንግሥት በኢትዮጵያና በዓባይ ግድብ ላይ የተለሳለሰ አቋም መያዙ ለውድቀቱ ምክንያት መሆኑን እየተናገረ ነው፡፡

ሁለተኛ ከላይ ከተጠቀሰው ምክንያት ጋር ተያያዥነት ያለው ቢሆንም፣ ግብፅ በአንድ በኩል የባለሙያዎቹ ሪፖርትን አለመቀበልዋና በሌላ በኩል የቡድኑን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር ድርድር እንዲደረግ መስማማቷ እርስ በርስ የሚጣረሱ አካሄዶች ናቸው፡፡

ሦስተኛ ሪፖርቱን በተመለከተ በሚስጥር ተይዞ መቀመጥ በነበረበት ጊዜ አንዳንድ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ ተብለው ለሚገመቱ አገሮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተላልፎ እንዲሰጥ ማድረጓ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ዋሽንግተን ፖስትን ጨምሮ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሪፖርቱን ድምዳሜ በተሳሳተ መንገድ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህ እንግዲህ በአገር ውስጥ የሚደረገውን አሉታዊ የሚዲያ ቅስቀሳን ጨምሮ ማለት ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ ግብፅ የሪፖርቱን ውጤት መቀበሏን በግልጽ ባታሳውቅም፣ የባለሙያዎች የቡድንን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር በቅርቡ ያለውጤት የተበተነውን ጨምሮ ሦስት ጊዜ ድርድር ተቀምጣ ነበር፡፡

ከኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግና ይህንን ተግባራዊ የሚያደርግ ኮሚቴ ለማቋቋም በሁለቱም የመጀመርያ ድርድሮች ግብፅ ተስማምታ ነበር፡፡

በኮሚቴው አወቃቀር ላይ አንዳንድ ውዝግቦች የነበሩ ቢሆንም፣ በመጨረሻ በኮሚቴው ውስጥ ሦስቱን አገሮች የሚወክሉ ዜጐች ብቻ እንዲካተቱ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ ይህ የኢትዮጵያ አቋም ነበር፡፡ ኮሚቴውም ምክረ ሐሳቡን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የውጭ አማካሪ ድርጅትን የመቅጠርን ሥራ ጨምሮ አማካሪው የሚያቀርበውን ሐሳብ ይገመግማል ይላል፡፡

ባለፈው ሳምንት በካርቱም በተደረገው ሦስተኛው የድርድር ዙር ግን የግብፅ ተወካዮች ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት እንዲቀጠር ይጠይቃሉ፡፡ የውኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ግብፆች እንዲቀጠር የፈለጉት የውጭ አማካሪ ድርጅት ቀደም ሲል ስምምነት ከተደረሰበት መንፈስ ውጪ የሚቋቋመውን ኮሚቴ በበላይነት የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዲኖረው የሚል ድብቅ አጀንዳ የያዘ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ድርድሩ ያለውጤት ሲበተን በቀጣይነት ግን ለመነጋገር ቀጣሮ ተይዟል፡፡

የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባል የሆኑት በዓባይ ወንዝ ፖለቲካ ላይ ግንባር ቀደሙ ተመራማሪው ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በግብፅ የቀረበው የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን እንዲመሠረት ብትቀበልም በሁለት ነገሮች አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡ አንደኛው የባለሙያዎቹ ቡድን በሦስቱ አገሮች የጋራ መግባባት (ሙሉ በሙሉ) መመሥረት አለበት የሚል የኢትዮጵያ አቋምን ግብፅ መቀበል አለመቻሏ ነው፡፡

ሁለተኛው የባለሙያዎቹ ቡድን የሚመሠረተው ከሦስቱም አገሮች የተውጣጡ አባላትን ያቀፈው የምክረ ሐሳቡን አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለሙያዎች ቀጥሮ ሥራውን ሲያስፈጽም ድንገት አለመግባባት ከተፈጠረ እንጂ፣ አሁን የሚመሠረትበት አመክንዮ የለም የሚለው የኢትዮጵያ አቋም ነው፡፡

ሌላው ስብሰባው ያለ ውጤት እንዲበተን ምክንያት የሆነው ሦስቱም አገሮች የጋራ መግባባት እንዲኖራቸው ግብፆች ሰባት መርሆች ይዘው መቅረባቸው ነበር፡፡ የመግባባት ሰነድ መፈራረም የዚሁ ስብሰባ አጀንዳ ካለመሆኑም ባሻገር፣ ቀደም ሲል በተለይ የውኃ አጠቃላይ የስምምነት ማዕቀፍ ላይ ሲፈራረሙ፣ ከአሥር ዓመት በላይ ከቆዩ በኋላ አሁን እንዲህ ዓይነት አጀንዳ ላይ መነጋገር ዋናውን ጉዳይ ወደ ጐን ለመግፋት ያለመ በመሆኑ ኢትዮጵያ ያልተቀበለች ምክንያት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ እንደ ዶ/ር ያዕቆብ እምነት፣ ጥያቄው ሒደቱን ወደ ኋላ የሚመልስ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የተደረገውን የሚቃረን መርህ ነው፡፡

ዴይሊ ኒውስ የተባለ ጋዜጣን ጨምሮ አብዛኞቹ የግብፅ ሚዲያዎች ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ዋቢ አድርገው የዘገቡት ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ ‹‹ከሦስቱም አገሮች የተውጣጣ አንድ ኮሚቴ እንዲቋቋም ግብፅ ያቀረበችው ሐሳብ በኢትዮጵያ ተቀባይነት አላገኘም፤›› በሚል፡፡

ምን ማለት ነው?

ዓለም አቀፍ የውኃ ኤክስፐርቶች ያሉበት ቡድን ግድቡን አጥንቶ ሪፖርቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ ያቀረበውን የምክረ ሐሳብ ለመተግበር ተደጋጋሚ ድርድር እየተደረገ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ድርድሩ እንከን እያጋጠመው ይመስላል፡፡

ዶ/ር ያዕቆብ፣ ‹‹ወደፊት ድርድሩ ምን የሚሆን ይመስልዎታል?›› በማለት ከሪፖርተር ለቀረብላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹አሁን እየተሠራ ያለው ሥራ በባለሙያዎች ደረጃ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት እንዲደረግ ነው፡፡ በቁጥር ተለክቶ ተወስኖ የሚገለጽ ነገር ነው፡፡ ግብፆች ያንን ነገር መቀበል አይፈልጉም፤›› ብለዋል፡፡

እንደተደራዳሪም እንደ የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪም የጀመሩትን ምላሽ በመቀጠል፣ ‹‹በቴክኒክ ደረጃ ያለውን ነገር ወደ ላይ ወደ መሪዎች ግብፆች ተመልሶ እንዲሄድና ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ እስካሁን የተሠራውንና የተለፋበትን መና የሚያስቀር ነው፡፡ እንዳልተሠራ ሆኖ ወደ ኋላ የሚመለስ ከመሆኑም በላይ፣ በዚያውም ግብፆች የፖለቲካ ውዝግቡን ለሚዲያ ቀልብና ትችት ይዳርጋሉ፤›› ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል እያንዳንዷ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ የምትታይ መሆኗን፣ ድርድሩ በዝርዝርና በቴክኒክ አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ እንጂ ወደ ፖለቲካ ተመልሶ የሚሄድበት መንገድ በሩ ዝግ ነው ብለዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህርና በዓባይ ውኃ ውዝግብ ላይ ጥናት ያካሄዱት አቶ ዘሪሁን አበበ በበኩላቸው፣ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ተደራዳሪውን ዶ/ር ያዕቆብ ሐሳብ ይደግፋሉ፡፡ ‹‹በግብፅ በኩል ለማድረግ የሚፈለገው አንድና አንድ ነው፡፡ የግድቡ ሥራ እንዲቋረጥ ወይም በጣም ትንሽ ሆኖ እንዲገነባ ነው፡፡ ያ እስካልተሳካላቸው ድረስ ጉዳዩ ሁሌም ፖለቲካዊ መልክ ይዞ በሚዲያ እንዲራገብና ኢትዮጵያን ለማስተቸት ይፈልጋሉ፤›› ብለዋል፡፡ ዞሮ ዞሮ ፍላጐታቸው ቀደም ሲል በብቸኝነት የተፈረመውን እ.ኤ.አ. የ1959 ‹‹ውል›› ማሽከርከር እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ እንደ አቶ ዘሪሁን ገለጻ፣ ግብፆች በአንድ በኩል የተፋሰሱን አገሮች የውኃ ትብብር ማዕቀፉን በጀርባ እየመጡበት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የያዘው መንገድ እንዳለ ሆኖ፣ በዓባይ ተፋሰስ አገሮች ሥራ ላይ የዋለውንና ሕግ ሆኖ የፀደቀውን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በፈራሚ አገሮች ፓርላማ እንዳይፀድቅ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

የተመናመነው የመደራደር አቅም

በዓባይ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች በሦስት አገሮች መካከል ብቻ የሚደረጉ የሦስትዮሽ ድርድር ሆነዋል፡፡ ቀደም ሲል በግድቡ መገንባት ተቃውሞ ቢጤ አሰምታ የነበረችው ሱዳን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አቋሟን ለመከለስ ተገዳለች፡፡ በመሆኑም አሁን በጉዳዩ ላይ በሚደረጉ ድርድሮች ጐልተው እየወጡ ያሉት ጫፍ የረገጡ ውዝግቦች በሁለቱ አገሮች ማለትም በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ሆነዋል፡፡ ይኼውም ከ80 በመቶ በላይ የዓባይን ውኃ ጥቅም ላይ በምታውለው ግብፅና ለዓባይ ውኃ 86 በመቶ አስተዋጽኦ በምታደርገው ኢትዮጵያ መካከል ነው፡፡ ውዝግቡ በተለያዩ መንገዶች የሚገለጽ ሲሆን፣ የሱዳን አቋም መለወጥ የግብፅን የመደራደር አቅም እየተመናመነ እንዲመጣ ምክንያት መሆኑን አንድ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸው እንዲገለጽ የማይፈልጉ የውኃ ዲፕሎማሲ ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የግብፅ የመደራደር አቅም የተመናመነው ግብፅ ውስጥ ባለው ቀውስ ምክንያት ብቻም አይደለም፡፡ እንዲያውም ሚዲያዎቻቸው ከሚዘግቡት ማስተዋል እንደሚቻለው፣ የግብፅ ፖለቲከኞች አገራቸው ከገባችበት ቀውስ መውጣት የምትችለው አንድ ትልቅ ውጫዊ የሆነ አጀንዳ በመፍጠር መሆኑን የተስማሙ ይመስላሉ፡፡ እሱም የዓባይን ጉዳይ በማቀንቀን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የተባለችውን ‹‹ነባር ጠላት›› ማስቀደምና የውስጥ ጉዳያቸው በድርድር እንዲቆይ ማድረግ ነው፡፡ እንደ ዲፕሎማቱ እምነት ሱዳን በግድቡ ላይ የነበራት አቋም ሲለወጥ በግብፅ ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ነበር የፈጠረው፡፡

የዓባይን ግድብ በተመለከተ የሱዳን አቋም መለወጥ ብቻ ሳይሆን፣ የግድቡን ተፅዕኖ ያጠኑት የውኃ ባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት የግብፅ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩትን ሴራ አክሽፎባቸዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ግብፆች በኢትዮጵያ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያደርጉት ጉትጐታ ተቀባይነት እንዳይኖረው አድርጐታል፡፡ በተቃራኒው የኢትዮጵያን አቋም በይፋ ሙሉ ለሙሉ ተሰሚነት አገኘ ባይባልም፣ አንዳንድ ትልልቅ መገናኛ ብዙኃን ሚዛኑን በጠበቀ አኳኋን መዘገብ ጀምረዋል፡፡ አሁን ቴክኒካዊ የሆነ ድርድር ወደ ፖለቲካ ደረጃ ከፍ ብሎ ውዝግብ እንዲፈጥር የሚፈለግበት ምክንያት ይኸው ነው፡፡

ቀደም ሲል ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን የማዳከም ስትራቴጂ የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግሥት ግድቡን ሙሉ ለሙሉ በራሱ ወጪ ለመገንባት ነበር ያቀደው፡፡ በመሆኑም በፕሮጀክቱ ተፈጥሮም ሆነ ፕሮጀክቱን በተመለከተ የወጣው ዓለም አቀፍ ሪፖርት ግብፅ በውጭው ዓለም ልታሳርፍ የነበረውን ተፅዕኖ በእጅጉ ቀንሶታል፡፡

‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ፣ በቅርቡ ለግብፅ የውጭ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ እንዳትውል ትሰጋ የነበረችው ሱዳን አቋም መለወጥ ብዙ ነገሮችን በግብፆች ላይ ያወሳሰባቸው ይመስላል፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ነገሮች ማስታወስ ግድ ይላል፡፡

አንደኛው ከሁለት ዓመት በፊት የአሜሪካ አንድ የደኅንነት ድርጅት (Stratford) እና ዊኪሊክስ ይፋ እንዳደረጉት፣ ግብፅንና ሱዳን ኢትዮጵያንና ታላቁን ግድብ ለማጥቃት ሐሳብ ነበራቸው ተብሎ ነበር፡፡

ሁለተኛው ሱዳን ሥጋት በሚፈጥረው የሁለቱ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ ትሳተፋለች የሚል ግምት ያልነበረ ቢሆንም፣ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማጥቃት የቅርብ ጐረቤት የሆነችው የሱዳንን ግዛት እንደ መንደርደርያ ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ግምት ነበር፡፡

ግብፅ የዓባይን ውኃ በብቸኝነት ለመጠቀም ታዋቂና በአብዛኛው የውኃው ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጵያ ውጪ የተደረጉት እ.ኤ.አ. የ1929ና የ1959 አሮጌ ስምምነቶች በአዲሱ ሁለገብ የውኃ አጠቃቀም ማዕቀፍ (CFA) በስድስት አገሮች ፈራሚነት መተካታቸውና ሕግ ሆነው መፅደቃቸው ይታወሳል፡፡

ሪፖርተር