የወያኔ የሃሰት ይቅርታ እስር አፈና እና ግድያን በኦሮሚያ መውለዱን ቀጥሏል::

Minilik Salsawi's photo.

የወያኔ የሃሰት ይቅርታ እስር አፈና እና ግድያን በኦሮሚያ መውለዱን ቀጥሏል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Wellega‬ ‪#‎Arsi‬ ‪#‎Harerge‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የፌዴራል ፖሊስን የለበሱ የወያኔ አግኣዚ ወታደሮች እና ቅጥረኞች በአርሲ ወለጋ እና ሃረርጌ በሰላማዊው ሕዝብ ላይ የግድያ የእስር እና አፈና ተግባራቸውን መፈጸም መቀጠላቸው ሲታወቅ ሕዝቡም በደል በቃኝ ግድያ ይቁም ወታደሮች ይውጡልን ሲል ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል::

Minilik Salsawi's photo.

በዛሬው እለት በወለጋ ነቀምት ከኒው ጄኔሬሽን ዩንቨርስቲ ስድስት ወንዶች እና አንዲት ሴት ተማሪዎች በፖሊሶች ከዩንቨርስቲው ታፍነው መወሰዳቸው ታውቋል::የወያኔው አሻንጉሊት ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጊዜ መግዣ እና ለማደናገሪያ ይቅርታ የሚለውን ቃል ከተናገረ በኋላ ግድያው አፈናው እስሩ እና ድብደባው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆችን በጥይት ማቁሰል በሕወሓት አግኣዚ ወታደሮች ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ሰላማዊውን ሕዝብ መውጫ መግቢያ አሳጥተውታል::ይህ በፎቶ ላይ የምትመለከቱት በአርሲ የሙኒሳ ወረዳ ነዋሪ ታዳጊ ሃጂ ብዙነህ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በአግኣዚ ጥይት ቆስሎ በአሰላ ሆስፒታል በመታከም ላይ ይገኛል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

5 Comments on “የወያኔ የሃሰት ይቅርታ እስር አፈና እና ግድያን በኦሮሚያ መውለዱን ቀጥሏል::”

  1. ዝባዝንኬ ሳታበዛ ወያኔ ስልጣኑን በሰለጠነና በሰላም ማስተላለፍ ይሻልሃል።
    አልቻልክበትም። ፳፬ ዓመት ሙሉ ተሞከርክ ይህም የኛ ህዝብ ሆኖ እንጅ ሌላ ማን ይሰጥህ ነበር። በዚህ ሁሉ ጊዜ አንዴ ያፈጻጸም ችግር ነው፣ ሌላ ግዜ ጸረ ስላም ወዘተ ኃይሎች ናቸው እያልክ ሰንካላ ምክንያቶችን እያቀረብክ እዚህ ደረስክ።
    ፳፬ ዓመት እኮ አንድ ልጅ ተወልዶ ያደገበት ግዜ ነው። በዚህ ወቅት የተወልዱ ልጆች እንኳን ምን እያሉህ እንደሆነ ልብ ብለህ አስተውል፣ ሌላውን ያረጀ ናፋቂ ምናምን እያልክ ለማንቋሸሽ ብትሞክር ማለቴ ነው።
    በክብር መውረድ ምን ነውር አለው።

  2. ብሄራዊ እርቅ ወታደራዊ ብሄር ተኮር ሳይሆን ህዝባዊ መንግሥትን መመሥረት የኢትዬጵያ ህዝብ ውሳኔ ነው በወታደራዊ መንግሥት ሥልጣን ያለ መንግሥት ህዝብን ሳይፈጅ እንዲሁ አይወርድም እና ሌጣችንን ከምንገረፍ እኛም ህዝቡም ይታጠቅ በሰላማዊ መንገድ ጥረቶች እየገደበ ያለን መንግሥት መወገድ ይኖርበታል።

  3. ኦርቶዶክስ ሳይጠፋ ውሸት አይጠፋም።
    ሃ/ማርያም ይቅርታ የጠየቀው በድምፃችን ይሰማ አስገዳጅነት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*