Image

ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በእያንዳንዱ የሕወሓት የልደት በዓል ማለትም የካቲት 11 በዋነኝነት ከሚከበርበት የትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ተገኝተው በሚያደርጉት ንግግር በዓሉን ሁሌም ድምቀት ይሰጡት ነበር፡፡

ሥልጣን ላይ ያለው ኢሕአዴግ ዋነኛ መሥራች የሆነውን ሕወሓት የረጅም ጊዜ ጠንካራ ሊቀመንበሩን ያጣው ባለፈው ዓመት በዓሉን ከማክበሩ ስድስት ወራት በፊት ነበር፡፡

አቶ መለስ ለመጀመርያ ጊዜ ያልተገኙበት 38ኛው በዓል ግን እሳቸውን በመዘከር በሐዘን ድባብ ነበር ያለፈው፡፡ ተተኪያቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም በወቅቱ በበዓሉ ላይ ቢገኙም፣ በአቶ መለስ መሪነት እዚህ ደርሷል ያሉት ሥርዓት ከፍተኛውን መስዋዕትነት ከፍሎበታል ካሉት ከትግራይ ሕዝብ ጋር እጅና ጓንት በመሆን እንደሚሠሩ፣ ‹‹የማፅናኛ›› ንግግር አድርገው ነበር የተመለሱት፡፡

ዘንድሮ የተከበረው 39ኛው የሕወሓት በዓል ግን ባለፈው ዓመት በሐዘን ድባብ ያለፈውን በዓል ያካካሰ በሚመስል ሁኔታ እጅግ ደማቅ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ላለፉት 22 ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆየው ኢሕአዴግ ዋነኛ አካል የሆነው ሕወሓት፣ በሚቀጥለው አርባኛ የልደት ዓመቱ በበለጠ በደመቀ ሁኔታ ያከብራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የዘንድሮው ግን ከተገመተው በላይ ደማቅ ሆኖ ተከብሯል፡፡

የሕወሓት በዓል እጅግ እንዲደምቅ ምክንያት የሆነው ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለየ የሠራው ነገር ኖሮ አይመስልም፡፡ እንዲያውም ድርጅቱ ጠንካራ መሪውን በሞት ካጣ በኋላ መረጋጋት ተስኖት በውስጥ መከፋፈልና እርስ በርስ በመወነጃጀል ማሳለፉ ይነገራል፡፡ የድርጅቱ ሌሎች አንጋፋ መሪዎችም ያላግባብ ከአመራር መሸኘቱ ከፍተኛ ትችት ያስተናገደበት ዓመት ነበር፡፡ በሌሎች ዓመታት እንደተለመደው የድርጅቱን የትጥቅ ትግል ታሪክ በሚያወሱ ዘጋቢ ፊልሞች፣ የጦር ውሎዎችና ሥልጣን ላይ በቆየባቸው ጊዜያት ያስመዘገበው ልማት በመንግሥት ሚዲያ ታጅቦ ነው በዓሉ የተከበረው፡፡

ይህ ጽሑፍ ዋና ዓላማው የሕወሓትን የልደት በዓል ወይም የድርጅቱን የትጥቅ ትግልና መስዋዕትነት ለመተረክ አይደለም፡፡ የዘንድሮው የድርጅቱ የልደት በዓል እንዲደምቅ ምክንያት የሆነው የተለየ አንድ ውጫዊ የሆነን አጋጣሚ መነሻ በማድረግ አገራዊ አንድምታውን መዳሰስ ነው፡፡

‹‹ሴሲና›› ታሪካዊው አውሮፕላን

ወጣት ተስፋሁን አምባቸው በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ካፌ ውስጥ ሻይ ቡና እያለ በኢቲቪ በቀጥታ ሲተላለፍ የዋለውን የድርጅቱን በዓል ሲመለከት ነበር፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበርም ሆኑ ሌሎች አመራሮች ያደረጓቸው ንግግሮች ምን እንደሚሉ ቀድሞ እንደሚያውቅ ሰው ለመስማት እምብዛም የጓጓ አልነበረም፡፡ የተስፋሁንን ቀልብ መሳብ የጀመረው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር መኖራቸውን ሲመለከት ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የቅርብ ወዳጅ እንደበሩ የሚነገርላቸው ፕሬዚዳንት አል በሽር፣ በዚህ የሕወሓት በዓል መገኘታቸው ብቻ አይደለም የተስፋሁንን ቀልብ የሳበው፡፡

የተስፋሁንና የጓደኞቹ ወሬ የሚያጠነጥነው በሕወሓት የልደት በዓል ላይ አልነበረም፡፡ ፕሬዚዳንት አል በሽር ኢትዮጵያ መጥተው በሕወሓት በዓል ላይ ሲገኙ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡ የግሉ ሚዲያ እምብዛም ትኩረት የሰጠው ባይመስልም፣ የመንግሥትን ሚዲያ ለተከታተሉ አብዛኛዎቹ ሰዎች አነጋጋሪ የሆነው የእነተስፋሁን ጓደኞችንም ቀልብ የሳበው የፕሬዚዳንቱ መገኘት ነው፡፡ የብዙ ኢትዮጵያውያን ዜጐችን ቀልብ የሳበው ግን የፕሬዚዳንቱ መገኘት ብቻ በራሱ አይመስልም፡፡ በግንቦት 1983 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስና አቶ ሥዩም መስፍን፣ አቶ ተፈራ ዋልዋና ሌሎች የሕወሓት ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ድርጅቱ ባካሄደው ጦርነት ደርግን አሸንፎ ወደ አራት ኪሎ ታላቁ ቤተ መንግሥት ሲገባ በአንድ አውሮፕላን ነበር የመጡት፡፡ ከሱዳን ካርቱም ወደ አዲስ አበባ የመጡበት አውሮፕላን አብራሪ የነበሩት ቀድሞ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ጄኔራል አልፋታህ በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል፡፡ በወቅቱ በጉዞ ላይ እያሉ የዚህ ታሪካዊ አውሮፕላን አንደኛው ሞተር ከሥራ ውጪ በመሆኑ፣ አደጋ አፋፍ ላይ ሆነው በወቅቱ ታጋይ ሥዩም መስፍን ከአብራሪውና ከድርጅቱ ሊቀመንበር ታጋይ መለስ ዜናዊ የተለዋወጡዋቸው ‹‹ኑዛዜ›› የሚመስሉ ምልልሶች ነበሩ፡፡ በተለይ አቶ ሥዩም፣ ‹‹ይኼ ሕዝብ ዕድለኛ አይደለም ማለት ነው፣ እኔ ነኝ ጉድ ያደረጉኩህ፡፡ ጓዶች በመኪና እንድንመጣ አስጠንቅቀውን ሳለ በፕሌን እንድንመጣ በማድረጌ አዝናለሁ፤›› ሲሉ፣ ታጋይ መለስ በበኩላቸው በፈገግታ፣ ‹‹አንተ ባስክብንኮ›› ማለታቸውን አቶ ሥዩም አውስተዋል፡፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር የነበሩት አብራሪው ጄኔራል አልፋታህም ከታጋዮች ጋር የቅርብ ወዳጅ የነበሩ በመሆናቸው ትውስታቸውን እንዲህ በማለት ነበር የገለጹት፡፡

‹‹አንድ የማስታውሰው ነገር ቢኖር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ፣ አል በሽርና እኔ ተቀምጠን እየተወያየን ነበር፡፡ ለብዙ ጊዜያት የሕወሓት የትግሉ አካል መሆኔን ተመልክቶ አምባሳደር እንድሆን ሲጠይቀኝ እኔም አምባሳደር ሆንኩኝ፡፡ እኔ የአውሮፕላን አብራሪ ብቻ ሳልሆን ደርግንም የምታገል አካል ነበርኩ፡፡ የዚህ ታላቅ ታሪክ አካል መሆኔ እጅግ ያስደስታል፤›› ነበር ያሉት፡፡

‹‹ሴሲና›› በመባል የሚታወቀውና ከአስፈሪው አደጋ ያመለጠው ይህ ታሪካዊ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ በስጦታ የተበረከተ ሲሆን፣ በመቐለው የሰማዕታት ሙዚየም ውስጥ እንዲቀመጥ ተወስኗል፡፡

የፕሬዚዳንት ሐሰን አል በሽር ንግግርም ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስና ሕወሓት ጋር የነበራቸው የቀረበ ወዳጅነት፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት በተመለከተ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለታዳሚዎቻቸው ከፍ ባለ ድምፀት ያለው ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቡን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጠንሳሽነት የተመሠረተው ድርጅት ራዕይ ተግባራዊ መሆኑን ነበር የተናገሩት፡፡ ‹‹የሰማዕታት ደም ሊካስ የሚችለው ሰማዕታት የወደቁባቸው ተራሮች፣ ሜዳውና ሸንተረሩ በልማት ሲሸፈኑ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የሕወሓት ሊቀመንበር አቶ ዓባይ ወልዱም ንግግር አድርገዋል፡፡

ከጉርብትናም በላይ ወዳጅነት

የፕሬዚዳንት አል በሽርና በኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ጄኔራል አልፋታህ በዚሁ የሕወሓት በዓል መገኘታቸው ትልቅ ቀልብ የሳበበት ምክንያት የሁለቱ አገሮች መልካም ጉርብትና ብቻም አይደለም፡፡

በቅርቡ ኢትዮጵያውያንና ግብፃውያንን እያጨቃጨቀ ያለው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከጉብኝቱ ጀርባ ያለ ይመስላል፡፡ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የተነሳውን አለመግባባት ለመፍታት ሱዳንን ጨምሮ ላለፈው አንድ ዓመት የተካሄደው የሦስትዮሽ ውይይት ትልቅ ሥፍራ የተሰጠው ነበር፡፡ በሦስተኛው ውይይት ሒደቱ ያለውጤት ቢበተንም፣ የግብፅ ታሪካዊ ወዳጅ የሆነችው ሱዳን በድርድር ሒደት ውስጥ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ማዞሯ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስጦታ ነበር፡፡

ቀደም ሲል ግብፅና ሱዳን በዓባይ ላይ የተዋዋሉዋቸው አግላይ ስምምነቶች (1929 እና 1959) የውኃውን ክፍፍል ለሁለቱም አገሮች ማድረጋቸውና ሁሌም የሱዳን አቋም ከግብፅ ጋር የተገናኘ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁለቱም አገሮች ከተፋሰስ አባል አገሮች በስድስቱ የተፈረመውን የአሥር ዓመት የውይይት ውጤት በሆነው የዓባይ ፍትሐዊ የውኃ አጠቃቀም ማዕቀፍ (CFA) በእንቢተኝነት ፀንተው ነበር፡፡ ከዚያም በተጨማሪ አንዳንድ የአሜሪካ የስለላ መረጃዎች እንዳጋለጡት፣ በግብፅና በሱዳን ባለሥልጣናት መካከል በተደረጉ ሚስጥራዊ ግንኙነቶች፣ ግብፅ ግድቡን ለማውደም የሱዳንን ግዛት ለመጠቀም ዕቅድ ነበራት፡፡ የአሁኑ የሱዳን አቋም መለወጥ ግን በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የነበረው የኃይልና የዲፕሎማሲ ሚዛን እንዲቀለበስ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት የግብፅና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አንዳንድ የተካረሩ ቃላት እየተለዋወጡ ሲሆን፣ ከፕሬዚዳንት አል በሽር ጋር በጋራ በመቐለ በሕወሓት በዓል ታዳሚ የነበሩት የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የግብፅን አካሄድ በመቃወም ግልጽ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሊ ካርቲ ለሱዳን ትልቁ ሚዲያ ሱዳን ትሪቢዩን እንደተናገሩት፣ የግብፅ ባለሥልጣናት በሚዲያ እየሰጡዋቸው ያሉት ተንኳሽ መግለጫዎች ሁኔታውን የሚያባብሱ ናቸው፡፡ ‹‹የሱዳን አቋም ግልጽ ነው፡፡ በግብፅ ባለሥልጣናት በቀውሱ ላይ ሱዳን በምትጫወተው አወንታዊ ሚና እንዲጠቀሙ ነግረናቸዋል፡፡ የቀድሞ ገዥዎቻቸው ግትርነት አላሠራ ብሏቸዋል፤›› ብለዋል፡፡ ራሳቸው ፕሬዚዳንት አል በሽርም ቀደም ሲል በግልጽ ቋንቋ የታላቁን ዓባይ ግድብ መገንባት እንደሚደግፉ ተናግረው ነበር፡፡

ሱዳን የአቋም ለውጥ ለምን አደረገች?

የዓባይን ውዝግብ በተመለከተ ቀደም ሲል በሱዳንና በግብፅ መካከል የነበረው ግንኙነት መዳሰስ የዛሬውን ለመገንዘብ ይረዳል፡፡ በተለይ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረሙትን ሁለቱን ስምምነቶች መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1929 በታላቋ ብሪታንያና በግብፅ መካከል የተደረገ ነው፡፡ ለሱዳን የተሰጠ የውኃ መጠን አራት ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ሲሆን፣ የተቀረው 48 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ደግሞ ለግብፅ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት ግብፅ በፈለገችው ጊዜ በወንዙ ላይ ግድብ የመሥራትና የመጠቀም ሥልጣን ያላት በመሆኑ፣ ሱዳን ይህንን ለማድረግ የግብፅን ፈቃድ እንደትጠይቅ ትገደዳለች፡፡

ሁለተኛው ስምምነት፣ እ.ኤ.አ. በ1959 የተፈጸመ ነው፡፡ ይህ በሱዳንና በግብፅ መካከል የተደረገ ስምምነት ነበር፡፡ በቀድሞው የውኃ ስምምነት ያልታወቀ የውኃ መጠን በመገኘቱ በዚህ ስምምነት የሱዳንን ድርሻ ወደ 18.5 መቶኛ ኪዩቢክ ሜትር ከፍ እንዲል የተደረገ ቢሆንም፣ ሱዳኖች ውኃውን የመጠቀም መብታቸው በግብፅ በጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ መረዌ የተባለው ግድብ ከአራት ዓመታት በፊት ተገንብቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በውኃ ለመሙላት እስካሁን ሱዳኖች ፈቃድ አላገኙም፡፡ ሮዜሬስ የተባለውን ግድብ የውኃ መጠኑን ከፍ ለማድረግ ጠይቀውም እስካሁን አልተፈቀደላቸውም፡፡

የውኃው ዋነኛ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያን ጨምሮ የላይኛው ተፋሰስ አገሮችን ያገለሉ እነዚህ ስምምነቶች ውኃውን በግብፅና በሱዳን መካከል የሚከፋፍሉ ቢሆንም፣ ሱዳን በስምምነቱ ተጠቃሚ እንዳልሆነች ትገነዘባለች፡፡ ግብፆች በሱዳኖች ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ዛሬ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ በሚኒስትሮች ደረጃ ሳይቀር እጃቸው ረዘም ያለ እንደነበረ ቢታወቅም፣ በአሁኑ ወቅት ጫናው እየተሸረሸረ መጥቷል፡፡

በመስኖና የውኃ ሚኒስትር የወሰንና የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሱዳኖች በዓባይ ውኃ ጥቅማቸው የሚጠበቅላቸው ከግብፆች ጋር በማበራቸው ሳይሆን ከላይኛው ተፋሰስ አገሮች ጋር በመተባበራው መሆኑን በተግባር ታዝበዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተከዜ ግድብ በመገደቡ ምክንያት ባልተለመደ ሁኔታ በርካታ ገበሬዎች በመስኖ ከፍተኛ ልማት እያከናወኑ መሆናቸው ይነገራል፡፡ ቀደም ሲል በጎርፍ ይጥለቀለቁ እንደነበር፣ አሁን ከዚህ ችግር መገላገላቸውና በደለል ይሞላ የነበረው ወንዛቸው አሁን ከዚህ ችግር ወጥቶ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ሲሰጥ ማየታቸው ለሱዳኖች አቋም መለወጥ ዋና ምክንየት መሆኑን ኃላፊው ይናገራሉ፡፡

ዶ/ር ያሲር መሐመድ በሱዳን የውኃ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ናቸው፡፡ በኔዘርላንድስ ደግሞ የዩኔስኮ የውኃ ትምህርት ተቋም የውኃ ሀብት ተጋባዥ መምህር ናቸው፡፡ ከሦስት ወራት በፊት በመቐለ በተካሄደው አንድ የውኃ ኤክስፖርቶች ቴክኒካዊ ምክክር ላይ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በወቅቱ በአጋጣሚ አግኝተናቸው ስለጉዳዩ አጭር ቆይታ አድርገን ነበር፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የግብፅ ሥጋት ኢትዮጵያ በምትገነባው ግድብ የውኃው መጠን እንዳይቀንስ አይደለም፡፡ የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች በወንዙ ሊለማ የሚችል መሬት ተደምሮ አንድ ላይ የሱዳንን ያህል አይሆንም፡፡ እስካሁን ግን ሱዳን በከፍተኛ ደረጃ የመስኖ ልማት እምብዛም ተጠቃሚ አይደለችም፡፡ የወደፊት ዕቅዷ ግን ይኼንን ውኃ ጥቅም ላይ በማዋል ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችን መሳብ ነው፡፡ እንደሳቸው እምነት፣ ግብፅ የምትጎዳው እዚህ ላይ ነው፡፡ የውኃውም መጠን የሚቀንሰው ሱዳን ውኃውን ለመስኖ መጠቀም የጀመረች ቀን ነው፡፡

ዶ/ር ያሲር መሐመድ እንደሚሉት፣ ግብፆች ግልጽ ባያወጡትም በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳዩት ተቃውሞ በተዘዋዋሪ በዋናነት በሱዳን ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ‹‹የውክልና ጦርነት ነው፡፡ እውነተኛ ችግራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን ከሱዳን ጋር ነው፡፡ ውዝግቡን ግን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሆን ይመርጣሉ፤›› ብለዋል፡፡

የታላቁ የዓባይ ግድብ መገንባትን የሚደግፉት የውኃ ተመራማሪው እንደሚሉት፣ የሱዳን መንግሥት ሰፊ ለም መሬቱን ተጠቅሞ በመስኖ ማልማት የሚችለው ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ግድቦችን ከሠራች ብቻ ነው፡፡ ‹‹ግብፆችም ሱዳኖችም ይህንን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ግን ይህንን የሚገነዘቡ አይመስለኝም፤›› ብለዋል፡፡ እንደ እሳቸው እምነት፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በወንዙ ላይ ስትራቴጂካዊ የሆነ ትብብር ማድረግ አለባቸው፡፡

የሱዳኑ የውኃ ምሁር አስተያየት ማረጋገጫ የሚመስል አንድ መረጃ ተገኝቷል፡፡ የተከዜ ግድብ ከተሠራ በኋላ የደለል መሙላት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን፣ የሱዳኑ አትባራ ወንዝ የውኃ መጠን በአሥር እጥፍ መጨመሩ የሱዳን መንግሥት ይፋ አድርጓል፡፡

ሱዳኖች ያሳዩት የአቋም ለውጥ ከራሳቸው ተጨባጭ ጥቅም በመነሳት መሆኑን ለሪፖርተር የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት በበዓሉ ላይ መገኘት ጥልቅ የሆነ ወዳጅነት መመሥረቱ አመላካች ነው ብለዋል፡፡ ‹‹መምጣታቸውም ለአገራችንና ለሕዝባችን ያላቸውን ጥልቅ ድጋፍና ከበሬታ የሚያሳይ ነው፤›› ይላሉ፡፡ የሁለቱም አገሮች ወዳጅነት ምን ደረጃ እንደደረሰ አመላካች መሆኑን በማስረዳት፡፡

ሱዳንና ኢትዮጵያ ትናንትና

የሱዳንና ኢትዮጵያ ግንኙነት ታሪክ ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የተለየ አይመስልም፡፡ አንዱ የሌላውን አማፂ ቡድን የመደገፍ አዝማሚያዎች ያሳዩ ነበር፡፡ በደርግ ጊዜ ኢትዮጵያ በቅርቡ ነፃነታቸውን ላገኙት የደቡብ ሱዳን ኃይሎች (SPLM) እና በተቀረው የሰሜን ሱዳን አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አማፂዎችን ትደግፍ ነበር፡፡ ሱዳን በበኩሏ፣ አሁን ሥልጣን ላይ ላለው ሕወሓት፣ ለኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅትና በሕወሓት አሸናፊነት ለተበታተነው ለኢዲዩ ከፍተኛ ወታደራዊና የትጥቅ ድጋፍ ታደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የሁለቱም አገሮች ጐርባጣ ግንኙነት የተቀየረው ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ነበር፡፡ ባለፉት ቅርብ ዓመታትከ ኢትዮጵያ ጋር ያላት መልካም ጉርብትና በቀዳሚነት የሚነሳ ነው፡፡ የሱዳን ገዢ ፓርቲ ብሔራዊ እስላማዊ ግንባር (National Islamic Front – NIF) እና የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አል በሽር ከኤርትራ እስላማዊ ኃይሎችና ከኤርትራ መንግሥት በተለይ ደግሞ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያላቸው አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ የሚለው ግንኙነት፣ የኢትዮ ሱዳን ትብብር ዘላቂነትን ሁሌም ጥርጣሬ ላይ የሚጥለው ነበር፡፡

በሁለቱም አገሮች ከፍተኛ የጋራ የድንበር ኮሚሽን አማካይነት በቅርቡ የድንበር መካለል ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግሥት ትችቶችን ባይቀበልም፣ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን እየተሰጠ ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰማ ሰንብቷል፡፡ ያም ሆኖ ግን ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ሁለቱም አገሮች በመልካም ጉርብትና ላይ የተመሠረተ ግንኙነት አላቸው፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ በሁለቱም ሱዳኖች መካከል በተከሰተው የድንበር ጦርነት ዋና ገለልተኛ ሸምጋይ ሆና የተገኘች ሲሆን፣ በተመድ ጥላ ሥርም ቢሆን አቢዬ ላይ ከሠፈረው ሰላም አስከባሪ ኃይል አብዛኞቹ ከኢትዮጵያ የተውጣጡ ወታደሮች ይገኙበታል፡፡

ደቡብ ሱዳኖች ነፃነታቸውን በሕዝበ ውሳኔ ከማግኘታቸው ትንሽ ቀደም ብሎ፣ በዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት የክስ ዋራንት ተቆርጦባቸው የነበረው ፕሬዚዳንት አል በሽር የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ድጋፍ ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ በወቅቱ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነታቸው ከፍ ብሎ የነበረው አቶ መለስ፣ ፕሬዚዳንት አል በሽርን ከዚህ ክስ ነፃ እንዲሆኑ በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ያደረጉት የተሳካ ጥረት ለሱዳን ፕሬዚዳንትና መንግሥት ትልቅ እፎይታ የሰጠ ነበር፡፡

http://www.ethiopianreporter.com/index. … B%E1%8B%AD

ባህር ዳር እና አዲስ አበባ የከተመውን ሕወሓት መራሹ የብአዴን ስብሰባ ውጥረት ነግሶበታል።በቅርቡ ከፍተኛ የብኣዲን አመራሮች የፖለቲካ ጉዳዮች ሰለባ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል::
ምንሊክ ሳልሳዊ:- የአቶ አለምነህ መኮንን ንግግር አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ብኣዴን ለሕወሓት ግን አዳዲስ ታማኝ አሽከሮችን ለመሾም በሩን ወለል አድርጎ ከፍቶላታል::ከአዲስ አበባ እና ከባህር ዳር የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት የብኣዲን አመራሮች የፖለቲካ ጉዳዮች ሰለባ እንደሚሆኑ እና እነሱንም በአዳዲስ የሕወሓት ታማኞች ለመተካት መታሰቡን ተጠቁሟል:: የአቶ አለምነህን መኮንን ንግግርን ተከትሎ እና የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴና ጫና አያይዞ እንዲሁም ስለ ሙስና እና የፖለቲክ መዳከም ያነሳው የብኣዴን ስብሰባ በከፍተኛ መፈራራት እና የራስን መብት እስከመጠራጠር በሚያደርስ መልኩ እንደተካሄደ ተሰምቷል::

ውስጣዊ የፖለቲካ አፈና እንዳለ የጠቆመው ይህ የብኣዴን ስብሰባ እንዲሁም በከፍተኛ ፍራቻ እና ውጥረት የተደረገ ሲሆን የአለመተማመን ስሜቶች የመጠራጠር ሁኔታዎች እንደነበሩበት ከአመራሮቹ የመጣ መረጃ ይጠቁማል::በስፋት ሂስ እና ግለሂስ ይሰጥበታል ቢባልም ከዚህ ቀደም አቶ መላኩ እንዳሉት የሕወሓት ስውር እጆች እንዳይዘረጉ የሚል ፍራቻ በአመራሮቹ መካከል አለመተማመን ነግሶ ታይቷል::በአቶ አለምነህ ንግግር ዙሪያ ሕወሓት የራሱን እርምጃ ካልወሰደ አመራሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ቢናገሩ ሁኔታዎች ተዘናግተው ወደ ሙስና ተለውጠው ወደ ፖለቲካዊ አፈና ስለሚያመሩ መጠንቀቅ ይበጃል የሚሉ የውስጥ አስተያየቶች በግል እንደነበሩ በምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተጠቁሟል::

በአመራሮቹ መካከል ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከታች ካድሬዎች የተሰበሰቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ዙሪያ ውይይት መደረጉን ተጠቁሟል::ከአቶ አለምነህ ንግግር ጀምሮ እስከ የፖለቲካ የበላይነት ….አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተጠይቀዋል:: የድርጅታችን አሰራር ኢዲሞክራሲያዊ ነው በውጪ የሚሰበከው ፕሮፓጋንዳ እና በገህድ የምንየው የተለይየ ነው:: የአቶ አለምነህ ንግግር የኢሕኣዴግ የበላይ ሹማምንቶች ለአማራው ብሄር ያላቸው ጥላቻ ውጤት ነው:: ብኣዼን ከሕወሓት እኩል ታግሏል ማንም ከማንም የነሰ መስዋትነት አልነበረውም ሁሉም ለነጻነት በሚል እኩል መስእዋት ነው የሆነው ቁልፍ የበላይነት ያለው በአንድ ብሄር ስር ነው አማራ ላይ ጫናው በርትቷል የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን አቶ አለምነህ የተናገሩት ንግግርን ተከትሎ በብኣዴን አመራሮች እና ካድሬዎች መካከል ከፍተኛ የጥርስ መነካከስ ብሶበት የታየ ስብሰባ ነበር::ድርጅቱን የማይፈልጉ አባላት ራሳቸውን ሊይሰንብቱ ይችላሉ ሁኔታዎችን በሂደት እንፈታዋለን ሲሉ አቶ በረከት ተደምጠዋል::ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን አስተይየቶች እና ጠንካራ ውይይቶች በቀጣይነት ይካሄዳሉ መፍራቱ እና መጠራጠሩ ለማቆም እንሞክራለን ሲሉ መረጃውን የሰጡ አባላት ተናግረዋል::

ከአቶ አለምነህ ጉዳይ ጎን ለጎን በጥብቅ የቀረበው ጉዳይ እና ምናልባት የብኣዴኝ መኮንኖች አቀረቡት የተባለው ተብሎ የሚጠረጠረው የብኣዴን አባላት በሙሰኞች ላይ የተጀመረውን ዘመቻ ተከትሎ በወታደራዊው ክፍል ፓርቲን እና መንግስትን ደንብን እና ህግን መደበቂያ በማድረግ ከፍተኛ ህገወጥነት እና ሙሰኝነት ይፈጸማል የሚል አቤቱታ ለድርጅታቸው ጥቆማ ቢያቀርቡን ተሰሚነት ሊያገኙ አለመቻላቸው እያበሳጫቸው መሆኑን ገልጸዋል:: የሙስናውን ክፍል በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት የሕወሓት ጄኔራሎች ናቸው ስለዚህ በእነሱ ላይ ምርመራ ሰፋ ያለ ምርመራ ይደረግ የሚሉ ጥቆማዎች አበርትተን ብናቀርብም ምንም አይነት መልስ ልናገኝ አልቻልንም ይልቅ የሕወሓት ስውር እጆች የፖለቲካ ባላንጣዎቻቸውን በማፈን ላይ መሆናቸውን እና በቅርቡም ከፍተኛ የብኣዴን አመራሮች ወደ ፍርድ ቤት በሙሰኝነት ስም እንደሚቀርቡ ተናግረዋል::ይህ በእንዲህ እንዳለም አስቸኳይ ስብሰባ በባህር ዳር ሲጠራ በአዲስ አበባ ደግሞ የብኣዼን (አማራ)የጦር መኮንኖችን የሰበሰበ እና ለመጪው ግምገማ መንገድ ይጠርጋል የሚል ምስጢርዊ ግምገም እንደተካሄደ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::ይህ የአማራ መኮንኖችን ብቻ ለይቶ የሰበሰበው ጉዳይ በብኣዴን ውስጥ የተፈጠረን አጣብቂኝ ያስደነገጣቸው እና የአማራው የጦር መኮንኖች ውስጥዊ ችግሮች እንዳይፈጥሩ ለማስፈራራት እና ሽብር ለመፍጠር እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ ለማድረግ የታቀደ ሴራ ነው ሲሉ መረጃውን ያቀበሉ መኮንኖች ተደምጠውል:: በቡድን በቡድን ተከፋፍለን የምንወያይበት ጉዳይ ይኖራል የተባለ ቢሆንም ስብሰባው እንደጀመረ በአማራው መኮንኖች ላይ ጫና የሚፈጥሩ እና የሚያሸብሩ መልእክቶች ተደምጠዋል:: በተለያዩ ምክንያቶች ሰራዊቱን እንድትለቁ ማድረግ ይቻላል እስከማለት የደረሰ ዛቻ እንደተደሰኮረ ተመልክቷል::የመከላከያ ሰርዊት ውስጥ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝሩን እመለስበታለሁ ::ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ከሳምንታት በፊት ራሱን የአማራ ክልል ብሎ በሚጠራው የክልል አምባገነን ጁንታ አስተዳዳሪ ነኝ የሚለው የብኣዴን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አለምነህ መኮንን በድርጅቱ የውይይት መድረክ ላይ የአማራውን ህዝብ ለሃጫም እና ልጋጋም እንዲሁም መርዝ ብሎ መሳደቡን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ የውጪ እና የውስጥ ተቃውሞ በየአቅጣጫው እየተነሱ መሆኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የደረሱ መረጃዎች ጠቁመዋል::

ሰሞኑን በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቻቸው መካከል ግለሰቡን የተመለከተ አለመግባባት መከሰቱን እና ጥያቄዎች ከአባላቱ በስፋት እየመጡ መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ጠቅሰው የአዲስ አበባ እና አከባቢው የድርጅቱ ካድሬዎች ግለሰቡ እና ሁኔታው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል እስከማለት ደርሰዋል:: ይህንን ለመናገር የፈለገው ለምንድን ነው ተልእኮውስ ምንድነው? በሌላው ብሄር ላይ ይህ ነገር ቢነገር የድርጅታችን እርምጃ ምን ይሆን ነበር? ግለሰቡ በህግ ሊጠየቅ ይገባል::የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተጠየቁ ቢሆንም አመራሮቹ እስካሁን መልስ ከመስጠት ይልቅ ኢዲሞክራሲይዊ በሆነ መንገድ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ በማስፋት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ጸረ-… እያሉ ጠያቄዎችን በመወንጀል እና ዋናውን ክትትላቸው ያደረጉት ድምጹን ቀድቶ ማን አውጣው የሚለውን የማይመለስ ጥያቄ ይዘው አደና ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል::

ከድርጅቱ አንዳንድ ካድሬዎች እንደሚሰማው የድምጹን ቅጂ ያወጡት የሕወሓት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ እና ሕወሓትን በጥርጣሬ የሚይስቡ እንዲሁም ግንቦት ሰባት ናችሁ ብለው እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚፈልጉትን የብኣዴን ካድሬዎች ለመዋጥ የተደረገ ሴራ ነው::በድርጅታችን ውስጥ የማይበጁትን አንጠባጥቦ የራሱን ለመሰግሰግ ያሰረው ሕወሓት መንገድ አገኘ ቢሉም በለላ ወገን ደግሞ በድርጅቱ የተማረሩ እና የለውጥ ፍላጎት ያላቸው የብአደን አመራሮች አሹልከው ያወጡት እንደሆነ ይነገራል።ካድሬዎቹ ክፉና ደጉን እንድንለይ ላደረገን ኢሳት ቴሌቭዥን ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተደምጠዋል:: በአመራሮቹ እና በካድሬዎቹ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በዚሁ ከቀጠለ አቶ አለምነህ የድርጅት ስራ ብቻ እንዲሰሩ ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት እና በክልሉ ላይ የተሰጣቸውን ስልጣን ለስም ብቻ እንዲቀመጥ የሚደረግ እንደሚሆን እና ቀስ በቀስ ከድርጅቱ ገፍቶ በማስወጣት አምባሳደር አድርጎ መሾም የሚሉ አስተያየቶች ከድርጅቱ አከባቢ ተደምጠዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ
=============================================
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የብሄር ተዋፅኦን እና የመኮንኖች ቅነሳን በተመለከተ ከፍተኛ የሆነ ክርክር መነሳቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ ከሆነ በዚህ ሰሞን በተካሄዱ ተከታታይ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ በአንድ ብሄር በተሰበሰቡ ጄኔራሎች የተሞላ ነው: የመኮንኖች ቅነሳ ለምን አስፈለገ? ለምንስ አማራው እና ኦሮሞው ላይ አተኮረ ?ሰራዊቱ እና ቤተሰቡ በኑሮ ውድነት እየዋተተ ነው ከፍተኛ መኮንኖች በሙስና ተዘፍቀዋል ህገመንግስቱ አልተተገበረም የሚሉ የህዝብ አቤቱታዎች ተበራክተዋል … የሚሉ በሰራዊቱ ውስጥ ተጠንቷል ተብለው በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ ክርክር እና ውይይት የተደረጉ ቢሆንም በሕወሓት ጄኔራሎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንዲሁም ሞራልም ያልጠበቁ ስድቦች ካለውጤት እንደተበተኑ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::

የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው ያሉት ጄኔራል ሳሞራ ጥያቄውን የፓርቲ ስብሰባ እስኪመስል ድረስ ጮኽውበታል::በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል::

የሰራዊቱ መኮንኖችን ቅነሳ በተመለከተ የማይታጠፍ እቅድ ስለሆነ ተግብርዊ ይሆናል ያሉት ሳሞራ ብሄር ለይተን ያደረግነው ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና የመከላከያ ሰራዊቱ ተጠንቶ የሚወሰድ ኢርምጃ ነው ብለዋል::ለሰራዊቱ የምናደርገው ድጎማ የለም::ያልተመቸው ካለ ሰራዊቱን መሰናበት ይሽላል ሲሉ በቁጣ የመለሱ ሲሆን ሙስና የሚባለው ማስረጃ ያለው ሄዶ ሊከስ ይሽላል ከዚህ ውጭእ ስም ማጥፋት ነው ሲሉ ተደምጠዋል :;ህገመንግስቱን እና መንግስታዊ ስርኣትን በተመለከተ መልካም አስተዳደር እና ልማት ስለሰፈነ ቢዚህ ልይ ምተኮር ስፈላጊ አይደለም ብለዋል:: ከሰራዊቱ አባልት መሃል ገብተን ያስጠናነው ጥያቄ ነው እየተወይየንበት ያሉትን ሰነድ በተመለከተ ማንም የጦር መኮንን አስተያየት ያልሰጠበት እና ያልጠየቀ ሲሆን ሁሉም በዝምታ በማዳመጥ ሳይወያይ መስማማት አለመስማማቱን ሳይገልጽ የተነገረውን እንደ መመሪያ ተቀብሎት መውጣቱን ምንጮቹ ተናግረዋል:: ምንሊክ ሳልሳዊ

በርሱፈቃድ በጋሻው ተሾመ የተባለው የ24 አመት ወጣት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኘው የህብረት ባንክ በጥበቃ ሰራተኝነት ለአንድ ወር ሲሰራ የቆየ ሲሆን ዛሬ 6 ሰዓት አካባቢ ባንኩ ለጥበቃ በሰጠው ጠመንጃ ሶስት ግዜ በመተኮስ ነው ራሱን ያጠፋው፡፡

Image

ሁዳዴ ፆምን ለመፆም ተዘጋጅተዎል??

ነገ ሠኞ የካቲት አስራ ሠባትቀን ሁለት ሺ ስድስት ዓመተ ምህረት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ዐብይ ፆም ይጀመራል።
ለመፆም ተዘጋጅተዎል?ዘንድሮ ፆም ለነፍስ ብቻ ሣይሆን ለስጋም ጠቃሚ እየሆነ ነውና ሀኪም ቀይ አብርቶ በስጋ ምክንያት ሥጋት ላይ መሆንዎን ሣያረዳዎ በንስሃ አባትዎ ምክር ፆሚ ይሁኑ።
ቢፆሙ ሸንቃጣ ይሆናሉ።ስጋዎ ፈተና ላይ አይወድቅም።መንፈስዎ ይረጋጋል።ባይፆሙ ኪሎዎ ይጨምራል።ከሀኪም ፊት አይርቁም።ቁና ቁና ይተነፍሣሉ።ወጪዎ ይጨምራል።አልጋና ብልግና ሊያዘወትሩ ይችላሉ።
ኪስዎ ከመጀመርያው ፆሚ ከሆነ የኔ ምክር እርስዎን አይመለከትምና ዘና ይበሉ።ፆም ሲፆሙ ሆድዎን ብቻ ማዕቀብ አይጣሉበት። ምላስዎን አደብ አስገዟት።ዓይንዎን ከዳሌና ጭን ላይ ይንቀሉ።ጆሮዎ የአመት ረፍት ያስወጡት።እግርዎ አይንጦልጦል።ያኔ የወጣልዎ ምርጥ ፆሚ ይሆናሉ።አንድ ነገር ረሣሁ።በልብዎ ግርግዳ ያከማቹትን የቂምና የጥላቻ ዶሴ ፈጥነው ይደልዙ።ዲሌት ያርጉት።የቂምና የበቀል ጎሬ የሆነ ልብና ጭንቅላት ይዘው ከአምላክዎ ጋር መገናኘት እንደማይችሉ ይገንዘቡ።ልብዎ በቂም ኔትወርክ ተጨናንቆ ወደ ፈጣሪዎ የሚያደርጉት ማንኛውም ጥሪ አይሠማምና ውዝፍ ሂሣብዎን ያወራርዱ።ያኔ ሁዳዴን ፆም ለመፆም ሚኒማውን ያሟላሉ።
ሃምሣ አምስት ቀናት ወጥረው ቢፆሙ ለስጋዎም ሆነ ለነፍስዎ ርጋታና ዕርካታ ያገኛሉ።ቅበላን ለመሆኑ እንዴት አሣለፉት? ጮማ ቆረጡ? ከጠጇስ ጨለጡ ?ከስጋ ወደ ሽሮ ሊሸጋገሩ የቀረዎ እራት የተባረከ ይሁን።
አክሊለ ሠማያት ዘ መካነ ሠላም

የአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ ኢላማቸዉ አድርገዉ ካወደሟቸዉ ዋና ዋና የአገራቸን ተቋሞች ዉስጥ የመጀመሪያዉ ይሄዉ የአገርና የህዝብ ደጀን የነበረዉ ተቋም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየተባለ የሚጠራዉ ተቋም ለጎጠኞች ጥቅምና የስልጣን መራዘም የቆመ፤ በዘረኝነት የተካፋፈለ፤ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ ሙያዊ ብቃት የሌለዉና የወገንና የአገር ፍቅር እንዳይኖረዉ ተደርጎ የተደራጀ ሰራዊት ነዉ። ይህንን ሠራዊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የወያኔ ሠራዊት እያልን የምንጠራዉም በዚሁ ምክንያት ነዉ።
ዛሬ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ዘረኞች ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የአገር መከላከያ ተቋም የሚታማዉ በዘረኝነት፤ በሙያ ብቃት ማነስና የአንድ ፓርቲ ጥቅም አስከባሪ በመሆኑ ብቻ አይደለም፤ ተቋሙ ከእነዚህ ዋና ዋና ጉድለቶቹ በተጨማሪ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋም ላይ በፍጹም ያልታዩ ሌሎች ትላልቅ ጉድለቶች አሉበት። ከእነዚህ ጉድለቶች ዉስጥ አንዱ የወያኔ የመከላከያ ተቋም ህገ መንግስቱ ከሰጠዉ ኃላፊነት ዉጭ በንግድና በንብረት ይዞታ ላይ ላይ መሰማራቱ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ከዚህ ፀባዩ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ሠራዊት ተቋም ዉስጥ ከላይ እስከታች የሰፈነዉ ቅጥ ያጣ ሙሰኝነት ነዉ። ዛሬ የወያኔን የመከላከያ ተቋም፤ የህወሀትን ፓርቲና ኤፎርት በሚል ምህጻረቃል የሚታወቀዉን የወያኔን የገንዝብ ማምረቻ ድርጅት ነጣጥለን ወይም አንዱን ከሌላዉ ለይተን ማየት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በላፈዉ አመት ወያኔ እራሱ ያቋቋመዉ ፀረ ሙስና ኮሚሺን የገንዘብ ዝርፊያን፤የንብረት መባከንንና መዝረክረክን አስመልክቶ ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከጠቀሳቸዉ መንግስታዊ ተቋሞች ዉስጥ ቀዳሚዉን ደረጃ የያዘዉ የመከላከያ ተቋም ነዉ። ሆኖም ፓርላማዉም ሆነ የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ሪፖርት የሰጡት ምላሽ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞች ከአሁን በኋላ ያሻቸዉን ያክል ገንዝብ ቢዘርፉ የሂሳብ መዝገባቸዉ “ለአገር ደህንነት” ሲባል በኦዲት ኮሚሺን አይመረመርም የሚል ምላሽ ነበር። እንግዲህ ይህ በሙሰኝነት የተጨማለቀ፤ ለህግ የማይገዛና መጠበቅና መንከባከብ የሚገባዉን የአገር ኃብትና ንብረት የሚዘርፍ ተቋም ነዉ ባለፈዉ ሳምንት “የመከላከያ ቀን” ተብሎ አመታዊ በዐል የተከበረለት።
መናገሻ ከተማችን አዲስ አበባ ዉስጥ በየቦታዉ የሚታዩትን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ሰርተዉ የሚያከራዩት የወር ደሞዛቸዉ ከ2500 ብር የማይበልጥ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የተሰገሰጉ የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ኢትዮጵያ ዉስጥ ትርፋማ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ትላልቅ ሆቴሎች፤ የአገልግሎት ተቋሞችና የንግድ ድርጅቶች ከፍተዉ ቁጥር ስፍር የሌለዉ ኃብት የሚያጋብሱት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ ድሃዉና የወያኔ ዘረኝነት ሰለባ የሆነዉ ኢትዮጵያ ሰራዊት ለተመድ ተልዕኮ በተሰማራባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ተመድ የሚከፍለዉን የቀን አበል ኪሳቸዉ ዉስጥ እየከተቱ ሚሊዮነሮች የሆኑትና በየዉጭ አገሩ ዉድ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ተቋሞችን የሚገዙት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ። የወያኔ መከላከያ ተቋም ጉድ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ ይህንን ወንጀለኛ ተቋም ቃላት እየደረደሩ ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ በጥቅሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ኃብትና ንብረት እንዳሻዉ መዝረፍ እንዲችል የኃይል ሽፋን የሚሰጥ ተቋም ነዉ ማለት የሚበቃ ይመስለናል።
ወያኔና ስር የሰደደዉ ዘረኛ ስርዐቱ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እስካልተነቀሉ ድረስ ወያኔ ዝርፊያዉን የወያኔ መከላከያ ተቋምም የወያኔንና የደገፊዎቹን ዝርፊያ በመሳሪያ ማጀቡ አይቆምም። የወያኔን ዝርፊያ ለማስቆምና አገራችንን ከተጋረጠባት አሳሳቢ አደጋ ለመታደግ ብቸኛዉ መንገድ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ ብቻ ነዉ። ግንቦት 7 የፍትህ፤የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረዉ ህዝባዊ ትግል እንደ አገር መከላያከያ አይነቶቹ ቁልፍ የአገር ተቋሞች በሚሰሯቸዉ ስራዎች ሁሉ የአገርንና የህዝብን ጥቅም እንዲያስጠብቁ ለማድረግ ነዉ። የግንቦት 7 ትግል አላማ የመከላከያ፤ የደህንነት፤ የፖሊስና የፍትህ ተቋሞች የአንድ ፓርቲ ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች መሆናቸዉ አብቅቶ የአገርና የህዝብ አለኝታ እንዲሆኑ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ቅዱስ አላማ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ተግባራዊ ማድረግ ስለማይቻል ነፃነት፤ ፍትህ፤ዲሞክራሲ፤ ሠላምና እኩልነት የናፈቀዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ ከሚለዉ የአገር አድን አላማ ጎን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪዉን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ምንሊክ ሳልሳዊ :- የረዳት አብራሪው ወንድም “ወንድሜ የአእምሮ ህመምተኛ ነው::” ብሎ ለመመስከር ወደ ስዊዘርላንድ በወያኔ ወጪ እንደሚሄድ የመረጃ ማረጋገጫዎች የተገኙት በዚሁ ሰሞን ሲሆን ከመሄዱ በፊት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን ከቤተሰቡ የተገኙ መረጃዎች ያሳይሉ::

ቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ እንደሆነ እና የሃይለመድህን አበራ መኖሪያ ቤት ተገልብጦ መፈተሹን ከሱ ጋር ቀረቤታ አላት የተብለችው እህቱ በቁም መታሰሯን የስዊዝ ፖሊስ ለሃይለመድህን የፍርድ ሂደት .. እና የብኣዴን የዲያስፖራ አስተባባሪ እንዲሆን በእጩነት ተመልምሎ በስር ብዛት ምክንያት የተዘነጋው ወንድሙ ዶ/ር እንዳለማው የአሜሪካ ራዲዮ ቃለምልልስ እና በቤተሰብ ውስጥ የተነስው አለመግባባት እንዲሁም ሌሎችን በዚህ ባለፉ ቀናቶች የሰማናቸው የረዳት አብራሪ ሃይለመድህን ጉዳዮች ናቸው::ምንሊክ ሳልሳዊ

ለመንደርደሪያ ያህል ባለፈው ካየነው የውል ጫፉን ለመያዝ ያህል ሃይለመድህን የመንፈስ ጭንቀት ስለተጠናወተው የሚለውን የመንግስት እጅ አለበት የተባለበት እና ቤተሰቡ በችኮላ የአብራሪውን መልካም ስም ያጎደፈበት የተባለለት ጹሁፍ ተከትሎ እህቱ የጻፍኩት ሱሁፍ ተጠልፏል እኔ እንዲህ አላልኩም ያልኩት ሌላ ነው ባለችበት ይህንንም በሌሎች የቤተሰቡ አባላት በተረጋገጠበት ሁኔታ እንዳለ ሆኖ የቤተሰቡ አባላት በራሳቸው ጥንቃቄ ጉድለት ለመንግስት የፖለቲካ ፍጆት ከመዋላቸውም በላይ ተምረው በራስ አለመተማመን እና ጥንካሬያቸውን እንዲያጡ የተደረገበት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ይጠቁማል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ተበራክተዋል::

ረዳት ካፒቴኑ ቤተሰቡ ላይ የሚደርሰው ጫና በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም መስካሪ የማያሻው ጉዳይ ነው:: አዝውንት የሆኑት እናት እና አባቱ ላይ ከሚደርስ ውንጀላ እና እየደወሉ ከማስፈራራት ጀምሮ በሃገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቹን ምንም አይነት መግለጫ እንዳይሰጡ እስከመከልከል እስከመዛት እስከማስፈራራት ተመሳሳይ ወያኔያዊ ሽብሮች ካለማቋረጥ እንደቀጠሉ ነው::

የመንግስት አካላት አለማቀፍ ውርደት እና የፖለቲካ ሽንፈት ያላበሰው የሃይለመድህን ጄኔቭ ላይ መክተም ለሚሰጡት መልስ የጨነቃቸው ወያኔዎች ቤተሰቡ ለፍጆታቸው ለመጠቀም እንደተገደዱ እያየን ነው:: ህይለመድህን የኢኮኖሚ ችግር የሌለበት እና በፈለገው ጉዳይ ከሃገር ወጥቶ መቅረት እንደሚችል የወያኔ አደርባዮች በአንደበታቸው መስክረዋል::የሃይለመድህን በሰላማዊ የእገታ ድርጊቱ የጠየቀው የፖለቲካ ጥገኝነት እንጂ ሌላ አይደለም ለምን ይህንን ሊጠይቅ ቻለ እንዴት ሊያስበው ቻለ ማለት የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ቢሆንም በሁለት የነጻነት እና የአፈና ክልል የሚኖሩ ቤተሰቦቹ ልእሱ ቅርብ ነን ያሉ የተጋጩ ምላሾችን አስቀምጠዋል:: የአጎቱ ልጅ ነኝ ያለንው እና በነጻነት ለመናገር እድሉ ያላት በአሜሪካ የምትኖረው የአጎቱ ልጅ … ሃይለመድህን የሃገሩ ጉዳይ የሚያንገበግበው ጀግና ወንድማችን ነው ስትል …. ለአሜሪካ ራዲኦ የወያኔ ቃላቀባይ ተብሎ በሚታማው ጋዜጠኛ የተጠየቀው የብኣዴን እጩ ምልምል የሆነው የአብራሪው ታላቅ ወንድም ድ/ር እንዳለማው ደሞ ወንዴሜ የፖለቲካ እውቀት ያሌለው የኣእምሮ ጭንቀት የተጠናወተው ሲል ቤተሰባዊ ሞራል ባልጠበቀ መልኩ ሲናገር ወንድሙ የስዊዝን መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁት ይዘንጋው አሊያም የወያኔን የፖለቲካ ፍጆት ያጡዘው ሊያብራራ አልቻለም ::ምንሊክ ሳልሳዊ

የሃይለመድህን አበራ ኢምፔሪያል ሆቴል አከባቢ የሚገኘው መኖሪያው ግኡዝ ቤት እንኳን እስኪደነግጥ የተባለለት የደህንነት ፍተሻ ተደርጎ ንብረቱ በመንግስት ተዘርፎ መወረሱን እያየን ባለንበት ወቅት ቤተሰቡ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ እያየን መንግስት በራሱ ሽብር ስራ ምን ያህል እንደተጋለጠ እና እንደተሸበረ እያወቅን ባለንበት ሰአት በአለም ላይ የሚኖሩ ዲያስፖራዎች ድምጻቸውን በአደባባይ ለማሰማት ከያሉበት እየተጠርሩ መሆናቸው ሌልው ወያኔ ላይ የደረሰ ሽንፈት ነው:: አለማቀፍ የዲያስፖራው ቡድኖች በኢትዮጵያ ያለውን የመብት መጣስ በተመለከተ አትኩሮት እንዲያገኝ የተደረገ ድርጊት ነው ብለው አምነውበት ሃይለመድህን አበራን በነጻ ለማስለቀቅ የራሳቸውን ዘመቻ በመጀመር ጀግና የሚል ስያሜ ሰተውት ስራቸውን በግብረሃይል በተግባር እየሰሩ ነው::

የስዊዝ ፖሊስ የሃይለመድህንን ጤንነት መስክሮ ጠበቃ እንደሚያቆምለት እና የፍርድ ሂደቱም በቅርቡ እንደሚጀምር በገለጸበት በዚህን ወቅት ኢትዮጵያውያን ሃይለመድህን ይለቀቅ !!! ብለው ድምጻቸውን እያሰሙ ባሉበት ሰኣት የወያኔው መንግስት ጨንቆት የሚለው ባጣበት እና በፈጠራ ወንጀል ድራማ ለመስራት በሚኳትንበት በዚህ ጊዜ እውነታውን ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ለመስረዳት የእያንዳንዳችን ጥረት ወሳኝነት እንዳለው እና ለሕዝቦች የመብት ትግል የሚከፈሉ መስዋትነቶች እንዳይዳፈኑ አጥብቀን መታገል ያለብን መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ::ምንሊክ ሳልሳዊ #MinilikSalsawi

የወያኔ መንግስት ሁሉም ዜጋ በህግ ፊት እኩል ነው እያለ ሲፅፍና ሲናገር እንሰማለን፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግ ይህንን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በአመለካከት ከኔ እስካልተለያየህ ድረስ ማለቱ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡

የወያኔ ጁንታ የፍትህና የጸጥታ አካላት ህግን ተመርኩዘው በህገወጥነት እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት የተባሉት የሚወስዱት ህገ-ወጥ እርምጃ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የወያኔን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን “ከወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች” አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡ የፍትህ አካላትም ክስ የሚመሰረቱበትን የግለሰቡን ማንነት አስቀድመው ከወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ዳኞችም እንግዲህ በአንፃሩ ከወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በአመለካከት ያልተለዩ ከሆኑ ወንጀል ቢፈፅምም ተጠርጣሪ ጠያቂ አለበት ማለት ይከብዳል፡፡ የፖለቲካ ታማኝነቱ ሳይታወቅ የተከሰሰ አባል እንኳ በችሎት ላይ እያለም ክሱ እንዲሰረዝለት የሚደረግበት አጋጣሚ አለ፡፡

የህግ የበላይነት ባልተከበረበት ሀገር ስለዴሞክራሲያዊ መብቶች ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡ ሁለቱን ለብቻቸው ነጥሎ ማየት ሁኔታውን ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ዴሞክራሲ እየገነባ እንደሆነ በየቀኑ ከመቶ ጊዜ በላይ ራሱ በሞኖፖል ይዞ በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየነገረን ነው፡፡ በየጊዜው ይህንን ሃሰት እና የውሸት ዲስኩር እየሰማን መሄድ ማለት ሃገርን እና ህዝብን እያላሸቁ መሄድ ስለሆነ እያንዳንዳችን ለዲሞክራሲያዊ መሰረታዊ መብቶች መከበር የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል::

ወያኔ/ኢህኣዴግ የመንግስትን ስልጣን ተቆጣጥሮ መንግስታዊ ሽብርን እያስፋፋ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳቶችን በህዝብ ላይ እያደረሰ መሆኑ የሚታውቅ ሲሆን ህዝቦች አስፈላጊውን የዜግነት መብቶቻቸውን እንዳያገኙ ሞራላቸውን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማሸበር እና በሃይል በመግደል የስልጣን መስፋፋቱን ቀጥሎበታል::የህግ የበላይነት እንዲከበር እና የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መብቶችን ለመጎናጸፍ በጋራ የመታገል የግድ ነው::

ካምፓላ ተለጣፊ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቋቋም ነው።
የወያኔ ቆንስላ በዩጋንዳ ቅዳሜ ህወአት ውብድናና የጀመረበትን ሠላሣ ዘጠነኛ ዓመት ሲያከብር ተለጣፊ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በአምሣሉ ለመፍጠር በፓስፖርት የሚኖሩን ኢትዮጵያዊያን ተጋዳላይ ፍሬወይኒ ዮሐንስ በስልክ እየጠሩ ሲሆን ስደተኛ ነን ባዮቹን ደግሞ አቶ አምሣሉ እንዲገኙ እያባበለ መክረሙን ከውስጥ አዋቂዎች የተገኘው መረጃ ጠቆመ።
ወያኔ ከትግራይ መቀሌ ውጪ መከበር የማይገባውን ቀን ካምፓላ ላይ ማክበሩ የሐገሪቱን ካዝና
እንደፈለገ እንደሚጫወትበትና እስከዛሬ በታሪክ ውንብድና የጀመረበትን ቀን በማክበር ሐፍረት የማይሠማው
ህወአት ብቻ መሆኑን ሐገር ወዳዶች ይናገራሉ።
ስደተኞች ወያኔ ኤንባሲ የሚሄዱበት ምንም አይነት ምክንያት እንደሌላቸው አውቀው ከፈንጂ ወረዳ እንዲርቁ መንገር እንደሚገባና እግራቸውን ለማይሠበስቡ ስደተኞች ግን ለዩጋንዳ መንግስትና ለዩኤንኤችሲአር በማጋለጥ እውነተኛ ስደተኞች ደህንነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው በስልክ ያነጋገርናቸው ወገኖች ከስፍራው ገልፀውልናል።

የአማራውን ህዝብ ለሃጫም ልጋጋም ….. በማለት በመርዛም ሕወሓታዊ ምላሱ መርዝ ብሎ የተሳደበው የብኣደኑ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር የባህር ዳር የተቃዋሚዎችን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ተከትሎ አማራውን አልሰደብኩም የሚል ንግግር ማድረግ መጀመሩ በድርጅቱ ውስጥ የገባውን ድንጋጠ ያመለክታል።

አቶ አለምነው መኮንን የጭንቁ ቀን ሲመጣ “አማራውን አልሰደብኩም” ብሎ በክልሉ መገናኛ ብዙሃን መለፍለፍ መጀመሩን እየሰማን ነው፤ ሰውየው የአንድነትና የመኢአድ የተቃውሞ ሰልፍ 2 ቀናት ብቻ ሲቀሩት ለማስተባበል መሞከሩ የብአዴንን ውጪ ነብስ ግቢ ነብስ ያሳያል ።

የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡

ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ህዝቦች ይልቅ የሚያመሳስሉን፣ የምንጋራቸው በርካታ እሴቶች አሉን፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያውይነታችን (ዜግነታች) የጋራችን ነው፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ ተብሎ በጅምላ ዜግነት ሊሰጠው አይችልም፡፡ አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ለመሆን መደራጀት አይጠበቅበትም፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ‹‹ኦሮሞ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ግለሰብ አማርኛ ተናጋሪዎች ‹‹አማራ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ሶማልኛ ተናጋሪዎን ‹‹ሶማሊ››…….እያሉ ነው ኢትዮጵያውያንን ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› በሚል አዲስ ማምነት የሚደረድሩን፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ የሚባለው ከግለሰቦች እንጅ ከምንም የመጣ አይደለም፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር ካለበት መጀመሪያ መቅደም የሚገባው የስሪታቸው የግለሰቡ መብት ነው፡፡

ኦሮሞ፣ አማራ፣ትግሬ….› እየተባሉ የተቦደኑት ህዝቦች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ እንዲያውም ኦሮምኛ ተናጋሪው ‹‹ኦሮሞ›› ከሚባለው ውጭ ከአማርኛ ተናጋሪው ጋር የሚጋራው በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ አማርኛ ተናጋሪው ‹‹አማራ›› ከተባለው ይልቅ ከኦሮምኛ ተናጋሪው ጋር የሚያመሳስሉት በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ ለአብነት ያህል ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ፣ ….ተናጋሪው ህዝብ ከቋንቋውም በላይ አንዱ የሌላውን ድንበር ተሸግሮ ከሌላኛው ቋንቋ ተናጋሪ ጋር በእምነት፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ገመዶች ይገናኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአንድ ብሄር ሰዎች አይደሉም፡፡ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እንዲህ እስካሁን በጥንካሬ የዘለቀው በድንበር ተሸጋሪው ማንነቱ እንጅ በጠባብ ‹‹የብሄር›› ማንነት ታጥሮ አይደለም፡፡ ኦርቶዶክሶቹ፣ ፕሮቴስታንቶቹ፣ ካቶሊኮቹ በ‹‹ብሄር›› የታጠሩ አይደሉም፡፡

የአንድ ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ…መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ በ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ሶማሊ…….›› ስም በጅምላ ከመነገድ ያለፈ ስለ እያንዳንዱ ህዝብ አያስጨንቀቃቸውም፡፡ 30 ወይንም 40 ሚሊዮን የአንድ ‹‹ብሄር›› ህዝብ በአንድ ጉዳይ ሊከፋ አይችልም፡፡ ቢያንስ ከገዥዎች ጋር ሆኖ የሚጠቀም አይጠፋም፡፡

ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን ግን የሚድበሰበስ ነገር አይኖርም፡፡ ሁሉም የግለሰብ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የአገሪቱ ህዝብ መብት ይከበራል፡፡ የግለሰብ መብት ካልተከበረ ግን የማንም መብት ሊከበር አይችልም፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድን አስተድደራዊ ብልሹነት እና የዘረኝነት አድልዎን ያማከለ የኢትዮጵያን እና የአማራን ጉዳይ ያካተተ አንገብጋቢ አጀንዳዎች ይዞ እንዲሁም በግሉ ከጀርባው አልወርድ ያሉትን የወያነ ቅማሎች ደህንነቱን የሚያበረውን አውሮፕላን በመጥለፍ አሊያም በማገት በሰላም ጀነቭ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን የተመለከቱ ዘገባዎች መውጣታቸውን እንደቀጠሉ ነው።

በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ድጋፍ የተቸውረው ይህንን የጠለፋ /እገታ ጉዳይ በተመለከተ የወያነው መንግስት ለውጥ የሚያደርግበት እና ለፖሊሲዎቹ አፋጣኝ አትኩሮት ሊሰጥ ይገባዋል ከሚሉ የስር አቱ ደጋፊዎች ጀምሮ እስከ የሃገሪቷን የሰብ ኣዊ መብት ጥሰቶች እያነሱ የፖለቲካው ምህዳር ጥበቱን በዘረኝነት ልይ የተመረኮዘን የኢኮኖሚ ብዝበዛውን እና የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ጎን ያገለለውን ስር ኣት ማስረጃ እያጣቀሱ በመተቸት ጠላፊውን የደገፉ እንዲሁም በተሰቡን ጨምሮ ጀግና እስከማለት የደረሱበት ሁነታ ተከስቷል።

እስካሁን ድረስ ጠላፊውን በተመለከተ ምንም አይነት ዝርዝር ጉዳዮችን ያልተናገረው የስዊዘርላንድ ፖሊስ አይሮፕላኑ በተጠለፈበት ሰኞ የወጡ ዘገባዎች እንደሚይመለክቱት ረዳት አብራሪው የደህንነት ስጋቶች እንዳሉበት እና በሃገሪቱን ያለው ስር ኣት የሚከተላቸው የዘረኝነት አስተዳደር እና የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲሁም የአየር መንገዱ የአስተዳደር ብልሹነት የፈጠሩት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።

የወያነ ስር ኣት የቅርብ ሰዎች የረዳት አብራሪውን ስም እና የበተሰቡን ስም ጥላሸት ከመቀባት ጀምሮ ጉድዩን ወደ ዘረኝነት የወሰዱትም ጠባቦች ሲኖሩ ወደ ወያነ ጠጋ ብለው ለመኖር የፈለጉም ሃይለመድህንን አብጠልጥለዋል ሆኖም አንዳቸውም አልተሳካላቸውም።….

ጉዳዩን በቅርብ እየተከትተለ ያለው የኢሳት ተለቭዥን በተሰቦቹን ወዳጆቹን ጓደኞቹን እና የአየር መንገድ ሰዎቹን በማነጋገር ሰፊ ጊዘውን ሰቷል። ያነጋገራቸው የበተሰቡ አባላት ሃይለመድህንን በመደገፍ የሃገር ጉዳይ የሚያንገበግበው ጀግና ሲሉት ወዳጆች እና ጓደኞቹ የሃይለመድህንን መልካምነት በይፋ መስክረዋል። እንዲሁም የአየር መንገዱ ሰራተኞች የሃይለመድህንን ታታሪነት እና ጸባየ ሸጋነት አረጋግጠዋል።

እንዲሁም ቢቢኤን ራዲኦ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ጠበቃ እንዳቆሙረት በፕሮግራሙ ላይ ዘግቧል። የጠለፋውን ሁነታ ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ደህንነት ስራ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገለውና በክትትልና ደህንነት ስጋት ከአመት በፊት ድርጅቱን ለቆ በስዊዘርላንድ ጥገኝነት የጠየቀው ሚካኤል መላኩ ከኢሳት ጋር ባደረገው ሰፊ ቃለምልልስ፣ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነትና የአስተዳደር መበላሸት አጋልጧል።

ወጣቱ ፓይለት የተለያዩ አውሮፕላኖችን አብርሮ ልምድ ካካበተ በሁዋላ 767 የተባለውን አውሮፕላን በረዳት ፓይለትነት ለማብረር መቻሉን የገለጸው ሚካኤል፣ በዚህ ደረጃውም ከፍተኛ የሆነ ክፍያ የሚከፈለው በመሆኑ የገንዘብና የምቾት ችግር እንደማያጋጥመው ገልጿል። አብራሪው የ3 ሺ ሰራተኞችን ዋይታ ይዞ መምጣቱን የሚናገረው ሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኑ ሊቆምለት ይገባል ብሎአል

የካፒቴን ሃይለመድህን የጠላፋ ምክንያት አወዛጋቢ ሆኖ በቀጠለበት ሁኔታ ፣ ካፒቴኑ ከአጎቱ ከዶ/ር እምሩ ስዩም ሞት ጋር በተያያዘ እየተረበሸ መምጣቱን አቶ አሳምነው መላኩ የተባሉ የካፒቴን ሃይለመድህንን አጎት በመጥቀስ በአሶሺየትድ ፕሬስና በክርስቲያን ሞኒተሪንግ ተዘግቧል። አዲስ አበባ የኑቨርስቲ በድረገጹ ባሰፈረው መረጃም የዶ/ር እምሩ አሟሟት መንስኤ እንግዳ እንደሆነ ጠቅሷል። ኢሳት በበኩሉ ከዘመዶቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ዶ/ር እምሩ በሰዎች መገደላቸውን አንዳንድ የቤተሰብ አባሎች እንደሚያምኑና አጎቱን ማን ገደላቸው የሚለው ጥያቄ አለመመለሱን ዘግቧል።

ይሁን እንጅ የዶ/ር ስዩም ባለቤት ነኝ ያሉ ወ/ሮ አንጓች ቢተው ባለቤታቸው የሞቱት ታህሳስ ወር ላይ ጧት ፍላሚንጎ አካባቢ ተሳፍረው ቤተመንግስት አካባቢ ሲደርሱ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ መሞታቸውን፣ የሞታቸውም ምክንያት በልብ ህመም ምክንያት መሆኑን በመግለጽ ሰው ገደለው ተብሎ የቀረበው ዘገባ ስህተት መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል። ወ/ሮ አንጓች ካፒቴን ሃይለመድህን በአጎቱ ምክንያት እንደተረበሸ ተደርጎ በሚሰጠውን አስተያየት ዙሪያም ምንም የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ፣ ከካፒቴኑ ጋር በአመት በአል ወቅት ካልሆነ ብዙም እንደማይገናኙ ተናግረዋል።

ካፒቴን ሃይለመድህን ከአጎቱ ሞት ጋር በተያያዘ ይረበሽ ነበር በማለት መግለጫ የሰጡትን ሌላውን አጎት አቶ አሳምነውን ለማግኘትና ማብራሪያ ለመጠየቅ የተደረገው ሙከራ አልተሰካም። በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየቱን የጠየቅነው ዘጋቢያችን፣ ዶ/ር ስዩም በልብ ህመም መሞታቸውን ካፒቴን ሃይለመድህን የሚያውቅ ከሆነ፣ የሚጨነቅበት ምክንያት አይኖርም፣ ከአጎቱ ሞት ጋር በተያያዘ የሚሰጠው አስተያየትም ትክክል ላይሆን ይችላል ብሎአል።

ጠላፊው አውሮፕላኑን ወደ ጄኔቭ ከመውሰዱ በፊት ሮም ላይ ማረፉን የገለጸቸውን ዜና በተመለከተ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አውሮፕላኑ ሮም ላይ እንዳላረፈ በመግለጽ አስተያየታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ኢሳት በድጋሜ ተሳፋሪዋን ባነጋገረበት ወቅት፣ በአቋሟ በመጽናት አውሮፕላኑ ሮም ላይ አርፎ ወደ ሚላን ሲያቀና መጠለፉን፣ የበረራ ትኬቱዋን ለኢሳት በመላክ ትክክለኛ መረጃ መስጠቱዋን በድጋሜ ተናግራለች።

ጉዳዩ እንዴት ሊሆን ይችላል ስንል ጥያቄ ያቀረብንለት ሚካኤል መላኩ አውሮፕላኑ ሮም ላይ አርፎአል በሚል የተላለፈው ዘገባ ትክክለኛ ነው ብሎ እንደሚያምን የአየር መንገዱን አሰራር በመግለጽ አስረድቷል
የመንግስት የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን አውሮፕላኑ ካርቱም ላይ ማረፉን ፣ ቀጥሎ ደግሞ ካርቱም ላይ ማረፍ የነበረበት ቢሆንም ተጠልፎ ማረፍ ሳይችል ቀረ ብለው የገለጹት የአየር መንገዱን አሰራር ሳይዉቁ የተናገሩት አሳፋሪ ንግግር ነው ብለዋል። በአየር መንገድ የበረራ ታሪክ አውሮፕላኑ በቀጥታ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም እንደሚያርፍ በመግለጽ ካርቱም ላይ ማረፍ ነበረበት የሚለውም ትክክል አይደለም ብሎአል።

አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ፓይለቱ አውሮፕላኑን ይዞ ጄኔቫ ላይ በመሽከርከር ለማስፈራራት ሙከራ አድርጎ ነበር በማለት ዘገባዎችን አቅርበዋል። ይሁን እንጅ እንደ ሚካኤል ገለጻ ማንኛውም አውሮፕላን ከማረፉ በፊት ነዳጅ ማቃጠል ስለነበረበት ፓይለቱ ይህን ማድረጉን እንዲሁም ለ10 ደቂቃ ጉዞ ብቻ የሚበቃ ነዳጅ ነበረው ተብሎ በመገናኛ ብዙሃን የቀረበውም ትክክል ያልሆነና በአየር መንገዱ ህግ መሰረት ለ2 ሰአት በረራ የሚያበቃ መጠባበቂያ ነዳጅ እንደሚይዝ ገልጿል። — at Minilik Salsawi.

የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት (ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን አምባገነንነት፣ ከፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይ ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና፣ እስርና ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል። በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል። በዚህም በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል። አክትቪስት ታማኝ በየነ፣ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለ-መጠይቅ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

iframe

Image

የደህንነት ስጋት ፤የአስተዳደር ብልሹነት እና የዘረኝነት መድልዎን የሚቃወም የአይሮፕላን ጠለፋ

ታዋቂነታችን በድርቅ በድህነት ብሎም በጭፍጨፋ ደሞ በሰብኣዊ መብት ጥሰት

ምንሊክ ሳልሳዊ :- በሃገሪቱ የተንሰራፋውን የደህንነት ስጋት በመልካም አስተዳደር እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልዎ ተከትሎ የተደረገው የአይሮፕላን ጠለፋ ህዝቦች በገዛ አገራቸው በደህንነት ላይ ምን ያህል ስጋት እንዳጠላበት እና በመኖር ህልውናቸው ላይ ኢትዮጵያውያን የስርአቱ ፖሊሲዎች እያሸማቀቋቸው እንደሚገኙ አለም ካለፈው ጊዘ በተሻለ እውነታውን ፍንትው አድርጎ እየመሰከረ ነው።

የሕወሓት መራሹ ጁንታ ወደ ስልጣን በጠበንጃ ሃይል ከመጣ ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሰብኣዊ መብት ህጎችን ካለምንም ማርቅርቅ እና ድካም ከሌሎች በመገልበጥ በወረቀት ላይ ከማስፈሩም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ የሰው አገር ህግን እና አለማቀፍ ድንጋጌን ከሃገራችን ሁኔታ ጋር ሳይገናዘቡ በስፋት በደመነፍስ ለፍጆታ የተጻፈበት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በየትኛውም አለም ሃገራት ያልተከሰተ የአለም አቀፍ ህጎችን ግልባጭ በከፊል በህገመንግስት እንዲሁም የገዢ ፓርቲን የፖለቲካ ፕሮግራም በከፊል ደባልቆ በጋር እንደ አውራ ህግ የወጣባት ሃገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት::ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃ የተደነገጉባት አገር ነች፡፡ እንግዲህ ይህ ሆኖ እያለ ነው በአገሪቱ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከአገሪቱ ብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::
የቀድሞ መንግስትን ሽንፈት ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የፍፃሜ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ጭራሽ ብሶበት ቁጭ አለ፡፡ የሕወሓት ወንበሩን መቆጣጠር ተንተርሶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተለይም ሒዩማን ራይት ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የወያኔን ጁንታ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በማብጠልጠል ነበር የተቀበሉት፡፡ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች አቤቱታ ማሰማታቸውን አላቆሙም፡፡ ጋዜጠኞችን የሃሳብ ነጻነት ከሚገድብ ጥቃት በመከላከል ላይ የተሰማሩ የመብት አስከባሪ ድርጅቶችም ወያኔ በሚፈጥረው ከባድ የሰብኣዊ መብት ጥሰት በየጊዜው መክሰስ ሥራቸው ሆኗል::የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው በሚያወጣው ዓመታዊ መግለጫው ወያኔን በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፖለቲካ መብቶችን ማፈን ይከሰዋል፡፡ ባሁን ወቅትየእነኚህን አካላት መግለጫዎች የታወቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶች በመቀባበል ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብቶች በመጣስና በማፈን ወደር የሌላት አገር እንደሆነች ዓለም እንዲረዳው እያደረጉ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በአስከፊ ድርቅና ረሃብ ለመታወቅ እንደበቃችው ሁሉ ወያኔ የዜጎችን መብቶች በመጣስና በማፈን እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጽመው ወንጀል በዓለም ላይ ታዋቂነትን እያተረፈ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም;ወያኔ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን መብቶች ለመጣስ ስለሚጠቀምባቸው ዘደዎች የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና ማብራሪዎች እጅግ ዘግናኝ ናቸው፡፡የወያኔ መሪዎች የፖለቲካ ተቀናቃኖችን ለማዳከም ሲሉ ንፁኃንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ዘዴዎችን ሥራ ላይ እንደሚያውሉ በተለያዩ ይፋዊ ሪፖርቶች ላይ ሁሉ ከነማስረጃው እየተነገረ ይገኛል::

የህ የሰብኣዊ መብጥ ጥሰት እየተባባሰ የሚሄድበት ምክንያት ወይኔ በአብዛኛው ካድሬዎች ዘንድ በስፋት ሰርጾ እንዲገባ ያደረገው የተቃዋሚዎች ጥላቻ እና እንዲሁም የተቃዋሚው ቡድን የትግል አቅጣጫው በተመሳሳይ መልኩ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ መሆኑ ነው::ተቃዋሚዎች የታጠቁ ሃይላት ባለመሆናቸው የመርሃቸው እንቅስቃሴ የተገደበ እና ለፖለቲካ እና ለሚዲያ ፍጆታ የዋለ ተዳፍኖ የሚገኝ ሲሆን የወያኔው ግን በታጠቁ የጸጥታ ሃይሎች እና በፖለቲካ ማጭበርበሮች ላይ ስለተመረኮዘ ካድሬዎቹ በተሰጣቸው የጥላቻ ተግዳሮት እና ወያኔያዊ ስልቶች የፈጠሩትን ጥቅማጥቅሞች ጠብቀው ለማቆየት ሲባል ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::

ይህ ፍርሃት እና ጥላቻ በወያኔ ከትልቅ እስከ ትንሽ ካድሬዎች አናት ውስጥ ስር ለስር በመስደድ የፈጠረው ነገር ቢኖር ማንኛውም ዜጋ ተቃውሞ ካሰማ በወንጀለኛነት በመፈረጅ በማሳደድ በማጥፋት እረፍት ለማግኘት እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲራወጡ የህዝብን የበላይነት አፈር ከተውታል::ማእከላዊ የወያኔ ጁንታ በዲሞክራሲ ባለመወቀጣቸው የህጎችን የበላይነት ማረጋገጥ ካለመቻሉም በተጨማሪ በህዝብ እና በዲሞክራሲ ላይ በደሎችን የሚያደርሱ ባለስልጣናት የሚጠየቁት በሃገሪቱ የበላይ ህጎች ሳይሆን በወያኔያዊ የፓርቲ መመሪያዎች በመሆኑ በጥቅም መተሳሰር በፈጠርው ዝግ መንገድ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተብራከቱም ከመሆኑ አልፎ የእለት ተእለት ተግባራት አካል ሆነዋል:: የአይሮፕላን ጠለፋዉም ከላይ ከገለጽኩት ጉዳዮች ጋር ቁርኝት ያለውና በሃገሪቱ እየተተገበረ ያለውን የቡድን አምባገነንነት በማጋለጥ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውቷል።

Image

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ:: ለተፈጥሮ ሃብት የጠየቀው ዓለምዓቀፋዊ እውቅና ውድቅ ሆነ::

ምንጭ = ጎልጉል
ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር።

EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት – ማዕድን፣ ዘይት፣ ብረታብረትና ጋዝ – ከመሬት በሚወጣበት ጊዜ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን ያህል ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለባቸው አገራት ድርጊቱ ለሙስና እና ግጭት በር እንደሚከፍት ይናገራል፡፡ በመሆኑንም ድርጅቱ አገራት ለሚያቀርቡት የዕውቅና ጥያቄ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ልማትና እድገት በሚል ሰበብ የሕዝብ ሃብት የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት የህዝባቸውን መብት ለሚረግጡ አገራት የሚያቀርቡትን የዕውቅና ማመልከቻ ውድቅ ያደርጋል፡፡

የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጭ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እውነት ነው። ምንጩ እንዳሉት ኢህአዴግ በውሳኔው በመበሳጨት ይግባኝ ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ ነው። ድርጅቱ (EITI) አንድ አገር ለሚያቀርበው የእውቅና ማመልከቻ በመስፈርቱ መሰረት ግምገማ ካካሄደ በኋላ እውቅና እንዲሰጥ ሲያምን በራሱ ድረገጽ ላይ የዚያን አገር ስም በመመዝገብ ተጠቃሹ አገር ከተፈጥሮ ሃብት ጋር በተያያዙ ኢንቨስትመንቶች የሚገኘው ትርፍ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል የሚል እውቅና በመስጠት ምስክርነቱን ያሰፍራል፡፡

ኢህአዴግ የመጀመሪያው የማመልከቻ ጥያቄ ያቀረበው በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ2009 አካባቢ ነበር፡፡ ከEITI አምስት መስፈርቶች መካከል አንዱ፤ ማመልከቻ የሚያቀርቡ አገራት ከመያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ በመያዶች ላይ አፋኝ ሕግ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ እውቅና ሰጪው ድርጅት – EITI – የኢህአዴግን ማመልከቻ ውድቅ አድርጎታል፡፡ የEITI ቦርድ ይህን ዓይነት ውሳኔ ሲያስተላልፍ ያሰፈረው ነገር ኢትዮጵያ በእጩ አባልነት ለመመዝገብ በመጀመሪያ በመያዶች ላይ ያወጣችውን ሕግ ማስወገድ አለባት የሚል እንደነበር የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በድረገጹ ላይ አስቀምጦታል፡፡ በወቅቱ የተሰጠው ይህ ብያኔ በEITI እውቅና አሰጣጥ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ ተጠቁሞም ነበር፡፡
የEITI ዕውቅናን ለማግኘት ቋምጦ የነበረው ኢህአዴግ በድርጅቱ ውሳኔ ባለመደሰት ጥቂት ዓመታትን ቆጥሮ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ በአቶ ሃይለማርያም በመመራት በድጋሚ ዕውቅና የማግኘት ዘመቻውን ማጠናከር ጀመረ፤ በይፋም እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ የማዕድን ሚ/ር መ/ቤትም ዕውቅና ማግኘቱ በጣም የሚያስፈልግ እንደሆነ በይፋ በመናገር ዘመቻውን አጧጡፎ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አሠራር በዓለምአቀፉ ድርጅት ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኢህአዴግ Ethiopia Revenue Transparency Initiative (ERTI) የሚባል “ተለጣፊ” ተቋም በመመሥረት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ለEITI በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጾዋል፡፡

ጉዳዩን በቅርብ ይከታተሉ የነበሩ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ኢህአዴግ በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር 2013ዓም በድጋሚ ማመልከቻ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው ለዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አሳወቁ፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ ማሻሻያ እያደረጉ ነኝ የሚል ማስመሰያ ለማቅረብ የሞከረ ቢሆንም የመያዶችና የጸረ አሻባሪነት አፋኝ ሕጎቹ በተጨማሪ በቴሌኮሙኒኬሽን በኩል በስልክና ኢንተርኔት የሚያደርውን ህዝብን የመሰለል ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት እንደሆነ በመጥቀስ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ክፍሎች EITI ዕውቅና እንዳይሰጥ መወትወታቸውን ተያያዙ፡፡

እነዚሁ ወገኖች በተደጋጋሚ ያደረጉት “የወረቀትና የፔቲሽን ትግል” እየተባለ የሚቃለለው ትግል ውጤት በማምጣት ኢህአዴግ በደጋሚ ያስገባው የአባልነት ማመልከቻ ሰሞኑን ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ EITI ማመልከቻ በሚመዝንበት በሁሉም መስፈርቶች ኢህአዴግ ወድቋል፡፡
አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ።

ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው መክሸፉ ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ህግ መታፈኑ የሚያመላክት እንደሆነ የሚጠቅሱ ክፍሎች፤ ከኢህአዴግ ከፍተኛ ፍላጎት አኳያና ሰሞኑን በተለያየ አቅጣጫ እየተወጠረ ከመምጣቱ አንጻር ሁኔታው አጣዳፊና ፋታ የማይሰጥ በሽታ ምልክት እንደሆነ በምጸት ይናገራሉ፡፡

ስለEITI ውሳኔ ባጭሩ እንዲያብራሩልን የጠየቅናቸው ባለሙያ እንዳሉት “አንድ ዩኒቨርሲቲ ህንጻ በማስገንባቱና አስተማሪዎችን በመቅጠሩ ብቻ ዩኒቨርስቲ ተብሎ ሊጠራ አይችልም። ዩኒቨርስቲው ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት ተገምግሞ እውቅና የሚሰጠው መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልቶ ስለመገኘቱ ምርመራ ተደርጎበት ፈተናውን ሲያልፍ ብቻ ነው። በዚሁ መሰረት አልፎ እውቅና ያላገኘ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብቶ መማር የተሳትፎ ያህል ነው። መስፈርቱን አሟልተው እውቅና ካገኙት ጋር መወዳደር ስለማይችል ተመራጭ አይሆንም። በተመሳሳይ Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የተባለው ድርጅትም ከየአገራቱ እውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብለትን ጥያቄ /ማመልከቻ/ የሚመዝንበት መስፈርቶች አሉት። ኢህአዴግ የተፈተነው በዚሁ አቅልጦና አንጥሮ በሚያወጣው መመዘኛ ነው ብለዋል፡፡”

ስለጉዳዩ የተጠየቀው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የህዝብ ግንኙነት ግብረ ኃይል ጉዳዩን በጥልቀት የሚያውቀውና ገና ከጅምሩ ሲከታተል የቆየው መሆኑን በመግለጽ በበርካታ ፈርጆች ከሚያካሂደው ትግል አንጻር በዕቅድ ሲያከናውነው የቆየ መሆኑን አመልክቷል። የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለጎልጉል እንዳለው ከሆነ “የEITI ውሳኔ ኢትዮጵያን እንደ አገር የሚጎዳ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ውሳኔው ኢህአዴግ በራሱ ግትረኝነትና እብሪት ያመጣው ጣጣ በመሆኑ የራሱን ተግባር ተከትሎ የተወሰነው ውሳኔ በአገሪቱ ላይ በማንኛውም መልኩ ለሚያደርሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግና ህወሃት ናቸው” ብሏል። በማያያዝም የጋራ ንቅናቄው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ በማውጣት አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ወገኖች እንደሚበትንና ተቋሙ በውሳኔው እንዲጸና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ለተሰማሩ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ አመልክቷል።

አስፈላጊውን ግብር እና ቀረጥ እስከከፈልን ድረስ የጸጥታ አስከባሪዎች ስራ እና የህገመንግስቱ ትርጉም ይነገረን::
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ዞር ብለን ካለፍነው የኢትዮጵያ የፍትህ ታሪክ እንዳነበብነው ከወላጆቻችን እና ከቅርብ መካሪዎቻችን እንደሰማነው የፊውዳሉ ንጉሳዊ ስርኣትም ይሁን የወታደራዊው ደርግ አገዛዞች በፍትህ አካላት ላይ ፖለቲካን ተገን አድርገው ፍትህን ያዛቡበት ቦታ አልተጠቀሰም :: የፖለቲካ ባላንጣዎቻቸውን ፍትህን ለሃሰት ተጠቅመው ማስረጃ ፈብርከው በየእስር ቤቱ በህገወጥነት አላጎሩም:: እነዚህ ሁለት ሰው በላ እና አራጅ መንግስታቶች የማንንም ህዝብ መብት በፍትህ ስም አልተጋፉም በፍርድ ቤቶች ላይ አዛዥ አልሆኑም::

ፍትህ ካለ ሰላም አለ:: ፍትህ ካለ የተደበላለቁ ስሜቶች ራሳቸውን ይገዛሉ:: ፍትህ ካለ የበላይ አካላት ለህዝብ ይታዘዛል:: ፍትህ ካለ ዲሞክራሲ ይጎለብታል:: ፍትህ ካለ ማንኛውም ሰው በነጻነት ይዘዋወራል:: ፍትህ ካለ እያንዳንዱ ሰው የራሱን መብት ያቃል;የሌላውንም ያከብራል … ፍትህ ካለ የጸጥታ ሃይሎች የወጡበትን አብራክ አይረግጡም የእናት ሃገር ማህጸንን አያደሙም ህዝብን አያስለቅሱም ወዘተ….. ስለዚህ ፍትህ ላይ ማተኮር የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው::

አሁን ግን እያየነው ያለው ፍትህ ከሁለቱ መንግስታት በተለየ ሁኔታ ህዝብን በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስክ ቁም ስቅሉን እያሳየው ነው:: የሃገሪቱ ህገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ እና ውጪ በፖለቲካ መስክ የአይናቸው ቀለም ያላማረ ተቃዋሚዎች ይደበደባሉ ይታሰራሉ ይገረፋሉ በፍርድ ቤት በሃሰት መረጃ ከህግ ትእዛዛት ውጭ የረዥም አመት እስር ይከናነባሉ:: እንደ መንግስት ባለስልጣናት ሳይሰርቁ ደፋ ቀና ብለው ያፈሩት ንብረት ይወረሳል::ከዛም አለፍ ካለ በአደባባይ ይረሸናሉ:: በደህንነት ሃይሎች ይገደላሉ:: ይህ የሚያሳየው የጸጥታ ሃይሎች ከህግ በላይ ሆነው ፍትህን መግደላቸው ነው:: የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳይንቀሳቀሱ የጸጥታ ሃይሎች እንቅፋት ከመሆን አልፈው ወደ አንድ ፓርቲ ያደላ ኮንትሮባንዳዊ ፖለቲካ እየፈጸሙ ነው:: በፓርቲዎች ላይ ወከባ እየደረሰ ነው:: የጸጥታ ሃይሎች ደሞዝ የሚከፈላቸው ከህዝብ ኪስ ሆኖ ሳለ የሚያዋክቡት እና ፍትህ የሚያጎድሉበት የሚያስለቅሱት ግን ይኸው ደሞዝ የሚከፍላቸውን ህዝብ ነው::

ህገ መንግስት አዋጅ መመሪያ አያለ መንግስት የሚያወጣው እና ፓርላማ አጸደኩ የሚለው ለህዝቡ ምንም የሰጠው ትርጉም የለም ጠቀሜታውም ዜሮ ነው ህዝቡ በኑሮ ውድነት እየደቀቀ ባለበት ሰአት ላይ ጥቂት ሰዎች ገነው በኢኮኖሚ መበልጸጋቸው በማህበራዊው መስክ የሚደረገውን ህብረተሰባዊ ጠቀሜታዎችን ማሳጣታቸው የፍትህን በአደባባይ መሰቀል ያመለክታል:: ይህ ሁሉ ተያይዞ የጸጥታ ሃይሎች ህዝብን አይዞህ ባይነታቸውን ትተው የባለስልጣናትን ወንበር እየጠበቁ ነው:: ስለዚህ ለመንግስት አስፈላጊውን ግብር እና ቀረጥ እስከከፈልን ድረስ የጸጥታ አስከባሪዎች ስራ እና የህገመንግስቱ ትርጉም ይነገረን::ፍትህ ላይ እናተኩር::

ጋዜጠኞች ቁጭ ብለው የሞሪኒሆን ፈረስ ሲጠብቁ ገንዘቤ 3 ሪኮርዶችን ሰበረች:: ከአድዋ ድል ቀጥሎ የኢትዮጺያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረገው አትሌቲክስ ነው:: አትሌቶቻችን በሄዱበት ውድድር ሁሉ ድልን ተጎናፅፈው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን አለም ላይ ከፍ አድርገው ያውለበልቡታል::

እንግሊዞች እግር ኳስን በፍቅር ይወዱታል:: አለም ላይም ሊጋቸው ተወዳጅ እንዲሆን በሚዲያቸው በመጠቀም ተፅኖ አሳድሮዋል:: በአትሌቲክስም ከሀገራቸው አንድ አትሌት ትንሽ ውድድር ካሸነፈ ብዙ ያወሩለታል:: አለም ላይ ያሉ ተርጓሚ ጋዜጠኞችም እዬንኑ ግነት አግንነው ያወሩታል::

በእንግሊዝ ሚዲያ ቀኝ ከተገዙ ሀገራት መካከል የኢትዮጺያ ሚዲያ አንዱ ነው:: ስለ ቀነኒሳ 2ኛ መውጣት ይልቅ ስለ ሞፋራ ሰባተኛ መውጣት ብዙ ይወራለታል:: “የእንግሊዝ ሚዲያ ጅራፉን ያነሳል የኢትዮጺያ ሚዲያ ጅራፉን ያጨዋል”

ገንዘቤ ዲባባ ሰሞኑን አለም ላይ በ15 ቀን 3ሪኮርዶችን እንደ ከረሜላ ኮረሻሽማለች:: የኢትዮጺያ ኔትዎርክ ሳይስተካከል እሷ 3 ሪኮርዶችን ጨፈላልቃለች:: ገንዘቤ በኢትዮጺያ ሚዲያ ሽፋን በበቂ ሁኔታ አልተሰጣትም ብዬ አስባለው:: የሞሪኒሆ ስለ ፈረስ ወሬ በትንታኔ እየቀረበ የገንዘቤ 3 ሪኮርዶች እንደ ዜና ብቻ ቀርበው ሲታለፉ ያስተዛዝባል:: ኢትዮጺያ ውስጥ የእግር ኳስ ጋዜጠኞች እንጂ የስፖርት ጋዜጠኞች ዬሉም የሚለውን ያረጋግጣል::

“ውድድሩ የግል ነው ሀገርን አይወክልም” የሚል ክርክር ሊመጣ ይችላል…. ግን ደደቢት እኮ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የግል ውድድር ነው ሲጠራ የኢትዮጺያው ደደቢት ተብሎ ነው:: በአትሌቲክስም ተመሳሳይ ነው:: “ኢትዮጺያዊቷ (ዲባባስ ፋሚሊ) ገንዘቤ ዲባባ አለም ላይ ነገሰች” ነው የሚባለው::

ገንዘቤ እንደ ምንያህል በጋዜጣ “እንግሊዛዊ ብሆን የኢትዮጺያ ሚዲያ ብዙ ያወራልኝ ነበር” ብትል የእግር ኳስ ጋዜጠኞች እኮ ተሰደብን ብለው በማህበራቸው በኩል መግለጫ ያወጡ ይሆናል:: ምነው ባለች ያስብላል::

ገንዘቤ አቦ እንኳን ተወለድሽ…. እንኳን ሰባበርሽ…. እንኳንም ደስ አለሽ…. ኢቲ ፉፋ

“ሪኮርዱ ቦሌ ፈረሱ ጉለሌ”
የቡና ቁርስ – በEphrem Amare

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በራሳቸዉ እጅ የጻፉት ማኒፌስቶ በግልጽ እንደሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ጫካ ገብተዉ የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ያነሳሳቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸዉ ጥላቻና መሰረተ ቢስ ቂም በቀል ነዉ። ይህ ጥላቻቸዉ ደግሞ አማራዉን በመግደልና ግዛቱን ሲያሻቸዉ ከራሳቸዉ ክልል ጋር በመቀላቀል አለዚያም ለጎረቤት አገሮች በመሸለም ብቻ ሊቆም ወይም ሊገታ አልቻለም። እነሆ የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።
ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማዳከም፣ ለዘመናት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያገለግለኛል ብሎ ዘመቻ ከከፈተባቸው ብሄረሰቦች አንዱና ዋንኛው የሆነው የአማራ ህዝብ በራሱ ማንነት እንዲያፍርና ብሄራዊ ኩራቱ እንዲሟሽሽ ላለፉት 23 አመታት በግብር ከፋዩ ህዝባችን ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛዎች ሳይቀር ከፍተኛ የስነ ልቦና ዘመቻ ተካሂዶበታል። በአማራ ሥም አማራውን የወያኔ አገር የማፍረስ አጀንዳ አስፈጻሚ ለማድረግ የተሾሙበት ተላላኪዎች በህወሃት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አጋጣሚዎች አማራውን የሚያዋርድና የሚዘልፍ አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ ሰምተናል አይተናል። ይህ ተግባራቸው ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ፍቅር ያልነበረው ዘረኛው አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከዚህች አለም በሞት ከተሰናበተ ቦኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።
የህወሃት መሪዎች አማራው ላይ ያላቸው ጥላቻ ወደሥልጣን ከመጡ ቦኋላ የተፈጠረ ሳይሆን ገና በጫካ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በጻፉት የድርጅታቸው የፖለቲካ መረሃግብር በግልጽ እንደተቀመጠው ለትግል ያነሳሳቸውም አማራ ብለው የሚጠሩት ብሄረሰብ እንወክለዋለን በሚሉት ብሄረሰብ ላይ አድርሰዋል በሚሉት የፈጠራ በደልና ቂም እንደሆነ አረጋግጠዋል። ላለፉት 23 አመታት አማራው ከሚኖርበት የራሱ ክልሉ ሳይቀር እንዲፈናቀል ተደርጎ እየደረሰበት ያለው በደል የዚህ የቆየ የወያኔ ቂም በቀል ውጤት መሆኑ ግልጽ ነው።
ሰሞኑን አለምነው መኮነን የተባለ ሆድ አደር የባንዳነት ተግባሩን በመፈጸም በአለቆቹ ፊት ግርማ ሞገስ ለማግኘት እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ እጅግ በወረደና ጸያፍ በሆነ ቃላት ያን ያህል ሲዘባበትበት መደመጡ አማራውን ብቻ ሳይሆን መላውን የአገራችንን ህዝብ አስቆጥቶአል።
በእርግጥ አለምነው መኮንን አማራን በማዋረድ የመጀማሪያው የወያኔ ተላላኪ አይደለም። የህወሃቶቹን ቁንጮዎች ስድብና ዘለፋ ወደ ጎን ትተን በወያኔ የዘር ፖለቲካ አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን ከፍተኛ አመራር እነ እነታምራት ላይኔ ተፈራ ዋልዋና በረከት ስሞን በተለያየ ወቅት ንቀትና ስድባቸውን አሰምተውናል። አለምነህ መኮንን እንደዚያ በወረደ ቃላት አማራውን ሲያዋርድ በስብሰባው አዳራሽ የነበሩ ህወሃት የፈጠራቸው የብአዴን ልጆች በሳቅ ካካታ ሲያጅቡት እንደነበረ እድሜ ለኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ከአዳራሹ ሾልኮ ለህዝብ ጀሮ የደረሰው የኦዲዮ ድምጽ አጋልጦአል።
ሁላችንም፤ እንደምንገነዘበው ወያኔ የገዛ ብሄረሰባቸውን ረግጠው በመግዛት የጥፋት አላማውን እንዲያስፈጽሙለት በራሱ አምሳል ከፈጠራቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን በታሪኩ አንድም ለህዝቡ የቆመ መሪ አፍርቶ አያውቅም። ለራሳቸውና ከአብራኩ ለተገኙት ህዝብ ምንም አይነት ክብር የሌላቸው የብአዴን መሪዎች ጣሊያን አገራችንን በወረረችበት ወቅት ለሆዳቸው ሲሉ ከባዕድ ጋር ተሻርከው ህዝባቸውን ካስጨፈጨፉት ባንዳዎች የከፋ ተግባር በህዝባቸው ላይ እየፈጸሙ ነው።
ወያኔ ለም የሆነውን የአማራ ግዛት እንዳለ የኔ ነው ወደሚለው የትግራይ ከልል ሲወስድ፤ በአማር ክልል ወስጥ በቀሩት ለም ቦታዎች የህወሃት ታማኝ ካድሬዎችን ከያሉበት እያጓጉዘ ሲያሰፍር፤ የአገሬውን አርሶ አደር እያፈናቀለ ለራሱ ታማኞች ለም መሬት እየሸነሸነ ለሰፋፊ እርሻ አገልግሎት ሲያድል አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን አንድም የተቃውሞ ድምጽ አሰምቶ አያውቅም። የብአዴን መሪዎች የወያኔን ተልዕኮ ከማስፈጸም አልፈው በሟቹ አለቃቸው በመለስ ዜናዊ ሥም እየማሉ በአገራችን ኢትዮጵያና በሚያስተዳድሩት የአማራ ህዝብና ክልል የሚፈጽሙት በደል ብዙ ነው። ልክ እንደ ብአዴን የዘረኛውን ወያኔ የጥፋት ፖሊሲ ለማስፈጸም ከሚተጉት አንዳንዶቹ አማራውን ከክልላቸው ለማጽዳት በቤኒሻንጉል፤ በቤንች ማጅና ጉራፈርዳ ወረዳ እርምጃ ሲወስዱና ንብረታቸውን ቀምተው ባዶ እጃቸውን ሲያባርሩዋቸው ብአዴን ቁጭ ብሎ ተመልካች ነበር። ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰነው ዳር ድንበራችን ላይ በተነሳው የባለቤትነት ጥያቄም ላይ የወሰደው አቋም በህዝብና በታሪክ ፊት ውሎ አድሮ የሚያስጠይቀው ነው።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደሚገነዘበው ፋሽስቱ ወያኔ በአገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸመው ያለው አንዱን ዘር ከሌላው ጋር የማጋጨትና በተናጠል ደግሞ እያንዳንዱን ለይቶ የማዋረድና የማጥፋት ተግባር አሁን የተጀመረ ክስተት አይደለም። የቆየና ወያኔ ህዝባችንን ከፋፍሎ ለመግዛት ከመነሻው ሲጠቀምበት የነበረ ስልት ነው። ስለዚህ ወያኔ በራሱና በተላላኪዎቹ አማካይነት ላለፉት 23 አመታት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውና የፈጸመው ግፍ፤ ውርደትና መከራ እንዲያበቃ ሁላችንም እጅ ለ እጅ ተያይዘን መነሳት ይኖርብናል። በወያኔ ከፋፋይ አጀንዳ እርስ በርስ እየተናቆርን የጥቃት ሰለባ የመሆናችንን እንቆቅልሽ ለማስቀረት ከኛ በላይ ሃይል ያለው አይኖርም።
በተለይ ግንባር ቀደም የወያኔ ሰለባ የሆነው የአማራ ህዝብ ወጣት በጫንቃው ላይ ተፈናጠጠው የወያኔን የጥላቻና የበቀል እርምጃ የሚያስፈጽሙትን ከአብራኩ የተገኙ ባንዳዎች ላይ የጥቃት ክንዱን መሰንዘርና ለክብሩ መቆሙን ማሳየት ያለበት ጊዜው አሁን ነው።
በብአዴን ሥር የተሰባሰቡ የአማራ ተወላጆች፤ በመከላኪያ ሠራዊቱ፤ በፖሊስና በደህንነት፤ በወጣት ማህበር፤ በሠራተኛ ማህበርና በተለያየ ሙያ ማህበር ብአዴን ራሱ ያደራጃቸው ሁሉ ለክብራቸውና ለኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ሲሉ ከትግሉ ጎን በመሰለፍ የወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚያካሂደውን ትግል እንዲቀላቀሉ ንቅናቄው ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ኢሕአዴግ የዘረጋቸው ትላልቅ ፕሮጅክቶች የሕዝቡ ተሳትፎ እንደሚጠይቁ የተገነዘቡት በርካታ የኢሕአዴግ ደጋፉዎችና አባላት፣ ኢሕአዴግ መሰረታዊ ማሻሻያዎችን እንድያደርግ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲያሰፋ፣ እስረኞችን እንዲፈታ ዉስጥ ዉስጡን ጫና እያደረጉ እንደሆነ ከኢሕአዴግ አካባቢ ያሉ ምንጮቻችን ይገልጻሉ።

ትግራይን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በኢሕአደግ ዘንድ ባሉ የመልካም አስተዳደር፣ የኢፍትሃዊነት ችግር ላይ፣ እንዲሁም አልቻል በተባለው የኑሮ ዉድነት የተነሳ፣ የሚነሱ ተቃዉሞዎች እየተበራከቱ መሆኑ ያዩ ኢሕአዴግን የሚደግፉ ወገኖች፣ ኢሕአዴግ የሕዝብን ጥያቄ እንዲያዳምጥ፣ ከሕዝብ ግር እንዲታረቅ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።
«የዛሬዎቹ ኢሕአዴጎች የዚህ የደሃ ሕዝብ እንባና ሮሮ የማያትያቸው ናቸው»
«እዚህ አገር ላይ መልካም አስተዳደር ድራሹኑን ጠፏቷል»
ኢሕአዴጎችን «እነዚህ ክፉ የጫካ ሹሞች ….»
«ሕዝቡ ተማሯል»
«አስተዳደሩ ተበላሽቷል። የአቶ መለስን የቀድሞ አባባል ልዋስና በስብሷል ማለት ይቻላል»
«እዚህ ክፍለ ከተማ ሕዝብ አስለቅሶ በሙሰኝነት ሲነሳ የሰማችሁት ግለሰብ፣ የድርጅት አባል ስለሆነ ተብሎ ወዲያኛው ክፍለ ከተማ ሲሾም ታዩታላችሁ። ይሄ ነገር ምንድን ነው ስትሉ ,አይ ግድ ለየም ሂሱን ወጧል የሚሉት አነጋገር አላቸው»
«የሕዝብ እንደራሴ ተብለው የተመረጡ፣ ፓርላምዉን ያጣበቡ ብዙ ናቸው። መቼ ነው ወደ መረጣቸው ሕዝብ ሄደው ምንድን ነዉ ችግሩህ ያሉት ?፡»
እነዚህ አባባሎች የተናገሩት አቶ ቢኒያም ከበደ ይባላሉ። የኢትዮጵያ ፈርስት ድህረ ገጽ አዘጋጅ ናቸው። እርሳቸው ገለልተኛ መሆናቸውን ቢናገሩም የገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ደጋፊ እንደሆኑ የነገርላቸዋል። በተለይም ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊን በጣም እንደሚወዱና እንደሚያደንቁ በተለያዩ ጊዜ ሲገልጹ ተሰምተዋል።፡
አቶ ቢንያም በአሁኑ ጊዜ መኖሪያቸውን ከአሜሪካን ወደ አዲስ አበባ በማዞር ከዚያዉ ከአገር ቤት አልፊ አልፎ ዘገባዎች ያቀርባሉ።
በቅርቡ በድህረ ገጻቸው ላይ፣ ባልተጠበቀ መልኩ፣ በኢሕአዴግ ላይ ጠንካራ ትችት አሰምቶናል። አቶ ቢንያም ኢሕአዴግ እየበሰብሰ እንደመጣ በመናገር በአገሪቷ መልካም አስተዳደር ፈጽሞ እንደጠፋ፣ ህዝቡ በኢሕአዴግ ካድሬዎች እየተጎላላ እንዳለ ይናገራሉ። የዉሃ እጥረት ከፍተኛ ደረጃ በመድርሱ ጀሪካን እየያዝን ነው የምንወጣው ያሉት አቶ ቢኒያም፣ የመብራት ችግር በጣም አሳዛኝ መሆኑን ሲገለጹ፣ «መብራቱ አሥሬ እየበራና እየጠፋ፣ የምሽት ዳንስ ቤት ነዉ የሚመስለው» በማለት ነበር።
99.9 በመቶ የሚሆኑ በፓርላማ የሚቀመጡ የሕዝብ እንደራሴዎች ላይ ሳይቀር፣ አቶ ቢኒያም ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል። « በቴንትድ (በጠቆረ) መስኮት መኪና ዉስጥ ተሸሸገው ፣ ከሕዝቡ የማይገናኙ፣ የተደበቁ፣ የሕዝብኑን ብሶት የማያዳምጡ ናቸው» ሲሉ የፓርላማ ተወካዮች ምን ያህል የማይረቡ መሆናቸውን አቶ ቢኒያም ለማስረዳትም ሞከረዋል።
ኢሕአዴግ የሕዝብ ጥያቄ የማይሰማና ሕዝብን የማያከብር ከሆን፣ ይሄ የመረረዉ ሕዝብ ቅጣቱን እንደሚያወርድ ያስጠነቀቁት አቶ ቢኒያም፣ ኢሕአዴግ አፋጣኝ ለዉጦች እንዲያመጣ፣ ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥና ሕዝብን እንዲያከበር መክረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮና መኖርያ ቤት በሚገኝበት ታላቁ ቤተ መንግሥት አጥር ዙሪያ ገባው ላይ የሚገኘው የመስቀል ቅርጽ፣ የእስልምናና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖቶች መሪዎችን አነጋገረ፡፡
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ባለፈው ሳምንት ቅዳሜና እሁድ በሐዋሳ ባካሔደው የምክክር መድረክ ላይ ‹‹አገሪቱና መንግሥቱ የእኩልነትና የዜጎች መንግሥት ነው፤›› ያሉት የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ ኪያር ሙሐመድ አማን÷ ከቀድሞው ሥርዐት አንጻር አሁን የሚያበረታቱ ነገሮች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

ይኹንና በሴኩላሪዝምም ቢኾን ፍጹምነት ባለመኖሩ ‹‹አገር የጋራ ነው ከተባለ በኋላ የጎደለ ነገር አለ፤›› በሚል አዘውትረው ጥያቄ የሚያቀርቡላቸው ሰዎች መኖራቸውን ሸኽ ኪያር ጠቅሰዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይቀርቡልኛል ካሏቸው ጥያቄዎች መካከል ‹‹ለምሳሌ፡- ታላቁ ቤተ መንግሥት በመስቀል ነው የተከበበው፤ ይህ መጥፎ ነገር ሊያመለክት ይችላል›› የሚሏቸው እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
ታላቁን ቤተ መንግሥት የከበበውን መስቀል፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንደቆመው የደርግ ሐውልት ያህል እንዲታይ በሚል ለጥያቄው መልስ እንደሚሰጡ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ “በአክሱም አንዲት ጎጆ መስጊድ እንኳ ለመገንባት እንዴት አልቻልንም?” ተብለው ሲጠየቁ የዚህን ያህል ‹‹የቀልድ መልስ እንኳ ለመስጠት አልተቻለም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ነገሮችን ለማከም መቅደድ አለብን›› የሚል የዐረብኛ ብሂል እንዳለ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ሁልጊዜ ጥላሸት መስለው ይታያሉ ያሏቸውን ችግሮች ለመፍታትና መልስ ለመስጠት ይቻላል ወይስ አይቻልም ሲሉ በፈገግታ የታጀበ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸኽ ኪያር ጥያቄ ላይ ፈጥነው አስተያየት የሰጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ሸኽ ኤልያስ ያቀረቧቸው ነገሮች ሌሎች ስለጠየቋቸው እንጂ ራሳቸው ፕሬዝዳንቱ አምነውበት እንዳልሆነ ከአነጋገራቸው መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡
በጥያቄው ስለ መስቀልም ስለ አክሱምም መነሣቱን ያስታወሱት ፓትርያርኩ፣ ‹‹ሁለቱም የቆዩ ናቸው እንጂ አሁን የተፈጠሩ አይደሉም፤›› ሲሉ ተናግረዋል፤ ‹‹በዚህ ግቢ (ስብሰባው በተካሔደበት ሌዊ ሪዞርት ማለታቸው ነው) ያየናቸው ዋርካዎች ድሮ የነበሩ ናቸው፤ አሁንም ይጠቅማሉ፤ ከቆረጥናቸው ጉዳት ነው፤ ከኖሩ ይጠቅሙናል፤›› በማለት የቆየው ታሪክ መጠበቅ እንዳለበት በምሳሌ አስረድተዋል፡፡ ‹‹የመስቀሉ ቅርጽ የቆየ ታሪክ ነው፤ በታሪካዊነቱ ተከብሮ ተጠብቆ መኖር አለበት፤ በአክሱም ስላለው ነገር ከተነሣም የእኛም ጥያቄ ወደ ረጅምና ዝርዝር ነገር ይሔዳል፤›› በማለት የሁሉም ታሪክ በየራሱ መታወቅና መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

መከባበርም መቻቻልም እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ፓትርያርኩ፣ “አገሩ የኹላችንም ነው፤ የነበረው ታሪክ ደግሞ በታሪካዊነቱ ተከብሮ መኖር አለበት” በሚል ለሸኸ ኪያር ጠያቂዎቹ ምላሽ መስጠት እንደሚቻል በፈገግታ የታጀበ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ የውይይቱ ተሳታፊ ከኾኑ ሌሎች የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችም ሆነ የምክክር መድረኩን ከመሩት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች የተሰጠ ምላሽና አስተያየት አልነበረም፡፡
የመስቀልና ዘውድ አምሳል በተቀረጹባቸው አጥሮች የተከበበው ታላቁ ቤተ መንግሥት፣ የምኒልክ ቤተ መንግሥት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ንጉሡ በ1878 ዓ.ም ያሠሩት መንበረ መንግሥታቸው ነበር፡፡ የተለያዩ መኖርያ ቤቶችን፣ እልፍኞችንና አዳራሾችን እንዲሁም ቤተ ጸሎቶችን ያካተተው ቤተ መንግሥቱ÷ የታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም፣ የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እና የሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ይዋሰኑታል፡፡

በተለይ የዘውድ አምሳል በጉልላቱ ላይ የሚታይባት የበኣታ ለማርያም ገዳም የንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ፣ የንግሥታቱ እቴጌ ጣዪቱና ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እንዲሁም የልዕልት ፀሐይ ኃይለ ሥላሴ ዐፅሞች ያረፉበት ሲኾን የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮና መኖርያ የኾነው ከደርግ መንግሥት ጀምሮ ነው፡፡
ለሁለቱ የሃይማኖት መሪዎች መነጋገርያ የኾነው ጉዳይ መነሻ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ የግጭትና ሰላም ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር በኾኑት ዶክተር ታረቀኝ አዴቦ የቀረበው ‹‹በአገራችን የሃይማኖት ተቋማትና ተከታዮች በሰላም አብሮ የመኖር ወርቃማ ተሞክሮና የማስቀጠል ፋይዳው›› የተሰኘ ፅሁፍ ነው፡፡

የአገራችን ሕዝቦች ‹‹እንኳን በብርሃን ዘመን በጨለማው ዘመንም ጭምር›› የሃይማኖት ብዝሐነትን በመሠረቱ ያለመግባባትና የግጭት መነሻ ሳያደርጉ በሰላም አብረው እንደኖሩ የሚያትተው የጥናት ጽሑፉ፣ በሰላም አብሮ መኖር÷ ብዝሐነትን እንደ ነባራዊ ኹኔታ የመቀበል፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የትግል ስልት የመከተል፣ የብዝሐነቶች ነጻነትና እኩልነት መረጋገጥ አስተሳሰቦች ጥምረት መኾኑን ይገልጻል፡፡
የሃይማኖት መሪዎች በሰላም አብሮ የመኖር አርኣያ በመኾን ከቅድመ አያቶቻችን ጀምሮ ለዘመናት የቆየውን በሰላም አብሮ የመኖር ዕሴት በውስጣቸውም ይኹን በመካከላቸው፣ አስተሳሰቡንና ተግባሩን በማስፈን ለሚቀጥለው ትውልድ የማስተላለፍ ታሪካዊ አደራና የዜግነት ግዴታ እንዳለባቸው ያስገነዝባል- ጥናታዊ ፅሁፉ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት፣ ያለፈውን ታሪካዊ እውነታ ተቀብሎና ዕውቅና ሰጥቶ፣ የወቅቱን ነባራዊ ኹኔታ መሠረት አድርጎ ወደፊት በመቃኘት፣ በአገራችን ብዝሐነትን ተቀብሎ በተገቢው ኹኔታ ለማስተናገድ አቅጣጫ ያስቀመጠ ብቸኛው የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ነው የሚሉት ሌሎች የጥናታዊ ጽሑፍ አቅራቢዎች÷ መንግሥታዊ ሃይማኖትን ከሠየመው የንጉሣዊው ሥርዐት ሕገ መንግሥትና ፀረ – ኹሉ ከነበረው የወታደራዊ ሥርዐት ሕገ መንግሥት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት የሚለይባቸውን መርሖዎችና ድንጋጌዎች ዘርዝረዋል፡፡
የሃይማኖት ተቋማት ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን ለተከታዮቻቸው የማስተማር ሓላፊነታቸውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት ይኖርባቸዋል ያሉት ጽሑፍ አቅራቢዎቹ፣ የመንግሥትና የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትና ሠራተኞችም ሴኩላሪዝምንና ሃይማኖት ነክ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በጥብቅ በመተግበር፣መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን ያረጋገጠውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ማስከበር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በሃይል ለመግዛት መሞከር የውድቀት ምልክት ነው!!
ለሂሊናቸው ሶይሆን ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩና ለታሪክ ደንታ ቢስ የሆኑ ሁሉ በኢህኣዴግ የተዛባ ሚዛን ልማታውያን ናቸው፡፡ ልማታዊ የሚል መዳልያ ከኢህኣዴግ የሚገኝ ትልቅ የክብር ሽልማት ነው፡፡

የጠ/ሚ ሃ/ማርያም ደሳለኝ ቆይታ ከልማታውያን ጋዜጠኞች
ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ ልማታዊ ነጋዴ፣ ልማታዊ መመህር፣ ልማታዊ ሃኪም፣ ልማታዊ ቄስ፣ ልማታዊ ሼክ—- ልማታዊ የሚል መዳልያ ከኢህኣዴግ የሚገኝ ትልቅ የክብር ሽልማት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ኣይነት ሽልማት የሚሰጣቸው የተወሰኑ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህም ኢህኣዴግ በህዝብ ላይ የፈለገውን አፈና ሲፈፅም ፣ የሃገር ኢኮኖሚ በሙስና ሲበዘብዝ ለምን ያማይሉ፣ ለሂሊናቸው ሶይሆን ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩና ለታሪክ ደንታ ቢስ የሆኑ ሁሉ በኢህኣዴግ የተዛባ ሚዛን ልማታውያን ናቸው፡፡

ሁላችን እንደ ተከታተልነው 04/06/06 ዓ/ም ከሁለት ሰዓት ዜና በኃላ ጠ/ሚ ሃ/ማርያም ደሳለኝ እነዚህ ኣብዛኛዎቻቸው ልማታውያን ጋዜጠኞች ጠርተው የቼዝ ጭዋታ (chess play) በማካሄድ ሰዓታቸውን ኣሳልፈዋል፡፡ በዛ ጭዋታ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ኣብዛኛዎቻቸው ልማታውያን ስለነበሩ ሲያቀርብላቸው የነበሩ ጥያቄዎችም ልማታውያን ናቸው፡፡ ነገር ግን ኣንድ ሁለት የሚሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በተለይ ስለ መብራት ማቋረጥ፣ ወሃ እጥረት፣ የሞባይል ኔትወርክ ችግር፣ ስለነጋዴዎች ስጋት፣ ስለኢኮኖሚያዊ ሁኔታና ስለሚቀጥለው ምርጫ ዝግጅት — ወዘተ መጠየቃቸውና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ኣራባና ቆቦ የሆነ መልስ እንደ ተሰጣቸው ጆራችን ሰምተዋል፡፡

ስለሚቀጥለው ምርጫ የተነሳ ጥያቄ ሲመልሱ
ተቋዋሚ ፓርቲዎች በሚቀጥለው ምርጫ ወደ ፓርላማ እንዲመለሱ ምን የታሰበ ነገር ኣለ? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ “የሚወዳደር ኣካል ራሱ ኣዘጋጅቶ መቆየት ኣለበት ካልሆነ በኢህኣዴግ ለተቋዋሚ ፓርቲዎች የሚሰጥ ትሩፋት ኣይኖርም” የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥተዋል፡፡
ጥያቄው ግልፅና የማያሻማ ነበር፡፡ የጋዜጠኛዋ ጥያቄ ኣሁን ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ (በጣም ጦቦ) ወይ ደግሞ ኢህኣዴግ በራሱ ልክ የሰፋው የፖለቲካ ምህዳር ትንሽ ይሻሻል ወይም ቀዳዳ ይፈጠርለት ይሆን? እንዲሁም ተቋዋሚዎች በሄዱበት ሁሉ እየተከታተሉ ማዋከብና በፈጠራ ክስ ማሰርና ማስፈራራት ይቀንስ ይሆን ማለ~ ነው እንጂ በምርጫ ጊዜ በየትም ሃገር በገዢ ባርቲ ለተቋዋሚ ፓርቲዎች እንደ ዳቦ የሚከፋፈል ትሩፋት ወይ የፓርላማ ወንበር እንደሌለና ሊኖርም እንደማይችል ጠፍቶባት ኣይደለም ጥያቄው ያቀረበችላቸው፡፡

“የሚወዳደር ፓርቲ ራሱ ኣዘጋጅቶ መቆየት ኣለባት” ብሎዋል ጠ/ሚ ሃ/ማርያም፡፡ ጥሩ ኣባባል ነው፡፡ ነገር ግን በምን መልኩ መዘጋጀት እነደሚችሉ ቢነግ[ቸው ጥሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም፡

1/ ተቋዋሚ ፓርቲዎች ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጠቅመው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ በእርስዎና የእርስዎ ተከታዮች በተከለከሉበት ወቅት (ለምሳሌ ያኣንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ኣመራሮችና ኣባላት በክልሎችና በተለይ በኣዲስ ኣበባ ይህንን በመሞኮራቸው ስንቴ ታስረዋል ስንቴ ተደበድበዋል)፡

2/ ህዝብ በመሰብሰብ ኣላመቸውን ለማስተዋወቅ ፍቃድና መሰብሰብያ ኣዳራሽ ለጠየቁ ፓርቲዎች በእርስዎና በእርስዎ ተከታዮች ኣንዴ የሚጠብቅ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለት ኣንዴ ደግሞ ስራችን እያስፈታችሁን ነው በሚል ተልካሻና ኣስገራሚ ምክንያት በሚከለከሉበትና በሚታሰሩበት ይባስ ብሎም 5 ኪሎ ስንዴና ኣንድ ሌትር ዘይት ከቀበሌ በሚሰጣቸው ኑሮዋቸው በሚገፉ በኣንድ ለ5 ኔትወርክ ያታቀፉ የቀበሌ ሴቶችና ምንም ያማያውቁ ከእድሜ በታች የሆኑ ልጆች ሰብስባችሁ እንሰዲሰድብዋቸውና እንዲደበድብዋቸው እያደረጋችሁ ባላችሁበት ጊዜ (ለምሳሌ የዓረና ፓርቲ አመራሮችና ኣባላት በታህሳስና በጥሪ ወር በሽሬ፣ በዓዲ ግራትና በሑመራ) ፈሪውን ህ.ወ.ሓ.ት/ኢህኣዴግ ያደረገውን ኣፈና፡

3/ በሃገራችን ፖለቲካ ላቅ ያለ እውቀት ያላቸውና ለፖለቲካዊ ለውጥ ቆራጥ ኣቋም ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፈጠራ ክስ የፈረዳችሁባቸውና እያስፈራራችሁባቸው ባላችሁበት ጊዜ (ለምሳሌ በዚህ ሳምንት ያአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑ ኣቶ አስራት ጣሴና ወጣት ደራሲና ፖለቲከኛ ዳንኤል ተፈራ)፡

4/ የተቋዋሚ ፓርቲ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው በምክንያት እንዲባረሩና እንዲዋከቡ እያደረጋችሁ ባላችሁበት ጊዜ፡

5/ የሃገሪቱን መገናኛ ብዙሃን 24 ሰዓት በቁጥጥራችሁ ውስጥ ኣስገብታችሁ ለግለ ሰብና ለፓርቲዎች ስም ማጥፋት ዘመቻ በምታወልበት ሃገር፡

6/ ዜጎች የፈለጉትን ሃሳብ እንዳይገልፁና የፈለጉትን የፖለቲካ አቋም እንዳይኖራቸው በ1 ለ5 የስለላ ኔትወርክ ሰርታችሁ ነፃነቱ በነጠቃችሁት ህዝብ በአጠቃላይ መንግስት የመንግስት ስራ ትቶ የፓርቲ ስራ በሚሰራበትና መንግስት መንግስትነቱን ትቶ የተራ ሽፍታ ስራ በሚሰራበት ጊዜ እንዴት ኣድርገው ነው ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ራሳቸው ለውድድር መዘጋጀት የሚችሉት?

ሌላው ጠ/ሚ ደጋግመው ሲሉት የነበረ ጉዳይ ስለ ምርጫ ሂደት ነው፡፡ “ምርጫው ልክ እንደ ቅድሙ ሁሉ ነፃ፣ ፍትሓዊ፣ ዲሞክራስያዊና በህዝቡ ላይ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን እንደ መንግስት በቂ ዝግጅት እናደርጋለን” የሚል ኣስገራሚ ኣባባል ነበር፡፡

መቼ ነው ኢህኣዴጎች ከረጆ ከመስረቅ (ከመቀየር)፣ የተቋዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎ ኣስፈራርቶ ከማባረር፣ ህዝብ በነፃነት እንዳይመርጥ ከማስፈራራትና ከመደለል እንዲሁም ከማደናገር ኣልፋችሁ ነፃ፣ ፍትሓዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄዳችሁት? መቼ ነው በህዝብ ላይ ተኣማኒነት ያተረፈ ምርጫ ከንግግር ኣልፎ በተግባር የተደረገው?

በ1997 ዓ/ም ኣንፈልጋችሁም ብሎ ድምፁ ለነፈጋችሁ የኣዲስ ኣበባ ህዝብ ጥይት ያጎረሳችሁት ረስታችሁታል ማለት ነው? የወጋ ቢረሳ የተወጋ ኣይረሳምና ጠ/ሚ ሃ/ማርያም በኣጠቃላይ ኢህኣዴጎች የምትናገሩትና የምትሰሩት ፍፁም ስለማይገናኝ ይህ ኣይነት ቁማር በመጨረሻ ላይ ለናንተም ጠቃሚ ስላልደለ የኢትዮጵያ ህዝብ ህገ-መንግስታዊ መብቱ ተጠቅሞ የፈለገውን ሃሳብ በነፃነት እንዲያራምድ፣ እንዲሰበሰብና ኣቋሙ በሰላማዊ ሰልፍ እንዲገልፅ ብትፈቅዱለት ጥሩ ነው፡፡ ካልሆነ ህዝብ ኣፍነህ ለመግዛት መመኮር የቱንዝያ፣ የግብፅና የሊቭያ የቀድሞ ዲክታተር መሪዎች መጨረሻ ላይ እንዳላማረባቸው ከዚህ ይማረን እያላችሁ ስትከታተሉት የነበረ የትናንት ሓቅ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም ትእግስተኛና ኣስተዋይ በመሆኑ እስካሁን ትእግስቱ ኣማጥጦ በመጠቀም የታገሰ ነው ያለው፡፡ ነገር ግን ትእግስት መጠን ኣለው፡፡ ስለዚ ትናንት ነገ ስለማይሆ ትእግስቱ ተማጥጦ እንዲያልቅ ባትገፋፉት ጥሩ ይመስለኛል፡፡
በሃይል ለመግዛት መሞከር የውድቀት ምልክት ነው!!

መኢአድና አንድነት ፓርቲ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡
ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሰጠ መግለጫ !!!!
ብአዴን ኢህአዴግ የአማራን ህዝብ የመምራት የሞራል ልዕልና የለውም፤ ህዝብ ያዋረዱ አመራሮቹም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል፡፡

Image
የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚገነዘበው በዚህች ታሪካዊት እና የጥቁር ህዝብ ድል ማዕከል፤ የነፃነት ተምሳሌትና የአፍሪካ ህዝብ ኩራት በሆነች ሀገር የኋላ ዘመን ውጣ ውረድ ውስጥ ሰፊው የአማራ ህዝብ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአንድ ተሰልፎ ለሀገር ግንባታ ተኪ የሌለው ሚና ተጫውቷል፡፡ በዚህም የተነሳ በአምባገነኖች ጡጫ ተደቁሷል፡፡ ዛሬም እንደ ትላንቱ በገዢዎቹ እየተረገጠ ያለ ህዝብ ነው፡፡
ይህ ህዝብ እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም በየጋራው እና በየሸንተረሩ ተበታትኖ የኔ እንዳይላት እንኳን በተነፈገው ኩርማን መሬት አፈር እየገፋ ለመኖር መዳረጉ ሳያንስ የኢህአዴግ ፖለቲካ ሌላ ሰቀቀን ጨምሮ ‹‹ጨቋኝ ገዥ መደብ የነበረ፤ ትምክህተኛ›› በሚል ጎራ መድቦ ያልዘራውን ግፍ እንዲያጭድ እያደረገው እንደሆነ ይስተዋላል፡፡
የአማራ ህዝብ እንደሌላው ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ዘመኑ ባነበራቸው የአገዛዝ ሥርዓቶች የጭቆና ቀንበር ተጭኖት፤ የግፍ ፅዋ የተጋተ መሆኑ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተሰወረ አይደለም፡፡
ይሁን እንጂ ይህንን ህዝብ እወክላለሁ የሚለው የትላንቱ ኢህዴን የዛሬው ብአዴን ያፈራቸው አመራሮች ስልጣን በመቆናጠጥ የገዛ ህዝባቸውን ከመናቅና ከማዋረድ አልፈው ‹‹ትላንት ሽርጣም ያለህ ትምክህተኛ አንገቱን ይድፋ ዛሬ ተራው ያንተነው›› በማለት በግፍ እንዲገደል ማድረጋቸው ሰቆቃው ከህዝብ ህሊና ሳይወጣ አቶ መለስ ‹‹ጫካ መንጣሪ ሞፈር ዘመት›› ብለው እንደተሳለቁበት ሁሉ በሳቸው ራዕይ አስቀጣይ በዛሬዎቹ የብአዴን አመራሮችም ያው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ አገዛዙ የደረሰበትን አሳፋሪ ደረጃ በግልፅ ያሳያል፡፡
የክልሉ ምክትል ፕሬዘዳንት እና የብአዴን ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን በቅርቡ አደረጉት ተብሎ የተደመጠው አስነዋሪ ንግግርም የክልሉን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ የናቁ እና ያዋረደ፤ የሀገሪቷን ህገ- መንግስት በግልፅ የጣሰ የወንጀል ተግባር ነው፡፡ በተጨማሪም የአማራን ህዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ ለመነጠልና አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር የተደረገ ዘመቻ ነው፡፡
የኢህአዴግ አገዛዝ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከተጫነበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም ክልል ያለው ህዝብ በራሱ ቋንቋ ተናጋሪዎች በግፍ እየተገዛ፤ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተገፍፎ በድህነት አረንቋ ውስጥ እየኖረ ቢሆንም የአማራን ህዝብ እንወክላለን እንደሚሉት ብአዴኖች የሚመራውን ህዝብ በአደባባይ በተደጋጋሚ የዘለፈ፤ ያዋረደ እና አንገት ያስደፋ ድርጅት አለ ለማለት ይቸግራል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የአማራን ህዝብ የመምራት የሞራል ልዕልና የሌለውን ብአዴን ኢህአዴግን ለመታገል መላውን አባላትና ደጋፊዎቻችንን ከጎናችን በማሰለፍ በፅናት እና በብቃት መታገል ያለብን ወሳኝ ጊዜ ላይ እንደሆንን እንገነዘባለን፡፡
መላውን ህዝብ ከዳር እስከ ዳር አንቀሳቅሰን ሰላማዊ ትግሉን ፍሬያማ በማድረግ አገዛዙ እንዲለወጥ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ የጀመርነውን ሰላማዊ ትግል አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እያረጋገጥን የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በስርዓቱ ላይ ያለንን ተቃውሞ እናሰማለን፡፡ ይህ ትግል ህዝብ ያዋረዱ አመራሮች በተገቢው ፍጥነት ለፍርድ እስኪቀርቡ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የባህርዳር እና አካባቢው ነዋሪዎችም በነቂስ በመውጣት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተቃውሞውን እንዲገልፅ ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ድል የህዝብ ነው !!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
የካቲት 6 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

:evil:
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ልብ ብለው ከሆነ በዚህ ሳምንት ሕወሓት/እሕኣዴግ በሁለት ጉዳዮች ላይ ተመርኩዞ የተለይዩ ተግባራትን ከውኖ ራሱን አጋልጦ አደባባይ ላይ አምባገነንነቱን አስመንጥሮ ተሽከርክሮ አሸባሪነትን እና አሸባሪዎችን እንዳቀፈ ጉዞውን እየተንገዳገደው ነው::

ሕወሓት በዚህ ሳምንት የራሱ የውስጥ ሽኩቻ እና የኢሕኣዴግ አባል ድርጅቶች የለውጥ እንቅስቃሴ አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተቱት ለመውጣት በሚይደርገው መፍጨርጨር ሌላ አዳዲስ የሽብር ድርጊቶቹን ማንገውለል ይዟል:: ያው እንደተለመደው ድሮም እጆች ሁሉ ወደ ሕወሓት ቢያመለክቱም የአሁኑ ለየት ብሎ የራሱን ጣቶች ወደ ራሱ መቀሰሩ ነው::

ሕወሓት/ኢሕኣዴግ እና የሙስሊሙ ጥያቄዎች
ኢሕኣዸግ በህገመንግስቱ መሰረት በወንጀል መከሰስ አለበት::

ሓይማኖት እና ፖለቲካ እንደማይገናኙ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ በሕገመንግስቱ የተረጋገጠ ጉዳይ መሆኑ እየታወቀ በገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው ወንጀል በሕገመንግስቱ መሰረት ወንጀለኛው ሕወሓት/ኢሕኣዴግ መሆኑ በይፋ ተረጋግቷል:: እስካሁን ድረስ መልስ ያልተገኘለት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄ በመንግስት ማነቆ እና በባለስልጣናቱ ሽብር የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ንጽሕናቸው እየታወቀ ወህኒ ቤት አስቀምጦ የራሱን ፖለቲካዊ መጅሊስ መገንብቱን በይፋ አምኗል:: በሽብር ስልት የገነባው መጅሊስ ላለው ስርኣት ትዛዥ የሚሆን እና የፖለቲካ ታማኞችን ያቀፈ መሆኑ በይፋ ማመኑ ሕወሓት ምን ያህል በሃይማኖቶች ውስጥ አብዮታዊ ዲሞክራሲን አስርጾ ለአገዛዙ በሚያመቸው መንገድ እንደቀረጸው አመነም አላመነም የታወቀውን ጉዳይ ግን በአቦይ ስብሃት በኩል ዘርግፎታል::ከቦሌ የተፈጠረው ሕገወጥ መጅሊስ በህያሉ እና አሸባሪው ሕወሓት እና መሪዎቹ ተጀምሮ እና ተስፋፍቶ እስከሽልምት ደርሶ መንግስት ሕገመንግስቱን እንደጣሰ እና በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ እንደገብ ሲያረጋግጥ የሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ንጽሕና እንዳመነ እና ሴራው ለሽንፈት እንደዳረገው ተረጋግጥውል::

ሕወሓት ቅጥረኞቹ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች

እንደፈለጉ ቢናገሩ የማይታሰሩ ሰዎች አሉ አዎ አሉ ከተቃዋሚ ፓርቲ ከጋዜጠኞች እንዲሁም ከሌላው ዘርፍ…ስም መጠቃቀስ አስፈላጊ ባይሆንም ሕወሓት ይህን ሰሞን በየፓርቲው አስርጎ ባስገባቸው ቅጥረኞቹ አማካኝነት..የኣንድነት ኣባላትን
በፓርቲው ውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን እና ለገዢው ፈታኝ የሆኑ የፖለቲካ ሃሳቦችን የሚያመነጩትን ለይቶ …እንዲሁም የማይታሰሩ እንደፈለጉ የሚለፈልፉ እና የሚጽፉ ጋዜጠኞች እንደ እስክንድር ነጋ ያሉትን ጠንካሮችን አሳልፈው በ24 ሰዓት ያስያዙ ….. አሁንም ሌሎችን ከፕሬሱ እንዲወገዱ የሚሰሩ አስመሳዮች ወዘተ…..

የኣንድነት አመራሮች በሰበብ አስባብ የጻፉትን ጹሁፍ ተገን በማድረግ እና የፈጠራ ምርመራ ጀምሮ ለማዋከብ እና ለማወናበድ እንደገሃዳዊ ምክንያት ተያዘ እንጂ ዋናው የስርኣቱ አላማ ጠንካራ አመራር አባላትን በማሰር ከወዲሁ ፓርቲዉን ለማዳከም የታቀደ እና በውስጥ ቅጥረኞች እየተሰራ ያለው የብተና እና ፓርቲውን በቅጥረኞች ቁጥጥር ስር አውሎ ፓርቲውን ታማኝ ተቃዋሚ ለማድረግ የታቀዳ ሴራ ነው::

የሃይለማርያም መለሳዊ መግለጫ

ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን የህዳሴ ግድብ ግንባታና ከሱዳንና ግብጽ ጋር ያለውን ድርድር አስመልክቶ ድርድሩ እንዳላለቀ ፣ የኢትዮ ሱዳን የድንበር መካለልን በተመለከተ እየተናፈሰ ያለውን መሬት ለሱዳን ተሰጥቷል የሚለውን ወሬ አስመልክቶም ይህን መሰል ወሬዎች ምርጫ ሊደርስ አካባቢ መነዛታቸው አዲስ አይደለም ያሉ ቢሆንም የድንበሩን ጉዳይ በተመለከተ ካርቱም ሄደው የፈረሙት ፊርማ ሳይደርቅ እንደለመዱት ዘባርቀዋል::

እስከ 6 ወር ድረስ ህዝቡ ይዘናጋል በሚል እደምታ መግለጫቸውን የሰጥኡት የሕወሓቱ የሃሰት ስልጡን ሓይለማርያም የቴሌኮም ችግር በማስፋፊያው ስራ ሳቢያ የተፈጠረ ነው ከ6 ወራት በኋላ ለውጥ ይታያል ሲሉ ሰው ይታዘበኛል ያልፈጠረባቸው አቶ ሃይለማርያም አይን ቀቅለው ሳያበሏቸዋልቀሩም መሰል የአዲስ አበባ የውሃ ችግርንም በተመለከተ 24 ሰዓት ውሃ የሚያገኘው የከተማዋ ክፍል 75% ብቻ እንደሆነና የተቀረውንም ለማስተካከል መንግስት ይሰራል በማለት ከባድ የሆነ ውሸት ለጥፈው ዞር ብለዋል:: የውጭ ምንዛሪ እጥረትንና የባንኮች የብድር መስጠት ብቃት መመናመንን አስመልክቶ የተነሳውን ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትሩየእውቀት እጥረት ይሁን ሃቅን ማድበስበስ በቂ ማብራሪያ አልሰጡበትም፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ

የካቲት 11 የተፈበረከው ሕወሃት ማለት እጅግ አሳፋሪ እና አሸባሪ የማፊያ ድርጅት ነው::

ሕወሓት ….. በምንሊክ ሳልሳዊ
= ህጻናትን በማደጎ እና በጉዲፈቻ ስም ይቸበችባል:: እንዲሁም በወሲብ ንግድ ውስጥ በመሰማራት
በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የደላላ ኤጀንቶችን በማቋቋም ታዳጊ ወጣት ሴቶችን
ለሽያጭ ::ባለስልጣናቱ በብዙ መቶ ሺዎች ዶላሮች አፍሰዋል ::

= በስሩ ያደራጃቸውን ቡድኖች የዲፕሎማቲክ ካባ በማልበስ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ላይ እንዲሰማሩ እና ዲፕሎማቶች ከፍተሻ ነጻ ስለሆኑ በረቀቀ ስልት ካናቢስ ሃሺሽ እና መሰል ድራጎችን በማዘዋወር ስራ እና ንግድ ላይ ተሰማርቷል::

= ህገወጥ የሰው ዝውውር እና የአካላት ስርቆት ድርጊቶችን ይፈጽማል:: ወደ ተለያዩ የመካከለኛ ምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ የመሳሰሉ ሃገራት በህገወጥ መንገድ ሰዎችን በማዘዋወር ከባድ ወንጀል እየተሰራ ሲሆን ይህንን ስራ የሚሰሩ አካላትን ሰርቀው ሰውን በመግደል የሚከብሩ ደላሎች ከባለስልታናት ትእዛዝ የሚወርድላቸው እና ሕወሓት በአባልነት የመዘገባቸው ነው::

= በግብጽ እና በየመን በረሃዎች እንዲሁም በሱዳን ሊቢያ ድንበር ላይ ስደተኞችን በማፈን የተለያዩ የገንዘብ መጠኖችን በመጠየቅ ቤተሰብን በማስጨነቅ ሴቶችን በመድፈር አከላትን አውጥቶ በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማሩት የሕወሓት አባላት የሆኑ ግለሰቦች ናቸው::

= የአገሪቷን መሬት ለውጭ ባለሃብቶች በመሸጥ ወገንን ለስራ ጥነት ለስደት ለመፈናቀል የሚዳርጉት በሕወሓት ሃይሎች የሚመሩት በአቋራጭ የከበሩ አባላቱ ናቸው::ከተላያዩ አከባቢዎች ለውጪ ኢንቨስተሮች በሚል ስም የተሸጡ መሬቶች የሽያጭ ገቢያቸው የት እንደሄደ እንደማይታወቅ እና ሸጡ የተባሉት ክልሎች እንኳን ለአከባቢው ነዋሪዎች ካሳ ያልከፈሉበት እና ያላቋቋሙበት ሁኔታዎች በገፍ ታይተዋል::

= በተለያዩ ጊዜያት በአዲስ አበባ እና በክልሎች ቦንቦችን በማፈንዳት ንጹሃን ዜጎችን በመግደል እና በማቁሰል የሽብር ስራ ላይ የተሰማራው ሕወሓት የተቃወሙትን ሁሉ የሚወነጅልበት አንዱ ብልሃቱ ቢሆንም ሞኝነቱ አዘንብሎ ተገኝቷል::አልቸባብን እና ሃማስን ከመሳሰሉ አሸባሪ ከሞባሉ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮች ምስጢራዊ ስምምነት በመፍጠር ምስራቅ አፍሪካ እና መካከለጫው ምስራቅ ላይ ከፍተኛ ስጋት ለመፍጠር እና ዜጎቹን ለማስፈራራት እጅግ አሳፋሪ እና ዘግናኝ ድርጊቶችን ፈጽሟል: በመፈጸም ላይ ይገኛል:: ምንሊክ ሳልሳዊ

ብልህ የጥንቶቹንም ለመከተል አይፈልግም፤ ዘልዓለማዊ ነው የሚባል ደረጃ ለመመደብም ሆነ ለማስቀመጥ አይሻም፡፡ ይልቁንም የራሱን ዘመን መርምሮ ለዚያ የሚያዋጣውን ዘዴ ይዘይዳል፡፡“የብልህ አመራር ማለት ገዢው የሱ ሰዎች ልክ እሱ ያዘዘውን ያሰቡ እንዲመስላቸው ማድረግ ነው፤” ትላለች የሩሲያዋ ታላቋ ካቴሪን፡፡ ቀጥላም “ይሄን ለማድረግም፤ አንድ እርምጃ ከህዝቡ ፍላጐት መቅደምና ከአልቀበል – ባይነቱ ጋር መላመድ ነው” ትለናለች፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል! ራመድ ብለን የንግሥቲቱን አካሄድ ስንመረምር ለውጥን ያለጉልበት በዘዴ እንዴት ለማምጣት እችላለሁ? የማለት፤ ጥበባዊ ፍላጐትን የመቀዳጀት ጥያቄን ይሰርጽብናል፡፡ የኛ ዕቅድ፣ መርህ፣ ስትራቴጂ ወዘተ. ከሰማይ በወረደ ኃይልም አይታጠፍም፣ አይቀየርም፣ የምንለውን፤ በልባምነት አውጠንጥነን እንድናይ የሚያግዘን አስተውሎት ነው፡፡

ተቃዋሚዎቻችንን ወይም በግልባጩ ገዢዎችን የምናይበትን ሁኔታ በሁለት ታዋቂ የሰንጠረዥ ጨዋታዎች ምሳሌነት ለማፀኸየት እንሞክር፡፡ አንደኛው፤ ቼዝ ነው፡፡ ሁለተኛው፤ ጐ የሚባለው ጨዋታ ነው ፡፡ ቼዝ ጨዋታ፤ በጠባብ ሜዳ የምንጫወተው ሠንጠረዥ ነው፡፡ 32 ጠጠሮች አሉት – አለቃና ምንዝር የሆኑ። ከሁለቱም ወገን የሚሠለፉ፡፡ የቼዝ ጨዋታ የጠላትን ወታደርና መኮንኖች ግንባር ለግንባር እየገጠሙ መደምሰስ ነው፡፡
በአንፃሩ በ “ጐ” ጨዋታ፣ ከቼዝ ስድስት ጊዜ በሰፋ ሰፊ ሜዳ በየጐራው 52 ጠጠሮችን በጥቁርና በነጭ አሰልፎ መፋለም ሲሆን፤ ዘዴው እያንዳንዱን ጠላት በመክበብ ከእናት ክፍሉ ለይቶ መጠጊያ ማሳጣት ነው፡፡ ከዚያም እንዲሟሽሽና ሽባ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

በሰፊው ማሰብ፣ ትንሽ ቦታ ሰውቶ፣ ቀስ በቀስ ሰፊ ቦታ መያዝ፤ በመጨረሻም ማሸነፍ ነው፡፡ ሁለቱን ስልቶች ጠንቅቆ ማወቅ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ሠንጠረዥ እጅግ ጠቃሚ ነው! ቅልጥፍናን ከገዢ መሬት በላይ የማየት ክህሎት ይኑርህ ነው ነገሩ!
እጅ መስጠት የሚጀምረው ከአንጐል ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ አስቀድመህ የባላንጣህን አዕምሮ ክበብ ይላሉ፤ የፖለቲካ ፀሐፍት ቀስቅስ፣ ግንዛቤ ፍጠር፣ አንቃ ነው፡፡ የማዖን የጦር ዘዴ ለአዕምሮ ጦርነት ማሰብ ድንቅ ነው፡፡

“ጠላት ሲገፋ አፈግፍግ፡፡ ጠላት ካምፕ ውስጥ ሲያርፍ እረፍት – ንሳው፡፡ ጠላት ሲዳከም አጥቃው፡፡ ጠላት ሲያፈገፍግ አንተ ግፋ፡፡” ዘመኑ የአዕምሮ ትግል ወቅት ነውና አዕምሮህን አስላ፡፡ እቅድህን አጥራ፡፡ ስትራቴጂህን በጥንቃቄ ቀንብብ እንደማለት ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ከብጤህ፣ ከእኩያህ፣ ከአምሳያህ፣ የፖለቲካ አዕምሮ – ፈርጁ ከአዐምሮ – ፈርጅህ የሚጣጣም የፖለቲካ ባልንጀራ አበጅተህ ወቅቱ በሚፈቅደው ዛፍ ጥላ ሥር ሆነህ፣ ንጋት፣ ቀትርና ጨለማ ለይተህ፣ መጓዝ እንዳለብህ ማወቅ ነው ታላቁ ቁምነገር፡፡ እንዲያው በጥቅም – ቀደም – አካሄድ ለእለት – እንጀራ የተጐዳኘኸውን ወይም ብረት – ድስትና ሸክላ – ድስት ሳትለይ የተወዳጀኸውን ሁሉ የፖለቲካ ወዳጄ ነው ብለህ ከተጓዝክ “ከማይመጥነው ሰው ጋር የሚካኤል ማህበር ጠጣ፤ ተራውን ሳያጠጣ ሞተ” ከመባል አታመልጥም!!#MinilikSalsawi

“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግንበነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት … ዶናልድ ያማሞቶ ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በመንታመንገድ ላይ ነች ብለኸን ነበር መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከመንገዱ ላይ ገለል በሉልን” አቶ ኦባንግ ሜቶ
እንዴት እዚህ ተደረሰ?

የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድርጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም እነዚህን ጉዳዮች ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ ስም (ህወሃት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው።

ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱም አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል። ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረው ነበር።
ኢህአዴግ ከአሜሪካ ጋር የመሰረተው ግንኙነት ከቶውንም ንፋስ እንደማይገባው ተከታዮቹ ሙሉ በሙሉ ያምናሉ። በተለይም የህወሃት ሰዎች አሜሪካ ከህወሃት ጋር ያሰረችው ቀለበት የሚወይብ አይመስላቸውም። የአሜሪካና የ”ህወሃት ፍቅር” ትምክህት የሆነባቸው የአሜሪካን ባለስልጣናት ህወሃት ኢትዮጵያን እስከ ዘላለም እንዲመራ ልዩ ቅባት እንደቀቡት የሚናገሩም አሉ። አሜሪካ ለህወሃት/ኢህአዴግ የምትሰጠው ጭፍን ድጋፍ ሊጤን እንደሚገባው በማሳሰብ ተስፋ ሳይቆርጡ የታገሉና የሚታገሉ ደግሞ ይህ ትምክህት አንድ ቀን እንደሚተነፍስ በእምነት ሲናገሩ ቆይተዋል።

ኢህአዴግን በዲፕሎማሲና በሰከነ የትግል ስልት መታገል ይበልጥ አዋጪ እንደሆነ ከሚያምኑት ወገኖች መካከል አቶ ኦባንግ ሜቶ ቅድሚያውን ይይዛሉ። አቶ ኦባንግ የሚመሩት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የሚያራምደውን እምነት አስመልክቶ “ከወረቀትና ፒቴሽን ከማስፈረም ያልዘለለ” በማለት የሚቃወሙና የሚተቹ የመኖራቸውን ያህል ልብና ቀልብ ሰብስበው የሚከተሏቸው ወገኖች ቁጥር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው። እምነትም እየተጣለባቸው ነው።

በወገኖቻቸው ብቻ ሳይሆን በውጪው ዓለም ያላቸው ተቀባይነት፣ ብሎም አመኔታ እንዲሁ ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ ወኪል ተደርገው እየተወሰዱም ነው። አቶ ኦባንግ ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ ታላላቅ መድረኮች ሲሳተፉ የሚያቀርቧቸው ንግግሮችም ቀልብ የሚገዙና መልዕክታቸው የሰፋ በመሆኑ ሰፊ አድማጭ አላቸው። ሰሞኑንን በአሜሪካ ምክርቤት (ኮንግረስ) የጸደቀውን ድንገተኛ ውሳኔ አስመልከቶ “ኢህአዴግ ሳይወድ በግዱ በሩን በርግዶ ይከፍታል” ባይ ናቸው። ውሳኔውንና የውሳኔውን አካሄድ ከአነሳሱ ጀምሮ ጠንቅቀው እንደሚያውቁት ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አሜሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው እንዲሁ ከመሬት ተነስታ ሳይሆን በከፍተኛ ትግል ነው። ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል የአውሮፓ አገሮችም የአሜሪካን ፈለግ እንዲከተሉ ሥራችንን አጠናክረን ጀምረናል” ብለዋል።
አዲሱ ውሳኔ ሕግ እና የኢህአዴግ ህልውና!

እያነጋገረ ያለው የእርዳታን አጠቃቀም አስመልክቶ ጥር 31 ቀን 2014 በአሜሪካን ኮንግረስ የፀደቀው አዲስ ውሳኔ ሕግ ነው። ውሳኔው አሜሪካ የምትሰጠው ርዳታ በትክክል ህዝብን ሳይጎዳ በስራ ላይ መዋሉንና አለመዋሉን እንዲቆጣጠር ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መ/ቤት (State Department) ትዕዛዝ የተላለፈበት ነው። እንግዲህ ይህ ትዕዛዝ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የሚነሱት መከራከሪያዎች በርካታ ቢሆኑም በምላስ “ነጻ ነኝ” የሚለውና በግብር “ለጌቶቹ ጥሩ ባሪያ” በመሆን 22 ዓመት የዘለቀው ኢህአዴግና ከአሜሪካ ግንኙነታቸው በነበረበት መንገድ ስለመዝለቁ ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ። አሜሪካ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው በወፍ ዘራሽ ሳይሆን በሂደት እንደሆነ በመጥቀስ አቶ ኦባንግ ሜቶ ከሚያቀርቡት ሃሳብ ጋር ይስማማሉ።

የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መረጃ ላይ ተንተርሰው ለሚያወጡት ሪፖርት “ተራ የማበሻቀጪያና የማጣጣያ” መልስ በመስጠት፣ ሲለውም ተቃዋሚዎችን የሚደግፉና የኢህአዴግ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እምነት /የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና/ “ቅንቅን” የሆነባቸው የምዕራብ አገራት “ተላላኪ” በማስመሰል አሁን ድረስ ሲዘልፋቸው መቆየቱ አይዘነጋም። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት አሁን አዲስ ለጸደቀው የአሜሪካ ቅድመ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የርዳታ መርሃ ግብር እነዚህ ክፍሎች በቁጥጥርና በክትትል በኩል ሪፖርታቸው ዋና ግብዓት ስለሚሆን ኢህአዴግ መንታ ፈተና ውስጥ እንደሚወድቅ ቅድመ ትንበያዎች አሉ።

በዚሁ መነሻ ኢህአዴግ የህልውናው መሰረት የሆነውን እርዳታ ለማግኘት “የፖለቲካ አመለ ሸጋ ሆኖ የዘጋቸውን በሮች ከፍቶ የሚመጣውን የህዝብ ወሳኝነት መቀበል፣ አሊያም በሂደት ሰልሎና ተሽመድምዶ መክሰም የመጨረሻው እድል ፈንታው ይሆናል” የሚሉ ወገኖች ጥቂት አይደሉም።

ኢህአዴግ በመንታ መንገድ ላይ – የህጉ ተጽዕኖ ከፖለቲካና ኢኮኖሚ አንጻር
ውሳኔውን ከፖለቲካው እንደምታና ከኢኮኖሚው ጣጣ ጋር በማያያዝ አስተያየት የሰጡን እንደሚሉት ከሆነ ጉዳዩ አደጋ አለው። እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጠቅላላው የምዕራብ መንግስታት ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕርዳታ በየዓመቱ ያገኛል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ ከአጠቃላይ አመታዊ በጀቱ 50% የሚሆነውን ይሸፍንለታል። ከአሜሪካን ብቻ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር በየዓመቱ በዕርዳታ መልክ ያገኛል። ይህም ከአሜሪካ የሚገኘው ርዳታ ብቻውን የበጀቱን አንድ ሶስተኛውን ይሸፍንለታል።
በዚህ መነሻ የኮንግረሱ ውሳኔ በኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ እንደሆነ በጀርመን የልማት ኢኮኖሚክስ ባለሙያው (Development Economist) ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ይናገራሉ። ይህ እሳቸው “ዱብዕዳ” ያሉት ውሳኔ የፖለቲካ ውዝግብ ማስነሳቱ የማይካድ ነው። ኢህአዴግ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የሚያገኘውን ድጎማና ርዳታ ለምን ተግባር ሲያውለው እንደነበር ከማንም በላይ ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ከቅድመ ሁኔታ ጋር የተያያዘ የዕርዳታ አሰጣጥ ከኢኮኖሚ ይልቅ የፖለቲካና የስነልቦናው ተፅዕኖው እንደሚያስከትልበት እኚሁ ምሁር ያስረዳሉ።

ከአጠቃላዩ የማክሮ ኢኮኖሚ አንጻር ውሳኔው ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ በዝርዝር በማስቀመጥ አስቀድሞ መናገር ባይቻልም አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል መገመት እንደማያዳግት ዶ/ር ፈቃዱ ከጎልጉል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። “ከአጭርና ከመካከለኛ ጊዜ አንፃር ስንመለከተው የአገዛዙን የኢኮኖሚ አካሄድ ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ ይችላል” ያሉት ባለሙያው፣ “… ወደፊት አዳዲስ የስራ መስክ መክፈት፣ በኢኮኖሚው ዕድገት፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝትና በውጭ ሚዛን ዕድገት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተፆዕኖም ቢሆን ይህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። ይሁንና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እርስ በርሱ የተያያዘ ስላልሆነና፣ አብዛኛው ህዝብም በኢንፎርማልና ከእጅ ወደ አፍ በሚገኝ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚተዳደርና የሚሳተፍ ስለሆነ ሊጎዳ የሚችለው በዘመናዊ መስክ የተሰማራውን ሰራተኛና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ነው” በማለት ቅድመ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።

ሲያብራሩም ከቅድመ-ሁኔታና ከጥብቅ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ በዕድገት ስም የሚፈስ ዕርዳታ በአጠቃላይ ሲታይ በህዝቡ ኑሮ መዛነፍ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ዝቅተኛ መሆኑንን የሚያመለክቱት ዶ/ር ፈቃዱ፣ ከ10-11በመቶ “ያለማቋረጥ” አደገ በሚባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ መሻሻል ጋር ተያያዥነት እንደሌለው ይናገራሉ። ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠለት እርዳታ ቢቀነስ ወይም እንዳለ ቢታገድ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ በቁርጥ ማስቀመጥ እንደሚያዳግትም ባለሙያው ይጠቁማሉ። በዚህ ዓይነቱ የዕርዳታ አካሄድ እስካሁን የተጎዳው ህዝብ በመሆኑ የዕርዳታው መቀነስ ወይም መታገድ አገዛዙን እንጂ በዚያ አካባቢ የሚኖረውን ህዝብ በቀጥታ የሚመለከት አይሆንም። በህዝብ ኑሮ ላይ የሚከተለውን ማህበራዊ ኪሳራ ተምኖ ማስቀመት ቢችግርም “ወያኔ ቅድመ ሁኔታውን ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ በተለይም በቀጥታ በኗሪው ህዝብ ህይወት ላይ አዎንታዊ ውጤት ማሳየቱ ግን የማይቀር ነገር ነው” ሲሉ ግርድፍ ምልከታቸውን ያኖራሉ። በሴፍቲኔት፣ በአነስተኛና ጥቃቅን፣ ወዘተ የህዝቡን ኑሮ እየቀየርኩ ነው የሚለው “ልማታዊው” ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነት በቅድመ ሁኔታ የተወጠረ ዕርዳታ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ቀውስ ያመጣል በማለት የራሱን ቅንብር እንደሚሰራ የሚከራከሩም አሉ፡፡

ፖለቲካዊ ይዘቱን የዳሰሱት ዶ/ር ፈቃዱ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን በመጠቆም ለውይይት የሚጋብዝ ፍንጭ ሰጥተዋል። “ውሳኔ ሕጉ ያካተታቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከረዥሙ አጠቃላዩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር ስናየው ግን በዕውነቱ እንደዚህ ዓይነቱ ከቅድመ-ሁኔታ ጋር የተያያዘ ዕርዳታ ላይጎዳው ይችላል። አገዛዙ ከምዕራቡ አገራት የሚመጣበትን ግፊት የሚቋቋም መስሎት የሚታየው ከሆነ ፊቱን ወደ ቻይናና ወደ ሌሎች ቅድመ ሁኔታን ከማያሰቀድሙ አገሮች ዕርዳታ በማግኘት ከአሜሪካን የሚሰጠውን ዕርዳታ ሊያካክስና በነበረበት ሁኔታ ለመቀጠል መንፈራገጡ” አንደማይቀርም አመላክተዋል። ይህ ግምታቸው ግን ጥርጣሬያቸው እንዳለ ሆኖ ነው።

“ኢትዮጵያ ካለችበት የጂኦ ፖለቲካ፣ የአፍሪካ ህብረት ዕምብርትና መቀመጫም ስለሆነች ቻይናዎች ከራሳቸው የንግድ መርህ አንጻር ዕርዳታውን ከመስጠት ወደኋላ ሊሉ አይችሉም” ሲሉ የጉዳዩን ሌላ መልክ ያሳዩት ዶ/ር ፈቃዱ፣ አማራጩ ከአሜሪካንም ሆነ ከተቀረው የምዕራቡ ዓለም ጋር ተላትሞ ወደ ቻይና ፊትን በማዞር የሚደመደም ከሆነ አገዛዙ ዕድሜውን ለማሳጠር ራሱ እንደወሰነ የሚቆጠርበት ይሆናል። ኢህአዴግ አምርሮና የመጣው ይምጣ በሚል ቅድመ ሁኔታዎችን አላሟላም፣ ዕርዳታችሁንም አንፈልግም የሚል ከሆነ አሜሪካን አማራጭ ለመፈለግ ልትሞክርና ይህንንም እንደማስፈራሪያ ተጠቅማ ልትለሳለስ” እንደምትችል ዶ/ር ፈቃዱ አመላክተዋል።

እንደወያኔ የሚታዘዝላት ድርጅትና መሪ እስካላገኘ ድረስ ኢህአዴግ ላይ አደጋ እንዲነግስ ወይም ከነጭራሹ እንዲወገድ አሜሪካ ትሰራለች ብለው እንደማያምኑም ገልጸዋል። “እንዲያውም” አሉ ዶ/ር ፈቃዱ “በኮንግረሱ የፀደቀው ህግና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (State Department) እንዲቆጣጠረው የተደረገው የዕርዳታ አሰጣጥ ዘዴ፣ የኦባማ አስተዳደር ሌላ መንገድ ፈልጎ ኮንግረሱን በማለፍ፣ በቀጥታ ከአሜሪካን የውጭ ዕርዳታ አሰጣጥ ጋር ባልተያያዘ መንገድ የኢህአዴግን አገዛዝ በተዘዋዋሪ ሊረዳበት የሚችልበት መንገድ እንደሚኖር መጠራጠር ይቻላል” ሲሉ ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ገደቡ በተለይም አገዛዙ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰላም ጥበቃን፣ የፀረ-ሸበርተኝነትን፣ የድንበር ጥበቃንና እንዲሁም የመከላከያ አዛዡን ስታፍ ሰራተኞች ስለማይመለከት ተጽዕኖው በወታደሩ ላይ ዝቅ ያለ መሆኑንን አንደማሳያ ይጠቁማሉ።

ፍርድ ቤቶችን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ቁጥጥር ስር ውጭ ማድረግ፣ የሚዲያ፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና የመሰብስብ ነፃነት፣ እንዲሁም ሌሎች በቅድመ ዕርዳታው መስፈርት ሆነው የተዘረዘሩትን አንኳር ጉዳዮች ኢህአዴግ አጥብቆ የሚፈራቸውና ህልውናውን አደጋ ላይ የሚጥሉት በመሆናቸው በቀላሉ ለመቀበል የሚያዳግተው መስፈርቶች እንደሆኑ ለማንም ግልጽ ነው ሲሉ ዶ/ር ፈቃዱ ተናግረዋል። ይልቁኑም “እስካሁን ድረስ ለምን ዘገዩ? የሚመለከተው አካልም ሆነ የኦባማ አስተዳደር እስካሁን ድረስ ምን አስጠበቃቸው? አሁን ምን አዲስ ነገር ታያቸው? እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሰቃይ ላይ አልነበረም ወይ? ለ22 ዓመታት የአገዛዙ የጭቆና ድርጊት ከአሜሪካ መንግስት የተሰወረ ጉዳይ ነበር ወይ? የሚሉት ጉዳዮች ሲነሱ የጸደቀውን ህግ ጉዳይ በጣም እንቆቅልሽ ያደርገዋል” በማለት ከጉዳዩ ጀርባ አንድ በጊዜ ሂደት እየጠራ የሚሄድ ጥቅል ጉዳይ ስለመኖሩ አመላካች እንደሆነ ምሁሩ ያስረዳሉ። በዚሁ መነሻ ፓለቲካዊ ትርጉሙ በቀላሉ ሊታለፍ የማይችልና ለአገዛዙ አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጥርበት እንደሚሆን መገመቱ ከባድ እንዳልሆነ ይገልጻሉ።

“በሌላ ወገን ግን ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለውን ያህል፣ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖም ሊኖረው ይችላል። ምናልባት አገዛዙ የተወሰኑ ነገሮችን የሚያሟላ ከሆነ ተቃዋሚው ኃይል ወደ መመቻመች /ኮምፕሮማይዝ/ ውስጥ በመግባት ለአጠቃላይ ነፃነት የሚደረገው ትግል አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርገዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነትና የብልጽግና ጉዳይ የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው በሚፈልገው አካሄድ ብቻ የሚወሰን ይሆናል ማለት ነው” ሲሉ አጠቃላይ ስጋታቸው ያስቀመጡት ዶ/ር ፈቃዱ፣ አጠቃላይ ህዝቡን የሚጠቅም የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሀብት ክፍፍል፣ በተለይም የመሬት ጥያቄ፣ እስከዛሬ ድረስ የተፈጠረው አዲስ የይዞታና የህብረተሰብ ግኑኝነት፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ዲሞክራቶች በሚፈልጉት መንገድ ላይፈቱ በሚችሉበት ሁኔታ መሰናክል ይደርስበታል። ስለዚህ ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ህግ የዛሬው አገዛዝ ወደፊት በስልጣን ዙሪያ ሊኖረው የሚችለው ተሳትፎ፣ የኃይል አሰላለፍ ጉዳይና የፓለቲካው አወቃቀርና አካሄድ ጉዳይ ላይ፣ የኢኮኖሚያዊና የህብረትሰብ ግኑኝነት፣ ማለትም የሀብት ክፍፍልና አዲስ ሀብት በአዲስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሳሪያ የመፍጠር ጉዳይ፣ የማህበራዊ ጥያቄ ጉዳይ፣ እነዚህና ሌሎች ለአገሪቱ የወደፊት እንደህብረተሰብ መኖርና መገንባት አንፃር በሰፊው ካልታየና ተቃዋሚ በሚባለው ጭንቅላት ውስጥ ካልተብላላ አደጋም ሊኖረው ይችላል።

በሌላ አነጋገር የዕድገታችንን ጉዞ ሊያጣምመው ይችላል። ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ህግ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ቢሟላና አገዛዙም እንደፖለቲካ ኃይል ተፎካካሪ ሆኖ የሚቆይ ከሆነ ወደፊት ለሚወሰዱ አገርን የሚጠቅሙ የዕድገት ዕርምጃዎች መሰናክል እንደሚሆን መጠርጠር ይቻላል። በሌላ አነጋገር የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ አገዛዝ ባሻገር ሊገነባው የሚችለው አዲስ ኢትዮጵያ የብዙ ዓመታት ህልም ሆኖ ሊቀር እንደሚችል የራሳቸውን አማራጭ ምልከታ አስቀምጠዋል። ሌላኛውንም መንገድ አካተዋል።
በሌላው በኩል ደግሞ ይህ ውሳኔ ህግ በገዢው መደብ ውስጥ ቅራኔን መፍጠሩ እንደማይቀር፣ ህይወታቸውን ከአሜሪካን መንግስት ጋር ያያዙ ኃይሎች፣ በተለይም ግፊቱ እየበዛ ሲሄድ ወደፊት የሚመጣባቸውን አደጋ በማጤን ውሳኔ ህጉን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ ተግባራዊ እናድርግ በሚሉ (ዘመናዊ ወያኔዎች) እና ውሳኔ ህጉን አንቀበልም በሚሉ አክራሪ ኃይሎች መሀከል ፍጥጫ መፈጠሩ እንደማይቀር ዶ/ር ፈቃዱ ግምገማቸውን አኑረዋል።

ቀጥሎስ?
በጉዳዩ ዙሪያ ከጎልጉል ጋር ወደፊት ሰፊ ቃለ ምልልስ ለመስጠት ፈቃዳቸውን የገለጹት አቶ ኦባንግ “እዚህ የተደረሰው በወፍ ዘራሽ ዝም ተብሎ አይደለም፤ ብዙ ተለፍቶ ነው። የአውሮፓ አገራት ተመሳሳይ ጥያቄ ሲቀርብላቸው አሜሪካን ምክንያት ሲያደርጉ ነበር። አሁን ሊያቀርቡ የሚችሉት አንዳችም ምክንያት የለም። አጠናክረን ስራችንን እንሰራለን። ሰክነን እንታገላለን። ኢህአዴግ ሳይወድ በግዱ በሩን ይከፍታል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከአውሮፓ አገራት ጋር አጋሮቻቸው በመሆን ስራቸውን በአዲስ መልክ እያጠናከሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ይህንን አዲስ ህገ ውሳኔ በማስረጃነትና በማቅረብ የአውሮፓ መንግሥታም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤ በሚሰጡት ዕርዳታም ሆነ ድጎማ ላይ ኢህአዴግን ተጠያቂ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ መርዳት ባይችሉም እንኳን ኢትዮጵያውያን ለሚያደርጉት ትግል እንቅፋት እንዳይሆኑ አበክረን እንወተውታለን ብለዋል አቶ ኦባንግ፡፡

አዲስ ስለ ጸደቀው ውሳኔ ህግ ለተጠየቁት “ብዙ ለመናገር ጊዜው ገና ነው። ኢትዮጵያዊያን በጎሳና በዘር የደም አዙሪት ውስጥ እየፈሩ እንዲኖሩ ሲደረግ የነበረው ድጋፍ ግን ማክተሚያው የተቃረበ ይመስለኛል፤ ኢህአዴግ እኔ ሥልጣን ከለቀቅሁኝ በአገሪቷ ውስጥ ደም መፋሰስ ይሆናል፤ ኢንተርሃምዌ የዘር ዕልቂት ይካሄዳል፤ የአፍሪካ ቀንድም ቀውስ ውስጥ ይገባል፣ ወዘተ በማለት እየዘላበደ የተቃዋሚውን ኃይል ከማዳከም አልፎ ሕዝቡ ፍራቻ ውስጥ በማስገባት አሜን ብሎ እንዲኖር የተጠቀመበት ማደንዘዣ ኃይሉ እየደከመ መጥቷል፤ ይኽኛው የውጭው ነው” የሚል ጥቅል መልስ ሰጥተዋል።

የመንታው መንገድ መሃንዲስ – ቻይና?
ቻይና ከኢህአዴግ በተለይም ከህወሃት ከፍተኛ ሰዎች ጋር አላት ከሚባለው “የተለወሰ ሽርክና” አንጻር አሜሪካ የምትሰጠውን የበጀት ድጎማና ርዳታ በየዓመቱ እየሸፈነች ኢህአዴግን ትታደጋለች የሚለው ጉዳይ ቻይና ከምትከተለው መሰረታዊ የንግድ እምነትና አንጻር በዜሮ የሚባዛ እንደሆነ ይነገራል። ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነዳጅና ማዕድን እየተከተለች የምትገባበት ኢንቨስትመንት እያከሰራት እንደሆነ የሚናገሩ ክፍሎች ቻይና የሃይል ሚዛኑን ተመልክታ ርምጃዋን ከማስተካከል ያለፈ ስራ እንደማትሰራ ይናገራሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን ይፋ ሆኖ የሰነበተውና የቻይናን “የዓይን ቀለም” የቀየረው የጃፓኑ ጠ/ሚ/ር የኢትዮጵያ ጉብኝትና የፖለቲካ መሞዳሞድ በቻይናና በኢህአዴግ መካከል የግንኙነት መሻከር እንደሚፈጥር የፖለቲካ እሳቤ አለ፡፡ ኢህአዴግ ከቻይና ታሪካዊ ጠላት ጃፓን ጋር በግልጽ ይህንን ዓይነቱን “ያደባባይ ፍቅር” ማሳየቱና የፖለቲካ ቅርጫ ውስጥ መግባቱ የምዕራቡ ወዳጅ ከሆነችው ጃፓን ጋር በመወገን በምዕራባውያን የድጎማ ዕቀባ ጭስ እንዳይታፈን መተንፈሻ እየፈለገ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ሰጥቶ በመቀበል፣ አበድሮ በመውሰድና የአምባገነኖችን ህልውና ለማስጠበቅ የሚውል ቴክኖሎጂን በመገንባት አፍሪካን እያለበች ያለችው ቻይና ኢህአዴግ ከምዕራባውያን የሚያኘው እርዳታ ቢቋረጥበት ከብድር በዘለለ በየዓመቱ ሌሎቹ እንደሚያደርጉት በጀት እየደጎመች የኢህአዴግን ነፍስ ለመጠበቅ የምትምልበት ዘመን ሊኖር እንደማይችል ከግምት በላይ የሚናገሩ ክፍሎች፣ ኢህአዴግ መለሳለስ በመሳየት ቆዳውን ሊቀይር ይችላል የሚለው እምነት አላቸው። አሜሪካ አሁን የያዘችው አቋም ከምትከተለው አዲሱ ፖሊሲዋና በሂደት የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመርምሮ የተያዘ ስለሆነ እንደ HR2003 በውስዋስ (ሎቢ) ሊቀለበስ የሚችል እንዳልሆነ አጥብቀው ይናገራሉ።

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ ዲፕሎማት ጠቅሰን ገመዱ በኢህአዴግ ላይ እየከረረ እንደሚሄድ በዘገብን ወቅት “ኢህአዴግ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እስር ቤቶችን እንዳይጎበኙ እንደከለከለው ማድረግ አይችልም … በደቡብ ሱዳን ያለው የፖለቲካ ቀውስ፣ በሶማሊያ ጭብጡ ያለየለት ሁከት፣ በኤርትራ ያለው የዛለ መንግስት እጣፈንታና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ጥቂቶች እንዲበለጽጉ ያደረገው ኢህአዴግ መጨረሻው አሜሪካንን በእጅጉ ሃሳብ ላይ ጥሏታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ የሄደው ቁርሾና የጥላቻ ፖለቲካ ሳይፈነዳ ኢህአዴግን ማረቅ የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል። ይህንን አጀንዳ አሜሪካ በቀላሉ ተጭበርብራ የምትቆልፈው አይሆንም። ኢህአዴግ በጎሳ ደምና እኔ ከሌለሁ አገርና አፍሪካ ቀንድ ይተራመሳል በሚል የሚነግደውን ንግድ አሜሪካኖቹ ተረድተዋል ብለን ነበር፡፡ የአሜሪካው ምክርቤት እንደራ የሆኑት ክሪስ ስሚዝ “በሽብር ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ተባብሮ መስራት ህዝብን ለማፈንና ረግጦ ለመግዛት ዋስትና አይደለም” በማለት መናገራቸውን ከዲፕሎማቱ አስተያየት ጋር አክለን ነበር፡፡

አዲስ የወጣውን ውሳኔ ህግ አሜሪካ በኢህአዴግ ላይ ፊቷን እያዞረች መሆኗን ማሳያ ነው በማለት የሚወስዱ ክፍሎች ይህ ህግ ከቀድሞው HR2003 ፈጽሞ የተለየ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የዛሬ አስር ዓመት፤ HR2003 በምክር ቤት ደረጃ የእንደራሴዎችን ከፍተኛ ድጋፍ ካገኘ በኋላ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) አጽድቆት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ የአሜሪካ ፖሊሲ እንዳይሆን በመደረጉ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች መከኑ። በወቅቱ የህጉ መርቀቅና እንዲጸድቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያስበረገገው ኢህአዴግ ጡረተኛ የሴኔት አባላት ከሚመሩት ዲኤልኤ ፓይፐር ከተባለ የውስዋስ (ሎቢ) ቡድን ጋር ከፍተኛ በጀት በጅቶ ታገለ። ባፈሰሰላቸው መጠን ወትዋቾቹ ባልደረቦቻቸውን ጠመዘ&#48

የአንድ ብሄር የበላይነት እና አድሏዊነት ካልተወገደ ሰራዊቱ እንዳይታመስ ያሰጋል::

በወያኔ እና በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት የጦር መኮንኖች እና ወታደሮች መሃል ጋብ ያለው ጡዘት ጊዜውን እየጠበቀ እየገነፈለ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ በላኩት መልእክት ጠቁመዋል::በሕወሓት ጄኔራሎች የሚመራው የመከላከያ ሰራዊቱ የበታች የጦር መኮንኖችን ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ደህንነት ቢሮ ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ከሰራዊቱ መቀነስ ያለባቸው የቀድሞ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የነበሩ የጦር መኮንኖች ዝርዝር ተጠንቶ ለኢታማጆር ሹሙ የቀረበ እና ይህንንም መሰረት አድርጎ መኮንኖቹን ከሰራዊቱ ውስጥ ለመቀነስ መታቀዱን ምንጮቹ ገልጸዋል::

እንደ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ ከቀረቡት 2369 ከምክትል መቶ አለቅነት እስከ ኮሎኔልነት ማእረግ ያላቸው የቀድሞ የበረሃ ታጋዮች የአሁን መኮንኖች ውስጥ አላስፈላጊ የሚባሉት ተጣርተው ከሰራዊቱ በዳረጎት የሚቀነሱ ሲሆን ከደርግ ስርኣት ጋር ቁርኝት የነበራቸው ከብሄራዊ ውትድርና ሰራዊቱን የተቀላቀሉት በቦርድ እና በጤንነት እክል በጡረታ የሚሰናበቱ እንዲሁም በማስጠንቀቂያና በደምወዝ ቅጣት የሚታለፉ እንዳሉም ታውቋል:: ይህንን ሁሉ ችግር የፈጠረው በመሃከላቸው የተነሳው የአንድ ብሄር የበላይነት እና አድሏዊነት የዘር ቆጠራ የፖለቲካ ሕዝባዊ ጥያቄዎች እና የሕገመንግስት ተግባራዊነት ክርክር የጫረው አለመግባባት ሲሆን በሰርኣቱ ውስጥ የተጠየቀው የጥቅማ ጥቅም ጥያቄም ሌላኛው መነካከሻ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃገር ውስጥ እና በአለማቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ያለውን የወያኔውን የአሸባሪነት ሕግ በሕገመንግስቱ ውስጥ ለማካተት ጥናት ሊጀመር ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደነበረው የአደገኛ ቦዘኔዎች ሕግ በሂደት አይን እያየ አሁን ያለውን የአሸባሪነት ህግ ማክሰም የሚል ሃሳብ ተይዞ ጥናቱ እንደሚካሄድ ታውቋል::ምንልክ ሳልሳዊ

(በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት) ምንጭ ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ
የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡

ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት›

በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

ሁኔታው በዚህ አያበቃም፡፡ ምንም እንኳን የመጠየቂያ ሰዓቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና መነጋገር ስንጀምር ‹‹በቃ… ቶሎ ጨርሱ›› የሚባልባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የእስር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማለትም ለሳሙና፣ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለሻይ ለቡና፣ ለውስጥ አልባሳት፣ ለውኃ ማከሚያ/ውኃ አጋር/ ወዘተ፤ ገንዘብ የሚያስፈልገን ቢሆንም እና እንደሚያስፈልጉ ቢታወቅም ጉዳዩ ለይቶለት የማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መበቀል ሆኗልና ለአንድ ወር ከአንድ መቶ ብር በላይ መጠቀም እንዳንችል የተከለከልን የመሆኑ አሳፋሪ ሐቅ ነው፡፡ ይህ እየተፈፀመ ያለው ደግሞ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ሰብኣዊ ክብራችንን የማዋረድ ሙከራዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡
በአገራችን ላይ እኔ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የጨረስኩት ዝዋይ በመሆኑ ብዙ ወዳጅ ዘመዶቼ በእዚህ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ለአካባቢው ነዋሪዎች በሳምንት እንዲጠይቁን የተፈቀደላቸው አንድ ቀን /ረቡዕ/ ብቻ ሲሆን ‹‹የት ነው የምታውቁት? እንዴት አወቃችሁት? ምንድን ነው የሚያመላልሳችሁ?›› በሚሉትና በሌሎችም ጥያቄዎች ተደናግጠው መምጣቱን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡

ሀገሩ ሞቃታማ ነውና በዚያ ላይ በእያንዳንዱ ቤት እስከ 150 ሰው ይታሰርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ እስረኛው የቱንም ያህል ፅዳቱን ለመጠበቅ ቢሞክርም የተባዩ መርመስመስ የእነ ትኋን እንዲህ መራባት፤ ለማሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ገላን ሲቆፍሩ ማደር ነው፡፡ ሊናገሩት ይከብዳል፣ አንባቢንም ቅር ያሰኛል፤ ግን ይህ የፊልም ትረካ ሳይሆን በእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ ደባ ነው፡፡ […] ግን የባሰ አታምጣ ማለት ነው!

የዝዋይን ልጅ ውሃ ጠማው

ግን የባሰ ነገር አለ፡፡ አፈር ቅጠል የማይል ምግብ ይቀርብናል፡፡ ‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ› ከፍተኛ የውኃ እጥረት /ዝዋይ ሀይቅ አናት ላይ ተቀምጠን/ አለ፡፡ የእስር እስር እንዲሉ ጄኔራል መኮንኖቹን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አባሪዎቻቸውና ሌሎች ሌሎች የተወሰንን እስረኞች የምንገኘው በልዩ ቅጣት ጭለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ እንደምንም ለመቋቋም ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ አዲሱ ስልት ግን መዘዙ በጣም አደገኛ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት ያለው፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው፣ እያንዳንዱ የመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር የሚያሳስበው እያንዳንዱ ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ስንል ድምፃችንን እናሰማለን፤ በሕክምና ንፍገት ወደሞት እየተገፋን ነው፡፡

ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!

ከወር በፊት ገደማ ወጣቱ የአንድነት ፓርቲ አባል ናትናኤል መኮንን ለሕክምና በሪፈር ወደ ቃሊቲ ተልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የዛኑ ዕለት ሕክምናውን ተነፍጎ ከሌሊቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ እስካሁን በሕመሙ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የኢብአፓ ሊቀመንበር የነበረው ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር እንደዚሁ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር ተብሎ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ ዘዴው ተፈፃሚ ሆነበት እጁን አጣጥፎ ተቀምጧል፡፡ ከሕመሙ ጋር በተያያዘ በአካሉ ላይ አሳሳቢ ሁኔታ እየታየበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ገልጬው የነበረው የእኔ የኩላሊት ሕመም አሁን ለመቀመጥም፣ ለመንቀሳቀስ እያወከኝ የሚገኝ ሲሆን፣ እኔን ከቃሊቲ ዝዋይ ለማምጣት የተደረገው የተቀናጀ መረብ ሩብ ያህሉን ለሰብኣዊነት አውለውት ቢሆን ኖሮ እኔም ፋታ፣ እነሱም እርካታ ባገኙ ነበር፡፡ ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!

የጄኔራል መኮንኖቹ አባሪዎች የነበሩት ኮረኔል ተስፋዬ ኃይሉ እና ኢንጂነር ክፍሌ ስንሻው፣ በዶክተር መረራ በሚመራው ኦሕኮ ፓርቲ አባል የነበሩት አሕመድ ነጃሺ፣ በጭለማ ቤት የከረመው ተስፋሀን ጨመዳ፣ የቤንሻንጉሉ አዛውንት ወዘተ ተገቢውን ሕክምና በማጣት ሕይወታቸውን ያጡ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ እንዴት ሕክምና ይከለከላል!? ግፍና ጭቆና ተቃውመው ደማቸውን ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ታጋዮችን በሥልጣን ማግስት ከፍርድ በመለስ በየእስር ቤቱ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው በሕክምና እጦት ሲረግፉ በእርካታ ማርመምን ከየት ተማሩት!? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይላል!? ሰው የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከቶ ምን ይላሉ!?

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ምንሊክ ሳልሳዊ:-አሜሪካ ውስጥ ያፈንዳ የገደለ ይተኮሰ የፈጀ …. አሜሪካዊ ዜጋ አሸባሪ ተብሎ ሲከሰስ ሲዘለፍ አላየንም ይልቅ እብድ ንክ ምናምን በሚል ከእስር ቤት ወደ ፍርድ ቤት እና ምርመራ ይሄዳል:: አሜሪካንም እኮ የአሸባሪዎች ህግ አላት:: ሆኖም ዜጎቿን አታጠምድበትም:: ከሌላ አገር ዜጋ ጋር አያይዛ ቲለጥፈዋለች … የአሜሪካ ዜግነት እንኳን ቢኖረው ኦሪጂኑን ነው የምትጠራው እንጅ አሜሪካዊ አሸባሪ ብላ አደባባይ ዜጎቿን በንዝህላልነት አታስርም አትገልም አታንገላታም:: ሌሎችም አገራት እንዲሁ …በአሸባሪነት ህግ ዜጋን አያጠምዱም :: የአሸባሪነት ህግ ከምንጩ በአሸባሪነት አሜሪካን የመዘገበቻቸውን አሸባሪ ድርጅቶች (ሕወሓትን ይጨምራል) ለመዳኘት የወጣ ነው::

እዚህ ጋ ግን ሲመጡ እኛ አገር የህጉ ትርጉም ለየት ብሎ እያየነው ነው::በዚህ ህግ ይዳኛሉ የተባሉት እነ አልቃይዳ እና የታጠቁ መሰሎቹ ሳይሆኑ የተዳኙበት የራሳችን ዜጎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ያውም ያልታጠቁ ብእር እና ወረቀት ያነገቡ የህዝብን ነጻነት እና መብት ያስተማሩ ወዘተ… ናቸው:: በአለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪነትን ለመቆጣጠር የተባለው ዜጎችን ማጥመድ መሆኑ አሳሳቢነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሃገራችን አሸባሪነ የተባሉት ግን የማናውቃቸው ሰዎች ሳይሆኑ መንግስትን በይፋ የተቃወሙ ለውጥ የጠየቁ የፖለቲካ መሪዎች ጋዜጠኞች እንዲሁም ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውን የጠየቁ የሃይማኖት ምሁራን ናቸው::እንዲሁም የሰብኣዊ መብታቸው ተጥሶ ከህጉ ውጪ በላያቸው ላይ ከባድ እና አደገኛ የሆነ ፕሮፓጋንዳ እየተካሄደባቸው ሳይመሰከርባቸው እና ማስረጃ ሳይቀርብባቸው ወንጀለኛ ተደርገው እንዲታዩ ተደርጓል::

ይህ የሽብር ህግ በተለያየ ጊዜ እንዲስተካከል እና እንዲለወጥ እንዲሻሻል ዜጎችን ማጥመድ እንዲያቆም .. የተለያዩ ቡድኖች አገሮች እና ኢትዮጵያውያን የገዛ የወያኔ ስርኣት አባላት ሳይቀሩ እየተናገሩ ነው :: ግን የወያኔው ጁንታ ይህንን ለስልጣን ማስረዘሚያ እና ለተቃዋሚዎች ማፈኛ እየተጠቀመበት ነው::በአለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ እንደሆነ የሚታወቀው ሕወሓት ምእራባውያን እየነቁ እንዳይነቁ አድርጎ እያጭበረበራቸው በሚያገኘው የብድር እና የእርዳታ ገንዘብ ዜጎችን ለማፈን እና ለመግደል እየተጠቀመበት ነው::ይህ የሽብር ህግ የማያፍናቸው አፋኞቹን የአገሪቱ ባለስልጣናት እና በተቃዋሚ ውስጥ የተሰገሰጉ ባላንጣዎችን የሚያሳፍኑ ብቻ ነው::

ይህንን ህግ በተመለከት መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ በየጊዜው ለማፈኛነት መጠቀምን የመረጠው የወያኔ ጁንታ ከትግራይ እስከ ሞያሌ ከጋምቤላ እስከ መልካጀብዱ እና ጎደ በሃገሪቱ በተለያዩ ማእዘናት ዜጎችን በማሳደድ ሰርተው እንዳይኖሩ እንዲፈናቀሉ የፖለቲካ እምነታቸውን እንዳያራምዱ እንዳይጽፉ እንዳያነቡ በማድረግ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሽብርን እየነዛ አሸባሪ እያረገ በማሰር ከአገር ተሰደው እንዲወጡ በማድረግ እና በመግደል ጭምር ወንጀል እየፈጸመ ስለሚገኝ ህዝቦች በጋራ ታግለን ስርኣቱን መቃብር ልንከተው ይገባል::

ምንሊክ ሳልሳዊ:-ሕንፃ- መኪና -ቪላ -ኢሮ -ብርና ዶላር -ጠበንጃ እና ቦምብ- እየተቆጠረ ሙስና እንደሚወራልን ሁሉ … የሃገሪቷን ዜጎች የጎዳ ;ሕግን እና ህገመንግስትን ያጣመመ; የራሱ መንግስት ያለውን;የፖለቲካ ባላንጣዎችን እና የግል ቂምበቀሉን ተገን አድርጎ የተንቀሳቀሰ ; መብት ጥሰት የፈጸመውን ;የዜጎችን መብት ያፈነውን ;ህገወጥ ተግባር በዜጎች ላይ የፈጸመውን ;ከህገወጦች ጋር የተባበረን ተቆጥሮ ;በፖለቲካ ሙሰኝነት መች ነው ለፍርድ የሚቀርበው??

በሃገሪቱ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ በሕወሓት መሪነት እየተፈጸመ ያለው ደባ እጅግ በረቀቀ መንገድ ከመስፋፋቱም በላይ በሙስና ስም የሚጠመዱ ሰዎች በውስጥ የፖለቲካ ቁርሾ ላይ የተለየ ሃሳብ ያነገቡ እና ስውር እጆች የሚያጠምዷቸውን እንደሆነ እያየን ነው ይህ ራሱን ችሎ በገዢው ፓርቲ ውስጥ የሚካሄድ የውስጥ ሽኩቻን የታከከ ፖለቲካዊ ሙስና ነው::
በየድርጅቶች ውስጥ የተለየ ሃሳብ እና የትችት ሙድ ያላቸውን ሰዎች ወይንም ከነማን በነማን እየጦዙ ነው የቡድን ስሪት ተለጣፊ አመራሮችን ለማፈን ሃያልነትን መጠቀም የፖለቲካ ሙስና ነው::እስከዛሬ እርምጃ ተወሰደባቸው የተባሉ ሰዎች ከፖለቲካ ጋር በተገናኘ ችግር እንዳለ መረጃዎች ሲጠቁሙ በግል ቂም በቀለም የታሰሩ ሰዎች አላግባብ እየተንገላቱ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዥነት የእስር ቤት ውስጥ ያለውን ሁኔታ ተቃዋሚን እንዲሰልሉ የተያዙ አስመሳይ የሙስና እስረኞች እንዳሉ የታወቀ ጉዳይ መሆኑ በራሱ የፖለቲካ ሙስና ነው::

በጠበንጃ ሃይል የያዙትን ስልጣን ተጠቅመው በምርጫ በህዝብ ተመርጠናል የሚሉ አካላት ህዝባዊ አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ አነስተኛ እና ጥቃቅን ሆድ አደር ካድሬዎችን በማሟሟቅ ላወጡት እና ላጸደቁት ህጋቸ ተገዢ ከመሆን ይልቅ እንደፈለጉ እና እንዳሻቸው ራሳቸውን ከአገሪቱ መናብርታት እኩል በማሰለፍ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ ተገን አድርገው እና ተጠቅመው የሚፈልጉትን እየጠቀሙ የማይፈልጉትን እያጠቁ ይገኛሉ::ፖለቲካዊ ሥልጣንን በመጠቀም ያላግባብ ዜጋን መጉዳት በራሱ ፖለቲካዊ ሙስና ነው፡፡

የግል ቂም በቀል የፖለቲካ አመለካከት እና ተመሳሳይ ጉዳዮችን በማጣቀስ ልዩነት ጠላትነት የሚመስላቸው ያልበሰሉ የስርኣቱ ካድሬዎች የግል ጸበኞቻቸውን የፖለቲካ ባላንጣዎቻቸውን ለፖለቲካ የንግድ ድርጅቶቻቸው አስጊ የሆኑትን ጠንካራ ነጋዴዎች በሙስና አልተሳሰር ያሉ ኢንቨስተሮችን የፖለቲካ ባላንጣ ቤተሰቦችን እንደ ጠላት በማየት መሬት እንዳያገኙ መከልከል፣ ፈቃድ መሰረዝ እና አለመስጠት ፣ የያዙትን መንጠቅ፣ የባንክ አካውንታቸውን ማገድ እና ብድር እንዳያገኙ ማከላከል ፣ የብቃት ማረጋገጫ እንዳትሰጧቸው፣ የሥራ ፈቃዳቸው እንዳይታደስ፣ ወዘተ እየተባለ መጉዳት፣ ማንከራተትና ሕገወጥ ተግባር በመፈጸም ስልጣንን ያለአግባብ የሚጠቀሙ ያልበሰሉ ፖለቲከኞች የሚፈጸሙት የፖለቲካ ሙስና በአገሪቱ አግጥጦ እየታየ ነው፡፡

ራሳቸው ያወጡትን እና አፈጻጸሙ እና አተረጓጎሙን እንኩዋን በተግባር ያልተረዱትን ሕግ በመጣስ ባለስልጣናት የግል እና የወል ጠላቶቻቸውን ድርጅቶቻቸውን ማሳሸግ ማጉላላት ማዘረፍ ማስደብደብ ባልሆነ ወንጀል መክሰስ፣ ፋይል ማስከፈትና ማስፈረድ በተግባር ይታያል፡፡ ጎን ለጎን ዘመድ እና ወዳጅ ለሆነና ከራስ ፍላጎት ጋር የሚስማማ ሥራ ላለው ደግሞ ሕግ ቢጣስም እንዳይጠየቅ፣ እንዳይያዝ፣ እንዳይከሰስ፣ ከተከሰሰም ፋይሉ እንዲዘጋና ክሱ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነም ሳይያዝ ወደ ውጭ አገር እንዲሸሽ በማድረግ ከኢኮኖሚ ሙስና ይልቅ ከፖለቲካ ሥልጣን አጠቃቀም አንፃር ሲታይ ግን ሥልጣንን መከታ በማድረግ የሚፈጸም አደገኛ የፖለቲካ ሙሰኛ ነው፡፡ ሕንፃ- መኪና -ቪላ -ኢሮ -ብርና ዶላር -ጠበንጃ እና ቦምብ- እየተቆጠረ ሙስና እንደሚወራልን ሁሉ … የሃገሪቷን ዜጎች የጎዳ ;ሕግን እና ህገመንግስትን ያጣመመ; የራሱ መንግስት ያለውን;የፖለቲካ ባላንጣዎችን እና የግል ቂምበቀሉን ተገን አድርጎ የተንቀሳቀሰ ; መብት ጥሰት የፈጸመውን ;የዜጎችን መብት ያፈነውን ;ህገወጥ ተግባር በዜጎች ላይ የፈጸመውን ;ከህገወጦች ጋር የተባበረን ተቆጥሮ ;በፖለቲካ ሙሰኝነት መች ነው ለፍርድ የሚቀርበው??

ከትላት በስቲያ እሁድ የካቲት 2\2006 ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል በተካሄደው በዚህ የሽልማት ስነስርዐት ላይ የህወሃት አባት የሚባሉት አቦይ ስብሃትን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ፣ የአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ፀጋዬ ሀይለማሪያም ፣ የህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት ዶክተር አህመድ አብዱረህማን ፣ የፌዴራሉ ህገ ወጥ መጅሊስ ምክትል ፕሬዚደንት ታጋይ (ሸይክ ከድር ) ፣ የአንዋር መስጂድ ኢማም ሀጂ ጡሃ ሃሩን ፣ የ10 ሩም ክፍለ ከተማ ሃላፊዎች ፣ የወረዳና የክፍለ ከተሞች መጅሊስ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ፡፡

ከሽልማቱ በኋላ ንግግር ያደረጉት አቦይ ስብሃት መንግስት በሙስሊሙ ጉዳይ ጠልቃ እንደገባ የሚያረጋግጠውንንግግራቸውን አድርገዋል ፡፡ አቦይ ስብሃት በአዳራሹ ለተገኘው ሰው ባደረጉት ንግግር
“ … ማንኛውም ነገር ከፍተኛ ጥረት ከተደረገበት ስኬት ይኖረዋል ፡፡ የሙስሊሙ ትግል ሲጀመር በጣም ተደናግሮን ነበር ፡፡ በኋላ ብዙ አስበንበት ስናበቃ ለምን መንግስትን የሚደግፍ መጅሊስ አናቋቁምም አልንና ጥረት ጀመርን ፡፡እኔ እራሴ ሄጄ ግዴላችሁም ከየክፍለ ከተማው ሙስሊም ሆነው መንግስትን የሚደግፉ ሁለት ወይም ሶስት ሰዎችን ብቻ ፈልጉልኝ አልኩ …፡፡ የጀመርነው ከቦሌ ክፍለ ከተማ ነው ፡፡ ወደ አምስት ሰዎችን አገኘንና እነሱን አደራጀን ፡፡ በኋላ ሌሎችም ክፍለ ከተሞች የቦሌን ተሞክሮ እንዲተገብሩ አደረግን ፡፡

ሁሉም ክፍለ ከተሞች ጥቂት ሙስሊሞችን አደራጁ ፡፡ ከዚህ በኋላ ነገሩ ሁሉ የተቃና ሆነ ፡፡ እኛም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተወሰኑ ሰዎች
መደራጀቱን ስናውቅ ጉዳዩን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮና ክፍለ ከተሞች እንዲረከቡንና በበላይነት እንዲቆጣጠሩት አደረግን ፡፡ እንዲህ
እያለ የሄደው ጥረት አሁን አክራሪዎችን ለማቆም የሚያስችል ጉልበት እንድናገኝ ረድቶናል … ” ብለዋል ፡፡

ይህ የአቶ ስብሃት ነጋ ንግግር መንግስት በሙስሊሙ ጉዳይ ጠልቃ አልገባሁም እያለ ከሚያስተባብለው ጋር የሚጋጭ እንደሆነ ተገልፇል ፡፡ በበርካታ ጉዳዮች ንግግር ያደረጉት አቦይ ስብሃት ኢስላምን የሚያጥላላ ንግግርም አድርገዋል ፡፡ “ቅድም የፌዴራሉ መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢው ሸህ ከድር እንዳለው የዱሮው እስልምና ሌላ ነው ፡፡ እኔ ከድርን በፊት ጀምሮ ትግራይ ውስጥ አውቀዋለሁ ፡፡ ምርጥ የህወሃት ታጋይ ነበር ፡፡ አብሮን ታግሏል ፡፡ አሁን ደግሞ ሙስሊሙን እያገለገለ ነው ፡፡ እስልምና እነዚህ የታሰሩት ሰዎች እንደሚሉት አይመስለኝም ፡፡
እስልምና እነዚህ ሰዎች እንደሚያሳዩት ዓይነት ዕምነት ከሆነ እንደ ዕምነት አያስፈልግም ፡፡ ፈፅሞ ሰዎቹ ለሀገር አይሆኑም ” ብለዋል ፡፡ በዚህ
ንግግራቸው በቦታው የነበሩ ሙስሊሞችም ጭብጨባ ለግሰዋቸዋል ፡፡

ኢትዮጵያዊው ዓረናና ኤርትራዊው ህወሓት!

ዓረናዎች “ህወሓት ኤርትራን ያስቀድማል። በመሆኑም ህወሓት የሻዕቢያ ተላላኪ ነው” ስንል ህወሓቶች ደግሞ “ዓረና ከትግራይን ህዝብ ጠላቶች ከሆኑ እንደነ አንድነት ፓርቲ ጋ ለመዋህድ ጥረት እያደረገ ነው” ይላሉ።

እርግጥ ነው፤ ዓረና ኢትዮጵያዊ ነው። ከኢትይጵያውያን ድርጅቶች ጋርም አብሮ ይሰራል። ከአንድነት፣ ደቡብ ሕብረት፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ እና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድና አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነው።

ዓረና እንደ ህወሓት ኤርትራዊ አይደለም። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ለመጉዳት ከሻዕብያ ጋር በማበር አይሰራም። ኢትዮጵያውያንን በጠላትነት እየፈረጀ የሻዕብያ አገልጋይ አይሆንም። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን እንጂ ኤርትራውያን አይደለንም። ኤርትራውያንን ለመጥቀም ኢትዮጵያውያንን አንበድልም። ስለዚህ ከሻዕብያ በላይ አንድነት ፓርቲን እናስቀድማለን። ምክንያቱም አንድነት ፓርቲ ኢትዮጵያዊ ነው። ኢትዮጵያም የሁላችን የጋራ ነች። ምናልባት ከሻዕብያ ጋር አብረን የምንሰራው የኢትዮጵያና የኤርትራ የጋራ ጥቅም የሚከበርበት መድረክ ሲፈጠር ብቻ ነው።

ዓረናና ህወሓት አልተሳሳቱም። ዓረና ከኢትዮጵያውያን ጋር ይሰራል። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነው። ህወሓት የሻዕብያ ተላላኪ ነው። ምክንያቱም ህወሓት ኤርትራዊ ነው። ህወሓት ኤርትራዊ መሆኑ ችግር የለውም። ችግር የሆነው ህወሓት ኤርትራዊ ሁኖ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ለኤርትራ አሳልፎ እየሰጠ ግን የኢትዮጵያ መንግስትነት መቆጣጠሩ ነው። ለኤርትራውያን እየሰራ ኢትዮጵያውያንን እወክላለሁ ማለቱ ነው ችግሩ። ህወሓት ለኤርትራ መቆም የሚያስደስተው ከሆነ ኤርትራን ያስተዳድር፤ የኤርትራን ህዝብ ይወክል። ኢትዮጵያን እያስተዳደረ፣ የኢትዮጵያ ህዝብን እወክላለሁ እያለ ለኤርትራ ጥቅም መስራቱ፣ ኤርትራውያንን መወከሉ ግን ወንጀል ነው። ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስትነት ከተቆጣጠረ ለኢትዮጵያውያን ጥቅም መስራት ነበረበት።

ህወሓት የኢትዮጵያ ስልጣን ይዞ ኤርትራን ለማስገንጠል ይሰራል፣ ዓሰብን ለኤርትራ ይሰጣል፣ ዓሰብ የኛ መሆኑ ስንከራከር ህወሓት ከኤርትራውያን በላይ ዓሰብ የኤርትራ መሆኑ ይሟገታል። ለኤርትራውያን መቆም ካለበት ለምን ወደሚወክለው ኤርትራ አይሄድም?

ዓረና ከኢትዮጵያውያን ድርጅቶች መዋሃዱን ይቀጥላል። ህወሓትም ለኤርትራውያን ማገልገሉ ይቀጥል። በዚሁ መሰረት “ዓረና ከአንድነት ፓርቲ ጋር እየተወሃደ ነው” ብላች ሁ ክሰሱን። ለኛ ችግር አይሆንም፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያውነታችን አምነን በኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን አማራጭ የፖለቲካ አቅጣጫ የሚያቀርብ ጠንካራ ሀገራዊ ፓርቲ የመመስረት ዕቅድ አለን። ህወሓትም ሻዕብያን ማገልገሉ ይቀጥል ምክንያቱም ህወሓት የኤርትራ ተወካይ (በኢትዮጵያ) መሆኑ እናውቃለን።

ህወሓት ግን ዓረና ከአንድነት ጋር የመዋህዱ ዜና ሲሰማ እንዲህ ከተደናገጠ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጭምር ስንዋሃድስ ምን ሊሆን ነው? ዓረና ከአንድነት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ብዙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋርም ይወሃዳል። ጠንካራ ሀገራዊ ፓርቲ መመስረት እንፈልጋለንና።

ህወሓት ኤርትራን ሲያስበልጥ ዓረና ግን ኢትዮጵያንን ያስቀድማል።

It is so!!! Abrha Desta

አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ የጥርጣሬና የሟርት ዘመን ምልኪዎች

አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡
የሌሎችን ግብና አዕምሮ ማማለልንና ማዘናጋትን የሚያውቁበት ሰዎች እንዳሉ አንርሳ! ተስፋ በመስጠት እንደዳማና እንደ ቼዝ ጠጠር (ወታደር) በፈለጉት አቅጣጫ ይገፉናል፡፡ ፍላጐታችንን ያከበሩ በመምሰል ፍላጐታቸውን የሚያሟሉ ሰዎች አደገኞች ናቸው፡፡ ፀሐይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ አይደለም፡፡ ለነገ እበላዋለሁ የሚል ጅል ተኩላ ግን ምን ጊዜም አይጠፋም፡፡ ይህን ሁሉ የሚታዘብ ህዝብ እንዳለ የሚያውቅ ካለ የብልህም ብልህ ነው፡፡ በዚህ የተካኑ ሰዎችን በዐይነ – ቁራኛ ማየት ያባት ነው፡፡ ስሜትን ተቆጣጥሮ ደባና ሴራን ጠንቅቆ ማየትና በጠዋት መንቃት ተገቢ ነው፡፡ ድቀትና ዝቅጠት ሲያይል አሉባልታና ጥርጣሬ ይነግሳል፡፡

በእንዲህ ያለው ሰዓት አፍ – አዊ እየበረከተ፣ ልባዊና ተግባራዊ እየሳሳ ይመጣል፡፡ ይሄኔ መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ የአንድ ነገር ዋጋ በዚያ ተገልግለን በምናገኘው ጥቅም አይለካም፡፡ ይልቁንም ያንን ነገር ለማግኘት በምንከፍለው መስዋዕትነት ነው የሚለካው፡፡ አገር እንገነባለን ስንል ይህን ብሂል አለመርሳት ነው፡፡ ይሆነናል የምንለውን ሰው መርጠን ስንሾምም ይህንን አለመዘንጋት ነው፡፡ ባለሙያው እያለ ስለዚያ ሙያ የሚያወራ ሲበዛ ጠንቀቅ ማለት ያሻል፡፡

ህግ ብቻውን ሁሉን ጉዳይ አይጨርስልንም፡፡ አስተዋይ አመራር፣ አስፈፃሚና ተጠያቂነትን ገምጋሚ እንዲኖር ያሻል፡፡ ያ ደግሞ ግልጽነትን ልማድ የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡በምንም ዓይነት ግን የፖለቲካ ትግልን እንደማይተኩልን ማሰብ ተገቢ ነው! የፖለቲካ ትግል ከሁሉም በፊት መደራጀትን፣ ተደራጅቶም መስዋዕትነትን፣ በሀገር ላይ ለውጥ የማየት ልባዊ ስሜትን ይጠይቃል! በተግባር ሳይሆን አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ ተግባራዊና የሚለውን የሚተረጉም ማህበረሰብ ካልፈጠርን ሟርት ይበዛል ::

እውን ሻዐቢያ እና ህወሀት ተጣልተዋልን
(ሁኔ አቢሲኒያዊ)
ማማ እና የሾላ ወተት ሁለቱም ወተት ናቸው የሚለያቸው ነገር ቢኖር ማማ ማማ መባሉ ሲሆን ሾላ ደግሞ ሾላ መባሉ ነው እንደዚሁ ህወሀት እና ሻዐቢያም የስም እንጂ የይዘትም ሆነ የአላማ ልዩነት የሌላቸው ጸረ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ፀረ ኢትዮጵዊ መሆናቸው ሀቅ እና ምስጢር ያልሆነ ነው ይልቁንስ በዚህች አነስተኛ ጦማር ማሳየት የፈለኩት ሻዐቢያን አምነው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመቀየር ከኢሳያስ ጋር ስለተወዳጁ ወገኖቻችን ጉዳይ ነው
ምርጫ 2002 በተቃረበበት ወቅት በኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ቀረበ የተባለው እና በፊታውራሪ ህወሀቶች ጭምር ድጋፍ ተሰጥቶት ነበረ የተባለው የስልጣን እንልቀቅ ጥያቄ ውድቅ የተደረገው እኛ ስልጣን ከለቀቅን ሻዐቢያ በእጅ አዙር ሀገሪቷን ሊመራት ስለሚችል ስልጣን መልቀቃችን ሊታሰብ የማይችል ነው ሲሉ በተላላኪ ጋዜጠኞቻቸው በኩል አስነገሩ ብዙሀኑ ምስኪን የግል ጋዜጦችም ይህንን ጉዳይ አንስተው ከሁሉም ጆሮ እንዲዳረስ አደረጉ፡፡ ይህ ሁኔታ ወያኔ ኢህአዴግን በሁለት መንገድ ተጠቃሚ አደረገው እነርሱም፡-
1. ሻዐቢያ እውነትም ፀረ ኢትዮጵያዊ ነው ኢህአዴግ ከወደቀ ደግሞ ሻዐቢያ ኢትዮጵያን ይቆጣጠራል የሚለው አስተሳሰብ ውስጥ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ ጥልቅ ብሎ እንዲገባ ያስቻለ ሲሆን
2. በሌላ በኩል ዲያስፖራ ላይ የመሸጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነ ኦነግ ከኢሳያስ ጋር ተለጥፈው ለምን ውጤታማ ሳይሆኑ ቀሩ እንኳን ብለው ሳያጤኑ ሻዐቢያ የወያነ ጠላት ስለሆነ ለእኛ እና ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛው ኢትዮጵያን ነጻ የማውጫ መንገድ አስመራ ላይ መክተም ነው ብለው አውጀው የማይታመነውን ኢሳያስን አምነው አስመራ ከተሙ፡፡
እነዚህ ሁለት ከላይ የጠከስኳቸው ሁለት አብይት ጉዳዮች ወያኔን ተጠቃሚ ያደረጉ እንዲሁም የኢትዮጵያን ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ነበሩ፡፡
እውን ህወሀት እና ሻዐቢያ ተጣልተዋል ወይስ ጥላቸው ለሚዲያ እና ለህዝቡ ጆሮ ብቻ ነው?
ኤርትራ የከተሙ ፓረቲዎችስ ስለምን ውጤታማ አልሆኑም?
እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እስኪ በቅድሚያ ይህንን ሀሳብ በአዕምሯችን እናሰላስለው
ሻዐቢያ አሰብ የራሱ እንዲሁም የኤርትራ ንብረት እንደሆነ ያምናል
ህወሀትም አሰብ የኤርትራዊያን ንብረት እና ሀብት ነው ብሎ ያምናል
በተቃራኒው ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሰብ የኢትዮጵያ ነው አልፎም ተርፎ የኤርትራን መገንጠል የማይደግፉ ናቸው ታድያ የኛ ፓርቲዎች እንደምን ብለው ነው ኢሳያስን አምነው አስመራ ላይ የከተሙት እውን ኢሳያስስ አሰብ የኢትዮጵያ ናት ብለው የሚሰብኩት ተቃዋሚዎች ይሻሉታል ወይስ ኤርትራ ነጻ ሀገር ነች አሰብም የኤርትራ ነች የሚለው ወያኔ?
ህወሀት እና ሻዐቢያ በስልጣን ላይ ለመቆየት የማይገድሉት ሰው የማይቆፍሩት መሬት የለም በኤርትራ ሪፈረንደም ወቅት እስካሁን ትርጉሙ ሊገባኝ ባልቻለ መልኩ የመለስ ዜናዊ እናት ኢትዮጵያ ሬድዮ ላይ ቀርባ ኤርትራዊያን ነጻ ሀገር ስለሆኑ እንኳን ደስ ያላቹህ ያሉ ሲሆን ነጻነቱም እንደሚገባቸው ተናግረዋል ነገር ግን ከአመታት በኋላ እነዚሁ የህወሀት ባለስልጣናት እናቶቻቸውን ሁሉ ያስደሰተውን መልካ ግኑኝነት ወደኋላ ብለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተፈጠረ ተባለ እና ከ 78000 በላይ ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲፈጁ ተደረገ ይህም ጠንካራ የነበረውን የኢትዮጵያ ወጣት እሳት ውስጥ የማገደ ብሎም የቀረው ጠንካራ ወጣት እንዲሰደድ ምክንያት የፈጠረ ሴራ ነበር በጦርነቱ መሀል መሪዎቻችን ምን ያደርጉ እንደነበር በቅርቡ ዊኪሊክስ ላይ ካየነው በኋላ ጦርነቱ የድንበር ሳይሆን ወጣት የማስፈጃ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
በአንድ ወቅት መሳሳት ልማዱ የሆነው ስብሀት ነጋ አዳልጦት በብሄራዊ ቲያትር የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች እጅግ የሚዋደዱ እና ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ካለ በኋላ ኤርትራን የሚወር አንድ ሀገር ቢመጣ ቀድመን ጦራችንን ከኤርትራ ወንድሞቻችን ጋር እናሰልፋለን በማለት መናገሩን ለሚያስታውስ ግለሰብ ግን ህወሀት እና ሻአቢያ ተጣልተዋል የሚለው ብሂል እውነታነቱ ለኢቲቪ ተመልካች እንጂ ማሰብ ለሚችል ሰው መራር ቀልድ ነው የሚሆነው፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ በኤርትራ የሚገኙ የት.ብ.ዴ.ን አባላት ነጻ እናወጣዋለን ያሉትን የትግራይ ህዝብ ነጻ ከማውጣት ይልቅ ወታደሮቻቸው አስመራ ውስጥ ኬላ ጠባቂ እንደሆነ በማህበራዊ ድህረ ገጾች አነበብኩ የተጠበኩት ነገር ስለሆነ ባይገርመኝም የወያኔን እድሜ እያራዘመን እንደሆነ ሲገባኝ ግን አዘንኩኝ በነገራችን ላይ የኤርትራ ተቃዋሚዎችንም ሰብስቦ በመያዝ ረድፍ ህወሀትም ለሻዐቢያ ውለታ እየሰራ እንደሆነ ጠጋ ብሎ የሻዐቢያ ተቃዋሚዎችን ያነጋገረ ግለሰብ የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡
ስለ ሻአቢያ ደህንነት ከህወሀት በላይ የሚጨነቅ ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ሻዐቢያ ማለት ለህወሀት ዘብ ነው ህወሀት ለሻዐቢያም እንደዛው እናም ከሻዐቢያ ጋር በመወዳጀት ወያኔን እንጥላለን ሀገራችንንም ነፃ እናወጣለን ማለት ሞኝነት ስለሆነ ቆም ብለን አካሄዳችንን ማሳመር ይኖርብናል፡፡
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ምንሊክ ሳልሳዊ :- የህዝብን ኑሮና የሀገርን ውስብስብ ችግሮች በወቅቱ የመፍታት ቅን ልቦና ከሌለ ዕጣ- ፈንታ ወዳዘዘው ውድቀት ማምራት ግድ ይሆናል፡፡ የአስተዳደር ብስለታችን፣ የዲፕሎማሲያችን ጥራት፣ ስለፓርቲና ስለ ሀገር ያለን ግንዛቤ፤ የምንመራውን ህዝብ አመኔታና ተቀባይነት የሚያስገኘው ቁልፍ ነገር መሆኑን መቼም ቢሆን መቼም እንወቅ፡፡ የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደገዝጋዡ ሳይሆን እንደ አጋዡ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ ማደራደር ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡

የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደገዝጋዡ ሳይሆን እንደ አጋዡ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ ማደራደር ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡
ለትናንሽ የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሔ ሳንሰጥ ወደ ውስብስብና ግዙፍ ችግርነት እንዲያድጉ ከፈቀድንና ቸልታችን ከበዛ፤ ያለ ጥርጥር ወደ ፖለቲካዊ ችግርነት ማደጋቸው አይቀሬ ነው፡፡ የወሎ ረሃብ እንደተነናቀ ወደ አብታዊ ማዕበልነት ተለወጠ፡፡ የሚሊተሪ ዲክታተራዊ አገዛዝ መናጠጥ፣ የቢሮክራሲያዊ በደል ማጠጥ፣ የሥልጣን መባለግና ያላግባብ መበልፀግ የአማጽያንን መፈልፈልና የተቃዋሚን ቁርጠኝነት መውለዱን ወለደ፡፡

ዛሬም የህዝብን ኑሮና የሀገርን ውስብስብ ችግሮች በወቅቱ የመፍታት ቅን ልቦና ከሌለ ዕጣ- ፈንታ ወዳዘዘው ውድቀት ማምራት ግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ የመንግሥት ዋንኛ ትኩረት የአንበሳውን ድርሻ ይውሰድ እንጂ የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጐች ወዘተ የነገዋ አገራችን ዕጣ-ፈንታ ይመለከተናል ማለት ኤጭ የማይባል ነገር መሆኑን ልብ ማለት ደግ ነው!

ዕጣ-ፈንታችንን አናመልጥም፡፡ የዕጣ-ፈንታችን አካል ነን፡፡ የምንለው፣ የምናቅደው፣ የምንራዕየው ሁሉ የእኛው አካል ነው፡፡ በተናገርነው እንነገርበታለን፡፡ በደነገግነው እንቀጣበታለን፡፡ በደሰኮርነው እናፍርበታለን ወይም እንኮራበታለን፡፡ በተለይ መንግስት ስንሆን ባወጣነው ህግ እከሌ ከእከሌ ሳንል፣ ወገናዊና ኢፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ መተዳደርና መቀጣት አለብን፡፡ የመንግሥትነታችን ትልቅ ቁም ነገር የህዝብን ደህንነትና የሀገርን ህልውና መታደግ ነው፡፡ ይህ ዋና ኃላፊነት ነው፡፡ ህዝብ እንዳይሸበር፣ እንዳይጠራጠር፣ ዕምነት እንዳያጣ ማድረግ፤ በአገሩ፣ በመንግሥቱና በኃላፊዎቹ ላይ የመተማመን ስሜት እንዲያድርበት ያደርገዋል፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ

……………..
ጌታቸው ሽፈራው በእኛ አገር በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ‹‹ፖለቲካ›› የሚባለው መብት መጠየቅ፣ እውነታውን መጻፍና መናገር ነው፡፡ ስለ ውሃ እጥረት፣ ሙስና፣ መብራት፣……ጮኽ ብሎ ያወራ ከዘመድና ጓደኛው ‹‹ይህን ፖለቲካህን ተወን!›› ይባላል፡፡ ፌስ ቡክን ጨምሮ በአብዛኛዎቹ ሚዲያዎች ደግሞ እነዚህን መሰረታዊ መብትና አቅርቦቶች ላይ የሚነሳውን ፖለቲካ ለማለዘብ (ለመራቅ) ‹‹ፖለቲካን በፈገግታ፣ የፖለቲካ ቀልዶች፣ የፖለቲካ ሽሙጥ፣……ፖለቲካን በጎሪጥ…..›› የሚባሉ አቀራረቦች ተለምደዋል፡፡

በተቃራኒው ገዥዎች ህዝብን የሚበድሉት፣ የሚዘርፉት፣ የሚያሰቃዩት ፊት ለፊት፤ በገሃድ ነው፡፡ ስለ መብት የሰበኩ ፖለቲከኞች፣ ስለ ለውጥ የጻፉ ጋዜጠኞች፣ ስለ እምነታቸው ያስተማሩ አማኞች ‹‹ሽብርተኛ›› ተብለው ታስረዋል፡፡ በርካታ ህጻናትና እናቶች ጎዳና ላይ ጸሃይና ቁር እየተፈራረቀባቸው እየተመለከትን ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ተከልክሏል፡፡ ሚዲያዎች በተራ ካድሬ ትዕዛዝ ይዘጋሉ፡፡ በዚህ ዘመን አገር እየተሸጠ ነው፡፡ ስሙን በቅጡ የማይጽፍ ‹‹ታጋይ››ና ካድሬ የማይገባውን ደም ወዝ ሲከፈለው ባለ ዲግሪዎቹ አንድ ቀን ያልተማሩትን ድንጋይ ፈለጣ በአማራጭነት ቀርቦላቸዋል፡፡ ለኢትዮጵያውያን የተነፈገው ለም መሬት ለሳውዲና ለህንዶች በሲጋራ ዋጋ እየተቸበቸበ ነው፡፡ ….ኧረ ስንቱ!?

ይህ እንግዲህ ፊት ለፊት የምናየው መራራ ሀቅ ነው፡፡ ታዲያ ለዚህ አይን ያፈጠጠ ጭቆና፣ በደል፣ አምባገነንነት የምን ፈገግታ ነው? ምንስ ይቀለድበታል? እንዴትስ በጎሪጥ ይታለፋል? በእርግጥ ህዝባችን ‹‹ፖለቲካ›› ብሎ በጠባቡ የሚተረጉመውም ይሁን ከዚህ የሚሰፋው ፈገግታ፣ ቀልድ፣ ድርድር፣ ስምምነት፣ መመቻመች……አያስፈልገውም እያልኩ አይደለም፡፡ በእኛ አገር ደግሞም በአሁኑ ወቅት ግን ፖለቲካው ፊት ለፊታችን የተደቀነ፣ የእያንዳንዱን ቤት ያንኴኳ፣ አገር ያከሰረ፣ ህዝብን ያዋረደና ያስናቀ ሆኗል፡፡ ይህን ፖለቲካ በፈገግታ፣ በሹክሹክታ፣ በለበጣ፣ በጎሪጥ፣ በአሽሙር እንለፈው ካልን አሽሙሩም፣ ቀልዳ ቀልዱም፣ ለበጣውም በራሳችን ላይ መሆኑ ነው፡፡ መርጉ የተጫነን እኛውን ራሳችን ላይ ነውና!

ከወራት በፊት ነው፡፡ ውሃ ለመቅዳት ተሰልፈን ከተሰለፉት ጋር ለአቅርቦቱ ችግር የ‹‹መንግስት››ን ድክመት አንስተን እንወያያለን፡፡ ‹‹ቀለል›› ባሉ ጉዳዮች አብሮን ሲያወራ የነበረ ወጣት ‹‹አይ እኔ ፖለቲካ አልወድም! አታነካኩኝ!›› ብሎን ራሱን ‹‹ነጻ አወጣ!››፡፡ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ይቺ ሽሽት የተለመደች ስለሆነች አልገረመኝም፡፡ አንድም ወሬውን የሚያስጀምረው ሰው ጆሮ ጠቢ ይሆናል፣ አሊያም ለጆሮ ጠቢ ያጋልጠኛል ከሚል ፍርሃት የመነጨ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ጥቂት ከቆየን በኋላ ወጣቱን ስለራሱ ስጠይቀው በሹክሹክታ ስለዚህ መንግስት ብልሹነት ማውራት ጀመረ፡፡ አባቱ የደርግ ወታደር ከተባለው የአገሪቱ ሰራዊት በግፍ ተባረዋል፣ 97 ላይ አባቱ ታስረው ስቃይ ደርሶባቸዋል፣ አባል ባለመሆኑ ለአንድ አመት ተኩል ስራ አላገኘም፣ በግድ የድጋፍ ሰልፍ ይወጣሉ፣ ቤታቸው ውስጥ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ነው……….፡፡

ይህ ፖለቲካው መርግ የሆነበት፣ በብልሹ ፖለቲካው እስከ ምናምኑ የተነከረ ልጅ ነው እንግዲህ ‹‹አታነካኩኝ!›› የሚለው፡፡ ከዚህ ውጭ ምን ሊያደርጉት እንደሚፈልግ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ፌስ ቡክም ሆነ ሌላ ቦታም ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞኛል፡፡ በደል የደረሰበት ሰው ዜና ልትዘግቡለት ስትሉ ‹‹አይ ያጠብቁብኛል፣ ትንሽ ቆይ!፣ ለስለስ አድርገው፣ እንዳታስመታኝ፣….›› ይላችኋል፡፡ ገዥዎቹ ደግሞ ይህን ይወዱታል፡፡ የሹክሹክታ፣ የለበጣ፣ የሀሜት፣ የፈገግታ……‹‹ፖለቲካ›› ከልኩ እንደማያልፍ ያውቁታል፡፡ እነሱ ፊት ለፊት እየበደሉ፣ የጎሪጥ እያየ የሚያልፍ፣ በቅኔና ቀልድ የሚናገር ህዝብ ለስልጣናቸው በእጅጉ ምቹ ሆኖላቸዋል፡፡

እኔም እላለሁ! መብታችን ለማስከበር፣ አቅርቦት ለማግኘት፣ ክብራችን ለማስጠበቅ፣……..መናገር፣ መጠየቅ፣ መቃወም ያለብን እንደወረደ፣ ፊት ለፊት እንጅ ቀልድ፣ ፌዝ፣ ቅኔ፣ አሽሙር፣ ሽሙጥ የሚያስፈልገን ጊዜ ላይ አይደለንም፡፡

“ግድብ ሲጠናቀቅ የግብፅ ፖለቲከኞችን ዓይን ይከፍታል::” አምባሳደር ዲና
“ግብፃውያን ዛቻን ትተው ገንቢ በሆኑ ስራዎች ማተኮር አለባቸው::” ውጭ ጉዳይ

በማንኛውም አገር ወንዙን በብቸኝነት ለመጠቀም የሚነሳ ፍላጎትና ታሪካዊ መብት ለማስቀጠል የሚደረግ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም። ግብፃውያን ፋይዳ የሌለው ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብና ዲፕሎማሲያዊ ዛቻዎችን ትተው ገንቢ በሆኑ ስራዎች ማተኮር እንደሚገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢዜአ እንደገለፁት የተለያዩ የግብፅ ባለስልጣናት፣ የዩኒቨርስቲ ምሁራንና ፖለቲከኞች በየጊዜው የሚለቋቸው ዛቻዎች ተገቢ አይደሉም ፋይዳም የላቸውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዛቻን በዛቻ አይመልስም ያሉት ቃለ አቀባዩ ዛቻ በየትኛውም ነገር ጥቅም እንደሌለው ገልፀዋል።እንደ አምባሳደር ዲና ገለፃ ለግብፅም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመው ተባብሮ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከሁሉም የተፋሰሱ አገሮች በጋራ በመስራት ተጠቃሚ ሲሆኑ ብቻ ነው።የናይል ወንዝ የአንድ አገር ስጦታ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የተፋሰሱ አገሮች ስጦታና ሁሉም እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበት የጋራ ወንዝ መሆኑንም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

አምባሳደር ዲና እንደተናገሩት በማንኛውም አገር ወንዙን በብቸኝነት ለመጠቀም የሚነሳ ፍላጎትና ታሪካዊ መብት ለማስቀጠል የሚደረግ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም።ግብፃውያን የናይል ጉዳይ በህገ መንግስታቸው መስፈሩ ሳይሆን ጠቃሚው ከተፋሰሱ አገራት ጋር ፍትሃዊና ማንንም የተፋሰሱ ሀገር በማይጎዳ መንገድ የናይል ወንዝን ለመጠቀም የተፈረመው የኢንተቤ ስምምነት መቀበል መሆኑን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

አምባሳደር ዲና የኢንቴቤ ስምምነትን አለመቀበል ከሁሉም የተፋሰሱ አገሮች ጋር ያቀያይማልም ብለዋል። አንድ አገር ህግ ሲያወጣ በማንኛውም ነገር የሌላ አገር ጥቅም የሚጎዳ መሆን የለበትም ያሉት ቃለ አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተፋሰሱ አገሮች የሚወጡ የውሃ ህጎች ከዓለም ዓቀፍ ውሃ ህጎች ጋር የሚጋጩ መሆን የለባቸውም፡፡ የዓለም ዓቀፍ ህጎችም አይፈቅዱም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር ዲና እንዳሉት በካርቱም በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል ሲካሄድ በነበረው ውይይት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ስብሰባዎች የዓለም ዓቀፍ ኤክስፐርቶች ፓናል አጥንቶ ያቀረበው ምክረ ሃሳብ ተግባራዊ የሚያደርግ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተው ነበር፡፡ ነገር ግን ግብፆች በሦስተኛው ስብሰባ ባመጡት አዲስ ሃሳብ ምክንያት ውይይቱ ያለ ቀነ ቀጠሮ መበተኑን አስታውሰዋል፡፡ ውይይቱ ያለ ቀነ ቀጠሮ የተበተነበትም ምክንያት በግብፅ በኩል ዳግም ጥናት የሚያካሂድ የውጭ ዜጎችን ያካተተ አዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮሚቴ የመመስረትና ያጠናው ውሳኔ ተግባራዊ ይሆናል በሚል የቀረበው ሃሳብ በኢትዮጵያና ሱዳን በኩል ውድቅ በመደረጉ እንደሆነ የገለፁት አምባሳደር ዲና ውይይቱ ወደ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ማዘንበሉም ሌላው ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

ግብፃውያን ጠቃሚው ገንቢ አቋም መያዝ ነው ብለው ጥርጣሬን ትተው የዓለም አቀፍ ኤክስፐርቶች ፓናል አጥንቶ ያቀረበው ምክረ ሃሳብ ደጋግመው ሊያዩት እንደሚገባ ጠቁመዋል።አምባሳደር ዲና ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የተፋሰሱን አገሮች ጥቅም አይጎዳም ይበልጥ የተፋሰሱ አገራት በኢኮኖሚ የሚያስተሳስር መሆኑን ገልፀው ግድቡ በመላው ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ቀን ከሌት እየተሰራ መሆኑንና ለአፍታም እንኳን ሳይቋረጥ ያለ ምንም የውጭ ዕርዳታ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል፡፡የህዳሴው ግድብ ሲጠናቀቅ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ጥሩ ግንኙነት ይፈጠራል፤ ይህም የተሳሳቱ የግብፅ ፖለቲከኞችን ዓይን ይከፍታል ብለን እናስባለን ብለዋል።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፤ የነፃ አውጪ ዎቻ ችን ( የግንቦት 7) የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ, በቤልጄም የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ወኪል ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ እንደጻፈው

iframe

Image

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚል ርዕስ ባለፈው ሰሞን በኢንተርኔት ያሰራጩት ጽሑፍ ነው። ጽሁፉ በጋዜጦችም ላይ ታትሞ ይሆናል። ፕሮፌሰር መስፍን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከአንድ ገጽ ባልበለጡ ማስታወሻዎች የሚወረውሯቸው ሃሳቦች ከመጠናቸው በላይ እንደሚናገሩ ማስተዋል ይቻላል።

“አይ ሀበሻ! ሀበሻና ሆድ” በሚል ርእስ እንደ የጻፉት ዓይነቶቹ በብዙዎች ዘንድ ባለመወደዳቸው ጫጫታን መፍጠራቸውም ታይቷል። በበኩሌ (በውስጣቸው መረን የለቀቁ ስድቦችን ባይጨምሩ ኖሮ) የአንዳንዶቹ ማስታሻዎች ሃሳቦች የምጠላቸው አይደሉም። እንዲያውም በነካ እጃቸው “ሀበሻና ስንፍና፣ ሀበሻና ፈሪነት፣ ሀበሻና አቋራጭ መንገድ ፈላጊነት፣ ሀበሻና አሉባልታ፣…” በሚሉ ርእሶች ተጨማሪ ማህበራዊ ሂስ ቢያቀርቡ ጥሩ ነበር የሚል ምኞት አለኝ።

ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ወደሆነኝ የፕሮፌሰር መስፍን ጽሑፍ እናምራ። ለነገሩ “አይ ስብሃት ነጋ!” የሚለው ጽሁፍ ለዚህ መጣጥፍ መነሻ ሆነኝ እንጂ፤ በአጠቃላይ በፕ/ር መስፍን ጽሁፎች ላይ ለዘመናት ሳስተውለው የኖርኩትና ሊታረም የሚገባው ጉዳይ አለ። “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚለው ጽሁፍም ላይ የሚስተዋለው ይኸው ነው።

ፕሮፌሰር መስፍን “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚል ርእስ ያዘጋጁትን ጽሁፍ “የሚቀድሱት” በስድብ ነው። እንዲህ ይላሉ፤ “በኢትዮጵያ ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሃት ነጋ ብቻ ነው። እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊነት ያለው ግለሰብ ነው…” ይላሉ። ይህንን አባባላቸውን ግን እንደ ምሁር በምሣሌ አስደግፈው፣ በማስረጃ አንተርሰው በማቅረብ እንድናምናቸው አያደርጉንም። ማሳመኑም ይቅር! ግን እርሳቸው ራሳቸው ከአቶ ስብሃት የተሻሉ ናቸው ወይ? አይመስለኝም!

ፕሮፌሰር መስፍንን ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ በቅርበት፣ ከዚያ በፊት ደግሞ በዝና አውቃቸዋለሁ። አቶ ስብሃትስ የፓርቲም የመንግስትም ስልጣን አያጡም። የመንግስትም፣ የፓርቲም፣ የእድርም፣ ስልጣን ሳይዝ፤ ባለስልጣናትን፣ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተማሪዎችን፣ እንደ እኔ ያለውን ተራ ዜጋ እና አልፎ ተርፎ ፈጣሪን ጭምር የሚሳደብ፣ የሚያንጓጥጥ፣ የሚያሽሟጥጥ፣ የሚዘልፍ፣… ከፕሮፌሰር መስፍን የሚበልጥ ሰው በሀገሪቱ ይገኛል? በኔ እምነት ሪከርዱ በእጃቸው ነው!

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ማስረጃ ለማቅረብ ብዙ ርቀት መኳተን አያስፈልግም። ይቺን ጽሁፍ ከማዘጋጀቴ በፊት በቅርብ ጊዜያት የተሰናዱ የፕሮፌሰሩን አስር መጣጥፎች አይቼ ነበር። በሚገርም ሁኔታ በአስሩም ላይ በተደጋጋሚ ያየሁት “ደደብ፣ ደንቆሮ፣ እውቀት ሳይኖረው፣ መሃይም፣…” የሚሉትን የስድብ ቃላት ነው። አቶ ስብሃትንም “እውቀት ሳይኖረው አዋቂ የሆነ” ይሏቸዋል። ለመሆኑ ፕሮፌሰር መስፍንን እውቀት ያለውንና የሌለውን ሰው አረጋጋጭ ተቋም ያደረጋቸው ማን ነው? ከአቶ ስብሃትና ከእርሳቸው “ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን” የሆነውስ ማን ነው? ፍርዱን ለአንባቢ ልተወው!!!

በነገራችን ላይ አቶ ስብሃት በምጣኔ ሀብት (ኢኮኖሚክስ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መመረቃቸውን ሰምቻለሁ። የፕፌሰር መስፍን ሊቅነትም ቢሆን በመልክዓ-ምድር (ጂኦግራፊ) እንጂ በዓለም ላይ ባሉ የእውቀት መስኮች ሁሉ ባለመሆኑ የሌሎችን እውቀት በአግባቡ ለመመዘን “ብቃት አላቸው” ብሎ ለመቀበል አስቸጋሪ ነው። ስለሆነም፣ ክቡር ፕሮፌሰር! በአቶ ስብሃት ዓይን ውስጥ “አለ” የሚሉትን ጉድፍ ሲጠቁሙ በራስዎ ዓይን ውስጥ የሚስተዋለውን ግንድ ዘንግተውታልና ልብ ቢሉት መልካም ነው እላለሁ።

እንዲያው የእውቀት ነገር ከተነሳ አይቀር አንድ ነገር ማለት ወደድሁ። እኔ እንደሚገባኝ እውቀት ማለት የአንድን ማህበረሰብ ችግር ለመቅረፍ የቻለ እንደሆነ እንጂ ሦስት አራት ዲግሪ ተሸክመው ራስን “በሊቅነት” ተራራ ቢያሳክሉት ትርጉም ያለው አይመስለኝም። በዚህ ረገድ አቶ ስብሃትንና ፕ/ር መስፍንን በማነጻጸር ውጤቱን ማየት እንችላለን። አቶ ስብሃት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ፣ በተለያዩ ት/ቤቶች አስተማሩ፣ በቢሮክራሲውም ውስጥ (በገንዘብ ሚኒስቴር) ጥቂት ሰሩና የመጡበትን ማህበረሰብ ‘ከጭቆና አወጣለሁ’ ብለው ጫካ ገቡ። የፖለቲካ ድርጅት መሰረቱ። መሪም፣ ተራ ተዋጊም፣ ሰላይም፣ ካድሬም፣ ዘበኛም፣ ሽማግሌም፣… ሆነው አገለገሉ። ምንም ይሁን ምን የተነሱለትን ዓላማ ለድል አበቁ። ስልጣንም፣ ሹመትም አገኙ። ፕሮፌሰር መስፍንስ?

ፕሮፌሰር መስፍንም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ። እዚያው አስተማሩ፣ እዚያው ተመራመሩ፣ እዚያው ሊቅ (ፕሮፌሰር) ሆኑ።… ደርግ ሊወድቅ አካባቢ “የሽማግሌ መንግስት” ለማቋቋም ሞከሩ – አልተሳካም ከሸፈ! የሰብአዊ መብት ድርጅት አቋቁመው ጥሩ ስራ በመስራት ላይ ሳሉ ለውጤት ሳያበቁት በጅምር ተውት – አሁንም ክሽፈት! የፖለቲካ ፓርቲዎችን አስታርቃለሁ ብለው ተነሱ። ይሄም አልተሳካም – ክሽፈት! ቀስተ ደመና የተሰኘ ፓርቲ አቋቋሙ። ፓርቲውን ለውጤት ማብቃት ሲገባቸው ይሄ እንደማይሳካላቸው ገና ከጅምሩ ሲገባቸው “አሻሮ ይዞ ወደ ቆሎ” እንደተጠጋው ብልጥ አንድ ወር ያልሞላው ፓርቲ ይዘው እንደ መኢአድ ካሉ ፓርቲዎች ጋር ተቀናጅቼ እሰራለሁ አሉ። በመሀል ላይ ይሄም እንደማይሳካ ሲረዱ “ቅንጅቱ የቅቤ ገበያ ሁኗል” በማለት ከአመራርነት ራሳቸውን አገለሉ። ምርጫው ተቃርቦ ነገሩ ሲጋጋልና ፖለቲካው ሲደምቅ ወደ ፖለቲካው እንደገና ተመለሱ። … ታሰሩ… በይቅርታ ተፈቱ… ታመሙ… ዳኑ… እንደገና ፓርቲ አቋቋሙ… ተጣሉ… መርህ ይከበር አሉ… እያለ ይቀጥላል ታሪካቸው። ውጤቱስ – ምንም! – ሌላ ክሽፈት!!! የአንድ ሰው አዋቂነት የሚለካው ባስመዘገበው ውጤት ነው የምንል ከሆነ ከአቶ ስብሃትና ከፕሮፌሰር መስፍን ባለሙሉ እውቀት ሊባል የሚችለው ማን ነው ታዲያ? ፍርዱን አሁንም ለአንባቢ እተወዋለሁ።

ወደ ሌላ ጉዳይ እናምራ። ፕሮፌሰር መስፍን “አይ ስብሃት ነጋ!” በሚል ርእስ በጻፉት ጽሁፍ ውስጥ “በኢትዮጵያ ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሃት ነጋ ብቻ ነው” ከሚለው ቀጥሎ ያሰፈሩት ሃሳብ “…[ስብሃት ነጋ] እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊነት ያለው ግለሰብ ነው” የሚል ነው። በዚህም ረገድ ቢሆን፤ በአፄ ኃ/ስላሴም፣ በደርግም ይሁን በኢህአዴግ የአስተዳደር ዘመን “ራሱን የቻለ ሉዓላዊነት ያለው ግለሰብ” ከፕሮፌሰር መስፍን ውጪ ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። ፕሮፌሰሩ በሦስቱም መንግስታት “ሉዓላዊነታቸውን” አረጋግጠው የኖሩ ሰው ናቸው።

ፕሮፌሰር መስፍን ለየትኛውም ስርዓት እጅ ሳይሰጡ ሃሳባቸውን እንደልባቸው እየተናገሩ መኖራቸውንና መብትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ያደረጉትን ጥረት አደንቃለሁ። ነገር ግን እንደ እርሳቸው ሁሉ ሌሎች ሰዎችም “የእኔ” የሚሉት ፍላጎት፣ እምነትም ሆነ አመለካከት ያላቸው መሆኑን ዘንግተው ወይም ሆነ ብለው በጉልበታቸው የተቀዳጁትን “ሉዓላዊነት” በመጠቀም የሌሎችን መብት ለመጨፍለቅ ሲፍጨረጨሩም ለዘመናት ተመልክቻለሁ። ለዚህ አባባሌ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ሁለት ምሣሌዎችን ላቅርብ።

የመጀመሪያው ማስረጃ ከአቶ ስብሃት ጋር የተያያዘ ነው። ፕሮፌሰር በፈለጉት ሰዓት፣ በፈለጉት መድረክ ላይ ብቅ ብለው መንግስትንም፣ ኢህአዴግንም፣ አቶ ስብሃትንም ወይም ሌላ ግለሰብን ወይም ፓርቲ ይተቻሉ። ከትችትም አልፈው ደስ በሚላቸው (ከእሳቸው በማይጠበቅ) ቋንቋ ጭምር ይሳደባሉ፣ ያንቋሽሻሉ፣ ይዘረጥጣሉ፣ ያጣጥላሉ፣…። እርሳቸው እንደዚያ በማለታቸው “ለምን እንዲህ ብለህ ጻፍክ ወይም ተናገርክ” ያላቸው የመንግስት አካል ስለመኖሩ በእርግጠኛነት ለመናገር እቸገራለሁ። ምክንያቱም ፕሮፌሰር መስፍን በጻፉት ጽሁፍ ተከሰሱ ሲባል አልሰማሁም። እርሳቸውስ?

አቶ ስብሃት አንድ መድረክ ላይ ተገኝተው “እንዲህ አሉ” መባልን ሲሰሙ ፕሮፌሰር ፀጉራቸውን ይነጫሉ። “ደፋሩ፣ ደንቆሮው፣ እውቀት የለሹ፣… ስብሃት እንዴት እንዲህ ይላል? እሱ እንደልቡ ተናጋሪ ነው! ማን ከልካይ አለው!…እንዴት?… እንዴት?…” የሚል መንፈስ ያለው ሃሳብ ሲሰነዝሩ ይታያሉ። “እኔ የምናገረው ሁሉ ለሀገር ይበጃል፣ አንድም ስህተት የለውም። እናም እንደፈለግኩ መናገር እችላለሁ። ስብሃት ግን በሃገሩ ምንም ዓይነት ጉዳይ ላይ መናገር አይችልም” መሆኑ ነው ነገሩ!!!

‘የተሳሳተ ነው’ የሚሉትን የማንንም ሰው ሃሳብ መተቸት፣ አቃቂር ማውጣት አንድ ነገር ነው። እርስዎ በፈለጉት ጉዳይ ላይ እንዳሻዎት እየተናገሩ ሌሎች አይናገሩ ማለት ግን ተገቢ አይመስለኝም። እንዲያው ለነገሩ እርስዎ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አብሮ መሄድ ያለበትንና የሌለበትን ሰው እንዲመርጡና ቀጭን ትእዛዝ እንዲያስተላልፉ ስልጣን የሰጠዎት ማን ነው? እርስዎ ከመሬት እየተነሱ እከሌ ደደብ ነው፣ እውቀት የለውም፣… የማለት ስልጣን ያቀዳጀዎትስ እኮ ማን ነው?

ፕሮፌሰር መስፍን ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙበትን ሁለተኛውን ምሣሌ ላቅርብ። ከምርጫ 97 በኋላ በቅንጅት ውስጥ የነበረው የሃሳብ ክፍፍል አለቅጥ በጦዘበት ወቅት አንዱን ጓደኛዬን ፕሮፌሰር መስፍን ቤታቸው ድረስ እንዲመጣ ካደረጉ በኋላ “ስማ! ይሄ እከሌ የሚባለው ጓደኛህ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሃሳቡን ካልቀየረ በጋዜጦች ላይ በመጻፍ በሕዝብ እንዲጠላና እንዲወገዝ አደርገዋለሁ” እንዳሉት ያኔውኑ እየበረረ መጥቶ ነበር ያጫወተኝ። ታዲያ ከዚህ በላይ ራስን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት አድርጎ መሾም አለ? ታዲያ ከዚህ በላይ ራስን በመንግስት ውስጥ ያለ መንግስት (A state within a state) አድርጎ መሾም አለ? ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያን ሕዝብ በጋዜጣ ላይ ወጥተው ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተቀመጥ ሲሉት የሚቀመጥ፣ ፀጥ ለጥ ብሎ፣ እርሳቸው እንዳሉት ሆኖ የሚገዛ ሳይመስላቸው አይቀርም። ያ ባይሆን ኖሮ ከላይ እንደተጠቀሰው ‘ሕዝቡ አንቅሮ እንዲተፋው አደርጋለሁ’ የሚል ደፋር ሃሳብ አይሰነዝሩም ነበር።

ስለፕሮፌሰር መስፍን ሳስብ በርካታ ነገሮች ግርም ይሉኛል። በአንድ በኩል የሰዎች ሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ ሰዎች ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲገልጹ እታገላለሁ ይላሉ። ይሄ ጥሩ ነው -የተቀደሰ ሃሳብ! በሌላ በኩል፤ አንዳንድ ሰዎች እርሳቸው የማይወዱትን ወይም የማይደግፉትን ሃሳብ ሲናገሩና ሲጽፉ ደግሞ “የተሳሳተ ነው” የሚሉትን ሃሳብ አንጥረው በማውጣት እንደ ምሁር መተቸት ሲገባቸው የሃሳቡን ባለቤት ቁምስቅሉን ያሳዩታል። እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርገው ያዋርዱታል። ለምን ተናገርክ፣ ለምን ጻፍክ ብለው ይዘልፉታል፣ ያብጠለጥሉታል። እንዲህ ያለው ሁኔታ አንድ ጊዜ፣ ሁለት ጊዜ ቢሆን ምንም አልነበረም። እድሜ ልካቸውን እንዲህ ያለ (Double Standard የሆነ) አቋም ማራመድ ትዝብት ላይ የሚጥል ነው። ከአንድ ምሁርም የሚጠበቅ አይመስለኝም።

የ“Double Standard”ን ነገር ካነሳሁ አይቀር ሌላ ምሣሌ ልጨመር። ፕሮፌሰር መስፍን የቀድሞው ቅንጅት አመራር አባል በነበሩበት ወቅት በ“ቅንጅት” ዙሪያ የተሰባሰበው ኃይል በርካታ ጊዜውን የሚያጠፋው በንትርክና በጭቅጭቅ መሆኑን ሲያዩና ይህ ኃይል አንድ ሆኖ በመስራት ውጤት ላይ እንደማይደርስ ሲገባቸው ከምርጫው በፊት ከ”ቅንጅት አመራርነት” ለመውጣት በጻፉት ማመልከቻ ያቀረቡት ምክንያት “ቅንጅት የቅቤ ገበያ ሆኗል። እኔ በዚህ አካል ውስጥ ሆኜ የታሪክ ተጠያቂ መሆን አልሻም” የሚል እንደነበር አስታውሳለሁ። አቶ ልደቱ መጽሐፍም ላይ ይኸው ተጠቅሷል።

የሚገርመው ነገር እርሳቸው ሊኖሩበት ያልፈለጉትን “ቅንጅት” እነ አቶ ልደቱ የራሳቸውን ምክንያት አቅርበው “በቅቤ ገበያው ውስጥ መሆን አንፈልግም” ሲሉ ደግሞ የጊዜ ገደብ (Ultimatum) በማስቀመጥ በጋዜጣ እጽፍባችኋለሁ አሉ። ነገሩ እኔ የፈለግኩትን፣ ደስ ያለኝን፣ ያሻኝን፣… አደርጋለሁ፣ ሉዓላዊ ነኝ…። እናንተ ግን ይህንን የማድረግ መብት የላችሁም፣ እኔ በምላችሁ መንገድ ሂዱ ነው። ታዲያ ይሄ ከ“Double Standard”ነት አልፎ አምባገነንነት አደለም?

ፕሮፌሰር መስፍን በአቶ ስብሃት ነጋ ላይ ወዳነሱት ሌላ ጉዳይ እናምራ። “[አቶ ስብሃት] በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ስልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል። ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም። ስብሃት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም…” ይላሉ። ይህንን የፕሮፌሰር መስፍንን ሃሳብ ሳነብ ከት ብዬ ነው የሳቅኩት። እንዲህ ብሎ የሚጽፍ ወይም የሚናገር ሰው “ፈሪሐ እግዚአብሔር ያለው፣ ለነፍሱም ለስጋውም ያደረ፣ ለታላላቆቹ፣ ለእኩዮቹና ለታናናሾቹ ተገቢውን ሰብአዊ አክብሮት የሚሰጥ ሰው መሆን እንዳለበት አምናለሁ። ፕሮፌሰር መስፍን ግን እንዲህ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሥነ-ምግባርና ግብረ-ገብነት ይናገሩት እንደሆነ እንጂ በተግባር ሲገልጡት ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም።

የእኒህን ሰው ተግባራት ልብ ብዬ ሳስተውል በርግጥ እኒህ ሰው በወላጆቻቸው ተቆንጥጠውና ተገስፀው፣ በኢትዮጵያዊ ባህልና ወግ ታንጸው ነው ያደጉት? የሚል ጥያቄ ድቅን ይልብኛል። በበኩሌ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ከአቶ ስብሃት በባሰ መጠን “ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብለው የሚፈሩት” ምድራዊ ኃይል እንደሌለ በጥሩ ሁኔታ አስተውያለሁ። እናም አቶ ስብሃት ላይ ‘አየሁ’ የሚሉትን ግድፈት መጀመሪያ ከራስዎ ላይ እንደ አሮጌ ቁና አሽቀንጥረው ይጣሉ ፕሮፌሶሬ!

አሁንም ወደ ሌላ የፕሮፌሰር መስፍን እና የአቶ ስብሃት ጉዳይ እናምራ። “ስብሃት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አደለም። ዋናው ነገር መናገሩ ነው” ይላሉ። እርስዎስ ፕሮፌሰር? እውነት ከአቶ ስብሃት የተሻሉ ነዎት? ለመሆኑ እርስዎ አስቦ መናገሩ ይቅርና የተናገሩት ትክክል ስለመሆኑ ነገሩ ካለፈ በኋላ አስበውት ያውቃሉ? እርስዎ በምንም ጉዳይ ላይ የሚሰነዝሩት ሃሳብ ሁሉ ትክክል፣ ሌሎች የሚናገሩት ግን ምንም ይሁን ምን ስህተት ተደርጎ የሚወሰደው በየትኛው መመዘኛ ነው?

አቶ ስብሃት ሰው ናቸው። እናም አቶ ስብሃት የሚናገሩት ሁሉ ትክክል ሊሆን እንደማይችል አስባለሁ። ያም ቢሆን የተሳሳተውን ሃሳብ ነቅሶ በማውጣት ‘ይሄ ይሄ ስህተት ነው’ ይባላል እንጂ አቶ ስብሃት የተናገረው ሁሉ ስህተት ነው ብሎ መደምደም ትክክል የሚሆንበት ሥነ-አመክንዮ (Logic) የለም። በኔ እይታ ከፕሮፌሰር መስፍን ይልቅ የሚናገሩትን የሚያውቁት አቶ ስብሃት ናቸው። አቶ ስብሃት ምንን መቼ መናገር እንዳለባቸው ጭምር አስበው እንደሚናገሩ አስተውያለሁ። እንዳመጣላቸው የመዘርገፉ ሁኔታ የሚታየው በፕሮፌሰር መስፍን ዘንድ ነው ባይ ነኝ። ፕሮፌሰር መስፍን ጥንቆላ ጀምረው ካልሆነ በስተቀር “ስብሃት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም” የሚል ሃሳብ ባልሰነዘሩም ነበር።

ፕሮፌሰር መስፍን “…[ዮ]ናስ አበበ እንደሚነግረን ‘አቶ ስብሃት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር’….” ካሉ በኋላ “ስብሃት ይህንን ያደረገው ‘ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ [እና] በከባድ ጥያቄ… የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ’…” መሆኑን ይነግሩናል። እንዲህ ዓይነት የ‘ሳይሆን አይቀርም’ መላምት የሚያነሳ ሰው እንዲህ ያለ ተግባር የመፈጸም ልምድ እንዳለው መጠርጠር ፕሮፌሰሩ በሄዱበት መንገድ መንጎድ ስለሚሆን መተውን መረጥኩ።

እንዲያው ለነገሩ አንድ ሰው የሚከራከርበትን ወይም ሀሳብ የሚያቀርብበትን መድረክ “እንዲህ ያለ ገጽታ ይኑረው” ቢል ሀጢያቱ ምኑ ላይ ነው? ይህንን የማለት መብት የለውም ሊሉን ነው ፕሮፌሰር?! በሰለጠኑት ሀገሮችም እኮ “ድምጼም ምስሌም እንዳይቀረጽ፣ ፎቶም እንዳልነሳ” የሚል ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡበት አሰራር አለ። አንዳንዶቹ እንዲያውም ንግግር እንዲያደርጉ ሲጋበዙ ይህንን ፍላጎታቸውን የሚገልጹበት ፎርም እንዲሞሉ ይደረጋል። ታዲያ አቶ ስብሃት መከራከርም መነጋገርም የምፈልገው (ብለው ከሆነ) ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ብቻ ነው የማለት መብት የላቸውም ነው የሚሉን ፕሮፌሰር መስፍን? እንዲህ ያለ የመብት ጥያቄ ማንሳት በየትኛው ሎጂክ ነው ከጥያቄ መፍራትና ከጭብጨባ መፈለግ ጋር ሊገናኝ የሚችለው? በበኩሌ “ሌባ እናት ልጇን አታምንም” የሚለውን ብሒል ከማስታወስ የዘለለ ትርጉም ያለው ሆኖ አልታየኝም። ይህንን ‘ቅድመ ሁኔታ’ ያቀረበው ፕሮፌሰር መስፍን የሚያውቁት ሰው ቢሆን ኖሮ፤ ይኸኔ እርሳቸው ሲያሞግሱትና ሲያወድሱት ይገኙ ነበር።

“ስብሃት ነጋ ዋና ዓላማው በሙሉ ነፃነት የመጣለትን እንደመጣለት መናገር ነው” ይሉና ምሣሌዎችን ይደረድራሉ ፕሮፌሰር መስፍን። እንደመጣለት በመናገር ረገድ እውን ፕሮፌሰር መስፍን ከደሙ ንፁህ ነኝ ብለው ጣታቸውን በሌሎች ላይ ለመቀሰር ይችላሉ? በበኩሌ አይመስለኝም። ይህንን አባባሌን ለማስረገጥ እስቲ የሚከሉትን አብነቶች እንይ።

ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ “አማራ የሚባል ብሔር/ሕዝብ የለም” አሉ ፕሮፌሰር መስፍን። ነገሩ የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ አለፈ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ አሁንስ አማራ የለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ደግሞ “አሁን እንኳ አማራ የሚባል ሕዝብ/ብሔር እየተፈጠረ ነው” አሉ። “የለም” የተባለው አማራ በአጭር ጊዜ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ባይገባንም ይህንንም ሰምተን አለፍነው። በምርጫ 97 ለቅስቀሳ ወደ ትግራይ ሄዱና “የትግራይ ሕዝብ በፋብሪካ እንደወጣ ሣሙና…” ነው የሚል ሃሳብ መናገራቸውን ሰማን። … ሌሎችንም ምሣሌዎች መጥቀስ ይቻላል። ታዲያ በአቶ ስብሃትና በፕሮፌሰር መስፍን መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ሁለቱም የሚያምኑበትን ይናገራሉ። በዚህ ረገድ ፕሮፌሰር መስፍን አቶ ስብሃትን “እንደመጣልህ ተናጋሪ ነህ” ብለው ለመክሰስም፣ ለመውቀስም ሆነ ለመተቸት የሚያስችል የሞራል ብቃት ያላቸው ሆኖ አይታየኝም። ‘እኔ እንደመጣልኝ ብናገርም እችላለሁ፣ ስብሃት ነጋ ግን አይችልም’ እያሉን ከሆነ ፕሮፌሰር ጤናቸው መመርመር አለበት ባይ ነኝ። ፕሮፌሰር ስለኤርትራውያን ሰብአዊ መብት ቋሚ ጠበቃ ሆነው ሲከራከሩ ትክክል፣ አቶ ስብሃት ስለኤርትራውያን ኢትዮጵያዊነት ሲናገሩ ስህተት የሚደረግበትም አግባብ ትክክል አይመስለኝም።

ፕሮፌሰር መስፍን አቶ ስብሃት ነጋን “እንደመጣለት የሚናገር፣ ዘባራቂ፣ ሳይማር የተማርኩ ነኝ የሚል፣… ወዘተረፈ” ማለታቸውንም ከዚሁ ጽሁፋቸው አንብቤአለሁ። የፕሮፌሰር መስፍን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪነት አልፋና ኦሜጋ እንግዲህ ይሄ ነው! አቶ ስብሃት “ወያኔ” ስለሆኑ ሰብአዊ ክብር አያስፈልጋቸውም እያሉን እንዳይሆን ፕሮፌሰሩ! ድንቄም የሰብአዊ መብት ተሟጋች! ከመሬት ተነስተው በአደባባይ፣ በጋዜጣ፣ በመጽሔት፣ በኢንተርኔት ላይ የሰውን ሰብእና እያጎደፉ፣ ሰድበው ለሰዳቢ አሳልፈው እየሰጡና እያዋረዱ የሰዎች መብት ተቆርቋሪ መሆን የሚቻል አይመስለኝም። እንዲያ የሚሉ ከሆነ ፌዝ ነው!

አቶ ስብሃት ስለሰሚያዊ ፓርቲ ሰልፍ መከልከል ተጠይቀው “አላውቅም” ማለታቸውንም ፕሮፌሰር መስፍን “አላውቅም ማለት ለመዘላበድ ይጠቅማል” በማለት አቶ ስብሃትን ይዘልፋሉ። ወይ ፕሮፌሰር መስፍን! አላውቅም ማለት መዘላበድ የሚሆነው በየት ሀገር ነው ፕሮፌሰር?! ሲናገሩ “እንዳመጣለት የሚናገር” ማለት፤ “አላውቅም” ሲሉ “መዘላበድ ነው” ማለት ምን የሚሉት አማርኛ ነው? ለፕሮፌሰር መስፍን “መዘላበድ” የሚለው ቃል በትክክል ገብቷቸው ይሆን? ሽቅብ ወደ ላይ መናገር በወሎ አማርኛ “ያርማጃ ልጅ!” ያሰኘኛል ብዬ ሰጋሁ እንጂ መዘላበድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት ጥሩ ምሣሌ ነበረኝ። ‘ወይ ነዶ የሐመር ጌታ’ አለ ሰውየው!

ስለ ፕሮፌሰር መስፍን እና ስለ አቶ ስብሃት ጉዳይ ከዚህ በላይ ባልቀጥል ጥሩ ነው። ይሁን እንጂ፣ ጽሁፌን ከመቋጨቴ በፊት አንዳንድ የማጠቃለያ ነጥቦችን ላንሳ። ፖለቲከኛ በነበርኩባቸው ዓመታት አንድም ቀን አግኝቻቸው ከማላውቃቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት አንዱ አቶ ስብሃት ነጋ አንዱ ናቸው። ከአቶ ስብሃት ይልቅ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበረኝ።

ይህንን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት ለአቶ ስብሃት ጥብቅና ለመቆም ወይም ልዩ ፍቅርና መቆርቆር ስላደረብኝ አይደለም። ይህንን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት በፕሮፌሰር መስፍን ላይ የተለየ ጥላቻ ስላደረብኝም አይደለም። ፕሮፌሰሩ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ገደማ “አብዱራህማንና ጓደኞቹ” እያሉ፣ ከደርግ አባላትና ከመንግስቱ ኃ/ማሪያም ጋር እያነጻጸሩ፣ በ“ሳይሆን አይቀርም” ጥርጣሬ የሌለብኝን ነውር እየደረደሩ በሰባት ጋዜጦች ላይ (እርግጠኛ ነኝ ዛሬ የሚያፍሩበትን) ጽሑፍ ጽፈውብኝ እንኳ አቅሙም ጉልበቱም እያለኝ መልስ አልሰጠኋቸውም ነበር። በሳቅ በፈገግታ ነበር ያለፍኳቸው።

ለአቶ ስብሃትም ለፕሮፌሰር መስፍንም ልዩ አክብሮት አለኝ። ሁለቱም ለኢትዮጵያ ያስፈልጓታል ባይ ነኝ። ሁለቱም በሚያቀርቧቸው አንዳንድ ሃሳቦች እስማማለሁ። ሁለቱም በሚሰነዝሯቸው አንዳንድ አስተያየቶች ደግሞ አልስማማም። ጠቤም፣ ፍቅሬም፣ ጥላቻዬም ሆነ ቅያሜዬ ከሚያፈልቋቸው ሃሳቦች ጋር እንጂ ከእነርሱነታቸው (ከሰብእናቸው) ጋር አይደለም። ሁለቱም በአባትነ&#472

ሆድን በጎመን ቢደልሉት…
#Ethiopia #Blueparty Brhanu Tekleyared Ze Ethiopia #UDJ #Medrek #MinilikSalsawi
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች የሰማያዊ ፓርቲን በውህደት ላይ ያለውን አቋም ሲኮንኑት ይስተዋላል፡፡ ኩነናው ፓርቲው በውህደት ላይ ያለውን አቋም የግለሰብ አቋም ነው እስከ ማለት ይደርሳል፡፡ ስለዚህም የዚህ ጽሑፍ አላማ የፓርቲውን በውህደት ላይ ያለውን አቋም እንዲሁም እውን ፓርቲው በግለሰብ ፖለቲካዊ አቋም የሚመራነውን? የሚለውን ለአንባብያን ለማብራራት እና ለመመለስ ያሰበ ነው፡፡

እኔ እስከማውቀው ፓርቲው በውህደት ላይ ፈጽሞ የተዘጋ አቋም የለውም፡፡ ለዚህም ነው በተለያዩ ጊዜያት ፓርቲው በሚሰጠው መግለጫ ላይ አሁን ባለንበት ሁኔታ ውህደት የሚባል ነገር ቦታ የለውም የሚለው፡፡ ፓርቲ እንደ ፓርቲ የተለያዩ የቤት ስራዎች እንዳሉበት ስለሚያምን እነዚህንም የቤት ስራዎቹን በአግባቡ እና በጥራት ለመስራት ስለሚያስፈልግ ከዚህም ባሻገር ሌሎችም ፓርቲዎችም ከውህደት በፊት በአግባቡ የቤት ስራቸውን መስራት እንደሚኖርባቸውም ከማመን የተነሳ የተያዘ ጊዜያዊ እና ወቅታዊ አቋም መሆኑን ለአንባቢ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡

በሃገራችን የፓርቲ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የፓርቲዎች የመዋሃድ እና እርስ በእርስ የመበላላት ታሪክ ቢኖርም ዋናው መነሳት ያለበት ነገር ግን ከእነዚህ ታሪኮች ምን ተምረናል የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ታሪክ አሁንም የሚነግረን ከታሪክ የማንማር የታሪክ ቱባ መሆናችንን ነው፡፡ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን የሆነው እና የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ኋላ የመለሰውን የ1997 ዓ.ም ምርጫ እንደ ማሳያ ሊቀርብ ይችላል፡፡ቅንጅት እንዴት ተቋቋመ? ማን ምን አተረፈ? ማንስ ምን ተጎዳ? ስንት ፓርቲዎች ህይወታቸውን ወይም ህልውናቸውን አጡ? የሚሉት እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡ እነዚህ የትናንት ታሪኮቻችን ፍንትው አድርገው የሚያሳዩን ከፓርቲዎች ውህደት በፊት ምን መሰራት እንዳለበት ነው፡፡

‹‹ወንዙን ስንደርስ እንሻገረዋለን!›› በሚል አስተሳሰብ የሚደረግ ውህደት ወንዙንም ተሻጋሪውንም የሚጎዳ ስለሆነ ፈጽሞ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ቅንጅት በወቅቱ ባደረገው የወረቀት ውህደት ወንዙ ጋር ሳይደርሱ ተራራው ላይ ሲፈረካከሱ ለማየትተችሏል፡፡ ይህም ሆድን በጎመን ቢደልሉት ልበት በዳገት ይለግማል የሚለውን የሃገራችን ብሂል እንድናስታውስ ያደርጋል፡፡ ከውህደት በፊት ቅድሚያ አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ አብረን ለመስራት ያለን ተነሳሽነት ምን ያህል እንደሆነ ማስተዋል ይኖርብናል፡፡

እነዚህ ውህደትን የሚያቀነቅኑ ፓርቲዎች ሰማያዊ ፓርቲ እንደ ፓርቲ ባደረጋቸው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እና ዝግጅቶች ላይ ድጋፍ ለማድረግም ሆነ ለመሳተፍ እንዲሁም አብሮ ለመስራት ካደረጉት ጥረት ይልቅ ባይሳካላቸውም እንቅስቃሴዎቹን ለማሳነስ እና ለማጥላላት የተደረጉ ሙከራዎች ይብሱ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25/2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ባካሄደ ጊዜ ሰልፉን በጋራ ከማሳካትና ከመሳተፍ ይልቅ ከአንዳንድ የፓርቲ አመራሮች ሳይቀር እንዴት ተፈቀደላቸው ብለው ገዢውን ፓርቲ ለመውቀስ የዳዳቸውም ነበሩ፡፡

ታዲያ የራሳቸውን የቤት ስራ እንኳን በአግባቡ መስራት የተሳናቸው ፓርቲዎች እንዴት ጣታቸውን ወደ ሰማያዊ ለመቀሰር እንደሚችሉ ፈጽሞ ሊገባኝ የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡ ፖለቲካን ማኪያቶ መጠጫ ያደረጉ ፓርቲዎችም እንኳን ሳይቀሩ ፓርቲው በውህደት ላይ ያለውን ጊዜያዊ አቋም ለመኮነን ሲሞክሩ ማየት አስቂኝም አሳዛኝም ጉዳይ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ ባለቤት እንደ ግለሰብ ከውህደት በፊት አንድ በሚያደርጉን ነገሮች ላይ ተቀራርበን ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ይኖርብናል ብሎ ያምናል፡፡ አንዳንዶች በውስጣቸው ካለው “የብሔር ተዋጽኦ አናሳነት” አንጻር ውህደትን ሲያራግቡ መመልከት የተለመደ ነው፡፡

ሲጀምር አሁንም እንደ አምባገነኑ ኢህአዴግ ከፋፋይ የጎሳ ፖለቲካን ለማስቀጠል ከሚደረግ ሙከራ ተለይቶ አይታይም፡፡ ይህም ደግሞ መጽሐፉ ኢትዮጵያዊ ቀለሙን እንዲሁም ነብር ዥንጉርጉርነቱን ሊቀይር አይቻለውም እንደሚለው ትውልደ ኢህአዴጋውያን በፓርቲዎች ውስጥ አላግባብ ባገኙት ዜግነት የሚያራምዱት እና የሚያቀነቅኑት አስተሳሰብ መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ ክፍተቶቻችንን በጊዜያዊነት ለመደፋፈን ሲባል የሚደረግ የጥድፊያ ውህደት መጨረሻው አሁን ካለንበት የፖለቲካ አዘቅት ለመውጣት የሚደረግ ትግልን እንዲሁም የህዝብን አመኔታ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ወደኋላ ሊመልሰው ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡

መቼም እባብ ያየ በልጥ ይበረያል እንደሚባለው ሊሆን ቢችልም እንኳን እንደ ፓርቲ መጠንቀቁ አይከፋም፡፡ በአግባቡ የቤት ስራችንን ሳንሰራ በፍጹም የቤት ስራቸውን በአግባቡ ካልሰሩ ፓርቲዎች ጋር ውህደት መፈፀምም ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ቅድሚያ ሁላችንም ያለንበትን በእሾክ የተሞላውን የዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ ምህዳር በመጥረጉ አንድ ላይ መስራት ይኖርብናል፡፡ ወንዙን በመሻገር አግዘኝና ይህንን እሰጥሃለው የሚባል ትብብርም ለህወሓት እና ሻዕቢያም እንዲሁም ለህወሓት እና ኦነግም አልበጀም፡፡ ትርፉ በደም እና በስጋ የተሳሰሩ ህዝቦችን በጠላትነት ከማፈራረጅ እና በደም ከማቃባት የዘለለ አልሆነም፡፡

ስለዚህም ትብብራችንም ሆነ ውህደታችን ከጥቅም ተኮርነት እና ጊዜያዊ ሆሆይታ ባሻገር የህዝብን የወደፊት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ዛሬ ዳቦ ያቋረሰ እና ፈንዲሻ ያስበተነ ውህደት ወይም ትብብር ነገ ሃገር ሊያቋርስ እና ህዝብን ሊበትን ይችላልና ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል፡፡ ውህደት ማለት የልብ እንጂ የወረቀት መሆን የለበትም፡፡ ሁሉም የቤት ስራውን ሰርቶ ሲጨርስ መሰረታዊ ልዩነቶቹ ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ ድርድር በማድረግ ውህደት ለመፈጸም በሩን ከፍቶ የሌሎችን መምጣት ሚጠባበቅ ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም የተዘጋ በር በተደጋጋሚ የሚያንኳኳ መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በውህደት ላይ ያለውን አቋም የአንድ ግለሰብ አቋም አድርገው በማቅረብ የፓርቲውን እና የአባላቱን ስም ለማጉደፍ የሚደረግ ሙከራ እውነትነት የሌለው ፍሬ አልባ ነገር መሆኑን ለማስረዳት ሰማያዊ ፓርቲ እንዴት እና ለምን ተፈጠረ የሚለውን ብቻ ማየት በቂ ይመስለኛል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የተቋቋመው ግለሰቦች ከህግ በላይ ሆነው መተዳደሪያ ደንብ እና መርህ እየተጣሰ መቀጠል የለብንም በሚል አቋም ከፓርቲ ጥለው በወጡ ግለሰቦች መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ታዲያ እነዚህ ህግ እንጂ ግለሰብ አይመራንም ያሉ አባላት እንዴት ዛሬ ለግለሰብ አስተሳሰብ ተገዢ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይታሰባል? እዚህ ጋር መዘንጋት የሌለበት ሁሉም የፓርቲ አባላት እንደ ፋብሪካ ውጤት ተመሳሳይ የሆነ አቋም አላቸው ተብሎ ሊወሰድ አይገባም፡፡ከአባላት ውስጥ ውህደትን የሚደግፉ ሊኖሩ ቢችሉም የእነዚህን አባላት አመለካከት ፓርቲው ለፓርቲው ጥቅም ከማሰብ መሆኑን ቢገነዘብም አብዛኛው የፓርቲው አባላት ለውህደት ጊዜው አሁን አይደለም ብለው የሚያምኑ በመሆናቸው የተያዘ አቋም እንጂ የአንድ ግለሰብ አቋም አይደለም፡፡

የፓርቲው ሊቀ-መንበርም ሆኑ የተቀሩት አመራር አካላት አብዛኛው የፓርቲው አባላት የሚያራምዱትን አቋም የራሳቸው ሆነም አልሆነም የማራመድ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን የሚያውቁ እንጂ የራሳቸውን ሃሳብ በሌሎች ላይ ለመጫን የሚደረግ ምንም አይነት ሙከራ የለም ብሎ ደፍሮ መናገር ይቻላል፡፡ በውህደት ላይ የፓርቲው አመራር አካላት የያዙት አቋም የሁሉም አቋም ላይሆን ቢችልም ሰማያዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እንደመሆኑ መጠን የአብዛኛውን አቋም የማራመድ ግዴታ እንዳለባቸው እንዲሁም ይህንንም ግዴታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆናቸውን ፓርቲው ያምናል፡፡

በመጨረሻም ፓርቲዬ ሰማያዊ ውህደት ፈጽሞ አያስፈልግም ብሎ የማያምን እና ከፓርቲዎች ውህደት በፊት ብዙ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገቡ የሚያምን መሆኑ እንዲሁም ሌሎች እንደ ፓርቲ መቀጠል ስላልቻሉ ብቻ ድክመታቸውን ወደ ሌላው በማጋባት ህልውናቸውን ለማስቀጠል የሚደረግ ሙከራ የመጠፋፋት ድርጊት እንጂ ውህደት አይደለም ብሎም ያምናል፡፡በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ከየትኛውም ፓርቲ ጋር አንድ በሚያደርጉን ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶቻችንን ተቻችለን እና ተከባብረን ለመስራት የምንፈልግ እና እየሰራንም የምንገኝ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል፡፡ የሆሆይታ ውህደት ከታሰበው ጥንካሬ ይልቅ ድክመትን ሊያመጣ ይችላልና በሰከነ አዕምሮ ቢታይ ይሻላል፡፡ ካልሆነ ግን ከላይ እንዳልኩት ‹‹ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል፡፡› #Miniliksalsawi

Image

የሐረር ሕዝብ ብሶቱ ቀጥሏል፡፡ አዲስ አበባ ያሉ ባለሥልጣናትም ዝምታቸው ቀጥሏል፡፡
በሃረር የህዝብ ብሶት ይገነፍላል የሚል ስጋት አይሏል::የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ በዘር ማንዘር የተሳሰረ የሙስና ሰንሰለት ዘርግቷል::የምንሊክ ሳልሳዊ ዘገባ::

በሃረሪ ብሄራዊ ሊግ የሚመራው የሃእርሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት እያለ ራሱን የሚጠራው ወያኔ ሰራሹ የጎሳ ጁንታ በሃረር እና አከባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ በደሎችን እየፈጸመ እንዲሁም ሃገርን እና ህዝብን እየዘረፈ በሙስና እና በመልካም አስተዳደር አጣብቂኝ ውስት ተዘፍቆ ህዝቡን እያስለቀሰ መሆኑን ከአከባቢው የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

በሐረር የሚገኙት የክልሉ ባለስልጣናት ዋና ግባቸው ስለልማትና ስለ መልካም አስተዳደር ሳይሆን ዘርፎ ስለመክበር እና በጫት ሱስ እግርን አጣጥፎ ከቤት ተጎልቶ መዋል ከሆነ አመታቶች ተቆጥረዋል፡፡ የክልሉ መንግስት መዋቅር በጎሳ የተቆጣጠረ በዘመድ አዝማድ፣ በዘር የተያያዘ በመሆኑ ማን ለማን ጥያቄውን አቤቱታውን እና ብሶቱን ማሰማት እንዳለበት አስቸጋሪ ሆንዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አዛውንቶችን በመደብደብ ሰውን ከነህይወት በማቃጠል እና ፍርድ በማጓደል እንዲሁን ከባድ ወንጀሎችን በመስራት የተካነው የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ እና አባሎቹ እንዲሁም የኦሕዴድ ተጠሪዎች ማሰር፤ ማባረር በፍርድ ቤት ማስወሰን፣ መቀማት፣ በልዩ ኃይል ማስደብደብ የመሳሰሉትን ድርጊታቸው የእለት እለት ተግባር ስለሆነ ሕዝቡ ለምዷቸዋል፡፡ በሃረር በጎሳ እና ካልተሳሰሩ የገንዘብ ሰንሰለት ካሌለ ባለሀብት የመሆን እድሉ የለም ፡፡ ማንኛውም ነገር የሃሰት እና የይስሙላ ነው፡፡ ለሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ገንዘብ ካልከፈለ ባለሀብት መባል ዘበት ነው::

ክልሉ የህዝቡን ትርታ ለማዳመጥ በሚል ለይስሙላ በጠራው ስብሰባ ላይ የተለያዩ ድርጅቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ተሰባስበው ውይይት በተደረገበት፣ የክልሉን ጉድፍ ያጋለጡና የተናገሩ ግለሰቦች በማግሥቱ የሥራ ዕገዳና ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው መደረጉ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ የህዝብን ብሶት ያሰሙ የመብት ረገጣ ዛቻ እና ስድብ ደርሶባቸዋል እየደረሰባቸውም ነው::

ይህንን ዘገባ ያጠናከረው ምንሊክ ሳልሳዊ እንዳለው ከከተማው የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች እንደሚጠቁሙት በሐረሪ የህግ ትርጉም በተግባር ሳይሆን በሃሰት-የህዝብ እድገት በጋራ ሳይሆን በወረቀት እና በጎሳ ነው፡፡ ከከፍተኛ የክልሉ አመራር ጀምሮ እስከቀበሌ ሹማምንት በውሸት የተሞሉ ናቸው::ዘረኝነትና የጎጥ መጠራራት ገንኖ፣ የጎሳ ፖለቲካ አክራሪነት ተስፋፍቶ፣ የሰው መብት እንደ ትቢያ በሚበተንበት ክልል፣ መልካም አስተዳደር አለ ተብሎ በፌዴራሉ ቱባ ባለስልጣናት መነገሩ የሚያስተዛዝብ ነው፡፡ ከማእከላዊ የመንግስት ቢሮዎች የሚመጡ የፌዴራሉ ባለስልጣናት የሚቀርብላቸውም ሆነ ይዘውት የሚሄዱት ሪፖት እጅግ አስደንጋጭ መሆኑ እየታወቀ የፌዴራል ባለስልታናት ዝምታ የፖለቲካ ስልጣን ማስጠበቂያ አስመስሎታል:: ህዝብን የሚያዳምጥ አስተዳደር ያጣው የሃረር ነዋሪ ቁጣው ገንፍሎ አደባባይ ሊወጣ ይችላል የሚል ስጋቱ አይሏል::የምንሊክ ሳልሳዊ ዘገባ::