የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ምክትል ሊቀ-መንበርና ሌሎች ሁለት ሰዎች ታሰሩብኝ አለ – VOA
ታሳሪዎቹ ላለፉት አምስት ቀናት ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ያደረሰን ዘገባ ጠቁሟል።
ታሳሪዎቹ ላለፉት አምስት ቀናት ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ያደረሰን ዘገባ ጠቁሟል።
የኖርዌይ ከለላ ጠያቂዎች ድርጅት ከፍተኛ አማካሪና የሕግ ባለሞያ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ስደተኞች ስጋታቸው ተገቢ ነው ይላሉ።
አህመድ 29 ዓመቱ ነው። ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ፤ ከኬንያ ደግሞ በብራዚል በኩል አድርጎ ወደ ፐሩ ኢኳዶር፤ ኮሎምቢያ፤ ፓናማ ይሸጋገርና በማእከላዊ አሜሪካ ደግሞ ወራት የፈጀውን የኮስታሪካ፤ ኒካራጓ፣ ሆንዱራስ፤ ጓቲማላ፣ ከዚያ በሜክሲኮ በኩል ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ያደረጉትን ጉዞ ያብራራል።
ዶክተር መረራ በዚህ ቅዳሜና እሁድ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ የሚካሄድ ”Vision Ethiopia” የተባለ ሲቪል ማህበረሰቦችና የፓለቲካ ድርጅቶች ጉባኤ ላይ ንግግር ሊያደርጉ ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሊመጡ ነበር።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ተከሳሾች፥ ለአራተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከሁለት ሣምንታት በፊት የመኪና መተላለፊያ መንገድ ዘግታችሁ ነበር ተብለው የታሠሩ 11 ተማሪዎች ደግሞ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
መንግስት ጉዳዩን በገለልተኛ አካላት ኢንዲጣራ እንዲያደርግና ችግሩን የፈጠሩት በሕግእንዲቀጡ አሳሰበ።
አቶ ንጉስ ገብረመድህን የተባሉ ኢትዮጵያዊ የሰው ልጅና እንስሳትን የመጉዳት መርዛማ ይዘት የሌለው የትኋን መድኃኒት ቀምመው አዘጓጅተዋል። የመድኃኒት ቅመማ እና የሕብረተሰብ ጤና ሳይንስ ባለሞያ አቶ ንጉስ ከሦስት ንጥረ ነገሮች ቀምመው ያዘጋጁት ይህ መድኃኒት በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑን ተረጋግጧል። …

የቀድሞው የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሁድ ኦልመርት (Ehud Olmert) ለአንድ ዓመት ከሰባት ወር የተፈረደባቸውን እሥር በዛሬው እለት ጀምረዋል። ሮበርት በርገር ለአሜሪካ ድምጽ ከእየሩሳሌም አጭር ዘገባ ልኳል። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል – ያድምጡ → listen

ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ ናቸው የሚባሉት የልዩ ኃይሉ አባላት በክልልሉ ዋና ዋና በሚባሉት አኝዋክና ኝዌር ጎሣቸው ተከፋፍለው መጋጨታቸው የተገለፀ ሲሆን ፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ገብተው ሁኔታውን መቆጣጠራቸውን እነዚሁ የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ባሁኑ ወቅት እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ይገኛሉ። በቅርቡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ለአውሮፓ ፓርላማ አባላት ማብራሪያ ለመስጠት ብራሰልስ እንደነበሩም ተዘግቧል። ዶክተር ብርሃኑን ወደ ዋሺንግተን ያመጣቸው ጉዳይ ምንድነው?በኢትዮጵያ መንግሥት ባሸባሪነት መፈረጃቸው በጉዞዎቻቸው ላይ ችግር ፈጥሮ ይሆን? ድርጅታቸው የአርበኞች ግንቦት 7 የወቅቱን በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ እንዴት ያየዋል? ሰሎሞን ክፍሌ ከዶክተር ብርሃኑ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ካነሳቸው ጥያቄዎች አንዳንዶቹ ናቸው። የውይይቱን ክፍል 1 ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ። ያዳምጡ → listen

የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳ፣ ቱጁቤ ኩሳና ነሞ ዳንዲ ወደ ተለያዩ ከተሞች ደውለው ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሉ። ያዳምጡ → listen
ኦሮምያ ክልል ውስጥ የተወሰደው የኃይል እርምጃ “ስህተት መሆኑን የኢትዮጰያ መንግሥት ባለሥልጣናት አምነዋል” ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አስታውቀዋል፡፡
በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባንና የፊንፊኔ ዙሪያ ዞኖችን የከተሞች ማስፊፊያ እቅድ ተንተርሶከተቀሰቀሰውና በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶችተማሪዎች ሲያካሂዱ የቆዩት የተቃውሞ እንቅስቃሴ የክልሉ መንግስት እቅዱንመተዉን ካስታወቀም በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።
ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ጊዳ ወረዳ፤ ጉደቱ አርጆ ከተማ በተከናወነ የሰርግ ሥነ ሥርዓትላይ በጭፈራው መሃል የተቃውሞ ድምጽ …
በሬክተር የምድር ንዝር መለኪያ 4.3 ያስቆጠረ የመሬት ነዉጥ ባለፈዉ እሁድ ምሽትና ሰኞ ጥዋት በሃዋሳ ከተማ መሰማቱ ተዘገበ።
የምድር ነዉጡ በሰዉ ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት አላደረሰም ተብሏል። ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮሮሬሽን ትንታኔ የሰጡ የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከርሰ-ምድር ጥናት ምሁርን መግለጫ ተንተርሶ እስክንድር ፍሬዉ ዘግቧል።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።
በኢትዮጵያ፥ በኦሮሞ ተቃዋሚዎችና በመንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች መካከል ለሁለት ወራት ግድም ግጭቶች ከተካሄዱ በኋላ፥ ባለሥልጣናቱ የአዲስ አበባን ግዛት ለማስፋት የኦሮሞ ገበሬዎችን ያፈናቅላል የተባለውን ማስተር ፕላን መሠረዛቸውን አስታውቀዋል።
ታዛቢዎች ግን፥ የመንግሥቱ ባለሥልጣናት የማስተር ፕላኑን ለመሰረዝ በወሰዱት እርምጃ ላይ ጥርጣሬ አላቸው።
እርምጃው በእርግጥ የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን ያመለክታል? ወይስ ለቀረቡበት ተቃውሞዎች ማስታገሻ ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ።
ባልደረባችን ሳሌም ሰለሞን ያጠናቀረችው ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል።
ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
በመሰላ አባድር ከተማ ደግሞ የአንድ ሌላ ተማሪ አስክሬን ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ተገኘ፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
በኦሮሚያ በሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ ወታደሮች መስፈራቸዉንም አስታወቁ።
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል ከስምንት ሳምንታት በፊት የጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባንና የፊንፊኔን ልዩ ዞኖችን ለማቀናጀት የተነደፈዉን ማስተር ፕላን በመቃወም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ትላንትና በዛሬዉ እለት በጂማና በሃሮማያ ዩኒቬርሲቲዎች ተካሂደዋል፥ የመንግስት ጸጥታ አስከባሪ ሃይሎችም ተማሪዎቹን በመደብደብ ተቃዉሞዉን መበተናቸዉ ታዉቋል።
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ በተፈጠረው ተቃውሞና አለመረጋጋት ምክንያት “ተገደለ” ያሉት ሰው ቁጥር ሰማንያ ዘጠኝ መድረሱን የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ ባለአምስት ጥያቄ መግለጫ አውጥቷል፡፡
የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ በኦሮሚያ ከተሞች ከሕዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረዉ ተቃዉሞ ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀጥሏል። ተቃዋሚዎቹ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ ለተገደሉት ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል የሚል መፈክርም ጨምረዋል።
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በዛሬው ዕለት መታሠራቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር ኣቶ ይልቃል ጌትነት ኣስታወቁ። ኣቶ ይልቃል ጌትነት ይህንና ወቅታቂ ጉዳዮችን በተመለከተም በነገው ዕለት መግለጫ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።ይህ ጉዳይ በተመለከተ ከቶ ይልቃል ጌትነት ጋር አጠር ያለ ቆይታ ያደረገችው ጽዮን ግርማ ነች ።
ሰማያዊ ፓርቲ፤ የፓርቲው ልሳን የኾነው የ”ነገረ ኢትዮጵያ” ጋዜጣ አዘጋጅና ሌሎች ሦስት ንቁ ተሳታፊ አባላቶቹ እንደታሠሩበት አስታወቀ፡፡
ኦሮሚያ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ ሁለተኛ ወሩን ያዘ።
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና ከኦሮሚያ ከተሞች ዐዋጅ ጋር ተያይዞ ኦሮሚያ ውስጥ በተነሣው ተቃውሞና ግጭት የብዙ ሰው ሕይወት መጥፋቱና ከ3500 ሰው በላይ መታሠሩን ኦ.ፌ.ኮ አስታወቀ፡፡ከአምስት ወራት በፊት የተፈቱት የቀድሞ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባም መታሠራቸው ታውቋል፡፡
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች የሆኑ ከመቶ በላይ ረዳት መምህራን ከሁለት ዓመታት በፊት ለጠየቁት የሥራ ዕድገት መልስ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው እየተናገሩ ነው፡፡
በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ፣ በጉጂ ዞን፣ በሃርቀሎ ወረዳና በሆሮ ጉዱሩ፤ በወለጋ ኢበንቱ ወረዳ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸውና በመከላከያ አባላት እየታሠሩ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የቴሌቪዥን ዘጋቢውንና ዜና አቅራቢውን ፍቃዱ ምርካናን ከእሥር እንዲፈቱ ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ቡድን – ሲፒጄ ጠየቀ፡፡
የጂቡቲ የጸጥታ ሃይሎች ዛሬ በአንድ ሀይማኖታዊ ኩነት ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልኛ አገልግሎት ተናግረዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ ሃይማኖታዊው ኩነት እንዳይካሄድ ያስጠነቀቁ ቢሆንም አዘጋጆቹ ችላ እንዳሉትና ሟቹ ሃይማኖታዊ መሪ ሼኽ ዮኒስ ሙሴን ለማሰብ እንደተሰባሰቡ ምንጮች ጠቁመዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ የተሰባሰቡትን ሰዎች ለመበተን ሞክረው እንደነበር ጂቡቲ ያሉት ጋዜጠኞችና እማኞች ተናግረዋል። በሀገሪቱ ያለ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደተገድሉ ዘግቧል። ሌሎች ምንጮች ደግሞ ከዛ የበዛ ነው ይላሉ።
የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አራተኛው ፓትሪያርክ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከረዥም ጊዜ ህመም በኋላ ዛሬ ማረፋቸው ታውቋል።
ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ሲቃወሙ ሰንብተዋል። የተቃውሞን ጅምር የሚያትተውን የማርታ ፋን ደር ቮልፍ የአዲስ አበባ ዘገባ ጨምራ፤ ጽዮን ግርማ የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ የተመለከት ርእሶችን ይዛለች፡፡
በትናንትናው እለት በኦሮሚያ በሰላማዊ ሰልፍ ወቅት የተገደለ ወጣት የቀብር ሥነ-ስርዓት።
የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል፡፡
በሰሜን ጎንደር እና አካባቢው በቅማንት ብሔረሰብ አባሎችና በአማሮች መካከል ግጭት መከሰቱና የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ትላንት ባስተላለፍነው ዝግጅት ማሰማታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የችግሩ ሰላባ ከሆኑት መካከል አንድ ሰማቸን ለመግለጽ ያልፈለጉ የትግራይ ተዋላጅን አነጋግረናል።
ውጭ ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ከሃገር ውስጥ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሁከት አስመልክቶ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ።
የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ያገረሸው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ፡፡የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሰጡት አስተያየትም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
“አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ፤ በእነኚህ ጉዳዮች ላይ፥ በዓላማው ላይ፥ በይዘቱ ላይ፥ የተማላ ግልጽነት፥ የተሟላ መተማመን፥ የተሟላ የጋራ መግባባት ባልተያዘበት ሁኔታ እነዚህ ጥያቄዎች እየተነሱ እያሉ የክልሉ መንግስት አይቶ እንዳላየ ሆኖ ዘሎ ወደ አፈጻጸሙ የሚገባበት ሁኔታ አይኖርም። ይሄንን ለሕብረተሰቡ ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን።” የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር…
ሳውዲ አረብያ ለመጀመርያ ዚዜ ሴቶችን ያሳተፈ ምርጫ አካሄደች
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዛሬ (Dec. 7) ፕሮግራማችን ባለመደመጡ ይቅርታ እንጠይቃለን። በዚህ እለት 44ቱም የአሜሪካ ድምፅ ራድዮና ቴሊቪዥን እንዲሁም በኢንተርነት የሚሰራጩ ፕሮግራሞች ያልተደመጡበት ምክንያት በሕንፃው የኤሌትሪክ ሓይል ሥርጭት በመግጠሙ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን። ፕሮግራማችን በነገው እለት ይደመጣል።
ዝናቡ በመቅረቱ የተዘራው ጤፍም ሆነ ስንዴ ምርት አለማፍራቱን የምዕራብ አርሲ አርሦ አደሮች ገልፀዋል።
በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በተማሪዎች የሚካሄድ ሰልፍ ዛሬም መቀጠሉ ታዉቋል።
በተቃዋሚዎች ላይ የጸጥታ አስከባሪዎች በሚወስዱት እርምጃም የሰዉ ሕይወት እንደጠፋ፥ የቁሰሉና የታሰራ እንዳሉ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ቃለ ምልልስ የሰጡ ነዋሪዎችና የተቃዋሚ ፓለቲካ ተወካዮች ተናግረዋል። በነሞ ዳንዲ የተጠናቀረዉን ዘገባ ዝርዝር ትዝታ በላቸዉ ታቀርባለች።
የብሪታንያ የጦር አይሮፕላኖች ሶርያ ውስጥ የአየር ድብደባ ጀምረዋል። ድብደባውን የጀመሩት የብሪታንያ የምክር ቤት አባላት እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ጽንፈኛ ቡድን ለማሸነፍ እንዲቻል የሀገሪቱ ስትራተጂ እንዲሰፋ ዴቪድ ካምሩን ያቀረቡትን ሃሳብ ካጸደቀ በኋላ ነው – VIDEO ↓
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
በትናንቱ ዕለት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወታቸው ያለፈና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች እንደነበሩ ተገለጸ። በተለይም ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (Haramaya University) በደረሰ ግጭት የመንግሥት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ሁለት ተማሮች መሞታቸው ታውቋል።