ሸክሙ አስቸገራቸው፣ መተንፈስ ጀመሩ፣ ወንዶቹ ሲፈሩ፣ ሴቶች ተዳፈሩ፣ የሕሌናቸውን፣ ደፍረው ተናገሩ። ባለፈው ለት ሜሮን በግጥም ተነፈሰች፣ የውዳሴ ከንቱ፣ መመሪያውን ጣሰች፣ ሥሙኝ ብላ ጮኸች፣ ውርድ ከእራሴ እያለች፣ ለሁሉ አዳረሰች፣ ለሁሉም አሰማች፣ ያለውን አንድ በአንድ፣ እየዘረዘረች፣ ወቼ ጉድ አሰኘች፣ ሕዝብን አሥደመመች ወዳጅ …

ሴቶች ደፈሩ Read more »

ዛሬ በአዲስ አበባ የጥምቀት ባህል ላይ የቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖት የታቦት ሽኝት ላይ ከወያኔ ደጋፊዎችና ሰላዮች ጋር በተፈጠረ ግጭት በርካታ ወገኖች የቆሰሉ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። በግጭቱ ወቅት የፌዴራል ፖሊሶች ከወያኔ ደጋፊዎች ጎን ተሰልፈው ወጣቶችን በፋሽስታዊ ጭካኔ ግንባራቻው እስኪተረተር ሲደበድቧቸውና …

ዛሬ አዲስ አበባ በጥምቀት በዓል ላይ ከወያኔ ፖሊሶች ጋር በተፈጠረ ግጭት በርካታ ወገኖች ተጎዱ፥ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ Read more »

የዛሬው የጥምቀት በዓል እንዲህ ሰማያዊ ሆኖ ነው የተከበረው፡፡ አዘጋጆቹ የቲሸርቱን ቀለም እንዲቀይሩ በደህንነቶችና በፖሊስ ወከባና ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም ‹‹የምንለብሰውን ልብስ ቀለም አትመርጡልንም›› ብለው ሰማያዊውን ቲሸርት ለብሰውት ውለዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት እስማኤል ዳውድ ዛሬ ከጠዋቱ በ12፡30 ገደማ ሁለት ታጣቂ ፖሊሶች እና ሁለት የደህንነት ሰዎች መኖሪያ ቤቱ መጥተው ጃንሜዳ ፊት ለፊት በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ መታሰሩ ተገለጸ፡፡ እስማኤል ዳውድ በአንድነት ፓርቲ በኩል በምትታተመው የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ በ …

የአንድነት ፓርቲ አባሎች ጃንሜዳ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሩ Read more »

ሴራሊዮን ውስጥ በአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ ህይወቱ ያለፈውና በሽታው ኢቦላ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የደም ናሙናው ወደ ውጭ ለምርመራ የተላከው ኢትዮጵያው ጋር ግንኙነት አለው የተባለው የአምቡላንስ ሰራተኛና ከእሱ ጋር ተገናኝተዋል የተባሉ ሌሎች 10 …

ፖሊሶች በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ሰፈር ከኢቦላ ጋር በተያያዘ አሰሳ እያደረጉ ነው – (ነገረ ኢትዮጵያ) Read more »

(አርአያ ተስፋማሪያም) ልኡል ገ/ማርያም ይባላል፤ የሕወሐት አባል ሆኖ በዳኝነት ያገለግላል። በዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት፣ በቅንጅት አመራሮችና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ እድሜ ልክና ሞት የፈረደ ነው። ዙቤር የተባለ ሃብታም የገዛ ጓደኛውን በውሻ እያስነከሰ በጥይት ደብድቦ ከገደለው በኋላ ጉዳዩ የቀረበው ልዑል ዘንድ ነበር። የፈርደበት …

ፍርደገምድሉ ዳኛ ልኡል ገ/ማርያም Read more »

(ዳዊት ከበደ ወየሳ) ሰሞኑን የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርስ የነበረው ጣይቱ ሆቴል በእሳት ወደመ:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታዲያ “አቃጠሉት” እና “አቃጠሉበት” የሚሉት ድምጾች በርክተዋል:: “አቃጠሉበት” የሚለውን የጨዋታ ክር መምዘዝ ከጀመርን; የቤቱ ባለቤት ፍጹምዘአብ ጋር ያደርሰናል:: ፍጹምዘአብ የትግራይ ተወላጅ ነው:: ግን ደግሞ የትግራይ …

ከሆቴሉ ጀርባ… በወላፈኑ ውስጥ የሚታየው ፍጹም ዘአብ አስገዶም ማን ይሆን? Read more »

የሲዳማ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆነው አቶ አንተነህ አሰፋ ‹‹ማደራጀት ህገ ወጥ ነው፣ ፓርቲያችሁ ወጣቶችን እየመለመለ ወዳልሆነ አቅጣጫ እየወሰደ ነው›› በሚል መታሰሩን የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ደም መላሽ አበራ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አንተነህ አሰፋ በትናንትናው ዕለት ከምሽሩ 12 አካባቢ …

የሲዳማ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ‹‹ማደራጀት ህገ ወጥ ነው›› ተብሎ ታሰረ Read more »

በዳንኤል ተፈራ ያሳለፍነው ሳምንት በሕወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተሰልተው፣ ታስቦባቸው ይፋ ከተደረጉና አሻንጉሊቱ ምርጫ ቦርድ እንዲፈጽመው በህወሃት ሰዎች ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቶት ገቢራዊ እንዳደረገው የሚጠረጠረው የፖለቲካ ጉዳይ ይፋ የተደረገበት ነበር፡፡ ይሄው ጉዳይ በአይረቤ ሰበብና በምክንያት አልባ ሁነት ግን ዳግም ከቤተ-መንግስት በወጣ ትዕዛዝ በሚመሰል …

የኢትዮጵያ ምርጫ መቆመሪያ ተቋም ገመና Read more »

(Finote-Netsanet) – ወይዘሪት ወይንሸት፣ ንፍስ ስልክ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ሁለት ሰዎች ከረፋዱ 5፡30 ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባት ለፍኖተ-ነፃነት የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡ ወይዘሪት ወይንሸት፣ ነፍሰጡር መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን ደብዳቢዎቹም ሆዷን በመርገጥ ድብደባውን ሲፈፅሙባት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደብዳቢዎቹ ድብደባውን ፈፅመው የተሰወሩ ሲሆን …

የአንድነት ፓርቲ ሴቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመባት Read more »

(ከሄኖክ የሺጥላ) ጸሐይቱ የድል ብርሃኒቱ የነጻነት ቀንዲሊቱ እምቢታሽ ያስጨነቃቸው ድልሽ የረበሻቸው ባንዳነት የወለዳቸው ባንዳነት ያሳደጋቸው ባንዳነት የሰየማቸው ይኸው ምን ቀራቸው ? እንደ እባብ እየተሳቡ ጠግበውም ስለ ተራቡ የማጀትሽ እንጀራ ሞሰብሽ ባይመልሳቸው እልፍኝሽን አቃጠሉት ያው በለመደ እጃቸው ! ጣይቱ አንቺ እናቲቱ …

ጣይቱ ( ከሄኖክ የሺጥላ ) ክፍል አንድ Read more »

ደረጀ ነጋሽ በአዲስ አበባ የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ተሠርታ በምትመረቅበት ጊዜ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ መኳንንት ለምረቃው ተጠርተው ነበር፡፡ ለተጠራው እንግዳ ማሳረፊያ እንጦጦ አይበቃ ስለነበር እቴጌ ጣይቱ ከእንጦጦ ተራራ ሥር ያለው ሕዝብ ሁሉ ለሚጠራው እንግዳ መጠለያ ቤት እንዲሰጥ ለመኑ፡፡ እንግዳ የሚያሳድር ሁሉ …

ጋሼ ጳውሎስ ኞኞ በጻፈው “አጤ ምኒልክ” መፅሐፍ ገጽ 328-330 የሆቴሉ ታሪክ እንዲህ ይነበባል Read more »

ናኦሚን በጋሻው ጥያቄዉ አሁን ምርጫዉን ቦይኮት የማድረግ እና ያለማድረግ አይደለም። የአንድነት ፓርቲ ምርጫዉን እንደሚወዳደር ይፋ በማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ነበር። ብዙዎች “አንድነት እንዴት ምርጫዉን እወዳደራለሁ ይላል” የሚል ትችት አቅርበው ነበር። የአንድነት አመራሮች ግን፣ አንድነት በምርጫዉ የሚሳተፈው በምርጫ ቦርድ ተማምኖ ሳይሆን በሕዝቡ …

የመርጋና የትግስቱ ታንጎ ዳንስ (አንድነትን በተመለከተ) Read more »

ተዉኝ አትቀስቅሱኝ አታንቁኝ ከእንቅልፌ፥ የናንተን ካልነካሁ መስመር ተላልፌ፥ እንዳሻኝ ልጋደም ላስቲኬን ለብሼ፥ በቃሽኝ ካላለች ምስኪኗ ፍራሼ። እኮ ተዉኝ በቃ ከቶ አታስጨንቁኝ። ለምን አትነሺም ብላቹ አጠይቁኝ። ምን ላደርግ ልነሳ ከሰመመን ልንቃ? ሀሰት ስልጣን ስትይዝ እውነት ተደብቃ፥ የቃየልን ዙፋን የአቤልን ሰቆቃ፥ የጥጋብ …

ተዉኝ Read more »

…አርቲስት አስቴር በዳኔ ከተቀመጠችበት ወደፊት ወጥታ ማይኩን ስትጨብጥ ፍርኃት ቢጤ እንደወረራት ከመጀመሪያው ያስታውቃል፡፡ ‹‹በጣም ነው የሚያስፈራው፤›› በማለት የጀመረችውን አስተያየቷን የያዘችውን ማስታወሻ እያነበበች አስተያየት መስጠት ቀጠለች፡፡ ‹‹ይህንን ዕድል ተመቻችቶልን በቴሌቪዥን ስናየው የኖርነው ታሪክ ለማየት ስለቻለን እጅግ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ በፊት የነበረኝ ያልተጨበጠ አመለካከት በመረጃ የተደገፈ ሆኗል፤›› በማለት ሐሳቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹እውነትን መናገር እወዳለሁ፡፡ የሐሳብ ነፃነትም አለ፡፡ በእርግጥ […]

ዐይኔ አይታክተው ፤ ላንችም አለቀሰ ጣይቱ አቃጠሉሽ? ፤ ቅርስ ተደመሰሰ ተመሪው ባለሀብት ፤ ማን ይሆን ወራሹ ባለሥልጣን? ወይስ ፤ ሙስናን አጉራሹ? አዲሲቷ ኢትዮጵያ ፤ ኃዘንሽ መራራ ኩራት ሥልጣኔሽ ፤ ማንነት አሻራ የአንድ ዘር ተደርጎ ፤ የነገደ አማራ ፍርድ ተላልፎበት ፤ …

ጣይቱ! Read more »

http://www.eaglewingss.com/%E1%8B%A8%E1 … %E1%8C%A5/

የጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ እጅ ያለዉ ዶሮ ወጥና ፖለቲካ
Samson K.

Posted By Samson K.

በቅርቡ ተጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደስ አለኝ ዓረብ ሐገር ያዩትን ወገንና አዉሮፓ መጥተዉ ያዩትን የወገን ችግር፣በምፀት ሲገልፁ- ብዙ እንቶ ፈንቶ ተናግረዉ ነበር ፈረንጆቹ bla -bla ይሉታል ፣ ከዛ ዉስጥ ግን አንድ አነጋገራቸዉ ቀልቤን ስባ ሌላም ነገር አስታወሰችኝና ትንሽ ልበል ብዬ እኔም ብዕሬን አነሳዉ ።

ምን ሆነዉ ነው እንደዚህ በሰዉ ሐገር እሚሰቃዩት -ሐገራቸዉ ቢሆኑ ጠግበዉ መብላት እንደሚችሉ, ስደተኛዉን ኢትዮጵያዊም ሆነ ያገሪቷን ክብር በወረደ ቃላት ሲዘባበቱበት ከራሳቸዉ አንደበት ሰማሁና ፣ ታዲያ ይሔን ግዜ ምን አሰብኩ እኝህን ጠቅላይ ሚንስትር በዙሪያቸዉ ያሉ የድሮ ማርክሲስት ኤሊትሶች ይህን እንዲናገሩ እና እንዴት ከጨወታ እያስወጡዋቸዉ እንደሆነና መጨረሻቸዉም ከግዜሩም ከሰይጣኑም እንዳይሆኑ ተደርጎ የስርዓቱ የተሞላ አሻንጉሊት ሲሆኑ ማየቱ እንደዜጋም እንደሰዉም ስላሳዘንኝም ነዉ ።

ባንድ ዎቅት በፈረንሳይ ዓብዮት የፈረንሳይ የተራቡ ጭሰኞች በ፩፯፯፭ 1775 በፈረንጆቹ አቆጣጠር ባነሱት የዳቦ ጥያቄ ልዕልቲቷን ማሪይ አንቶይነት Marie Antointte ዳቦ ከሌለ ለምን ኬክ አይበሉም ዎይንም ደግሞ ኬክ ይብሉ ብላ የተናገረችዉን በወቅቱ የነበረዉ ምሁር ዓብዮተኛ የልዕልቲቷን አባባል በሁለት መንገድ ሰንጥቆ የህዝብ ቁጣ public plight መቀስቀሻ ተደርጎ በወቅቱ የነበረዉን የቡርዥዋ የመደብ አርስቶክራሲ aristocracy ችግር በማሣየትና እና የልዕልቲቷን ኦስትሪያዊነት ከፈረንሳይ ሞናርኪ ሉዊስ ፩፮ኛLouis XVI. ለመገንጠል የርስዋን አባባል ለፖለቲካ ትርፍ ተጠቅመዉበታል ።(ላንባቢያን- እንደማስታወሻ እንደምርቃትም ትሆነን ዘንዳ በዚች ዙሪያ ትንሽ ብናክል)-በነገራችን ላይ እዚህ ጋር አንባቢያን ስለዚህ አባባል በተለያዩ የታሪክ ፅሁፎች ዉስጥ ለምን ኬክ አይበሉም ያለችዉ ማሪያ ተረዝ Maria Therese ትባል የነበረች የፈረንሳዩ የሉዊስ ፩፬ኛ XIV ሚስት የነበረችዉን እንደሆነም ይነገራል ይህንንም የፃፈዉ ለመጀመሪያ ግዜ ዤን ዣኹዊዝ Jean -Jacques Rousseau ይባል የነበረ የፖለቲካ ፈላስፋ ‘ኑዛዜ’ ዎይንም ‘ኮንፌሽን confession ‘ብሎ ባሳተመዉ መፅሐፉ ዉስጥ እንዳሰፈረ የተለያዩ መጣጥፎች ይናገራሉ በዚ ጉዳይ እስካሁን ብዙ የታሪክ ፀሐፍት ለሁለት እንደተከፈሉ ነዉ ፤አንደኛዉ ወገን Marie Antoinette የማሪዬ አንቶይነት አባባል ሲል ሌላኛዉ ደግሞ የማሪያ ተሬዝ Maria Thereseነዉ እንዳለ ነዉ ። Louis XVIIሉዊስ ፩፰ኛም በራሱ ብዕር በ፩፯፱፩ (1791) አጠናቅሮ እንደፃፈና ኣባባሉም የማርያ ተረዝ መሆኑን የፃፈዉ ማስረጃም እንዳለ እሚተርኩ አሉ )

እናም ታዲያ ወደተነሳሁበት ርዕስ ስመለስ የኙ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማሪያም ደስ አለኝ የጀርመን German ጉብኝት ወገን በመጠለያ ካምፕ ዉስጥ ባዶ ዱቄት ሲበላ አይተዉ የተናገሩት የማሪዬን Marie A.ዎይንም ማሪያ ተረዝ Maria Therese አባባል ስላስታወሰኝ እና መጨረሻቸዉም ስላሳዘነኝም ነዉ። ዱቄት ለምን ይበላሉ ዶሮ እያለ ከሆነ አባባላቸዉ ለኛ ሐገሩ ሐይለ ማሪዬ Marie የዘመናችን ያበሻ አባባል phrase ሆና እንዳትቀር ያስፈራል ፤ ከሆነ እንግዴ ሳንወድ በግድ ከ ማሪዬ Marie .A እና ከ ማሪያ Maria Therese ጎን ሌላ ያበሻ ሃይለ ማርዬ Marie ልንጨምር ግድ ይላል ማለት ነዉ- አጃኢብ ነዉ ። ለኛ ሐገርም ራሳቸዉን ለለዩ የመደብ ማርኪሲስት aristocrats መካከልና በቅዠት እሚኖረዉን የምንዱባን ህይዎት ባጠቃላይ ባያሳይልንም በከፊል ግን የሳቸዉ አባባል ያለዉን የመንግስትና የህዝብ ክፍተት ፍንትዉ አድርጎ ያሳያል – ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

ብዙዉን ግዜ ያንድ ሐገር ጠቅላይ ሚንስትር ባገር ጉዳይ ስራ ላይ በሚሆንበት ግዜ የራሱ ያነጋገር ዘይቤዎች፣ የሚናገራቸዉ የሚጠቀማቸዉ ቃላትና አባባሎች ዕጅግ ጥንቃቔ ይደረግባቸዋል ፤ያም እሚሆነዉ የባለስልጣኑ አነጋገርና አካሔድም ሆነ አቀማመጥ ፕሮቶኮል የመላዉን ህዝብ እና ሐገር ስለሚወክል ነዉ ። ስለዚህ የራሱ የሆኑትን ልማዶችና ዕምነቶች በህዝብ ፊት ዎይንም በማንኛዉም የሚዲያ መገልገያ አዉታሮች ላይ ዕንዳይጠቀም የስራዉ ሃላፊነትና የስልጣኑ ደረጃ ባያስገድደዉም ፣ነገር ግን ብያንስ ግድ ይሏል። ይሔም ማለት በቀላል አገላለፅ ክብርንና ደረጃን ሐገርንና ህዝብን በሚመጥን መልኩ ማለት ነዉ፤ ፕሮቶኮል ጠባቂ ዎይንም ደምብ ጠባቂ ሹሙ ቢቻል ቀድሞ ይቀርፀዋል፤ ካልሆነም ቀድሞ ምክር ይሰጣል ። የዶሮ ወጥ ይዞ ስለመጉዋዝና ስለግርድና ስራ፣ ስለ ወገን ሰደተኝነት ማብጠልጠልና ተራ አነጋገርና ቃላትን መጠቀም ትርፉ ራስንና አገርን ማዋረድ ካልሆነ በቀር ሌላ የፖለቲካ ትርፍ አለዉ ቢባል ጅልነት ነዉ።

ለዛዉም ደግሞ ሲደተኞቹ የጦር ምርከኞች ሳይሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች ሆነው የጀርመን መንግስትም ወስዶ ማስጎብኘቱ ሌላዉ ልብ ያላሉት እና ያልተዘጋጁበት ይመስላል ፤ ይህም ቢሆን ባዉሮፓ የስደተኞች አያያዝ ህግ መሰረት ለጀርመን መንግስትም ቢሆን የፖለቲካ ኪሳራ ነዉ ፤የታደጉዋቸዉን ሰደተኞች ለገዳያቸዉ ዎይ ደግሞ አሳዶ ላስወጣቸዉ መልሰዉ ካስጎበኙም የሚያሳዝን ነዉ። ይልቅ የዶሮ ወጡን ይዘዉ የመጡት ለዘመዶችዎ ከሆነ እና እዛዉ ጣቢያ ዉስጥ በስደተኛ ስም ለልዩ ስራ የተመደቡ ከሆነ ዕርግጥ ነዉ እነዚያ ሰዎች ምን ጎሎአቸዉ እና ምን አጥተዉ አንደሆነ እኛም አናውቅም እርሶንም ያ ከሆነ ያንገበገቦ ሚስኪኑን ትክክለኛ ስደተኛ ሳይደርቡ ለይተዉ ቢነግሩን ጥሩ ነበር።

በጀርመናዉያንም ጓደኞቻቸዉ ‘ኸይም’ heim (መጠለያ) ትርጉሙ ተነግሮአቸዉ’ እተዘጋጀ የስደተኞች ጣቢያ ተኪዶ ወገንን -ያንድ ሐገር ጠቅላይ ሚኒስትር ቆሞ ሲያሾፍና ሲዘባበት ያንን በህዝብ የመገናኛ ጣቢያ እንደ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ ወሰደዉ መደስኮሩ ፣ ፖለቲካ ሳይሆን ተራነትንና መደዴነትም ነዉ። ያገር ክብር የህዝብ ክብርን ከምንም በላይ ተምሳሌት ሆኖ እሚገለፀዉ በመሪዉ ነዉ ይሔን ክብር ነዉ ፈረንጆቹም DIGNITYዲግኒቲ እሚሉት ሐገር ህዝቡ ቢደኸይም በምንም ዓይነት ግን የራስ ክብርን dignityዲግኒቲ አሳልፎ አንድ ያገር ጠቅላይ ሚኒስትር እራሱንና ህዝቡን ባደባባይ አያዋርድም ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የክርስቲያን ሃይማኖት መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥም ሙሴ ያንን በባርነት ስር የነበረዉን ወገኑን አዝኖ አከበረው እንጂ አላዋረደዉም ፤ ክብር ለሰዉ በሰዉነቱ ፣ክብር ለህዝብ በማንነቱ፣ ክብር ለወገን በወገንነቱ ፣መስጠት ልማታዊ ባያረግም ነገር ግን ስልጡን ያረጋል ሙሉ ስብዕናንም ያላብሳል።

ጉብኝቱን የፈቀደልዎት የጀርመን መንግስት ዘመዶችዎ በመጠለያ ጣቢያዉ እንደነበሩ አሳዉቀዉ ከሆነ ፣ይኼም ቢሆን ለራስዎ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ኪሳራ ሲሆን ለመላዉ ኢትዮጵያዊ ግን ዉርደት ነው። የጀርመን መንግስት ለርስዎ ጣቢያዉን ማስጎበኘቱም ባለም አቀፍ የስደተኞች አያያዝና የደህንነት ህግ አንቀፅ ጥሰት ሊያስጠይቀዉ እንደሚችል ሊያዉቁትም በተገባ ነበር ፤ ይሔንንም ባደባባይ ሲያወሩ ባዶ አማኝና ባዶ ፖለቲከኛ መሆንዎን ነው የሚያሳየዉ ።ለዚህም ነዉ የፕርቶኮል አስፈላጊነት በመሪ ደረጃ እንዲህ ያሉ ተቀጣጣይ የሆኑ አነጋገሮችን ቀድሞ እሚያርመዉ፤ ያለበለዚያ ራስንም አገርንም ተኩሶ እንደመምታት ነዉ ። ጠቅላይ ሚኒስትራችን የፊንላንድ finish ተማሪም ሆነዉ ኸይም heim ምን ማለት እንደሆነ አለማወቆን በሚድያ መናገርም በዉነት የፖሊቲካ አሽሙርም (political sarcasm) አለያም ደግሞ መሞዳሞድ( humor) ሊሆን አይችልም፤ ይልቅ ትዝብት ዉስጥ ነዉ የጣሎት።ጠቅላይ ሚኒስትራችን በፊኒሽ Finish ምድር የዉሃ ጥናት ትምህርቶን ሲወስዱ master ማስተር አድርገዉ የወጡት በዉሃ ላይ መንሳፈፍን ብቻ ይመስላል ለዚህም ነዉ በፖለቲካዉም ከሞራሉም አኳያ ራስዎን ሳይሆኑ እንደብርቅዬዋ የፊንላንድ ዳክዬ ተንሳፈዉ የሚታዩት the whooper swan ።

ለዚህ ርዕስ መነሻ የሆነን የሰሞኑ ትኩስ የመነጋገሪያ ኣጀንዳ የሆነዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንጝግር ነዉ። ዋናዉ መልክታችን የሰዉየዉ የራሳቸዉን ህዝብ ማሳነሱና መዝለፉ ላይ ሳይሆን ሰዎቹ የተዘለፉበትን ምክንያቶች ላይ ትንሽ ለማለትና ምናልባትም ጠቅላይሚኒስትሩ ራሳቸዉንና ሰርዓታቸዉን ዞር ብለዉ ቢያዩበት ከሚል ነዉ።

ዛሬ በኢትዮጵያ ስለሚታየዉ የወጣት ሰቶች፣ ወጣት ዎንዶች ፣ የባለሙያ ምሁራን ስደት ዋናዉና ትልቁ ምክንያቱ የኢኮኖሚ ምኪንያት ሳይሆን ባገሪቱ ያለዉ የሰርዓት ኣልበኝነትና ስርአቱ ባመጣዉ የፖለቲካ ጫና ነዉ ።

ዛሬ ያለዉ የገዢዉ ሥርዓት በሰዉ ፍልሰት ንግድ በግልፅ በመሰማራቱና ባሰማራቸዉና ስርዓቱ በዘረጋዉ ዘመናዊ የሰዉ ንግድ ቀለበት ዉስጥ አንዲገቡ በተደረጉ ዜጎችና በተለይ ድግሞ ሆን ተብሎ በዘዴ የመሬት ንጥቂያና ዝርፊያዉ ባልተማሩና ምንም አይነት የስራ ሙያ ትምህርትና ልምድ በሌላቸዉ ሚስኪን የገበሬ ልጆች ከብቶቻቸዉን እና ያላቸዉን ጥሪት በዘዴ እንዲሸጡ እየተደረገ ገበሬዉን ያለዓምራች ሃይል እንዲሆን በማድረግና ያገሪቱን መሬት እና አንጡራ ሃብት ለዉጭ ባለሃብቶች አየተሰጠ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስዉም መሬቱም እኩል እየተሸጠ እንዲሰደድ በማስገደድና የመኖሪያ ቦታ በማሳጣትም ጭምር ነዉ።

እንዲሁም ዜጋዉን መሬት አልባና አገር አልባ በማድረግ ስደተኛ የሚል ተቀፅላ ስም ዎይንም መጠሪያ እንዲሸከም በመደረጉ ነዉ። ሰደተኛ በሚያደርገዉ የሥርዓቱ ዉጤት የዜጎች ስቃይና ያለፍላጎት የተሸከሙት ስደተኛ የሚለዉን ስም ነዉ ።

ዛሬ ያንድ ኢትዮጵያዊ የስደት ጉዞዉን እና አገር ለቆ የሚወጣበትን ሚክንያቶች በቅጡ ለተገነዘበ ሰዉ ኢትዮጵያዉያኖች ባገራቸዉ ያለዉን ከባድ ስራ ንቀዉ ሳይሆን ባገራቸዉ ያለዉን ከባድ የፖለቲካ ጫና፣ አፈና፣ ግድያ፣ እስር፣ የስራ ዕጦት፣ የምግብ ርሃብ፣ እና የነፃነት ርሃብና ፣ የቁም ቅዠት የሆነዉን የኑሮ ልዩነት ሽሽት የፍትሕ አለመኖር መሆኑ ግልፅና የማያከራክር ነዉ ።

እዚም በረንጆቹ አገር ዛሬ ያበሻን ስደተኛ በለበጣ ለተሻለ ሕይዎት ስደትን የሚመርጥ የስደት ገበያተኛ የሚል ቅፅል ስም አስከማዉጣት ተደርሶአል ፤በዚሁ አገር አባባል እንደወረደ አሲል ሾፐርስ asyl kjopers ፡ በንግሊዝኛዉ አሳይለም ሾፐር ASYLUM SHOPER ማለት ነዉ ። የዚን ወገን ህዝብ እመራለሁ የሚሉ ያገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝ የዶሮ ዎጥ ይዘዉ መምጣታቸዉ ካዉሮፓ ዱቄት ሰፋሪዎች ጋር ሆነዉ የራስ ወገንን ችግር እያዩ ማላገጡ የሚያስከብር ሳይሆን ራስን እሚያዋርድና ራስንም መስደብ መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል ።ዱቔት ሲያቦኩ እና የሰዉ መኪና ተደግፈዉ ፎቶ እሚልኩ ያልዋቸዉ ወገኖች ናቸዉ በያረብ ሃገር ፣ባዉሮፓ፣ ባሜርካ ፣ኤሲያ ሌት ተቀን እየሰሩ ባገራችን ያለዉን የዘመናት ድህነት ለመቀንስና ቢያንስ የየራሱን ቤተሰብ በመደጎም ዙሪያ በዉጭ ያለዉ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነዉ ትልቁን የለት ተዕለት ኑሮን በመሸፈን ላይ ያለዉ እንጂ መንግስት አደለም ዜጎቹን እየደጎመና እያኖረ ያለዉ ፣ መንግስት ይልቅ በተቃራኒዉ ህዝቡን ኣዋርዶ በያገሩ እየሔዱ ልመናን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል ።

ባሁንዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬቱንና ልጁን በዘዴ ከተቀማዉ ያብዛኛዉ ማህበረሰብ ክፍል የሚገኘዉ ወጣት ስደተኛ ሴትም ሆነ ዎንድ በዓረብ ሐገራት ተበትኖ በግርድናም ይሁን በሞያ ስራ ላይ የተሰማራዉ ወገን ፡ በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብና ማህረሰብ ከዛም አልፎ በዚያች አገር በተለይም የኢኮኖሚዉ ግንባታና የለት ተዕለት የህብረተሰቡ ኑሮ ዉስጥ ከፍተኛዉን ድጋፍና ተሳትፎ አያረገ ያለዉ ይኸዉ ባረብ ሐገራትና በሌላዉ ዓለም የተበተነዉ ሰደተኛ የተባለዉ ኢትዮጵያዊ ወገን ነዉ ።ይህ ደግሞ ሊያስመሰግነዉና ተበረታቶ ትክክለኛዉን የዜግነት ክብሩንና መብቱን ሊከበርለትና ዋስትና ሊኖረዉ ሲገባ ፤አሁን ያለዉ መንግስት በራስ ወገን ስቃይና ደም ፡ንግድ ዉስጥ ተገብቶ በራስ ዙሪያና ለራስ ብቻ እየተኖረ ወገንን ፡አገር አልባ አድርጎ የተበላሸ የዶሮ ወጥ ባዉሮፓና ባረብ አገር ይዞ መዞሩ ከሙቀቱ ወደ በረዶ – ከበረዶዉ ወደ ሙቀቱ ወጡን ይዘዉ ቢያጉዋጉዙ ትርፉ የዶሮ ወጡን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚንስትራችንንም ሆነ ፖለቲካቸዉን እጅ እጅ እንዲሉ አድርጎዋቸዋል ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ስርዓታቸዉ ጠቅልሎ ባመጣዉ ችግር መልሰዉ ራሳቸዉ በራስ ወገን እና ዜጋ ላይ ማላገጥ አዋቂነት ሳይሆን ራስንና አገርን ማዋረድ ነው ። በጀርመን ሐገር የሚገኘዉን ‘ኸይም ‘ Heim መጠለያ ጣቢያ ሂደዉ፣ ዱቔት ሲፈጩ ባዩት ከማላገጥ የሰሩትን ዶሮ ወጥ በትኩሱ ባገር ቤት ጠርተው የበተኑትን ወገን ሊያበሉት ቢሞክሩ ምንኛ በመጠናቸዉ ፣ዶሮ ወጥ ሰርተዉ ባገሪቱ ጎዳና በየቦታዉ ለወደቁ ህፃናትና አረጋዊያን ቢያበሉ ምንኛ በመጠናቸዉ ፣የሰሩበትን ያመታት ጥሪት በገዛ አገራቸዉ በጉምሩክ ፈታሽና በግዜዉ ባለስልጣኖች የተዘረፉት ሴት እህቶቻችን በየመንገዱ ቀን ለቀን ባዶአቸዉን ግራ ገብቷቸዉ ያሉትን ፣እንደገና ዳግም ለመከራ ስደት መንገድ ላይ ያሉትን -በሰዉ ሐገር ያለዉን ከሚጎበኙ በገዛ አገሩ ሰደት ዉስጥ ያለዉን ቢጎበኙ ምንኛ መልካም ነበር።

እርግጥ ነዉ በዚ ልማታዊ መንግስት ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የፈረንሳይ የታሸገ የመአድን የተጣራ ዉሃ french evian mineral water ገዝቶ የሚጠጣ ባለግዜ የደሃ ሃገር ቡርዥዋ እንዳለ ሁሉ ከቆሻሻ ገንዳ ከዉሻ ጋር እየተጋፋ በተራቡ እና በደከሙ ጣቶች የቁሻሻ ገንዳ ዉስጥ ሲቆፍሩ የሚዉሉም አሉ ፤ይኼንን ሃይማኖተኛዉና ፖለቲከኛዉ ጠቅላይ ሚንስትራችን ምናልባት ከየትኛዉ የስራ ዘርፍ ዉስጥ እንደመደቡት ባናውቅም ዛሬ ያ ሚስኪን ወገን ወስፋቱን መዝጊያ ለማግኘት ፡ከጠዋት እስከማታ ከተራቡ ዉሾች ጋር መከራዉን ሲቆፍረዉ እየኖረዉ ነው ፣ ጠቅላይ ሚንስትራችን ሰደተኛዉን ባገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ከባድ ስራ ሸሸተዉ የወጡ ብለዉናል ፤ እንዴት አይሸሽ ከባዱስ ስራ የትኛዉ ይሆን?? ለጠቅላይ ሚንስትራችን ፣ ሰዉ ተሰልፎ በቁሙ ለጉርሻ ትርፍራፊ ምግብ ባደባባይ ሲሰለፍ ፣ ህፃናት በጎዳናና በመማሪያ ክፍል መሃል ከተማ ዉስጥ እየተራቡ ፣ ወገን በቁሙ በየበረሃው በቁሙ እየተበለተ፣ ወገን በየሃይቁ እንደሳርዲን ታጭቆ ፡ በመጨረሻም እንደ ጉማሬ ተነፍተዉ ዉሃ አንሳፎ እየተፋቸዉ በመላዉ ዓለም እየታየ፣ እንደዕባብ በሰዉ አገር እየተቀጠቀጡ ፣ እንደዓሳ በዘይት ፊታቸዉ እየተጠበሰ ፣ በጠራራ ፀሃይ መህል ከተማ ዉስጥ ወጣት ሴት ልጅ በግፍ ተድፍራ ስትገደል ሴቶች እንዴት ሸሽተዉ አይሰደዱ ?? ተነግሮ የማያልቀዉን መከራና ስቃይ ሲጋት እሚኖረዉ በዝቶ እያለ፣ጠቅላይ ሚንስትራችን ይሔን የማህበራዊና የኢኮኖሚ የፖለቲካ ቀዉስ ስደተኛዉ ላይ ደፍድፈዉ በራስ ጥጋብና ምርጫ ህዝቡ እንዳመጣዉ ተደርጎ መዘባበት ትናንት እንደተባለዉ ከርስዎ በፊት በነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ስለድርጀቶ የተነገረዉን መንቀዝና የፖለቲካ የመጨረሻዉ ብስባሴ ባንድ ዎቅት አሰምተዉን ነበር አሁን ማን ይንገረን ? ?

ከሞራልም አኳያ ቢሆን በየትኛዉም የዕምነት መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ እንዲህ አይነቱን ስብዕናና ክፋት – በሀይማኖት የቅዱስ መፅሐፎቻቸዉ መገሠጭያውንም ማስተማሪያዉንም ከትበዉ ይዘዋል ፤ያን ላንባቢያን እንደምርጫቸዉ ስንተወዉ ለሞራልና ለግብረግብ እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የዕምነት አባቶች ግን የሳቸዉን አነጋገርና ትዕቢት ክፍተቱን ከሞራልና ከክርስትና አኳያ እንዴት እንደሚሞሉት በማስተዋል እንጠብቃለን ፣ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ከሆነም ከነማብራሪያቸዉ እንጠብቃለን።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዴት እንደሚረዱትና እንደሚያዩት ባናውቅም ዛሬ ያለዉ ሃበሻ ኢትዮጵያዊ ባሜሪካም ሆነ ባዉሮፓ ያለዉ ሂስፓኒክ አደለም ፣ዛሬ ባረብ አገር ያለዉ ሃበሻ- ኢትዮጵያዊ ፡ ይሁዲ አዶለም ይሔንን እሳቸዉ ተምረዉ ባደጉበት የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ትምህርት የህዝብ የራስ ወገንን ክፍተኛ ፍልሰት exodus ለያይተዉ ማየት አለመቻላቸዉ ምናልባትም ያገዛዙ ዋና ኤሊትሶች ፈረንጆቹ horse hood ሆርሰ ሁድ የሚሉትን ለሳቸዉም ባንገታቸዉ አጥልቀዉላቸዉ ይሆን ? እንዲህ ግራ ቀኙን እንዳያዩ አድርገዉ እሚጋልቧቸዉ? ፣እጅ- እጅ ብሎ እጅ- እጅ ካለ የዶሮ ዎጥ ጋር ዝም ብሎ መጋለብ ፣ አሳፋሪም አስነዋሪም ነዉ።

ተፃፈ – ስለ- ክብር፤ ለመላዉ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲሁም በህይዎት ለሌሉ እና ባገራቸዉም ካገራቸዉ ዉጭ በግፍ ላለቁ ሁሉ።

ከድሬዳዋ ተነስተው ኤርትራ ቀይ ባህር ዳርቻያረፉት የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተሮች ጉዳይ ለወያኔ ራስ ምታት ሆኖበት ሰንብቶአል። ሄሊኮፕተር ይዘው ኤርትራ የገቡት ኢትዮጵያውያን የአየር ሃይል አብራሪዎች ማንነት እና በወያኔ ላይ ያላቸው ተቃውሞ ምን እንደሆነ ገና አልታወቀም። በተያያዘ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከማንኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሽባ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። አማራ እና ኦሮሞ የጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ከስራ ውጭ ተደርገዋል። የትግራይ አብራሪዎችና ቴክኒሻኖች ደ’ሞ በጣት የሚቆጠሩ በመሆናቸው አየር ሃይልን በትግራይ ሰዎች ብቻ ለማንቀሳቀስ አልተቻለም። በተለይም ክኒሻኖች በአብዛኛው አማራና ኦሮሞዎች በመሆናቸው ወያኔ ችግር ውስጥ ወድቆአል። የፌክ ፌደራሊዝም ውጤት ይኸው ነው።

ከቀጣዩ ምርጫ ጋር በተያያዘ ወያኔ ብዙ ፈተናዎች ከፊቱ ተደቅነውበታል። ህወሃትና ብአዴን የስልጣን ሽኩቻ ላይ መሆናቸው ሰሙነኛ ወግ ነበር። ኦህዴድ ከጨዋታ ውጭ ሆኖአል። ድቡብ ህዝቦች፤ አልነበሩም – የሉምም። ኦህዴድን ያልያዘ የኢህአዴግንሊቀመንበርነት (ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ጭምር) መያዝ እንደማይችል ግልፅ ነው።ስለዚህ ህወሃትና ብአዴን የኦህዴድ አባላትን በግለሰብ ደረጃ በመቀራመት የራሳቸው ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ይሻኮቱ ይዘዋል። ኦህዴድ ለራሱ እንዳያስብ ተደርጎ ስለተሽመደመደ ከፊቱ የተደቀነው ጥያቄ፣ “ማንን ላንግስ?” የሚለው ብቻሆኖአል። ርግጥ ነው፤ የኦህዴድ አባላትን በቅርብ እንደማውቃቸው አማራ ወደ ስልጣን ከሚመጣ ህወሃት ስልጣን ላይ ቢቆይ ይመርጣሉ። ግን ደግሞ በዚህ ወቅት የአካባቢያችን ዋነኛ ጠላት ወያኔ እንጂ የአማራ ፖቲከኞች እንዳልሆኑ የሚያጡት አይመስለኝም። ወያኔ ቢወድቅ ደመራው ወዴት እንደሚወድቅ አለመታወቁ ለማናቸውም ቢሆን አሳሳቢ ነው። ሁኔታዎች ተወሳስበዋል።የኦህዴድ አመራር መግባባት ችሎ ቢደራጅ ህወሃትና ብአዴንላይ ተፅእኖ ማድረግ ይቻለው ነበር። ለአብነት ከኢህአዴግ አባል ድርጅትነት ቢወጡ ጠንካራ ተደራዳሪ መሆን በቻሉ። ከፓርላማው ራሳቸውን ቢያገልሉ ወያኔ የኦሮሞን ህዝብ ማክበር በጀመረ ነበር። በርግጥ እንዲህ ያለ ወግ፣ “እንጀራ የለም እንጂ – ወጥ ቢኖር ኖሮ” እንዲሉ ሊሆን ይችላል።

የወያኔ አመራር አባላትም መስቀለኛ መንገድ ላይ ናቸው። አማራ ወደ ስልጣን ከሚመጣ ኢትዮጵያ ብትፈራርስ እንደሚመርጡ ግልፅ ነው።የአቦይ ስብሃት ነባር አቋምይታወቃል። ሃይለማርያምና ደመቀ (አገውና ወላይታ – ፕሮቴስታንትና ሙስሊም) ወደ ስልጣን ሲመጡ፣ “የኢትዮጵያን ስልጣን ከአማራና ከኦርቶዶክስ አፅድተነዋል” ብሎ በሬድዮ ሲናገርተሰምቶአል። ለነገሩ የተሳሳተ አይመስለኝም። ኮሎኔል መንግስቱ በማፈራረስ የጀመረውን የኦርቶ – አማራ ቢሮክራሲ ወያኔ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆታል። ስለዚህ ብአዴን (አማራ ነው ከተባለ) የፈለገውን ያህል ቢፍጨረጨር የጋረዳለቲን በተመንግስት እንዲቆጣጠር ሌሎች አይፈቅዱለትም። ህወሃት ደብረፅዮንን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሊያመጣ ማሰቡ ሲናፈስ የሰነበተው ወሬ ልክ አይመስለኝም። ደብረፅዮን የቴክኒክ ሰው ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለማሽከርከር የሚቻለው ፖለቲከኛ አይደለም። በዚህ ወቅት ህወሃት ወደ ስልጣን ሊያመጣው የሚችለው ብቸኛ ተቀባይነት ያለው ሰው ቢኖር ቴዎድሮስ ነው። ትውልዱ ከአድዋ የሚመዘዘውን፣ አስመራ ተወልዶ ማደጉ የሚነገርለትን ቴዎድሮስ አድሃኖምን በመለስ ዜናዊ ወንበር ላይ ማስቀመጥም ቢሆን ግን ለህወሃት አስቸጋሪ ነው። ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚናከስ ጥርስ የለውም ተብሎ ይታማል። ኢትዮጵያን ለመምራት ደግሞ የሚናከስ ብቻ ሳይሆን፣ የሚቦጭቅና የሚያኝክ ጥርስ ያስፈልጋል። ህወሃት ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወደ ስልጣን ማምጣት ይመኙ ይሆናል። ቴዎድሮስ ስልጣኑን ቢይዝ ለህወሃት ጥቅም ነው። አደገኛ ጉዳትም ግን አለው። ጫጫታውን አይችሉትም። ከውስጥም ከውጭም የሚወረወርባቸውን የተቃውሞ ፕሮፓጋንዳ መሸከም ስለመቻላቸው ርግጠኛ አይደሉም። ስለዚህ ሃይለማርያምን ወይም እሱን የመሰለ ታዛዥ ሰው እየለዋወጡ፣ ከጀርባ እየተቆጣጠሩ ድምፃቸውን አጥፍተው ስልጣን ላይ መቆየቱን ይመርጡ ይሆናል።

ሃይለማርያም በህወሃትና በብአዴን ተከቦ ስራውን ሲሰራ ሰንብቶአል። መከላከያ፣ ደህንነትና ውጭ ጉዳይን ማዘዝ አይችልም። መንግስትን መንግስት ሊያሰኙ የሚችሉት እነዚህ ሶስቱ ቁልፍ ቦታዎች ደግሞ በህወሃት የተያዙ ናቸው። በጌታቸው አሰፋ፣ በሳሞራ የኑስ እና በቴዎድሮስ አድሃኖም መዳፍ ስር ናቸው። ስለዚህ ሃይሌ ቴክሱ ስልጣን አልባ ሆኖ (በጌታ ፈቃድ) የታዘዘውን ሲሰራ ቆይቶአል። ያም ሆኖ ሃይለማርያም በተቀረው የአስተዳደር ቦታ የተቻለውን ያህል የደቡብ ሰዎችን ለመሰግሰግ መሞከሩ አልቀረም። ይህ ሁኔታ እንግዲህ ለረጅም ጊዜ በአማራ ተይዞ የቆየውን የማእከላዊ መንግስት የአስተደዳር ቦታዎች እያዳከመ ስለሚሄድ፣ የአዲሳባን ቢሮክራሲ የሰው ሃይል ሚዛን ስለሚያመጣጥነው ወያኔዎችም አይጠሉትም። ከዚህ ባለፈ ሃይለማርያም ሊያደርግ የሚችለው የለም። “ሃይሌ ጥርስ አብቅሎ እነ አባይ ፀሃዬን አልታዘዝም ማለት ጀምሮአል” የሚለውን ሹክሹክታ ለጊዜው ለማመን እቸገራለሁ። መጠበቅ ይሻላል።

ኦቦ ሌንጮ ለታ ለቀጣዩ ምርጫ ወደ ፊንፊኔ ያቀናል ሲባል ተሰንብቶ ነበር። እምን እንደደረሰ አልተከታተልኩትም። ሌንጮ ጠቅልሎ ቢገባ ግን ወያኔ የሚጎዳ እንጂ የሚጠቀም አይመስለኝም። እንኳን ሌንጮ ገብቶ መረራ ጉዲና እንኳ እያዋዛ ፈተና ውስጥ ጨምሯቸዋል። በቀጣዩ ምርጫ በመጠኑም ቢሆን ወያኔን ሊፈታተን የሚችለው መረራ ጉዲና ነው። ስልጣን ይገለብጣል ተብሎ ባይታመንም ጥቂት የፓርላማ ወንበሮችን ያገኝ ይሆናል። ሌንጮ ተሳክቶለት ፊንፊኔ ገብቶ አስማተኛውን የኦነግ ባንዴራ ማውለብለብ ቢችል የምርጫ ሜዳውን ሞቅ ደመቅ ባደረገው። ወያኔም ቢጫ ወባ በሽታው በተቀሰቀሰበት ነበር። በነገራችን ላይ “ODF” የሚለው ምህፃረ ቃል Oromia Defence Force መስሎ ይሰማኛል።

አሜሪካኖች ህወሃትን እየደገፉ መሆኑ አይካድም። ህወሃትም ቢሆን ለአሜሪካ ብብቱን ከፍቶ ሰጥቶአቸዋል። አሜሪካኖች በህወሃት አመራር ባገኙት ጥቅም ደስተኛ ቢሆኑም፤የወያኔ ስርአት በስልጣን እንዲቆይ ይፈልጋሉ ማለት ግን አይደለም። “አናሳ ብሄረሰብ በስልጣን ላይ ሊቆይ ከሚችለው በላይ ገዝታችሁዋል። ከዚህ በላይ መሄድ አትችሉም። ችግር ሳይገጥማችሁ ቦታውን ብትለቁ ይሻላል።” ብለው ደጋግመው መክረዋቸዋል። ወያኔ የህዝብ ድጋፍ ስለሌለው አገሪቱን ገፍቶ ገፍቶ ገደል ይጨምራታል ብለው ሊሰጉ ይችላሉ። አሜሪካኖች እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ያሉትን ከጀርባ ደጋግፈው ወደ ስልጣን ለማምጣት እንደሚፈልጉ ይታወቃል። ስለ ኦሮምያ ነፃነት የሚያስቡ ወጣቶችን ግን አሜሪካኖች በጣም ይፈሯቸዋል። “በኢትዮጵያ አንድነት” የሚያምን፣ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችል ወጣት ኦሮሞ ለማግኘት መከራቸውን ሲያዩ ሰንብተዋል ይባላል። የሚሳካላቸው አይደለም። በርግጥ በመጪው ዘመን የኦሮሞን ህዝብ በትክክል የሚወክል ሃይል ወደ ስልጣን ካልመጣ የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ምእራባውያኑ አስጠንተው ደርሰውበታል። ያም ሆኖ ኦሮሞዎች ካላቸው አቅም አንድ አስረኛውን እንኳ እንዳልተጠቀሙ ይታመናል።

የአንድነት ሃይሎች የፖለቲካ አካሄድ ቀልድ ይመስለኛል። አንዳርጋቸው ፅጌ፣ “ነፃነትን የማያውቅ ነፃአውጪ” ብሎ ነበር። “አንድነትን የማያውቁ አንድነቶች” ከፕሮፓጋንዳ ባሻገር የትም መሄድ አልቻሉም። ኢትዮጵያዊነት ባለቤት አጥቶአል። ህይወቱን ቀርቶ እንቅልፉን የሚሰዋለት እያጣ ነው።ጠጋ ብሎ ላያቸው “አንድነቶች” በጎንደርና በጎጃም፤ በወሎና በመንዝ ተከፋፍለው ሲሻኮቱ ይገኛሉ። የጎንደር – ሸዋ ሽኩቻቸውን ሳይፈቱ ኦጋዴን ኢትዮጵያዊነትን እንዲዘምር ይመኛሉ። ብዙውን ጊዜ የአማራ ፖለቲከኞች፣ “ኦሮሞ ወንድሞቻችን” ማለት ያበዛሉ። በአማራ ፖለቲከኞች ዘንድ፣ “ግማሽ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ፋሽን ሆኖአል። በአንፃሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ “አማራወንድሞቻችን” የሚል አባባል ሲጠቀሙ ሰምቼ አላውቅም። አንደኛው ተለማማጭ የመሰለበት ምክንያቱ ምንድነው? ከልብ ስላልሆነ ይመስለኛል። “ወንድሞቻችን” የሚለው አባባል የለበጣ ነው።የኦሮሞን ህዝብ ስነልቦና “የቡርቃ ዝምታ” በተባለው መፅሃፌ ጥሩ አድርጌ በመግለፄ እኔ የአማራ ህዝብ ባለውለታ እንደሆንኩ ይሰማኛል። አሁንም አማራ ፖለቲከኛ ወንድሞቼን በግልፅ መምከር እፈልጋለሁ። ጊዜ እያመለጠ ነው። የአማራ ፖለቲከኞች ከሽማግሌ ኦሮሞዎች ጋር ዛሬውኑ ተግባብተው ለመስራት ካልሞከሩ በርግጥም ጊዜ እያመለጣቸው ነው። ሽማግሌዎቹ ቢያንስ በኢትዮጵያዊነት ስር ኖረዋል። ወደውም ሆነ ተገደው ለባንዴራው ዘምረዋል። አዲሱ የኦሮሞ ትውልድ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙን ባንዴራ አጥብቆ ይጠላዋል። አማርኛን ይጠየፋል። ‘ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ማለት አይፈልግም። የአንድነት ሃይሎች ዛሬውኑ መባነን አለባቸው። ዮሃንስ መጥምቁ፣ “ከኔ በሁዋላ የሚመጣው በእሳት ያጠምቃችሁዋል!” እንዳለው እየመጣ ያለው የኦሮሚያ አዲሱ ትውልድ ከአበሻ ጋር ቁጭ ብሎ መነጋገር ስለመቻሉ እጠራጠራለሁ። መልካም አዲስ አመት፤ መልካም የገና በአል ይሁንልን። አላህ ይርዳን። አሜን!

አንዳርጋቸው እንዴት ከወያኔ እጅ ሊገባ እንደቻለ ዛሬም ድረስ ግልፅ መረጃ የለም። የተለያዩ መላ ምቶችን እየሰማን፣ እያነበብን ቆይተናል። አንዳርጋቸውን በቅርብ ከሚያውቁት አንዱ እንደመሆኔ እኔም ካለኝ መረጃ በመነሳት የራሴን ግምት መውሰዴ አልቀረም። የኔን ግምት ይፋ ከማድረጌ በፊት ሌሎች የሚሉትን ለመስማት በሚል እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ሳልፅፍ ቆይቼ ነበር። አሳማኝ መረጃ ሳይፃፍ ወይም ሳይገለፅ ጊዜው ስለረዘመ እነሆ! እኔም የግል አስተያየቴን ለማኖር ወሰንኩ… (ቅዳሜ ለንባብ ይበቃል)

አባመላኩ ወደምንኩስና አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ልብስ ሰፊ እንደነበሩ ይታወቃል። ምን አነሳስቷቸውና በምንስ ምክንያት በአንድ ጀምበር ወደ ምንኩስናና ብሎም ወደክህነት እንደገቡ የሚያውቁት እሳቸው ብቻ ነው። ስለእሳቸው በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ብድግ ብለው ተነስተው ከተሰወሩ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምንኩስና ቆብ …

ዜና ቤተክርስቲያን የታደሰ ሲሳይ “ገበና መሸፈኛ የበለስ ቅጠል” አባ መላኩ ጌታነህ (“ፋኑኤል”) ከድጡ ወደማጡ Read more »

ሄኖክ የሺጥላ ያው እንደምታውቁት ኢትዮጵያ ግድብ እንጂ ውሃ የለም ። ሿ የሚል የውሃ ድምጽ ከጠፋ ቆየ ፣ አረ ተውት ! ድሮ ድሮ ሸራተን ርችት ሲተኮስ ነበር ሰው ጣራ ላይ ወጥቶ የሚያየው አሁን አሁን በቃ ድንገት አንድ ቡዋንቡዋ ለባቡር መንገድ ሲወጣ …

አንዳንድ ሃሳቦች ስለ ውሃ እና መብራት መጥፋት – ሄኖክ የሺጥላ Read more »

ከዶ/ር በቀለ ገሠሠ እጁ ወርቅ ሆኖ አፉ ወለላ አንደበቱ ርቱዕ እጅጉን የሰላ አ ቋሙ ጥብቅ አንዴ እማይላላ አግዜር እያለለት የዘለዓለም ከለላ የኃይሉ ሞት ወሬ የለዉም አንዳች መላ። ሞት ራሷ እልም ብላ ትሙት ኃይሉ አይሞትም ዝም ብላችሁ አትሙት። በረከተ መርገምን እያድበለበለልኝ …

ሞት ራስዋ ትደፋ እንጂ ኃይሉ አይሞትም Read more »

ከአርአያ ተስፋማሪያም ጄ/ል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ለመውጣት ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች እንዳይወጡ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል። ከመከላከያ የጦር አዛዥነታቸው በጄ/ል ሳሞራ የኑስ እንዲነሱ የተደረጉት ጄ/ል አበባው ከአገር እንዳይወጡ የተደረገበት ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ …

ጄ/ል አበባው ታደሰና ፍጥጫው Read more »

ለአቶ ዛይድ መነሳት ምክንያት የሆነው ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ላይ ባይተነተንም፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔውን እንዳሳለፈ ደብዳቤው አትቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለትራንስፖርት ሚኒስቴር ሪፖርት ያቀርባል፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየው የመንገድ ባለሥልጣን ቦርድም ሰብሳቢ ናቸው፡፡ ሰሞኑን አቶ …

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል ከሥልጣናቸው ተነሱ Read more »

ሰናይ ገ/መድህን ይባላል። በኤርትራ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ የአማርኛ አገልግሎት ክፍል ውስጥ እ.አ.አ. ከ1998 እስከ 2011 ድረስ ሰርቷል። በዚሁ የረዥም ጊዜ የጋዜጠኝነት ሙያው ነበር ሰናይ ከተስፋዬ ገ/አብ ጋር አስመራ ውስጥ በቅርብ ለመተዋወቅ የበቃው። ዛሬ ኗሪነቱ ሜልበርን፣ አውስትራሊያ የሆነው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ሰናይ …

ተስፋዬ ገ/አብ በኤርትራዊ ጋዜጠኛ እይታ Read more »

ኤድዋርዶ ባይሮኖ የስነጽሁፍ ሰው እንዳይሉት ለአንባቢያን በትኖአቸው ያለፈው ድንቅ መጣጥፎቹ ከስነ-አይምሮ ፈጠራ አድማስ ባሻገር የላቁ፥ የዘንድሮን ደርሶ ብሄርተኛ ጦማሪዎችን ክፉ ባህሪ እና የሰይጣናትን ስነልቦና ያልተላበሰው፥ ከታላቁ የወሎ ርሀብ በኋላ በደራሲ ብርሀኑ ዘርይሁን ብሩህ ብዕር ተስሎ በመጽሀፍት አለም የኖረውን በጎ ሰው …

ይድረስ ለጳውሎስ ኞኞ Read more »

ተሻለ መንግሥቱ (ከአዲስ አበባ) ኢትዮጵያ እጅግ ድሃና ኋላ ቀር ከሚባሉ የዓለም ሀገሮች ተርታ የምትሰለፍ መሆንዋን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ያረዳሉ – እኛም በዘግናኙ ኑሯችን ይህንኑ መራራ እውነት እያረጋገጥነው እንገኛለን፡፡ በሰብኣዊ መብት አያያዝ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥልጣኔና በመሳሰሉ የሀገርና የሕዝብ ጤናማ ዕድገት መለኪያዎች …

ትንሹ መለስ በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ Read more »

ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ነው። በተለይ በትግሉ ላይ የተሰማራነው ኢትዮጵያዊያን፤ ለዚህ ትክክለኛ መልስ መሥጠት አለብን። ለዚህ የምንሠጠው መልስ፤ ትብብሮችን ወይንም ውህደቶችን፣ ልዩነቶችን ወይንም መራራቆችን ያስከትላል። ከዚህ መሠረታዊ ጥያቄና ለዚህ ጥያቄ ከምንሠጠው መልስ፤ ማንነታችንን ብሎም የተሰባሰብንበትን ድርጅት ማንነት ማወቅ ይቻላል። እንግዲህ ሀገራችን ባለችበት ቀውጢ ሰዓት፣ የታጋዩ ክፍል ባለበት የተበታተነ ሀቅ፣ የተበታተነ ትግል በመከተል ትግሉ ማዕከል ባልያዘበት ሁኔታ፣ […]

ሎስ አንጅለስ በወያኔ አምባገነኖችና አጋፋሪዎቻቸው ልትጎበኝ ዝግጅቱ ከታቀደ ቆይቷል። እንዳውም የሃይለማሪያም የክብር ድግሪ መሸለሚያ ወይም መሳለቂያ ልትሆን ታጭታለች። የወያኔ ሥራ አስፈፃሚዎች እነ ወንድወሰን መስፍን፣ እነአበራ ገብሬ፣ እነፀሃይ ኃይሉና የሮዛሊንድስ ምግብ ቤት ባለቤቶች ወንድማማች ፍቅረና ሞገስ ጌቶቻቸዉን ሊቀበሉ ሽርጉዱን ተያይዘውታል። የሮዛሊንድስ …

የወያኔ ቆይታ በሎስ አንጅለስ Read more »

አበበ ቶላ የቴዲ አፍሮ አዲሱ ዜማ “በሰባ ደረጃ” በዋዛ የምንለቀው አይመስልም። ”ቴዲ ያስተፈስህ ልበ-ሰብ” እያሉ ደጋግመው የሚሰሙት እንጂ ይገጥመዋል አይገልጸውም። እያንዳንዱን ስንኝ ድጋሚ ሲሰሙት ”ፓ!” ብለው እየተደንቁ ድጋሚ እያጠነጠኑ የሚያዳምጡት ገራሚ ዜማ ነው። የፌስቡኳም መግቢያስ ለምን ትቅርባችሁ… ሰባ ደረጃን የእኛ …

የቴዲ አፍሮ አዲሱ ዜማ “በሰባ ደረጃ” Read more »

ሄኖክ የሺጥላ በምዕራብ አፍሪካ የተነሳውን የኢቦላ ቫይረስ ተከትሎ የተለያዩ ሃገራት ወረርሽኙ ወደታየባቸው ሀጋሮች የሚያደርጉትን ማንኛውም አይነት የአየርም ሆነ የየብስ፣ የንግድና የቱሪዝም ፣ የትምህርትና የስልጠና እና ሌሎችንም አይነት የንግድ ይሁን መሰል ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች አቁመዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ፣ አይዞዋችሁ ፣ ወደተባለው …

ኢቦላና ወያኔ (ሄኖክ የሺጥላ) Read more »

አሳቤ አበበ (ከቶሮንቶ) ሰሞኑን በአንድነትና መ.ኢ.አ.ድ መካከል ተጀምሮ ለነበረው ውህደት በወያኔ የተከሰቱ መሰናክሎች ሳያንሱ በአሜሪካ ከሚገኙ ደጋፊ ነን ከሚሉ አቶ ግርማ ካሳና አልዩ ተበጀ እንዲሁም እዚያው ኢትዮጵያ ባሉት ዶ/ር ያዕቆብ ሐይለማርያም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላይ የተወረወሩትን የማፍረሻ ድንጋይዎች ቆም …

በአንድነት ፓርቲ ላይ ደጋፊ ነን ከሚሉ የተወረወሩትን ድንጋይዎች ቆም ብሎ ማጤን ተገቢ ነው Read more »

ነፃነት ዘለቀ ይህን የአንዱአለም አራጌን በራሱ አገላለጽ ከጠባቧ የቃሊቲ እስር ቤት የተጻፈ ግሩም መጽሐፍ ሳነብ የተሰማኝን ስሜት ባጭሩ ለመግለጽ እንጂ ሥነ ጽሑፋዊ ደንብ የተከተለ ሂስ ወይም የመጽሐፍ ግምገማ ለመስጠት አለመነሳቴን መግለጽ እፈልጋለሁ – መሆኑን እንዴት ከረማችሁ? ከሁሉ በፊት ግን ከሰሞነኛ …

“ያልተሄደበት መንገድ” – ሊነበብ የሚገባው ድንቅ መጽሐፍ Read more »

ሻለቃ ፀአዱ የህወሓት ታጋይ የነበረች ናት። ከኤርትራና ጣሊያን የዘር ግንድ ያላት ሻለቃ ፀአዱ የቀይ ቆንጆ ናት፤ ገፅታዋን በመመልከት ማንነትዋን በቀላሉ መገመት ይቻላል። የሽማግሌው ስብሃት ነጋ ባለቤት ነበረች። ሽማግሌው ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በአብዛኛው የድርጅቱ አባላት የሚታወቁበት ባህርይ ሴሰኝነታቸው ነው። ከፀአዱ ጋር …

የስብሃት ነጋ ባለቤት ሻለቃ ፀአዱና ሟቹ ዶ/ር ልኡል Read more »

ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር) ጸጋየ አየለ ይግዛው ይባላል። የ፴፬ ዐመት ባለትዳርና የልጆች አባት ነበር። ጎንደር ሆስፒታል ውስጥ በራዲዮሎጂስትነት ሲሰራ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባል ነህ በሚል ፖሊስ የሚያደርስበትን ወከባ ለመሸሽ ወደ ደብረማርቆስ ሄዶ በአንድ የግል ክሊኒክ ተቀጥሮ መስራት ይጀምራል። ነገር ግን የፈራው …

የጸጋየ አየለ ገዳይ አሜሪካ ይገኛል Read more »

ይህ ትዉልድ ትክክለኛዉን መላ እስኪያገኝ ፋታ ስጡን እንላለን!

http://www.eaglewingss.com/%e1%8b%ad%e1 … %e1%8a%9d/

መላ ያጣ የጊዜአችን ሰሞንተኛ መካሪ ያጣ የቀንም የጭለማም አስማተኛ ፡፡ ደግሞ የተካነ ቶሎ የሚላመድ የሚያላምድ፣እባብን ከርግቡ ምላስን ከሆዱ፤ ደግሞ አዋኪም ኣዋቂም የምላስ ዳንኪረኛ፡፡

አንዳንዴ አበሻ የዋሁ ያዳምና የ ሔዋን ጠላት እባብ ነው ብሎ የራሱን ምላስ ትቶ የባቢቱን ሲጠነቀቅ ይኖራል ፡፡ አሁን አሁን እኮ ተናዳፊዉ ሰዉ ነዉ፡፡ ተናዳፊዉ እባብ ቀረና ሰዉ መርዘኛ እባብ ሆኖዋል ሂዩማን ቬኖም (human venom)፡፡ እናም ታዲያ የሰሞንተኛዉ አስማተኛ ምላስ ነገረ ስራዉ ሁሉ በምላሱ መርዝ የዋሁንም የሱንም አጫፋሪም ተቃዋሚም በራሱ መርዝ በክሎ አንድ ላይ ወደ ራሱ የሆድ ከርስ አንጦርጦስ ለመክተት የተነሳ ይመስላል፡፡

የምላስና የሆድ አስማተኛ ይቅርታም ይሉኝታም የሌለዉ ብቻ የሱ ስራ በነዛ በረጂም ለሁለት በተሰነጠቁ መርዛማ ምላሶቹ አሳስቶም አሞኝቶም ፤አግባብቶም አቆላምጦም፤አባብሎም ያ ካልሆነም ደግሞ እንደግዜው መስሎም ከዚህም ከዚያም ያገኘዉን ወደዚያ መዉጪያ ወደሌለዉ የከርስ ዎይንም የሆድ አንጦርጦስ መክተት ነው የሱ ዓላማ፡፡

ዛሬ እዚህ ያለንበት የፈረንጆቹ ማህበረሰብ ዉስጥ በተመስጦ እሚወያዩት ስለ ምህዋር ጠፈር ብላክ ሆል ስለሚሉት የስበትን ሚስጥር ሰለማወቅ ነዉ ሚስጥሩን ሳይንሳቸዉ ገና ትክክለኛዉን መልስ ባያገኝም፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን የዕኛን የፖለቲካ አዙሪትና ስበት ብንፈልገዉ ደግሞ የሰዉ ሆድ ዉስጥ ሆኖዋል እምናገኘዉ ፡፡ሆድም ብላክ ሆል (black hole) ሆነ ላበሻ ፡፡ትዉልዱ ለፖለቲካ ለዉጥና ለመልካም አስተዳደር ለፋትሕና ለዲሞክራሲያዊ ለዉጥ ይታገላል ፣ነገር ግን ደግሞ ትግሉ በሆድ ዎይንም በከርስ ስበት ምክንያት ተኮላሽቶ ይኸዉ የዚህ ትዉልድ ስቃይና መከራ እንደ ዓዲስ እየትራዘመ ይገኛል፡፡

ባሁኑ ዎቅት ኢትዮጽያና ኢትዮጵያዉያንን ስላለባቸዉ የማህበራዊ የምጣኔ ሃብታዊ ፖለቲካዊ ችግሮች ተስታከዉ በሚካሄዱ ባስመሳዮችና ባላዋቂዎች ፖለቲከኛ ነን ባዮች ምክንያት የትግሉ አቅጣጫ ላይ ደንቃራ ሆነዉ ይታያሉ፡፡እነዚህ መርዛማ አስመሳዮች በዘመናዊ አዳራሾች በዘመናዊ የመገናኛ መረቦች የመላዕክትም የፃዲቅም የሴይጣንም ፤የታዋቂ ሰዉ ስምም የጅግናም ሰዉ ስምና ክብር ፤በምላሳቸዉና በባዶ እራሳቸዉም ላይ እየጫኑ ፡ቡድን እያበጁ በመዋገን በፖለቲካ ዕምነት፥ በፖለቲካ አመለካከት ዎይንም ደግሞ በምክንያታዊነት ሳይሆን፡ እንዳዉ ብቻ ለጥቅም አሊያም በመንደርተኝንትና በጥላቻ ባዶ ኢትዮጵያዊኛ ከበሮ ዕየተደለቀ እርስ በርስ ሲቆለማመጡ ሲካካቡ እና የኮሚቴ ሹምና የቴሌቭዥን የክብር ዕንግዳ እየተደራረጉ ሲካካቡ ከርመዉ ዛሬ ደግሞ አንዱ አስማተኛ ድንገት ከጉያቸዉ አፈትልኮ ወጥቶ የጥንት የጠዋቱን ከነጉዲት በፊት ያመልክ የነበረዉን ዋናዉን ሴይጣን መልሶ ተቀላቅሎ ዛሬ ሌላ ዙር ነጋሪት በተቃዋሚዉ ፓርቲና ማህበረሰቡ ላይ ዕየተጎሸመ ያለኛ በቀር የፖለቲካ መንገድም እዉነትም ሐርነትም የለም እየተባልን ነዉ፡፡

ዛሬ በሁለቱም ጎራ የሚታየዉ የባዶ ዓርበኝነት ድራማ የብዙሃኑን ህዝብ የለዉጥ ጥያቄና የዚህን ወጣት ትዉልድ ትግል እያጓተተና እየጎዳዉ ይታያል፡፡ለዚህም የሚታዩት ምክንያቶች ያላዋቂ ሳሚ መብዛትና ፥ያመራር ችግር፤ተጠያቂነት የሌለዉ የባለሞያና የፖለቲካ አናርኪዝም (anarchism) ዋናዎቹ ችግሮች ቢሆኑም እነዚህን ችግሮች ተንተርሰዉ ዘመኑ ባፈራዉ የሜድያ መረቦች የመስኮት (window )አስመሳይ ፖለቲከኞች ማን እንደኛ ለ ኢትዮጵያ የሚሉ ስግብግቦችና ራስ አድናቂ (narcissist) በ ኢትዮጵያ ህዝብ የለዉጥ ትግል ላይና በዚህ ዓዲስ ወጣት ትዉልድ የለዉጥና የዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ላይ ትልቅ የተህዋስ ወረርሽኝ (virus epidemic) ሆነዉበት ይገኛል፡፡

ከድሮ ጀምሮ አንድ የለመድነዉና ያደግንበት አጉል ባህል አለ፡፡ ወቅታዊ ያልሆነ ዘመንተኝነት አብሮን አድጎ ይኸዉ ይኼን ኮተታችንን እዚህም እሰዉ አገር አምጥተን እርስ በርስ መደናቆር ይዘናል፡፡ ባንድ ዎቅት ንዋይ ደበበ የ ጥቅምት አበባ ነሽ አሉ ብሎ ዘፍኖ ጠዋትም ማታም በበጋም በክረምትም ትንሹም ትልቁም የዘፍነዉ ነበረ ከዛም ደግሞ ሐይልዬ ታደሰ የተባለ ድምጻዊ ይሞታል ዎይ ታዲያ ( Link )እምትለዉን ዘፈን አዉጥቶ በማህበረሰቡ ዉስጥ በጣም ከመደጋገሙ የተነሳ በግዜዉ የነበረዉን ማህበረሰባዊ ነዉር ማህበረሰባዊ የሞራል ዝቅጠት ራሱ ኪነትና ስነጥበብ አብረዉ ዓብረዉ ቡሄራዊ ነዉራችንን አንድ ላይ ስንዘፍነዉና ዳንኪራዉም ሲመታ ነበረ፡፡ ታድያ በግዜው የነበረዉ ማህበረሰባዊ ነዉር ከመደጋገም (cliches) ከመሆን አልፎ ግቦ ስጭም ግቦ ተቀባይም ራሱ ተጎጂዉም ማህበረሰብ ነዉሩን አብሮ ይዘፍነዉ ነበር፡፡ ዛሬም ያለዉ የሆድ ዎይንም የከርስ ነዉራችንን በትንሿ መስኮት (window) ዳንኪራዉ እየተመታልን ጠዋትና ማታ የግዜዉን ተደጋጋሚ ቃላቶች መስማት ግድ ይሏል፡፡የዘንድሮ የፓልቶክ አድማጭ እና እራሱ ፓልቶክ (paltalk) ክፍሉም እዛዉ አገራችን እንዳሉት የነ መላዉያኑ ሰፈር የመርካቶ ሙዚቃ ቤቶች ሲመስል ሰዉም ደግሞ ሙዚቃ ቤቶቹን ከቦ እሚዉለዉን መስሎኣል ፡፡

እዚህ በዳያስፖራዉ የዕለት ተዕለት ኑሮ ዉስጥ ለኑሮ ማደላደያና ለእንቶ ፈንቶ የፖለቲካ ፍጆታ መገልገያ ተደርገዉ የተያዙ የዘመኑ ተደጋጋሚ ቁልፍ ቃላቶች (cliches) ሆነዉ የቀሩ አሉ፤ለምሳሌ ብንወስድ፣ ኢትዮጵያዊ ዓርበኛ፤ ዎያኔ ሻዕቢያ ፤ግንቦት ሰባት አሸባሪ አዋኪ፤ዎይንም (terrorist) ባንዳ ሆዳም፤ ቅጥረኛ ሰላይ፤ እነዚህ ክሊሸስ (cliches) በገዢዉ መደብም ሆነ በተቃዋሚዉ ጎራ ሲያስፈልጋቸዉ ማዕረግ መስጫ ካስፈለገም ማዉገዢያና ማጥቂያም ማሰሪያም ሆነዉ ያገለግላሉ፡፡ማናቸዉም ነፃ የሆኑ አስተያየቶችና አመለካከቶች በነዚህ የዘመኑ የዳያስፖራ ፖለቲከኞች ዘንድ የስም ተቀፅላ ዎይንም ታፔላ እየተለጠፈላቸዉ በቀጥታ የነሱን የፖለቲካ ገበያና ህልዉና እንዲያስጠብቁ አርገዉ የጠቀሙባቸዋል፡፡

ዛሬ እየሰማን ያለነዉ የፖለቲካ ዓመለካከት ልዩነትን ዎይንም የፖለቲካ ዕምነትን ሳይሆን ይልቁንስ የግለሰቦችን የሆድ እና የዓመል ዥዋዥዌ እንደትልቅ የፖለቲካ አጀንዳ በየመገናኛ መረቡ ላይ ሲያራግቡት ነዉ፡፡ ዛሬ ይህ ትዉልድ እነሱ ባጨማለቁትና ባመሳቀሉት አሁን ድረስ እየተሰቃየበት ነዉ ፡፡ማህበረሰቦች በግለሰቦች ምላስና ሆድ ዋጋ እየወጣላቸዉ ማንም ባተሌ እየተነሳ የፈለገዉን ስም በራሱ ላይ እየጫነ በስደት ያለዉን ነፃ ማህበረሰብ እያመሱት ይገኛሉ፡፡እሚገርመን ደግሞ ከመላዉያን ሰሞንተኛ አስማተኛ ሰሞኑን የወሰደዉ በቀል አይሉት ክህደት፣ ቅጥፈት አይሉት ስሕተት፣ ርካሽ የፖለቲካ ኮተት፤ተዓማኒነት ዎይንም ደሞ ተቀባይነት እንዲያገኝና የነፃዉን ህብረተሰብ ድጋፍና ቀልብ ለመሳብ የብዙሃኑን የልብ ትርታ አፈንፍኜ አግኝቻለዉ በማለት ባዶ ዲስኩር ሲያረግ ከርሞአል ፡፡

ዛሬ ባብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ በዝምታ የሁለቱን የውሸት ዓርበኞች ዳር ሁኖ የቆመበትን ምክንያቶች ይኸዉ ተዓምረኛ አስማተኛ ለከርሱ ፍጆታ ሲል እንደፖለቲካ አቝዋምና በዝምታ ላለዉ ህብረተሰብ ደርሶ አሳቢ ሆኖ ይህንኑ ማህበረሰብ እንደ አንድ ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብት የፖለቲካ ገፀ በረከት አድርጎ እዛዉ ላለዉ የገዢ መደብ ለማቅረብ ባዶ የዓርበኝነት ዕምቢልታ እየተነፋ ይገኛል።ይብላኝልኝ ግን በደመቀበት ሲደምቁ ለነበሩ አዋቂ ነን ባዮች ፣በዘር በሃይማኖት ፣በእከክልኝ ልከክልህ ፣ በሰዉ ያንገት ስፋት ፣በከርሱ ስፋት ፣ወርድና ቁመት ማዕረግ እየሰጡ ሆይ ሆይ ሲሉ ለነበሩ ይብላኝልኝ።

በነዚህ አስመሳዮች ከርስ እዚህም እዚያም አሁንም ድረስ እንደትንሿ የጠረጴዛ ኳስ ሲመቱና እየተመቱ ላሉ ፣እነሆ ከያለንበት እንዲህ እንላለን፡፡ ዛሬ የምናያቸዉ የመድረክ ተዋንያን በትንሽዋ መስኮት (window) እየተወኑ ያሉት የፖለቲካ ተዉኔት በራሳቸዉ ድርሰት እራሳቸዉንና ቡችሎቻቸዉን እየተውኑ መሆኑን እንዲያዉቁት ። መላ ያጣዉ ይህ ትዉልድ ግን ትክክለኛዉን መላ እስኪያገኝ ፋታ ስጡን እንላለን።

ፖሊስ ምርመራውን አልያዝኩትም የማውቀው ነገር የለም ብሏል:: ባለፈው ኦክቶበር 13 2013 በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ከመደረጉ ቀደም ብሎ በቦሌ ኡዋንዳ አከባቢ የደረሰው ፍንዳታ ሆን ተብሎ ህዝብን ለማሸበር በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑን ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል:: …

ባለፈው ሳምንት በቦሌ የተከሰተው የቦምብ ፍንዳታ በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑ ተረጋገጠ Read more »

1- ሼህ መሃመድ አላሙዲን የወርቁን ማእድን አጠቃላይ ይዞታ በእጃቸው ያደረጉ እና በሟች መለስ ዜናዊ ትእዛዝ በመቶሺዎች የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ገበሬዎችን በማፈናቀል የአገሪቱን መሬት የያዙ….የሃብት መጠን 10 ቢሊዮን ዶላር 2-ወይዘሮ አዜብ መስፍን የቀድሞ የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት እና በህዝባዊ መጠሪያዋ “የሙስና እናት” …

የ2013/2006 የአመቱ ታላላቅ የኢትዮጵያ ሃብታሞች Read more »

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ Breast Cancer Awareness for Ethiopians – Amharic Translation [pdf] ወርሃ ኦክቶበር (ጥቅምት)በአለም የጡት ካንሰር ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ ወቅት ነው፡፡ ወሩን በሙሉ በዓለም ላይ ሕዝባዊና የግል ድርጅቶች የፕሮግራሞቻቸውና የእንቅስቃሴዎቻቸው ትኩረት ሁሉ በጡት ካንሰር መንስኤ ላይ በማትኮር፤ …

ስለጡት ካንሰር ለኢትዮጵያኖች የጥሞና ማሳሰቢያና ማስገንዘቢያ Read more »

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታ በር ወረዳ ነዋሪዎች አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ከተማ ያደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያወግዙ በከፍተኛ ጫና እና ማስገደድ ጥረት ቢያደርግም የጠበቀውን ያህል ሰው እንዳልወጣለት ምንጮቻችን ከስፍራው ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ኢህአዴግ ትናንት ሐምሌ 17 ቀን 2005ዓ.ም. ጠዋት በኩታ በር አንድነትን በሰላማዊ ሰልፍ እንዲቃወሙ የአስገዳጅ ጥሪ የተደረገላቸው አብዛኞቹ ነዋሪዎች ባለመሳተፋቸው ኢህአዴግ የወረዳውንና […]

የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሀብት ለመመዝገብ፣ ከመጪው ኅዳር ወር ጀምሮ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ፤ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። 45ሺ ባለሥልጣናት፤ ይህን የሀብት ምዝገባ፤ እንዲያከናውኑ እቅድ የተያዘ ሲሆን ፣ ለዚህም ፣ ቅድመ-ዝግጅት እየተደረገ ነው። መሳይ መኮንን፣ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ፤ የሥነ-ምግባር ትምህርት እና መገናኛ …

45 ሺ የመንግሥት ባለስልጣናትና የሚጠበቀው የሀብት ምዝገባ Read more »

ከአዲስ አበባ 401 ኪሎ ሜትር በስተሰሜን በምትገኘው ታሪካዊቷ የወሎ ክፍለ ሀገር(የአሁኑ ደቡብ ወሎ ዞን)ከተማ ደሴ ልክ እንደ አዲስ አበባ የክረምቱ ዝናብና ብርድ ቢያስቸግርም የነዋሪዎቿ እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ የምን አዲስ አበባ ያሰኛል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ሲዘፈንላት የኖረው የነዋሪዎቿ ውበት፣ ተግባቢነትና በሙስልም ክርስቲያኑ በፍቅር ተግባቦት የሚያስቀና ኑሮ እንጉርጎሯዊ አድናቆት ይሰማል፡፡ ይህ ደግሞ በተግባርም እውነት መሆኑንን ስመለከት አቦ ደሴዎች […]

ሐምሌ 3 ቀን 2005 ትናንት በማለዳ ነበር ተነስቼ ከሰሚት ወደ ሳሪስ ያቀናሁት፡፡ የሐምሌን ቀዝቃዛ የጠዋት አየር እየተመገብኩ ከጓደኞቼ ጋር ከተቀጣጠርኩበት ሐበሻ ካፌ ስደርስ ሰዓቴ ከጥዋቱ 1፡30 (7፡30 AM) ይል ነበር፡፡ ሁላችንም ከየአቅጣጫዉ በዚያች አነስተኛ ካፌ ከተሰባሰብን በኋላ ቁርስ ቢጤ እንደ …

የቃሊቲ ዉሎ ከነእስክንድር ነጋ ጋር – በበትረ ያዕቆብ Read more »


 

በሚኪያስ በቀለ
 “Any law that uplifts human personality is just. Any law that degrades human personality is unjust. One has not only a legal but a moral responsibility to obey just laws. Conversely, one has a moral responsibility to disobey unjust laws… for an unjust law is no law at all.” Dr. Martin Luther King
የመንግሥት ወይስ የሕዝብ ሕግ?
በኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ ሽብር አዋጅ የወጣው በ2001 ዓ.ም ላይ ሲሆን የአዋጁ ረቂቅ የተለያዩ የአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ደርጅቶች እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አዋጁ የዜጎችን የሰብኣዊ መብቶች አደጋ ውስጥ ስለሚከት መስተካከል እንደሚኖርበት ድምፃቸውን አሰምተው ነበር፡፡ ነገር ግን መንግሥት ትችቶቹን ከቋፍ ሳይከት አዋጁን በ2001ዓ.ም ከ547 የፓርላማ አባላቶቿ ውስጥ 378ቱ በተገኙበት በ268 የአዎንታ ድምጽ፣ በ91 ተቃውሞ እና በ1 ድምፀ ተአቅቦ የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 ኅብረተሰቡን ከአደጋ ለመጠበቅ በሚል አወዛጋቢውን ሕግ አውጥቶ ማስፈጸም ጀምሯል፡፡
አዋጁ በወጣበት ቀን “ባለራዕዩ” የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴት መለስ ዜናዌ የአዋጁን ትክክለኛነት (Ligitimacy) ለፓርላማው ሲያብራሩ “… አዋጁን ስናረቀቅ ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ እና ከአውሮፓ አገራት ጥሩ ጥሩውን ቃል በቃል….ለምሳሌ በነዚህ ሃገራት ባለው ሕግ አሸባሪ ብሎ የመፈረጅ ሥልጣን የሕግ አስፈፃሚው ሲሆን እኛ ግን የሕግ አውጪው ሥልጣን እንዲሆን አድርገናል…” ብለው ነበር፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር በዓለማችን የሕግ የበላይነት ከሰፈነባቸው አገራት የፀረ ሽብር አዋጁን “ቃል በቃል” መገልበጣቸው ሕጉን ትክክለኛ ሊያስብለው እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሠራ የተፈጥሮ ሕግ (Universal law) እንደመኖሩ አንድ ሕግ
ሲወጣ ሀገሪቷ ካላት ሁኔታ እና በሕጉ ከሚተዳደሩት ማኅበረሰቦች አንፃር መሆን እንዳለበት (Capable of being complied with) በማወቅ ይሁን ባለማወቅ ጠ/ሚኒስትሩ የዘነጉት መሠረታዊ የሕግ አወጣጥ መርሕ ነው፡፡ የሰው ልጅ የመኖር (የሕ.መ.አ.15*) እና ከማንኛውን የአካል አደጋዎች የመጠበቅ (የሕ.መ.አ.16*) በዓለማችን ላይ ሁሉ ዕኩል የሚሠሩ የተፈጥሯያዊ መብቶች አሉት፡፡ ነገር ግን እነዚህን መብቶች ለመጣስ በየሃገራቱ ብቻ አይደለም በየኅብረተሰቡ የተለያዩ አደጋዎች እንደመኖራቸው መብቶቹን ለማስጠበቅ የሚወጡት ሕጎች (እንደ ፀረ ሽብር ሕግ) ከቦታ ቦታ እና ከጊዜ ጊዜ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የተለያዩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሕግ ሲረቀቅ የሌላ ሀገሮች ተመሳሳይ ሕግጋት (raison d’etre) መመልከት ተገቢ ቢሆንም በሕጉ የሚተዳደረውን ማኅበረሰብ ጥያቄ መመለስ ዋነኛው አላማው ነው፡፡ (Law must deliberately meet one of the prevalent ‘needs’ of the society) የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ የራሱ የሆነ የአስተሳሰብ እና የአኗኗር ዘይቤ አለው፡፡ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ፣ እንግሊዝ ወይም አውሮፓ ዕኩል ለሽብር ጥቃት የተጋለጡ አገሮች አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያ የፀረ ሽብር አዋጅም ኢትዮጵያን ከሽብር አደጋዎች ለመጠበቅ እንዲያስችል ተደርጎ መረቀቀ ይኖርበታል እንጂ ከሌላ ሀገር ሕጎች ላይ ቃል በቃል መገልበጥ የለበትም፡፡

የሰብኣዊ መብት የሚያስከፍል የሽብር ጥቃት በኢትዮጵያ?
የሰብዓዊ መብት መንግሥት በመልካም ፍቃዱ አይሰጠንም፣ የሰው ልጆች ሆነን ስለተፈጠርን ብቻ የምናገኘውና በቀለም፣ በዘር፣ በሀብት እና በመሳሰሉት ሳንለያይ ያለምንም አድሎ የምንጠቀመው በነጻ በእግዚያብሄር አማሳል ስለተፈጠርን ብቻ የሚኖረን መብት ነው፡፡ መንግሥት መብቱን ባይሰጠንም የመጠበቅ ኃላፊነቱ ግን የሱ፤ የሀገር (የመንግሥት) ኃላፊነት እንጂ የግለሰቡ (የእኛ) ኃላፊነትም አይደለም፡፡ የሰብኣዊ መብትን የመጠበቅ ኃላፊነት የመንግሥት ነው ስንል መብቶቻችን እንዳይገፈፉ በሕግ አግባብ የመጠበቅ፣ መብቶቻችን ሲገፈፉ አግባብ ባለው የፍርድ አካሄድ የማስጠበቅ እና ሕግ የተላለፈውን መቅጣት አለበት እንደ ማለት ነው፡፡ ችግሩ የሰብኣዊ መብቶቻችን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ የመንግሥት እንደመሆኑ መብቶቻችንንም ለመጣስ የመጀመሪያው እራሱ መንግሥት ነው፡፡
ይሄም የሥልጣን ፍቅር ያሰከረው፣ ሥልጣን እና/ወይም መሣሪያ ከሕዝብ የሚበልጥ መስሎ የሚታየው መንግሥት ላይ በብዛት ይታያል፡፡ መንግሥት የሰብኣዊ መብቶች ሊጥስ ከሚችልባቸው አጋጣሚዎች ዋነኛው የኅብረሰቡን ጥቅም (Public interest) ለማስጠበቅ የተወሰኑ ግለሰቦች የሰብኣዊ መብት መጣስ ይኖርባታል በሚል ነው፡፡ የኢትዮጵያው የፀረ ሽብር አዋጁም የብዙኃኑን ሠላም ለማስጠበቅ በሚል የግለሰቦችን ሰብኣዊ መብት እየጣሰ መፈፀም ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን የተላየዩ ሰብኣዊ መብቶችን የሚያስጥስ የሽብር አደጋዎች በኢትዮጵያ ውሰጥ የሉም፡፡ ይልቁንም ከአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ በዊኪሊኪስ ድረ ገጽ አማካኝነት ሾልኮ የወጣው መረጃ (Ref. No. #06ADDISABABA2708) ተፈፀሙ ከተባሉት የሽብር ጥቃቶች በጳጉሜ 1 ቀን 1998 ዓ.ም ተፈፀመ የተባለው ሦስት የቦንብ ጥቃት እራሱ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደፈፀማቸው እና ኤርትራንና ኦነግን ተጠያቂ እንዳደረገ ይገልጻል፡፡
የሌለን ሽብር መፍጠር ይልሃል ይህ ነው፡፡ ስለዚህ የሽብር ጥቃት በማያሰጋበት እና “አሸባሪ” በሌለባት ኢትዮጵያ የተለያዩ የሰብኣዊ መብቶችን እየገፈፉ የፀረ ሽብር አዋጅን ማስፈፀም ከአደጋ የሚጠብቀው ሕዝቡን ወይስ መንግሥትን? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በመጀመሪያ የፀረ ሽብር አዋጁ በሕገ መንግሥት ውስጥ ከተካተቱት የሰብኣዊ መብቶች ውስጥ የትኛዎቹን ይጥሳል? የሚለውን መመለስ ያስፈልጋና ጥቂቶቹን እንሆ፡፡
ከፍተኛ ጥንቃቄ (Due Deligence) ለሰላማዊ ሰልፍ
የሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲታሰብ ንብረቶችን ማጥፋት፣ በፖሊስ ላይ ጥቃት መፈፀም እና የመሳሰሉት ወንጀል ከመሆናቸው ባሻገር ሠላማዊ የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ይሸረሽሩታል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተግባራት ወንጀል ቢሆኑም ሽብር አይደሉም፡፡ ይልቁንም “ማንኛውንም ሰው ወይም ቡድን የፖለቲካ፣ ሃይማኖታዊ፣ ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ በማሰብ በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር… የሕዝብ አገልግሎት ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጠ፣ የያዘ፣ በቁጥጥር ስር ያደረገ፣ ያቋረጠ፣ ወይም ያበላሸ እንደሆነ…” የሽብር ድርጊት እንደተፈፀመ የፀረ ሽብር አዋጁ ይደነግጋል (የፀ.ሽ.አ.አ.3(6)*) ነገር ግን የሕዝብ አገልግሎት ማቋረጥ ኅብረተሰቡን ምን ዓይነት አሳሳቢ አደጋ፤ ለዛውም እንደ ሽብር የሚቆጠር አደጋ ውስጥ እንደሚጥል ግልጽ አይደለም፡፡ ደግሞም የሠላማያዊ ሰልፍ ሲደረግ በመቶዎች፣ በሺሕዎች ወይም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ በወጣበት የትራንስፖርት እና የመሳሰሉት የሕዝብ አገልግሎቶች ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ የቴሌኮሙኒኪሽን፣ የመብራት ኃይል፣ የውኃና ፍሳሽ ወይም ሌላ የመንግሥት ሠራተኞች ተቃውሞ ኖሯቸው ከሥራ የመቅረት አድማ ቢያደርጉ የሕዝብ አገልግሎት ሊቋረጥ ይችላል፡፡ በዚህ ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ሆኑ የሥራ መቆም አድማ ያደረጉት የሽብር ድርጊት ፈፀሙ ሊባል ነው? የሠላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት (የሕ.መ.አ.30(1)*) በተዘዋዋሪ ተገፈፈ ማለት ይሄ ነው፡፡ ለዚህም ነው የተለያዩ ባለሙያዎች እና ድርጅቶች አዋጁ የሽብር ድርጊቶችን ሲያብራራ አደናጋሪ (vague) እና ሰፊ (broad) ስለሆነ መሻሻል ይገባዋል እያሉ የሚጮሁት፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰፊ ክፍተት መተው በፍ/ቤቶች የተለያዩ ትርጉሞች እንዲሰጡት ከማድረጉ ባሻገር የፍትሕ ሚኒስቴር የፈለገውን ሰው እና/ወይም ድርጅት በሽብር ወንጀል ከሶ ችሎት ለመገተር መንገዱን ክፍት ያደረገዋል፡፡
የመረጃ ነጻነት እንደዋዛ
ታዋቅው የሕግ ሊቅ እና ፈላስፋ Seneca የሰው ልጅ ከተፈጥፎ ጋር በነጻነት ያለማንም ጣልቃ ገብነት መኖር ይኖርበታል ይላል፡፡
“Man is a sprit and his ultimate goal is the perfection of his reason in that sprit. Because man is a rational animal, his ideal state is realized when he has fulfilled the purpose for which he was born. And what is it that reason demands of him? Something very easy – that he live in accordance with his own nature.”
Man is a rational animal! የሰው ልጅ የሚያገናዝብ እንስሳ ነው፡፡ የሚያግናዛበው በአካባቢው ከሚያገኛቸው እውነታዎች አንፃር ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ልጅ ስለፈለገው ነገር ማወቅ ይፈልጋል፡፡ ከፈለው መረጃ ላይ፡፡ ያገኘውን መረጃ አገናዝቦ የፈለገው አቋም የመያዝ መብትም አለው፡፡ መንግሥትን ጨምሮ ማንም ሰው ይህንን ዕወቅ ይህንን አትወቅ እንዲለው አይፈልግም፡፡ የማወቅ፣ የማገናዘብ፣ አቋም የመያዝ ብቻ አይደለም አቋሙን ለፈለገው ሰው ያለምንም ፍርሐት የማሳወቅ መብት አለው፡፡ ምክንያቱም ሰው ነውና፡፡
መንግሥትን ከራሱ አማካሪዎች ይልቅ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የነጻው ፕሬስ ካልተቸው ሁሌም ትክክል ነኝ ማለቱ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ትክክል መሆን ሥልጣን ላይ ለመቆየት ብቸኛው አማራጭ ነውና፡፡ እንኳን በዚህ ፓርላማው፤ የአንድ ፓርቲ ግለሰቦች በሞሉበት ሀገር እና የጦፈ ክርክር ባለበት ፓርላማም የኅብረተሰቡ እና የፕሬስ ትችት ለመንግሥት የሥራ ወሳኝ ነው፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 6 እንዲህ ይለናል፡፡ “…የሽብር ድርጊት እንዲፈፅሙ ወይም ለመፈፀም እንዲዘጋጁ ወይም በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያበረታቸው ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ የሚገፋፋቸው እንደሆነ አድርገው ይረዱታል ተብሎ ሊገመት የሚችል መልዕክት ሆን ብሎ ወይም በግዴለሽነት ያተመ ወይም ያሳተመ እንደሆነ….” ሽብርተኝነትን ማበረታታት ስለሆነ ከ10 እስከ 20 ዓመት ያስቀጣል፡፡ የሽብር ድርጊትን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የሚያበረታታ መልዕክት ምንድነው? ለሚለው አዋጁ ለሽብር ድርጊት ይገፋፋል ተብሎ የሚገመት መልዕክት ነው ብሎ ይመልሳል፡፡ ማን ነው አንድን መልዕክት ለሽብር ይገፋፋል የሚለውን ግምት የሚሰጠው? መንግሥት ወይስ ማን? ከሽብር ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው መልዕክት ሲያስተላልፍ ማለት ሲቻል ሽብር ይገፋፋል ተብሎ የሚገመት መልዕክት ነው ብሎ እስከ 20 ዓመት እስር መቅጣት ለምን አስፈለገ? በዚህ ዓይነት አቃቢ ሕግ ሽብርን ያበረታታል ብሎ ካሰበ ማንኛውንም የመንግሥት ትችት የሽብር ድርጊትን አበረታታ ብሎ ሊከሰው ነው ማለት ይሆናል፡፡ ለዛውም የሽብር ድርጊት በሚያወዛግብ ሁኔታ በተብራራበት የሕግ ማዕቀፍ፡፡
ማበረታታት (Encouragement) ከሚል ማነሳሳት (Incitement) በሚል ጠንካራ እና ሕጋዊ መርሕ መተካት ይቻል ነበር፡፡ ማነሳሳት (Incitement) የወንጀል ሕጋችን ሲያብራራው “ሌላውን ሰው በመጎትጎት፣ ተስፋ በመስጠት፣ በገንዘብ፣ በስጦታ፣ በማስፈራራት ወይም በማናቸውም ሌላ ዘዴ አንድ ወንጀል እንዲያደርግ ያግባባ እንደሆነ…” አነሳሹ የሚቀጣው ወንጀሉ ቢያንስ ተሞክሮ (Attempt) እንደሆነ” (የወ.ሕ.አ.36(1)*) ነው ይላል፡፡ ሌሎች ወንጀሎችን ማነሳሳት እንደዚህ ባለው ጠባብ ሕግ ለዛውም የተባለው ወንጀል ዝግጅትን (Preparation) አልፎ ወንጀሉ ቢያንስ ከተሞከረ ብቻ (Attempt ላይ ከደረሰ) እያስቀጣ ሽብርን ያህል ለኅብረተሰቡ አደገኛ የሆነ ወንጀል “ሽብርን ያበረታታል ተብሎ ስለታሰበ” ብቻ እስከ 20 ዓመት ማስቀጣቱ አግባብ አይደለም፡፡
ይህ ሲባል የነጻው ፕሬስ የሕትመት መልዕክቶች በሙሉ ሽብርን አይቀሰቅሱም እና አያስቀጡም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የሚያስቀጣው መልዕክት ከሚያደርስው የአደጋ አጣዳፊነት (Imminent) እና ወሳኝነት (Neccessity) አንፃር መመርመር ይኖርበታል፡፡ አደገኛ መልዕክትን መተርጎም ለፍ/ቤቶች ብቻ ሳይሆን ጠበብ ባለ የሕግ ማዕቀፍ መካተቱ ለሀገሪቷ የሚጠቅሙትን መልዕክቶች በተቃራኒው አደገኛ ናቸው ብሎ ከመቅጣት ይሰውራልና ቢታሰብበት አይከፋም፡፡ ከዓለማችን የተሰባሰቡ የሕግ ሊቆች እና ከተባበሩት መንግሥታት የተሾሙ ባለሙያዎች በተገኙበት በተረቀቀው የጁሃንስፐርጉ መርሕ ላይ ለኅብረተሰቡ አደጋ የሚያጋልጡ መልዕክቶች ማስቀጣት ያለባቸው ሦስት ሁኔታዎችን (Pre conditions) ሲያሟሉ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ “መልዕክቱ አፋጣኝ አደጋን ለማድረስ የተሳበ ከሆነ (Immenint)፣ መልዕክቱ አደጋውን ማድረሱ እርግጥ ከኖነ (Probable) እና በመልዕክቱ እና በሚደርስው አደጋ መካከል የተቀራረበ ግንኙነት ካለው (Cause and Effect)” ናቸው፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ ግን እነዚህን መዘርዝሮች ማሟላት አይደለም አንዱንም አያካትትም፡፡ እነ ውብሸት ታዬ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና የመሳሰሉት ነገ ጠባ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ለኅብረተሰቡ መረጃን በማድረስ፣ በመንግሥት ላይ ትችት በማቅረብ የሚሠሩ ታታሪ ጋዜጠኞች ናቸው ብለው የዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ሲሸልሟቸው የደከሙላት ኢትዮጵያ ግን የሽብር ድርጊትን አበረታታቹኋል ብላ ማረሚያ ቤት የላከቻቸው፡፡ አራሚዎቹን ወደ ማረሚያ፡፡ ይህ አካሄድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 የተገለፀውን የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብት ከመጣሱ ባሻገር ኅብረተሰቡ በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ያለውን አመኔታ እንዲያጣ ምክንያት ሆኗል፡፡
በሃያማኖት ጣልቃ ገብነትን መቃወም እንደ ሽብር
መንግሥት ሕዝቡን ለመቆጣጠር እና ያለምንም ስጋት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ካሉት አማራጮች ውስጥ ዋነኛው በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባት ነው፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ በሃይማኖቱ አይደራደርም፣ የሃይማኖች አባቶች ትክክል ነው ያሉት የእግዚአብሔር/የአላህ ቃል ነውና ለቃሉ መገዛት ግድ ይሆናል፡፡ ፈጣሪ የሾመውን ፈጣሪ ያውርደው እንዲሉ፡፡ በጣልያን በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተወለደው የሕግ ሰው Nicolo Machiavelli ለመሳፍንት መመሪያ በጻፈው The Prince በተሰኘው መጽሐፉ መንግሥት በሃይማኖት ሕዝቡን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችል ሲገልጽ፤
“…touching which all difficulties are prior to getting possession, because they are acquired either by capacity or good fortune, and they can be held without either; for they are sustained by the ancient ordinances of religion, which are so allpowerful,èandèofèsuchèaècharacterè thatè theèprincipalitiesèmayèbeè held no matter how their princes behave and live.” ይላል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥትም በችሎታ (Capacity) ወይም በተወዳጅነት (good fortune) ኅብረተሰቡን መቆጣጠር ስለማይችል፤ ከፋፍለህ ግዛ (Divide and rule) ከሚለው የማካቬሊ መርሕ በተጨማሪ በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ጣልቃ መግባቱ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ነገር ግን የሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሃይማኖት እና መንግሥት የተለያዩ (የ.ሕ.መ.አ.11*) መሆን አለባቸው በሚል ሰፊ ተቃውሞ ለማድረግ በቅርቡ ወኔውን አግኝቷል፡፡ መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ እየገባ ነው፣ የአሕባሽ አስተምህሮት ማስፋፋት ይቁም በሚል በመንግሥት ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሠላማዊ የሆነ ተቃውሞ ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ ነገር ግን መንግሥት በተግላቢሽ የሃይማኖታዊ መንግሥት የማቋቋም ድብቅ አጀንዳ እንጂ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ የላቸውም በሚል ከ500,000 በላይ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ የአዎንታ ፊርማ አግኝቶ የተቋቋመውን የኮሚቴ አባላት በፀረ ሽብር አዋጁ ከስሶ ጉዳዩ በፍ/ቤት በመታየት ላይ ያገኛል፡፡ የክርክሩ ውጤት (ውሳኔ) የሚተላለፈው በገለልተኛ ፍ/ቤት ይሁን በሕግ አስፈፃሚው አካል ቀጭን ትዕዛዝ (የፍ/ቤቶችን ገለልተኝነት ሳልገጽ ማለፍ አግባብ ስለማይሆን) ግልጽ ባይሆንም ከሕጉ አንጻር ነጻ የመውጣት ዕድል ቢኖራቸውም ካለው ነባራዊ ሁኔታ እና ከበፊት ተሞክሮዎች ጥፋተኛ ሊባሉ የሚችሉበት አጋጣሚ የሰፋ ነው፡፡
ለአደጋ የተጋረጠው የፍርድ አካሄድ (Due process of law)
የፀረ ሽብር ሕጉ ለመስፈጸም ማስረጃ ለማሰብሰብ በሚደረጉ ተግባሮች፣ በፍርድ ቤት በሚኖረው አካሄድ፣ እና በማረፊያ ቤቶች የተከሳሾች እና ከጉዳዩ ተያያዥነት አላቸው ብሎ ፖሊስ የጠረጠራቸውን ግለሰቦች የሰብዓዊ መብት እንደሚጣስ ልብ ይሏል፡፡
የወንጀል ተከሳሾች “ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍ/ቤት….የመሰማት” ሕገ መንግሥታዊ መብት አላቸው (የሕ.መ.አ.20(1)*)፡፡ ነገር ግን በፀረ ሽብር አዋጁ የሚከሰሱ ተጠርጣሪዎች ከወንጀል ስነ ስርዓት ሕጉ 14 ቀን በመጨመር የጊዜ ቀጠሮ ትንሹ 28 ቀን እንደሆን ከመደንጉ ባሻገር ይህ ጊዜ እስከ 4 ወራት ሊዘልቅ እንደሚችል ይደነግጋል (የፀ.ሽ.ሕ.አ. 20(3)*)፡፡
ሌላው የፀረ ሽብር አዋጁ የሚጥሰው የግለሰብን የነጻንት መብት ሲሆን (Right to privacy) “በሽብርተኝነት የተጠረጠረን ሰው የስልክ፣ ፋክስ፣ የሬድዮ፣ የኤሊክትሮኒክስ፣ የፖስታ እና የመሳሰሉትን ግንኙነቶች ለመጥለፍ ወይም ለመከታተል…. ጠለፋውን ለማስፈፀም ወደ ማንኛውም ቤት ውስጥ በሚስጥር የመግባት… “መብትን ለፖሊስ እና ለደኅንነት መብቱን ይሰጣል (የፀ.ሽ.አ.አ.14(1)*)፡፡ በዚህ የተገኙትንም ማስረጃዎች በሚስጥር መጠበቅ እንዳለባቸውት ይደነግጋል (የፀ.ሽ.አ.አ.14(2)*)፡፡ ይህም የግል ሕይወት የመከበር እና የመጠበቅ የሰብኣዊ መብትን (የሕ.መ.አ.26) በግልጽ ከመጣሱ ባሻገር የተያዙት ማስረጃዎች በሚስጥር ሲጠበቁ አይታዩም፡፡ አኬልማዳ፣ ጀሀዳዊ ሃረካት እና የመሳሰሉት የኢቲቪ ዶክመንተሬዎች ማስረጃዎቹ በሚስጥር ከመያዝ ይልቅ ቀድሞ ተከሳሾችን ባደባባይ ለመወንጀል ጥቅም ላይ እንደዋሉ ያረጋግጣል፡፡ ይህም ወደ ሚቀጥለው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ያሸጋግረናል፡፡
ማንኛውም ተከሳሽ በፍርድ ቤት ቀርቦ እና ማስረጃ ተሰምቶ ጥፋተኛ እስከሚባል እንደ ነጻ ግለሰብ መቆጠር (presumption of innocence until proven guilt) እንደሚኖርበት ሕገ መንግሥታችን ቢደነግግም (የሕ.መ.አ.20(3)*) በቴሌቪዥን ዶክመንተሪዎች እና የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ጭምር ተከሳሾች የሽብር ድርጊትን በመፈፀም ዙሪያ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ተሳትፈዋል በሚል መግለጫዎች ሲሰጡ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ የሙስሊሞች ጉዳይ ‹‹መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ›› ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጋ እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ የጅሃዳዊ ሃረካት በሚለው የዶክመንተሪ ፊልም የደንበኞቻችን ስም ጠፍቷል በሚል የ8 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያን በፍ/ቤት ለመጠየቅ የፍትሐ ብሐር ክስ እንደጀመሩ በቅርቡ ሰምተናል፡፡ ክርክሩ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችን እንደተከሳሽ ማካተቱ የሕግ የበላይነትን ያሳየናልና በርቱ ብያለሁ፡፡
የሚስጥሪያዊነት ስነ ምግባር በሽብር ምርመራ…
የተለያዩ ባለሙያዎች ከሥራ ዘርፋቸው አንፃር የሚጠበቁባቸው የሥነ ምግባር ኃላፊነቶች አሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ምስጥራዊነት (Confidentiality) ነው፡፡ ነገር ግን አዋጁ የባለሙያዎቹን ሥነ-ምግባር ወደ ጎን በመተው፤ ለሽብር እንኳን የባለሙያ ሥነ-ምግባር የሰብኣዊ መብትም ይጣሳል ይለናል፡፡ አዋጁ በማስረጃ አሰባሰብ አካሄዱ “…[ፖሊስ] ለምርመራው የሚረዳው መሆኑን በሚገባ የሚያምንበት መረጃ ወይም ማስረጃ ከማናቸውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ ባለሥልጣናት፣ ባንክ፣ የግል ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፡፡ መረጃ ወይም ማስረጃ የተጠየቀው ወገን መረጃውን ወይም ማስረጃውን የመስጠት ግዴታ አለበት” ይላል (የ.ፀ.ሽ.አ.አ.22*)፡፡ በዚህም ምክንያት ጠበቃ ደንበኛው የሕግ ወኪሌ ብሎ ያማከረውን፣ ሐኪም ታማማሚው ለሕክምና እንዲረዳው ብሎ የተናገረውን ሚስጥር ብቻ ሳይሆን የንስሐ አባት ይፀዩልኝ ዘንድ ብሎ የተነገራቸውን ጉድ ጭምር ለደኅንነት ወይም ለፖሊስ አንድም ሳይደብቁ የመናገር ግዴታ ይጥላባቸዋል፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ፡፡
ለኢ-ፍትሐዊ ሕግ አንገዛም!!!
በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ትክክለኛ (Right) እና ፍትሐዊ (Just) ያልሆነ ሕግ ከመጀመሪያው አስገዳጅነት የለውም ይለናል፡፡ ሕብረተሰቡም ይህንን ሕግ የመቃወም ሕጋዊ ብቻ አይደለም የሞራልም ተጠያቂነት አለበት፡፡ በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ሲወጣ የኅብረሰቡን አመለካከት እና ጥያቄ ግምት ውስጥ ካልከተተ ሕጉ የመንግሥት እንጂ የሕዝብ አይሆንም፡፡
የመንግሥት ሕግ ደግሞ በጀርመኑ ናትዚ ጊዜ ያለውን ከፍተኛ ተግዳሮት አይተናል፡፡ የጀርመን ፕሮፌሰር Fuller ኢፍትሐዊ ውሳኔዎች የሚፈጠሩት በፍርድ ቤቶች ችግር ሳይሆን በዋነኛነት በሕግ አውጪዎቹ ድክመት እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ ሕጎች ይላሉ ፕሮፌሰር ፉለር Morality of duty ብቻ ሳይሆን Morality of Aspiration ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህም ማለት አንድ ሕግ በኅብረሰቡ ዘንድ ሊያስተዳድረን ይገባል የሚል እምነት ከሌላቸው በግዴታ ብቻ በሕጉ መገዛታቸው በቂ አይደለም፡፡ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት እና አንዱ ከሌላው ጋር ያላቸውን ቁርኝትና እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡
“The morality of aspiration…is the morality of the Good Life, of excellence, of the fullest realization of human powers…Where the morality of aspiration starts at the top of human achievement, the morality of duty starts at the bottom. It lays down the basic rules without which an ordered society is impossible, or without which an ordered society directed toward certain specific goals must fail of its mark.”
ኢትዮጵያ ለሽብር ጥቃት ያን ያህል የሚያሰጋ ደረጃ ላይ እንደሌለች ሁላችንም የምናውቀው ኩነት ነው፡፡ በሱማሊያ ጦርነት መሳተፏ ከአልሻባብ ለሚሰነዘር ጥቃት ያጋልጣታል የሚል ስጋት ቢኖርም በአሁኑ ጊዜ ግን አሸባሪ ተብለው እየተፈረጁ የምናየው የሀገር ውስጥ ግለሰቦችን እና/ወይም ቡድኖችን እንጂ ከሱማሊያ የሚመጡትን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ምንም ጭቆና ቢደርስበት ከነበረው የረዥም ጊዜ የአስተሳሰብ ደረጃ (Moral standard) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሽብር ድርጊት ተብለው የሚወሰዱትን እንደ አጥፍቶ ማጥፋት፣ የንፁሐንን ዜጋ ሕይወት ለመደራደሪያነት የማቅረብ ዓይነት ተግባራትን እንዳማይፈፅም እሙን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተራበበት ጊዜ እንኳን አመፅ/ሽብር አላስነሳም፡፡ ስለዚህ ለሽብር ጥቃት ርቃ የምት&#487

እንደሚታወቀው ሁሉ ከሁለት ዓመት በፊት የቤተ ክርስቲያኗ ሕንጻ ግዢ ክፍያ ሳይጠናቀቅና በተለይም ከፍተኛ የሕግ ክፍተቶችን በመያዝ የቤተ ክርስቲያኗን ሰላም በማናጋት ብጥብጥን ለማስነሳት ምክንያት ሆኖ የነበረው፤ በሥራ ላይ ያለው የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ስለነበር፤ ይህ ቤተ ክርስቲያኗ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የማያካትት እና …

የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች Read more »

ከአሰግድ ታመነ [ ኖርዌይ ] የቀድሞው የወያኔ መሪና አንባገነኑ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞተው ተቀብረዋል አፈሩን ድንጋይ ያድርግላቸውና እንዳይነሱ ምን ይታወቃል ተጭበርብሬ ነው ልመለስ ብለው እንዳይመለሱ ፈራው፡፡ እንደሚታወቀው የወያኔውን መሪ በስልጣን ዘመኑ ማለትም ለሁለት አስርተ አመታት በወጣና በገባ ቁጥር ከቤተ-መንግስት …

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ፡፡ Read more »