ዜና ቤተክርስቲያን የታደሰ ሲሳይ “ገበና መሸፈኛ የበለስ ቅጠል” አባ መላኩ ጌታነህ (“ፋኑኤል”) ከድጡ ወደማጡ

አባመላኩ ወደምንኩስና አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ልብስ ሰፊ እንደነበሩ ይታወቃል። ምን አነሳስቷቸውና በምንስ ምክንያት በአንድ ጀምበር ወደ ምንኩስናና ብሎም ወደክህነት እንደገቡ የሚያውቁት እሳቸው ብቻ ነው። ስለእሳቸው በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ብድግ ብለው ተነስተው ከተሰወሩ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምንኩስና ቆብ ጭነው ወደ ሰፈራቸው እንደተመለሱና ምንም ዓይነት የገዳም ኑሮ፣ ሥርዓቱና ሥነምግባሩ ያልነካቸው፤ የከተማ ጩሉሌ ወይም በዘመኑ ቋንቋ “አራዳ” እንደሆኑ ነው። አባ መላኩ በልብስ ሰፊነት ይተዳደሩ በነበሩበት ጊዜ የተቀደደ ልብስን ይሰፉ እንደነበረና አዲስ ጨርቅ ወይም ጣቃ ቀደው ይሰፉም እንደነበር አራሳቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል። የተቀደደን መጥቀም፣ የተቦጨቀን መጣፍ ወይም የተዛነፈውን ማስተካከል የማንኛውም ልብስ ሰፊ ተግባሩ መሆኑ አይዘነጋም። ታዲያ አባ መላኩ ከልብስ ሰፊነት ሙያ ይዘውት ወደ ቤተክህነት የመጡት መቅደዱን፣ መሸርከቱንና መጉመዱን ብቻ ነው። አሁን ግን የሚቀዱት ሐይማኖትን፣ የሚሸረክቱት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እንዲሁም የሚጎምዱት ደግሞ የምዕመናንን ሕሊናና አመለካከት ነው። ለነገሩስ “ግም ለግም አብረህ አዝግም” እንደሚባለው አባ መላኩ ክህነቱ የተሰረዘበትን የዝሙት ቀበኛውን ታደሰ ሲሳይን ቢሸፍኑና ጋሻ ጃግሬ ቢሆን ምን ይገርማል? ሁለቱም በግብራቸውና በባህሪያቸው ተመሳሳይ  መሰሪዎችና አታላዮች በመሆናቸው ነው።

አባ መላኩ በሹመትና በስልጣን ሰክረው፣ የተናገሩን ቃል አጥፈው፣ የተፉትን ልሰው በፊት አውግዘዋቸው ከነበሩት ከቀደሞው አባ ገብረመድህን (አቡነ ጳውሎስ) ጋር  ህሊናቸውን ሸጠው መቀላቀላቸው፤ የደለበ ስጋ እንጂ ህሊና እንደሌላቸው በገሃድ “መላኩ በመላኩ” ላይ የመሰከሩበትን፣ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ መሆናቸውንና ቀላማጅነታቸውንና አታላይነታቸውን የሚያረጋግጠውን እራሳቸው አባ መላኩ የተናገሩትን ከዚህ በታች አዳምጠው የራስዎን ፍርድ ይስጡ። በዚህም መሠረት ከሰባት ዓመት ገደማ በፊት በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚሰራጨው ነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ ላይ አባ መላኩን አስመልክቶ የቀረበ መርሃግብር ለግንዛቤ እንዲረዳ እንዳለ እዚህ ላይ አቅርበነዋል። (አባ መላኩ ይህንን የተናገሩት ከዛሬ 17 ዓመት ገደማ በፊት ነው)።

አባ መላኩ በወዶገብነት ተመልሰው ለወያኔና ለአባ ገብረመድህን (አቡነ ጳውሎስ) እጅ ከመስጠታቸው በፊት በስደት ለሚኖረው ሕዝብ በሃሰት ይናገሩ የነበረው በዝርዝር ሰፍሯል። አባ መላኩ በዚህ ንግግራቸው ላይ በመጀመሪያ እንዴት ከኢትዮጵያ ውጭ እንደተላኩና በምንስ ሁኔታ ወደ አሜሪካን አገር እንደመጡ በራሳቸው አንደበት ተናግረዋል።  ከተናገሯቸው ውስጥ ዋና ዋናውን ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

“…አቡነ ጳውሎስን ከሚቃወሟቸው የቤተክርስቲያን ልጆች አንዱ ነኝ…”

  “….ስደተኝነት ጥገኝነት እንዲሰጠኝ ጠይቄ አሁን የምኖረው በስደተኝነት

     እንደሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ…”

 “… ለቤተክርስቲያንና ለሃገር እንደቆሙት ካህናት እኔም አንዱ ተቃዋሚ

     መሆኔ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ…”

  “…እኔም እኝህን ሰው (አባ ገብረመድህን) እግዚያብሔርን ትተው ዛሬ

   የመንግስት አገልጋይ በመሆናቸው እኔም ከሚያወግዟቸው ክፍል አንዱ

  እኔ መሆኔ በዚህ አጋጣሚ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ።…”

 ከሁሉም በላይ በጣም የሚገርመው፣ የሚያሳዝነውና የሚያስተዛዝበው ንግግራቸው ላይ ከመጽሃፍ ቅዱስ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 6 ቁጥር 2 ጠቅሰው የተናገሩት ነው። ይኽውም “….የእግዚያብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል የሚገባን አይደለም….”  ይህ ከ17  ዓመታት በፊት የጠቀሱት የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ዛሬ እራሳቸው ላይ እየመሰከረባቸው ይገኛል።  እሳቸው ናቸው በአሁን ጊዜ ለማዕድና ለሥልጣን በመቆም የኢትዮጵያን ህዝብ እግር ከወርች ጠርንፈው በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን እየጨፈጨፉ፣ እያፈናቀሉ፣ እያሰደዱና እያሰቃዩ ለሚገኙት ለወያኔዎቹ ለነ ስብሐት ነጋና አባይ ጸሐዬ መሳሪያ የሆኑት። አባ መላኩ ጌታነህ የጀመሩትን የማወናበድና የማምታታት ተልዕኮ አጠናክረው ቀጥለውበታል። እራሱ አስረጅ የሆነውን በሬዲዮ የተላለፈውን መርሃ ግብር ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ። አባ መላኩ

 

 

 

5 Comments on “ዜና ቤተክርስቲያን የታደሰ ሲሳይ “ገበና መሸፈኛ የበለስ ቅጠል” አባ መላኩ ጌታነህ (“ፋኑኤል”) ከድጡ ወደማጡ”

  1. Abba Melaku is a malicious person who is engaged in the distraction of
    Ethiopian Orthodox Tewahedo Church by using his authority to do criminal acts such as supporting the adultery of Taddese. He should be brought to justice for his crimes. He is a habitual lair. By listing to this recording I can say that he shouldn’t continue his duties as priest in the church or anywhere. I really wonder why the members of the church accept this demon by ignoring the facts. Christianity a religion of responsibility and action. But Abba Melaku manipulated the faithful’s oblivion to his advantage. Please, my fellow Ethiopians take action, don’t be irresponsible. Abba Melaku and Taddese are partners in crime.

      • ከላይ አስተያየት የሰጡ አቶ ተክሌ እንደጠቆሙት፤ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው የሰው ሚስት ያባለገውና በተለያዮ የዝሙት ቅሌቶች የተጨማለቀው ታደሰ ሲሳይ ክህነቱ በይፋና በሕዝብ ፊት ከተሰረዘበት በኋላ አንኳ እየሄዱ ከሱ እጅ መስቀል የሚሳለሙና ገንዘባቸውን የሚሰጡ ምዕመናን ናቸው። ወንጌል እኮ የሚያስተምረን ክፉውን እንድንጠየፍና ከበጎ ነገር ጋር እንድንተባበር ነው እንጂ እኛም የጥፋቱና የኃጢአቱ ተባባሪዎች እንዳንሆን ነው። በይሁዳ መልእክት ምዕራፍ 1 ቁጥር 4 ላይ እንደተጻፈው “ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢያተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ”። አባ መላኩ ለታደሰ ሲሳይ ሽፋንና ድጋፍ ሲሰጡ ክርስቶስን መካድ አይደለምን??? ከታደሰ ሲሳይና ከአባ መላኩ ጋር መተባበርና ከነሱ ጋር መቆም ማለት ክርስትናን አውግዞ ሌላ እምነት ከመፍጠር አይለይም። አዲስ እምነት ፈጥረናል ከተባለ ደግሞ እልፍ አዕላፋት ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ሐዋርያትና ሌሎችም የተጋደሉላትና ከሁሉም በላይ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ያነጻትን ቤተክርስቲያናችንን ለእውነተኛ አባቶች አስረክበው ይልቀቁልን። ምዕመና እባካችሁ ሰምታችሁ እንዳልሰማችሁ፣ አይታችሁ እንዳላይችሁ አትለፉ። ይህ ጉዳይ እኮ ኃይማኖታችሁ ነው። በቸልታና “እሱ ያውቃል” እያላችሁ በስንፍና አትለፉት። የናንተ ዝመታና ትብብር ነው ለአጥፊዎቹ የልብ ልብ የሆናቸው።

  2. ወያኔ የበግ ለምድ ለብሦ ቪዛ አሥመትቶ በየሀጉሩ በትኗል በተዘዋዋሪ የውጭ ምንዛሪውን ለማጎልበትና ለሥደት መንግሥት ምሥረታ ላይ እንዳይውል በማሠብ ይህ የወረበላ ቡድን ሀይማኖቶችን መሠረት እያናጋ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*