የአንድነት ፓርቲ አባሎች ጃንሜዳ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሩ

የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት እስማኤል ዳውድ ዛሬ ከጠዋቱ በ12፡30 ገደማ ሁለት ታጣቂ ፖሊሶች እና ሁለት የደህንነት ሰዎች መኖሪያ ቤቱ መጥተው ጃንሜዳ ፊት ለፊት በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ መታሰሩ ተገለጸ፡፡ እስማኤል ዳውድ በአንድነት ፓርቲ በኩል በምትታተመው የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ በ ቁጥር 3 እትም ላይ የጠቅላይ ሚንስትር ልጅ ለሆነችው ለዩሀና ግልፅ ደብዳቤ በሚል ጽሁፍ ጽፎ ነበር፡፡ ይህ ወጣት በጋዜጦች እና በሶሻል ሚዲያ ላይ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ የሆነ ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስበት እንደነበር በተደጋጋሚ ለፓርቲው አባሎችና ለጓደኞቹ ይገልጽ ነበር፡፡ ከታሰረ በኋላ ሊጠይቁት ከሄዱት 3 አባላት መካከል ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪን በተጨማሪ ማሰራቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ፡፡
[አናንያ ሶሪ]