ጣይቱ!
ዐይኔ አይታክተው ፤ ላንችም አለቀሰ
ጣይቱ አቃጠሉሽ? ፤ ቅርስ ተደመሰሰ
ተመሪው ባለሀብት ፤ ማን ይሆን ወራሹ
ባለሥልጣን? ወይስ ፤ ሙስናን አጉራሹ?
አዲሲቷ ኢትዮጵያ ፤ ኃዘንሽ መራራ
ኩራት ሥልጣኔሽ ፤ ማንነት አሻራ
የአንድ ዘር ተደርጎ ፤ የነገደ አማራ
ፍርድ ተላልፎበት ፤ ይጥፋ ይሙት በቃ
ሲያጠፉት ሲያሳዱት ፤ ዘወትር በሰቆቃ
ነፍስሽ እርቃን ቀረች ፤ በሐፍረት ተሸማቃ፡፡
አሁን እኔ ሰው ነኝ? ፤ ልጅሽ ዜጋሽ ነኝ ባይ?
ዝም ብየ የማይሽ ፤ ከስር ስትነቀይ?
ጥር 3 / 2007 ዓ.ም. @Amsalu Gkidne
