45 ሺ የመንግሥት ባለስልጣናትና የሚጠበቀው የሀብት ምዝገባ
የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሀብት ለመመዝገብ፣ ከመጪው ኅዳር ወር ጀምሮ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ፤ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
45ሺ ባለሥልጣናት፤ ይህን የሀብት ምዝገባ፤ እንዲያከናውኑ እቅድ የተያዘ ሲሆን ፣ ለዚህም ፣ ቅድመ-ዝግጅት እየተደረገ ነው። መሳይ መኮንን፣ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ፤ የሥነ-ምግባር ትምህርት እና መገናኛ የሥራ ሂደት መምሪያ ዋና ኀላፊ የሆኑትን አቶ ብርሃኑ አሰፋን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።