የግብፅ እልቂትና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ
ግብፅ ጥይት፥ አረር፥ እየዘራች፥ አስከሬን-አጭዳ በእሳት ታጋያለች።ያቺ አስከሬን ለዝንታ-ዓለም የሚቀመጥባት ሐገር ዛሬ የሰዉ አካል ይተለተልባታል።ያቺ የጥንታዊ ሥልጣኔ ጎተራ፥ ያቺ የታሪካዊ የቅርስ ቋት፥ ያቺ ሥልታዊት ሐገር ታወረች? ወይስ አበደች? እዉሩ ወይም እብዱስ ማነዉ?
ግብፅ ጥይት፥ አረር፥ እየዘራች፥ አስከሬን-አጭዳ በእሳት ታጋያለች።ያቺ አስከሬን ለዝንታ-ዓለም የሚቀመጥባት ሐገር ዛሬ የሰዉ አካል ይተለተልባታል።ያቺ የጥንታዊ ሥልጣኔ ጎተራ፥ ያቺ የታሪካዊ የቅርስ ቋት፥ ያቺ ሥልታዊት ሐገር ታወረች? ወይስ አበደች? እዉሩ ወይም እብዱስ ማነዉ?
ኢቲዮ ቴሌኮም ፣ ከፊል የቴሌኮሙዩኒኬሽን ማስፋፊያ ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚሆን 800 ሚሊዮን ዶላር የሚያስወጣ ውል፣ ZTE በሚል ምህጻር ከታወቀው የቻይና ኩባንያ ጋር ተፈራረመ። ቀደም ሲል፣ ከሌላው «ሁዋዌ» በሚል መጠሪያ ከታወቀው
ኤርትራዊው ስደተኛ ለተሻለ ህይወት ከሀገሩ ጠፍቶ ወደ ሱዳን እንደሄደ ይናገራል።
በኢትዮጵያ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝ አሁንም ማነጋገሩ ቀጥሏል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ የሙስሊሞች የሐይማኖታዊ ነፃነት ጥያቄ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በዚያው መጠን መንግሥት የሚወስደው እርምጃ እየጠነከረ ሄዷል ።
ሞስኮ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለዉ በ14ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዉያኑ አትሌቶች ድል ቀንቶአቸዋል።
ከአምስት ወራት በፊት በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግሥት የመሩት እና ራሳቸውን የሀገሪቱ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት ብለው የሠየሙት ሚሼል ጆቶጂያ እአአ በነገው ዕለት ነሀሴ 18፣ 2013 ዓም ቃለ መሀላ ይፈፅማሉ።
ግብፅ ውስጥ ከዛሬው የዕለተ ዓርብ (ጁምዓ) ጸሎትና ስግደት በኋላ አዲስ የተቃውሞ ማዕበል የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ከካይሮ በስተሰሜን 130 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘው ፣ ካፍር ኧል ሼክ በተሰኘው ክፍለ ሀገር፣ በፖሊስና በታጠቁ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር ደጋፊዎች በተደረገ ግጭት 10 ሰዎች ሲሞቱ ከዚያ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ቆስለዋል።
ሰላም በንግዱ ዘርፍ የተሰማራች እና የራሷ ሱቅ ያላት የ 19 ዓመት ወጣት ናት። ንግዷን በሙሉ ኋላፊነት እንዴት እንደምትወጣው ገልፃልናለች።
ካሜሩን በደቡቡ የሀገርዋ ከፊል የሚገኘውን የባካሲ ልሳነ ምድር ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች። ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ካሜሩንን እና ናይጀሪያን እአአ ከ1993 ዓም ወዲህ በይገባኛል ጥያቄ ሲያወዛግብ የነበረው ይኸው አካባቢ
ዜግነታቸዉን ቀይረዉ ለሌላ ሀገር የሚሮጡ አትሌቶችን በታላላቅ የዉድድር መድረኮች ላይ መመልከት አዲስ መሆኑ ቀርቷል። ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዳይ ጎልተዉ ይታዩ የነበሩ ኬንያዉያን አትሌቶች ተራዉን ለኢትዮጵያዉያኑ የለቀቁ ይመስላሉ።
በዓለማችን ሶስት ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በሁለት የአሜሪካን ዶላር የየቀን ኑሯቸዉን ይገፋሉ። የጀርመኑ የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን Brot für die Welt ማለትም ዳቦ ለዓለም የተሰኘዉ የልማት ተቋም እንዲህ ያሉ የድሃ ደሃ የሚባሉ ወገኖችን ኑሮ ለመደጎም በተለያዩ ሀገራት ይንቀሳቀሳል።
የፌደራል ትራንስፖርት፤ መለስተኛ አውቶቡሶች በሌሊት ፣ ራቅ ካሉ አካባቢዎች ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይጓዙ፣ የሥራ እንቅሥቃሴአቸውም በ 150 ኪሎሜትር እንዲገደብ መወሰኑ ፣ቅሬታን ያስከተለ መሆኑ ተነገረ። የተሽከርካሪዎቹ የመጫን አቅም ከፋብሪካው
ጥበብ በፀጋዋ የተላበሰችዉ ሙዚቃ አቅፋ ያሳደገችዉ ዕንቁ የሙዚቃ አባት ጥላሁን ገሰሰ ለ53 ዓመታት በዘለቀው የመድረክ ቆይታው በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ልዩ ጣዕም ባላቸው ሙዚቃዎቹ፤ ዘላለማዊ የሆነ ስምን ተክሎ አልፎአል ።
የቱኒዚያዉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበር ፖርቲ የሌለዉ መንግስት እንዲመሰረት ከተቃዋሚዎች የሚቀርበዉን ጥሪ እንደማይቀበሉ አስታወቁ። የአናህዳ ፓርቲ ሊቀመንበር ራሺድ ጋኑቺ ግብጽ ዉስጥ የሚታየዉ ሁኔታ ለቱኒዚያ ማስፈራሪያ ሳይሆን የሀገሪቱን ቀዉስ ለመፍታት ፓርቲዎች ወደዉይይት እንዲገቡ የሚጋብዝ መሆኑን ዛሬ አመልክተዋል።
ግብጽ ውስጥ ትናንት የተወሰደውን የኃይል እርምጃ፤ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በጥብቅ ነው ያወገዘው።
እ ጎ አ በ 2030 ምናልባትም ከዚያ ቀደም ብለው ሰዎች ወደ ማርስ ይጓዙ ይሆናል። ለጤና የሚስማማ አየር በሌለባት ፣ ሣር ቅጠል በማይታይባት፣ ቀይ አቧራ በሸፈናት ማርስ ፤ እንዴት ኅልውናቸውን ጠብቀው ይቆያሉ? በጤናስ መመለስ ይቻላል ወይ? ወደ ማርስ
በግብፅ መዲና በካይሮ፤ ከሥልጣን የተወገዱት የሙሐመድ ሙርሲ ደጋፊዎች በተቃውሞ ከመሸጉባቸው አደባባዮች እንዲነሱ ለማድረግ ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ፣ ቢያንስ 124 ሰዎች መገደላቸውን AFP አስታወቀ። በሌላ ዜና የሞቱት 95 ፤ የቆሰሉት ደግሞ
አፍሪቃ ያለፈውን አሠርተ-ዓመት ባልተቋረጠ የኤኮኖሚ ዕድገት በማሳለፍ ለውጭው ዓለም የመዋዕለ-ነዋይ ባለቤቶች ከመቼውም ይልቅ ማራኪ እየሆነች መምጣቷ በየጊዜው የሚጠቀስ ጉዳይ ነው።
የፕሬዝዳት ማሕሙድ አባስ ፅሕፈት ቤት «ለድርድሩ ትልቅ እንቅፋት» ባለዉ የሠፈራ መንደር ግንባታ ላይ ሁለቱን ወገኖች የምታደራድረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ግልፅ እንድታሳዉቅ ጠይቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ የመንግሥታቸዉን ግልፅ አቋም ግልፅ ማድረጋቸዉ አልቀረም።
ባለፈዉ ሳምንት ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በአንድ ትልቅ አሮጌ ጀልባ ተሳፍረዉ ወደሞልታ ደሴት ሲቃረቡ ጀልባዉ ተበላሽቶ ከመቶ በላይ ስደተኞች ነፍሳቸዉን የሚታደግ እስኪያገኙ ባህር ላይ ለቀናት ሲጨነቁ ቆይተዋል።
ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብለዉ የተጠበቁት ቢላል የተሰኘዉ የኢንተርኔት ራዲዮ ሁለት ጋዜጠኞች እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ድረስ ወደፍርድ ቤቱ ብቅ እንዳላሉ ተገለጸ።
የሞስኮዉ ሉዙኒኪ ኦሎምፒክ ስታዲዮም ከ33ዓመታት የሻምበል ምሩጽ ይፍጠር ድርብ ድልና ከሻምበል እሸቱ ቱራ አስደናቂ ዉጤት በኋላ ትናንት ማምሻዉን በመካከለኛ ርቀት ሩጫ ታሪክ ተሠራበት ትላለች ሞስኮ የምትገኘዉ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ።
የጀርመን የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት ፣ለልማት ፖለቲካ ና ለሰብዓዊ መብቶች ልዩ አስተዋጽኦ ላደረጉ ጋዜጠኞች ተሰጥቷል ።
ከማልታና ከግሪክ ቀጥሎ በርካታ አፍሪቃውያን ስደተኞች የሚጎርፉባት አውሮፓዊት ሃገር ኢጣልያ ናት።በአንዳንድ የኢጣልያ ግዛቶች መንግሥት ህገ ወጥ የሚላቸው አፍሪቃውያን ስደተኞች ደግሞ በኢጣልያ ጎስቋላ ህይወት ነው የሚገፉት።
የሴት ልጅ ግርዛት በተለያዩ 28 ሃገራት ተግባራዊ እንደሚሆን ሲነገር የቆየ ጉዳይ ነዉ። አሁን አሁን ግን በሰዎች ከሀገር ወደሀገር መዟዟር ምክንያት ቀድሞ በማይታወቅበት አካባቢ ሁሉ እየተዳረሰ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፊደሪሽን የልዑካን ቡድን ትናንት ባካሄደዉ አስቸኳይ ስብሰባ ሞስኮ በመካሄድ ላይ ባለው 14ኛዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና ባለፈዉ ቅዳሜ በተካሄደዉ የሴቶች ማራቶን ዉድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለዉ፤
ለጋዜጦች መብት የሚሟገተዉ ድርጅት CPJ በኢትዮጵያ ዉስጥ በጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ እንዳሳሰበዉ ገለጸ።
እስራኤልና ፍልስጤም የጀመሩት ቀጥተኛ የሰላም ድርድር ነገ ረቡዕ እንደሚቀጥል የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ የማሊ 2ኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኑ። ምንም እንኳን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይወጣም በኬይታ አንፃር ለከፍተኛው የሀገሪቱ ሥልጣን የተወዳደሩት የቀድሞው የገንዘብ ሚንስትር ሱማይላ ሲሴ ትናንት ባልተለመደ ሁኔታ ሽንፈታቸውን በመቀበል
የዓለም ዜና
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ የማሊ ፪ኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሸናፊ ሆኑ። ምንም እንኳን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይወጣም በኬይታ አንፃር የተወዳደሩት የቀድሞው የገንዘብ ሚንስትር ሱማይላ ሲሴ ሽንፈታቸውን በመቀበል ትናንት ከተፊካካሪያቸው ኬይታ ጋ በመገናኘት የእንኳን ደስ ያልዎት ምኞታቸውን መግለጻቸውን አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ-ህዝብ ጠበብት ጥናታዊ ትንበያ እንደሚጠቁመው ከሆነ ፣ ምድራችን፣ እ ጎ አ እስከ 2100 ዓ መተ ምኅረት፤ 11 ቢሊዮን ያህል ዜጎችን ማስተናገድ ግድ ሳይሆንባት አይቀርም። አሁን የዓለም ህዝብ ቁጥር 7 ቢሊዮን ነው።
ትምህርት ቤቶች ለረዥም ጊዜ የሚዘጉበት የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት በርካታ የጀርመንና የእስራኤል ወጣቶች የልምድ ልውውጥ መርኀ ግብር የሚያካሂዱበት ወቅት ነው ። ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ ጀርመናውያን ወጣት በጎ ፈቃደኞች በእስራኤል ማህበራዊ አግልግሎቶችን በመስጠት ላይ ናቸው
አሁን ሶስተኛው ትውልድ ላይ መድረሱ እየተነገረ ነው፤ አልቃይዳ። የመጀመሪያው ትውልድ በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ከመስከረሙ የ2001 ዓም ጥቃት በፊት የነበረውን እንቅስቃሴ ይጠቀልላል። ሁለተኛው ትውልድ ደግሞ የአልቃይዳው ዋና ሰው ቢን ላደን እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ የነበሩትን ሁነቶች ያካትታልል። ሶስተኛው ትውልድ የቢን ላደን መገደልና የአረብ
ዩኤስ አሜሪካ እና አፍሪቃ፣ «አፍሪካን ግሮውትስ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት» በምሕፃሩ «አ ጎ አ» በሚል ውል ባነቃቁት የንግድና የኤኮኖሚ ትብብር ዛሬ በአዲስ አበባ ምክክር ማካሄድ ጀመሩ።
በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገሮች ከተለያዩ መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የልማት ርዳታ ያገኛሉ። ኢትዮጵያ አፍሪቃ ዉስጥ ከፍተኛ የልማት ርዳታ ከሚያገኙ ሃገር ግንባር ቀደሟ ናት
በማሊ ዛሬ 11.08.2013 ፪ኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።
በምርጫው የሚወዳደሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ እና የቀድሞው የገንዘብ ሚንስትር ሱማይላ ሲሴ ናቸው።
የዕለቱ ዜና
በናይጀሪያ የምክር ቤት እንደራሴዎች ለአካለ መጠን ያለደረሱ ሕፃናት ሴቶች ሊዳሩ ይቸላሉ የሚለውን ሕግ ወደፊትም ሊሰራበት ይችላል ካሉ በኋላ በሀገሪቱ ሰፊ ክርክር ተነስቶዋል። ሰሞኑንም በኤኮኖሚ መናኸሪያ በሆነችው በሌጎስ ከተማ አደባባይ በመውጣት «ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት እንጂ ለሙሽራነት አልደረሱም » የሚል መፈክር አሰምተዋል።
የዩጋንዳ የተቃውሞው ወገን የአገሪቱ ፓርላማ ፤ የህዝብን የመሰብሰብ መብት የሚያርቅ አዲስ ህግ ፣ ከትናንት በስቲያ ማጽደቁን አስመልክቶ ፣ ዓለም አቀፉ ማሕበረ-ሰብ ጣልቃ ይገባ ዘንድ ተማጽኖ ለማቅረብ መዘጋጀቱ ተነገረ። በአዲሱ ህግ መሠረት፤ ማንኛውንም
ከአንድ አመት በፊት ነበር «ጋንግናም ስታይል» በገበያ ላይ የዋለው።ደቡብ ኮሪያዊው አቀንቃኝ ፕሳይ በዚህ አዝናኝ የዳንስ ቪዲዮ በአለም አቀፍ እውቅናን አገኘ። ቢንያም ዳና ደግሞ «የኛ እስታይል» ሲል ተጫውቶታል።
የዕለቱ ዜና
የኢትዮጵያ እድሜ ጠገብ ቅርሶች ላይ በተለያየ አቅጣጫ ጥፋት እየፈጸመ መሆኑን፤ በሕገ ወጥ ቅርስ አቀባዮች የሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ወደ ዉጭ እየተጋዘ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ።
1434ኛው የእድ አል ፈጥር በዓለ ዛሬ በሙሥሊም ሀገራት ተከበረ። ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የሙሥሊሙ ህብረተሰብ አባላት በአዲስ አበባ ስቴድየም የተካሄደውን የበዓሉን አከባበር ሥነ ሥርዓት ወደዚያ በመሄድ እና በዙርያው በመገኘት ተከታትለውታል።
በሳውዲ ዐረቢያ ፣ በየመን እና በዩኤስ አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙሥሊሞች ዕለቱን እንዴት እንዳከበሩት ከጄዳ፣ ከሰንዓ እና ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪሎቻችን ጋ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርገናል።
የዕለቱ ዜና