ፕሬዝዳት ኦባማ የሚተማመኑበትን እቅዳቸዉ ለማስፈፀም-የሚተማመኑበትን ዘመናይ ጦር ከምርጥ መሳሪያዎቹ ጋር አዝምተዋል።የሶሪያ የቅርብ ወዳጆች ሩሲያ፥ ቻይና እና ኢራን የድብደባዉን ዕቅድና ዘመቻ አጥብቀዉ ይቃወማሉ።የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን ከዚሕም አልፈዉ አሜሪካና የተባባሪዎችዋን አቅድ አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።

ሶሪያ ውስጥ መርዘኛ ጋዝ በመጠቀም ባለፈው ሣምንት ተካሂዶ በነበረ ጥቃት ከሶሥት መቶ የሚበልጡ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉ ወዲህ የዳማስቆስን መንግሥት ተጠያቂ በማድረግ የአየር ድብደባ ለማካሄድ በዩ ኤስ አሜሪካና በአጋሮቿ የተያዘው ዝግጅት ውጣ-ውረድ እየበዛው ነው።

የሶሪያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ፈፅሟል የተባለው የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቃት በተባበሩት መንግስታት ፈታሾች በመጣራት ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ምዕራባውያን መንግሥታት በሶሪያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር የተዘጋጁ ይመስላል ከህግ አንፃር ሲታይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ዓለም ዓቀፉን ህግ የሚጥስ እርምጃ ነው ።

በአዲሱ የትምሕርት ዘመን ላይቤሪያ ዩኒቨርስቲ ያመለከቱ 25 ሺህ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናውን መውደቃቸው የላይቤሪያ የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን እንደሚያመለክት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ሳይቀሩ አምነዋል ።

ቀሬ ቤተእስራኤላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ የትናንቱ ጉዞ የመጨረሻው እንዳይደለ ቤተ እስራኤላዊ የፓርላማ አባል ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ትንናት እስራኤል የገቡት ኢትዮጵያውያን አይሁዶች እጎአ በ2010 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የሚገኙ ቀሪ የቤተ እስራኤል ወገኖች በ 3 ዓመት ውስጥ ተጠቃለው እስራኤል እንዲገቡ በታቀደው መሠረት የተከናወነ ነው።

ይኽው መፀሀፍ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ ለቀሪው ትውልድ የሚያቆይ ታላቅ ቅርስ መሆኑን በመፀሃፉ ምረቃ ላይ ተገልጿል ። መፀሃፉ ለህትመት የበቃው ደራሲው ተስፋዮ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ በኋላ ነው ።

ፎቶ አንሽው ሚካኤል ፀጋዬ በተለያዩ አገሮች አውደ ርዕይ አሳይቷል። ከዚህ ባሻገር ፎቶዎቹ በታዋቂው ሳምንታዊ የጀርመን መፅሄት «ዴር ሽፒግል» ታትመው ወጥተዋል። ሮይተርስን እና ብሉምቤርግን የመሳሰሉ የመገናኛ ብዙኋንም በፎቶዎቹ ተጠቅመዋል።

የዕለት- ከዕለት ዓለም አቀፍ የአየር ጠባይ መዝጋቢዎች ፤በዓለም ዙሪያ ስለተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች የሙቀት መጠን መግለጽ አይሳናቸውም። ለምሳሌ ያህል፤ የኢትዮጵያ መዲና ፣ አዲስ አበባ ፤ ዛሬ ያለው የሙቀት መጠን ፣ ቢበዛ 19 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው።

ቱሪዝም በርከት ባሉ ታዳጊ ሃገራት በያመቱ በብዙ ሚሊያርድ የሚቆጠር ገንዘብ የሚያስገኝ ጠቃሚ የኤኮኖሚ ዘርፍ ነው። በሌላ በኩል ይሄው ዘርፍ ሙስናና ቀውስ የተጣባው መሆኑም ይታወቃል። ተጠቃሚዎቹ እጅግ ጥቂት በእጣት የሚቆጠሩ ናቸው።

የአሜሪካ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ታጋይ የነበሩት ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ታዋቂዉ ንግግራቸዉን ያደረጉበት 50ኛ ዓመት ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ እየተከበረ ይገኛል።

አራት መቶ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላዉያን ለዓመታት ሲያልሟት ወደነበረችዉ ምድር በዛሬዉ ዕለት ተሸንተዋል። ቀሪዎቹን ደግሞ ይህ ጉዞ የመጨረሻዉ ነዉ መባሉ እንዳሳዘናቸዉ የቤተ እስራኤላዉያን ማኅበር ገልጿል።

የግብፅ ጦር ሐይል በሐገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዝዳትን ከሥልጣን ማስወገዱ፥ መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ወገኖችን መግደል፥ ማሰሩ ብዙ ሲያነጋግር፥ሕዝባዊ አብዮት ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀጣጠለባት አምባገናናዊዉን ሥርዓት በምርጫ የተኩት የቱኒዚያ ፖለቲከኞች እርስ በርስ እየተወዛገቡባት ነዉ

ባለፈዉ ሳምንት ደማስቆ ዉስጥ ደርሷል ለተባለዉ የአደገኛ ኬሚካል መሳሪያ ጥቃት የአረብ ሊግ የሶርያ መንግስትን ተጠያቂ አደረገ። በመቶዎች የተገመቱ ሰዎችን ሕይወት ያሳለፈዉ የኬሚካል መሳሪያ ጥቃት ተጠያቂዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ድርጅቱ ጠይቋል።

የፊታችን መስከረም ለሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ ላይ ናቸው። ፓርቲዎቹ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ይረዳል ባሉት መንገድ የመራጩን ህዝብ ቀለብ ለመሳብ እየጣሩ ነው።

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም በዓለም ዙሪያ በወባ በሽታ 660 ሺ ሰዎች ማለቃቸዉን የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ ማለትም 90 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት ደግሞ አፍሪቃ ዉስጥ ነዉ። የዛሬ ሶስት ዓመት በወባ በሽታ 220 ሚሊዮን ሰዎች ተይዘዉ እንደነበር የዓለም የጤና ድርጅት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሄሊኮፕተሮቹ አገልግሎት እንዲሰጡ ለታሰበው ተግባር አመቺ እንዳልሆኑና የጥራት ደረጃቸውም ከጊዜው ጋር አብሮ የሚሄድ እንዳይደለ ዛሬ ታትሞ የወጣው ፍራንክፉርተር አልገማይነ የተባለው የጀርመን ጋዜጣ ዘግቧል ።

ሠፊዉ ዓለም የግብፅን እልቂት ፍጅት፤ የሌላዉን ዓለም አፀፋ በቅጡ ለማስተንተን እንደገና ጊዜ አልነበረዉም።ወይም የሰዉ ደም ጠጥቶ ደም የሚጠማዉ ምድር ለሌላ ጥማቱ እርካታ ሶሪያን በመርዝ ጋዝ ሲያጥናት ትልቁም፥ ትንሹም፥ ምሥራቁም ምዕራቡም ቱጃሩም፥ ሐያሉም በሶሪያ የእልቂት ዜማ ያንጎራጉር ሌላዉ ይፎክር-ይዝት ገባ።

የድርጅቱ አመራር አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሚወስዳቸው እርምጃዎች የቀይ ባህር አፋሮችን እንደሚገድል እንደሚያስርና ከቀያቸው እንዲሰደዱ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ።

የቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ፣ አምና ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ወዲህ የአገሪቱ ፖለቲካዊ ፣ ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ገጽ ምን ይመስላል?

በማዳጋስካር ከአራት ዓመት ተኩል በፊት መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ወዲህ ደሴቲቱ እከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። በሀገሪቱ ይካሄዳል የተባለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በተደጋጋሚ መተላለፉ የሚታወስ ነው።

ጠጋ ብለው ሳያውቁ፤ የቀኝ ጽንፈኛ አመለካከታቸውን ብቻ በማንጸባረቅ፤ የውጭ ተወላጆችን፣ በጭፍን የሚጠሉ ፣ የሚያጥላሉ አካራሪ ጀርመናውያን በየጊዜው ነው ተቃውሞአቸውን የሚያሰሙት።

በምርጫ ሥልጣን የያዙት መሀመድ ሙርሲ በጦር ኃይሉ ከሥልጣን ተነስተው በታሰሩ በ7 ሳምንታቸው ሙባረክ ከእስር ቤት መውጣታቸው በሙባረክ ተቃዋሚዎች ዘንድ የግብፅ ህዝባዊ ንቅናቄ የመቀልበሱ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል ።

ያኒንግ እንደሚያምኑት የአሜሪካ ጦር ሶሪያ ከዘመተ የደማስቆ መንግሥትን የምትደግፈዉ ኢራን አሜሪካኖች ነገር እንደፈለጓት ነዉ የምትቆጥረዉ።የእስራኤል ደሕንነትም ላደጋ መጋለጡ አይቀርም።«ከዚሕም በተጨማሪ» ይላሉ ያኒንግ አሜሪካኖች «ጣልቃ መግባት» መጀመሪያዉ እንጂ ፍፃሜዉ እንደማይታወቅ ካለፈዉ አስር ዓመት ልምዳቸዉ በቅጡ መማር አለባቸዉ።

በግብጹ ግጭት መንስኤ አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄዱት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባሳለፉት ውሳኔ መሰረት ሕብረቱ ለግብፅ ጦር የሚውሉ የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች ሽያጭ አግዷል ። «በሀገር ውስጥ ህዝብን ለመጨቆን የሚውል የማንኛቸውም የጦር መሣሪያዎች የውጭ ንግድ ፈቃዶች» ታግደዋል ።

ምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ታንዛንያ በተለይ በአገር ጎብኚዎች ዘንድ ፣ እንጎሮንጎሮ እና ሴሬንጌቲ በተባሉት ቦታዎች በሚገኙት የዱር እንስሳትና ዓራዊት ክልሎች ትታወቃለች። ከዛ ባለፈስ የታንዛንያን ባህል ምን ይመስላል?

የአየር ንብረት፣ ከአህጉራዊና ከክፍለ-ዓለማዊ የባህርና የአየር ለውጥ ሁኔታዎች ጋር የተሣሣሰረ በመሆኑ ፣ ተጽእኖው የቅርብም የሩቅም ሊሆን ይችላል። ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ፣ ብርቱ ዝንም ነው ሲጥል የከረመው? መንስዔው ምን ይሆን ?በአመዛኙ ወቅቱን

የጋዜጠኞችን መብት በማክበር ቻድ ከአንድ መቶ ሰባ-ዘጠኝ ሐገራት አንድ መቶ-ሃያ አንደኛ ናት።ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከሃያ ዓመት በፊት በመንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሰፊ፥ በረሐማዋን፥ አፍሪቃዊት ሐገር ሕዝብ በብረት ጡንቻ እንደደፈጠጡት ነዉ።

በደቡብ ክልል ጋሞጎፋ ዞን ቁጫ ወረዳ የማንነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ከአንድ ወር ተኩል ገደማ በፊት ታስረው ከነበሩ ከሁለት መቶ የሚበልጡ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በወቅቱ ተፈተዋል።

የዚምባብዌ የሕገ-መንግሥት ፍርድ ቤት ባለፈዉ ወር የተካሄደዉ ምርጫ የሀገሪቱን ሕግ የተከተለ ነዉ ሲል የቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ አድርጓል። ፕሬዝደንታዊዉ ምርጫ ነፃ እንዳልነበረ የሚሞግቱት ወገኖች በበኩላቸዉ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ መንበራቸዉን እንዳይለቁ መንገድ አመቻችቷል ሲሉ ተችተዋል።

ቤተ እሥራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ወደ እሥራኤል የማጓጓዙን እና የተለያዩ የቤተሰብ አባላት የማዋሀዱን ስራ ለማፋጠን በኢትዮጵያ አይሁዳውያን ስም የተቋቋሙ በርካታ ማህበራት እና ድርጅቶች አሉ።

አዲስ አበባ ዉስጥ የመለስ መታቢያ ድርጅት ያዘጋጀዉ ቤተ-መፅሐፍት ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ሲከፍት፥ በእንጦጦ እና በሌሎችም የሐገሪቱ ክፍሎች ችግኞች ተተክለዋል፤

።የግብፅ ፀጥታ አስከባሪዎች የሙስሊም ወንድማማቾች መሪ መሐመድ ባዲን አስረዋቸዋል።ማሕበሩ እስካሁን ምክትል መሪዉ የነበሩትን መሐመድ ኢሳት የመሪነቱን ሥልጣን እንዲይዙ መወሰኑን አስታዉቋል።ማሕበሩ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫዉ እንዳስታወቀዉ ጦር ሐይሉ በሚወስደዉ የማሠርና የሐይል እርምጃም ትግሉ አይቋረጥም

ኢትዮጵያ ዉስጥ በHIV ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱ እየተነገረ ነዉ። በአንጻሩ የጸረ ኤድስ መድሃኒት የሚወስዱ HIV በደማቸዉ የሚገኝ ወገኖች ቁጥር መቀነሱ ተገልጿል። መድሃኒቱ ከተጀመረ መቋረጥ እንደማይኖርበት ነዉ ባለሙያዎች የሚያሳስቡት።

ጀርመን ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራት በግንባር ቀደምትነት በዚህ ዓመት 5 ሺህ የሶሪያ ስደተኞችን ለመውሰድ ቃል ገብታለች ። በጀርመን ፌደራል መንግሥት የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ኦለ ሽሮደር እንደተናገሩት ጀርመን ከለላ የምትሰጠው ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሶሪያውያን ብቻ ነው ።