በኢትዮጵያ ፣ መስከረም ወር ፣ክረምት አልፎ ከባድ ደመና የሚገፍበት ሰማዩ የሚጠራበት ፤ ምድሪቱ በለምለም ሳርና በተፈጥሮ አበባ አጊጣ የምትታይበት ወቅት፣ ጥቢ ሲሆን ፣ በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች ደግሞ ብርቱ ዝናም የሚያጋጥምበት ፣ ማዕበልም

በሶማሊያ የተወለዱት የሴቶች ተሟጋች እና ሞዴል ዋሪስ ዲሪ ባለፈው ረቡዕ የሴት ልጅ ግርዛት ሰለባ የሆኑ የሚረዱበት «ዴዘርት ፍላወር ሴንተር» የተባለ ማዕከል በርሊን ውስጥ መርቀው ከፍተዋል።

የተመድ ዋና ፀሃፊ ባን ጊሙን በሶርያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በኬሚካላዊ መሳርያ ማለቃቸዉን በጥብቅ አወገዙ። ዋና ጸሃፊ ባን ይህን የገለጹት በሶርያዉ የእርስ በርዕርስ ጦርነት ጅምላ ጨራሽ መሳርያ ለጥቃት ጥቅም ላይ ዋለ ከተባለ በኋላ፤

የሶማሊያ መንግሥትን ለማጠናከር እና ሰላምን ለማረጋገጥ ፣ልማትን ለማስፋፋት በሚያስችል አዲስ ዕቅድ ላይ የተወያየ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ትናንት በብራስልስ ተካሂዷል።

እንደገና የተደላደለ መንግሥት ማቋቋም ይቻላት ዘንድ 22 ዓመታት የተለያየ እርዳታ ሲደረግላት የቆየችው ሶማልያ አሁንም ከዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችና መንግሥታት ቻንቃ አልወረደችም።

በርግጥም በመሪዎቹ ሽኮቻ፣ በወጥ፣ ራዕይ ጉድለት፣ በመርሕ እጠት ከትንሽነት ወደ ምንምነት ያሽቆለለ ትንሽ ፓርቲያቸዉን ለመንግሥት ሥልጣን ተጋሪነት፤ አብቅተዋል።በዚሕ ይወደሳሉ።የምክትል መራሔ መንግሥትነቱን መንበርም፥ ከትቢያ ያነሱትን ፓርቲያቸዉን የሊቀመንበርነት ሥልጣንም እንዲለቁ ያስገደዷቸዉ ግን የራሳቸዉ ፓርቲ የቅርብ ጓዶቻቸዉ ናቸዉ

3 የተቃውሞ ፓርቲዎች፤ በተለያዩ ጊዜያት ሊያደርጓቸው የነበሩ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች፤ በመንግሥት በኩል መደናቀፋቸውን ገልጸው፤

በነጻ የመጻፍና የመናገር ዋጋው ምን ይመስላል? በሚል ርእስ፣በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ይዞታ ላይ ያተኮረ ዐውደ ጥናት(ሴሚናር)መስከረም 4 ቀን 2006 ዓ ም፤ በእስዊድን መዲና በእስቶክሆልም ተካሂዷል።

2006 ካባተ ፣ ዛሬ 5ኛ ቀኑ ነው። ታዲያ ስላለፈ ዓመት ስንብትና ስለአዲስ ተስፋ በመነገር ላይ ባለበት ሰሞን፣ በእንወያይ ሳምንታዊ ዝግጅታችን፣ዛሬ ሌላ ርዕስ አይደለም የመረጥን።

መሃመድ ኡመር እንደሚለው በአልሸባብ መካከል ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ክፍፍል ተፈጥረዋል በክፍፍሉ ሳቢያ የጥቃት ኢላማ ከሆኑት መካከል አል አሜሪኪ ኣንዱ ሲሆኑ በጥቃቱ የኣህመድ መዶቤ እጅ እንዳለበት ግን በስፋት ይነገራል። አህመድ መዶቤ ከሶማሊ ላንድ እንዲያውም መሐመድ ኦመር እንደሚለው የኢትዮፕያ አካል ከሆነው የኦጋዴን አካባቢ የወጡ ናቸዉ።

ብዙ ሰዎች የሚቀጥለው ዓመት፣ ወይንም በአዲስ ዓመት ይህን አደርጋለሁ በማለት እቅድ ያወጣሉ። ተግባሩን ለመፈፀምም በተለይ በመጀመሪያዎቹ ወራት በትጋት ይንቀሳቀሳሉ። እኛም በዛሬው የወጣቶች ዓለም « የአዲስ ዓመቱ እቅዴ እና እንዴት እውን እንደማደርገው» በሚል ርዕስ ዝግጅት ይዘናል።

ዛሬ ለንደን ብሪታንያ ምክር ቤት ፊትለፊት የተሠለፉት የኦሮሞ ተወላጆች እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነዉ።የብሪታንያ መንግሥት ሠልፈኞቹ «ዜጎቹን ይበድላል» ላሉት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሠጠዉን ድጋፍ እንዲያቆም ሠልፈኞቹ ጠይቀዋል

ጀርመናዊ ሔር ቶማስ ባህ፣ ከሰሞኑ ቦይነስ አይረስ ፤ አርጀንቲና ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ፤ የዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ይሆኑ ዘንድ መመረጣቸው የሚታወስ ነው። እነህ የአስፖርት ባለሥልጣን በሙያቸውና ችሎታቸው፤ በብዙ ሰዎች ዘንድ አድናቆትን

ኢትዮጵያን በጋራ ችቦ አቀጣጥለን አሮጌዉን ዓመት ሸኝተን እንቁጣጣሽ ብለን በአበባ የሆሽ 2006ዓ.ምን በብሩኅ ተስፋ ተቀብለናል! እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገራችሁ

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዑሑሩ ኬንያታ ምክትል ፣ ዊልያም ሩቶና አብሮአቸው የተከሰሰው ጋዜጠኛ ጆሽዋ ሳንግ፤ ፣ በዛሬው ዕለት ደን ኻኽ ውስጥ ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው በሰጡት ቃል፤ በሰብአዊነት ላይ የፈጸምነው ወንጀል

ኢትዮጵያዊት ጉዲፈቻ ልጃቸዉን አሰቃይተዉ ገድለዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸዉ አሜሪካዉያን ባልና ሚስቶች በተያዘባቸዉ ወንጀል ጭብጥ የጥፋተኝነት ብይን ተወሰነባቸዉ። ለማደጎ ከኢትዮጵያ ለወሰድዋት ህጻን ሐና ዊሊያምስ በ13 ዓመትዋ ህይወትዋ እንዲያልፍ በማድረግ ጥፋተኞች ናቸዉ ሲል የወሰነዉ አንድ የአሜሪካ ፍርድ ቤት ነዉ።

( የልጅነት ልምሻ) ፖልዮ ከምስራቅ አፍሪቃ አገሮች መጥፋቱ ሲነገር ቢቆይም ሰሞኑን የወጣው ዜና እንደሚያመላክተው ሶማሊያና ኬንያ ውስጥ መከሰቱ ተሰምቷል።

የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ፣ በ 2000 ዓ ም፤ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት በቆረጠው ቀጠሮ ዛሪ ደን ኻኽ ኔደርላንድ በሚገኝበት ፍርድ ቤት ቀረቡ። በኬንያ 2000 ዓ ም በነበረዉ ምርጫ ማግሥት ለሳምንታት በተካሄደው የጎሣዎች ግጭት

የመለስ ዜናዊ አስተሳሰብና ምግባር ሕዝብን በተለይም ፖለቲከኞችን በተራራቀ ተቃራኒ ጫፍ እንዳቆሙ መሞታቸዉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበጎ ወይም በመጥፎ፥ ወይም በሁለቱም መሐል-ክፉኛ መንካቱ እንደማይቀር ያኔ ተብሎ ነበር።አሁንም አልቀረም።

ነሃሴ ወር አጋማሽ ሶርያ መንግስት በመርዘኛ ጋዝ ተጠቅሞአል ለተባለበት ወንጀል፤ ምዕራባዉያን አሳድ ላይ የአየር ጥቃት ለማካሄድ እቅዳቸዉ ላይ በሁለት ወገን የተከፈሉ ይመስላል። ሶርያ መንግስት በበኩሉ የኬሚካዊ መሳርያ ጥቃትን እንዳልፈጸመ እየገለፀ ነዉ።

ብራዚል ውስጥ ለሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የአፍሪቃ እና የአውሮፓ አገሮች ማጣሪያ ውድድር፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሲካሄዱ ቆይተዋል።

ብዙ ወጣቶች ያልደፈሩትን ሥራ በተሰጥዎ እንደሚሰራ ይናገራል። ፋንቱ ያኖ። የ20 ዓመት ወጣት ነው። ከታናሽ ወንድሙ ጋ በአዲስ አበባ፤ ቂርቆስ አካባቢ ይኖራል። በሬ ማረድ ከጀመርኩ 3 ዓመት ሆነኝ ይላል።

አንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ «የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት» በሚል ርእስ ለፊታችን መስከረም አምስት ቀን ለሚጠራው ህዝባዊ ስብሰባ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።

በ ተ መ ድ ጣልቃ ገብ ጦር በሚደገፈው የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ መንግስት እና በሩዋንዳ እንደሚደገፉ በሚነገርላቸው የ M 23 አማጺያን መካከል አፋጣኝ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ተጠየቀ።

የዊኪሊክስ መስራች ጁልያን አሳንጅ፣ ለንደን በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ ጥገኝነት ከጠየቀ በኋላ ስለ ዊኪሊክስ ብዙ መባሉ ቀንሶ ነበር።

በየዓመቱ ከ 11 በመቶ በላይ ዕድገት እያስመዘገብኩ ነው የሚለው የኢትዮጵያ መንግሥት የኃይል ፍላጎቱን ለማሙዋላት በስፋት ከተያያዛቸው ፕሮጀክቶች መካከል ኣንዱ የጊቤ ወንዝን ተከትለው የሚገነቡት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ

ሶስት ሳምንት ግድም የቀረዉ የፌደራል ጀርመን ምርጫ የአገሪቱን ፖለቲከኞች፤ በየመድረኩ እያፎካከረ እና እያተቻቸ ፤የቃላት ጦርነቱ እየተጋጋለ፤ ህዝቡ የምርጫዉን ቀን በመጠባበቅ ላይ ነዉ።

የቡድን 20 ሃገራት የ 2 ቀናት ጉባዔ፣ ዛሬ በሴንት ፒተርስበርግ ፣ ሩሲያ ተጀምሯል። ጉባዔው፤ በዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና በተለይም ባለፉት 5 ዓመታት ፣

ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ እና ከፍተኛ ባለስጣኖቻቸዉ የአሜሪካ ምክር ቤት ለፕሬዝደንቱ ሶርያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት የመፈጸም መብት እንዲሰጣቸዉ ጥያቄ ማቅረባቸዉን ቀጥለዋል።

በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዉያን ባለፉት ሠላሣ ዓመታት እስራኤል ገብተዋል። ይሁንና ቤተ እሥራኤላውያኑን ከሀገሪቱ ኅብረተሰብ ጋ የማዋሀዱ ተግባር ዛሬም ትልቅ እክል ይታይበታል።

የኬንያ ባለስልጣናት በዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት (ICC) ክሳቸው ሊታይ ጥቂት ሳምንታት ሲቀረው፤ የሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኬንያ የICC መቋቋሚያ ዉል ፈራሚነቷን ታነሳ ዘንድ ትናንት ሲከራከር ውሏል።

ሰዎች ካለፈ እጅግ መጥፎ ድርጊት ፣ እስከምን ድረስ ትምህርት ይቀስማሉ? በተለያዩ ዘመናት ያጋጠሙ ሁኔታዎችን ፤ ጦርነቶችን ፤ ወረራዎችን ፤ ውዝግቦችን ስንመረምር ፣ ሰው፤ ጭካኔ የሚያሳይባቸው መሣሪያዎች በሥነ ቴክኑኒክ ተሻሽለው ተሠርተው ከመቅረባቸው

የግብጽ የጦር ፍርድ ቤት በ52 የሙስሊም ወንድማማቾች አባላትና ደጋፊዎች ላይ ከአምስት ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራትን በየነ። ከተከሰሱት መካከል አንዱ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

በተከታታይ የሚፅፉና አስተያየት የሚሠጡት አፍሪቃዉያን ምሁራን እንደሚሉት የቀድሞ አዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎች ተመልሰዉ አፍሪቃን ቢገዙ የአሕጉሪቱን ሕዝብ በራሱ ወገኖች አሁን ከሚያየዉ ስቃይ ይገላግሉታል

UNAIDS በመድሃኒት ስርጭትና ቁጥጥር ረገድ ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገሮች ጋ ስትነፃፀር በተሻለ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የገለጸዉ በያዝነዉ ዓመት ግንቦት ወር ነዉ። እንደድርጅቱ ዘገባም በቫይረሱ አዲስ ከሚያዙት ይልቅ መድሃኒት የሚወስዱ ወገኖች ቁጥርም ከፍ ማለቱን ያመለክታል።

ከየክልሉ የተውጣጡ የአስተዳደር አባላት እና የሃይማኖት ተጠሪዎች ባለፈው ሳምንት ከማክሰኞ እስከ ኀሙስ በአፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ተገኝተው ሀገር አቀፍ ጉባኤ ማካሄዳቸው ይታወሳል።