በሶማልያ የቀጠለው ውጊያ
የአክራሪው የአል ሸባብ ሚሊሺያዎች በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ውስጥ በጣሉት ጥቃት ከሰላሳ የሚበልጥ ሰው ተገደለ።
የአክራሪው የአል ሸባብ ሚሊሺያዎች በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ውስጥ በጣሉት ጥቃት ከሰላሳ የሚበልጥ ሰው ተገደለ።
ጀርመን በበርሊን ባዘጋጀችው እና ትናንት በተካሄደው ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ የስቴድየም ውድድር በሶስት ሺህ እና በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር ሩጫ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ታሪኩ በቀለ እና መኮንን ገብረ መድህን አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል። ኬንያዊው ዴቪድ ሩዲሻም አስራ ሶስት …
አራት ሺሕ አራት መቶ አስራ-ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች ሕይወታቸዉን ለኢራቅ በረሐ ገብረዋል።ከሠላሳ-እስከ አርባ ሺሕ የሚገመቱ ቆስለዋል።ሌሎች የአዕምሮ በሽተኛ ሆነዋል።
የኤኮኖሚክስ እና የአካውንቲንግ ምሁራን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ባቀረቡት የአምስት ዓመት የኤኮኖሚ መርሀ ግብር ሳይንሳዊ የኤኮኖሚ ግብዓቶች ላይ ያልተመሰረተ መሆኑን አመለከቱ። ምሁራኑ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ጠቅላይ ሚንስትሩ ባቀረቡት መንገድ ሊያድግ የሚችልበት የተመቻቸ ተጨባጭ ሁኔታ አለመኖሩን ገልጸዋል። ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ።
የተመድ ከአስር ዓመታት በፊት ባስቀመጠው የአምአቱ የልማት ግብ በዋነኝነት የድሆቹን ሀገሮች የጤና፣ የትምህርት ሁኔታን ለማሻሻል እና ድህነትን ለመቀነስ አቅዷል። የተመድ ከአስር ዓመታት በፊት ባወጣው የአምአቱ የልማት ግብ መሰረት በድሆቹ የዓለም ሀገሮች ውስጥ የሚታየውን የህጻናት ሞት እስከሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በጉልህ የመቀነስ …
አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አል-ሸባብ «የደነበሸ» ያለዉን የርዳታ እሕል እሰበሰበ ማቃጠሉን አስታወቀ።ቡድኑ ከርዕሠ-ከተማ መቃዲሾ ሰብስቦ ያቃጠለዉ አምስት መቶ ከረጢት እሕል የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት (WFP) ያከፋፈለዉ በቆሎና ስንዴ ነበር።የአል-ሸባብ የሞቃዲሹ አገረ-ገዢ ሼኽ አሊ መሐመድ ሑሴይን እንዳስታወቁት እሕሉ ለምግብ የሚዉልበት ጊዜ …
በአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት መካከል ከዚህ ቀደም የተነሳው ውዝግብ ፍርድ ቤት እያሟገተ ነው። ዛሬ ያስቻለው የአዲሰ አባባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፓርቲውን ጽህፈት ቤት ንብረት በኃይል ለመውሰድ ሞክረው ነበር ተብለው በተከሰሱ አባላት ላይ የተሰጠውን ምስክርነት አዳምጧል። ዘገባውን ለማዳመጥ እዚህ …
ከሰባት ዓመት በላይ ኢራቅ ከቆዩት የአሜሪካ ተዋጊ ጦር ኃይል አባላት የመጨረሻዎቹ ትናንት ኢራቅን ለቀው ወጥተዋል ። የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢራቅ ጦርነት ማብቃቱን ትናንት በይፋ አስታውቋል ። በርካታ ኢራቃውያን የአሜሪካን ጦር ሀገራቸውን ለቆ በመውጣቱ የተቀላቀለ ስሜት ነው ያደረባቸው ። …
ለኢትዮጵያ አማራጭ የመረጃ አግልግሎት ለመስጠት የተቋቋመውና ከኔደርላንድ የሚያሠራጨው ESAT በሚል ምኅጻር የታወቀው የኢትዮጵያ የሳቴላይት ቴሌቭዥን አገልግሎት ሥራውን ከጀመረ 4ኛ ወሩን ቢይዝም በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ፤ ለ 3ኛ ጊዜ ተቋርጧል። ይሁንና ከመጪው ሳምንት ጀምሮ እንደገና በተጠናከተረ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ፤ …
በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራቻን፤ ባለፈው ሳምንት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለማስፋፋት ፤ የመምህራንና በኢንተርኔት የሚቀርቡ የምርምር ጽሑፎች ድርሻ ፤
የቀድሞዉ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለገሰ ቢራቱ እንደሚሉት በምክር ቤት ዉስጥ ሰወስት መቀመጫዎች ብቻ ያለዉ ቅንጅት ከምርጫ ቦርድ የተቀበለዉ አርባ የምክር ቤት መቀመጫዎች ያሉት በማስመል ነዉ የኢትዮጵያ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ባለፈዉ ግንቦት ለተደረገዉ ምርጫ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የወሰደዉ የገንዘብ ድጎማ …
አስራ አራቱ የደቡባዊ አፍሪቃ መንግስታት የልማት ድርጅት፡ በምህጻሩ ሳዴክ አባል ሀገሮች ርዕሳነ ቤር እና መራህያነ መንግስት በናሚቢያ መዲና ዊንድሁክ ያካሄዱትን የሁለት ቀናት ጉባዔ ትናንት ማምሻቸውን አጠናቀቁ።
የቡሻሒሩ ማምንጫ ጣቢያ ግንባታ መጠናቀቁ እንደተሰማ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣን እስራኤል የኑክ’ሌር ጣቢያዉን በቦምብ ትመታዋለች በማለት አስፈራርተዋል።
የዜና አውታሮች ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ እንደዘገቡት፤ ዓርብ፣ ከቀትር በኋላ፤ በግብጽና እሥራኤል ድንበር ላይ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ፣ ሰዎችን ካገር -አገር በሚያሻግሩ ቡድኖችና በፈላስያን መካከል ፣ ተካሄደ በተባለ የተኩስ ልውውጥ 4 ኤርትራውያን ተገድለዋል።
የአውሮፓ መንግስታት ፣ ከዓለም የገንዘብ ቀውስ ጋር ተያይዞ ያጋጠማቸውን የብድር ጫና ለማቃለል ልዩ ልዩ የቁጠባ ዕርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ናቸው ።
ወደ አሜሪካ የመግብያ መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሆኑ ሀገራት ዜጎች 14 ዶላር እንዲከፍሉ ሊደረግ ነው። አዲሱ አሰራር ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ገቢራዊ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ፡ ከግንቦት ሰባት ጋ ጭምር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት ማስታወቃቸው ይታወሳል።
የአውሮጳ ህብረት ለፓኪስታን የጎርፍ አደጋ ሰለባዎች እስካሁን በቂ ርዳታ አላቀረበው ተብሎ እየተወቀሰ ነው።
20 ከመቶ የኤኮኖሚ ዕድገት ። ለአውሮፓውያን ይህ ህልም ብቻ ነው። አፍሪቃ ውስጥ ግን በተለይ ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በገፍ ትቸበችብ በነበረችው በአንጎላ ይህ ከጥቂት ዓመታት በፊት ህልም ሳይሆን ተጨባጭ ሀቅ እንደነበረ የሚካድ አይደለም ።
በመላው ዓለም የሚኖሩ ኤርትራውያን በአንድነት በመተባበር በኤርትራ ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲታገሉ ተጠየቀ ።
ኢትዮዽያ በስዊድን ያለውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን ጠቃላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከትላንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኤምባሲው ተልዕኮውን ሊወጣ ባለመቻሉ መዘጋቱንና ከዚያ ይልቅ በብራዚል መክፈት እንደሚሻል ገልጸዋል። የሲውዲን መንግስት ይህ የኢትዮዽያ መብት ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል። …
የኤርትራ ተቃዋሚዎች ጥምረት አዲስ አበባ ላይ የስደት መንግስት ማቋቋማቸው በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተሰምቷል።
አሜሪካውያን በእስልምና ሃይማኖት ላይ ያላቸው አሉታዊ አመለካከት እየሰፋ መጥቷል።
ዋና መሥሪያ ቤቱ ካሊፎርኒያ ዩናይትድ እስቴትስ የሚገኘው፤ ጉግል በመባል የታወቀው በኢንተርኔት የመረጃዎች አቅራቢ ማሺን፣
ጥንታዊው የሰው ዘር ይገለገልባቸው የነበሩ የድንጋይ መሳሪያዎች ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በሚመጡት 5 ዓመታት አከናውነዋለሁ በሚል ያወጣው ምጣኔ-ሀብታዊ አቅድ በጣም የተጋነነ መሆኑን ሐያስያን ቢገልጹም፣
የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን ኢትዮዽያና አሜሪካ የሚገኙትን ሁለቱን ሲኖዶሶች ለማስታረቅ የተደረገው ሽምግልና ገና ሳይካሄድ ቅድመ ሁኔታ ቀርቦበት ተሰናክሏል።
ድህነትን በአመዛኙ ለመቅረፍ፣ የሀገር ሁለንተናዊ ግንባታን ለማስፋፋት ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ዋናው አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑ ይታመንበታል።
ቀጣዩ የኤኮኖሚ ዝግጅት ፤
የሰሞኑ የሰፈጥሮ አደጋዎች በተለያዩ የዓለማችን ክፍል ጉዳት እያደረሱ ነዉ።
ከዛሬ ሁለት ዓመተ በፊት የዓለምን ቀልብ በእጅጉ በሳበው የዓለም የገንዘብ ቀውስ ሰበብ በአውሮፓ የህዝብ ቁጥር መናመንና የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት እንደ በፊቱ ትኩረት ሊሰጠው አልቻለም ።
በሳዉዲ ዐረቢያ በጄዳ ከተማ ካለመጠለያ እና ካለምግብ፡ ወደአገራቸዉ የሚመለሱበትን ዕለት በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ችግር አሁንም መፍትሄ ባላገኘበት ድርጊት ስቃያቸው እየከፋ ሄደ።
የእናቶች ጤና ለመጠበቅ፤ እንዲሁም በወሊድ ወቅት የሚቀጠፈዉን ነፍሳቸዉን ለመታደግ የታቀደዉ የተመድ የአምዓቱ የልማት ግብ መሳካቱ እያሳሰበ ነዉ።
የአሜሪካን መንግስት በግዛቱ እየኖሩ ሶማሊያ ዉስጥ አልሸባብ የተሰኘዉን ቡድን ለመደገፍ ተባብረዋል ባላቸዉ 14 ሶማሌያዉያን ላይ ክስ መሰረተ።
በዓለም በአልማዝ ማዕድን ሀብት ቀዳሚውን ስፍራ ከሚይዙት ሀገራት አንዷ ሴራልዮን ናት ። የሴራልዮን የአልማዝ ሀብት ሲነሳም ለዜጎቿ መተላለቂያ መሣሪያነት መዋሉ ሳይጠቀስ አይታለፍም ።
በዓለም ዙሪያ ፣ ሳምንቱን በተከናወኑ የተለያዩ የእስፖርት ውድድሮች ላይ ያተኮረው
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በእንግሊዘኛው ምህፃር UNHCR የሶማሊያ ስደተኞች ከሳውዲ አረቢያ በጅምላ በግዳጅ ወደ ሶማሊያ መባረራቸውን ለማስቆም የሚረዳ የመፍትሄ ሀሳብ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ማቅረቡን አስታወቀ ።
በአፋር አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል አለመኖር ኑሯቸዉን እንዳናጋ የአካባቢዉ ኗሪዎች ይናገራሉ።
ኬንያ አዲሱን ረቂቅ ህገ መንግስት በከፍተኛ ድምፅ መቀበሏን የሚያመላክቱ ዜናዎች እየወጡ ነዉ።
በኬንያ፣ ናኩሩ ከተማ አቅራቢያ እንጆሮ ውስጥ በሚገኘው ኤገርተን ዩኒቨርስቲ ጠቃሚ ንግግር የሚያሰሙና ተማራማሪ፤ ናቸው።
ዩኤስ አሜሪካና አፍሪቃ «አፍሪካን ጎውዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት» በአሕጽሮት «አጎዋ» በሚል ውል የንግድና የኤኮኖሚ ትብብር እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ጉዳይ ነው።
ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አፍሪቃ ወጣቶችን፤ የአፍሪቃን አምባገነን መሪዎች በመቃወም ለመሠረታዊ ለዉጥ እንዲጥሩ ጥሪ አቀረቡ።
በሀዋሳ 10 ሺህ ኩንታል የእርዳታ እህል በመጋዘናቸው የተገኘባቸው ፋብሪካዎች ታሸጉ
ኢትዮጵያ፤ ሱዳን፤ ኬንያና ዑጋንዳ ከልጅነት ልምሻ በሽታ ነፃ መሆናቸዉን የዓለም የጤና ድርጅት አመለከተ።
በጀርመን መንግስት በተሰጠ የ1ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮዽያ የሰለጠኑ 1ሺህ ያህል ፖሊሶች ደብዛቸው ጠፋ።
ባለፈው ቅዳሜ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኮልፌ በሚባለው አካባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከተገለፀው ከፍ ሊል እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ።
የርዋንዳ ህዝብ እአአ የፊታችን ነሀሴ ዘጠኝ 2010 ዓም አዲስ ፕሬዚደንት ይመርጣል።
የተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ጉባዔ እ ጎ አ በ 1948 ዓ ም፣ ያኔ በነበሩት 58 አባል አገሮች አጠቃላዩን ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት፤ የፖለቲካን የኤኮኖሚን፤
ትምህርት ለአፍሪቃ እድገት ቁልፍ ሚና አለው። በማዳመጥ መማር የተሰኘዉ የዶቼ ቬለ መረሃ ግብር በመገናኛ ብዙሃን የርቀት ትምህርት በሁሉም የአህጉሪቱ ክፍሎች እውቀትን ለማዳረስ በጥረት ላይ ይገኛል።
በአዉሮጻ የኢትዮጽያ የስፖርት ዉድድር እና የባህል ፊስቲቫል ትናንት በኔዘርላንድ አምስተርዳም ከተማ ላይ በደማቅ ሁኔታ መጀመሩ ተመልክቶአል።