ኢትዮጵያውያን በበርሊኑ አትሌቲክስ ውድድር
ጀርመን በበርሊን ባዘጋጀችው እና ትናንት በተካሄደው ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ የስቴድየም ውድድር በሶስት ሺህ እና በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር ሩጫ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ታሪኩ በቀለ እና መኮንን ገብረ መድህን አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል። ኬንያዊው ዴቪድ ሩዲሻም አስራ ሶስት ዓመት ሙሉ በቀድሞው የዴንማርክ አትሌት ዊልሰን ኪፕኬቴር ተይዞ የቆየውን የስምንት መቶ ሜትሩን ሩጫ ክብረ ወሰን ሰብሮዋል። በአንድ መቶ ፡ በሁለት መቶ እና በአራት መቶ ሜትር ሩጫም አሜሪካውያኑ፡ ጃማይካናውያኑ፡ ካናዳውያኑ እና እንግሊዛውያኑ ድል ተቀዳጅተዋል። ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ።