ሞቃዲሾ-አልሸባብ «የተበላሸ» እህል ቀበረ
አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አል-ሸባብ «የደነበሸ» ያለዉን የርዳታ እሕል እሰበሰበ ማቃጠሉን አስታወቀ።ቡድኑ ከርዕሠ-ከተማ መቃዲሾ ሰብስቦ ያቃጠለዉ አምስት መቶ ከረጢት እሕል የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት (WFP) ያከፋፈለዉ በቆሎና ስንዴ ነበር።የአል-ሸባብ የሞቃዲሹ አገረ-ገዢ ሼኽ አሊ መሐመድ ሑሴይን እንዳስታወቁት እሕሉ ለምግብ የሚዉልበት ጊዜ ሥላለፈበት ሰዎች ቢመገቡት ለበሽታ ይዳርግ ነበር።ባለሥልጣኑ ሕዝቡ ወደፊትም አለም አቀፉ ድርጅት የሚያከፋፍለዉን እሕል እንዳይመገብ ለሌሎችም አሳልፎ እንዳስሰጥና እንዳይሸጥ አስጠንቅቀዋል። በናይሮቢ የአለም ምግብ ድርጅት ቃል አቀባይ ፔተር ሰመርዶን እንደሚሉት ግን ድርጅታቸዉ መመገቢያዉ ጊዜ ያለፈ እሕል ለሕዝብ አያከፋፍልም።ቃል አቀባዩ አክለዉ እንዳሉት አል-ሸባብ ያቃጠለዉ እሕልም ድርጅታቸዉ ያከፋፈለዉ አይሆንም።
ለማዳምጥ አዚህ ይጫኑ [podcast]http://dw-world-od.streamfarm.net/Events/podcasts/amh/4347_podcast_amh_nachrichten/011f5125-podcast-4347-5932132.mp3[/podcast]