ኢትዮጵያና ስዊድን
ኢትዮዽያ በስዊድን ያለውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን ጠቃላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከትላንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኤምባሲው ተልዕኮውን ሊወጣ ባለመቻሉ መዘጋቱንና ከዚያ ይልቅ በብራዚል መክፈት እንደሚሻል ገልጸዋል። የሲውዲን መንግስት ይህ የኢትዮዽያ መብት ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል። በሲውዲን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አንድሬ ዮርሌ ለዶቸ ቬሌ እንደገለጹት ኢትዮዽያ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችበትን ምክንያት እንደማያውቁ ሀገራቸው በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የምትሰጥበት ምክንያት አንደሌላት ተናግረዋል። ኢትዮዽያ ይህን እርምጃ ብትወስድም ሲውዲን በአዲ አበባ ያለውን ኤምባሲዋን እንደማትዘጋው ኃላፊው አንድሬ ዮርሌ ገልጸዋል። ሙሉ ዘገባውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ።