የሶማሊያ ስደተኞች ከሳውዲ አረቢያ በግዳጅ መባረር

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በእንግሊዘኛው ምህፃር UNHCR የሶማሊያ ስደተኞች ከሳውዲ አረቢያ በጅምላ በግዳጅ ወደ ሶማሊያ መባረራቸውን ለማስቆም የሚረዳ የመፍትሄ ሀሳብ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ማቅረቡን አስታወቀ ።