ሰላማዊ ሰልፉ ተጀመረ!! ፎቶዎች ይመልከቱ
ሰላማዊ ሰልፉ ተጀመረ በመኪኖች ላይ በተገጠሙ ማይክራፎኖች አማካኝነት አዘጋጆቹ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ይገኛሉ
ሰላማዊ ሰልፉ ተጀመረ በመኪኖች ላይ በተገጠሙ ማይክራፎኖች አማካኝነት አዘጋጆቹ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ይገኛሉ
የአዲስ አበባ እና ጊዶሌ ሰልፍ – LIVE UPDATE ለመከታተል እዚህ ይጫኑ !
ጤና ይስጥልኝ ሃብታሙ አያሌው እባላለሁ። የአንድነት ለዲምክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙንተ ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ነኝ። የሚሊዮን ድምጽ ንቅናቄ በአንድነት ፖርቲ ቢጀመርም ንቅናቄው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ነው። የዴሞክራሲ፣ የስላም፥ የፍትህ፣ የነጻነትነ የአገር አንድነት ጥያቄ የአንድነት ፓርቲ ብቻ ሳይሆነ የእያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው። በአገራችን ኢትዮጵያ የመጻፍና የመናገር ነጻነት፣ የሃይማኖት ነጻነት፣ የመሬት […]
አንድነት በኦሮሚያ ክልልና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የመንግስት ሐይሎች በወሰዱት እርምጃ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰው ህይወት በመቀጠፉና ብዙዎችም ለአካል ጉዳት በመዳረጋቸው የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት መወያየት የግድ መሆኑን አስምሮበታል፡፡ በተማሪዎችና በተለይም በአምቦ ከተማ ህዝብ ላይ የተፈጸመው የመብት ጥሰት ምን ያህል መሆኑን ለማወቅ በቀጣዩ ሳምንት አንድነት የራሱን ልዑክ ወደ […]
በካዛንቺስ አካባቢ የቅስቀሳ ስራ ይሰሩ የነበሩ አባላት የሚሰሩትን ለመዘገብ ከቀስቃሽ ቡድኑ ጋር የነበረው የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ሐይሉ በታሰረበት የስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ከተያዘበትና በፍርድ ቤት ከቀረበበት ክስ ጋር በማይገናኝ ጉዳይ ሲቪል በለበሱ ደህንነቶች ምርመራ እንደተደረገበት ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ለሰጠው ሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ስራ ለመስራት ወደ አራት ኪሎና ካዛንቺስ አቅንተው የነበሩት […]
አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ የዕሪታ ቀን በሚል መሪ ቃል አንድነት ነገ ለሚያከናውነው ሰላማዊ ሰልፍ በጽህፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ በመውጣት በሰልፉ እሪታውን እንዲያሰማ ጠይቋል፡፡የመግለጫውን ሙሉ ቃል ያንብቡ፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) እሁድ የሚካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ የአዲስ አበባና አካባቢዋ ኗሪዎች […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የመሬት ጥያቄ ብዙ መስዋዕት የተከፈለበት ቢሆንም አሁን በባሰ ሁኔታ ወያኔ ከሁሉም ዜጋ ነጥቆ በግሉ አድርጎታል። ማንም ኢትዮጵያዊ የሃገሩ፣ የመሬቱ ባለቤት አይደለም። ከዚህ የባሰ ዜጎችን የማዋረድ ተግባር የለም። አባቶቻችን መሬታቸውን ለባዕድ አንሰጥም በማለት ህይወታቸውን ከፍለው አቆይተውናል። ዛሬ እኛ የራሳችን መሬት ባለቤት እንዳንሆን ሁላችንንም መሬት አልባ ያደረገን ስርዓት ዜጎችን አፈናቅሎ ካድሬዎቹን በመሬት ችብቸባ አሰማርቷል። ለባዕዳን ከመሸጥ አልፎ […]
ጤና ይስጥልኝ! ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን! ተክሌ በቀለ እባላለሁ፡፡ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ነኝ፡፡ የአንድነት የፖለቲካ አላማ ብዝሃነቷ የተጠበቀ፣ የግለሰብና የቡድን መብቶች የተከበሩባት፣ የበለጸገች፤ የአለምን ስልጣኔ እና እድገት የተቀላቀለች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነዉ፡፡ ለዚህ አላማ መሳካትም የምንከተለዉ ስልት ፍፁም ሰላማዊና ህጋዊነትን የተላባሰ አካሄድ ነዉ፡፡ በእዉቀት እና ጥበብ ላይ የተመሰረተ አማራጭ […]
ሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ለሚደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳው ዛሬም በደመቀ ሁኔታ መካሄዱን ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል። ትላንት የተደረጉ የመኪና ቅስቀሳዎች ወቅት መኪናዎችን እየተከታተሉ፣ በርካታ ሰዎች በመሰብሰባቸው፣ ቅስቀሳዎቹ በራሳቸው እንደ ሰልፍ የነበሩበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን፣ ይህ በሕዝቡ ዘንድ ያለው መነሳሳት ያላስደሰታቸው ገዢዎች፣ ሕግ መንግስቱን በመናድ ፣ በመኪና መቀስቀስ አትችሉም በሚል፣ ትላንት ማምሻዉን መኪናዎችን ወደ ማገትና […]
አንድነት በደራሼ ወረዳ በጊዶሌ ከተማ ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና አማግኘቱን ለማረጋገጥ ችለናል።፡ የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 29 ቀን ለሚረርገው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የክልሉ አስተዳደር እውቅና መስጠቱን ተከትሎ በሰላማዊ ሰልፉ የወረዳውና የአካባቢው ነዋሪ እየደረሰበት የሚገኘውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣የመልካም አስተዳደር እጦትና የካድሬዎች ጭቆናን በይፋ የሚቃወምበት እንደሚሆን ፓርቲው አስታውቋል፡፡ በ2002 የደራሼ ወረዳ ሕዝብ በራሱ አነሳሽነት ሰልፍ ወጥቶ የነበረ ሲሆን፣ […]
ጤና ይስጥልኝ ! ግዛቸው ሽፈራው እባላለሁ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ነኝ። አንድነት በኢትዮጵያ ሕጋዊ ፍቃድ አግኘቶ፣ በአገሪቷ ባሉ ክልሎች ሁሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሰ ድርጅት ነው። አንድነት ከማንም ኢትዮጵያዊና ድርጅት ጋር ፀብ የለዉም። የአንድነት ፖለቲካ የኢትዮጵያዊነት፣ የፍቅርና የመቻቻል ፖለቲካ ነው። አላማችን ፣ የበለፀገች፣ ልጆቿ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ልዩነት ሳይደርገባቸው እኩል የሆኑባት፣ አንድነቷና […]
በደቡብ ክልል ደራሼ ወረዳ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፊታችን እሁድ ለሚያደርገው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የክልሉ አስተዳደር እውቅና ሰጥቷል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ የወረዳውና የአካባቢው ነዋሪ እየደረሰበት የሚገኘውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣የመልካም አስተዳደር እጦትና የካድሬዎች ጭቆናን በይፋ የሚቃወምበት እንደሚሆን ፓርቲው አስታውቋል፡፡
ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካለችበት የኢህአዲግ ስርአት ለመላቀቅ እና ከገባችበት ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሜያዊ ውድቀት ወጥታ ህዝቡም ከወያኔ ስርዓት ተላቋ ወደ ተሻለ እና ወደ ተረጋጋ ሕይወት ለመድረስ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እና በሁሉም አቅጣጫ እና በሚችለው መንገድ መታገል ይጠበቅበታል:: ዛሬ ላይ ወያኔ ኢህአዲግ የእምነታችንን ነጻነት እያሳጣን የዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እየረገጠ እና የዜግነት ክብራችንን እና ነፃነታችንን […]
በዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ጥያቄያቸው እንዲመለስ ጫና ለመፍጠር የምግብ ማቆም አድማ ጀመሩ፡፡ አድማው ለ3 ቀን እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ ጥያቄያቸውም፡- 1ኛ የፖለቲካው ሥነ -ምህዳር እንዲሰፋና የፓርቲዎች በነፃነት የመንቀሳቀስና የመደራጀት መብት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣ 2ኛ አፋኝ የሆኑት የመያዶች ህግ፣ የፀረ-ሽብር ህግ፣ የፕሬስ ህግ እንዲሻሩና ነፃ የሙያ ማህበራት ላይ የሚደረገው አፈና እንዲቀም፣ 3ኛ በግሉ ሚዲያ ላይ […]
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አላስተናግድም ማለቱን የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ገለጹ፡፡ የህ/ግ ኃላፊው እንደገለጹት ከሆነ ማንኛውንም ህጋዊ አካል ወይንም ዜጋ በእኩልነት ማስተናገድ የሚገባው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳያቀርብ አናስተናግድም ማለቱ አንድ የሕዝብ አገልጋይ ነኝ ከሚል ተቋም […]
ዛሬ ማለዳ ሜክሲኮ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ሊቀመንበር፣የብሄራዊ ምክር ቤት አባሉ ዘላለም ደበበና ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ በፖሊስ የአስራ አራት ቀን የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው ፍርድ ቤቱ የአስራ አንድ ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ በመፍቀድ በእስር ቤት እንዲቆዩ ተወስኖባቸዋል፡፡ ፖሊስ በአንድነት አባላት ላይ ባቀረበው ክስ ‹‹ለቅስቀሳ ባልተፈቀደ ቦታ ሲቀሰቅሱ አግኝቻቸዋለሁ፣የተፈቀደላቸው ለሰላማዊ ሰልፍ […]
(ኢ.ኤም.ኤፍ) – በኦሮሚያ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ የተጀመረው ረብሻ ወደ ከተሞች እየተዘመተ መሆኑን ዛሬ ምሽት ያገኘነው መረጃ አሳውቋል። የአምቦ ዩኒቨርስቲ ረብሻ ወደ ከተማው ተዛምቶ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። በመዳ ወላቡም ከዩኒቨርስቲው አልፎ በከተማው በተነሳ ረብሻ ሶስት ሰዎች ሞተዋል። ዛሬ ቀን ላይ ደግሞ በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ኳስ ጨዋታ ይመለከቱ የነበሩ ከመቶ በላይ ተማሪዎች ላይ ቦንብ ተጥሎባቸው፤ ሰባ ያህሉ ላይ […]
በአዲሱ የአዲስ ማስተር ፕላን በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልል ገጠር መሬቶች የአዲስ አበባ ከተማ አካል ያደርጋቸዋል። ይሄን ጉዳይ በኦሮሞ ህዝብ ባጠቃላይ በኦሮሞ ተማሪዎች ደግሞ በተለይ ዓመፅ አስነስቷል። ማስተር ፕላኑ የገጠር ቦታዎች ማካተቱ በራሱ ችግር አይደለም። እንዳዉም ፕላኑ ኦሮምያ አልፎ መቐለም ቢያጠቃልል ደስ ባለኝ ነበር። ከተማ ቢያድግ መልካም ነው። ከተማ ሲያድግም በዙርያው ይሰፋል። ይህ ባህርያዊ […]
ጎንደር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታ አርምጭሆ ሰፈር፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች የከተማው አስተዳደር ‹‹ህገ ወጥ ሰፈራ ነው፡፡›› በሚል ቤቶችን ለማፍረስ መዘጋጀቱን ተከትሎ አፍራሾቹ ከህዝብ ጋር በፈጠሩት ግጭት ከ6 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ግጭቱ ከሶስት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ ቀጥሎ የነበር ሲሆን ምንጫችን ደውሎ በሚነግረን […]
ከታሰሩ የዞን ዘጠኝ አባላት መካከል አንዱ የሆነው ናትናኤል ፈለቀ በቅርበት እንደሚያወቅት የገለጹት የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ፣ አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝም ጨምሮ ላገኟቸው ባለስልጣናት ፣ ጋዜጠኞችን ማሰርና የዜጎንች ነጻነትን መገደድ ለኢትዮጵያ እንደማይጠቅም አሳሰበዋል። ከኢትዮጵያ ጋር አሜሪካ የቅርብ ግንኙነት እንዳላት የገልጹ ኬሪ፣ የዴሞክራሲና የሰባአዊመ ጉዳይ በጣም እንደሚያሳስባቸው ገለጸዋል። « እየተናገሩት ያለው እንዲሁ ለመናገር ያህል የተናገሩት፣ […]
http://realaudio.rferl.org/voa/AMHA/2014/04/30/38f91133-b4c4-4f9d-acb8-09627757c504.mp3
አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች፣ ተቃዉሞ እንዳሰሰሙ ገዳ.ኮም ድህረ ገጽ ዘገበ። ተማሪዎቹ የተለያዩ መፈክሮችን ያሰሙ የነበረ ሲሆን ፣ቁጥራቸው ከአምሳ እስለ መቶ እንደሚጠጋ በቪዲዮም የሚታየው ምስል ያመለክታል። ተማሪዎቹ ያሰሟቸው የነበረ መፈክሮች በእንግሊዘኛ እና በአፋን ኦሮሞ ብቻ የነበረ ሲሆን ከመፍክሮቹም ዉስጥ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ነበሩ፡ Our rights should be respected ! […]
አንድነት ፓርቲ፣ በአዲስ አበባ ሚያዚያ 29 ለሚያደርገው ሰላምዊ ሰልፍ ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል። የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ፣ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ፣ በአገሪቷ ክፍሎች ሁሉ ሕዝቡን ለመብቱና ለነጻነቱ ለማደራጀትና ለመቀስቀስ በበርካትከ14 በሚበልጡ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን ሕዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚይደርግ ይፋ አድርጎ በነበረው መሰረት ፣ የአዲስ አበባ ሰልፍ በሚደረግበት ቀን፣ በደቡብ ክልል በደራሼ ወረዳ የጊዶሌ ከተማ ታልቅ ሰላምዊ ሰልፍ […]
እስረኞቹ ህዝቡ በነቂስ በመውጣት የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል!! በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ «የእሪታ ቀን» በሚል መሪ ቃል የሰየመውንና እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት፣ ከህዝብ ጎን ሆነን ድምፃችንን እንዳናሰማ በግፍ የተወረወርንበት እስር ቤት ቢያግደንም፣ ከአርብ ጀምሮ […]
የአዲስ አበባ አስተዳደር እውቅና የሰጠውን የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ የቅስቀሳ ቡድኑን በማሰር ቅስቀሳውን ለማስተጓጎል እየሞከረ እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነው።፡ቅስቀሳው ከጽ/ቤት ተነስቶ በ4ኪሎ አሚሪካ አምባሲ፣ መነን ት/ቤት፣ አፍንጮ በር፣ ፒያሣ፣ ቸርቸር ጎዳና፣ ጥቁር አንበሳ፣ ፍልውሃ፣ ቤተመንግስት፣ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አቶ ዘካሪያስ የማነ ብርሃን፣ ዘላለም ደበበ፣ ነብዩ ኃይሉ፣ ነፃነት ዘገየ የሚገኙበትን ቡድን «ወረቀት እንድትበትኑ እንጂ የመኪና […]
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና ‹‹ሽብርተኛ›› በሚል የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት ከሌሎች እስረኞች በተለየ ሁኔታ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጎ መብቱ በመጣሱ፤ እንዲሁም በተፅእኖና ክልከላ ሰለባ በመሆኑ ከትላንት ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑን ቃሊቲ የሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ፡፡ በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ […]
ፖሊስ በመኪና፣ወረቀት በመበተንና ፖስተር በመለጠፍ መቀስቀስ አይቻልም በማለት እስር እየፈጸም ቢሆንም፣ ቀዳዳዎቹን በሙሉ በመጠቀም የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጹን እንዲያሰማ፣ አንድነት በሸገር ኤፍ ኢም 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ ማስታወቂያ እንዲነገርለት ተገቢውን ክፍያ በመፈጸም የመጀመሪያው ጥሪ ዛሬ እንዲተላለፍ መድረጉን ለማወቅ ችለናል። ኢቲቪ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻ ማስታወቂያቸዉን እና ፕሮግራሞቻቸዉን ለሕዝብ እንዲያስተዋውቁ ማድረግ የነበረበት ቢሆንም፣ አሁን አንድነት እንድ ሌሎች የቢራ፣ […]
ጋዜጠኛ ነብዩ ሃይሉ የቀስቃሾቹን እንቅስቃሴ ለመዘገብ በወጣበት ለእስር ተዳርጓል፡፡በካዛንቺስ ፖሊስ ጣብያ ከነብዩ ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ሊቀመንበር ዘካሪያስ የማነብርሃንና ዘላለም ደበበ ይገኙበታል፡፡የጣብያው ኃላፊዎች ‹‹ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል››የሚል ውንጀላ አቅርበውባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ብሮሸርና ፍላየር የሚያሰራጩ ወደ ቦሌ የተጓዙ አባላት መሳይ ትኩ፣ ማቲዎስ አርጉና አያሌው ዳርምያለውን ጃፓን ኤምባሲ (ጤና ጣቢያው) አካባቢ ባለው ፖሊስ ጣቢያ ታግተዋል፡፡ እስራቱ እና […]
https://www.youtube.com/watch?v=qQ26MKj_xU
አንድነት ፓርቲ ቅስቀሳ መርካቶዎች ሰልፉን ዛሬ ጀመሩት – ቪዲዮ ይዘናል
አዲስ አበባ በቅስቀሳ ደምቃ ዋለች ፣ ብዙዎች ታሰሩ:: የአንድነት ፓርቲ የእሪታ ቀን በሚል እሑድ ሚያዚያ 29 ቀን ለጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረገዉ ቅስቀሳ በደመቀ ሁኔታ ቀጥሏል። ብዙዎች ቢታሰሩም ቅስቀሳው እንዳልቆመ ለማወቅ ችለናል። በመኪና ቅስቀሳዎች ሲደረጉ ሕዝቡ በብዛት መኪናዎችን እየተከተለ ቅስቀሳውን ራሱ ሰልፍ ያሰመሰለበት ሁኔታ እንደነበረም ዘገባዎች ይገልጻሉ። ፖሊስ በ በእግራቹህ እየሄዳችሁ ወረቀት ማደል እንጂ በመኪና እንድትቀሰቅሱ […]
በተማሪዎች ዛሬ በተቀሰቀሰው ረብሻ፣ ከስድስት በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች እንደተገደሉ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገበ። ተማሪዎቹ አዲስ አበባ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ዞኖች በአዲስ አበባ ስር መሆኗ በመቃወም ሲሆን ሰልፍ የወጡት፣ በተነሳው ግጭት ሶስት በከተማ ያሉ ፎቆች ተቃጥለዋል። ከተቃጠሉት መካከል አንዱ ባንክ እንደሆነ ተዘግቧል።
በዶር መራራ የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ፣ በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጠቃለላቸዉን በመቃወም መግለጫ አወጣ። ኦፌኮ በመግለጫው፣ ፣ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፓላን፣ በልማት ስም የሚደረግ የመሬት ወረራ ብሎታል። በሕገ መንግስቱ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ እንደሆነ መገለጹን የገልጸው መግለጫው፣ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ሊኖር ስለሚገባዉ ግንኙነት በተመለከተም ይወጣል የተባለው ዝርዝር […]
ኢሕአዴግ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ላይ ፣ በተለይም ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ያለዉ ሕግ ወጥና ኢሰብአዊ ጥቃት አወገዘ። ዜጎችን የሚያምኑበትን የመናገር ሙሉ መብት እንዳላቸው ያስቀመጠው የአንድነት መግለጫ፣ ተቃዉሞ የሚያስሙ ወገኖች ሊደመጡ እንጂ ሊደበደቡና ሊታሰሩ እንደማይገባም ይገልጻል። አንድነት፣ በቅርቡ የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርህ፣ አዲስ አበባን ጨመሮ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ […]
አንድነት ፓርቲ ትላንት ሚያዚያ 21 ቀን ባወጣዉ መግለጫ በዞን ዘጠኖች እና ጋዜጠኖች ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ተግባር አዉግዟል። አገዛዙ ሆን ብሎ በአገራቸዉ ጉዳይ ላይ በተለይም ወጣቶችና የተማሩ እንዳይሳተፉ ለማስፈራራት ያደረገዉ እንደሆነ በመገልጽ እስረኞቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። «ፓርቲያችን ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ […]
የአንድነት ፓርቲ አባላት፣ ከትላንት ማክሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን ጀምሮ፣ በሃያ ሶስቱም ወረዳዎች፣ በየመንደሩ በስፋት ቅስቀሳ እያደረገ እንደሆነ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለከትል። አልፎ አልፎ ፖሊስ ከፈጠራቸው መጠነኛ ችግሮች በስተቀር፣ ቅስቀሳዉ እስከአሁን በጥሩ ሁኔታ እየተደረገ እንዳለም ለማረጋገጥ ችለናል። ትላንት በቅስቀሳ የተሰማሩ ስድስት አባላት ሜክሲኮ አካባቢ በፖሊስ ታግተው እንደነበረ መዘገባችን ይታወቃል። እስረኞቹ ፣ አንድነት የጠራዉ ሰልፍ ሕጋዊ እውቅና […]
የቀድሞው የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃምን ጨምሮ ታዋቂ ፖለቲከኞችና ምሁራን አንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸውን አንድ አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ከፍተኛ አመራሩ ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ታዋቂው ወጣት ፖለቲከኛና ደራሲ አቶ አስራት አብርሃ እና ሌሎች በርካታ ወጣት ምሁራን አንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸው ፓርቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እያገኘ ያለውን ተቀባይነት የሚያሳይ […]
ርዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ …….እያልን ስሞችን መዘርዘር እንችላለን። በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ዜጎች ሕገ ወጥና ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ የታሰሩ ወገኖቻችን፣ ከእሥር እንዲፈቱ ስንጠብቅ ፣ ሌሎች እየተጨመሩ ነው። ከቃሊት ዉጭ ሆነው እነ ርዪትን ሲጎበኙ የነበሩ አሁን እነ ርዮት አለሙን እየተቀላቀሉ ነው። ዞን ዘጠኞች ፣ እነ ጋዜጠኛ ተስፋአለም፣ የሚጽፉትን ፣ የሚጦምሩትን እኛም አንብበነዋል። በድብቅና በሚስጠር አልነበረም […]
ሚያዚያ 21 ቀን 2006 በአዲስ አበባ በሃያ ሶስቱም ወረዳዎች፣ በራሪ ወረቀቶች ለሕዝቡ በማደል ሰፊ ቅስቀሳዎች ሲደረጉ ዉለዋል። የቅስቀሳ ተግባራትን ለማጨናግፍ ፖሊስ አንዳንድ ቦታ ሲሞክር የተየበትም ሁኔታ የነበረ ሲሆን ስድስት አባላት በሜክሲኮ አካባቢ ታግተዋል። ከተሰሩ የአንድነት አባላት መካከል ሁለቱ በቅስቀሳ ላይ
የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የታሰሩ ብሎገሮች ጉዳያቸው በአስቸኳይ ታይቶ እንዲፈቱ በቀጥታ የኢትዮዮጵያን መንግስት መጠየቃቸው ቃለ አቀባይዋ ሚሲስ ፕሳኪ ገለጹ። የኢትዮጵያ መንግስት በሕገ መንግስቱ የተደነገጉትን መብቶች ማክበር እንዳለበት፣ አሜሪካ ጠንካራ አቋም እንደሆኑ የገለጹት ሚሲስ ፕሳኪ፣ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ጆን ኬሪ በአፍሪካ ጉብኘት ባደረጉበት ጊዜ ሁሉ የሰባአዊ መብት ጉዳይ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንደሚያነሱ ለመጠቆም ሞክረዋል። ከታሰሩ […]
የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 26 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ የእውቅና ደብዳቤ እንደሰጠ ቢታወቅም፣ ሕጉን ተከትለው ሰላማዊ የሆነ የቅስቀሳ ሥራ በመስራት ፣ ለሕዝቡ በራሪ ወረቀቶች ሲያድሉ የነበሩ ስድስት የአንድነት አባላት ሜክሲኮ አካባቢ በፖሊስ ተይዘው፣ በእሥር ላይ እንደሚገኙ፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል አሳወቀ። አስተዳደሩ ለአንድነት ፓርቲ በሰጠዉ የእውቅና ደብዳቤ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፣ ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ለዉስጥ ደህንነት […]
አንጋፋዉ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ቅዳሜ ሚያዚያ 18፣ ቀን በጊዮን ሆቴል ከአስር ሺህ ህዝብ በላይ በተገኘበት ፣ የፍቅርና የኢትዮጳይዊነት ጣእም ዜማዎችን ሲያቀርብ እንዳመሸ ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ታዋቂዎቹ «ጥቁር ሰው» እና «ያስተሰርያል» የተባሉት ዘፈኖች በሕዝቡ ጥያቄ በድጋሚ እንደዘፈኑ የተደረገ ሲሆን፣ሕዝቡ ዘረኝነትና ክፍፍል፣ ጥላቻና ቂም በቀለ እንደመረረዉ በመገልጸ ፍቅርን፣ የሰላምን እና የአንድነት መልእክት ማስተላለፉን ለማየት ተችሏል። በተለይም […]
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ ፓርቲያችን አንድነት አበክሮ በተደጋጋሚ እንደገለፀው ኢህአዴግ ያነበረው አምባገን እና ክፉ ስርዓት ዜጎች በተለያየ ጊዜ የሚያነሱትን የሰብዓዊ መብት፣ የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ የሚቀለብሰው ወታደራዊ አቅሙን በመጠቀም ነው፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ አካሄዱም ስርዓቱን ይቀናቀናሉ የሚላቸውን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎችና በግለሰብ ደረጃ ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎችን የተለያየ ስም እየሰጠ ወደ እስር ቤት አውርዷል፡፡ እያወረደም ይገኛል፡፡ […]
አንድነት ፓርቲ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሆኑት Jhon Kerry በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ደብዳቤ ፃፈ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የፊታችን ሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደሚያደርግ ማሳወቁ ይታወቃል። መጋቢት 28፣ ሚያዚያ 5፣ ሚያዚያ 19 ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ ፣ አስተዳደሩ በተለያዩ ምክንያቶች እውቅና ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነበር አንድነት የሰልፉን ቀን ለሚያዚያ 26 ያስተላለፈው።
የኢህአዴግ ፖለቲካ ዜጎችን የማሰር፣ ዜጎችን የማሸበር ፖለቲክ ነው። በቅርቡ በዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የሚያሳየው፣ አገዛዙ ሃሳብን በሃሳብ መመከት ሲሳነው የሃይል እርምጃ ለመዉሰድ ወደ ኋላ የማይል መሆኑን ነው። ኢሕአዴግ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ሳይሆን፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለማሸበር ሲል ያወጣዉ የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ በመጠየቅ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ማድረጉ ይታወሳል። በአገሪቷ ክፍሎች ያሉ ሚሊዮኖች፣ አገዛዙ ዜጎችን በማሸበር […]