አንድነት ፓርቲ በመጪው ዕሁድ ሰኔ 1 ቀን 2006 በደብረማርቆስ፣ በአዳማ/ናዝሬት እና በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ፤ የቅስቀሳ ስራውን የሚያስተባብሩ ሶስት ቡድኖች ከትላንት ጀምሮ ከዋናው ጽ/ቤት መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ ዛሬ በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚደረገውን ቅስቀሳ የሚያስተባብረው ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ በደብረ ማርቆስና በአዳማ የተጠናከረ ቅስቀሳ ከተሰራ በኋላ የፖሊስ የተሟላ […]

በቦስተንና አካባቢዋ ከ3ዓመት በፊት በወጣት ሀዲስ ግርማ መታስቢያነት የተቋቋመው የሀዲስ ግርማ የመታስቢያ ድርጅት የ3ኛ ዓመት ጉባዔ እሁድ ጁን 1 ቀን 2014 ዓ. ም. በረስል ዩዝ ኮሚኒቲ ሴንተር፣ ካምብሪጅ (Russell Youth Community Center, Cambridge, MA) በተለያዩ ዝግጅቶች በተሳካ ሁኔታ ተካሄዷል። በእለቱ ከተካሄዱት ፕሮግራሞች የመጀመሪያው እና የብዙዎችን ትኩረት የሳበው በዚህ አመት በሀዲስ ግርማ መታስቢያ ድርጅት እና በወላጆች […]

ጓዶች ዓረና ባደረገው እንቅስቃሴ በትግራይ ክልል ሙሉ ድጋፍ እንዳለው አረጋግጧል። ይሄን ጉዳይ ህወሓትም ተረድቶታታል። እናም የህወሓት አመራር አባላት ዓረናን ለማዳከም አባላቶቻችን በጥቅም በመደለል፤ ካልተሳካ ደግሞ በማስፈራራት እንዲሁም በድንጋይ በመውገር ህዝብን የማነሳሳት እንስቅስቃሴያቸው እንዲያቆሙ ለማድረግ ሞክረዋል። አልሆነም። እናም አሁም የዓረና አባላትን (አስተባባሪዎችን) ለማሳሰር ዉሳኔ ተላልፈዋል። አሁን በግፍ ማሰር ጀምረዋል። አባላትን በማሳሰር ዓረናን ማዳከም ግን አይቻልም። ምክንያቱም […]

ትዝ ይለኛል በ1997 ዓ.ም ይወጡ ከነበሩ ፕሬሶች ‹‹ነፃነት›› ጋዜጣ ትመስለኛለች በፊት ለፊት ገጽዋ ‹‹ንቢቱ መናደፍ ጀመረች!!›› የሚል ርዕስ ይዛ ነበር፡፡ የመለስን ‹‹እንከን የለሽ ምርጫ እናካሂዳለን›› የአደባባይ ቃል በጥይት ለመቀልበስ ሲሞከር የተሰጠ ርእስ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥም ዴሞክራሲን በወረቀት እንጂ በተግባር ለማረጋገጥ አልቻሉም፡፡ በአንድ እጃቸው ምዕራባዊያን እንዳይከፋቸው ዴሞክራሲን በሌላ እጃቸው ደግሞ የዴሞክራሲ መቀልበሻ ክላሽ ይዘው 23 […]

ተስፋዬ ዋቅቶላ (የአዳማ አንድነት ፓርቲ የሕ/ግንኙነት) “….ያኔ እንተያያለን…” በትላንትናው ዕለት የአዳማ አንድነት ሰልፍ ፈቃዳችንን ከ20ቀናት ደጅ ጥናት በኋላ ወስደናል፡፡ግን ከአስገራሚ ገጠመኞቹ ጥቂቱንም ቢሆን ማካፈል ግድ ይለናልና እነሆ፡፡ፈቃዱን ከመስጠታቸው በፊት ከከተማው ጸጥታ ክፍል ሶስት ሰዎች መጥተው ከንቲባው ጽ/ቤት ተጠርተው ገቡ፡፡እኛ በዚህ ዕለት ካልተሰጠን ላንወጣ ተነጋግረን ገብተናልና “ቶሎ ድረሱልኝ” ያላቸው ሰዎች መምጣት ደስ ብሎናል እንጂ አልፈራንም፡፡ሆኖም ነገርየው […]

አንድነት በአዳማ ስለመሬት ስሪትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ጠራው ሰልፍ ከ20 ቀናት በኋላ ዕውቅና አገኘ፡፡ ግንቦት 5 ነበር ደብዳቤያችንን ለከንቲባው ጽ/ቤት ያስገባነው፡፡ ጥያቄያችንም ግንቦት 10 ሰልፍ ለማድረግ ነበር፡፡ ሆኖም በከንቲባው ጽ/ቤት ቢሮክራሲ ለሰኔ 10 ሊፈቀድ ቀርቶ ሊያነጋግሩን እንኳን ባለመቻላቸው ወደ ከንቲባው የተላከው ደብዳቤያችን በከንቲባው አማካኝነት ከግንቦት 20 በኋላ ሊስተናገድ ከባንኮኒ ገብቶ ተቆለፈበት፡፡ ክትትላቸውን ያላቋረጡት የአዳማ አንድነት […]

የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነበረች። ይሄን ጊዜ ከኮሌጅ ተመርቃ፣ ሥራ ይዛ ምናልባትም ተድራ፣ የልጆች እናት ትሆን ነበር። አሁን ግን የለችም። ኮተቤ አካባቢ ነበር፤ ከአጋዚ ጦር አንዱ በተተኮስ ጥይት ተመታ ወደቀች። ሰኔ አንድ ቀን 1997 ዓ.ም። የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነው። በእጆቹ ድንጋይ አልያዘም። ተማሪ ነበር። ወደቤቱ ሲመለስ፣ በአካባቢዉ ግርግር ተፈጠሮ ስለነበረ፣ ሰላምና መረጋጋት እናመጣለን ባሉ […]

በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራ አስፈጻሚ አባል ወጣት መልካሙ አምባቸው ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ወጣት መልካሙ በጎንደር የሚደረገውን የድንበር ማካለል የአካባቢው ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን የሚያውቀውን […]

በሱዳን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ቀጥሏል:: በየጊዜው ለስራ ፍለካ ምክንያትና በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሀገራቸውን እየለቀቁ ወደ ሱዳን የሚገቡ ኢትዮጵያኖችን ብዙ ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያኖች ወደ ሱዳን ከገቡ በኋላ ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል :: በተለይም በሱዳን በሚኖሩ ኢትዮጵያን ዜጎቻችን ላይ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ኢሰብዓዊ ድብደባ እየተፈጸመባቸውና በሀገሪቱ ፖሊስ እና በሱዳን ማህበረሰብ ዘግናኝ […]

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በውህደት ጉዳይ ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ጋር ሲደረግ የነበረው ውይይት በመጠናቀቁና ሁለቱ ፓርቲዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ምክንያት የቅድመ ውህደት ፊርማ ስነ-ስርዓት ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መላኩን የመኢአድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነው ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ […]

የ ምርጫ ዘጠና ሰባት ሕልፈት ሕይወት የ አዲስ አበባን ወጣቶች ከምርጫ ወደ በርጫ በብርሃን ፍጥነት ሲመራቸው ቅንጅትም ከመንፈስነት ወደ ፈስነት የሄደበት መንገድ እንዲሁ ተመሳስይ ነብር። ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ነብር ሆነው የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች ከነብርነት ወደ ነበርንነት ፣ ቁልቁል ተንደርድረው ከዝግባነት ወደ ዘጋቢነት የተሸጋገሩበትን እጻዊ ( ምጸታዊ ጡዘት ) መንፈስ እና መንፈሰ ግስጋሴ ሳስበው ይገርመኛል። […]

የማለዳ ወግ … ካርል ሓይሰን ለሰብዕና የተጉ ብጹዕ ነበሩ ! ነፍሳቸውን ይማር ሰብዕናን መሰረት አድርገው በመላ አለም በበጎ የረድኤት እና ምግባረ ሰናይ ድርጅቶችን የመሰረቱ ብጹአን እንብዛም ባልበረከቱባት ምድር አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ በሰብአዊ ስራቸው መንፈሳዊ ቅናት ሰሜታችን የሚያጎኑ አልጠፉም። …ግን አይበረክቱም ከቀረው አለም ምልከታ ትናንትም ሆነ ዛሬ በእኛ ሃገር ለእኛ ስለሆነውና የሚሆነውን አድርገው ስላለፉት የእኔ […]

የለውጥ አስፈላጊነት ላይና ወያኔ መራሹ መንግስት ይበቃው ዘንድ ባብዛኛው ዜጋ ከተቻለ የሚለው እንዳለ ብዥታ የለም። ይህ ፍላጎት የብዙ ስረአቱ ውስጥ ያሉ ዜጎችም ጭምር መሆኑን የተለያዩ መረጃዎችን ጨምቆ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። በርግጥ የለውጡ አስፈላጊነት ላይ የሚስማሙና አይቀሬነቱን የሚያውቁ ነገር ግን ለውጡ የተረጋጋና ችግሮች ያልበዙበት እንዲሆን ይረዳል ብለው አገዛዙ ድርሻ በሚያደርግበት እንዲከወን የሚመኙ አሉ። ፈራ ተባ እያሉ […]

ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል። ይህንን ታላቅ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ኢሊባቡር ውስጥ ጉመሮ ሻይ ተክል መጥቶ በነበረበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት የተነገረን የፊልም ተዋንያን መሆኑን ብቻ […]

አሁን በኢትዮጵያ ባለው በቋንቋ ላይ ብቻ የተመሰረተ፣ የብሄረሰብ ፌዴራል አወቃቀርን በተመለተ ከሶስት የኦሮሞ ምሁራን ጋር የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ያደረገው መደመጥ ያለበት ዉይይት !

ዛሬ ከአገራችን አውራ ችግሮች መካከል ዋናው፣ የተደጋገሙ ውሸቶች ዕውነት የመሰሏቸው ቡድኖች የሚያጎኑት በጥላቻ ላይ የተመሠረተ የዘር ፖለቲካ እና አንድን ነገድ፣ በኢትዮጵያ ተፈጠሩ ለሚባሉ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርገው ነው ብዬ አምናለሁ። አይደለም የሚለኝ ከመጣም የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ነኝ። የተደጋገሙ ውሸቶች ሀውልት ሲያስቆሙ እያዬን ነው። የአኖሌን ሀውልት ለአብነት መመልከት ነው። የከተሞችን ስም ሲያስለውጥ እያዬን ነው። አዲስ አበባን […]

በአምቦ ከተማና በሌሎች የኦሮምያ ክልል ውስጥ የዩኒቭርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያቀረቡት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ በጨካኙ የአግዓዚ ጦር አልሞ ተኳሾች በጥይት መደብደብን ስለሆነ፣ ይህንን አሰቃቂ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ያውም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት መከበር ግምባር ቀደም መመሪያ ሆኖ በዓለማችን ላይ በገነነበት ጊዜ በመፈፀሙ፣ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህንን የተገነዘበው የባእዳንን ዓላማዎች ለማስፈፀም በጫንቃችን […]

ትናንት ቡራዩ ከተማ ፍርድ ቤት ቀርቦ በ500 ብር ዋስ እንዲፈታ ትዕዛዝ ተሰጥቶለት የነበረውን የፖለቲከኛና ደራሲ አስራት አብርሃምን የዋስ መብት አላከብርም በማለት ያሰረው የከተማይቱ ፖሊስ ከቅርብ ሰዓታት በፊት አስራትን በዋስ መልቀቁን ለሰላማዊው ታጋይ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ አስራ ለእስራት የተዳረገው የመድረክ ሰላማዊ ሰልፍን ለመቀስቀስ በቡራዩ የከተማ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በመታሰራቸው ለጥየቃ ባመራበት እንደነበርና ፖሊስም […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) እንደሚታወቀው የግንቦት 2ዐን 23ኛ ዓመት ለማክበር ጉድ ጉድ እያለ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ወደ ጠቅላይ አምባገነን ፓርቲነት ከተለወጠ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በ1983 ዓ.ም ሀገሪቱን ከመቆጣጠራቸው በፊት በርካቶች ስለ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን ክቡር ህይወታቸውን እንዲገብሩ ተደርጎ በተገኘ የዜጎቻችን መስዋእትነት መንበረ […]

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተከተ ከፍተኛ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ መውደሙን የመንግስት ሚድያዎች ዘገቡ። የመንግስት ሚድያዎቹ አደጋውን ቀለል በማድረግ በእሳት አደጋው የተጎዱ ተማሪዎች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ቢሉም የአይን እማኞች ግን የሚናገሩት በተቃራኒው ነው። በዩኒቨርሲቲው የተነሳ የእሳት አደጋ ከሌሊቱ 10 ሰዓት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የአደጋውን መነሻ ፖሊስ እያጣራሁ ነው ብሏል። እሳቱ በሌሊት በመነሳቱ የተነሳ በመኝታ ላይ […]

በአንድ ሀገር የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የዜጎች በሰብዓዊ መብት፣ በዲሞክራሲ፣ በፖለቲካ እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ያላቸው ንቃተ ህሊና የሚጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው። የሲቪክና የፖለቲካ ማህበራት ፣ የጋዜጠኞችና የነፃ ሚዲያዎች በብዛት መኖር ከሰፊ ተሳትፎ ጋር የማህበረሰብ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለውን ንቃተ ህሊና ማሳደግያ መሆናቸው ዕሙን ነው። ነገር ግን የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን በበጎ መልኩ አይቶ ከማበረታታት […]

የአወሊያ ትምህርት ቤት ኮሌጅና ሀይ ስኩል መምህራኖች ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን ከአመፅ ጋር በማያያዝ ለኮሚቴዎቹ በመሰከሩ መምህራኖች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ ። FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ] ከኑሮው ውድነት ጋር ተያይዞ የሚከፈላቸው ደመወዝ ከእጅ ወደ አፍ የሆነባቸው የአወሊያ ትምህርት ቤት መምህራን ግንቦት 4\2006 በአወሊያ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሰባሰብ የአወሊያ […]

የአራት ፓርቲዎች መድረክ የሆነው መድረክ ትናንት በአዲስ አበባ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቀደም ብለው የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ከተማ በፖሊስ መታሰራቸውን የሰሙት የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሐብታይ ገብረ ሩፋኤልና በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀለው ደራሲና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃ እስረኞቹን ሊጠይቁ በሄዱበት በወረዳው ከታሰሩ በኋላ ፖሊስ አቶ ሐብታይን ሲለቅ አቶ አስራትን በወረዳው አሳድሯቸው ነበር፡፡ […]

የከበረ ሰላምታችንን በቅድሚያ አያቀረብን፤ May 23, 2014 (ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፮ ዓ.ም.) በሰሜን አሜሪካ ዴንቨር ኮሎራዶ የአረመኔውን ከፍተኛ 15ቱ ቀይ ሽብር ተሳታፊ ከፋለኝ ዓለሙን ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የፍርድ ቤቱ ችሎት ከጠዋቱ 9፡30 ተሰየመ። ጉዳዩን ሲከታተል የነበሩት ጠበቆችና የሚመለከታቸው ተገኝተዋል። ከፋለኝ ዓለሙን ለመጀመሪያ ጊዜ በዴንቨር ኮልራዶ በመመልከት ወደ ፍርድ ይቀርብ ዘንድ ከፍተኛውን […]

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች መድረክ በጠራው ሰልፍ ተገኝተው መፈክር ሲያሰሙ እንደነበረ የሚገልጽ ቪዲዮ በሰማያዊ ፓርቲ ፌስ ቡክ ገጽ ተለቀቀ። ሊቀመንበሩን ኢንጂነር ይልቃልን ጨምሮ፣ ሰማያዊዎች የሰማያዊ ፓርቲ ከኔተራዎችን ለብሰውና የድርጃታቸው አርማ ይዘው ሳይሆን፣ እንደ ሌላው ህዝብ ሰልፉ እንደተቀላቀሉ ቪዲዮው ያሳያል።

·የሠሞኑ የአክራሪ ኦሮሞዎች እንቅስቃሴ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የነደፈውን የአዲስ አበባ ከተማን የማስፋፋት ዕቅድ ለመቃወም ሣይሆን ዐማራን ከምድረ-ገፅ ማጥፋት መሆኑን ያረጋግጣል። ሠሞኑን በዓለማያ፣ በአምቦ፣ በነቀምት እና በሮቤ (መዳወላቡ) ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የዐማራ ተማሪዎች ላይ በአክራሪ የኦሮሞ ተማሪዎች እና በኦሕዴድ ካድሬዎች ትብብር ዘርን መነሻ እና መድረሻ አድርጎ የሚፈጸመው ጥቃት፣ ማቆሚያ የሌለው እና የዐማራን ነገድ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት በትግሬ-ወያኔዎች እና በተባባሪዎቻቸው […]

በ10 ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባን አጥለቅልቋታል። ስላማዊ ሰልፉን የጠራው በፕሮፌሰር መራራ ጉድና የሚመራው መድረክ ፓርቲ ነው። ሃሳባችንን በነጻነት መግለጽ እንፈልጋለን ! ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችን ይከበር!!! ተቃውሞ ባሰም የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እናወግዛለን !!! መድረክ ለኦሮሞ ተማሪዎች ያለውን አጋርነት ይገልጻል !! ቪቫ መድረክ !!! መድረክ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን […]

‹‹ቪዛ ይሰጠንና ወደ ሱማሌያ ቢሆንም እንሂድ›› ቤታቸው የፈረሰባቸው በኮልፌ ቀራኒዮ አለም ባንክ አካባቢ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በማድረግ ቤቶችን ሰርታችኋል የተባሉ ዜጎች ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በሀይል ፈርሶ ንብረታቸው መወረሱን አመለከቱ፡፡ ከ15.000 የሚልቁ ነዋሪዎች በሚገኙበት አለም ባንክ አካባቢ ሰዎቹ አነስተኛ መጠለያ ያረፉባቸውን ቤቶች ከገበሬዎች ላይ በመግዛት መኖር ከጀመሩ አመታት መቆጠሩን ያስረዳሉ፡፡ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ልከውና ወደ ስራ […]

የአንድነት የድጋፍ ማህበር በሰሜን አሜሪካ በቅርቡ የተካሄደውን የንፁሐን ዜጐች ግድያና ማሰቃየት እንዲሁም ዜጎችን አገራችሁ አይደለም ተብለው ከቅያቸው የማፈናቀሉን ተግባራት በእጅጉ ያወግዛል፡፡ የአምቦ እና የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች አገዛዙ ያወጣውን የአዲስ አበባ ማስተር ኘላን በመቃወም ሠላማዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው የአካባቢው ባለስልጣናትና የመንግስት ታጣቂዎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል በመጠቀም በንፁሐን ዜጐች ላይ የጦር መሣሪያ በመተኮስ የብዙ […]

ጀነራል አለምሸት፣ በባለቤታቸው ወ/ሮ አንሻ ሰይድ ስም፣ በቅርቡ ያሰሩት ፎቅ፣ ግምሹ በወር 500000 ብር፣ ለአንድ ባንክ፣ ለበርካታ የቻይና ኩባንያዎችና አንድ ሬስቶራንት ተከራየ። በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች እየተጓተቱ ባለበት ወቅት የአገዛዙ ቱባ ባለስልጣናት ግንባታዎቻቸውን በተቀላጠፈ መንገድ ማጠናቀቅ መቻላቸው፣ አገዛዙ ምን ያህል በስልጣን ብልግና የተጨማለቀ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።

መግቢያ፤ በጥንቱ ዘመን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ፤ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። ባሁኑ ጊዜ ግን፤ በተለይ ግብጽ የአባይን ወንዝ እንደ ግል ንብረቷ በመቁጠር ኢትዮጵያ በገዛ ወንዟ ለመጠቀም የምታከናውነውን ጥረት መቃወም ብቻ ሳይሆን ማስፈራራትም ይቃጣታል። እንደሚታወቀው፤ ሰሞኑን በየድህረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፤ ትችቶችና አስተያየቶች ውስጥ ሰፊ ስፍራ ይዞ የሚገኘው በኢትዮጵያ በመገንባት […]

ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!! የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የመሀል ቀጠና ፅ/ቤት ለግንቦት 10 ጠይቆትየነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ የተለያዩ ሰበቦችና ምክንያቶች ሲድበሰበስ ከርሞ ለሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም መተላለፉን የመሀል ቀጠና ጽ/ቤቱ በጠራው የአስቸኳይ ስብሰባ መወሰኑንናይህንኑ ውሳኔውንም በቀን መወሰኛ ደብዳቤው ላይ ገልጾ ለአዳማ መስተዳድር ከንቲባ አቶ አብረሐም ማስረከቡን በመረጃ አያይዞ ገልጧል፡፡በመሆኑም ሰኔ አንድ የአንድነት […]

አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሀውዜን ከተማ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከመቀሌ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደርሰው እኛ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምናደርግ ስብሰባ የሚባል ነገር የለም በማለት ወደ አዳራሹ የሚመጣውን ሰው ድንጋይ በመወርወር ስብሰባው እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባውን እንዲታደም ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ሁለት አባላት ታርጋ በሌላቸው ሞተር […]

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ አባልና የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ትናንት ለምሳ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲያቀና ማንነታቸውን ባልለያቸው ሰዎች በድንጋይ መፈንከቱ ታውቋል፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 8፡00 እንደደረሰ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ በመቅረብ ምንም ሳያነጋግሩት በድንጋይ ፈንክተውት መሰወራቸውን አቶ ስንታየሁ ለፍኖተ […]

ከሰሞኑ ወያኔ መራሹ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያወጣው አዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሚያ ዞን ያካተተ ማስተር ፕላን እና የእዝ አስተዳደር ተግባራዊነትን በመቃወም በብዙዎች የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችና ሃገር ወዳዶች ሰፊ ህዝባዊ የመብት ማስከበር ንቅናቄ ተቀስቅሶ በመንግስት ቅጥ ያጣ ግድያና እስር ለጊዜው ጋብ ቢልም አሁንም ቢሆን በህዝቡ ውስጥ ሞልቶ ሊገነፍል የደረሰ ቁጣ አለ፡፡ በሌላ በኩል በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜ […]

መግቢያ፤ በጥንቱ ዘመን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ፤ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። ባሁኑ ጊዜ ግን፤ በተለይ ግብጽ የአባይን ወንዝ እንደ ግል ንብረቷ በመቁጠር ኢትዮጵያ በገዛ ወንዟ ለመጠቀም የምታከናውነውን ጥረት መቃወም ብቻ ሳይሆን ማስፈራራትም ይቃጣታል። እንደሚታወቀው፤ ሰሞኑን በየድህረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፤ ትችቶችና አስተያየቶች ውስጥ ሰፊ ስፍራ ይዞ የሚገኘው በኢትዮጵያ በመገንባት […]

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም ለማድረግ ያሳወቀው ሰልፍ ተከለከለ፡፡ መድረክ ሰልፉን ለመጥራት በሀገራችን መሰረታዊና ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን እንዲሁም በሳውዲና በአለም ዙሪያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ መሰረቱ የስደት መንስኤው ላይ በመሆኑ፣ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡ ሰልፉን ለማድረግ የታቀደው ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው የመድረክ […]

ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር […]

በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር አባል ፤የውህደት ጉዳዮች ፀሀፊና የፋይናንስ ክፍል ሀላፊ በሆኑት በአቶ ፀጋዬ አላምረው የተመራው ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሀሙስ ማለትም ከግንቦት 7ቀን 2006ዓ. ም ጀምሮ በሰሜን ቀጠና የሚገኙ የፓርቲውን አደረጃጀት መዋቅሮች በመገምገም ላይ ሲሆን በተለይ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲዎች የውህደት ጉዳይ በደጀን በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ የመኢአድ አባላት በቀረበ ጥያቄ […]

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በእንወያይ መድረኩ፣ የሕወሃት አባት ተብለው የሚታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ፣ የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባዉ መሐሪ፣ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉና፣ በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀሉት ደራሲና አክቲቪስት አቶ አስራት አብራሃ፣ በግንቦት ሃይ ዙሪያ ዉይይቶች በማድረግ ላለፉት 23 አመታት የነበረዉን ሁኔታ የቃኘ ሲሆን፣ በዉይይቱ ማብቂያ ላይ ኢሕአዴግን እና ተቃዋሚዎች ለአገር ጥቅም ሲባል […]