አቡጊዳ – የአዲስ አበባዉ የዛሬው ሚያዚያ 24 ቅስቀሳ (ቪዲዮ እና ፎቶዎች ይዘናል)

ሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ለሚደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳው ዛሬም በደመቀ ሁኔታ መካሄዱን ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል። ትላንት የተደረጉ የመኪና ቅስቀሳዎች ወቅት መኪናዎችን እየተከታተሉ፣ በርካታ ሰዎች በመሰብሰባቸው፣ ቅስቀሳዎቹ በራሳቸው እንደ ሰልፍ የነበሩበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን፣ ይህ በሕዝቡ ዘንድ ያለው መነሳሳት ያላስደሰታቸው ገዢዎች፣ ሕግ መንግስቱን በመናድ ፣ በመኪና መቀስቀስ አትችሉም በሚል፣ ትላንት ማምሻዉን መኪናዎችን ወደ ማገትና አባላትን ወደ ማሰር መድረሳቸው ተዘግቧል።

የዛሬው ቅስቀሳ ብዙ የመከና ቅስቀሳ ያለነበረበት ሲሆን፣ መኪና በማይገባባቸው መንደሮች ሁሉ በማይክሮፎን መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ እንደተደረገም ለማወቅ ችለናል።

በዛሬው ቅስቀሳ የታሰረ የአንድነት አባላ እንደሌለ ያረጋገጥን ሲሆን፣ ትልናት ከታሰሩት ሰባቱ ዉስጥ ሶስቱ በአንድ ፍርድ ቤት በዋስ ሲለቀቁ፣ ሌላ ፍርድ ቤት ደግሞ ለአራቱ የዋስት መብትን ከልክሎ እስከ ሚቀጥለው ቀጠሮ (ከአስር ቀናት በኋላ) በወህኒ እንዲቆዩ ወስኗል። ፍርድ ቤቱ ዋስትና ከከለከላቸው ዜጎችን መካከል የአንድነት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቤ አቶ ዘካርያስ የማነ አብ፣ አቶ ዘላላም፣የፍኖት ዋና አዘጋጅ አቶ ነብዩ እና አቶ ነጻነት ዘገየ ናቸው።

camp3

campaigning

camp2

camp1