ኦፌኮ – የስርዓቱ አራማጆች 30 እና 40 ካርታ እየተረከቡ ሽጠው ፎቅ እየሰሩ ነው (በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ የኦፌኮን መግለጫ ይዘናል)

በዶር መራራ የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ፣ በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጠቃለላቸዉን በመቃወም መግለጫ አወጣ።

ኦፌኮ በመግለጫው፣ ፣ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፓላን፣ በልማት ስም የሚደረግ የመሬት ወረራ ብሎታል። በሕገ መንግስቱ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ እንደሆነ መገለጹን የገልጸው መግለጫው፣ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ሊኖር ስለሚገባዉ ግንኙነት በተመለከተም ይወጣል የተባለው ዝርዝር ሕግ እስከ አሁን ድረስ፣ ይኸው ለሃያ አመት እንዳልወጣ ያትታል።

« በገጠር በኢንቨስትመንት ስም የኦሮሞ ገበሬ ማሳዉን ያለ በቂ ካሳና ዘላዊ የሥራ ዋስትና እየተነጠቀ ከመሬቱ እየተነቀለ ነው። በከተማም ነባር ባለይዞታው ቤቱ እየፈረሰ ያነበቂ ካሳና ዘላዊ ዋስትና ለድህነት ኑሪ እየተዳረገ ይገኛል። በአንጻሩም ጥቂት የስርዓቱ አራማጆችና ደጋፊዎች በገጠርም ሆነ በከተማ ቦታዉን እየተመሩ በዘመድ ወዳጅ ስም 30 እና 40 ካርታ እየተረከቡ ሽጠው በሃብት ላይ ሃብት ሲያካብቱ ይታያል። በኢንቬስትመንትናአ ልማት ስም ደግሞ ጥቂት ባለሃብቶች በሊዝ መሬቱን እየገዙ በአካበቱት ሃብት ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ሲገነቡ ይታያሉ። መሬቱንና ሃብቱን በግፍ የተቀማው ብዙሃኑ ሕዝብ ግን ለከፋ ድህነት ተጋልጧል» ያለው ኦፌኮ በመግለጫው፣ የአገዛዙ ጥቂት ባለስልጣናት፣ መሬትን እየሸጡ ትክቅ ዝርፊያ እያደረጉ እንደሆነም መግለጫ ይከሳል።

በጋምቤላ ፣ በባህር ዳር ፣ በትግራይ ….በኢንቨስትመንት ስም ዜጎች እንደተፈናቀሉ፣ በአምቦ አካባቢ፣ በጉዱ ፈርዳ፣ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ « ከኛ ብሄር ብሄረሰብ አይደላችሁም። ይሄ አገራችሁ አይደለም» በማለት ዜጎችን በግፍ የማባረር የዘር ማጽዳት ወንጀሎች እንደተፈጸሙ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል።

ኦፌኮ አሁን በኦሮሞ ገበሬዎች ላይ ደረሰ በሚለው ግፍ እንደተቆረቆረ፣ በሌሎች ዜጎች ላይ አሳዛኝ ክስትቶች ሲፈጸሙ ፣ በተለይም በኦሮሚያ ዉስጥ ኦሮሚያ ለኦሮሞዎች በሚለው፣ በኦሮሚያ ሕግ መንግስት ላይ በተቀመጠው ፖለቲካ ምክንያት፣ ኦሮሞ ያልሆኑ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲቆጠሩና ፣ «አገራችሁ አይደለም» ተብለው ሲፈናቀሉ፣ መግለጫ የሰጠበት ሁኔታ እምብዛም እንዳልነበረ የሚናገሩት ተንታኞች ፣ በኦፌኮ መግለጫ የተነበበው፣ ዜጎችን የማፈናቀል ተግባርን የመቃወም ሁኔታ፣ በሌሎች ወገኖች ላይ ሲደርስ መሰማት እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

ኦፌኮ የመድረክ አባል ድርጅት ሲሆን፣ አሁን ያለዉ የፌዴራል አወቃቀር እንዳይለወጥ፣ መሬትም የመንግስት መሆን አለበት ብሎ የሚከራከር ደርጅት እንደሆነ ይነገርለታል። ሌላው የመድረክ አባል የነበረዉ አንድነት፣ በቅርቡ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የደረሰዉን ግፍ አዉግዞ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ በፌዴራል አወቃቀርን እና በመሬት ባለቤትነት ዙሪያ ከኦፌኮ ጋር ልዩነት እንዳለው፣ በዚህ ምክንያት በመድረክ ዉስት ዉህደት ሊፈጠር እንዳልተቻለና አንድነት ከመድረክ በተግባር የተለየ፣ በኦፌሴል ግን ሊለይ የደረሰ ድርጅት እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ነው።

የኦፌኮን ሙሉ መግለጫ በቁቤና በአማርኛ

OFC_letter_April2014_6
የኦፌኮን ሙሉ መግለጫ በቁቤና በአማርኛ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !