አቡጊዳ – ሲቀሰቅሱ የታሰሩ የአንድነት አባላት ተፈቱ ፤ ቅስቀሳው ተጧጡፏል( ፎቶዎችን ይዘናል)
የአንድነት ፓርቲ አባላት፣ ከትላንት ማክሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን ጀምሮ፣ በሃያ ሶስቱም ወረዳዎች፣ በየመንደሩ በስፋት ቅስቀሳ እያደረገ እንደሆነ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለከትል። አልፎ አልፎ ፖሊስ ከፈጠራቸው መጠነኛ ችግሮች በስተቀር፣ ቅስቀሳዉ እስከአሁን በጥሩ ሁኔታ እየተደረገ እንዳለም ለማረጋገጥ ችለናል።
ትላንት በቅስቀሳ የተሰማሩ ስድስት አባላት ሜክሲኮ አካባቢ በፖሊስ ታግተው እንደነበረ መዘገባችን ይታወቃል። እስረኞቹ ፣ አንድነት የጠራዉ ሰልፍ ሕጋዊ እውቅና ማግኘቱን በማስረዳት፣ ትላንትናዉ ከእሥር ቤት እንደተለቀቁም አረጋግጠናል።
በዛሬው ቀን ደግሞ በካሳንቺስ አካባቢ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 6 የአንድነት ፓርቲ አባላት፣ አዛርያ መላኩ ሰፊው መኮንን ፣ ኤፍሬም ሰለሞን፣ በየነ አበበ፣ አበበ ቁምላቸው፣ ሻ/ል ክፍሉ በዳኔ ስኬታማ የቅስቀሳ ተግባራቸውን በሚያደርጉበት ጊዜ በፖሊስ ታግተው ወደ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የነበረ የነበረ ሲሆን ፣ እነርሱን ለጥቂት ሰዓት በእሥር እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ተፈተው ወደ ቅስቀሳቸው ተሰማርተዋል።
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ና በልደታ አካባቢ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ከነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል ኃይሉ ግዛው፣ ወርቁ አንድሮ እና ቴዎድሮስ ገብሬ በፖሊስ በፖሊሲ ታግተው ወደ ወህኒ ከተወሰዱ በኋላ ተፈተዋል።








