በአራት ዪኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፓልን በመቃወም ተቃዉሞውውቸዉን አሰሙ። በዉጭ አገር የሚገኘውና በቅርቡ የተቋቋመው የኦሮሞ ሜዲያ ንቴዎርክ ማስተር ፓልኑን በመቃወም ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ የነበረና የሚገኝ ሲሆን፣ በዶር መራራ ጉዳናን የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን ጨመሮ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች ፕላኑን አዉግዘዋል። የኦሮሞ ተማሪዎች ም በአምቦ፣ በወለጋ፣ በጂማና በሃረማያ ሰላማዊ በሆነመንገድ […]

ማዕከላዊን በከፊል አውቀዋለሁ፡፡ ትናንት ሰባት የሚሆኑ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮችና አክቲቪስቶች መታሰራቸውን ተከትሎ ወደ ማእከላዊ መወሰዳቸውን ሰምተናል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ጨለምተኛ ልመስል እችል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይኸው ነው፡፡ መጀመሪያ ክሱ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጊ ጥያቄ ነው፡፡ ይህን ለማወቅ ወሳኝ ፍንጭ የሚሰጠው የቤት ፍተሻው ነው፡፡ የታሰሩትን ሰዎች ቤት የሚፈትሹት ፖሊሶችና መርማሪዎች ቤቱን […]

ሰማያዊ በመባል የሚታወቀውና የወጣቶች ፓርቲ እንደሆነ አዘወትሮ የሚናገረው ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት በወጣ ልሳኑ ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ላይ ታዋቂውን ኢትዮጵያዊ ምሁርና በተቃውሞ ጎራ እድሜ ሳይገድባቸው ትግል እያደረጉ ያሉትን ምሁር ዶ/ር ኃይሉ አርአያን አሰደበ፡፡ የፓርቲው ልሳን ዶ/ር ሃይሉን ለመሳደብ የተገደደው የሚል ጠንካራ አቋም ስላላቸው ሲሆን ሳሙኤል አወቀ በተባለ ጎረምሳ ፀኃፊ በኩል ተብለው መገለፃቸው ብዙዎችን ያሳዘነ ሲሆን ከኢትዮጵያዊ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የመንግስታቸውን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ለፓርቲያቸው የፓርላማ አባላት ባቀረቡበት ወቅት(ሁለት ወንበር ከማጣታቸው ውጪ) ‹‹ዴሞክራሲያዊነት ለመንግስታቸው የህልውና ጉዳይ ››እንደሆነ አውስተው ነበር፡፡ልማታዊ በመሆናችን ዴሞክራሲን እንደ ትርፍ ነገር የምንቆጥር የሚመስላቸው ተሳስተዋል ለማለት አስረግጠው ሲናገሩ አድምጬ ነበር፡፡ ኢህአዴግ በየጊዜው የፖለቲካ አክሮባት እየሰራ ንፋሱ እንደወሰደው ከአንዱ ርዕዩተ ዓለም ወደ አንዱ እንደፌንጣ እየዘለለ ‹ልማታዊ ወ ዴሞክራሲያዊ ነኝ› እያለን ነው፡፡ድርጅቱ […]

በማዕከላዊ የሚገኙ የዞን ዘጠኝ አባላትን ከተፈቀደልን ለመጠየቅ ካልሆነም የታሰሩበትንና ፍርድ ቤት የሚቀርቡበትን ቀን ለማወቅ ወደ ስፍራው ዛሬ ማለዳ አምርተን ነበር፡፡የጦማርያኑ ቤተሰቦች ያመጡትን ምግብ ከማቀበል ውጪ ማንንም ሊያናግሩ እንደማይችሉ ተነግሯቸው በሐዘን እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ መቼ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ለሚለው ጥያቄም ኃላፊነት ወስዶ የሚናገር አካል በመጥፋቱ ማወቅ አልተቻለም፡፡ለምን ታሰሩ ለሚለው ጥያቄ ግን መልስ ከተባለ‹‹ ተረጋጉ መስማታችሁ መቼ ይቀራል››ተብሏል፡፡ […]

ከአዲስነገር ጋዜጣ አባላቶች መሰደድ እንዲሁም ከውብሸት እስክንድር እና ርእዮት አለሙ መታሰር በሁዋላ ለእኔ መንግስት በሚዲያ ሰዎች ላድ በጅምላ የወሰደው ትልቅ ክስረት ነው። ፅሀዮ መንግስታችንም የኢትዮጵያውያን በነፃነት የመኖር ህልም ማጨናገፉን ስራዮ ብሎ ተያዞታል ምን ያህል እንዳዘንኩኝ አላውቅም ብዙ ሰው ስለሀገሬ አያገባኝም ባሉበት ሰአት ስለሚያገባን እንጦምራለን( እንፅፋለን) በማለት ለሀገራቸው ያላቸውን ቀና ነገር በበሳል ብእራቸው ሲፅፉ ነው የማውቀው። […]

ከአርብ ሚያዚያ 17 ቀን ጀምሮ ኢሕአዴግ ዞን ዘጠኝ ተብለው በሶማል ሜዲያ ምህበረሰቡ የሚታወቁ ወጣት ጦማሪያንን ( ብሎገርስ) እንዲሆም ሌሎች ጋዜጠኞችን አይሰረ ሲሆን፣ እስረኞቹ ትልናት እሁድ ሚያዚያ 19 ቀን ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ታወቀ። የታሰሩ የዞን9 አባላትና ጋዜጠኞች ትላንትና እሁድ ሚያዝያ 19 አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ቤተሰብ ሳይወቅ እና የሕጝ ባለሞያ በሌለበት ሁኔታ ሲሆን፣ […]

ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 6ቱ ማለትም ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት፣ አጥናፍ ብርሀን፣ አቤል ዋበላ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጋዜጠኛ አስማመው ኃ/ጊዎርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያየ […]

በመድረክ እና በአንድነት መካከል ስላለው ግንኙነት ሁለት ኢትዮጵያዊያን የጻፉትን አነበብኩ። ዶር መሳይ ከበደ፣ መድረክ ዉስጥ ባሉ የዘዉግ ደርጅቶች እና በአንድነት ፓርቲ መካከል ያሉት የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶች የማይታረቁ መሆናቸውን በመገልጽ፣ አንድነት ጊዜዉን እና ጉልበቱን እነዚህ የዘዉግ ድርጅቶችን በማባበል ላይ ከማጥፋት፣ ከሌሎች አገር አቀፍ ድርጅቶች ጋር አብሮ እንዲሰራና እንዲዋሃድ ይመክራሉ። አቶ ዳዊት ተሾመ በበኩላቸው፣ ለዶር መሳይ መልስ […]

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ አመት የምህንድስና ተማሪ የሆነው ዮናስ ከድር ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ሲቀሰቅስ ተይዞ ጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ያለ ተማሪ በፖሊስ ታጅቦ ፈተናውን የመፈተን መብት ቢኖረውም ዮናስን ግን ‹‹አንተ የፖለቲካ እስረኛ ነህ፣ አንተን አጅበን ማስፈተን አንችልም፣ አንተን የሚያጅብ ፖሊስ የለንም!›› የሚሉ የተለያዩ ምክንያችን በመደርደር ለፈተና እንዳይቀርብ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች (እደግመዋለው) የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ህገመንግስቱን ተመርኩዘው የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄዎችን በመያዝ ወኪሎቻቸውን በመምረጥ ህጋዊ ውክልን በመስጠት ወደ ገዢው መንግስታዊ ቡድን ህግን አንብበው ለይተው አውቀው መብታቸውን እና ግዴታቸውን ተረድተው አቤቱታቸውን ለማሰማት በሄዱበት የወይኔው ስርአት እንኳን ደህና መጣችሁ በሚል የህሰት ወንበዴያዊ ፈገግታ በአስመሳይ ሰላም እና ፍቅር አቅርቦ እውቅና የሰጠ በማስመሰል ደም በተለወሱ ጥርሶቹ ነክሶ ለመያዝ እና ለአገዛዙ […]

መብራት ውሃ የስልክና የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎቶች መብቶች የህዝብ ናቸው!!!!! -ምንሊክ ሳልሳዊ አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ ነው …ይህ ደሞ ለየት ባለ መልኩ አብዮታዊ ነው:: እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልፍ ስፍራ የለውም:: እርስ በርሳቸው […]

የሰው ልጅ ግላዊና ማህበራዊ ህይወቱን ለማሻሻል እንዲሁም የለት ተለት ህይወቱን የተሻለ ለማድረግ በአካባቢው ወይም በሚኖርበት ሃገር ያለውን አካባቢያዊና መንግስታዊ ስርዓት ጤናማ መሆኑ ግድ ነው። የማህበረሰቡም የለት ተለት ህይወት ከግዜ ወደ ግዜ አስቸጋሪ እየሆነ ሲሄድ የዛ ማህበረሰብ መንግስት ወይም አገዛዝ መቀየሩ አንደኛው መፍትሄ ነው። እንደሁለተኛ አማራጭ መፍትሄ የሚወሰደው ደግሞ የነበረውን አገዛዝ ለአነስተኛና ከፍተኛ ለውጦች ካለው ምቹነት […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሕገመንግሥታዊ መብቴን በመጣስ ቅስቀሳ እንዳላካሄድ ታግጃለሁ፤ አባላቶቼ ያለ አግባብ ታስረውብኛልና ያቀረብካቸው አማራጭ ቦታዎች ወደጎን ተደርገው ህጉ በማይፈቅድለት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳደርግ ተነግሮኛል በሚል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ላይ በመሰረተው ክስ የቀረቡትን የክርክር ሃሳቦች ያደመጠው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ […]

የአዲስ አበባና የኦሮምያ ግንኙነት የፌደራል ስርዓቱ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ጊዜ አንስቶ እያወዛገበ ያለ ጉዳይ ነው። በቅርቡ ደግሞ የአዲስ አበባ አስተዳደር የ10 እና የ25 ዓመት የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን በማዘጋጀት በተለምዶ “ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር ለማቀናጀት ጥረት መጀመሩ ተድበስብሶ ያለፈውን የፌደራሊዝም ጥያቄ እንደገና እንዲያገረሽ አድርጎታል። የተቀናጀ የጋራ ልማት […]

የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር እውቅና ሰጠ። አስተዳደሩ፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ አስፈላጊዉን የእውቅና ፎርም በመሙላት ወደ ሰልፍ ተግባራቱ መሰማራት እንደሚችል ትላንት ለፓርቲዉ በላከው ደብዳቤ ማሳወቁ ይታወቃል። በዚያ መስረት የሰማያዊ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ በአስተዳደሩ የተጠየቀዉን የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ቅጽ ፎርም በመሙላት፣ ዛሬ ሚያዚያ 16 ቀን አስፈላጊዉን […]

ፖለቲካ አንድ ሰው በአንድ ሃገር ወይም ህብረተሰብ ያለው ስርዓት ወይም የመንግስት ፖሊሲዎችንና አገዛዝን በተጨባጭ በመተንተንና በመገምገም ከአመለካከቱና ከዕምነቱ ጋር አገናዝቦ በመደገፍ ሥርዓቱ ወይም ሁኔታው እንዲቀጥል ለማድረግ ወይም በመቃወም ሥርዓቱ ወይም ሁኔታው እንዲቀየር ለማድረግ አቋም ይዞ አቋሙንም ተግባራዊ ለማድረግ የሚንቀሳቀስበት የሥራ ዓይነት (Business) ነው፡፡ ስለዚህም ትክክለኛ ፖለቲከኞች የመንግስት ሥልጣን የያዘውም አካልም ሆነ ያልያዙት እና ሌላ አማራጭ […]

ንቅናቄው የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃና ፍትሐዊ ምርጫ (Millions of Voices for Free & Fair Election) የሚል መሪ ቃል ይኖረዋል፡፡ ከህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ማክሰኞ ዕለት የአንድነት ስራ አስፈፃሚ አስቸኳይ ስብሰባ ካደረገ በኋላ ትግሉን ወደ ህዝቡ ማውረድና ህዝቡ የትግሉ ባለቤት እንዲሆን ለማስቻል የተጀመረው ንቅናቄ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ተወያየ፡፡ ስራ አስፈፃሚው ወቅቱ 24 ሰዓት የሚሰራበት መሆኑን […]

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሚያዚያ 15 ቀን ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሊያደርግ ላሰበው ሰላማዊ ሰልፍ፣ በአስተዳደሩ ሕጋዊ አሰራር መሰረት፣ የሚገባዉን የእውቅና ፎርሞ እንዲሞላና ወደ ቅስቀሳ እንዲሰማራ ጠየቀ። «የእወቅና ጥያቄ ፎርም ሳትሞሉ ሕጉን በመጣስ ወደ ተለያዩ የተግባር እንቅስቃሴ የገባችሁ ስለሆነ ከዚሁ ተግባራችሁ ታቅባችሁ ወደ ህጋዊ አሰራር በመግባት ማሟላት የሚገባችሁን አማልታችሁ የ ወቅና […]

የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን በአዲስ አበባ ለጠራው ሰልፍ፣ ቅስቀሳ ያደረጉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ በፌስ ቡክ ገጹ ገለጸ። በአዲስ አበባ አስተዳደር አካባቢ ከተገኙ ምንጮቻችን በደረሰን ዘገባ መሰረት፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከደህንነት ሃላፊዎች ፣ ሚያዚያ 19 ቀን ለሰማያዊ እንዲፈቀድ መመሪያ መስጠታቸውን በመግለጽ ፣ «እስከ አሁን የሰማያዊ ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ የእውቅና ደብዳቤ […]

[email protected] ከፋሲካ/ትንሳኤ ቀን (ሚያዚያ 12) በስተቀር፣ ከመጋቢት 28 ጀምሮ ያሉ እሁዶችን ( መጋቢት 28 ፣ ሚያዚያ 5፣ ሚያዚያ 19 ቀን) የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ለማድረግ ቢያሳውቅም ከአስተዳደሩ እውቅና እስከአሁን ማግኘት አልቻለም። አገዛዙ የአንድነትን ሰልፍ ለምን እንደፈራ አልገባኝም። አንድነት ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ያለው እንደመሆኑ ሚሊዮኖች ይመጣሉ የሚል ጥርጣሬ ስላለም ሊሆን ይችላል። በአንጻሩ ሌላ የፖለቲካ ድርጅት የሰማያዊ ፓርቲ፣ […]

ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና እንደሚጠቁመው፣ የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 19 ሰልፍ ለማድረግ ቢጠይቅም፣ የፖሊስ አዛዞች በዚያን ቀን በቂ ጥበቃ ማዘጋጀት አንችልም በማለታቸው፣ አስተዳደሩ ሚያዚያ 26 ቀን እንዲደረግ ጠይቆ የነበረ ሲሆን፣ ለሚያዚያ 26 የእውቅና ደብዳቤ ለመዉሰድ ወደ አስተዳደሩ ጽ/ቤት ያመሩት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች፣ የእውቅና ደብዳቤ ሳይቀበሉ መመለሳቸውን ያነጋገርናቸው የአንድነት አመራር አባል ገለጹ። የአስተዳደሩ ሃላፊዎች፣ ከደህንነት ጽ/ቤት ለአንድነት […]

ሀገር የመገንጠል ዓላማ ይዞ የተነሳው የህወሓት ጁንታ፣ በስውር እና በአደባባይ የጫካ ልማዱን መሰረት አድርጎ ሲገድል መኖሩ አዲስ ባይሆንም፣ ከሰሞኑ መረር ያለ እርምጃ ‹‹ግድያ›› ማሰቡን ከጓዳው የወጣ የወሬ ምንጭ ደረሰን፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት ተገኝቼ ነበር፡፡ የመገኘቴ ዓላማም የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 26 የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የዕውቅና ደብዳቤውን ለመስጠት የተያዘውን ቀጠሮ በማክበር ነበር፡፡ […]

—— በአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር መሆናቸውን ለስድስት በተዳበሏት ቢሮ ውስጥ በምትገኝ ጠረጴዛ ጠርዝ ላይ የተቀመጠች ማስታወቂያ ትመሰክራለች፡፡ ግለሰቡ አቶ ማርቆስ ብዙነህ ይባላሉ፡፡የተዳከመ ገጽታ ተላብሰው ያደረጓትን ነጠላ ጫማ በእግራቸው እያጫወቱ እንግዶችን ይቀበላሉ፡፡ሲናገሩ እጅግ በጣም በዝግታ በመሆኑም የሚሉትን ለመስማት ጆሮን ፈገግታ ወደ ተለየው ፊታቸው ማስጠጋት ግድ ይላል፡፡ ከፊታቸው የቀረበላቸውን ወረቀት እየተመለከቱ ‹‹ ተነጋግረን መልስ […]

በተያዬ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲን የሚመለከት በርካታ ጽሁፎችን ለማየት ሞከርኩ ሁሉም ሰማያዊ ፓርቲን የሚወቀሱ ሆነው አገኘኋቸው፡፡ እኔ በእርግጥ ሰማያዊ ፓርቲ በተደጋጋሚ ብቻውን በመሄድ የዚህን ሀገር ትግል እንደሚለውጥ ሲናገር መስማቱ የዕለት ተዕለት ጉዳይ ሆኖ ቢሰነብትም ቅሉ በእነርሱ ከመቀየም ፓረቲውን ወደፓረቲ ደረደጃ እንዲድግ ቢሰራ ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ የተናጠል ጉዞ ደግሞ በርካቶች የጠሉት ይመስላል፡፡ እኔ ግን […]

ማንነታቸው ግልጽ ያልሆኑ የደህንነት ሰራተኞች፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት፣ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲያደርግ እውቅና ሊሰጥ እንደሆነ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አካባቢ ያሉ ምንጮቻችን ገለጹ። አስተዳደሩ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፉን ለማድረግ፣ አስቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ደብዳቤ ቢያስገባም፣ በዚያ ቀን ሌሎች ዝግጅቶች ስላሉ ለሚያዚያ 26 ቀን ለሰልፉ እውቅና እንደሚስጡ ባሳወቁት መሰረት፣ የአንድነት ፓርቲ […]

“የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልስ” በሚል መሪ ዓላማ ስማያዊ ፓርቲ ያደረገው ጥሪ የተከበረ ግብ ቢሆንም፤ ውጥንቅጥና ውስብስብ በሆነው፡ ሕወሃት በፈንጂ ባጠረው የተግል ጎዳና የሰማያዊ ፓርቲ ብቸኛ ጉዞ መምረጡን በክፍተኛ ኃዘንና ቅሬታ እንድመለከተው ተገድጃለሁ። ጥያቄው ስማያዊ ፓርቲን የመቀበልና አለመቀበል ጉዳይ መደረግ የለበትም። መግለጽም ካስፈለገ፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አድናቆት አለኝ። ይህንንም በተደጋጋሚ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ አስረግጬ መስክሪያለሁ። በኢትዮጵያና […]

“የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።…” የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ “የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነቁ። ሰው […]

ሶስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ገብተዋል “ረብሻውን ያነሱት ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው” የከተማው ኮሙዩኒኬሽን “ባህርዳር በተካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት የተቧደኑ ወጣቶች፣ ባለፈው ሐሙስ የሱሉልታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ በድብደባ በርካታ ሰዎች ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ፤ ቤት ንብረት ላይም ጥፋት እንደደረሰ የተናገሩት ጉዳት […]

የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ለማድረግ ላሰገባዉ የማሳወቂያ ደብዳቤ ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ምላሽ እንዳገኝ ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ። የአስተዳደሩ ደብዳቤ፣ ሰልፉን በታሰበው ሚያዚያ 19 ቀን፣ ማድረግ እንደማይቻልና ለሌላ ቀን እንዲያስተላልፈው የሚጠይቅ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ ግን፣ ለሰልፉ መራዘም የቀረቡት ምክንያቶች በቂ አይደሉም በሚል፣ ቀኑን እንደማይለወጥ፣ ባስገባው ሁለተኛ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አሳዉቋል። የሰማያዊ ፓርቲ በላከው ሁለተኛ ደብዳቤ፣ […]

የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንዳገኘ መዘገቡ ይታወቃል። አንድነት ሰልፉን መጋቢት 28 ቀን ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር በተባለው ቀን እውቅና ባለመስጠቱ፣ የተለያዩ ዝግጅቶ በመኖራቸውና የአመት በዓላትም ጊዜ በመሆኑ፣ ወደ ሚያዚይ 26 መሸጋገሩን የአመራር አባልቱ ይገልጻሉ። በዚህ ሂደት ከአስተዳደሩ ጋር በርካታ የደብዳቤ ልዉዉጦች የተደረጉ ሲሆን፣ […]

የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንደገኘ መዘገቡ ይታወቃል። በተመሳሳይ ሁኔተ የሰማይዊ ፓርቲ ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዚያ 19 ቀን በጃን ሜዳ ሰልፍ መጥራቱን ገልጿል። አስፈላጊዉን የማሳወቂያ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ እንዳሰገቡ ሰማያዊቾ ቢገልጹም፣ በተባለው ቀን ከአስተዳደሩ እውቅና ይሰጣቸው አይሰጣቸው እስከ አሁን የተወቀ ነገር የለም። ሰልፉን በጋራ መጥራት ለምን […]

«ህግን አክብረን ለድርድር የማናቀርበውን ህገመንግስታዊ መብታችንን አሳልፈን አንሰጥም። ታላቁ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 26፣2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይደረጋል፡፡» ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ገለጹ። ፓርቲዉ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አስፈላጊዉን እውቅና ያገኘ ሲሆን ፣ ከትንሳኤ በዓል በኋላ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎችና በአዲስ አበባ […]

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ። የሰልፉ ቀን ወይንም ቦታ እንዲቀየር የመጠየቅ እንጂ በጥቅሉ ለቀረቡት የሰልፍ ጥያቄዎች እውቅና አንሰጥም የማለት መብት አስተዳደሩ እንደሌለው በመጥቀስ፣ በአስተዳደሩ የተላከዉን […]

ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችn እጅግ በጣም ከባድና ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ለሰላም፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት ፣ ለነጻነትና ለኢትዮጵያ አንድነት፣ እልህ አስጨራሽ ትግል እያደረጉ ነው። «ሽብርተኞች ናቸው» በሚል በቃሊት ፣ በቂሊንጦ፣ ዝዋይ በመሳሰሉ ዘግናኝ እሥር ቤቶች እየማቀቁ ያሉ ፣ የሰላምና የዴሞክራሲ አርበኞች የሆኑ፣ ብርቅዬ የኢትዮዮጵያ ልጆችን መመልከቱ ይበቃል። አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ በቀለ ገርባ፣ […]

የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደሚያደርግ አሳወቀ። ሰልፉ የሚደረግበት ቀን የዳግማይ ትንሳኤ ቀን ሲሆን፣ ለሰልፉ እውቅና ከአስተዳደሩ፣ ይገኝ አይገኝ ገና የታወቀ ነገር የለም። የአዲስ አበባ አስተዳደር ከአንድ አመት በፊት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ከአራት ኪሎ እስከ ጥቅር አንበሳ ጋር እስካለዉ ሃዉልት ድረስ፣ ሰልፍ እንዲያደርግ እውቅና መስጠቱ፣ ይታወቃል። ለሰማያዊ ተፈቅዶ በነበረበት ቦታ፣ መጋቢት 28 ቀን […]

በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ሀገሪቱን ተቆጣጥሮ ስልጣን ከያዘ 23ዓመት አስቆጠረ። ይህን ያህል አመት በስልጣን ቆይቶ ህዝቡን በሰላም መምራት አልቻለም። ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ነፃ አውጥቻለሁ፣ ሀገሪቱንም እያሳደኩ ነው..ቢልም ህዝቡ ግን፥ ኑሮ ተወደደ፣ ሀገራችን ተከፋፈለች፣ ዲሞክራሲ የለም፣ ሰብአዊ የመብት ረገጣ እየተፈጸመ ነው በማለት ማማረሩን ቀጥሎዋል። ከብዙ ኢትዮጵያውያኖች ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ገብቶዋል። […]

በታዋቂዉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራዉ የሶሊዳሪቲ ንቅናቄ፣ የሚሊዮኖች ድምድ ለመሬታ ባለቤትነት እና ለፍትህ እንቅስቅሴን እንደሚደገፍና የእንቅስቃሴዉም አካል እንደሚሆን ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ። ሶሊዳሪቲ «እኛም ከሚሊዮኖች አንዱ ነን» በሚል ባወጣዉ መግለጫ፣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንቅስቃሴዉን እንዲቀላቀሉና የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስቧል። በግለሰብ ደረጃ ተራ ሰዎች ብንሆንም፣ ከተባበረንና ሚሊዮኖች ከሆነን ፣ ሊቋቋመን የሚችል ምንም ኃይል እንደሌለ የገለጸው የሶሊዳሪቲ […]

‘ዜጎች ነንና ፍትሓዊ ልማት ያስፈልገናል’ ሲንል አሰሩን። ‘ደማችን ገብረናልና ሰለማዊ ሰልፍ የመውጣት መብታችን ይከበርልን’ ስንል ደበደቡን። ‘ብዙ መስዋእት ከፍለናልና ነፃነታችንን አትንፈጉን’ ስንል ትጥቃችንን አስፈቱን። መብታችንን ለማስከበር ስንሞክር ገደሉን። ግን ይህን ሁሉ ወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የከፈሉት መስዋእት ዓላማው ምን ነበር? ደርግን ደምስሶ ሌላ ደርግ መመስረት? ይሄማ ሊሆን አይችልም። ደርግ’ኮ ደርግ ያሰኘው ተግባሩ ነው። ደርግን የምንጠላው ደርግ […]

መጋቢት 28 ቀን ይደረጋል ተብሎ የተጠበቀዉ የአንድነት የእሪታ ቀን ሰልፉ ፣ «ሰልፍ እንዲደረግ በታሰበበት ቀን፣ ሌሎች ዝግጅቶች ስላሉ በቂ ጥበቃ ልናሰማራ አንችልም» በሚል እውቅና ባለመስጠቱ ለሚያዚያ 5 ቀን መተላለፉ ይታወቃል። የሚያዚያ አምስቱን ሰልፍ በተመለከተ ምላሽ የሰጠው የአዲስ አበባ አስተዳደር፣ በሚያዚያ 5 ቀን ፣ ሩጫ ስለሚኖር ሰልፉ ለቅዳሜ ሚያዚይ 4 ቀን እንዲደረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለአንድነት ፓርቲ […]

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሁለተኛውን የሕዝብ ንቅናቄ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ፓርቲው ከዚህ ቀደመ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የሕዝባዊ ንቅናቄ መድረኮች አዘጋጅቷል። አሁን ደግሞ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪ ቃል ፕሮግራሙን ይፋ አድርጓል። ባለፈው እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በደሴ ከተማ ፕሮግራሙን በሰላማዊ ሰልፍ አከናውኗል። በደሴ ስለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍና “የሚሊዮኖች ድምፅ […]

የማርቆስ ብዙነህ ደብዳቤ፤ 1- “በርካታ ትምህርት ቤቶች፤ ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ፤ የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን” ይላል፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ክፍል ሀላፊ፤ በአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማንደፍሮ፤ መጋቢት 23 ቀን 2006/2014 የተፈረመው ደብዳቤ፡፡ አንድነት፤ ሰልፉን ለማድረግ ያቀረባቸው መስመሮች 3 ሲሆኑ፤ ሶስቱም መስመሮች […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ሊያደርገው ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የመስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍና ማሳወቂያ ክፍል ዘግይቶ በጻፈው ደብዳቤ የሰልፉ ቀን በሌላ ፕሮግራም መያዙን በመጥቀስ የቀን ለውጥ እንዲደረግ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡ ፓርቲው የቀረበውን አስተያየት በመቀበል ሰልፉ ለሚያዚያ 5 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን በመግለጽ ለመስተዳድሩ አሳውቋል፡፡ሆኖም መስተዳድሩ ዕለቱ በታላቁ ሩጫ መያዙን በመጥቀስ ለፖሊስ ጥበቃ […]

የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በአገሪቷ ዉስጥ ባሉ አሥራ አራት ከተሞች፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። እንቅስቃሴ በደሴ ሰላማዊ በማድረግ የተጀመረ ሲሆን፣ በሌሎች ከተሞች ከአንድነት ጽ/ቤቶች ወደ አደባባይ በሚሄድ ትይንተ ሕዝቦች በማድረግ ይቀጥላል። በደሴ ከተማ የተደረገዉን እንቅስቃሴ በደንቬር የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ስፖንሰር ያደረጉት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚደረገዉን የመጀመሪያው እንቅስቅሴን ላስ ቬጋሶች፣ ሃዋሳ አትላንታዎች፣ ድሬደዋን የደብተራ ፓልቶክ ክፍል፣ […]