አቡጊዳ – ሜክሲኮ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጩ የተንቀሳቀሱ የአንድነት አባላትን ፖሊስ አገተ
የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 26 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ የእውቅና ደብዳቤ እንደሰጠ ቢታወቅም፣ ሕጉን ተከትለው ሰላማዊ የሆነ የቅስቀሳ ሥራ በመስራት ፣ ለሕዝቡ በራሪ ወረቀቶች ሲያድሉ የነበሩ ስድስት የአንድነት አባላት ሜክሲኮ አካባቢ በፖሊስ ተይዘው፣ በእሥር ላይ እንደሚገኙ፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል አሳወቀ።
አስተዳደሩ ለአንድነት ፓርቲ በሰጠዉ የእውቅና ደብዳቤ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፣ ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ለዉስጥ ደህንነት ዋና መምሪያ፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን እና ለአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ፣ ግልባጭ ደብዳቤ የተላከ ሲሆን፣ ፖሊስ በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች እውቅና ያገኘን እንቅስቃሴ ለማሰናከል፣ ሰላማዊ ዜጎችን ማገቱ፣ ምን ያህል አንዱ የሚወስነውን ሌላ የሚሽርበት፣ አንዱ የፈቀደዉን ሌላው የሚከለክልበት፣ አገሪቷን ማን እየመራ እንደሆነ የማይታወቅበት ሁኔታ እንዳለ የሚያመለክት መሆኑ ብዙዎች ያናገራሉ።
የታሰሩ እስረኞች ስም ዝርዝር የሚከተለው ናቸው፡
ዳን ኤል ፈይሳ
አበበ ቁምላቸው
አብነት ረጋሳ
ሳሙኤል ይትባረክ
አያክሉህም ጀንበሩ
ዳግማዊ ተሰማ
http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/04/udj_permit.jpg