አቡጊዳ – እሁድ ሚያዚያ 29 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በጊዶሌ እንደሚደረግ የሚሊዮኖች ድምጽ አስታወቀ

አንድነት ፓርቲ፣ በአዲስ አበባ ሚያዚያ 29 ለሚያደርገው ሰላምዊ ሰልፍ ከፍተኛ ቅስቀሳ እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል። የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ፣ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ፣ በአገሪቷ ክፍሎች ሁሉ ሕዝቡን ለመብቱና ለነጻነቱ ለማደራጀትና ለመቀስቀስ በበርካትከ14 በሚበልጡ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን ሕዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚይደርግ ይፋ አድርጎ በነበረው መሰረት ፣ የአዲስ አበባ ሰልፍ በሚደረግበት ቀን፣ በደቡብ ክልል በደራሼ ወረዳ የጊዶሌ ከተማ ታልቅ ሰላምዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ታውቋል።

ሰልፉ እንዲደረግ በዋናነት የጠየቀዉ ህዝቡ ሲሆን፣ አስፈላግዊ ዝግጅት እንደተደረግም ለማወቅ ተችሏል። የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባላት ወደ ስፍራዉ ነገ እንደሚሄዱ የተገልጸ ሲሆን፣ የደራሼ ሕዝብ በርሱ አነሳሽነት ለመብቱን ለነጻነቱ መነሳቱ ለብዙዎች ትምህርት ሰጪ እንደሆነም ብዙዎች ይናገራሉ።
gidole
ወደ ጊዶሌ ከሚሰማሩት የአንድነት ከፍተኛ አመራር መካከል፣ የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ አባልና የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ስዮም እንዲሁም የምእራብ ቀጠና፣ የአንድነት አደራጅ፣ የፓርቲዉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል፣ አቶ ብርሃኑ ይገኙበታል።