በመኪና ቅስቀሳ ማድረጉን ፖሊሲ ቢያከላክልም፣ ቅስቀሳ በሸገር ሬዲዩ ለሕዥብ ጆር ደርሷል – ቪዲዮ ይዘናል

ፖሊስ በመኪና፣ወረቀት በመበተንና ፖስተር በመለጠፍ መቀስቀስ አይቻልም በማለት እስር እየፈጸም ቢሆንም፣ ቀዳዳዎቹን በሙሉ በመጠቀም የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጹን እንዲያሰማ፣ አንድነት በሸገር ኤፍ ኢም 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ ማስታወቂያ እንዲነገርለት ተገቢውን ክፍያ በመፈጸም የመጀመሪያው ጥሪ ዛሬ እንዲተላለፍ መድረጉን ለማወቅ ችለናል።

ኢቲቪ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻ ማስታወቂያቸዉን እና ፕሮግራሞቻቸዉን ለሕዝብ እንዲያስተዋውቁ ማድረግ የነበረበት ቢሆንም፣ አሁን አንድነት እንድ ሌሎች የቢራ፣ የሳሙና ….የግል ኩባንያዎች ገንዘብ ከፍሎ በኢቲቪ ማስታወቂያ እንዲነገርለት ጥረት እየተተደረገ መሆኑን የደረሰን ዜና ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ሕዝብ የሚከተለዉን ነበር በሸገር ራዲዮ ያደመጠው !