በአዲስ አበባ የሉ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃዉሞ አሰሙ – (ቪዲዮ ይዘናል)

አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች፣ ተቃዉሞ እንዳሰሰሙ ገዳ.ኮም ድህረ ገጽ ዘገበ። ተማሪዎቹ የተለያዩ መፈክሮችን ያሰሙ የነበረ ሲሆን ፣ቁጥራቸው ከአምሳ እስለ መቶ እንደሚጠጋ በቪዲዮም የሚታየው ምስል ያመለክታል።

ተማሪዎቹ ያሰሟቸው የነበረ መፈክሮች በእንግሊዘኛ እና በአፋን ኦሮሞ ብቻ የነበረ ሲሆን ከመፍክሮቹም ዉስጥ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ነበሩ፡

Our rights should be respected !
Our freedom should be respected !
Stop killing oromos !
Stop killing students !
We need justice, We need democracy !
Oromo is not inferior !

ተማሪዎች ሰልፉን ሲያደርጉና ተቃውሟቸዉን ሲያሰሰሙ ከፖሊሲ ጋር የተፈጠረ ግጭት ስለመኖሩ ብዙ የተዘገበ ነገር እየለም።

ትላንት በአምቦ ከተማ በተነሳዉ ረብሻ ስድስት ሰላምዊ ዜጎችን እንደተገደሉና ሶስት ፎቆች እንደተቃጠሉ የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወቃል። ዛሬ በወጡ የተለያዩ ዘገባዎች፣ በአምቦ ከ18 በላይ ፣ ስምንቱ የሚሆኑት ተማሪዎች፣ በጥይት እንደተገደሉ የሚያትቱ ዜናዎ በስፋት እየተዘገቡ ነው።

በተያያዘ ዜና በጊምቢ፣ ወለጋ፣ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን ላይ ጥቃት እንደደረሰም የሚጠቁሙ ምንጮች ደርሰዉናል። ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎችን ባለቤትነት፣ ሥር ያሉ ሱቆች በአክራሪዎች መቃጠሉን የደረሰን ዜና ያመለክታል።