የኦሎምፒክ ውድድሮች ኣጀማመር፣ የታሪክ ድርሳናት እንደሚጠቁሙት፣ ከ2700 ዓመታት በፊት ነበር፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ 776 ዓ ዓለም ገደማ መሆኑ ነው፣ በጥንታዊቷ ግሪክ፣ ኦሎምፒያ በምትባል ከተማ።

የጀርመኑ የልማት ትብብር ሚኒስቴር ጌርድ ሙለር ባለፈዉ ዓርብ በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከአፍሪቃ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት አፍሪቃ በሀገራቸው የውጭ ፖሊሲ ላይ ትልቅ ትኩረት ማግኘቷን አስታወቁ። ሚንስትሩ እንዳስረዱት፣

የካቲት  ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማው ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ፣ የግል ባለንብረቶችና ባለታክሲዎች በመላ አገሪቱ የጠፋውን ነዳጅ ተከትሎ ነዳጅ ለማግኘት ላይ ታች እየተንከራተቱ ሲሆን፣  የነዳጅ መጥፋቱን  ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፊም  ጨምሯል። ዘጋቢያችን እንዳለው ዛሬ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ 0.25 ሳንቲም ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ተገዷል፡ ነዳጅ ማደያዎችን ተዘዋውሮ የተመለከተው ዘጋቢያችን፣ በከተማው የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች …

የካቲት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታህሳስ ወር 2006 ዓም ጀምሮ በመዲናዋ  ሌሊት የሚጻፉ  የተቃውሞ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ትናንት ሌሊት በአስኮ መስመር ጀኔራል ዊንጌት ከሚገኘው አደባባይ ጀምሮ አወሊያ፣ካኦጄጄ፣ አስኮ የሚወስደውን ዋና መንገዱን በመሃል በሚከፍለው እስከ 2.5 ሜትር ቁመት ባለው ግድግዳ ላይ የሙስሊሙን የመብት ጥያቄና የትግል ቀጣይነት የሚያንፀባርቁ ጽሁፎች በተለያዩ …

ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ዋናው ምንጩ በሆነው፤ እ.አ.አ በ2013 (2006 ዓ/ም) ታትሞ ለንባብ በደረሰው፤ ካርልሔንዝ ዴሽነር (Karlheinz Deschner) “እግዚአብሔርና ፋሺሽቶቹ – የቫቲካን ሕብረት ከሙሶሊኒ፤ ፍራንኮ፤ ሒትለርና ከፓቬሊች ጋር” “God and The Fascists – The Vatican Alliance with Mussolini, Franco, Hitler, and Pavelic” በተሰኘው መጽሐፍ በተካተተው ማስረጃ ላይ ነው። የጽሑፌ ዓላማም በፋሺሽቶች ኢትዮጵያ ላይ ስለ ተፈጸመው እጅግ […]

በያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ ፊስቡክ የመገናኛ መረብ ከተመሰረተ 10ኛ ዓመቱን ደፈነ። በፊስ ቡክ ፤ህዝባዊ ቅስቀሳ፤ በፌስቡክ አብዮት፤ በፌስቡክ መማመር፤ በፊስ ብክ ትዉዉቅ፤ እንዲሁም በፌስቡክ ስድድብ ሌላም ሌላም ይታያል። በአሁኑ ግዜ የኢንተርኔት አገልግሎት የማግኘት እድሉ ያላቸዉ፤ የፊስ ቡክ መረብን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ ናቸዉ።

ፓርቲያችን አንድነት በተደጋጋሚ ከገዥው ፓርቲ ህግን ከለላ በማድረግ እና የመንግስትን ሥልጣን በመጠቀም የሚደርስበትን ከፍተኛ አፈና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን የበላይነት ለማረጋገጥ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በተለይም ፓርቲያችን በመላው የሀገራችን ክፍል የዘረጋውን መዋቅር በህዝባዊ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ በማሸጋገር በአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅዱ መሰረት እያከናወነ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ እና በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባዔ […]

የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ፡፡ ፍኖተ ነፃነት ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ በአራት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ክስ ለመመስረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መዘገቧ ይታወሳል፡፡ በቅርቡ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ […]

በሐዋሳው ስብሰባ የተጠበቀው የምዝገባ ዐዋጁ ረቂቅ ለውይይት ሳይቀርብ ቀረ የዐዋጁ ጉዳይ በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ሊመከርበትና አቋም ሊያዝበት ይገባል የሰላም ዕሴት ግንባታ ሰነዱ በአወዛጋቢ ይዘቱ ለተጨማሪ ግምገማ እንዲዘገይ ተደረገ የሃይማኖት ወይም እምነት ተቋማትን ለመመዝገብና የዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት በሚል መዘጋጀቱ የተገለጸውን የዐዋጅ ረቂቅና አሠራሩን በመቃወም የሚካሔድ እንቅስቃሴ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ መገለጫ መኾኑን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር …

(ሊያነቡት የሚገባ ሰፊ ትንታኔ)

 በኃይሌ ላሬቦ

የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስ የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅምን ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ። ማንዴላ የሚደነቁት፣ በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣ ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ የጥርጣሬና የሟርት ዘመን ምልኪዎች

አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡
የሌሎችን ግብና አዕምሮ ማማለልንና ማዘናጋትን የሚያውቁበት ሰዎች እንዳሉ አንርሳ! ተስፋ በመስጠት እንደዳማና እንደ ቼዝ ጠጠር (ወታደር) በፈለጉት አቅጣጫ ይገፉናል፡፡ ፍላጐታችንን ያከበሩ በመምሰል ፍላጐታቸውን የሚያሟሉ ሰዎች አደገኞች ናቸው፡፡ ፀሐይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ አይደለም፡፡ ለነገ እበላዋለሁ የሚል ጅል ተኩላ ግን ምን ጊዜም አይጠፋም፡፡ ይህን ሁሉ የሚታዘብ ህዝብ እንዳለ የሚያውቅ ካለ የብልህም ብልህ ነው፡፡ በዚህ የተካኑ ሰዎችን በዐይነ – ቁራኛ ማየት ያባት ነው፡፡ ስሜትን ተቆጣጥሮ ደባና ሴራን ጠንቅቆ ማየትና በጠዋት መንቃት ተገቢ ነው፡፡ ድቀትና ዝቅጠት ሲያይል አሉባልታና ጥርጣሬ ይነግሳል፡፡

በእንዲህ ያለው ሰዓት አፍ – አዊ እየበረከተ፣ ልባዊና ተግባራዊ እየሳሳ ይመጣል፡፡ ይሄኔ መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ የአንድ ነገር ዋጋ በዚያ ተገልግለን በምናገኘው ጥቅም አይለካም፡፡ ይልቁንም ያንን ነገር ለማግኘት በምንከፍለው መስዋዕትነት ነው የሚለካው፡፡ አገር እንገነባለን ስንል ይህን ብሂል አለመርሳት ነው፡፡ ይሆነናል የምንለውን ሰው መርጠን ስንሾምም ይህንን አለመዘንጋት ነው፡፡ ባለሙያው እያለ ስለዚያ ሙያ የሚያወራ ሲበዛ ጠንቀቅ ማለት ያሻል፡፡

ህግ ብቻውን ሁሉን ጉዳይ አይጨርስልንም፡፡ አስተዋይ አመራር፣ አስፈፃሚና ተጠያቂነትን ገምጋሚ እንዲኖር ያሻል፡፡ ያ ደግሞ ግልጽነትን ልማድ የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡በምንም ዓይነት ግን የፖለቲካ ትግልን እንደማይተኩልን ማሰብ ተገቢ ነው! የፖለቲካ ትግል ከሁሉም በፊት መደራጀትን፣ ተደራጅቶም መስዋዕትነትን፣ በሀገር ላይ ለውጥ የማየት ልባዊ ስሜትን ይጠይቃል! በተግባር ሳይሆን አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ ተግባራዊና የሚለውን የሚተረጉም ማህበረሰብ ካልፈጠርን ሟርት ይበዛል ::

እውን ሻዐቢያ እና ህወሀት ተጣልተዋልን
(ሁኔ አቢሲኒያዊ)
ማማ እና የሾላ ወተት ሁለቱም ወተት ናቸው የሚለያቸው ነገር ቢኖር ማማ ማማ መባሉ ሲሆን ሾላ ደግሞ ሾላ መባሉ ነው እንደዚሁ ህወሀት እና ሻዐቢያም የስም እንጂ የይዘትም ሆነ የአላማ ልዩነት የሌላቸው ጸረ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ፀረ ኢትዮጵዊ መሆናቸው ሀቅ እና ምስጢር ያልሆነ ነው ይልቁንስ በዚህች አነስተኛ ጦማር ማሳየት የፈለኩት ሻዐቢያን አምነው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመቀየር ከኢሳያስ ጋር ስለተወዳጁ ወገኖቻችን ጉዳይ ነው
ምርጫ 2002 በተቃረበበት ወቅት በኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ቀረበ የተባለው እና በፊታውራሪ ህወሀቶች ጭምር ድጋፍ ተሰጥቶት ነበረ የተባለው የስልጣን እንልቀቅ ጥያቄ ውድቅ የተደረገው እኛ ስልጣን ከለቀቅን ሻዐቢያ በእጅ አዙር ሀገሪቷን ሊመራት ስለሚችል ስልጣን መልቀቃችን ሊታሰብ የማይችል ነው ሲሉ በተላላኪ ጋዜጠኞቻቸው በኩል አስነገሩ ብዙሀኑ ምስኪን የግል ጋዜጦችም ይህንን ጉዳይ አንስተው ከሁሉም ጆሮ እንዲዳረስ አደረጉ፡፡ ይህ ሁኔታ ወያኔ ኢህአዴግን በሁለት መንገድ ተጠቃሚ አደረገው እነርሱም፡-
1. ሻዐቢያ እውነትም ፀረ ኢትዮጵያዊ ነው ኢህአዴግ ከወደቀ ደግሞ ሻዐቢያ ኢትዮጵያን ይቆጣጠራል የሚለው አስተሳሰብ ውስጥ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ ጥልቅ ብሎ እንዲገባ ያስቻለ ሲሆን
2. በሌላ በኩል ዲያስፖራ ላይ የመሸጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነ ኦነግ ከኢሳያስ ጋር ተለጥፈው ለምን ውጤታማ ሳይሆኑ ቀሩ እንኳን ብለው ሳያጤኑ ሻዐቢያ የወያነ ጠላት ስለሆነ ለእኛ እና ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛው ኢትዮጵያን ነጻ የማውጫ መንገድ አስመራ ላይ መክተም ነው ብለው አውጀው የማይታመነውን ኢሳያስን አምነው አስመራ ከተሙ፡፡
እነዚህ ሁለት ከላይ የጠከስኳቸው ሁለት አብይት ጉዳዮች ወያኔን ተጠቃሚ ያደረጉ እንዲሁም የኢትዮጵያን ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ነበሩ፡፡
እውን ህወሀት እና ሻዐቢያ ተጣልተዋል ወይስ ጥላቸው ለሚዲያ እና ለህዝቡ ጆሮ ብቻ ነው?
ኤርትራ የከተሙ ፓረቲዎችስ ስለምን ውጤታማ አልሆኑም?
እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እስኪ በቅድሚያ ይህንን ሀሳብ በአዕምሯችን እናሰላስለው
ሻዐቢያ አሰብ የራሱ እንዲሁም የኤርትራ ንብረት እንደሆነ ያምናል
ህወሀትም አሰብ የኤርትራዊያን ንብረት እና ሀብት ነው ብሎ ያምናል
በተቃራኒው ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሰብ የኢትዮጵያ ነው አልፎም ተርፎ የኤርትራን መገንጠል የማይደግፉ ናቸው ታድያ የኛ ፓርቲዎች እንደምን ብለው ነው ኢሳያስን አምነው አስመራ ላይ የከተሙት እውን ኢሳያስስ አሰብ የኢትዮጵያ ናት ብለው የሚሰብኩት ተቃዋሚዎች ይሻሉታል ወይስ ኤርትራ ነጻ ሀገር ነች አሰብም የኤርትራ ነች የሚለው ወያኔ?
ህወሀት እና ሻዐቢያ በስልጣን ላይ ለመቆየት የማይገድሉት ሰው የማይቆፍሩት መሬት የለም በኤርትራ ሪፈረንደም ወቅት እስካሁን ትርጉሙ ሊገባኝ ባልቻለ መልኩ የመለስ ዜናዊ እናት ኢትዮጵያ ሬድዮ ላይ ቀርባ ኤርትራዊያን ነጻ ሀገር ስለሆኑ እንኳን ደስ ያላቹህ ያሉ ሲሆን ነጻነቱም እንደሚገባቸው ተናግረዋል ነገር ግን ከአመታት በኋላ እነዚሁ የህወሀት ባለስልጣናት እናቶቻቸውን ሁሉ ያስደሰተውን መልካ ግኑኝነት ወደኋላ ብለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተፈጠረ ተባለ እና ከ 78000 በላይ ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲፈጁ ተደረገ ይህም ጠንካራ የነበረውን የኢትዮጵያ ወጣት እሳት ውስጥ የማገደ ብሎም የቀረው ጠንካራ ወጣት እንዲሰደድ ምክንያት የፈጠረ ሴራ ነበር በጦርነቱ መሀል መሪዎቻችን ምን ያደርጉ እንደነበር በቅርቡ ዊኪሊክስ ላይ ካየነው በኋላ ጦርነቱ የድንበር ሳይሆን ወጣት የማስፈጃ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
በአንድ ወቅት መሳሳት ልማዱ የሆነው ስብሀት ነጋ አዳልጦት በብሄራዊ ቲያትር የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች እጅግ የሚዋደዱ እና ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ካለ በኋላ ኤርትራን የሚወር አንድ ሀገር ቢመጣ ቀድመን ጦራችንን ከኤርትራ ወንድሞቻችን ጋር እናሰልፋለን በማለት መናገሩን ለሚያስታውስ ግለሰብ ግን ህወሀት እና ሻአቢያ ተጣልተዋል የሚለው ብሂል እውነታነቱ ለኢቲቪ ተመልካች እንጂ ማሰብ ለሚችል ሰው መራር ቀልድ ነው የሚሆነው፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ በኤርትራ የሚገኙ የት.ብ.ዴ.ን አባላት ነጻ እናወጣዋለን ያሉትን የትግራይ ህዝብ ነጻ ከማውጣት ይልቅ ወታደሮቻቸው አስመራ ውስጥ ኬላ ጠባቂ እንደሆነ በማህበራዊ ድህረ ገጾች አነበብኩ የተጠበኩት ነገር ስለሆነ ባይገርመኝም የወያኔን እድሜ እያራዘመን እንደሆነ ሲገባኝ ግን አዘንኩኝ በነገራችን ላይ የኤርትራ ተቃዋሚዎችንም ሰብስቦ በመያዝ ረድፍ ህወሀትም ለሻዐቢያ ውለታ እየሰራ እንደሆነ ጠጋ ብሎ የሻዐቢያ ተቃዋሚዎችን ያነጋገረ ግለሰብ የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡
ስለ ሻአቢያ ደህንነት ከህወሀት በላይ የሚጨነቅ ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ሻዐቢያ ማለት ለህወሀት ዘብ ነው ህወሀት ለሻዐቢያም እንደዛው እናም ከሻዐቢያ ጋር በመወዳጀት ወያኔን እንጥላለን ሀገራችንንም ነፃ እናወጣለን ማለት ሞኝነት ስለሆነ ቆም ብለን አካሄዳችንን ማሳመር ይኖርብናል፡፡
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ምንሊክ ሳልሳዊ :- የህዝብን ኑሮና የሀገርን ውስብስብ ችግሮች በወቅቱ የመፍታት ቅን ልቦና ከሌለ ዕጣ- ፈንታ ወዳዘዘው ውድቀት ማምራት ግድ ይሆናል፡፡ የአስተዳደር ብስለታችን፣ የዲፕሎማሲያችን ጥራት፣ ስለፓርቲና ስለ ሀገር ያለን ግንዛቤ፤ የምንመራውን ህዝብ አመኔታና ተቀባይነት የሚያስገኘው ቁልፍ ነገር መሆኑን መቼም ቢሆን መቼም እንወቅ፡፡ የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደገዝጋዡ ሳይሆን እንደ አጋዡ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ ማደራደር ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡

የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደገዝጋዡ ሳይሆን እንደ አጋዡ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ ማደራደር ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡
ለትናንሽ የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሔ ሳንሰጥ ወደ ውስብስብና ግዙፍ ችግርነት እንዲያድጉ ከፈቀድንና ቸልታችን ከበዛ፤ ያለ ጥርጥር ወደ ፖለቲካዊ ችግርነት ማደጋቸው አይቀሬ ነው፡፡ የወሎ ረሃብ እንደተነናቀ ወደ አብታዊ ማዕበልነት ተለወጠ፡፡ የሚሊተሪ ዲክታተራዊ አገዛዝ መናጠጥ፣ የቢሮክራሲያዊ በደል ማጠጥ፣ የሥልጣን መባለግና ያላግባብ መበልፀግ የአማጽያንን መፈልፈልና የተቃዋሚን ቁርጠኝነት መውለዱን ወለደ፡፡

ዛሬም የህዝብን ኑሮና የሀገርን ውስብስብ ችግሮች በወቅቱ የመፍታት ቅን ልቦና ከሌለ ዕጣ- ፈንታ ወዳዘዘው ውድቀት ማምራት ግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ የመንግሥት ዋንኛ ትኩረት የአንበሳውን ድርሻ ይውሰድ እንጂ የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጐች ወዘተ የነገዋ አገራችን ዕጣ-ፈንታ ይመለከተናል ማለት ኤጭ የማይባል ነገር መሆኑን ልብ ማለት ደግ ነው!

ዕጣ-ፈንታችንን አናመልጥም፡፡ የዕጣ-ፈንታችን አካል ነን፡፡ የምንለው፣ የምናቅደው፣ የምንራዕየው ሁሉ የእኛው አካል ነው፡፡ በተናገርነው እንነገርበታለን፡፡ በደነገግነው እንቀጣበታለን፡፡ በደሰኮርነው እናፍርበታለን ወይም እንኮራበታለን፡፡ በተለይ መንግስት ስንሆን ባወጣነው ህግ እከሌ ከእከሌ ሳንል፣ ወገናዊና ኢፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ መተዳደርና መቀጣት አለብን፡፡ የመንግሥትነታችን ትልቅ ቁም ነገር የህዝብን ደህንነትና የሀገርን ህልውና መታደግ ነው፡፡ ይህ ዋና ኃላፊነት ነው፡፡ ህዝብ እንዳይሸበር፣ እንዳይጠራጠር፣ ዕምነት እንዳያጣ ማድረግ፤ በአገሩ፣ በመንግሥቱና በኃላፊዎቹ ላይ የመተማመን ስሜት እንዲያድርበት ያደርገዋል፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ

……………..
ጌታቸው ሽፈራው በእኛ አገር በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ‹‹ፖለቲካ›› የሚባለው መብት መጠየቅ፣ እውነታውን መጻፍና መናገር ነው፡፡ ስለ ውሃ እጥረት፣ ሙስና፣ መብራት፣……ጮኽ ብሎ ያወራ ከዘመድና ጓደኛው ‹‹ይህን ፖለቲካህን ተወን!›› ይባላል፡፡ ፌስ ቡክን ጨምሮ በአብዛኛዎቹ ሚዲያዎች ደግሞ እነዚህን መሰረታዊ መብትና አቅርቦቶች ላይ የሚነሳውን ፖለቲካ ለማለዘብ (ለመራቅ) ‹‹ፖለቲካን በፈገግታ፣ የፖለቲካ ቀልዶች፣ የፖለቲካ ሽሙጥ፣……ፖለቲካን በጎሪጥ…..›› የሚባሉ አቀራረቦች ተለምደዋል፡፡

በተቃራኒው ገዥዎች ህዝብን የሚበድሉት፣ የሚዘርፉት፣ የሚያሰቃዩት ፊት ለፊት፤ በገሃድ ነው፡፡ ስለ መብት የሰበኩ ፖለቲከኞች፣ ስለ ለውጥ የጻፉ ጋዜጠኞች፣ ስለ እምነታቸው ያስተማሩ አማኞች ‹‹ሽብርተኛ›› ተብለው ታስረዋል፡፡ በርካታ ህጻናትና እናቶች ጎዳና ላይ ጸሃይና ቁር እየተፈራረቀባቸው እየተመለከትን ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ተከልክሏል፡፡ ሚዲያዎች በተራ ካድሬ ትዕዛዝ ይዘጋሉ፡፡ በዚህ ዘመን አገር እየተሸጠ ነው፡፡ ስሙን በቅጡ የማይጽፍ ‹‹ታጋይ››ና ካድሬ የማይገባውን ደም ወዝ ሲከፈለው ባለ ዲግሪዎቹ አንድ ቀን ያልተማሩትን ድንጋይ ፈለጣ በአማራጭነት ቀርቦላቸዋል፡፡ ለኢትዮጵያውያን የተነፈገው ለም መሬት ለሳውዲና ለህንዶች በሲጋራ ዋጋ እየተቸበቸበ ነው፡፡ ….ኧረ ስንቱ!?

ይህ እንግዲህ ፊት ለፊት የምናየው መራራ ሀቅ ነው፡፡ ታዲያ ለዚህ አይን ያፈጠጠ ጭቆና፣ በደል፣ አምባገነንነት የምን ፈገግታ ነው? ምንስ ይቀለድበታል? እንዴትስ በጎሪጥ ይታለፋል? በእርግጥ ህዝባችን ‹‹ፖለቲካ›› ብሎ በጠባቡ የሚተረጉመውም ይሁን ከዚህ የሚሰፋው ፈገግታ፣ ቀልድ፣ ድርድር፣ ስምምነት፣ መመቻመች……አያስፈልገውም እያልኩ አይደለም፡፡ በእኛ አገር ደግሞም በአሁኑ ወቅት ግን ፖለቲካው ፊት ለፊታችን የተደቀነ፣ የእያንዳንዱን ቤት ያንኴኳ፣ አገር ያከሰረ፣ ህዝብን ያዋረደና ያስናቀ ሆኗል፡፡ ይህን ፖለቲካ በፈገግታ፣ በሹክሹክታ፣ በለበጣ፣ በጎሪጥ፣ በአሽሙር እንለፈው ካልን አሽሙሩም፣ ቀልዳ ቀልዱም፣ ለበጣውም በራሳችን ላይ መሆኑ ነው፡፡ መርጉ የተጫነን እኛውን ራሳችን ላይ ነውና!

ከወራት በፊት ነው፡፡ ውሃ ለመቅዳት ተሰልፈን ከተሰለፉት ጋር ለአቅርቦቱ ችግር የ‹‹መንግስት››ን ድክመት አንስተን እንወያያለን፡፡ ‹‹ቀለል›› ባሉ ጉዳዮች አብሮን ሲያወራ የነበረ ወጣት ‹‹አይ እኔ ፖለቲካ አልወድም! አታነካኩኝ!›› ብሎን ራሱን ‹‹ነጻ አወጣ!››፡፡ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ይቺ ሽሽት የተለመደች ስለሆነች አልገረመኝም፡፡ አንድም ወሬውን የሚያስጀምረው ሰው ጆሮ ጠቢ ይሆናል፣ አሊያም ለጆሮ ጠቢ ያጋልጠኛል ከሚል ፍርሃት የመነጨ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ጥቂት ከቆየን በኋላ ወጣቱን ስለራሱ ስጠይቀው በሹክሹክታ ስለዚህ መንግስት ብልሹነት ማውራት ጀመረ፡፡ አባቱ የደርግ ወታደር ከተባለው የአገሪቱ ሰራዊት በግፍ ተባረዋል፣ 97 ላይ አባቱ ታስረው ስቃይ ደርሶባቸዋል፣ አባል ባለመሆኑ ለአንድ አመት ተኩል ስራ አላገኘም፣ በግድ የድጋፍ ሰልፍ ይወጣሉ፣ ቤታቸው ውስጥ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ነው……….፡፡

ይህ ፖለቲካው መርግ የሆነበት፣ በብልሹ ፖለቲካው እስከ ምናምኑ የተነከረ ልጅ ነው እንግዲህ ‹‹አታነካኩኝ!›› የሚለው፡፡ ከዚህ ውጭ ምን ሊያደርጉት እንደሚፈልግ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ፌስ ቡክም ሆነ ሌላ ቦታም ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞኛል፡፡ በደል የደረሰበት ሰው ዜና ልትዘግቡለት ስትሉ ‹‹አይ ያጠብቁብኛል፣ ትንሽ ቆይ!፣ ለስለስ አድርገው፣ እንዳታስመታኝ፣….›› ይላችኋል፡፡ ገዥዎቹ ደግሞ ይህን ይወዱታል፡፡ የሹክሹክታ፣ የለበጣ፣ የሀሜት፣ የፈገግታ……‹‹ፖለቲካ›› ከልኩ እንደማያልፍ ያውቁታል፡፡ እነሱ ፊት ለፊት እየበደሉ፣ የጎሪጥ እያየ የሚያልፍ፣ በቅኔና ቀልድ የሚናገር ህዝብ ለስልጣናቸው በእጅጉ ምቹ ሆኖላቸዋል፡፡

እኔም እላለሁ! መብታችን ለማስከበር፣ አቅርቦት ለማግኘት፣ ክብራችን ለማስጠበቅ፣……..መናገር፣ መጠየቅ፣ መቃወም ያለብን እንደወረደ፣ ፊት ለፊት እንጅ ቀልድ፣ ፌዝ፣ ቅኔ፣ አሽሙር፣ ሽሙጥ የሚያስፈልገን ጊዜ ላይ አይደለንም፡፡

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎቻቸው እንዲወዳደሩ ወይም ስልጣን እንዲይዙ ለማድረግ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡የውክልና ዴሞክራሲ እንዲጠነክርና እንዲጎለብት ፓርቲዎች የሚጫወቱት ሚናም ቁልፍ ነው፡፡ በሰለጠነው አለም የፖለቲካው ልቀት የሚለካው በፓርቲዎች ብዛት ነው፡፡የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት የሚፎካከሩ ፓርቲዎች ቁጥር ሁለት ቢበዛ ሶስት ነው፡፡ለምሳሌ በአሜሪካ ኋይት ሃውስ ለመግባት የሚፎካከሩት ፓርቲዎች ሁለት ናቸው፡፡ዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች፡፡ በእንግሊዝ ዋነኞቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሶስት ናቸው፡፡ወግ አጥባቂዎቹ (ኮንሰርቫቲቭ)የሰራተኛው(ሌበር ፓርቲ)እና ሊበራሎች፡፡ […]

አረና በሁመራ ለማድረግ ያቀደው ህዝባዊ ስብስበ በአዲግራት እንደተደረገው ሁሉ በሕወሃት አምባገነንነት ሳይሳካ ቀርቷል። የአረና አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ በፌስቡክ ብሎጋቸው : «ዓረና መድረክ በሑመራ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ለዓርብ ጥር ሰለሳ ቀጠሮ ይዞ፣ አስተዳዳሪዎችን አሳውቆ፣ የማዘጋጃቤት አዳራሽ ተፈቅዶለት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር የተሳካ ቅስቀሳ ቢያደርግም የሑመራ (እንዲሁም የወልቃይት) ህዝብ ጥሩ አቀባበል ያስደነገጣቸው የከተማው አስተዳዳሪዎች […]

በዶር መራራ ጉዱና የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፣ የወጣቶችን ሊግ ማቋቋሙ የዶር መራራ እና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ፌስቡክ ዘገበ። ሊጉ የኦሮሞዎች መብት በኢትዮጵያ እንዲከበር ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ በኦሮሚያ ዞኖች ይንቀሳቀሳል ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ አበባን ጨምሮ ሃያ አንድ የኦሮሞያ ዞኖች ሲኖሩ፣ አዲስ ለተቋቋመዉ የወጣቶች ሊግ፣ ተወካዮች ከአሥራ ሁለት ዞኖች እንደመጡም ለማወቅ ተችሏል። ወጣት ተወካዮች የመጡት፣ […]

ከማንነት ጋራ የተያያዙ ጥያቄዎች፣ ሙግቶች፣ በተቃራኒውም አስቀያሚ ሐሳብ አልባ ስድድቦች ሰሞኑን በርከትከት ብለዋል። ጥያቄዎቹና ሙግቶቹ መኖራቸውን አጥብቄ እደግፈዋለሁ። በእኔ እይታ አብዛኞቹ ምልልሶች ወይም ሙግቶች በመሠረቱ አዲስ ጭብጥም ሆነ መከራከሪያ አላቀረቡም። ቢሆንም የነበረውንም ቢሆን በአግባቡ በተደጋጋሚ እያነሱ ሐሳብ መለዋወጡ ጠቃሚ ነው፤ ሙከራው ቢያንስ እርስ በርስ መተዋወቅን ይጨምራል፤ አልፎም አዲስ ሐሳቦችን ለማፍለቅ እድል ይሰጣል። የማነ ናግሽ ኢትዮጵያዊ […]

አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ፣ ለገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የሰላምና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። «ኢሕአዴግ እኛን እንደ ጠላት እና ሽብርተኛ ማየቱን ማቆም አለበት። እኛም ደግሞ ኢሕአዴግን እንደ አዉሬ ማየት ማቆም አለብን። ከጥላቻ ፖለቲካ በመዉጣት ችግሮቻችንን በሰላም መፍታት መማር አለብን» ሲሉ ነበር፣ ለአገር በሚጠቅሙ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢሕአዴግ ጋር ለመስራት፣ ያሉትን ልዩነቶችን በዉይይት ለመፍታት አንድነት […]

በደቡብ አፍሪቃ ባለፈው ዓመት የተቋቋመው የ«አኻንግ ኤስ ኤ» ፓርቲ ሊቀ መንበር የሆኑት ፀረ አፓርታይድ ታጋይ ዶክተር ማምፌሌ ራምፌሌ እአአ የፊታችን ግንቦት ሰባት በሚካሄደው ቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ሄለን ሲለ አስታወቁ።

ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ የአገራችንን ፖለቲካ የተጠናወተው የ“…. ወይም ሞት” አስተሳሰብ ከአስርት አመታት በኋላም አለቅ ብሎን ዛሬም እኔ ከምደግፈው ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ቡድን ወይም አስተሳሰብ ውጭ ያለው መንገድ ወይም አማራጭ ሁሉ ገደልና ሞት ነው ብለው የሚያስቡ ፖለቲከኞችና ዓጃቢዎችን ቁጥር በብዙ እጥፍ አባዝቶ ቀጥሏል። በ‘ደርግ ወይም ሞት’ የጀመረው የኼው የተወላገደ እና ጸረ-ዲሞክራቲክ የሆነው አስተሳሰብ ሳንወጣ ዛሬም […]


ሰሞኑን በአዲስ ዘመን እና ኢዜአ ‹‹ጥናት›› ስም ገበያ ላይ ከወጡ አዲስ አባባሎች ውስጥ ‹‹ልማቱን መካድ›› የሚል ይገኝበታል፡፡ አባባሉ እንዲህ እንደዛሬው ጥናታዊ ዕውቅና አላገኘም ነበር እንጂ እንዲሁ በገደምዳሜው ግን ስሙ ይታወቅ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ እና ቲፎዞዎቹ ‹‹ተቃዋሚዎች ልማቱን ይክዳሉ›› ይላሉ፤ ልማቱ የኢሕአዴግ ትልቁ መንጠልጠያ ነው፡፡
ራሱን ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ መንግሥት ‹ሥልጣኑን ጠቅልዬ መያዝ የሚኖርብኝ እና ዴሞክራሲ ለመንፈግ የተገደድኩት ልማቱን ለማፋጠን ብዬ ነው› ይላል፡፡ አባባሉ ‹እኔ ሥልጣኑ ላይ ካልቆየሁ ልማት አይኖርም› የሚል ይመስላል፤ ሌሎች ልማት ማምጣት ስለማይችሉ ይሁን እነሱ ሥልጣን ላይ ከሌሉ አገሪቷ ላይ ሌላ ኃይል እንዳይመጣ ጦርነት ስለሚከፍቱ እኔንጃ – ልማቱ የሚጨናገፈው በምን እንደሆነ ተናግረው ግን አያውቁም፡፡ መቼም ልማት ማለት ግንባታ ሆኗል እና የግንባታ መሣሪያዎቹን እና መሥሪያ ቦታዎቹን ይዘው ከሥልጣን አይወርዱም ብለን እናስባለን፡፡

የበኩር ስህተት

የኢሕአዴግ እና የቲፎዞዎቹ የበኩር ስህተት ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን እና ልማትን እንደ አንድ ዓይነት ነገሮች መመልከታቸው ነው፡፡ ኢሕአዴግ ለዐሥር ዓመታት ያክል በተከታታይ አስመዝግቢያቸዋለሁ ለሚለውና ከሞላ ጎደል የዓለም ባንክ እና የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚያረጋግጡለት የኢኮኖሚ ዕድገቱን ነው፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገቱ በኢትዮጵያ መንግሥት አነባበብ ሁለት አሐዝ ይደርሳል፡፡ እርግጥ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢያቸው (GDP) አነስተኛ የሆኑ አገራት ሁለት አሐዝ የሚደርስ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያስመዘግቡበት ዕድል ሰፊ ነው፤ በተረጋጋ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ሒደት ውስጥ እስከሆኑ ድረስ፡፡ ችግሩ ይህንን የኢኮኖሚ ዕድገት ልማት ብለው የተረጎሙት ዕለት ነው የተጀመረው፡፡
ኢኮኖሚስቶች ኢኮኖሚያዊ ልማት ከኢኮኖሚያዊ ዕድገት በሰፊው እንደሚለይ፤ ዕድገት የልማት አንድ የአካል ክፋይ እንጂ አቻ ስያሜ እንዳልሆነ ይከራከራሉ፡፡ ባለሙያዎቹ ልማትን በጥቅሉ ሲተረጉሙት ‹የሕዝቦች የኑሮ ደረጃ መሻሽል፣ ለራሳቸው ያላቸው ግምት/አመለካከት መጨመር፣ ከጭቆና እና ጥገኝነት ነጻ መውጣት እንዲሁም ለኑሮ የሚበጁ የተለያዩ አማራጮች› ማግኘትን› ይመለከታል ይላሉ፤ ልማት በዜጎች ላይ በሚታዩ ለውጦች ላይ ያተኩራል፡፡ በዕድገት ምዘና ግን ድምር የአገሪቱ ገቢ ከዓመት፣ ዓመት መጨመሩ ላይ ብቻ የሚያተኩር በመሆኑ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ባይኖርም፣ የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ባይሻሻልም፣ ዜጎች ኢኮኖሚያዊም ይሁን ፖለቲካዊ ነጻነት ባይኖራቸውም በጥቂት የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እና በጥቂት የሀብታሞች የበለጠ መበልፀግ ላይ ብቻ የተመሠረተ የቁጥር መሻሻል ከታየ ዕድገት ሊባል ይችላል፡፡ (ንፅፅሩን የአንድን ሰው ተራ የዕድሜ እና የክብደት መጨመርን፤ ከሌሎች የሥነ-አዕምሮ፣ ምግባር፣ ኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ደረጃ ዕድገት ጋር እንደማነፃፀር  ነው – የመጀመሪያው ኢኮኖሚ፤ ሁለተኛው ልማት መሆኑ ነው፡፡)
ይህ የትርጉም ልዩነት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት እንጂ ልማት አለመሆኑን ይናገራል፤ ስለዚህ ልማቱ ከመካዱ በፊት በቦታው መኖር ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ (ከዚህ ርዕስ ጋር የተገናኘ ሙግት እዚህ ዞን ዘጠኝ ላይ የተጻፈ ጽሑፍ ላይም ማግኘት ይችላሉ፡፡)
የኢትዮጵያ ተርታ
ኢትዮጵያ የምዕራባውያን ዋነኛ ዕርዳታ ተቀባይ አገር ውስጥ ናት፡፡ እንግሊዝ እርዳታ ከምትለግሳቸው አገራት ከፍተኛ መጠን ያለውን የምትቀበለው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ካናዳ ከሐይቲ እና አፍጋኒስታን ቀጥሎ በሦስተኝነት ደረጃ እጇን የምትዘረጋው ለኢትዮጵያ ነው፡፡ እርዳታ አያኮራም፤ ሆኖም እንደኛ አገር ላለው ቁስለኛ ኢኮኖሚ አንድ የአገር መሪ እርዳታ ማስገኘት መቻሉን እንደ ድል መቁጠር የተለመደ ነው፡፡ የእኛም መንግሥት በዚህ ኩራት ይሰማዋል፡፡
አሳፋሪው ነገር ግን የሚመጣው ብዙዎቹ ለጋሽ ሃገራት የሚለግሱን ከነማን ተርታ አሰልፈው እንደሆነ የተመለከትን ዕለት ነው፡፡ ልገሳዎቹ ባብዛኛው በጦርነት ከተጎዱ አገራት ተርታ ነው፡፡ እኛ የእርስ በርስ ጦርነታችንን ካቆምን ሀያ ዓመታት ቢያልፉንም ዛሬም በጦርነት ከተጎዱና በተፈጥሩ አደጋ ከተናጡ አገሮች ተርታ እርዳታ የሚመደብልን አገር ነን፡፡ ይህ በልማት ምን ያህል ወደኋላ እንደቀረን አመላካች መራር እውነት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ አገራችን ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገሮች ተርታ ተሰለፈች ተብሎ ዝርዝሩ ሲታይ በኢኮኖሚያቸው ድቅቅ ካሉ አገራት ተርታ መሰለፏን ማየት የሚያስደስት ነገር አይደለም፤ የሚደሰኮርበትም አይሆንም፡፡ አንድ መቶ ብርን በሁለት እጥፍ ማሳደግ፣ አንድ መቶ ቢሊዮን ብርን በእጥፍ ከማሳደግ ይቀላል፡፡ የዕድገታችን ፐርሰንታይል ከፍ ብሎ መታየትም በዚህ ይገለፃል እንጂ የመንግሥታችንን በልማት መመንደግ የሚያረጋግጥ እውነታ አይደለም፡፡
ጠቅላላ ገቢያችን ከሕዝብ ብዛታችን አንፃር
ኢትዮጵያ በጠቅላላ የገቢ ዕድገቷ በዓለም 14ኛ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ፍጥነት እያደገ ያለው ጠቅላላ ገቢ ለሕዝብ ቁጥራችን ሲካፈል ዛሬም ውራ እንደሆንን ይነግረናል፡፡ በጠቅላላ ገቢ ለሕዝብ ቁጥር ምጣኔ ኢትዮጵያ በአይ.ኤም.ኤፍ. ደረጃ ላይ169ኛ ከ187 አገራት እና የዓለም ባንክም 169ኛ ከ180 አገራት አንፃር ተቀምጣለች፡፡ ያውም ይህ  ምጣኔ በሀብታሞች እና በድሆች መካከል ያለውን የገቢ ክፍተት ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም፡፡ ጠቅላላ የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ተሻሽሎ እንደሆነ እና እንዳልሆነ የሚገመግመው የተባበሩት መንግሥታት ሰብኣዊ ልማት ኢንዴክስ ላይ ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ዝቅ ብላ 173ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ስለዚህ ከልማት ራቅ ብለን እንደምንገኝ ብዙ እማኝ መጥራት አይጠበቅብንም፡፡

በዚያ ላይ ደግሞ በቅርቡ የኢኮኖሚስቱ ኢንተሊጀንስ ዩኒት እ.ኤ.አ. በ2014 ፈጣን ዕድገት ያስመዘግባሉ ብሎ ከገመታቸው ዐሥር አገራት ውስጥ ኤርትራ ሳትቀር 8 በመቶ እንደምታድግ (በ9ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ) ኢትዮጵያ ግን ዝርዝሩ ውስጥ መግባት አልቻለችም፡፡ ይህ ማለት የተጀመረው ዕድገትም፣ ልማት ደጃፍ ላይ ሳይደርስ ሊሸረሸር እንደሚችል እና መንግሥት የባለሙያዎቹን ምክር በመስማትና ሕዝባዊ ተሳታፊነትን በማሳደግ ለዘላቂ ልማት የሚያደርስ የኢኮኖሚ ግንባታ መስመር ማስመር እንዳለበት አመላካች ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በኢኮኖሚ ስርዓቱ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን እየቆጠሩ ‹‹ልማት መካድ›› የሚል ባጅ መለጠፍ ‹‹ልማታዊ›› አይደለም፡፡

ራስን “ኢትዮጵያዊ” ብሎ መጥራት ነውር እንዲመስል ጠንክረው የሚሠሩ አሉ። አልተሳካላቸውም ብዬ አልዋሽም። ምክንያታቸው እስከዛሬ የነበረው ኢትዮጵያዊነት አማራ ለበስ ነው፤ የዘውግ ብሔርተኝነት አንጂ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት (ማንነት) ብሎ ነገር የለም የሚለው ነው። መነሻ ነጥቡ እውነት ላይ ቆሞ፣ መድረሻው ግን ተራ ድምዳሜ ነው። በዘመን ጥፋት ዘንድሮን መቅጣት! እርግጥ ብዙኃን ኢትዮጵያውያን ዘውጋቸውን የሚያስቀድሙ ብሔረተኞች ሊሆኑ ይችላሉ። እኔንና መሰሎቼን ግን እነሱ ሸንጎ በሉት ጨፌ ውስጥ አስገድዶ የመክተት ወንጀል ነው። የራስን ማንነት በዘውግ ብሔር መግለጽ መብትም ምርጫም የሆነውን ያክል በኢትዮጵያዊነት መግለጽም ነውር ሊደረግ አይገባውም።

እኔን እንደ ምሳሌ

እኔ ባጋጣሚ ከተውጣጡ ብሔሮች ነው የተወለድኩት። ያደግኩትም ከዚያ በበለጠ አካባቢ በመጡ ቤተሰቦች መሐል ነው። የአብሮ አደግ ጎረቤቶቼ ቤተሰቦች ሙስሊም ጉራጌዎች፣ ወሎዬ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያን የወለጋ ኦሮሞዎች፣ ትግሬዎች… ናቸው። ልጅ እያለን ማን “ምን” እንደሆነ ትዝ ብሎን አያውቅም። ስናድግ ግን ስለዘውግ ማንነቶቻችን እንድንማር ብቻ ሳይሆን አንዱን እንድንመርጥ ተገደድን። (መማሩን ወደን መገደዱን ግን ከመጥላት ሌላ አማራጭ የለንም።)

ሁሉንም በቅጡ አልችላቸውም እንጂ የአማርኛም፣ ኦሮምኛም፣ ሶማልኛም፣ ትግርኛም፣ ጉራግኛም… ዘፈኖች ስሰማ ባለሁበት በስሜት እወዘወዛለሁ፤ በፍቅር የምበላቸው ምግቦች (ኪሴ ሁሌም አይፈቅድልኝም እንጂ) ክትፎ፣ ጨጨብሳ፣ (እና በተውሶ ፒዛ እና በርገር ሳይቀሩ) ናቸው። አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ ሐረርን የጎበኘሁት እና ሌሎችንም ልጎበኝ ቀናት የምቆጥረው የራሴ የሚል ውስጣዊ ስሜት ስላለኝ ነው። ለጉዞ ስወጣ “የእነርሱን ልጎብኝ” አልልም፤ “የአገሬን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ልጎብኝ” ብዬ ነው። ከኢትዮጵያ መውጣት የማልፈልገው እንደኢትዮጵያ የሚመጥነኝ እና የምመጥነው (fit የማደርግበት) ስፍራ እንደሌለኝ ስለማምን ነው። ልዩነታችን ጌጤ ነው። እኔ የሁሉም፣ ሁሉም የኔ ናቸው ብዬ ከልቤ አምናለሁ።

ነገር ግን ለፖለቲካ ግብአት ሲባል ኢትዮጵያዊ ማንነት ብሎ ነገር የለም አንዱን ማንነት ምረጥ ስባል ያመኛል። እንዳጋጣሚ በቤተሰቦቼ ካገኘሁት የዘውግ ማንነቶች ውስጥ የቱን ነው የምመርጠው? ካሳደጉኝ ጎረቤቶቼ የወረስኩትን ማንነትስ ለምን እቀማለሁ? አማራው ማንነቴስ? ኦሮሞው ማንነቴስ? ጉራጌው፣ ትግሬው፣… ማንነቴስ? ከድምር እኔነቴ አንዱን ብቻ መርጬ እኔ እንትን ነኝ አልልም፤ ነጠላ ማንነቶቼን በተናጠል አልወዳቸውም። ከድምሩ አንዱ ሲጎድል ያመኛል። ድምሩ ማንነቴ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ነው።

ኢትዮጵያዊነት እንደገና ይጤን

በታሪክ ሒደት ተጠቃሚ የነበሩ የዘውግ ማንነቶች አሉ። በተለይ አማርኛ ተናጋሪዎች (አማራዎች) ግምባር ቀደሞቹ ናቸው። ይህን መነሻ ይዘው ኢትዮጵያዊነትን ከአማራነት ጋር ቀላቅለው የሚደመድሙ ግን የራሳቸውን ትርጉም ይገምግሙ። የኔ ኢትዮጵያዊነት ግን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ካርታ የታቀፉ ማንነቶችን ሁሉ ያቀፈ፣ የሚያስተናግድ እና የሚያከብር ኢትዮጵያዊነት ነው።

ይህ ማለት ግን፣ አንድ ሰው አንድ ቋንቋ ብቻ ተናጋሪ በመሆኑ፣ የሚያውቀው ባሕልም የዚያን ዘውግ ብሔር ብቻ መሆኑ ኢትዮጵያዊ አያደርገውም ማለት አይደለም። ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ነው። ነገር ግን ራሱን በዚያ የዘውግ ብሔር ማንነት ለመግለፅ ከፈለገ መብቱ ነው። የዘውጉ ብሔር ኢትዮጵያዊነት በሕግም (እንበል ከየትኛውም የአፍሪካ አገራት በረዘመ) የታሪክ ዕድሜም የፀደቀ ነው። ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒ ላንዱ የዘውግ ብሔር የተለየ ውስጠኝነት (belonging) የማይሰማው ሰውም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን መነፈግ የለበትም።

ባለኝ መረጃ፣ መታወቂያ ላይ ብሔር የሚጻፈው አዲስ አበባ ብቻ ነው። እንዳጋጣሚ ደግሞ ከዘውግ ብሔርተኝነት ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን የሚመርጠው የአዲስ አበባ እና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪ የሆነው ሕዝብ ነው። አንድ ሰው ቀበሌ ሄዶ “እኔ ኦሮሞም፣ አማራም፣ ሶማሌም… አይደለሁ፤ ብሔር የሚለው ላይ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ይጻፍልኝ” ብሎ ቢሟገት ፖለቲካዊ ወንጀል እንደሠራ ተቆጥሮ ስሙ በጥቁር መዝገብ ይሰፍራል። መታወቂያውን ሊከለከል ወይም ቤተሰብ ካለው የአንዱን በውርስ ተለጥፎ በግድ ሊሰጠው ይችላል። ይህ ጭቆና ነው።

ብዙዎች “ኢትዮጵያዊነት” በሚሉ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሁሉ የሚያቀርቡት በፌዴራሊዝሙ እንደተሰነዘረ ጥቃት አስመስለው ነው። እንደዚያ የምር ማመናቸውን ግን እጠራጠራለሁ። እኔ ፌዴራሊዝሙ ላይ ከጥቃቅን ማስተካከያዎች በቀር ችግር የለብኝም። በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር አስፈላጊ ነው ከሚሉትም ወገን ነኝ። ይህ ሁሉ “ኢትዮጵያዊነት” እንዲያብብ እንጂ አንዲጠወልግ አያደርገውም። ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠወልገው የዘውግ ብሔረተኞች የከረረ ጥላቻ እና የተዛባ፣ ያልታረመ የኢትዮጵያዊነት ፍቺ ነው።

ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ የየትኛውም የዘውግ ብሔር ሙሉ አድርጎ አይገልጸኝም። ስለዚህ መታወቂያዬ ላይ “ኢትዮጵያዊ” ተብሎ ይጻፍልኝ።

“ግድብ ሲጠናቀቅ የግብፅ ፖለቲከኞችን ዓይን ይከፍታል::” አምባሳደር ዲና
“ግብፃውያን ዛቻን ትተው ገንቢ በሆኑ ስራዎች ማተኮር አለባቸው::” ውጭ ጉዳይ

በማንኛውም አገር ወንዙን በብቸኝነት ለመጠቀም የሚነሳ ፍላጎትና ታሪካዊ መብት ለማስቀጠል የሚደረግ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም። ግብፃውያን ፋይዳ የሌለው ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብና ዲፕሎማሲያዊ ዛቻዎችን ትተው ገንቢ በሆኑ ስራዎች ማተኮር እንደሚገባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢዜአ እንደገለፁት የተለያዩ የግብፅ ባለስልጣናት፣ የዩኒቨርስቲ ምሁራንና ፖለቲከኞች በየጊዜው የሚለቋቸው ዛቻዎች ተገቢ አይደሉም ፋይዳም የላቸውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዛቻን በዛቻ አይመልስም ያሉት ቃለ አቀባዩ ዛቻ በየትኛውም ነገር ጥቅም እንደሌለው ገልፀዋል።እንደ አምባሳደር ዲና ገለፃ ለግብፅም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመው ተባብሮ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከሁሉም የተፋሰሱ አገሮች በጋራ በመስራት ተጠቃሚ ሲሆኑ ብቻ ነው።የናይል ወንዝ የአንድ አገር ስጦታ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የተፋሰሱ አገሮች ስጦታና ሁሉም እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበት የጋራ ወንዝ መሆኑንም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

አምባሳደር ዲና እንደተናገሩት በማንኛውም አገር ወንዙን በብቸኝነት ለመጠቀም የሚነሳ ፍላጎትና ታሪካዊ መብት ለማስቀጠል የሚደረግ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም።ግብፃውያን የናይል ጉዳይ በህገ መንግስታቸው መስፈሩ ሳይሆን ጠቃሚው ከተፋሰሱ አገራት ጋር ፍትሃዊና ማንንም የተፋሰሱ ሀገር በማይጎዳ መንገድ የናይል ወንዝን ለመጠቀም የተፈረመው የኢንተቤ ስምምነት መቀበል መሆኑን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

አምባሳደር ዲና የኢንቴቤ ስምምነትን አለመቀበል ከሁሉም የተፋሰሱ አገሮች ጋር ያቀያይማልም ብለዋል። አንድ አገር ህግ ሲያወጣ በማንኛውም ነገር የሌላ አገር ጥቅም የሚጎዳ መሆን የለበትም ያሉት ቃለ አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተፋሰሱ አገሮች የሚወጡ የውሃ ህጎች ከዓለም ዓቀፍ ውሃ ህጎች ጋር የሚጋጩ መሆን የለባቸውም፡፡ የዓለም ዓቀፍ ህጎችም አይፈቅዱም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር ዲና እንዳሉት በካርቱም በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል ሲካሄድ በነበረው ውይይት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ስብሰባዎች የዓለም ዓቀፍ ኤክስፐርቶች ፓናል አጥንቶ ያቀረበው ምክረ ሃሳብ ተግባራዊ የሚያደርግ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተው ነበር፡፡ ነገር ግን ግብፆች በሦስተኛው ስብሰባ ባመጡት አዲስ ሃሳብ ምክንያት ውይይቱ ያለ ቀነ ቀጠሮ መበተኑን አስታውሰዋል፡፡ ውይይቱ ያለ ቀነ ቀጠሮ የተበተነበትም ምክንያት በግብፅ በኩል ዳግም ጥናት የሚያካሂድ የውጭ ዜጎችን ያካተተ አዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮሚቴ የመመስረትና ያጠናው ውሳኔ ተግባራዊ ይሆናል በሚል የቀረበው ሃሳብ በኢትዮጵያና ሱዳን በኩል ውድቅ በመደረጉ እንደሆነ የገለፁት አምባሳደር ዲና ውይይቱ ወደ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ማዘንበሉም ሌላው ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

ግብፃውያን ጠቃሚው ገንቢ አቋም መያዝ ነው ብለው ጥርጣሬን ትተው የዓለም አቀፍ ኤክስፐርቶች ፓናል አጥንቶ ያቀረበው ምክረ ሃሳብ ደጋግመው ሊያዩት እንደሚገባ ጠቁመዋል።አምባሳደር ዲና ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የተፋሰሱን አገሮች ጥቅም አይጎዳም ይበልጥ የተፋሰሱ አገራት በኢኮኖሚ የሚያስተሳስር መሆኑን ገልፀው ግድቡ በመላው ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ቀን ከሌት እየተሰራ መሆኑንና ለአፍታም እንኳን ሳይቋረጥ ያለ ምንም የውጭ ዕርዳታ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል፡፡የህዳሴው ግድብ ሲጠናቀቅ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ጥሩ ግንኙነት ይፈጠራል፤ ይህም የተሳሳቱ የግብፅ ፖለቲከኞችን ዓይን ይከፍታል ብለን እናስባለን ብለዋል።

እንደ ጁዶ እና ሌሎች ተመሳሳይ የራስ መከላከል ስፖርታዊ ጥበቦች ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም የተለመዱ አይደሉም። ሆኖም ጀርመን ነዋሪ የሆኑት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ወደ ኢትዮጲያ ሄደው በዚህ ስፖርት ወጣቶችን ማሰልጠን ከጀመሩ አንስቶ አንዳንድ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ሳይቀር ተሰልፈው የሚወዳደሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ማፍራት እንደተቻለ ገልፀውልናል።

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተዘጋጀው  የእምነት አኩልነትና ተቻችሎ የመኖር የሃይማኖት እሴትን ሊያጎለብት ይችላል የተባለ ረቂቅ አዋጅ ላይ የሚመለከታቸውን ወገኖች ሃሳብ ለማሰባሰብ  ከነገ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ምንጮቻችን ጠቆሙ። በዚሁ ስብሰባ ላይ በዋንኛነት የሚሳተፉት በአገሪቱ አሉ የሚባሉት 945 ያህል የእምነት ተቋማት መሆናቸውም …

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር 30 ኪሚ ርቃ በምትገኘው በደቡብ ጎንደሩዋ ሃሙሲት ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ገዢው ፓርቲ እየተበቀለን ነው ሲሉ ይናገራሉ። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር ሲያደርግ በነበረው ጦርነት ሃሙሲት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። በዚህም በቀል ይመስላል ይላሉ ነዋሪዎች ፣የህወሃት የደህንነት ሰዎች በከተማ ውስጥ አሉ የሚባሉ …

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ አሰግድ ጌታቸው ይመኑ ጥር 29 ቀን 2006 ዓም ለሁሉም የመስተዳድሩ ቢሮችና ለክፍለከተሞች በጻፉት ደብዳቤ ፣ ማንኛውም በግቢው ውስጥ የሚያድር መኪና የማን እንደሆነ ለማወቅ ይቻል ዘንድ ታርጋቸው ተገልጾ ይቅረብልን ብለዋል። ደብዳቤው በግልባጭ ለግቢው ጸጥታ ዴስክ ተመርቷል። መስተዳድሩ ይህን ደብዳቤ የጻፈው …

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊድን-ስቶኮሆልም በተካሄደው የቤት ውስጥ የ 3 ሺ ሜትር ውድድር አትሊት ገንዘቤ ዲባባ በአስደናቂ ብቃት በማሸነፍ  አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች። ገንዘቤ ዲባባ ርቀቱን በ8:ደቂቃ 16 ሴኮንድ  60 ማይክሮ ሴኮንድ በማጠናቀቅ  እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2007 ዓመተ ምህረት፣ ማለትም ከ 7 ዓመት በፊት  በአገሯ ልጅ በአትሌት መሰረት ደፋር  ተይዞ የነበረውን …

ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩናይትድ ስቴስት ከፍተኛ  ዲፕሎማት የሆኑት ምክትል ሴክሬታሪ  ቪክቶሪያ ኑላንድ- በዩክሬን ከ አሜሪካ አምባሳደር ጋር ስለ ዩክሬን ግጭት በስልክ ያወሩት ወሬ  ተጠልፎ በድረ ገፆች መለጠፉ አሜሪካን ማሳፈሩን ዘገባዎች አመልክተዋል። ቪክቶሪያ ኑላንድ  በዙሁ የስልክ ምልልስ ላይ ስለዩክሬን ግጭት ሲያወሩ የአውሮፓ ህብረትን ሲወቅሱና  በወረደ ቃላት ሲዘልፉ ይሰማሉ። በሁኔታው የደነገጠችው አሜሪካ ፦”ቪክቶሪያ …

የአንድነት ልሳ የሆነዉ ፍኖት ነጻነት፣ ሰበር ዜና ብሎ እንደዘገበዉ፣ ኢሕአዴግ አቶ ዳን ኤል ተፈራን ጨምሮ በርካታ የአመራር አባላትን ለማሰር እየትዘጋጀ እንደሆነ፣ በፍትህ ሚኒስቴር ያሉትን ምንጮች በመግለጽ ዘግቧል። « አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱን የፍትህ ሚ/ር ምንጮች አጋለጡ፡፡ ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ […]

ሕገ-መንግሥቱ የሚፈቅድልኝን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳላካሂድ ከልክለውኛል፤ አባላቶቼን ያለአግባብ በማንገላታት አስረውብኛል፤ ቅስቀሳ እንዳላካሂድ አግደውኛልና ድምፅ ማጉያዎቼን ቀምተውኛል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህና ፓርቲ (አንድነት) በሶስት የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ መሰረተ። ፓርቲው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሔር ችሎት ላይ ክስ የመሰረተባቸው ተቋማት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ […]

የአንድነት ፓርቲ ለበርካታ አመታት በዋና ጸሃፊነት ያገለገሉት አቶ አስራት ጣሴ መታሰራቸዉን የአንድነት ፓርቲ ሚሊየም ድምጽ፡ለነጻነት ፌስቡ ገጽ ዘገበ። «የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ “ዘለፋ አዘል ጽሑፍ” ጽፈዋል በሚል ፍርድ […]

የኢትዮ-ቴሌኮሟ ቅርፀ-ድምፅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰሞኑን “የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም” ትላለች። ዛሬ (ጥር 29/2006) ግን ማለዳውን ሙሉ ስልኮች ሁሉ “ዝም፣ ጭጭ” ብለው ነው ያረፈዱት። አዲስ አበባን ከስሪ-ጂ (ሦስተኛው ትውልድ የስልክ በይነመረብ ግንኙነት አቅም) ወደ ፎር-ጂ (አራተኛው ትውልድ አቅም) ለማሳደግ፣ ሌሎቹን ክልሎች ደግሞ ወደ ሦስት ትውልድ ለማሳደግ ሥራዎች እየተጣደፉ እንደሆነ በሚደሰኮርበት በዚህ ሰዓት ኔትዎርኩ እንደ ክሪስማስ ዛፍ ብልጭ ድርግም ይል ገብቷል።

በነገራችን ላይ እኛ 1·1% የኢንተርኔት ፔኔትሬሽን (ተዳራሽነት) ላይ ቁጭ ብለን 28% ደረስኩ ብላ እንቁልልጭ የምትለን ኬንያ፣ በሁሉም ቴሌኮም ድርጅቶቿ የሚቀርቡት የስልክ አገልግሎቶች ከ3ጂ በላይ ናቸው። (Keeping up with the Joneses has become mission impossible).

ምትሐተ-ኢትዮቴሌኮም

ዛሬ የገጠመኝ ደግሞ ለየት ይላል። ሌላ ሰው’ጋ እደውላለሁ ብዬ አብሮኝ ያለው ሰው’ጋ ደወልኩ፤ ቢጠራም አይነሳም። ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ስመለከተው የደወልኩት አብሮኝ ያለው ሰው’ጋ ነው።  “እንዴ የደወልኩት ላንተ ነው፤ አንተ ደግሞ አይሰማህም እንዴ?” ብዬ ሌላኛው ስልክ ላይ መደወሌን ቀጠልኩ። እሱ ደግሞ ኧረ እኔ’ጋ አልደወልክም ብሎ ስልኩን ሲያሳየኝ እኔ ከሌላኛው ሰው’ጋ ማውራት ጀምሬ ነበር። ከዚያ አብሮኝ ያለው ሰው የስልኩን ስክሪን ዓይኔ ላይ አምጥቶ ደቀነው። “befeqe is calling…” ይላል። “ኧረ እኔ ከሌላ ሰው’ጋ እያወራሁ ነው!” አብሮኝ ያለው ሰው ስልኩን ሊያነሳ ሲሞክር እምቢ አለው። ሁኔታውን ‘ምትሐተ-ኢትዮቴሌኮም’ ብለነዋል።

ስልኮቹ በተመሳሳይ ሰዓት ካልተገናኙ (synchronized ካልሆኑ) ማውራት አይቻልም። እንዲህ ዓይነቱ መቀዣበር የሚፈጠረው ስልኮች ሲጠለፉ ነው። ኢትዮቴሌኮም (ወይም ወዳጆቹ) ስልኬን አይጠልፉም ብዬ ባልጠረጥርም የሁሉንም ሰው ስልክ ይጠልፋሉ ብሎ መጠርጠር ይከብደኛል። ፍላጎቱ ቢኖራቸውም አቅም ያንሳቸዋል። የኔትዎርኩ ችግር ደግሞ ባገር የመጣ ነው።

ጠለፋና ማስፋፋት

ሑዋዌይ በአሜሪካ የደኅንነት ቢሮ የጠለፋ ሶፍትዌሮችን እና ሀርድዌሮችን ይጠቀማል በሚል ከገበያ አግዶታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ከዜድቲኢ ጋር አብሮ የሚሠራው የቢሊዮን ዶላር የኔትዎርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሸልሞታል። ለኛ መንግሥት መሪዎች የአሜሪካው ዜና የምስራች ነው። እንዲያውም ሳስበው ዶ/ር ደብረፅዮን የሑዋዌይን ኃላፊ “እስኪ የሚወራባችሁን ነገር እኛ ላይ ተግብሯትና ይህን ሕዝብ ሲያወራ እንስማው” የሚሉት ይመስለኛል።

ግሎባል ኢንተርኔት ሴኩሪቲ በሪፖርቱ እንደነገረን ተንቀሳቃሽ ስልኮች በኢትዮጵያ ከ3% (እ.ኤ.አ. በ2008) ወደ 18% በ2012 ተዳርሷል። እድገቱ ሸጋ ነው፤ ከጎረቤቶቻችን አንፃር ካላየነው ማለቴ ነው። ከነዚህ ወስጥም ኢንተርኔት የሚሠሩት ስልኮች 6·2% ብቻዎቹ ናቸው።

እንደ ትራንስፎርሜሽን እና ዕድገቱ ዕቅዱ ከሆነ ግን 40 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተንቀሳቃሽ ይኖራቸዋል። ዶ/ር ደብረፅዮን እንደነገሩን ደግሞ ሌሎች 16 ሚሊዮን የሚደርሱ 3 እና 4ጂ የሚሠሩ ስልኮች ሲጨመሩ 56 እናዳርሳቸዋለን ተብሏል። ማስፋፊያው ሲጨረስ 85% ሕዝቡን የሚያዳርስ የተንቀሳቃሽ ስልክ እናቀርባለን ተብሎ ታቅዷል። ‘See Separate’ የተባለ ድርጅት ግን በ2015 እ.ኤ.አ. ቁጥሩ 99·6 ሚሊዮን ይደርሳል ከተባለው ሕዝባችን ውስጥ 34·2 ሚሊዮን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ብቻ እንደሚኖሩ (ከዕቅዱ’ጋ ሲነፃፀር 22 ሚሊዮን ያነሰ እንደሚሆን) በሒደቱ (projection) ገምቷል።

የታቀደው ግብ ቢመ’ታ መልካም ነበር። ግን ከታቀደው በታች ተፈፅሞም፣ ጥራቱ ተጓድሎም እንዴት ይሆናል? እስከዛሬ በሁሉም ዘርፎች ላይ የዘገየንባቸው ነገሮች ላይ ከሚሰጡ እልፍ ሰበቦች ውስጥ ‘በተዳራሽነት ብዛት ላይ ስናተኩር ጥራት አመለጠን’ የሚለው ይገኝበታል። ሁለቱም ላይ ካላተኮርን ሌላ ምን ላይ አተኩረናል ሊባል ነው?

ከሁሉም ግን ስጋቴ የደወሉላቸውን ደንበኛ ማግኘት፣ በፈለጉት ጊዜ የማይችሉ 56 ሚሊዮን የስልክ ደምበኞች እንዳናፈራ እሰጋለሁ።