ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ

(ሊያነቡት የሚገባ ሰፊ ትንታኔ)

 በኃይሌ ላሬቦ

የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስ የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅምን ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ። ማንዴላ የሚደነቁት፣ በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣ ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …