አቡጊዳ – ኢሕአዴግ የአንድነት መሪዎች ለማሰር እየተዘጋጀ እንደሆነ ተዘገበ
የአንድነት ልሳ የሆነዉ ፍኖት ነጻነት፣ ሰበር ዜና ብሎ እንደዘገበዉ፣ ኢሕአዴግ አቶ ዳን ኤል ተፈራን ጨምሮ በርካታ የአመራር አባላትን ለማሰር እየትዘጋጀ እንደሆነ፣ በፍትህ ሚኒስቴር ያሉትን ምንጮች በመግለጽ ዘግቧል።
« አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱን የፍትህ ሚ/ር ምንጮች አጋለጡ፡፡ ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያው ዙር ክስና እስር በ4 አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡» ሲል የዘገበው ፍኖት፣ የክስ ቅድመሁኔታዎች በፍርድ ቤት መጠናቀቃቸውን ገልጿል።