በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን፡፡ የሁሉም መነሻና መድረሻ ዓላማ መንፈሳዊ ይሁን እንጂ እንደ መስቀል፣ ጥምቀትና ሬቻ… ያሉ አንዳንድ በዓላት ከመንፈሳዊነታቸው በተጨማሪ የባሕል መገለጫ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም በዓላቶቹ በሚከበሩባቸው […]

የአንድነት ፓርቲ፣ በሶስት ከተሞች ታላላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለማድረግ መወሰኑን ከሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡ ገጽ አነበብኩ። እንቅስቃሴዎቹ የሚደረጉባቸው ከተሞች፣ አድዋ፣ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ናቸው። በአድዋ እና በአዲስ አበባ ከሌሎች ደርጅቶ ጋር በጋራ በመሆን (ሚአድ፣ አረና፣ ትብርር፣ መድረክ..) ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቡ ሁሉ ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል በማሰብ ትልቅ አከባባር ለማድረግ ነው የታቀደው። […]

በሳዉዲ መንግስት በግፍና ጭካኔ ተባረው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ፣ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ፣ «መንግስት ትኩረት አልሰጠንም» በሚል ድምጻቸውን ለማሰማት የተሰባሰቡ ወደ 400 መቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን በፖሊሲ እንዲበተኑ መደረጉን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው የፍኖት ጋዜጣ ዘገበ። «ቦሌ አካባቢ ከሚገኘው ጊዜያዊ ማረፊያቸው፣ ከ400 በላይ ሆነው ቅሬታቸውን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማሰማት ያቀዱትን […]

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ትላንት ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት መከበር ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት በቅርቡ 93ኛ ዓመታቸውን ላከበሩት ሌተናል ጀነራል ጃገማ ኬሎ የክብር መግለጫ ምስክር ወረቀት እንዳበረከተላቸው የማህበሩ ምክትል ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ም/ጸሀፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ለፍኖተ ነፃነት የሚከተለውን ብሏል “ሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ታላቅ […]

ዶቼ ቬለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀዉ «ምርጥ የድረ-ገፅ አምድ» በመባል የሚታወቀዉ ሽልማት በዓለማችን ጥሩ እንቅስቃሴን በማድረጉ የሚታወቅን ድረ-ገፅ በማወዳደር ሽልማት ያበረክታል። በዓለም ዙርያ በድረ-ገጽ ላይ ስለላ እጅግ እየተጣነከረ በመምጣቱ በርካታ ተጠቃሚዎች የግል ምስጢር ሰነዳችን በሌሎች እጅ ይወድቃል የሚል ስጋት ላይ ወድቀዋል።

ሁለት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ የ«ኦብነግ» ባለሥልጣናትን አግተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት የኬንያ ፖሊሶች በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሠረተባቸዉ የመዲናይቱን ናይሮቢ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ክፍልን ጠቅሶ አዣንስ ፍራን ፕሪስ ዘግቦአል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ሊቀ መንበር፣ እንዲሁም፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሊቀ መንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ደጋፊዎቻቸውን ለመጪው ምርጫ ለመቀስቀስ በወቅቱ በአውሮጳ

ዶቼ ቬለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀዉ «ምርጥ የድረ-ገፅ አምድ» በመባል የሚታወቀዉ ሽልማት በዓለማችን ጥሩ እንቅስቃሴን በማድረጉ የሚታወቅን ድረ-ገፅ በማወዳደር ሽልማት ያበረክታል። በዓለም ዙርያ በድረ-ገጽ ላይ ስለላ እጅግ እየተጣነከረ በመምጣቱ በርካታ ተጠቃሚዎች የግል ምስጢር ሰነዳችን በሌሎች እጅ ይወድቃል የሚል ስጋት ላይ ወድቀዋል።

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ልዩ ዞን በቡራዩ ከተማ ትናንት የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ የፌደራል ፖሊሶች በከተማዋ ወጣቶች ላይ የሚፈጽሙት ተደጋጋሚ ግድያ፣ የጸጥታ ስጋት ስለፈጠረብን አካባቢውን ለቆ ይውጣ በማለት መጠየቃቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ገዳይ የፌደራል ፖሊሶችን ለፍርድ እናቀርባለን በማለት ህዝቡን ለማረጋጋት እየሞከሩ ነው። በህዝቡና በፌደራል …

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመጥቀስ እንደዘገቡት በደቡብ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ አስከፊ ረሀብ መከሰቱን ተከትሎ የህዝቡ ህልውና አደጋ ውስጥ ወድቋል። የሲኤን ቢሲ ዘጋቢ እንደገለጸው ችግሩን ለመቅረፍ እስከ 100 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ ያስፈልጋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የያዘው የምግብ ክምችት ማለቁንም በዘገባው ተገልጿል። እንደ ሲኤን ቢሲ ዘገባ …

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታሳሪ ቤተሰቦች፣ የሚዲያ ባለሞያዎችና የውጭ አገራት ዲፕሎማቶች  በተገኙበት በተካሄደው ችሎት  የታሳሪ ጠበቆች የምስክሮቻቸውን አድራሻ አሟልተው አለማቅረባቸው በፍርድ ቤቱ ተገልጿል። ጠበቆቹ የምስክሮችን ስም በፍጥነት ለማስታወቅ ያልቻሉት ጂሃዳዊ ሐረካት ፊልም ለህዝብ መለቀቁን ተከትሎ በምስክሮች ላይ ፍርሀት በማደሩና የተለያዩ አካላት ስለሚያስፈራሯቸው ለደህንነታቸው በመስጋታቸው መሆኑን እንዲሁም የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃዎች ለማቅረብ …

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሚዲያ ዝግ በመሆን ለኢህአዴግ ካድሬዎችና ሹሞች በተዘጋጀው ውይይት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን  በኢትዮጵያ በልማታዊ አጀንዳ የሚወከለው ኢህአዴግ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች ፓርቲዎች ወይ ይህንን የሚጻረሩ ናቸው፣ ወይም ትርጉም የሌላቸው ናቸው ብለዋል።  ኢህአዴግ ለረጅም ጊዜ  በስልጣን ላይ ለማስቀጠል በመድብለ ፓርቲ ስም ይዞ …

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ መንግስት ጋባዥነት ከኢህአዴግ መንግስት ጋር ድርድር ለማድረግ በናይሮቢ የተገኙት ሁለቱ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት አመራሮች አቶ ሱሉብ አህመድና አቶ አሊ ሁሴን ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ መወሰዳቸውን የኬንያ መንግስት ባስታወቀ ማግስት፣ ሁለት ለኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ተቀጥረው ይሰሩ ነበር የተባሉ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለሰልጣኖቹ ለምሳ ተጋብዘው በመጓዝ …

ባለፈው ቅዳሜ (ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም) በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን የድህረምረቃ ተማሪዎች የኢትዮጵያን የፕሬስ ሁኔታ በልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት ውስጥ የሚኖረውን ሚና በተመለከተ የአንድ ቀን የውይይት መድረክ አዘጋጅተው ነበር። መድረኩ ዘግየት ብሎ ቢጀመርም የተጠናቀቀውን ግን ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ነው። የውይይቱ ሙቀትና ግለት በፈጠረው ስሜት የሻይና ቡና እረፍትን ያስፈለገው አልነበረም። በውይይቱ […]

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።” ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። “ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል። የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ “እኔን ነው?” የሚለው ወዶ ይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

‹ጉድ ሳይሰማ…›› እንደሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስርዓቱ እየተፈፀመበት ካለው ጭቆናና በደል፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋ፤ አፈናና ስደት፤ ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት በተጨማሪም በአምባገነን ገዥዎች እየተዋረደ፣ በአደባባይ እየተሰደበና ሰብዓዊ ክብሩ እየተጣሰ ይገኛል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖም ሀገራችን ላይ ያለው ስርዓት ህዝቡን የሚያዋርድ፣ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ስልጣኑን የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ የሌለው ነው፡፡ ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ […]

አንዱ ዓለም ተፈራ
በዕርግጥ የአንድን የሀገራችን ክፍል ነዋሪዎች ጉዳይ አንስቶ በአንድ መንገድ ወይንም በሌላ መንገድ መነጋገር፤ ወደድንም ጠላንም፤ ያለንበት ዘመን ግዴታ ሆኗል። ትናንት አኝዋኮች ተረሸኑ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን ተከበው ተሰቃዩ፣ ኦሮሞዎች በእስር ቤት ታጎሩ እያልን እንደጮህን ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ በአማራዎች ላይ የሚደርሰውን በደል አንስተን መነጋገር ግዴታችን ሆኗል። የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲህ ሆኑ፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲያ ሆኑ ስንል ብዙ ዓመታት ቆጠርን።በማይዘነጋ መንገድ ደግሞ እያንዳንዱን ለይተን እያነሳን፤ ይኼኛውን ብቻ የሚያደርጉ የዚህኛው ክፍል ብቻ ተወላጆችና ለዚያ ክፍል ብቻ ተቆርቋሪዎች ተደርጎ ስለሚወሰድ፤ እያንዳንዱን ጉዳይ “ለሌሎች” መተውና ጠቅላላ ኢትዮጵያዊንን በሚነኩ ጉዳዮች ላይ ብቻ መቆም፤ የታጋይነት ምልክት ተደርጎ የተወሰደ ፈሊጥ ሆኗል። እኔ ይኼን ትክክል ብዬ አልወስደውም። ለእያንዳንዱ ጉዳይ ቆሜ እቆጠራለሁ።
በኢትዮጵያዊነቴ የምኮራና በዚያ ብቻ ሀገራዊ የፖለቲካ ተሳትፎዬን የምለካ ስለሆነ፤ ይህ ጉዳይ ከአእምሮዪ ውጪ ነው። አማራው አማራ በመሆኑ ብቻ ለሚደርስበት በደል መቆርቆር፤ የግድ ከአማራ መወለድ አለበት የሚል ካለ፤ ዘረኛ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ አያምንም። ለአማራው የሚቆረቆረውን ሁሉ ደግሞ ትምክህተኛ አማራ የሚል ሁሉ፤ ዘረኛ ነው። አማራን ይጠላል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰውን በደል የኔ ብሎ ያልተነሳ ታጋይ ነኝ ባይ፤ ባይ እንጂ ኢትዮጵያዊ ታጋይ ነኝ ሊል አይገባውም። በአኝዋኩ ወገናችን፣ በኦሮሞው ወገናችን፣ በአማራው ወገናችን፣ በኦጋዴኑ ወገናችን የሚደርሰው በደል፤ የእያንዳንዳችን በደል ነው ብለን መውሰድ ካልቻልንና፤ የአንዱን ወገን በደል ብቻ ይዘን የምናቅራራ ከሆነ፤ ውሸታምና ዘረኛ ለመሆናችን ሌላ መረጃ አያስፈልግም። በዚህ ጽሑፍ፤ የአማራ ክልል ም/ፕሬዚዳንት እና የብሔራዊ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የተናገሩት፤ ምን ያህል ፀረ-ኢትዮጵያና፤ ውሃው የተቀዳበት ምንጭ የወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ፓርቲና መንግሥት የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ እንደሆነ አሰምራለሁ። እናም ደግሞ ይህ አደገኛ መርዝ፤ ጠንቀኝነቱን አሳያለሁ።

Image

የአማራው ሕዝብ

በወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ገዢ ቡድን የፖለቲካ ስሌት፥ አማራውን ማጥቃት፤ ከሥር መሠረቱ ሲፈጠር ምሰሶዬ ብሎ የያዘው የትግል ምሰሶው ነው። ቀጥሎም የመንግትነቱን ካባ ካጠለቀ ወዲህ፤ ከራሱ አልፎ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሥልጣን መቆናጠጫ ዋና መሰላሉ፤ ይኼን መቀበልና መተግበር ሆኗል። ይህ ደግሞ ከአማራው ወገን ተወለድን ለሚሉትም ሆነ ከአማራው ወገን አልተወለድንም ለሚሉት ሁሉ የሚሠራ መለኪያ ሚዛን ነው። አንድ ጭንቅላት ብቻ ነው ያለው፤ የገዢው ቡድን ጭንቅላት። ስለዚህ አቶ አለምነው መኮነን ተናገሩት ወይንም አቶ ደሳለኝ ሀይለ ማርያም ተናገሩት ለውጥ የለውም። ሁሉም አፋቸው እንጂ ጭንቅላታቸው የነሱ አይደለምና! እናም የግለሰቡን የአቶ አለምነውን ሰውነት ሳይሆን፤ የአቶ አለምነው መኮነንን ጭንቅላት ነው ማስመዘን የምፈልገው። ቀደም አድርጎ ግን አቶ አለምነው ጭንቅላት አላቸው ወይ? ወይንስ ጭንቅላት የላቸውም? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው። በዕርግጥ በዚህ ወራሪ በመሰለ አስተዳደር ለመዘፈቅ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ማንነትን ሽጦ መቆም ግዴታ ነው። ይህ በአእምሯቸው ሳይሆን በሆዳቸው የሚመሩ ሰዎች ብቻ የሚሰበሰቡበት አስተዳደር ለመሆኑ ማስረጃ፤ የራሳቸውን ነፃነት አለማግኘታቸው ነው። ወይንም በትክክለኛው አነጋገር፤ ራሳቸውን መሸጣቸው ነው። አእምሮ ማጣታቸው ማለቱ ይቀላል።

ወንጀል ከተፈፀመ፤ እከሌ ወይንም እከሌና እከሌ ይኼን ሠሩ ወይንም ያንን ሳይሠሩ ቀሩ ብሎ አንድን ወይንም የተወሰኑ ግለሰቦችን መወንጀል፤ ተገቢ ነው። በአንድ ሀገር ያሉትን የአንድ የኅብረተሰብ ክፍል አባላትን ግን ለይቶ ይኼን አደረጉ በተለይም እንዲህ ናቸው ብሎ መወንጀል፤ ከግልብነቱ በላይ የኅብረተሰብን ምንነት አለማወቅን የሚያሳይ አጉሊ መነፅር ነው። ከዚህ ተነስቼ ነው የአቶ አለምነው መኮነንን ንግግር የምረዳው። እስኪ ከአቶ አለምነው መኮነን ንግግር ጠቀስ አድርጌ፤ ጭንቅላት አላቸው ወይንስ የላቸውም? ያስባለኝን ላሳያችሁ፤
፩ኛ፤ “ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት። ”
፪ኛ፤ “ የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል። ”
፫ኛ፤ “ በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው። ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም። ”
፬ኛ፤ “ ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት። ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም። ”
፭ኛ፤ “ ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው። ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው። ያንን ምግብ እየተመገበ ያቅራራል። ”
እዚህ ላይ አቶ አለምነው መኮነን ሁለት መልዕክት ባንድ ላይ አስተላልፈዋል። የመጀመሪያው፤ የአማራውን ጠባየ ቢስነት አመልክቶ፤ አማራውን መኮነን ሲሆን፤ በሥር አስደግፎ ደግሞ፤ አማራው ከሌሎች ቦታዎች በተሰደደበት ምክንያት መንግሥታዊ አካላት ተጠያቂ አይደሉም ብሎ ለማሳመን የተቀመመ መርዝ ነው። ለመሆኑ አቶ አለምነው መኮነን ኢሕአዴግ ራሱ፤ የአማራውን ከሌሎች መፈናቀል ትክክል አልነበረም ሲል፤ የት ነበሩ? መንግሥት በየደረጃው፤ “ደን ስለጨፈጨፉ ነው” ሲል፤ የት ነበሩ? ይኼ የናንተ ቦታ አይደለም ሲባሉ፤ የት ነበሩ? ወይንስ ኢሕአዴግ የአቶ አለምነው መኮነንን ጭንቅላት በመጠቀም፤ ያመነበትን ባደባባይ ተናግሮ በጓሮ በር ራሱን ነፃ ለማውጣት የለከካት መልዕክት ናት? የተፈናቀሉት በትምክህተኛነታቸው ሳይሆን በአማራነታቸው ነው። ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ አዛውነት፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ደሃዎች፣ ባለፀጎች፣ ሁሉም ታታሪ ሠራተኞች ተባረዋል። ያካባቢው ሰዎች በተቻላቸውና መንግሥታዊ መዋቅሩ በማያውቀው መንገድ ድጋፍና ሐዘኔታ ሠጥተዋቸዋል። ይህ መንግሥታዊ ተግባር ትክክል ስላልሆነ ወደ መጡበት ይመለሱ ሲል ኢሕአዴግ ራሱ ወስኗል። አቶ አለምነው መኮነን! በኢሕአዴግኛ አነጋገር ወንጀለኛው እርስዎና እንደርስዎ ያሉት አፈናቃዮች ናቸው። ተራዎ ደርሶ፤ እርስዎም መጠቀሚያነትዎ አብቅቶ፤ እስኪባረሩ ወይንም ዘብጥያ እስኪወረወሩ ድረስ፤ ከወገብዎ በደንብ ልምጥ ይበሉ!
አማራው እንዲህ ነው ብሎ መጮህ፤ አማራውን ሌሎች እንዲበድሉት ፍቃድ ፈርሞና ታርጋ ለጥፎ መሥጠት ብቻ ሳይሆን፤ አማራው በተፈጥሮ ጎደሎ ስላለበት፤ ከአማራ የተገኘ ሁሉ፤ አብሮ ለመኖር አይመችምና፤ ከያለበት አባሩት ማለት ነው፤ ከኢትዮጵያዊነትም! ይህ ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-ሰብዓዊነት ነው። ለነገሩ በዚህ ሹመት ከተመደበ በሆዱ ተንፏቆ በሆዱ ከሚያድር ሹም ሌላ ምን ይጠበቃል? አቶ አለምነው መኮነን ከአማራው ወገን ተወላጅ መሆናቸው ዋጋ የለውም። የአቶ በረከት ስምዖንም የአማራው ተወላጅነትና ተወካይነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ! እንዲህ ነው በአማራው ላይ መሾም ማለት!
በሌላ በኩል ስለ አንቀጽ 39 ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። እስኪ ለምን ቀረበላቸው የሚለውን እናጢን! አንቀጽ 39 አማራውን ለብቻው እንደ አማራነቱ የሚጎዳው ነው ወይ? አማራውን ማጥቂያ መሣሪያ በመሆኑ ነው ወይ? የአማራ ክልል ሰዎች እንዲጠይቁ የተገደዱት? ጥያቄውን ማንሳታቸው የሚያመለክተው፤ አንድም አማራን ማጥቂያ መሣሪያ በመሆኑ፤ ወይንም የኢትዮጵያን አንድነት አማራው አጥብቆ ስለያዘ ነው። ከዚህ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም። ታዲያ አማራው የሚጠቃበት መንገድ፤ በኢትዮጵያዊነቱ ነው ማለት ነው። በተለይም ኢትዮጵያዊነትን ስላጠበቀና በመላ ኢትዮጵያ ተበትኖ ስለኖረ። እናም አንቀጽ 39፤ “ኢትዮጵያን ለመጉዳት የታሰበ ወይንም አማራን ከማጥቃት ጋር የተያያዘ ነው።” ብለው ቢያንስ በአማራው ክልል ያሉት የራሱ የገዥው ካድሬዎች ያምናሉ ማለት ነው። ይኼ ራሱን ችሎ የሚታይ በመሆኑ እዚህ ላይ አስተያየት አልሠጥበትም። ለዚህ ጥያቄ የአቶ አለምነው መኮነን መልስ ደግሞ፤
፮ኛ፤ “ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ ታይቷል። ”
በዚህ መልስ የምረዳው፤ አቶ አለምነው መኮነን እንደ አቶ ደሳለኝ ሀይለማርያም የራሳቸውን ጭንቅላት ተጠቅመው የሚሠሩ ሳይሆን፤ በሟቹ “ባለራዕይ” መሪያቸው የሚጎተት መሆኑን ነው። ሟቹ ቢኖሩ ከዚህ የተለዬ እንደማይናገሩ ስለምናውቅ፤ አቶ አለምነው መኮነን ማስተላለፊያ ቀፎ መሆናቸውን ተረዳሁ። ታዲያ የአቶ መለስ ዜናዊን ቀሚስ ለምን አያጠልቁም? አዎ አምባገነኖች ከነሱ ሌላ በራሱ ጭንቅላት አስቦ የሚሠራ እንዲኖር አይፈልጉም። ታሪክም ይኼንኑ ነው የሚያስረዳን።
እንግዲህ አንደኛ፤ አቶ አለምነው መኮነን የራሳቸው ጭንቅላት የላቸውም ወይንም አከላቱ እንደ ግንድ በድኖ ከራሳቸው ውስጥ ቢኖርም፤ የገደል ማሚቶ ሆኖ ከማስተጋባት ሌላ ሙያ የለውም ማለት ነው። ሁለተኛ፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነን ተግባር፤ በአማራው ትምክህነት ማመካኘት፤ አደገኛና ለወደፊቱ የአማራውን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን፤ የአማራውን የኅብረተሰብ አካልነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ መርዝ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ልጠቁም የምፈልገው፤ ራሱ ኢሕአዴግ ሳይወድ ተገዶ ያመነበትን የአማራውን የማፈናቀል ወንጀል፤ ከኢሕአዴግ አሳልፎ በአማራው ላይ ለመለከክ የተደረገ የብልጠት ቅሌት ነው። ማሳረጊያው ግን፤ ይኼን መዘርዘሩ ሳይሆን፤ ይኼን ማውገዙ ሳይሆን፤ ይህ እንዳይደገም ሆነ ለዚህ ተጠያቂዎችን በሕግ ፊት ለማቅረብ፤ የታጋዩ ወገን ምን እያደረገ ነው? ነው። ይህ ትግል የኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያዊነታችን አንድ ራዕይ ኖሮን በአንድ ድርጅት ተሰባስበን የምንነሳበት ትግል ነው። ይህ የአማራው ብቻ እንጂ፣ የትግሬው፣ የኦሮሞው፣ የደቡቡ፣ የኦጋዴኑ፣ የአኙዋኩ የግል ጉዳይ ያልሆነ አይደለም። የኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነው።
ኢትዮጵያዊያን የኔ ብለን በአንድነት እስካልተነሳን ደረስ፤ መፍትሔው የውሃ ውቀጥ መፍትሔ ነው፤ ውሃን ቢወቅጡት መልሶ እምቦጭ ነውና! ከነአቶ አለምነው መኮነን ሆነ ከአሽከርካሪዎቻቸው ተወግዘውም ሆነ ተለምነው መፍትሔ እንዲሠጡን መጠበቅ፤ ላም አለኝ በሰማይ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ከጥር ከነገ አንስቶ እስከፊታችን ዓርብ፤ በ 126ኛው ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ፣ በክብር እንግድነት በመገኘት እንደሚሳተፉ ተነገረ። ስብሰባው የሚካሄድባት ከተማ ፣ የክረምት ኦሊምፒክ እስፖርት ውድድር የምታዘገጀው የሩሲያ ከተማ ሶቺ ናት።

ምንም እንኩዋን የገዢው ፓርቲ ወከባ ቢፈታተነንም ትላንት እሁድ በጎንደር ከተማ የጠራነው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ስኬታማ ነበር ሲል ስማያዊ ፓርቲ ኣስታወቀ።

የፓርቲው ም/ሊቀመንበር ዛሬ ለዶቸቬሌ እንደነገሩት መንግስት ከህዝብ እውቅና ውጪ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ኣሳልፎ ለመስጠት የያዘውን ስውር ደባ በመቃወም ነበር ስማያዊ ፓርቲ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግጭቱ የተከሰተው ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ለግጭቱ መነሻ የሆነውም ኮንሶዎች ባጋጠማቸው የመሬት እጥረት ሳቢያ ወደ ቦዲዮች አካባቢ ሄደው በመስፈራቸው መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ። በግጭቱ ከሁለቱም ወገኖች 4 ሰዎች ሲሞቱ፣ 3 ኮንሶዎች እና አንድ ፖሊስ ቆስለዋል። 72 ቤቶችም እንዲሁ ተቃጥለዋል። ከዚህ በፊት ሁለቱ ብሄረሰቦች በተደጋጋሚ ሲጋጩ ቆይተዋል። ቀደም …

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማዎቅ እንደተቻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር በዘላቂነት ለማቃለል በሚል ከዚህ በፊት ከነበረው የ 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም በተጨማሪ በአማራጭ የ 10/90 አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለመለስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው በ40/60 የቁጠባ …

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀኔራል ክንፈ ዳኛው ስራ አስኪያጅነት የሚመራው በስሩ ከ13 በላይ ኩባንያዎችን ዬያዘውና በብዙ ቢሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወይም ብኢኮ አሰራር ግለጽነት የጎደለው መሆኑን የጸረ ሙስና ኮሚሽን ባወጣው የ6 ወራት ሪፖርት ገልጿል። ብኢኮ ከተቋቋመበት ከ1995 ዓም ጀምሮ አሰራሩ ለሙስና በር የሚከፍት መሆኑ በተደጋጋሚ በኢሳት ሲዘገብ …

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚኒስትሮች በሚመራው የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችን እና የሚዲያውን ነፃነት የገፈፈ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡ ባህርዳር ከተማ በማካሄድ ላይ ባለው በዚህ የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ ” የፕሬስ ነፃነት በሀገሪቱ ሊኖር ባለመቻሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ጋዜጠኞች ሳይቀር ተሸማቀው እንዲሰሩ እየተደረገ ያለው የአስራር …

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ እውቁ የነጻነት ታጋይና በቅርቡ ከዚህ አለም የተለዩት ኔልሰን ማንዴላ ሀብቱን ያፈሩት በጆሀንስበርግ እና በኬፕ ታውን ከነበራቸው ቤት ሽያጭ እንዲሁም ከመጽሃፋቸው ከተገኘ ገቢ ነው። ማንዴላ ከእርሳቸው ጋር ሲሰሩ ለነበሩት ለእያንዳንዳቸው 50 ሺ የደቡብ አፍሪካ ገንዘብ እንዲሁም እርሳቸው የተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች 100 ሺ ራንድ እንዲሰጣቸው …

ኦሞት ኦባንግ – የታዳኝ አዳኝ ድራማ
ኢህአዴግም በበኩሉ እያደናቸው ነው
“ሁሉም ከህግ አያመልጡምና ዜጎች መረጃ በመሰብሰብ የቤት ስራችሁን ስሩ” ኦባንግ ሜቶ

ኦሞት ኦባንግ በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለፍርድ እንዲቀርቡ እየታደኑ ነው
ሰሞኑን አገር ጥለው መኮብለላቸው የተደመጠው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦሞት ኦባንግ በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታወቀ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፍትህ የተዛባባቸው ዜጎች ሁሉ መረጃ በማሰባሰብና ለድርጅታቸው በመላክ የዜግነት የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ኦሞትን ፍትህ ደጅ ለማቆም ከ19 ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በኅብረት እየሰሩ መሆናቸውም አመልክተዋል። በሌላም በኩል ኢህአዴግም “ነገር ሳይበላሽ” እያደናቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

በ2003 በጅምላ ለተጨፈጨፉና በሺህ ለሚቆጠሩ የአኙዋክ ተወላጆች መሰደድ ከመለስ ቀጥሎ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚባሉት አቶ ኦሞት፤ ሳምንት በፈጀ ግምገማ ከክልሉ ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸውና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መመደባቸው ይታወሳል። “እውነተኛው ወያኔ” እየተባሉ የሚጠሩት አቶ ኦሞት ምንም እንኳ በሚኒስትርነት ደረጃ ቢመደቡም በሙስና ተወንጅለው እንደሚታሰሩ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።

በሰኔ 10፤2005 ዓም (June 17, 2013) የጎልጉል ዘገባ ላይ እንደተጠቀሰው ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር ተደራጅቶ ለኢህአዴግ የድርጅት ቢሮ ቀርቦ ነበር። የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን የጠቆመው ዘገባ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ይፋ የሚያደርጉ ነበሩ። በወቅቱ “መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” ተብሎም ነበር። የመረጃ ምንጫቸውን ባይጠቅሱም አቶ ኦባንግ “ኦሞትን በተመለከተ ከበቂ በላይ መረጃ አለን፤ ህግ ፊት እናቀርበዋለን፤ በንጹን ደም ተጨማልቆና ህዝብ ላይ ግፍ ፈጽሞ መሰወር አይቻልም” በማለት በስልክ ለጎልጉል ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ በድንገት ምሳ እየተመገቡ ከመርዝ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው በድንገት ማለፉ ይታወሳል።

ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ ም ጀምሮ ሟቹ አቶ መለስ በላኳቸው አስገምጋሚዎች ለሳምንት በተካሄደ አውጫጪኝ አቶ ኦሞት “የአኙዋክ ተወላጆችን አስጨፍጭፈሃል” የሚል መነሻውና ዓላማው ግልጽ ያልሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። በወቅቱ ግምገማው ላይ የነበሩ እንዳሉት አቶ ኦሞት “እኔ በዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ከሆንኩ መሳሪያና ወታደር የሰጠኝ መለስም ይታሰራል” በማለት መልስ ሰጥተው ነበር።

በወቅቱ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት ድርጅት /አኢጋን/ አቶ መለስን በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ችሎት ተጠያቂ ለማድረግ ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ያገኘበትና አቶ መለስ ላይ ክስ እንዲመሰረት ውሳኔ የተደረሰበት ዜና የተሰማበት ነበር። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የጋምቤላ ምንጮች “አቶ መለስ አቶ ኦሞትን በጭፍጨፋው ተጠያቂ በማድረግና ርምጃ በመውሰድ ራሳቸውን ጲላጦስ ለማድረግ የወጠኑት አካሄድ እንደሆነ የፌዴራል ሰዎች ነግረውናል። ኦሞትም በሙስና በዘረጋው መዋቅር እስከላይ ድረስ ዘመድና ተቆርቋሪ ስላበጀ መረጃው ደርሶት ነበር” ብለዋል። /በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የተመሰረተው ክስ መለስ ቢሞቱም እስካሁን ክፍት ነው/

በሌላም በኩል ወቅቱ በክልሉ ኢህአዴግ ለልማት በሚሰጠው ርዳታ ዜጎችን ለማፈንና ረግጦ ለመግዛት የሚያስችለውን ሃይል ያደራጅበታል በሚል ተቆርቋሪዎች መረጃ አስደግፈው ባቀረቡት ክስ ዓለም ባንክ አጣሪ የላከበት ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ መሬታቸውን፣ የትውልድ ቀያቸውን በአንጋቾች የተነጠቁ ምስኪን ዜጎች ድምጽ ዓለም አቀፍ ትኩረት አግኝቶ ኢህአዴግን ክፉኛ የተፈታተነበት ነበር። ለዚህ ይመስላል ኢህአዴግ በግምገማ በርካታ የክልሉን ሃላፊዎች ወረዳ ድረስ በመዝለቅ በሙስና ሰበብ ሲያባርርና ሲያስር፣ አቶ ኦሞትን ወደ ፌዴራል በማዛወር በቅርብ ይከታተላቸው ነበር። አቶ ኦሞት ወደ ፌዴራል ሲዛወሩ “የቤንሻንጉል ጉምዝ ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹ ላይ የተደረገው ይፈጸምባቸዋል” ተብሎ አስቀድሞ ተተንብዮ ነበር።

ለአብነት ከላይ በተዘረዘሩት መነሻዎችና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ሳቢያ የአቶ ኦሞትና የህወሃት ግንኙነት ማክተሙን የሚናገሩት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች፣ “ቀደም ሲል ህወሃትን ሲያገለግሉ ኖረው መጨረሻቸው እስር እንደሆነው አራት የቀድሞ የክልሉ መሪዎች፣ ወይም እንደ አምስተኛው ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ስደት እጣ ፈንታቸው ይሆናል” የሚል ቅድመ ትንበያ ነበር።

አቶ ኦኬሎ አኳይ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ክልሉን ወክለው የተዛባ መረጃ እንዲሰጡ ታዘው ነበር። በአቶ አባይ ጸሃዬና ገብረአብ በርናባስ መመሪያ መሰረት ግጭቱ በጎሳ ላይ የተመረኮዘ የርስ በርስ እንደሆነ፣ በግጭቱ 59 ሰዎች ብቻ ሲሞቱ አንድ ቤት መቃጠሉን እንዲናገሩ የተሰጣቸውን መመሪያ ያልተቀበሉት አቶ ኦኬሎ ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ አገር ጥለው መሰደዳቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ በተደጋጋሚ ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ አቶ ኦኬሎ አኳይ በስደት ሆነው በይፋ በዚህ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት አለመድፈራቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ ጉዳይ ሆኗል።

ኦሞት የት ናቸው?

አቶ ኦሞት የክልሉ የደህንነት ሃላፊና ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ፍጹም ታማኝ ስለነበሩ በ2005 የተሰጣቸው የክልል መሪነት ስልጣን ለህወሃት ለሰሩት ውለታ የተከፈለ ወሮታ እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚወሰደው። በዚሁ መነሻ ይመስላል አብዛኛው የጋምቤላ ተወላጆች ለአቶ ኦሞት የከፋ ጥላቻ እንደነበራቸው የሚናገሩ ክልሉ ተወላጆች፣ ኦሞት ከአገር ኮበለሉ መባሉ አያስገርማቸውም።

አሁን ጥያቄው ኦሞት ከኢህአዴግ አፍንጫ ስር እንዴት አመለጡ? አሁን የት ናቸው? መጪው እጣ ፈንታቸውስ? የሚለው ነው። አዲስ አድማስ ባለፈው ቅዳሜ እትሙ አቶ ኦሞትን የግምባር ዜና አድርጎ ሲያቀርብ አገር ጥለው መኮብለላቸውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ማረጋገጣቸውን አስነብቧል። አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ኦሞት ከሁለት ወር በፊት ለስልጠና አውሮፓ ሲመጡ በነበራቸው ቪዛ ከሁለት ሳምንት በፊት ዓርብ ቀን አገር ጥለው እንደወጡ መረጃው አላቸው።

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከ19 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እየሰሩ መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ “ኦሞት መለስ በህይወት እያለ ቢኮበልል መልካም ነበር። አሁን ከኦሞት የምንፈልገው ችሎት ፊት በወገኖቹ ላይና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ፣ ቶርቸር፣ እስር፣ ዝርፊያ፣ የመሬት ንጥቂያ፣ ወዘተ አስመልክቶ እንዲናዘዝ ነው” ብለዋል። ኮብላዩ አቶ ኦሞት የት እንደሚገኙ ተጠይቀው “አሁን እዚህ ነው የሚባልበት ደረጃ ላይ አይደለንም። ግን መሰወር የሚችል አይመስለኝም። በደም ተጨማልቆ በስደት ተበዳይ መስሎ መኖር አይቻልም። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ከመለስ ጋር በተመሰረተው ክስ ላይ ኦሞት የተካተተ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። እኛ እንኳ ዝም ብንል ፍትህ በርዋን አትዘጋም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ አቶ ኦሞት አገር ጥለው የወጡት ከሁለት ሳምንት በፊት ሲሆን አንድ ሳምንት ቢዘገዩ ኖሮ እስር ቤት ይገቡ ነበር። አስቀድሞ በደረሳቸው መረጃ መሰረት አቶ ኦሞትን እስር ቤት እንዲወረወሩ የሚያዘው የአስር ማዘዣ የሚቆረጥበት ግምገማ ተዘጋጅቶ ነበር። እሳቸው አስቀድመው አገር ጥለው በመውጣታቸው ግምገማው ተስተጓጉሏል። ግምገማው የዓለም ባንክ አጣሪ ቡድን በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ሲገባ በሙስናና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ኢህአዴግ ርምጃ በመውሰድ ዝግጅት አጠናቆ ለመጠበቅ የሚረዳው ነበር። ግን አልሆነም።

በጋምቤላ በኢቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ከሚሰሩት መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችና የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው አቶ ኦሞት የሚደረግባቸውን ክትትል አልፈው አገር ሊወጡ እንደቻሉ ግምት አለ። አሁን “ባለሃብት” የሚባሉት እነዚህ ክፍሎች ባላቸው መዋቅር ሳቢያ አቶ ኦሞትን ሊታደጓቸው እንደሚችሉ ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ።

አቶ ኦሞት ሆላንድ ገብተዋል የሚሉም አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አውሮፓ ሊገቡ አይችሉም በማለት ግምቱን የሚያጣጥሉ አሉ። እነዚህ ክፍሎች ወደ ማሌዢያ ሄደዋል የሚለውን ምንጭ ይደግፋሉ። በስፋት እንደሚነገረው ከሆነ አቶ ኦሞት ኤዢያ እንደሚሄዱ የሚያጠናክሩ ምልክቶች አሉ። አብዛኛው የኢህአዴግ ባለስልጣኖች በማሌዢያ ባንኮች ገንዘብ አላቸው። አቶ ኦሞትም በተመሳሳይ የማሌዢያ ባንክ ተጠቃሚ ናቸው ተብሎ እንደሚገመት የሚቀርቧቸው ይናገራሉ። በተመሳሳይ በኢንቨስትመንት ስም የተወዳጇቸው ባለሃብቶች በኤዢያ ከለላ ሊሆኗቸው ስለሚችሉ የመጀመሪያ ምርጫቸው ኤዢያ እንደሚሆን ይስማማሉ።

ለጎልጉል ማንነታቸውን ሳይገልጹ መረጃ የሰጡ የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት “ኦሞት ርቆ አልሄደም ይያዝል” በማለት ግምታቸውን ሰጥተዋል። ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉ የገለጹት እኚህ ሰው “ኦሞት ብዙ ጉዳዮችን እንዳያበለሽ ጥንቃቄ ሲደረግ ነበር። እንዴት ለጊዜውም ቢሆን ተሰወረ?” የሚለው መነጋገሪያ መሆኑን ግን አልሸሸጉም። ኦሞት በወቅቱ የፈጸሙትን ከ400 በላይ የአኙዋኮችን ጭፍጨፋ፣ የተሳተፉበትን ሙስና፣ የመሬት ነጠቃ፣ ግድያ፣ ወዘተ የወንጀል ምስጢር በማውጣት ኢህአዴግን አሳጥተው ፍርድ እንዲቀልላቸው መደራደሪያ ከማድረጋቸው በፊት ኢህአዴግ የራሱ አደን አጠናክሮ እንደሚገኝ ተጨማሪ ዘገባዎች አሉ፡፡

አቶ ኦባንግ ሜቶ የኦሞት መሰወር አያስጨንቅም ባይ ናቸው። ኦሞትን ፍትህ አሳድዳ ትይዘዋለች የሚሉት አቶ ኦባንግ ትኩረታቸው ወንጀል የተፈጸመባቸው በሙሉ መረጃ በመሰብሰብና ወደ ጋራ ንቅናቄው በመላክ እንዲተባበሩ የመነሳሳታቸው ጉዳይ ላይ ነው። ህወሃቶች ወንጀል አሰርተው፣ መጨረሻ ላይ ፍትህ ወዳድ ለመምሰል በወንጀል ያጨማለቋቸውን ሰዎች ህግ ፊት አቅርበው እንደሚያስፈርዱባቸው ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ሌሎች ከዚህና ከቀድሞው ተሞክሮ ተማሩ። ኦሞትን ፍትህ አደባባይ ለማውጣት የሚሰራው ስራ ወንጀለኞችን ለመፋረድ የምናደርገውን ትግል አንድ ርምጃ ያሳድገዋል። እንደ ኦሞት ያሉት ወንጀለኞች ካሉበት ይለቀማሉ። ይህንን ማድረግ አቅም አለን። በደም ተጨማልቆ በስደት መኖር አይቻልም። ሌሎችም ካሁኑ ንስሃ ግቡ፤ ህብረተሰባችሁን አስቀድሙ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ህወሃትም ሆነ ኢህአዴግ በራቸውን መክፈታቸው ወይም ለውጥ እንዲመጣ እንዲፈቅዱ የሚገደዱበት ዘመን መቃረቡን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ነጻ ውጡና ህዝባችሁን ነጻ አውጡ፣ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለወንጀለኞች ቦታ የላትም፣ ትፋረዳቸዋለች” ሲሉ በድጋሚ ህዝብ በወንጀለኞች ላይ መረጃ በማሰባሰብ የቤት ስራውን በወጉ እንዲሰራ ጠይቀዋል።
>
> Please click the link to read the entire report http://www.goolgule.com/the-hunt-for-omot-obang-olum-continues/

እቅድ – ትራንስፎርሜችን – ራእይ = ኢሕአዴጋዊ መንጠራራት
አቅዶ የሚያብድ ሥውር አደገኛ ሕሊና፣ ቁምነገር አልባ ነው!

የሰላም ትልቁ ጠላት ከአቅም በላይ መመኘት ነው፡፡
የሥራ መንፈስ ከብዙሃኑ የልብ ፍቅርና የአገር መውደድ ስሜት ጋር በፅኑ መቆራኘት አለበት፡፡ ላገር አሳቢ እየመሰለ ውስጥ ውስጡን እንደሚቦጠቡጥ ሹም ባለበት ቦታ ዕቅድ ሲታቀድ ቢውል ፍሬ-ቢስ ነው የሚሆነው። ነባር ነባር በላተኛ አባርረን ትኩስ ትኩስ፣ ልጅ-እግር በላተኛ ካመጣን፤ የበላተኞች መተካካት እንጂ የአዲስ ደም – ቅያሪ አይሆንልንም፡፡ እጃችንን ዘርግተን የማንደርስበትን ነገር ለመጨበጥ መሞከር፤ በር ከፍተን ለዘራፊ እንደመተው ነው፡፡ የሰላም ትልቁ ጠላት ከአቅም በላይ መመኘት ነው፡፡ አሊያም የክቡር እምክቡራን ዕብደት ነው። “ከአቅም በላይ መኖር የዕድገት ፀር ነው” ይሉ ነበር ያለፈው ሥርዓት ነገረ-ሠሪዎች! ኮከብ እነካለሁ ብሎ ሠምበሌጥ ላይ መወድቅ ይከተላል፡፡ ለራስ ጥቅም ሲሉ የአገር ዕቅድ አወጣሁ ማለት መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ድህነት ባጠጠበት፣ ችጋር በተንሠራፋበት አገር እንደ ህንድ እጉልላቱ አናት ላይ ጥቂት ባለ ፀጋ ሰዎች ብቻ ተቀምጠው፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን መመኘት ከንቱ መገበዝ ነው፡፡

በአየር ላይ ህንጻ መገባት እንደማይቻለው ሁሉ ማቀድና በባዶ ሜዳ መመኘት እጅግ የተራራቁ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ማቀድ፤ በዝርዝር ያቀድኩትን ለመፈፀም ምን ምን አደርጋለሁ ማለትን፣ ያንንም ማስፈፀሚያ ፋይዳ ያለው ቁሳቁስንና አጋዥ የሰው ኃይልን፤ እንዴት እቀዳጀዋለሁ ማለትን፤ በመጨረሻም ቀን በቀን ሥራ ላይ ማዋልን ይጠይቃል፡፡ በዚህ ማህል ባይሳካስ ብሎ ማውጠንጠንን፣ ሁለተኛ ዘዴ መዘየድን እቅድ 2 እንዲሉ የግድ ማሰብን ይሻል፡፡ ካልሆነና አማራጭ ሁሉ ከተሟጠጠም በጊዜ ሀሳብን ለውጦ ወደ ሌላ ዕቅድ መሸጋገር ነው፡፡ ከዚህ ቀላልና ግልፅ መንገድ ውጪ በጉልበት ልሥራህ ቢሉት ሀብትንም ማባከን፣ የሰው ኃይልንም በአጓጉል መንገድ ሜዳ ማፍሰስ ነው፡፡ እግርህን በአልጋህ ልክ ዘርጋ፤ እንደማለት ነው፡፡ ይህን በአገር ደረጃ መንዝሮ ማየት ነው እንግዲህ አገርን ለማሳደግ መጣጣር፡፡ ከምንጨብጠው በላይ መጀመሪያ እጃችን ረዥም መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል;;

“ይህንንማ ማን ያጣዋል ይሄንን ማንም ያውቀዋል፡፡ ዝቅተኝነት’ኮ፣ የለጋ ምኞት መሰላል ነው ጠዋቱን ሥልጣን የጠማው:- ደረጃውን ሲያያዘው፣ ሽቅብ ሽቅብ ያንጋጥጣል ጫፉ ላይ ሲደርስ ግና፣ ጀርባውን ለመስጠት ይሻል ጧት የበላበትን ወጪት፣ ማታ ሰባሪ ይሆናል ቀና ብሎ ወደ ሰማይ፣ ደመናውን ብቻ ያያል እላይ ያወጣውን ታች ሰው፣ ቁልቁል ረግጦ ይሳደባል” ይላል የሺክስፒሩ ብሩተስ፡፡ ዞሮ ዞሮ ዕቅድ እንደ አቃጁ፣ ዕቅዱ እንደ ከዋኙ ነው፡፡ የሸር ዕቅድም፣ የአውቆ-አበድ ዕቅድም አለና ጠንቅቆ ማየት ይገባል፡፡ ታዋቂው ፀሀፌ-ተውኔት ፀጋዬ ገብረ መድህን በሚኒልክ ተውኔት፣ በኢልግ አፍ፣ እንዲህ ይላል፡- “ኮንቲ ኦሊኒ ግን ጭምት፣ ቀዝቃዛ፣ ነገር ለማሻከር ሆን ብሎ በዕቅድ የሚቆጣ፣ ሆን ብሎ በዕቅድ እንዳስፈላጊው ሁኔታ የሚያብድ፣ አንድ ነፃ መንግሥት ያለኔ ፈቃድ ለምን ሰንደቅ ዓላማ ተከለ ብሎ በነገረ-ቀደም አቅዶ እሚጮህ፤ … አቅዶ የሚያብድ ሥውር አደገኛ ሕሊና፣ ቁም – ነገር – አልባ ሰው ነው!” ከዚህ ይሰውረን፡፡ ዕቅዶች ይከወናሉ፡፡ ፓርቲዎች ይለመልማሉ፡፡ አገር ታድጋለች፡፡ የዕለት ጉርሥ የዓመት ልብስ ይኖረናል ማለት ያባት ነው፡፡ ሆኖም ያ እስኪሳካ ድህነት አንድያውን እንዳያደቀን ሁሉን በወግና በቅጡ ማስተካከል፣ መቆጣጠር፣ መተግበር ያስፈልጋል፡፡minilik salsawi

Image

“ሁሉም ከህግ አያመልጡምና ዜጎች መረጃ በመሰብሰብ የቤት ስራችሁን ስሩ” ኦባንግ ሜቶ
ኦሞት ኦባንግ በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለፍርድ እንዲቀርቡ እየታደኑ ነው

ሰሞኑን አገር ጥለው መኮብለላቸው የተደመጠው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦሞት ኦባንግ በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታወቀ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፍትህ የተዛባባቸው ዜጎች ሁሉ መረጃ በማሰባሰብና ለድርጅታቸው በመላክ የዜግነት የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ኦሞትን ፍትህ ደጅ ለማቆም ከ19 ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በኅብረት እየሰሩ መሆናቸውም አመልክተዋል። በሌላም በኩል ኢህአዴግም “ነገር ሳይበላሽ” እያደናቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

በ2003 በጅምላ ለተጨፈጨፉና በሺህ ለሚቆጠሩ የአኙዋክ ተወላጆች መሰደድ ከመለስ ቀጥሎ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚባሉት አቶ ኦሞት፤ ሳምንት በፈጀ ግምገማ ከክልሉ ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸውና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መመደባቸው ይታወሳል። “እውነተኛው ወያኔ” እየተባሉ የሚጠሩት አቶ ኦሞት ምንም እንኳ በሚኒስትርነት ደረጃ ቢመደቡም በሙስና ተወንጅለው እንደሚታሰሩ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።

በሰኔ 10፤2005 ዓም (June 17, 2013) የጎልጉል ዘገባ ላይ እንደተጠቀሰው ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር ተደራጅቶ ለኢህአዴግ የድርጅት ቢሮ ቀርቦ ነበር። የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን የጠቆመው ዘገባ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ይፋ የሚያደርጉ ነበሩ። በወቅቱ “መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” ተብሎም ነበር። የመረጃ ምንጫቸውን ባይጠቅሱም አቶ ኦባንግ “ኦሞትን በተመለከተ ከበቂ በላይ መረጃ አለን፤ ህግ ፊት እናቀርበዋለን፤ በንጹን ደም ተጨማልቆና ህዝብ ላይ ግፍ ፈጽሞ መሰወር አይቻልም” በማለት በስልክ ለጎልጉል ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ ኢሬሳበድንገት ምሳ እየተመገቡ ከመርዝ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው በድንገት ማለፉ ይታወሳል።

ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ ም ጀምሮ ሟቹ አቶ መለስ በላኳቸው አስገምጋሚዎች ለሳምንት በተካሄደ አውጫጪኝ አቶ ኦሞት “የአኙዋክ ተወላጆችን አስጨፍጭፈሃል” የሚል መነሻውና ዓላማው ግልጽ ያልሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። በወቅቱ ግምገማው ላይ የነበሩ እንዳሉት አቶ ኦሞት “እኔ በዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ከሆንኩ መሳሪያና ወታደር የሰጠኝ መለስም ይታሰራል” በማለት መልስ ሰጥተው ነበር።

በወቅቱ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት ድርጅት /አኢጋን/ አቶ መለስን በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ችሎት ተጠያቂ ለማድረግ ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ያገኘበትና አቶ መለስ ላይ ክስ እንዲመሰረት ውሳኔ የተደረሰበት ዜና የተሰማበት ነበር። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የጋምቤላ ምንጮች “አቶ መለስ አቶ ኦሞትን በጭፍጨፋው ተጠያቂ በማድረግና ርምጃ በመውሰድ ራሳቸውን ጲላጦስ ለማድረግ የወጠኑት አካሄድ እንደሆነ የፌዴራል ሰዎች ነግረውናል። ኦሞትም በሙስና በዘረጋው መዋቅር እስከላይ ድረስ ዘመድና ተቆርቋሪ ስላበጀ መረጃው ደርሶት ነበር” ብለዋል። /በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የተመሰረተው ክስ መለስ ቢሞቱም እስካሁን ክፍት ነው/

በሌላም በኩል ወቅቱ በክልሉ ኢህአዴግ ለልማት በሚሰጠው ርዳታ ዜጎችን ለማፈንና ረግጦ ለመግዛት የሚያስችለውን ሃይል ያደራጅበታል በሚል ተቆርቋሪዎች መረጃ አስደግፈው ባቀረቡት ክስ ዓለም ባንክ አጣሪ የላከበት ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ መሬታቸውን፣ የትውልድ ቀያቸውን በአንጋቾች የተነጠቁ ምስኪን ዜጎች ድምጽ ዓለም አቀፍ ትኩረት አግኝቶ ኢህአዴግን ክፉኛ የተፈታተነበት ነበር። ለዚህ ይመስላል ኢህአዴግ በግምገማ በርካታ የክልሉን ሃላፊዎች ወረዳ ድረስ በመዝለቅ በሙስና ሰበብ ሲያባርርና ሲያስር፣ አቶ ኦሞትን ወደ ፌዴራል በማዛወር በቅርብ ይከታተላቸው ነበር። አቶ ኦሞት ወደ ፌዴራል ሲዛወሩ “የቤንሻንጉል ጉምዝ ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹ ላይ የተደረገው ይፈጸምባቸዋል” ተብሎ አስቀድሞ ተተንብዮ ነበር።

ለአብነት ከላይ በተዘረዘሩት መነሻዎችና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ሳቢያ የአቶ ኦሞትና የህወሃት ግንኙነት ማክተሙን የሚናገሩት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች፣ “ቀደም ሲል ህወሃትን ሲያገለግሉ ኖረው መጨረሻቸው እስር እንደሆነው አራት የቀድሞ የክልሉ መሪዎች፣ ወይም እንደ አምስተኛው ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ስደት እጣ ፈንታቸው ይሆናል” የሚል ቅድመ ትንበያ ነበር።

አቶ ኦኬሎ አኳይ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ክልሉን ወክለው የተዛባ መረጃ እንዲሰጡ ታዘው ነበር። በአቶ አባይ ጸሃዬና ገብረአብ በርናባስ መመሪያ መሰረት ግጭቱ በጎሳ ላይ የተመረኮዘ የርስ በርስ እንደሆነ፣ በግጭቱ 59 ሰዎች ብቻ ሲሞቱ አንድ ቤት መቃጠሉን እንዲናገሩ የተሰጣቸውን መመሪያ ያልተቀበሉት አቶ ኦኬሎ ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ አገር ጥለው መሰደዳቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ በተደጋጋሚ ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ አቶ ኦኬሎ አኳይ በስደት ሆነው በይፋ በዚህ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት አለመድፈራቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ ጉዳይ ሆኗል።

ኦሞት የት ናቸው?

አቶ ኦሞት የክልሉ የደህንነት ሃላፊና ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ፍጹም ታማኝ ስለነበሩ በ2005 የተሰጣቸው የክልል መሪነት ስልጣን ለህወሃት ለሰሩት ውለታ የተከፈለ ወሮታ እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚወሰደው። በዚሁ መነሻ ይመስላል አብዛኛው የጋምቤላ ተወላጆች ለአቶ ኦሞት የከፋ ጥላቻ እንደነበራቸው የሚናገሩ ክልሉ ተወላጆች፣ ኦሞት ከአገር ኮበለሉ መባሉ አያስገርማቸውም።

አሁን ጥያቄው ኦሞት ከኢህአዴግ አፍንጫ ስር እንዴት አመለጡ? አሁን የት ናቸው? መጪው እጣ ፈንታቸውስ? የሚለው ነው። አዲስ አድማስ ባለፈው ቅዳሜ እትሙ አቶ ኦሞትን የግምባር ዜና አድርጎ ሲያቀርብ አገር ጥለው መኮብለላቸውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ማረጋገጣቸውን አስነብቧል። አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ኦሞት ከሁለት ወር በፊት ለስልጠና አውሮፓ ሲመጡ በነበራቸው ቪዛ ከሁለት ሳምንት በፊት ዓርብ ቀን አገር ጥለው እንደወጡ መረጃው አላቸው።

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከ19 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እየሰሩ መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ “ኦሞት መለስ በህይወት እያለ ቢኮበልል መልካም ነበር። አሁን ከኦሞት የምንፈልገው ችሎት ፊት በወገኖቹ ላይና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ፣ ቶርቸር፣ እስር፣ ዝርፊያ፣ የመሬት ንጥቂያ፣ ወዘተ አስመልክቶ እንዲናዘዝ ነው” ብለዋል። ኮብላዩ አቶ ኦሞት የት እንደሚገኙ ተጠይቀው “አሁን እዚህ ነው የሚባልበት ደረጃ ላይ አይደለንም። ግን መሰወር የሚችል አይመስለኝም። በደም ተጨማልቆ በስደት ተበዳይ መስሎ መኖር አይቻልም። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ከመለስ ጋር በተመሰረተው ክስ ላይ ኦሞት የተካተተ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። እኛ እንኳ ዝም ብንል ፍትህ በርዋን አትዘጋም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ አቶ ኦሞት አገር ጥለው የወጡት ከሁለት ሳምንት በፊት ሲሆን አንድ ሳምንት ቢዘገዩ ኖሮ እስር ቤት ይገቡ ነበር። አስቀድሞ በደረሳቸው መረጃ መሰረት አቶ ኦሞትን እስር ቤት እንዲወረወሩ የሚያዘው የአስር ማዘዣ የሚቆረጥበት ግምገማ ተዘጋጅቶ ነበር። እሳቸው አስቀድመው አገር ጥለው በመውጣታቸው ግምገማው ተስተጓጉሏል። ግምገማው የዓለም ባንክ አጣሪ ቡድን በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ሲገባ በሙስናና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ኢህአዴግ ርምጃ በመውሰድ ዝግጅት አጠናቆ ለመጠበቅ የሚረዳው ነበር። ግን አልሆነም።

በጋምቤላ በኢቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ከሚሰሩት መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችና የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው አቶ ኦሞት የሚደረግባቸውን ክትትል አልፈው አገር ሊወጡ እንደቻሉ ግምት አለ። አሁን “ባለሃብት” የሚባሉት እነዚህ ክፍሎች ባላቸው መዋቅር ሳቢያ አቶ ኦሞትን ሊታደጓቸው እንደሚችሉ ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ።

አቶ ኦሞት ሆላንድ ገብተዋል የሚሉም አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አውሮፓ ሊገቡ አይችሉም በማለት ግምቱን የሚያጣጥሉ አሉ። እነዚህ ክፍሎች ወደ ማሌዢያ ሄደዋል የሚለውን ምንጭ ይደግፋሉ። በስፋት እንደሚነገረው ከሆነ አቶ ኦሞት ኤዢያ እንደሚሄዱ የሚያጠናክሩ ምልክቶች አሉ። አብዛኛው የኢህአዴግ ባለስልጣኖች በማሌዢያ ባንኮች ገንዘብ አላቸው። አቶ ኦሞትም በተመሳሳይ የማሌዢያ ባንክ ተጠቃሚ ናቸው ተብሎ እንደሚገመት የሚቀርቧቸው ይናገራሉ። በተመሳሳይ በኢንቨስትመንት ስም የተወዳጇቸው ባለሃብቶች በኤዢያ ከለላ ሊሆኗቸው ስለሚችሉ የመጀመሪያ ምርጫቸው ኤዢያ እንደሚሆን ይስማማሉ።

ለጎልጉል ማንነታቸውን ሳይገልጹ መረጃ የሰጡ የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት “ኦሞት ርቆ አልሄደም ይያዝል” በማለት ግምታቸውን ሰጥተዋል። ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉ የገለጹት እኚህ ሰው “ኦሞት ብዙ ጉዳዮችን እንዳያበለሽ ጥንቃቄ ሲደረግ ነበር። እንዴት ለጊዜውም ቢሆን ተሰወረ?” የሚለው መነጋገሪያ መሆኑን ግን አልሸሸጉም። ኦሞት በወቅቱ የፈጸሙትን ከ400 በላይ የአኙዋኮችን ጭፍጨፋ፣ የተሳተፉበትን ሙስና፣ የመሬት ነጠቃ፣ ግድያ፣ ወዘተ የወንጀል ምስጢር በማውጣት ኢህአዴግን አሳጥተው ፍርድ እንዲቀልላቸው መደራደሪያ ከማድረጋቸው በፊት ኢህአዴግ የራሱ አደን አጠናክሮ እንደሚገኝ ተጨማሪ ዘገባዎች አሉ፡፡

አቶ ኦባንግ ሜቶ የኦሞት መሰወር አያስጨንቅም ባይ ናቸው። ኦሞትን ፍትህ አሳድዳ ትይዘዋለች የሚሉት አቶ ኦባንግ ትኩረታቸው ወንጀል የተፈጸመባቸው በሙሉ መረጃ በመሰብሰብና ወደ ጋራ ንቅናቄው በመላክ እንዲተባበሩ የመነሳሳታቸው ጉዳይ ላይ ነው። ህወሃቶች ወንጀል አሰርተው፣ መጨረሻ ላይ ፍትህ ወዳድ ለመምሰል በወንጀል ያጨማለቋቸውን ሰዎች ህግ ፊት አቅርበው እንደሚያስፈርዱባቸው ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ሌሎች ከዚህና ከቀድሞው ተሞክሮ ተማሩ። ኦሞትን ፍትህ አደባባይ ለማውጣት የሚሰራው ስራ ወንጀለኞችን ለመፋረድ የምናደርገውን ትግል አንድ ርምጃ ያሳድገዋል። እንደ ኦሞት ያሉት ወንጀለኞች ካሉበት ይለቀማሉ። ይህንን ማድረግ አቅም አለን። በደም ተጨማልቆ በስደት መኖር አይቻልም። ሌሎችም ካሁኑ ንስሃ ግቡ፤ ህብረተሰባችሁን አስቀድሙ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ህወሃትም ሆነ ኢህአዴግ በራቸውን መክፈታቸው ወይም ለውጥ እንዲመጣ እንዲፈቅዱ የሚገደዱበት ዘመን መቃረቡን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ነጻ ውጡና ህዝባችሁን ነጻ አውጡ፣ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለወንጀለኞች ቦታ የላትም፣ ትፋረዳቸዋለች” ሲሉ በድጋሚ ህዝብ በወንጀለኞች ላይ መረጃ በማሰባሰብ የቤት ስራውን በወጉ እንዲሰራ ጠይቀዋል።
==========================================================
የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ
“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”
በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።

በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል።

ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል።
“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።

ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ።

በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር።

አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ

“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ።

አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን። የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ።

ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት ተዛልፈው ነበር።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ ይደፍቃቸዋል። ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ እንደማይቻል አስታውቀዋል። አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።

“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል። ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል።

የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።
goolgul is a source

አዲስ አበባ የዳይመንድ ድራማ (ማጭበርበር) ተጧጡፏል!!!

ኔትዎርክ ያቆማል የተባለው የማሾ ዳይመንድ አራት ሚሊዮን ብር ተሽጧል::የዳይመንዱን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡት የውጪ ኤክስፐርቶች ናቸው::ባለሃብቶች በሚያውቋቸው እና በቅርብ ባልንጀሮቻቸው እየተጭበረበሩ ነው::

Image

በጥር ወር ገበሬው ሰብሉን ሰብስቦ የሚጨርስበትና ሠርግ የመደገስ አቅሙ የሚጎለብትበት ወቅት ነው። በዚሁ ተለምዶ ከተሜውም ለሠርግ ጥርን የሚመርጠው ይላሉ የአገራችን የልምድ አንትሮፖሊጅስቶች።

እንደሠርግ እጅ፣ እጅ የሚለኝ ነገር እየጠፋ ነው። ወይ ባሕላዊ አይሆን፣ ወይ ዘመናዊ እንዲሁ የጨረባ ተስካር ብቻ ሰው ሰብስቦ እዩኝ ማለት – ማለት የኛ አገር ሠርግ ትርጉም ሆኗል። ደግሞ የወገኝነቱ አበዛዝ!

ባለፈው ሒልተን ሆቴል ፊት ለፊት አፍሪካ ፓርክ አጠገብ ሙሽሮች የፎቶ ስርዓት እያደረጉ ነበር። ይህ እንግዲህ ከሠርጉ ዕለት ውጪ ለማስታወሻ የሚነሱት ፎቶ ላይ መሆኑ ነው፤ አጃቢ የለም።  አስፋልቱ ላይ ሙሽሪት ተዘርፍጣ፣ ሙሽራም እሷን እየተንከባከበ የሚያስመስለውን ድርጊት እያደረገ ፎቶ ሲነሱ አይቼ ሳበቃ በማየቴ እኔ አፈርኩ። ሚስቴ እንዲህ ዓይነት ነገር እናድርግ ከምትለኝ ጋብቻው ይሰረዝ ብትለኝ ውለታ እንደዋለልኝ እቆጥረዋለሁ።

የከተሜ ሠርጎች ከሠርጉ በፊት የስቱዲዮ ፎቶ መነሳትን ባሕል አድርገውታል። ስቱዲዮ ውስጥ፣ የተለመዱ የፎቶ አነሳስ ወጎች አሉ። ጥንዶቹ በፍቅራቸው ዘመን አድርገዋቸው የማያውቋቸውን (ለምሳሌ ሙሽራይቱ የሙሽራውን ከረባት እየጎተተች) ለማስታወሻ ፎቶ ይነሳሉ። እኔ የምለው፤ እነዚህ ጥንዶች ወደፊት ማስታወስ የሚፈልጉት ሆነው የማያውቁትን ነገር ነው እንዴ? ስቱዲዮዎቹ በውሸት ጥርብ ግድግዳዎች፣ እንስሳት፣ የሙዚቃ መሣሪያዎችና ጌጣጌጦች ያሸበረቁ ዓይነት ሲሆኑ ጥንዶቹ በኪራይ ልብስ “የውቡ ቤት” ፈርጥ ሆነው ይነሳሉ። ይህንኑ ፎቶም ለልጆቻቸው ማስታወሻ ብለው ሊያሳዩ ያቆያሉ።

ሠርጎች ባብዛኛው ወግ የሚበዛባቸውና ለታይታ የሚደረጉ ሆነዋል። አማራጭ አጥተው ከተጋቡ አስመሳይ ተፋቃሪዎች ጀምሮ ዕድሜ ልካቸውን ከፍለው የማይጨርሱትን ብድር ተበድረው ድል ያለ ድግስ የሚደግሱ ሠርገኞች ድረስ ቲያትሩ ብዙ ነው። አንዳንዶች ሠርግ የሚደግሱት “እወቁልኝ” ለማለት ሳይሆን “እዩልኝ” ለማለት ይመስለኛል። “አታገባም ብላችሁ ያማችሁኝ እነከሊት እርር በሉ አገባሁ…፣ ባለፈው በመርሴዲስ አገባሁ ብለሽ የተቆላሽብኝ እከሊት፥ ያው እኛም በሊሞ ተጋባን…” እየተባባሉ ይመስለኛል።

በዚህ ወር ካየኋቸው ሠርገኞች መካከል ቦሌ መንገድ ላይ ባመሻሹ ብርድ እየተፈጁ በክፍት ጂፕ መኪና ቆመው ሲሄዱ ያየኋቸው ጥንዶች በጣም ካሳዘኑኝ ውስጥ ይመደባሉ።
ካሜራ በሌለበት፣ ማንም ሥራዬ ብሎ በማያስተውላቸው ሁኔታ ምን ልሁን ብለው ነው በብርድ የሚገረፉት? የታይታ ፍቅር ተመልካች በሌለበትም ያደክማል።

ትዳር ቀላል ኃላፊነት የሚጠይቅ እርምጃ አይደለም፤ ትዳር ሠርግ ብቻ የሚመስላቸው ግን እልፍ ናቸው። መሠረታዊ የቤት ዕቃ ያላሟሉ ሰዎች ለሠርግ ድግስ ሊሞዚን በ30 ሺሕ ብር ይከራያሉ። 500 ሰው ጠርተው ውስኪ ይራጫሉ። ለዚህ መደገፊያ “ሠርግና ሞት አንድ ነው”፣ “ዓለምሽ ዛሬ ነው…” እያሉ ይዘፍናሉ። ኑሯቸው ግን የሚጀምረው ከሠርጉ ዕለት ቀጥሎ ነው። ጥንዶች የተጋቡ ዕለት የሕይወታቸውን አቅጣጫ ለመቀልበስ ወደሚያስቸግር አቅጣጫ እንደሚቀይሩ ሠርጉ እስኪያልፍ አይገባቸውም።

አንዱ ላገባ፥ ሌላው ገደል ገባ!

ከሠርግ ሰቀቀኖች ሁሉ የሚከፋው የወዳጅ ጓደኞች ፈተና ነው። በተለይ ሚዜ ተደርገው የሚመረጡ ሰዎች በዚህ የኑሮ ውድነት ኪሳቸው ይነቀላል። ሚዜዎች የራሳቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ ስለሚገደዱ ለወዳጅነታቸው ሲሉ ተበድረውም ተለቅተውም ቢሆን አላስፈላጊ ወጪ ውስጥ ይዘፈቃሉ። የወጪው አበዛዝ ደግሞ ወሰን የለውም። የየራሳቸው ሁለት ወይም ሦስት አልባስ እና ከሠርጉ ጋር የተያያዙ ሌ ሎች ወጪዎች ይኖራሉ። ለሚዜነት የተተዉ ጓደኞች ሳይቀሩ የመለመላሉ። እኔ በግሌ፣ ጓደኞቼን ሲያገቡ እንዳያስቸግሩኝ ከምጠይቃቸው ጉዳዮች አንዱ ለሚዜነት እንዳያጩኝ ነው።

የሕዝብ መብት ነፋጊ ሙሽሮች

ዛሬ፣ ዛሬ በየአደባባዩ ቅድሚያ እየወሰዱ አደባባይ ሦስቴ የሚሽከረከሩ ሙሽሮች የከተማ ትራፊክ ሲያጨናንቁ ማንም አሌ አይላቸውም፣ እነሱም አይጨንቃቸውም። ከሁሉም ከሁሉም የሚያበሽቀው ግን ከተማውን ሁሉ በጡሩምባቸው መረበሻቸው ነው። የነሱ ሠርግ የከተሜው ሁሉ ጉዳይ ይመስል መንገደኛውን ሁሉ በጩኸት በመረበሽ ይዝናናሉ። በተለይ በዚህ ወር ቅዳሜና እሁድ አደባባይ አካባቢ ጥቂት ሰዓት መቆየት ያማርራል።

በአገራችን፣ በተለይም በከተሞች የተፋቺዎች ቁጥር ከተጋቢዎች ቁጥር ጥቂት ነው የሚያንሰው። ጥንዶች ሠርጋቸው እንዲያምር የሚከፍሉትን ያክል መስዋዕትነት ያክል ትዳራቸው እንዲሰምር ቢተጉ ኖሮ የፍቺ ቁጥር በእጅጉ ይቀንስ ነበር። መደምደሚያዬ ነው።

ለዘመናት ቀጣይነት ያለው የተሟላ ሰላምና መረጋጋትን ኣጣጥማ የማታውቀው ኣፍሪካ፤ ኣንዳንድ የኣህጉሪቱ ፖለቲከኞች እንደሚሉት አመጹም ሆነ ጦርነቱ በቅኝ ኣገዛዝ ዘመን ለነጻነት ነው የነበረው። ከዚያ ወዲህም ቢሆን ቅኝ ገዢዎችን ከተኩት አምባገነኖች ጋር እስከሆነ ድረስ ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ በመሆኑ የሚጠበቅ እንጂ ኣስገራሚ ሊሆን ኣይገባም።

ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።” ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። “ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ […]

የሀገራችንን የፖለቲካ አካሄድ ለአርባ ዓመታት ተከታትያለሁ። ሀገሪቱን የሚመሩት ሆኑ ተቃዋሚዎች በውል የሕዝቡን ችግር የተረዱት አይመስሉም። የሕዝብን ይውንታ ያላገኙ በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ላይ የወጡትም ቢሆኑ፣ እሽ አትበሉን የንጉሥ ዶ ሮ ነን ባዮች ናቸው። ሕዝቡም የቅኝ ገዥዎችን እየተከላከለ ነፃነቱን አስከብሮ የኖረ ነወ። በዚህም ይኩራራል፣ ግን የራሱን ነፃነት እርሱን ከሆነ ሰው ይጠብቃል። በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ላይ የወጡትም በመሣሪያ […]

በዕርግጥ የአንድን የሀገራችን ክፍል ነዋሪዎች ጉዳይ አንስቶ በአንድ መንገድ ወይንም በሌላ መንገድ መነጋገር፤ ወደድንም ጠላንም፤ ያለንበት ዘመን ግዴታ ሆኗል። ትናንት አኝዋኮች ተረሸኑ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን ተከበው ተሰቃዩ፣ ኦሮሞዎች በእስር ቤት ታጎሩ እያልን እንደጮህን ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ በአማራዎች ላይ የሚደርሰውን በደል አንስተን መነጋገር ግዴታችን ሆኗል። የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲህ ሆኑ፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲያ ሆኑ ስንል ብዙ […]